Telegram Web Link
#ፍቅር በዚያ ወራት

(ክፍል 6)

........ሚካኤል.አ 

ሰኞ ከባድ ነው ። ከቀን ሰኞ ከወር ግንቦት ይከብደኛል። 

በዛ ላይ ሰኞነቱ ብቻ ሳይሆን ትምህርትቤት ስሄድ የሚገጥመኝ ጦርነት አለ ።

ጠላቶቼ ሁለት ናቸው!

ዶክተር እዘዝና ነጃት ...

የትምህርት ቤቱ በራፍ ጋር ስደርስ እግሬን ብርክ ብርክ አለኝ።

"ንፁህ ድፈሪ! "

እንዲህ ነኝ። 

ዮሀንስ አፈወርቅ ከጦርነት ሁሉ ትልቁ ጦርነት ራስን ማሸነፍ ነው ይላል ።

ሰማዕት በወፍጮ ይፈጫል...ስጋው እንደ ዱቄት ይበተናል...ገላው ይሰቀላል።

የዛን ዘመን ፅድቅ መመዘኛ ይሄ ነበር። አሁን ዘመን ተራቆ ከአካል ውጊያ ይልቅ ሰይጣን ጦርነቱን ቀይሮ ራስን በራስ ላይ አስነስቷል።

መቆሸሽን አውቆ ራስን ለንሰሀ የማዘጋጀት ጥፋቱ የቱ ጋር ነው?

ሁላችንም ከጥፋት ጋር ተወልደናል...ሀጥያትን በህይወት ልምዳችን ቀስመናል ... 

ሀጥያት እንደ ውሀ ነው ። እያሳሳቀ ሲውስድ እየሄድኩ ነው ወይ? ብለን ሳንጠይቅ ሄደናል።

መጠጥ...ዝሙት.. .ክፋት ሲወስድም ልክ እንደዚህ ነው። የትኛውም ሱሰኛ ነገ ሱሱን እንደሚያቆም ስለሚያምን ሱሱኛ ነኝ ብሎ አምኖ አይናገርም። 

ግን አንድ ከሰዓትን ጫት አልያም ሲጃራ መዝለል አይችልም።

የእኔን ውልደት የምፈልገው በዚህ መንገድ አይደለም።

ዶክተር ዛኪን ሳገኘው ከሌላ ወንዶች ጋር ተኝቻለው የሚል የመቅለል ስሜት እንዳይሰማኝ መበርታት አለብኝ። እኔ የምሸነፈው ከሱ በፊት የነበረኝን የወንድ ታሪክ በማሰብ አይሆንም። ከዛኪ በኋላ የምትኖረው ንፁህ ሌላ ታሪክ ነች። ቀሚሷ ለየትኛውም ወንድ አይገለብም...ይህች ንፁህ ድንግል ናት። 

ከዛክ ውጭ ማንም የማህደሯን ቁልፍ ከፍቶ አይጎበኛትም። ከዛኪ በኅላ አሸናፊ ነኝ።

ይሄን እያሰብኩ ወደ ክፍል ኮሪደሮች ተጠጋሁ ።

ዶክተር እዘዝን ሳየው ከመቼው እንደዛልኩ አላውቅም !

ሀፍረቴ ጀመረኝ። ያ ሁሉ ጀብዴ እምን ጉድጔድ ገባ ደግሞ ?

ይህ ሰው አውቆኛል...አሁን እሱ ላይ ልኩራ ብል እንኳ ቀምሻታለሁ ብሎ ይመፃደቃል ።

ይሄ ነው የእኔ ብስጭት!

ብዙ ሴቶች ለደረሰብን ወንድ ደካሞች ነን።

ስንቱ አይደል እንዴ ወልዶ ከብዶ አብቅቶ ከድሮው ፍቅረኛው ጋር በስህተት የወደቀው?

ወንዶችም ይሄን ስነ ልቦና ስለሚያውቁት ማገዶ እንደማንፈጅ አስበው ይደፍሩናል።

ቀድሞ ገላችን ላይ የተኛ ወንድ ቀለበት ም ልጅም እያየ የማሸነፍ ሞራል አለው።

እዘዝም በራስ መተማመኑ የመነጨው ከዚህ ይመስለኛል።

"ከክላስ በኋላ ደውይ ። ራት ከኔ ጋር ነሽ!" አለኝ።

ምንም አልመለስኩም። እንቢ የማለት ድፍረቱን አያሳጣኝ ያለው ስህተቴ ና ይሄ ግሬድ የሚሉት የአጋንንት መምህራን ሰንሰለት ነው።

እሱን እንቢ ብለው የትምህርት ህይወቴ እንደ ሸማኔ ቤት ይዝረከረካል ።

ዛክን የማጥመድ ሩጫዬ ቀለበት ውስጥ ይወድቃል ።

እንጃ ብቻ ዝም አልኩት ።  ዝም ማለቴ ለሱ እሺታ ነው። ለምን አልልም? 

ስህተቴ ለሱ የጨመረለትን በራስ መተማመን የኔ ፀፀት ሊቋቋመው አይችልም። በዛ ላይ ብስጭቱም አለብኝ።

ክፍል ገባሁ...

ስጋዬ ወንበር ላይ ተቀመጠ ። መንፈሴ ከጎኔ የለም። ሁሉም ተማሪ "ተሻለሽ ?" ይለኛል።

"አዎን ይመስገን " እላለሁ በባዶ እስትንፋሴ።

ነጃትን አየኋት ደግሞ ...

ከሩቅ እጇን አውለበለበችኝ። የሽንፈቴ ሰንደቅ አላማ የተውለበለበ ነው የመሰለኝ።

አፍታ ቆይቶ መልዓኬ መጣ ።

ክፍሉ ውስጥ ሲገባ ደስ የሚል መዓዛው ያውደናል ። ቀሳውስቱ በቅዳሴያቸው እጣኑን ሁሉ እሱ ላይ ይሆን የሚያጨሱትን?

ፊቱ ላይ ሰላም ያረባል...የሆነ ቅዱስ መንፈስ የሚከተለው ይመስለኛል።

"Welcome ንፁህ " አለኝ የሱን ትቢያ ሴት ።

አንገቴን በአክብሮት ወዘወዝኩለት። ነፍስያዬም እኮ እንዲህ ነው የምትዘልለት።

ከተዘፈዘፈችበት በክሪክ የማትነሳው ነጃት ዳስተሩን ተቀብላ ሰሌዳውን ስታጠፋለት ቀናሁ።

አያት ...

ደግሞ የሚያያት በስስት ነው ። በ አንድ ሰዓት ክፍለ ጊዜ ስድሳ ጊዜ እየሰረቀ ያያታል።

አበድኩ !

ባዶ ነፍሴ ቃተተች። 

እሱ አስተምሮ ... ሌሎች መምህራንም አስተምረው (ያስተምራሉ መሰለኝ)...ክፍለ ጊዜው ተገባደደ።

ነጃት ቀረበችኝ።... ላናግራት ስላልፈለግሁ ፊቴን አጨማድጄ ዝም አልኳት ። ደንግጣለች!

እንኳን መደንገጥ ለምን እንጦረጦስ አትወርድም?

የመጣችብኝ በሰላሜ ጣዖት ዛክ ነው። 

ሰው መጥላት የማልችለው ንፁህ ሰው ጠላሁ ። አምርሬ ጠላኌት ።

ስወጣ ፍጥነቴ ለራሴ ይታወቀኛል ። ከሩጫዬ የገታኝ የዛ ሰላቢ ስልክ ነው ። 

የሞባይል ስልኬ ላይ የደወለው እዘዝ ነው ።

ዝም ልበለው ይሆን?

እሺ ነገስ ?

እሺ ከነገ በስቲያስ?

ትምህርቴን ላቁምን ? ዛኪን አልየውን ?

የእዘዝን ስልክ ሳያነሱ ፊት መንሳት እኔን ከፉክክሩ ገበያ የሚያወጣኝ መሰለኝ።

ስልኩን ካነሳሁት ደግሞ ሌላ ተጨማሪ ፀፀት ላስተናግድ ነው።

እንጃ ብቻ በደመነፍሴ ስልኩን አነሳሁለት.. .


ይቀጥላል.. .

@wegoch
@wegoch
@paappii
ከበደሉ በጣም እንደው በጣም ያመመኝ እንደሚያዝንልኝ መዘብዘቡ ነው ፤ ያደረገውን
እያወቁ በዳይ ፣ አዛኝ መስሎ ሲጎዘጎዝ ሳይሰቀጥጠው መስማት የሚቻለው ምን አይነት
ጆሮ ነው !? አለማችን ያጎደፉት እየበደሉን ደግመው መጥተው ለበደላቸው ከአራምባ እና ቆቦ ምክንያት እየደረቱ የሚደረድሩ ፤ ተጠቅመው ሳለ እንደተጎዱ ሙሾ የሚያወርዱ ተርመስማሽ ነፍሶች ናቸው ። ደሞ የበደሉት ስለሚያብለሰለስሏት በደላቸውን ማፍዘዣ አሳማኝ የምትመስል ነገር አያጡም። ግሩምም የሚጠቅመውን ፣ የሚያምንበትን ደስታውን ለማግኘት የቻለውን ነገር ሁሉ አድርጎ የክህደቱ ህመም ትኩሳት እየፈጀኝ ሳለ መጣ ሊገስፀኝ ፣ መጣ የካደኝን አሳማኝ ያለውን ምክንያት ሊተነትን። አላማው አንድ ነው የጥፋተኝነት ስሜት ሲያቃጭልበት ማስታገሻው ሊያደርገኝ ነው ። ይሄ እውነት የሚጠፋኝ መስሎታል ፤ የቂል ሰው ድክመት በተወሰነ ነገር ሲበልጠን በሁሉም ነገር የሚበልጠን ይመስለዋል ። በእርግጥ እኔ አፍቃሪ ስለሆንኩ እሱ ላይ ያለኝ ተስፋ ጨርሶኑ ስላልሟሸሸ አዲስ ነገር ከነገረኝ ብዬ ሲቀጥረኝ ቀድሜ ነበር የደረስኩት የቱ አፍቃሪ ነው ያፈቀረውን ሰው አንደበት ችላ ማለት የሚቻለው ?!
አፍቃሪ መቼም የዋህ ፍጥረት ነው ፤ ተስፋው እንደበልግ ዝናብ ጥፍት ብርት የሚል! ሲቀጥረኝ አዲስ ነገር ጠብቄ ፣ አምሬ ለመገኘት መስታወት ላይ ተገትሬ ፤ ሊለኝ የሚችሉትን ነገሮች አውጠንጥኜ ፤ ፀልዬ ከቀጠሯችን እጅግ ፈጥኜ ተገኘሁ ግሩም ያው ነው አለባበሱ ፣ አወራሩ ፣ ብልጣብልጥነቱ ያው ነው። በራሱ መንገድ ለመሄድ ፍቅሬን ተረማምዶት በአዘንኩልሽ ሰበብ የልቡን ፀፀት እየዘበዘበ ይመክረኛል ።
ዝምታ እኮ ወርቅ ነው ፤ ስለምን ዝም አይልም?
ወይ ጭራሹኑ ቢጠፋስ ! በመንገዴ ዳና እየተከተለ ባያደማኝ ፤ መድማቴ ስላልገባው ይሆን ወይስ የራሱን ስሜት ለማጥገብ ይሆን ? ብቻ ሌላ ፀፀት እንዲሰማኝ ዶልቶ ነው የመጣው ። ከጀርባዬ ተሸሽጎ ያደረገውን ሆነ በግልፅ ያደረገውን በደል እኮ አውቃለሁ ምን አለ ይቅርታ
በድያለሁ ብሎ ቢሰናበተኝ ንስሃ ለመግባት ሄዶ ለንስሃ አባቱ ንፁህ ነኝ እያሉ ለማሳመን መዳከር ምን ይረባል? አንዳንድ ሰው ብልጥቱን የትም አስከትሎት ይገባል ፤ ለመንፃትም ሄዶ ቀድሞ ከሰራው በደል የበለጠ ሃጥያት ይከምራል
ግሩምን ሰማሁት ፤ አንድም ለእኔ የሚጠቅም ነገር አልያዘም ፤ ከፀፀት ለማምለጥ ነው
የመጣው ፤ ሊኮንነኝ ነው የመጣው ፤ በእኔ ምክንያት ስላጣው ነገር ሊነግረኝ ቃላት ሰናንዶ
ነው የመጣው። ለተካደች ፣ ለተበደለች እንዲህም ሆና ለምታፈቅረው አንዲት ሴት የሚለው ዝባዝንኬ መስማት ምን ይጠቅማታል ?
ምንም !! ስለምን ገና ለገና ታፈቅረኛለች ብሎ
ገና ለገና አንደበተ-ርትዑ ስለሆነ ገና ለገና ድሮ ስላሳመነኝ ገና ለገና ህሊናው ስለቆረቆረው እና ስለሚቆረቁረው ለምን እኔን በማይጠቅመኝ ላይ እና ባልዋልኩበት እንደ ኦሪት ፍየል ይሰዋኛል ።
ይሄን ሁላ የቃል ጋጋታ ሳይራራልኝ ማንጋጋት ነበረበት?? ሰነፍ ሰው ልብ ውስጥ ለመቅረት በሚያደርገው ጥረት ነው ከልባችን አንቅረን
የምናወጣው። በጥሞና ጣልቃ ሳልገባ ከሰማሁት በኋላ ራስ ወዳድነቱ በቀናት ብዛት እንደማይለወጥ ፤ ከነፍሱ ጋ የተጣበቀ ማንነቱ እንደሆነ ተገለፀልኝ ። እንደዛ ለምኜው ፣ ተስዬ ፣ ፀልዬ አምላክ አንተን እንቢ ያለኝ በአንድ ምክንያት
ነው.

ቢራራልኝ ነው!!!


@wegoch
@wegoch
@paappii

#Adhanom Mitiku
ሥዕል በማሳል ለ ወዳጅ ዘመዶ ስጦታ ያበርክቱ
በ+251984740577
ወይም @gebriel_19 ላይ ፎቶ በመላክ በ ተመጣጣኝ ዋጋ ማዘዝ ይችላሉ!
#ሥዕል_ብቻ የቴሌግራም ገፅ


@seiloch
@seiloch
Forwarded from ❀ርብቂ Ribki Photography (Ribka Sisay)
ከፊትሽ ለፍርድ ቆመናል!
ያጠፋም እንዲማር የማረም እንዲካስ ፍቃድሽ ይሁን!!
.......
ከአጭር ታሪክ የተወሰደ...
©Ribka Sisay
Feb, 06, 2022
@ribkiphoto
ሌላ ቀንም የአማን ጥያቄ ይከተለዋል ።

“አይ በዚህ ሰሞንማ የሆነ ነገር ተፈጥሯል ! ሎተሪ ወይ ዲቪማ ወቶልሀል 

መሰለኝ ”

ማርኮን በውስጡ የሚጮኸው መልሱ እንዲህ ይላል ። ሎተሪ ምንድነው ? በዛ 

ቢባል ገንዘብ ... የተሻለ ቤት መኖር የተሻለ መኪና መያዝ ። ይሄ ማለት ግን 

የተሻለ ሰውን የማየት ያህል አያስደስትም ። ዲቪስ ምንድነው? ሀገርን ጥሎ 

መኮብለል ፣ ድህነትን ደህና ሰንብት ለማለት የሚጓዙት ዘመናዊ ባርነት ! ይሄስ 

በበረሀ መሀል የፈለቀችን ምንጭ ከማየት በላይ እንዴት ደስ ሊል ይችላል ?

በረሀው እነ ሳባ ናቸው ። ሁሉ ነገራቸው ግለት ነው ፣ ሁሉ ነገራቸው ወከባ 

ነው ። ይስቃሉ ፣ ሲስቁ ይጮሀሉ …….. ካ ካ ካ ብለው ሲገለፍጡ ሲያይ እንደ ካካ ይጠየፋቸዋል ። ሲያወሩ ለአፋቸው ልጓም የላቸውም ። ለፋሲካ እርድተገዝቶ ገበያ መሀል ውስጥ እንደደነበረ በግ መቆሚያ የላቸውም ። ያንን ያነሳሉ ፣ ይሄን ይጥላሉ ፣ ሰው ያንጓጥጣሉ ፣ ከእነሱ የበለጠች ሴት ስትመጣ ስሟን ያብጠለጥላሉ ።

ሁሉ ነገራቸው ትኩረት መሳብ ነው ። እዚህች ምግብ ቤት ውስጥ የምትመገቡ 

ክቡራን ተማሪዎች ሁሉ እኛን ብቻ እዩን የሚል ስግብግብ የታዋቂነት ስሜታቸው 

በግልፅ አፍ አውጥቶ ይጮሀል ።

እኛ ስልጡን ነን ፣ የተሻለ እንለብሳለን ፣ የተሻለ ሽቶ እንቀባለን ፣ የተሻለ ሜካፕ 

እንለቀለቃለን ፣ ከሁሉ እንበልጣለን ፣ ከሁሉ እንለያለን ፣ ፊታችሁን አመድ 

በወረሳችሁ ተማሪዎች መሀል ለተዓምር የወረድን ንግስቶች ነን ፣ የውበት 

ሹሞች ነን እወቁልን የሚል ጩኸት !

እሱ በጩኸታቸው መሀል በተዓምር የወረደ ፅሞና ይታየዋል ፤ ፀጉሯን ተኩስ 

ሳይነካት ተፈጥሮ ያለሰለሰላት ሴት ትታየዋለች ፣ የእግር ጣቶቿ ቀለምም 

ይሁን የሚለጠፍ ጥፍርን አይሹም ፤ ብቻቸውን ውበት ናቸው ። ተረከዟ እንደ 

በረሀ እንቧይ ይቀላል ። ቆዳዋ እንኳን ተነክቶ ታይቶ ራሱ ትንቡክ ብሎ እንደ 

ቲማቲም የሚፈርስ ይመስላል ።

ዝምታዋን ተሻግረው በስልት ከምትገልጣቸው ከናፍሮቿ መሀል ላይ እንደ ነጭ እርግብ ክንፍ የነጡ ጥርሶች አሉ ። አቀማመጣቸው እንደ ሰሜን ኮሪያ ወታደር 

በእኩልነት ነው ። ስድር ናቸው ። ፈገር ስትል ከጥርሶቿ ፍካት በላይ የተወቀረ 

ድዷ የውበት ፍላፃ ይወረውራል ። እንደ መጥቆር ያለ ድድ በስልት ከተሰደሩ 

ጥርሶች በላይ ሲታይ አጃኢብ ያሰኛል ። ዓይኗ አይቅለበለብም ፣ አይቅበዘበዝም። 

ቅርዝዝ ብሎ ይጮሀል ። ከዓይኗ ቆብ ላይ የሚታዩት የሽፋሽፍት ፀጉሮች 

አርቴፊሻል ከሚተከለው ምናምንቴ በላይ ውበቱ ይጎላል። የእጅ ጣቶቿን በርቀት 

አይቶዋቸዋል ። ትንሿ የግራ እጇ ጣት አናት ላይ ቢንቢ የነከሰቻት ምልክት አለ ። ምናባሽ ነው አለቅጥ እንደዚህ የምትቆነጂው? ብላ ቢንቢዋ ቀድማው ስለነከሰቻት ለመጀመያ ጊዜ ሰውነቱን ትቶ ቢንቢ መሆን ተመኘ። እሷ የነካችውን የእንጀራ ጠርዝ ፣ እሷ የተቀመጠችበት ብርኩማ ፣ እሷ የተራመደችበት መሬትን ባደረገኝ ምናለበት ? አለ። ደግሞስ ምን ያለው የወንበር ነፈዝ ነው ተቀምጣበት ስትነሳ ይዞ የማያስቀራት ? ምን ያለው ገልቱ እንጀራ ነው ገና ስትቆርሰው እኔ ልብላሽ ብሎ የማያሰፈስፈው ?

እሺ ከሷ በላይ ውበት ከየት ይምጣላቸው ? ሌላው ቢቀር እሷን የሚያስተምረው 

ጅማ ዩንቨርስቲ ኪቶ ፉርዲሳ ካምፓስን ለምን ዓለም ተሰብስቦ አይሸልመውም 

? ለምን የምርጦቹ ምርጥ መዝጋቢው ጂንየስ ቡክ የእሷን ስም ከደረቱ ላይ 

አልተነቀሰውም ?

ዓለሙን ምን ነካው ? ሰው ፣ ተማሪው ፣ መምህሩ እና ሀገሬው እሷን አይቶ 

እንደዚህ እንደቀልድ ማለፍን እንዴት ቻለበት ? ወይስ ይህች ሴት ለእኔ ብቻ 

የምትታየኝ መንፈስ ናት ? ራሱን ጠየቀ።

“ እንጃ !” መልሶ ለራሱ ጥያቄ ራሱ መልስ ሰጠበት ።
Forwarded from Sunset Hiking
#Sunsethiking is hosting a day hike to " ENSARO"

💡Hiking Date :- July 10, 2021 (Hamle 03, 2014)

💵 Hiking Cost:- 900 ETB only

🛫Departure: Piasa (Taitu Hotel)
@12:30 LT

🎉🎊Package includes🎋🎊

🚍 Transportation
🌲 Bottled water
🌺 Guide + scout
🍂 photography 📷
💐 Breakfast
🏖 lunch
🧜‍♂️ Swimming
☕️ Coffee

💦Sanitizer & facemask mandatory!
☘️walking hour: 3 hour (up to 5 km of walking)
Hiking Level: Medium !

for more join the
🎸@sunsethiking👣
🏓@sunsetphotography📸
🍿@sunsethikers

🎫 tickets available at
@Paappii ( +251922303747)
አንዳንድ ትዝታ አለ
-ዝምታችን -ከዝምታ ገዝፎ በአርምሞ በተዘጋንበት ጊዜ :በዕዝነ ልቡናችን በኩል <<ኡኡ>> ብሎ የሚጮህ ፡፡ በለሆሳስ ÷በዝግታ ካሳለፍነዉ የእድሜ ዘመን፡ ቅፅበቶቻችንን ከሽርፍራፊ የልጅነት ምስላችን በልጦ ፡በልቦቻችን ጥጋጥግ ካንጠለጠልነዉ ፡ ተናፋቂ ትዝታወች መሀል ፡ ምናለ በደገምነዉ እያልን የምንመኘዉ፡፡
ከትላንት ትዝታወቻችን ጋር ፡ ባንቀላፋን ቁጥር ሳንሰለች ደጋግመን የምንኖረዉ፡፡ አንዳንድ ትዝታ አለ ፡ እንደወይን እያደር ጣዕሙ የሚጨምር ፡ በእምባ በተምሸርንበት ጊዜ እንኳ ÷ በሐዘን ወህኒ ተወርዉረን ፡ መረሳት ክፋ እድል ፊት ለፊታችን ሲጋረጥ፡ የመኖር ጣዕም ሲጎመዝዝ ÷በእቅፋ ሚያስጠልለን፡፡ አንዳንድ ትዝታ አለ በዘመን መጎስቆል ባረመምንበት ጊዜ እንደ አዲስ የሚወልደን ፡ የማያረጅ የእድሜያችን ሞቃት ምዕራፍ ፡፡ አነዳንድ ትዝታ አለ --- አየ ጉድ - ትዝ አለችኝ መሰል፡፡

ያብስራ እዮብ(ደብተራዉ)፡፡

@wegoch
#ዋንጫው
(ሚካኤል.አ)
"ቲቲን ቤቴ ልጋብዛት ነው" አለኝ ላሎ ።
በሀሳቡ ለመስማማት ታከተኝ...
"ዛሬ ብር አንባሩን ልደረምስላት ነው። የሆነ ፍንዳታ ከሰማህ እንዳትሳቀቅ" አለኝ ቀጥሎ ...ላሎ ዘናጭ ነው ። ሱፉን ግጥም አድርጎ ሲንቀሳቀስ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤት የተላከ ባለስልጣን ይመስላል ።
ደግሞ ቲቲን ሲተዋወቃት ደህንነት ነኝ ብሎ ነው። የሆነ ሰማኸኝ በለው ስልክ አለው ።
በዚህ ስማርት ዘመን ያን ስልክ ይዞ ሲንቀሳቀስ ያሳዝነኛል ።
የሆነ ቀን አንድ ግሮሰሪ ስንዝናና አንድ ለፍዳዳ ሰካራም እየደነሰ ላሎን ገፈተረው ።
ላሎ የመጀመርያውን ግፊያ በትዕግስት አለፈ ... ሰካራሙ ሰውዬ ጭራሽ እየተለፋደደ.. ."ወያኔዎችን ያባረርነው እንደዚህ መደነስ አምሮን ነው ... ኢንሶዳቲን " አለን። (አትፍሩ ለማለት የተጠቀማት የኦሮምኛ ቃል ነች። አካም አካም አትበሉ ብለው ጠሚው ፓርላማ ውስጥ የተናገሩትን አልሰማም መሰለኝ :) )
ሰካራሙ ጭራሽ ታስራ እንደተፈታች ጥጃ ፊታችን ቧረቀ...ደግሞ ላሎን ገፋው ... (ይቅርታ ደረመሰው ) ... የላሎ ትዕግስት ሙጣጯ ተፈፀመ ።
ከኪሱ ያን ድንጋይ ስልክ አንስቶ የሰካራሙ ግንባር ላይ አስቀመጠው ። ሰካራሙ ሊታረድ እንደተዘጋጀ በሬ አጓርቶ ወደቀ ።
ጭራሽ ከሰውየው ይልቅ ለስልኩ ተጨንቆ ተሯሩጦ አነሳት ።
ያ ስልክ ምን ይሆናል ብሎ እንደሆነ እንጃ!
ስልኩን ሲያነሳው እንኳን ሊሰበር ጭራሽ ከጥግ በኩል የተፈገፈገው ምልክት ጠፍቶ አዲስ ሆኖ አረፈው :)
በቃ ታድያ ላሎ ይሄን ስልክ ሲይዝ ደህንነት ነኝ የሚለው ጨረሩን ይለቃል።
"ተው ቲቲ ደህንነት ሳትሆን መምህር መሆንህን ያወቀች ቀን ጉድህ ይፈላል" ብለውም አልሰማ አለኝ። አሁን ደግሞ ጭራሽ ቤቴ ልጋብዛት ነው ሲል ከማርስ ላይ እንደመጣ ዩፎ ትኩር ብዬ አየሁት ።
ስጋቴን አልመከርኩትም...ውሀ ቢወቅጡት እንቦጭ ነው ! ብዬ ንቄ መተዌ ነው ።
ከዛ በኋላ ስሰማ አምስት ኪሎ የምትገኘው ደሳሳ የኪራይ ቤቱ ሊወስዳት መንገድ እየሄዱ ሳለ አንዲት ሰይጣን የላካት ፈልፈላ "ቲቸርዬ " ብላ ተንደርድራ አቀፈችው ።
ቲቲ መብረቅ የወደቀባት ይመስል ክው አለች። የሎጥ ሚስትን ይመስል የጨው ሀውልት ሆና ቀረች ። (ምስኪን ቲቲዬ !)
ከዛ እንደምንም አምጣ "አስተማሪ ነህ እንዴ? " ብላ ጠየቀችው ።
እሱ ደረቱን ነፋ አድርጎ ...
"ይሄ ከቨር ነው...ደህንነት ሆነሽ በሽፋን ነው መስራት ያለብሽ " አላት.. . ተንደርድራ የተጠመጠመችበትን ፈላ እንደ ሎሚ አሽቶ እየጨመቃት ። (በውስጡ ልጅቷን እንደ ኳስ ማንጠር ሁሉ ከጅሎ ነበር )
ሀውልቷ ቲቲ የእየሱስ እስትንፋስ እንደደረሰው በሽተኛ ነፍስ ዘራች ና መንገዳቸውን ቀጠሉ።
ልክ የላሎ ቤት ሲደርሱ ማመን አልቻለችም ።
ከቤቷ ጥበት የዝርክርክ ካልሲዎቹ ጥንባት ዊድ ሆኖ አዞራት ። ወደ ኋላ ተወነጨፈች።
እንኳን እግሯን ልትከፍትለት የልቧን በር ከርችማ ጥላው ፈረጠጠች (ያው ያለችውን መናገር ለሞራሉ ይከብዳል እንጅ እጅ ማስታጠቢያ ውስጥ እየኖርክ እኔን ስጀነጅን አይከብድህም ? ብላ ቅስሙን ከሽክሻለታለች)
በቃ !
ፍቅር በህንድ ፊልም ላይ ብቻ ያለ መንፈስ መሆኑ ያልገባው ላሎ ሱሰኛ ሆኖ አረፈው።
ሲጃራ እና ሺሻ ሲያንቦለቡል ትንሽ የገጠር ጎጆ ቤት የተቃጠለ ይመስል ነበር :)
ከዚህ ሙድ እንዲወጣ ብመክረው ብዘክረው እንደልማዱ አሻፈረኝ አለ ።
ዛድያ..ያ የተከበረ አስተማሪ ታድያ አንድ ቀን ሺሻ ቤት ሲያውደለድል በሰፈር ሚኒሻና በፖሊስ ተቀበደደ።
ሺሻ ቤቷ መልካቸው ከመወየቡ የተነሳ ያንድ አባትና እናት ልጆች በሚመስሉ ሱሰኞች ተሞልቶ ነበር ።
ከቤቷ ሲወጡ ...እንደ ዳርፉር ስደተኛ በሰልፍ ተቀጣጥለው ነው።
ለክፋቱ ደግሞ ሁሉንም የሺሻ እቃ አሸክመዋቸው በሰፈራችን በኩል ነበር የሚያልፉት ።
አቤት ሀፍረት !
አቤት ውርደት!
ምድር ደግሞ ለክፋቷ ተከፍታ አልውጥም አለቻቸው። ስንት ዶክተር ስንት ጠበቃ እየተግተለተለ ወጣ።
የላሎ አከራይቶ ሁኔታውን በጥንቃቄ ሲከታተሉ ቆዩና ወደኔ ጠጋ ብለው.. .
"ላሎ የምን ዋንጫ ነው የያዘው ?" ብለው ጠየቁኝ።
"የዓመቱ ምርጥ አስተማሪ ተብሎ ተሸልሞ ነው"
"ፎሊሶቹስ ምንድናቸው?"
"ዋንጫው የወርቅ ስለሆነ እንዳይዘረፉ እየጠበቋቸው ነው "
እልልልልልል አሉ እትዬ...
"ላሎ ድሮውንም የሚያኮራ ልጄ ነው ... ተመስገንልኝ ያኔ መድሀኒተ ዓለም :) "

@wegoch
@wegoch
@paappii
ሥዕል በማሳል ለ ወዳጅ ዘመዶ ስጦታ ያበርክቱ
በ+251984740577
ወይም @gebriel_19 ላይ ፎቶ በመላክ በ ተመጣጣኝ ዋጋ ማዘዝ ይችላሉ!
#ሥዕል_ብቻ የቴሌግራም ገፅ


@seiloch
@seiloch
"አሹ ሁለት ብር ይዘሀል?" አለኝ የመንደራችን ቀፋይ፣ ከሁለት ቀናት በፊት
'ምን ይሠራልሀል?' አልኩት የሁል ጊዜ ሠበቦቹ ስለሚያዝናኑኝ
"እራሴን ላጠፋ ፈልጌ አሪፍ ገመድ መግዛት ፈልጌ ነው" አለ ሳቅ እያለ
ከኪሴ ድፍን አሥር ብር አውጥቼ እየሰጠሁት
'ካሚል ሱቅ አሪፍ ሲባጎ ታገኛለህ፤ ሁለት ሜትሩን በሁለት ብር ይሸጥልሀል' አልኩት
"ታድያ አስር ብር ለምን ትሰጠኛለህ?" አለኝ ግራ ተጋብቶ
'በሥድሥት ብሩ ሶስት ሲጋራ አጭስ፤ በአንድ ብሩ መናዘዣ ወረቀት ግዛ' ብዬው ላልፍ ሥል
"የቀረችውን አንድ ብርስ ምን ላርጋት?" አለኝ በጭንቀት
'ወንድ ልጅ ባዶ ኪሱን አይሞትም!' አልኩት ኮሥተር ብዬ

ከሰዓት በሁዋላ ቀፋዬ ራሡን መሥቀሉን ሠማሁ።

ዛሬ፥ በሠልሥቱ ድንኩዋን ውሥጥ ካርታ እየተጫውትኩ ሳስበው የገረመኝ ነገር በኑዛዜው ማብቂያ አካባቢ ሞቱን ሥፖንሠር ሥላደረኩለት ማመሥገኑ ነበር!
.
.
.
.
'ማነህ ... ዳኛው፣ .... እስቲ ቦነስ ጻፍልኝ!'

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Ashenafi melese
" እሷ ምን ታርግ ፍቅርዋ ነው የገደለኝ ። በሳቁ ፣በለዛው ፣ በጭምትነቱ ጣሬን ሳያበዛ ጭጭ ያረገኝ ። ሰው ለምን ሳቅክ ተብሎ ይከሰሳል ? "

"የቱጋዬን ገድላ ሄደች? "

" ማን ?"

መልስ ፦ ተከሳሽና ተፈቃሪ


ካሊድ አቅሉ


ዳኛው ፦ " ተከሳሽ የክስ ማቅለያ አለሽ ?"

ተፈቃሪ ፦ " አዎ በጣም ያፈቅረኝ ነበር በህይወት ኖሮ ይሄን ቢያይ እንኳን ሞትኩ ነው ሚለው። "

ጠበቃ ፦ " እድሜ ልክ ነው መፈረድ ያለበት ሟችን ከሞት በላይ ገላዋለች "

እሷ የሞት ፍርዱን ትፈልጋለች ።
ለምን ቢባል አፍዋን ሞልታ ምትመልሰው መልስ አላት ።

"ለምን ? "

ከኔ ጋር ሰማይ ቤት ለመገናኘት ቀጠሮ አለን ያውም በግዜ ከሞትኩ ልትከተለኝ ከሄደች ቀድማ ልከተላት ።
" ያፈቀሩትን ሲያጡ ያገኙትን ይለማመጡ " በፍቅር አይሰራም በፍቅር ሚሰራው " የሚያፈቅሩትን ሲያጡ እራስን ማጣት ወይም እውነተኛ አፍቃሪ መፈለግ ነው ። "

አብዝቼ ወዳታለው አልፎም ገነት ላይ እየጠበኳት ነው ። የእሱ ገዳይ ተብላ እጇ ላይ ካቴና ታስሮ ፍርድ ቤት ገትረዋታል ።

እሷ ምን ታርግ ፍቅርዋ ነው የገደለኝ በሳቁ ፣ በለዛው ፣ በጭምትነቱ ጣሪን ሳያበዛ ጭጭ አረገኝ ። ሳቅ አብዝታ ባጠገቤ እኔም ስርዋን ስምግ ሄድኩ እንደ ቀልድ ምድርን ትቼ . . .

ሰው ለምን ሳቅክ ተብሎ ይከሰሳል ?

" ለመሞት ቀድሞ የወጣውም ጥፋተኛ ነው። "

ሊፈርዱባት ዳር ዳር ሲላቸው በድኑ አካሌ በር ከፍቶ ገባ ። " ነፍሴን ሰውታ አካሌን ለማን ነው ያስቀረችው ?"

"እንጃ "

አያለው ግን አላስተውልም ሰማለው ግን አላዳምጥም አለ አካሌ እኔው ጋር እኔው ነኝ እኔው ጋር የሌለውት ።
( ነፍሴ ተነጥቃለች )

አካሌ የሷ ጠበቃ መሆን ዳዳው መቼስ ነፍሴን ሰርቃለች ተብሎ አካልዋ አይቀጣም ።

ዳኛው ጎሮሮዋቸውን ጠርገው " ግራና ቀኙን አይተናል ፍርዱን ለከሰአት ።
አሉ የመዶሻውን ድምፅ በማስከተል ።


ይቀጥላል ክፍል 2 . . . . .

@wegoch
@wegoch
@paappii
ክፍል (2)
የመጨረሻው ክፍል

በተባለው ሰአት ፍርድ ቤት ቀረብን የሷን ፀጋ እነሱ ዘነጉት እንጂ የከሰመን ነፍስ ማፍፍት ድቅድቅን የምትሰልብ ፍፁም ስራ መሆንዋን እረስተዋል ወይንም አያውቁም አካሌ በድን የነበረውን የሷን ፍቅር ነስንሳበት ነፍሴን ፍክት አድርጋ ሙሉ አርጋ መልሳለች ። በነፃ ቢለቅዋት እንኳን ፍርድ ቤቱን ከሳ ካሳ መቀበል ያስፈልጋታል ።

" ለምን? " ቢባል

አማርሽ ብሎ መክሰስ ሳቅሽ ብሎ መውቀስ ምን ሚሉት ፈሊጥ ነው ?

ሰው በፀዳልዋ መቆም አቅቶት ከወደቀ እሷ ምን ታርግ አትራመድ አትናገር አትሳቅ አይባል . . .

በዚህ መሀል ከባድ የአላርም ድምፅ ከእንቅልፌ ቀሰቀሰኝ አሻግሬ ሰአቱን ሳይ ሁለት ሰአት ከሀያ ደቂቃ ይላል ድንግጥ አልኩ ከህልም ችሎት ወደ መኝታዬ ምድር ስመጣ ።

አምስት ሚስኮልና አንድ መልዕክት አለህ ይላል ስልኬን ድጋሚ ሳበራው "ሶስት ሰአት ላይ የተለመደው ካፌ ጠብቅሀለው"
ይላል የተላከው መልዕክት ። የህልሜን አለም ለመንገር ወደምንገናኝበት ካፌ ነፍሴን ጥዬ እሮጥኩ . . . . .
~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~
@kalidakelu

@wegoch
@wegoch
@paappii
በመፅሀፍ የሚገኝ ደስታ
ብሄራዊ ትያትር.. . Tommorow afternoon local 7.00
ለሰው መድሀኒቱ ሰው ነው ። መነሻችን የሰው ማህፀን መድረሻችን የሰውነት ስሪት ቀመር ነው።
ከሰው ማህፀን ተፈጥረን በሰውነት አፈር ውስጥ እንደበቃለን።
መድሀኒቴ እናንተ ናችሁ ... ስፅፍ የምናቤ ግብዓት ናችሁ ።
የፅሁፌ ትርፍ ገንዘብ አይደለም...አንድ መፅሀፍ ፅፈህ.. .ሀገር ምድሩ እስኪታዘብህ ፕሮሞት አድርገህ.. . ለሳምንት ምሽቶች መዝናኛ የሚሆን ትርፍ እንኳ አታገኝበትም።
ብዙ ደራሲዎች ለምን ትፅፋላችሁ ብትሏቸው መልሳቸው ምንም ነው። ስነ ፅሁፍ ልክፍት ነው... እያንዳንዱን ስራህን ቅርፅ አስይዘህ መሬት ስታወርደው አዲስ ፍጥረት ፕላኔቷ ላይ ያመጣህ ያህል ይሰማሀል።
ትርፍህ የሰው ሀሴት ነው። ለምሳሌ ሸግዬ ሸጊቱን ያነበቡ ሰዎች ሲደውሉ አንተ በፈጠርካቸው ታሪኮች ላይ በስሜትና ደስታ ሲያጫውቱህ የሚሰማህን እርካታ ብዬ ልገልፅልህ እችላለሁ?
...
ሸግዬዋን ነገ እንመርቃታለን። ሁላችሁንም ጋብዣችኋለሁ...ለብዙዎች በስልክም በቴክስትም እንዳትቀሩ ብያለሁ። ሌሎቻችሁም በስጋ ስራ ተወጥሬ ዘንግቻችሁ ቢሆን ይሄን ተረድታችሁ ነገ ተገኙልኝ።
ስትገኙ ከእናንተ የሚጠበቀው ፅሞናችሁን ይዛችሁ መምጣት ብቻ ነው።
ትኬትም ገንዘብም አልሻም...እናንተ መጥታችሁ በታላላቅ ገጣምያን እና ደራሲያን ስራዎች ተደስታችሁ መሄዳችሁ ብቻ ለኔ ክብር ነው ።
አክብሬ ጋብዣችኋለሁ።
አደራ !!
#ሚካኤል አስጨናቂ
የቤቱን ባለቤት እየናቁ እንዴት ቤቱን መውደድ ይቻላል ?

(ካሊድ አቅሉ )

ዊንታ ድምፅዋን ደመቅ አድርጋ አለምን በእስዋ ልክ ፈታች

" በአንድ ሳንቲም ሰውና አንበስ መሆን አንበሳው ካልቀና ወደ ሰው . . . "

ስንቴ ምንኖር መሰላት ? የምር አሁን ካልኖርን መች እውነተኛ ኑሮን እናጣጥማለን ህይወት ትርጉምዋ ማይገባን ደስታን ከገንዘብ ጋር በማስተሳሰራችን ይመስለኛል ያለመርካት እሳቤን ስናሳድድ በሞት እንቅፋት ተደፍተን መቅረት ። የውሸት ኖሮ የእውነት ሞት ።

መለስ አልኩና " እኔ ምልሽ ዊንታ መች ለማግባት ታስቢያለሽ ? "

" እእ ሀብታም ባል ብቻ ይምጣ መልኩ ውስጣዊ ውበቱ አልልም ጥልቅ ነው ምለው " ፈጣሪ እራሱ ሲጣንን ወደ ገሀነም ሲወረውር እንዲ አልፈጠነም ።

መዋደድን ፍቅርን ስብዕናን ህሊናን በሲኖትራክ ስትወጣባቸው ዳር ሆኚ አይኔን ይዤ የምታዘብ ይመስል ቀፈፈኝ ። ፍቅር እኮ ይቀድማል ትዳርን ያሳደገው መዋደድ አይደል ? የቤቱን ባለቤት እየናቁ ቤቱም መናቅ ይቻላል ?

" ያርግልሽ ባይባልም ለሀብት ያለሽ ቦታ ትዳርን ሳይሆን ሀብትን ምታገቢው ያስመስልብሻል ሀብታም ባል ቤት ያለው ድርጅት ያለው ዱባይ ሚያዝናና. . . "

" ሁለት እግር አለኝ ተብሎ ሁለት ዛፍ አይወጣም ያሉት ሁለት ለተራራቁ ዛፎች ነው ጥንድ የቆሙ ዛፎች ከሆኑ እግርን አንድ ላይ ገላን አንደኛው ላይ ማሳረፍ ይቻላል ። "

ልቆቆማት እንዳልቻልኩ ተሰማኝ ግን የተሸናፊ ወግ መሀል ላይ አሸናፊ መምሰል ነው ። ለዘብ ብዬ ቀጠልኩ " አትሸወጂ ሁለት ዛፍ ላይ መውጣት አንድ ሰውነት ሁለት ቦታ መክፈል ከባድ ነው ። ለአንዱ ላይ የሚወጣን ሀይል ሁለት ቦታ ከፍሎ ተንገላቶ ማለፍ ነው ። " መድፍ የሆነ መልስ ልካብኝ እሮኬት መልስ ላኩላት አፍዋን ጥያቄዋን መልስዋን ድማሚት እንዳገኘው ከተማ ብን አለ ። ፍርስራሾችዋ ብቻ ሰው ፊት ያንዣብባሉ አስተሳሰብዋ ብን ብሎ ጠፍቶ መልስ ሳይሰጠኝ አካልዋ በድን ሆኑ ጥላኝ መንገዱን ቁልቁል ተያያዛችው ወደ ታች የሚወርደው ገላዋ የስብዕናዋ ማሳያ ሆኖ ታየኝ የሚወርድ እግር የሚወርድ አይምሮ . . . .

@KALIDakelu

ሼር!!

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ፍቅር ና ጦርነት

ክፍል 1

ጳጉሜ 3 2013 ዓ.ም

ከቀን ወደቀን ቢሻለኝም የክረምቱ ብርድ ህመሜን ጨምሮታል ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያለሠው ድጋፍ መንቀሳቀስ ችያለሁ ሠፈር ውስጥ ዞር ዞር ማለት ጀምሬያለሁ ። እንዲያውም ከሞት ያተረፈኝን ለቤቴ ያበቃኝ አምላክን ለማመስገን ወደ ቤተ-ክርስቲያን እየሄድኩ ነው ። ለዚህ እበቃለሁ እግሮቼ እንዲህ መንቀሳቀስ ይችላሉ ብዬ አላሰብኩም ነበር ከ 2 ወር በላይ ከተቀመጥኩበት ዊልቸር እነሳለሁ እንዳሁኑ እንቀሳቀሳለሁ እንደ ሰው ቆሜ እሄዳለሁ ሚል ምንም ግምት አልነበረኝም ታዲያ እኔ አምላኬን ያላመሰገንኩ ማን ሊያመሰግን ከሞት መንጋጋ ያተረፈኝ ያላመሰገንኩ ማን ሊያመሰግን ማንም ለዛነው ወደ ቤተክርስቲያን በመሄድ ለማመስገን ማሰቤ።

ዝናቡ ሚያቆም ባይሆንም ለብርዱ ልብስ ደራርቤ ከቤት ወጣሁ ፧ ከቤታችን በቅርብ የሚገኘው መድሀኒአለም ቤተክርስቲያን ነው ። ከልጅነቴ ጀምሮ ያደኩት ቤተክርስቲያን ስለሆነ ስምልም ረሱ መድዬን ብዬ ነው ለቤታችን ቅርብ ነው 20ደቂቃ ቢፈጅ ነው አሁን ግን ለኔ ከ 45_60 ደቂቃ ሳይፈጅብኝ አይቀርም እራሴን ጠንክር በል ብዬ ጉዞዬን ጀመርኩ ።

መንገድ ላይ ብዙ ሰው ጋር አልተገናኘሁም በዝናቡ ና ገና ጥዋት በመሆኑ ምክንያት ግን ያገኘሁት ሰው ሁሉ ከንፈራቸውን እየመጠጡ ነው ሚያልፉት ሀዘኔታ ይሁን መገረም ባይገባኝም ምንም ምቾት አልሰጠኝም ። ወደ ቤተክርስቲያን እየደረስኩ ስመጣ ሠውነቴ በጣም ዛለ ድካም ተሰማኝ እንደምንም ብዬ የ ቤተክርስቲያኑን መግቢያ ተሳልሜ ለምእመናን ወደ ተሰራው መጠለያ ገብቼ አረፍኩኝ ። የተጎዳችው እግሬ ህመም መቋቋም አቃተኝ ስልኬን አውጥቼ ስመለከት ከቤት ከተነሳው 50 ደቂቃ ሆኖኛል በጣም አዘንኩ 50 ኪ/ሜ በምጓዝበት እግሬ 50 ደቂቃ ተጓዝኩ ብሎ እንዲህ መሆኑ አናደደኝ አይሰው መሆን ከንቱ በተፈጥሮ ተገረምኩኝ ግን ምንም ቢሆን መጠንከር እንዳለብኝ ለራሴ ነገርኩት ። በመጠለያው ትንሽ እንደቆየው ያላስተዋልኩትን ነገር አስተዋልኩ ያለሁበት በሴቶች ቦታ ነበር ድካሜ ሲጠፋልኝ ቦታ ለመቀየር ከተቀመጥኩበት ስነሳ እግሬ አቅም አቶ ወደድኩኝ ። ከየት መጣች ያልተባለች ልጅ "እኔን " ብላ እጇን ዘረጋችልኝ እኔ ማየው አፍዞኛል መላክ ያየው መሰለኝ ክንፉን የዘረጋ ግን ሴት መላክ ከየት መቶ ፤ ደሞ ማነው መላክን ወንድ ያረገው ብቻ ግራ ገባኝ አምላክ ለኔ የላካት መሰለኝ ባይኔ አካሏን ስቃኘው እንደኔው ፍጡር ናት ፈራሽ ገላ ነው የያዘችው በዛችው ደቂቃ አዘንኩላት ከገነት ተባራ ምድር ላይ ምደክም እንጂ እንደ ሰው የሁለት ሠዎች ውጤት አትመስልም ግን ምን መድረግ ይቻላል እንደኔው ፍጡር ናት ........

ክፍል 2 ይቀጥላል

@wegoch
@wegoch
@paappii
ፍቅርና ጦርነት

ክፍል 2

"ወንድም ተጎዳህ እንዴ.. ወንድም " ብላ እጄን ስትይዘው ከሀሳቤ ነቃው እንደምንም በሷ እገዛ አመቺ ቦታ ተቀመጥኩኝ እግሬን እንደ ፈለኩኝ ማንቀሳቀስ እንደማልችል ስትረዳ " እግርህን ሚያምህ ከሆነ ለምን መደገፊያ ክራንች ወይም ሚደግፍህ ሰው ሳትይዝ መጣህ " እንዳ ቀረቀረች ጠየቀችኝ "አይ ተሽሎኝ ነበር እኮ ትንሽ ስንቀሳቀስ ነው ያመመኝ " የእግሬ ህመሙ ሲብስብኝ በእጄ ጠበቅ አርጌ ያዝኩት "አይዞህ አምላክ ይርዳህ" ብላ ለመሄድ ስትዘጋጅ መንቀሳቀስ እንደማልችል ና ከሷውጭ ሊረዳኝ ሚችል ሰው እንደ ሌለ የቤተክርስቲያኑ መውጫ ደረጃውን ለመውጣት እንድትረዳኝ ስጠይቃት እሺታዋን ገልጻልኝ አስከምረጋጋ አብራኝ ቁጭ አለች ።

ለደቂቃዎች ሳናወራ ብንቆይም አለባበሷን አይቼ በዚህ በብርድ እንዲህ መልበሷን ና ቤተክርስቲያን ውስጥ መሆኑ ገርሞኝ "ይህ አለባበስ ለቤተክርስቲያን ይፈቀዳል" ብዬጠየኳት እንዳቀረቀረች ፀጉሯን እያስተካከለች "ሰው ነው እንጂ አምላክ ልብስን አያይም የልቤን ችግር ደሞ እሱ ያቃል " ብላ ለይስሙላ ፈገግ አለች ፈገግታዋ ውስጥ ሀዘን አለው ፈገግታዋ ውስጥ መጎዳት አለው ፈገግታዋ ውስጥ ብቸኝነት አለው ።

የለበሰችው ልብስ ስስ የሌሊት ልብስ ሲሆን ሰውነቷን በከፊል ያሳያል ፀጉሯ ፊቷን ካልሸፈንኩ ካልሸፈንኩ ሚል ይመስላል እርዝመቱ መጋረጃ እንጂ ፀጉር አይመስልም እግሮቿ በጭቃ ተበላሽተዋል ውበቷን ግን አልቀነሱትም ትኩር ብዬ ከተመለከትኳት በኋላ እንደበረዳት ገባኝና የለበስኩትን ሹራብ አውልቄ ሰጠኋት ፧ ትንሽ ብትግደረደርም ተቀብላኝ ለበሰችው ሰውነቷ ተፍታታ እንደንጋት ጮራ ፊቷ አበራ "ስምሽ ግን ማነው " ድንገት ጠየኳት ፈገግ ብላ " ፀጋማርያም እባላለሁ " አለችኝ እውነትም የማሪያም ፀጋ በግርምት ላይ ግርምት ጨመረችብኝ አድናቆቴን በሆዴ ደብቄ መሄድ እንደምንችል ነግሬያት ብድግ ስል እሷ ቀድማ ተነስታ ደግፋ አነሳችኝ እጄን ትከሻዋ ላይ አድርጌ መንገዳችን ጀመርን ።

የቤተክርስቲያኑን መውጫ አልፈን ዋና መንገዱ ላይ ስንደርስ ካልቸኳለች ቤቴ ቅርብ ስለሆነ እንድታደርሰኝ ጠየኳት ችግር እንደሌለው ነግራኝ መንገዳችንን ቀጠልን ፤ ቤት እስክንደርስ ስለብዙ ነገር አወራን ። በብዛት ስለራሷ ባትነግረኝም ችግር ውስጥ እንደሆነች ነገረችኝ እኔም ምን ሆኜ እንደተጎዳው ብጠይቀኝም በጦርነት ተጎድቼ እንደሆነ ብነግራት ትፈራለች ብዬ በቀልድ አድርጌ አለፍኩት የተለያዩ ነገሮችን እያነሳን እየተጨዋወትን ቤት ደረስን።

የጊቢውን በር ከፍቼ ወደውስጥ ገባን ቤቱን ከቤተሰብ የወረስኩት እንደሆነና ሁሉንም ክፍሎች ዋናውን ቤት ጨምሮ አከራይቼ እኔ ጥግ ላይ ያለችው ቤት ውስጥ እንደምኖጋ እያስረዳኋት እያለ ስልኬ ጠራ ቤቱ ክፍት እንደሆነና አውርቼ እስክጨርስ ገብታ እንድትጠብቀኝ ነግሬያት ስልክ ማውራት ጀመርኩኝ ። በጣም አስፈላጊ ስልክ ስለነበር ሳላስበው ብዙ ደቂቃ አወራው ስልኩን ጨርሼ ወደቤት ስገባ እንደ ህፃን ልጅ ጥቅልል ብላ ተኝታለች መላክ ይተኛል እንዴ ? ደሞ ማማሯ ውበት ማለት አንቺ ብሎ የተዘፈነው ለሷ ይሁን እንዴ ........

ክፍል 3 ይቀጥላል ......

@wegoch
@wegoch
@paappii
@wegoch
@wegoch
@paappii

#Narrated by Rediet

Written bye Ashenafi melesse
Audio
2024/09/26 23:17:42
Back to Top
HTML Embed Code: