Telegram Web Link
#ክፍል_አራት (የመጨረሻ ክፍል)
:
:
ደረሲ:-ሜሪ ፈለቀ
:
:
....“ባለቤትሽ? ኢሳያስ?…………”
“ቢሮዬ ድረስ እየመጣህ ለምን ትረብሸኛለህ ኢሳ?” “ናፈቅሽኝ!! ከዚህ በላይ ሳላይሽ መቆየት አልችልም። ”ከዩንቨርስቲ ጀምሮ የማውቀው ሰው ነው ኢሳያስ። ለ6 ዓመት አብሮኝ የቆየ
የትዳር አጋሬም ነው። አብረን በኖርንባቸው ጊዜያት መጀመሪያዎቹ አመታት በፍቅር ያጌጡ ነበሩ። እየሰነባበተ ግን ሳንጨቃጨቅ ያለፉ ቀናት ውስን ሆኑ። የሁለት ዓመት ልጃችን በሞት ስትለየን ሰላማችን ይብስ ደፈረሰ። ልጃችን የሞተችው በምግብ መመረዝ ነው። ታማ ስትሰቃይ ሁለታችንም ልንደርስላት አልቻልንም ነበር። ሰራተኛዋ ስትደውልልኝ ስራ ላይ ነበርኩ። ስልኬን እየሰማሁት ቆይቼ ለመደወል አስቤ ተውኩት። ግን ቆይቼም አልደወልኩም። ሌላ ስራ ያዝኩ። እናም ልጄን ሳልደርስላት ሞተች። እሱም በተመሳሳይ ምክንያት ስልክ ሳይመልስ ቀረ። ቆይቼ ስደርስ ዘግይቼ ነበር። ለዚህ በደሌ አንድ ሚሊየን ጊዜ ራሴን ብቀጣውም በቂ አይሆንም። ከኢሳያስ ጋር መወቃቀሱ አቁሳይ ስለነበር በሆነው ባልሆነው ሰበብ እየፈለጉ መነታረክ ሆነ ምሽታችን። ቤቱን ለቆ ከወጣ ሶስት ወር አለፈው።“ቁጭ ብለን እንድናወራ እፈልጋለሁ። ” አለኝ አይን አይኔን በልመና እያየ። ምንድነው ልለው የነበረው? ‘ውጣልኝ‘ ነበር ሌላ ጊዜ ቢሆን የምለው። አሁን የምትሸሸዋን ሴት አይደለሁም። ምንም ቢሆን የምትጋፈጠዋን ማህደር እየተለማመድኳት ነው። “እደውልልሃለሁ። ” ያልኩትን ያመነኝ አይመስልም። ተገርሞ እያየኝ ተሰናብቶኝ ወጣ። የገባኝ አንድ ነገር ሲሳይ በብዙ ፍጥነት ማንነቴን እያሾረው መሆኑ ነው። ወደ ቤቴ ገብቼ ሲሳይ ያለኝን አደረግኩ። «በህይወትሽ የምትሸሺው ነገር ምንድነው? መስታወት ፊት ቁሚና ለራስሽ ንገሪው። እመኚው!! መቀየር የማትችዪውን ነገር መቀበል ነው የሚፈውሰው።» ነበር ያለኝ የልጄን ፎቶዎች ከደበቅኩበት አወጣኋቸው። በመጀመሪያው ቀን ቀላል አይሆንም ነበር ያለኝ። ቀላል አልነበረም። ሁሉንም ፎቶዎች በፊት የተሰቀሉበት መለስኳቸው። መሸሽም መደበቅም መድሃኒት አይሆንም። ስሸሽ የተጠራቀመው እንባዬ ገደቡን ጥሶ አይኔን አደፈራረሰው። ስልኬ መጥራቱን እንኳን የሰማሁት ብዙ ከጠራ በኋላ ነበር። «ምን ሆነሻል? አልቅሰሽ አይደለምኣ?» ሲሳይ ነው። «ነው! አልቅሼ ነው።» እያልኩት ጭራሽ መንፈቅፈቅ ጀመርኩ። «እህህህ ምን ተፈጠረ ቆይ?» እቤቴ ደጅ ድረስ አድርሶኝ ነበር የተመለሰው። መልስ መመለስ እስኪያቅተኝ ሲቃዬ አነቀኝ። «በቃ በቃ እሺ መጣሁ። ስልኩን አትዝጊው እያወራሁሽ እደርስልሻለሁ። እኔ አጠገብሽ ሆኜ እንደፈለግሽ እንድታለቅሺ ፈቅድልሻለሁ። እስከዛ ግን ስወድሽ አታልቅሺ?» ብሎኝ ሊያስቀኝ እየሞከረ ከቤቱ ሲወጣ፤ «ብርድ እንዳይመታህ በደንብ ልበስ» ስለው «አትስጊ ካልሲ አጥልቄለታለሁ» ሲለኝ
ታክሲ ሲያናግር «የኔ እመቤት ደሞ ስስ ፒጃማ ፍለጋ ቁምሳጥኑን ዘረጋግፊው አሉሽ!» ሲለኝ ሲከፍል «ስንቴ መስታወት አየሽ?» ሲለኝ ሲደርስ እውነትም ማልቀሴን ትቼ ልቤ ተሰቅሎ እየጠበቅኩት ነበር። በሩን ከፍቼ
ተጠመጠምኩበት። ሙሽራውን በሰርጓ እለት ወደ መኝታ ቤታቸው እንደሚያስገባ ሙሽራ አቅፎኝ ወደሳሎኑ ገባ! ማልቀሴን እረሳሁት። ሳሎኑ ውስጥ የተሰቀለውን የእኔንና የኢሳያስን የሰርግ ፎቶ አይቶታል። ግን አልጠየቀኝም። ሌላ ነገር እያወራ ሲያስቀኝ ቆየ።
«ሲስ?»
«ወዬ እመቤቴ?»
«ስለእኔ ማወቅ ያለብህ ነገር አለ።»
«ምኑን ትነግሪኝ? በፎቶ አሳየሽኝኮ አስጎበኘሽኝ።» አለ ወደፎቶው እየጠቆመኝ።
«እየቀለድኩ አይደለም ሲስ! ከምሬ ነው።» «እሺ እመቤቴ ንገሪኝ! ይኸው! Am all yours!» ስለ ኢሳያስ እና ስለልጄ ነገርኩት ብቻዬን ስለፈልፍ ሲያባብለኝ እና ሲደባብሰኝ ብቻ ቆየ። ብዙ ደቂቃ እቅፉ ውስጥ ካቆየኝ በኋላ
«ባንቺ ደረጃ ካሉ ሴቶች ይልቅ አንዲት ምንም የማታውቅ የቤት እመቤት
የሰመረ ትዳር ለምን የሚኖራት ይመስልሻል?» አለኝ «ጭራሽ እንደዛ ስለመሆኑም እንጃልህ! ምን ለማለት ፈልገህ ነው?» «ይሄ ሀቅ ነው ብዙ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በጋራ ስምምነት ባስቀመጥነው ደረጃ ብዙዎቹ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ያሉ ሴቶች በትዳራቸው ስኬታማ አይደሉም።» «ምናልባት ከትዳራቸው ሌላ ትኩረታቸውን የሚሻ ሌላ ስራ ስላላቸው?» «እኔ አይመስለኝም። እነዛ በትዳር ውስጥ ለፍቅር ወይ ለልጃቸው አልያም በሌላ ምክንያት ዝቅ ማለትን ያውቁበታል። እስኪ አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ? ክርስቶስ ለባል የሰጠው ትእዛዛ ሚስትህን ክርስቶስ ቤተክርስትያንን በወደደበት ፍቅር ውደድ የሚል ነው። ያ ማለት ነፍሱን እስከመስጠት። ለሚስት ያላት ግን ሚስት ለባሏ ትገዛ ነው። የቱ የሚከብድ ይመስልሻል?» ሳልመልስለት ራሱ ቀጠለ። «ባትወጂም መገዛት ትችያለሽ። ወደሽ አለመገዛት ግን በፍፁም አትችዪም።» ዝም ነበር መልሴ። ከአንዱ ስሜት ወደሌላው መሻገር ምንም አይከብደውም። መከፋቴን አስረስቶኝ አመሸን። «ያው እንደምታውቂው ድንግል ነኝ። በዛ ላይ ቁስሉ ራሱ ሰበብ አይፈልግም።» ብሎኝ እኩለ ለሊት አልፎ ወደ ቤቱ ሄደ።

★ ★ ★
በሚቀጥለው ቀን በስራ የደከመ ሰውነቴን እየጎተትኩ መኪናዬጋ ደረስኩ።
መሽቷል። እቤቴ ገብቼ ማረፍ ነው ያማረኝ። ስልኬ ጠራ። ሲሳይ ነው።
“እራት በላሽ?” “አልበላሁም። ግን ደክሞኛል በጣም።” “እማ ቆንጆ እራት ነው የሰራችው። እየጠበቀችሽ ነው።” “ትቀልዳለህ እንዴ? ማን ነኝ ብዬ ነው እናትህ ቤት እራት ልበላ የምመጣው?” “ማንም መሆን አይጠበቅብሽም። ሰው መሆን የእማን እራት ለመብላት በቂ ነው።”

★ ★ ★
አመመኝ። የቤተሰቡ ፍቅር አሳመመኝ።
“ደህና ነሽ ግን?”
“ምነው ደስ አላለሽም?”
“ምነው ልጄ ከፋሽሳ?” ይሉኛል እየተቀባበሉ ። አመመኝ። የሚታገለኝን እንባ እየዋጥኩ የደመቀ እራት
በላሁ። የቤተሰብ ፍቅር ህመሜ፣ ንጭንጬ ፣ ሽንፈቴ፣ ድክመቴ መሆኑ
አልገባቸውም። ይሄን ፍቅር በዘመኔ አይቼው አንጊንቼው እንደማላውቅ አያውቁም። የሲሳይ እናት ፊቴን እያገላበጡ፣ ፀጉሬን እየዳበሱ የሆንኩትን ሲጠይቁኝ እናት እንደማላውቅ አያውቁም። አባትየው እየደጋገሙ ‘ልጄ‘ ሲሉኝ። አይኑ ለማያይ ያአረጀ አያቴ እየተላላኩ እና ምርኩዝ ሆኜ እንዳደግኩ አልገባቸውም። እህቶቹ እግሬ ስር በርከክ እያሉ ‘ሲሳይ አስከፍቶሽ ነው? እሱ እኮ ክፍት አፍ ነው።” ሲሉኝ አያቴ ሞቶ የአክስቶቼ ልጆች እንደምናምንቴ እየቆጠሩኝ ተምሬ መጨረሴን አያውቁም። ብዙ አወሩኝ። እቤት ይዟት የመጣ ብቸኛ ሴት መሆኔን ነገሩኝ።

★ ★ ★
እንደምንም ያመቅኩትን እንባዬን መኪናዬ ውስጥ ሲሳይ እቅፍ ውስጥ ዘረገፍኩት። አላባበለኝም። እየደጋገመ እንባዬን እየጠረገ ፣ ፀጉሬን እያሻሸ ጠበቀኝ። “አውሪኝ። የተሰማሽን ሁሉ አውሪኝ።” አለኝ። ሲቃዬ አላስወራ አለኝ።
ጣቶቹን ፀጉሬ ውስጥ ሰዶ ወደራሱ አስጠጋኝ። ይበልጥ ሲቀርበኝ ከመቃወም ይልቅ ልስመው ፈለግኩ። በሌላኛው እጁ እንባዬን ከጉንጬ ላይ ጠራረገው። ከንፈሩ ከንፈሬን የሚነካበት ሰዓት ረዘመብኝ። መጠበቅ አቃተኝ። ሳምኩት። ነፍስ በሚያሳርፍ መሳሙ ለደቂቃዎች ሳመኝ። “ምንም ይሁን ንገሪኝ፣ አንድም ሳታስቀሪ የተሰማሽን ንገሪኝ፣ አንቺ ራስሽን ከምትረጂው በላይ እረዳሻለሁ። እንባሽ ከመጣ አልቅሺ ብቻ ልስማሽ!” አለኝ መረጋጋቴን ሲያይ “አሁን እኮ መሽቷል። ሌላ ቀን ላውራህ?” “ማደር ካለብኝ እየሰማሁሽ አድራለሁ።”
አውርቼ የማላውቃቸውን ብዙ ነገሮች ነገርኩት። ሳለቅስ አያባብለኝም። እጄን እየደባበሰ ይሰማኛል። ስለቤተሰቦቼ ሁሉንም ነገርኩት። አያቴ ሲሞት ከልጅነቴ ጀም ምርኩዙ ሆኜ ስላደግኩ

ያለው
ን ንብረት ሁሉ ተናዞልኝ ነበር የሞተው። በንብረቱ ሳቢያ ዘመዶቼ ሁሉ በፊት ይጠሉኝ ከነበረው በብዙ እጥፍ ጠሉኝ። የደበቅኩት የለም ሁሉንም ነገርኩት። ያልሰማኝ የለም። ያለፍትን ውሳኔዎቼን በሙሉ ቆም ብዬ እንዳይ አደረገኝ። እቤቴ ስገባ እንደሌላው ቀን ኢሳያስ የሌለበት ወና ቤት አላስጠላኝም። አልጋዬ ላይ ጋደም ብዬ ከራሴ ጋር አወራሁ። “በራስሽ መተማመን ካለብሽ ራስሽን እወቂው። ጠንካራ ጎንሽን እና ድክመትሽን ለዪ፣ ድክመትሽን በጠንካራው ነገርሽ ለመሸፈን አትሞክሪ፣ ተጋፈጪው ማሻሻል ያለብሽን አሻሽዪ፣ ያለፈ ቁስልሽን ተቀበዪው እመኚው እንጂ አትሽሺው።” ያለኝን የሲሳይ ንግግር አሰብኩት። ደስ ብሎኝ ተኛሁ።

★ ★ ★
በጠዋት ወደስራ ስገባ ሲስተር ቀለምን ቀድማኝ አገኘኋት ። ጠርቻት ለልጆቿ
የሆነ ነገር እንድታደርግ የተወሰነ ገንዘብ ሰጠኋት። እጄን እያገላበጠች ስትስም
እንባዋ ነካኝ። አቀፍኳት። እስከዛሬ ልረዳት ባለመቻሌ ራሴን ረገምኩት። እቤቷ ሄጄ ልጆቿን ላይላት ለሳምንቱ መጨረሻ ቀጥርያት ስራ ጀመርን።
በህይወቴ ከመቼውም ጊዜ በላይ ደስተኛ ነኝ። ግን ደግሞ መንታ መንገድ ላይም ነኝ። ሲሳይና ኢሳያስ!! የብዙ ዓመት አለሁሽ ባዬ ግን በራሴ ትህምክትና ፍራቻ ያልተረዳሁት ኢሳያስ ሳልነግረው የማስበው እና የሆንኩት የሚገባው ሲሳይ መወሰን ነበረብኝ። ማናቸውንም መምረጥ ህመም አለው። ፈሪ ግን አይደለሁም። አልሸሽም።
★ ★ ★
ውሳኔዬን መጀመሪያ ለሲሳይ ማሳወቅ ፈለግኩና አገኘሁት። ነገርኩት።“እርግጠኛ ነሽ?” አለኝ መጀመሪያ ግራ እየተጋባ “አዎን። መቼም እንደዛሬ እርግጠኛ የሆንኩበት ውሳኔ የለም። ” መለስኩለት “አሁን ነው የገረዝሽኝ። ያማል።” አለኝ ድምፁን ዝግ አድርጎ “አዝናለሁ። አንተ በህይወቴ ፈጣሪ የላከልኝ መልዓክ ነህ። ባልጎዳህ በወደድኩ። ”አልመለሰልኝም። ግንባሬን ሳመኝ። ለመጀመሪያ ጊዜ ሲከፋው አየሁት። ሊሄድ መንገድ ከጀመረ በኋላ መለስ ብሎ እንዲህ አለኝ “ኢሳያስን እድለኛ መሆኑን ንገሪው!!”

★ ★ ★አሁን ጨረስን።★ ★

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Meri feleke
#ወግ_ብቻ
.
=> አድዋ እና ሰበቡ
©በሲራክ ወንድሙ
... ክፍል ፩
....... ይህ ፅሁፍ ኅብረ ኢትዮጵያ በሚል ርዕስ በቴዎድሮስ በየነ በ2008 ዓ.ም ከታተመው የታሪክ መፅሀፍ ውስጥ የአድዋ ድል ከሚለው ምዕራፍ ላይ ለአንባቢ እንዲበጅ (እንዲገባ) በሌላ ቅንፍ በትንሹ እውቀቷን ለማስጨበጥ በሌላ ሌላ ቅንፍ ለመላው አፍሪካ የነፃነት በዓል ምክኒያት በማድረግ ከ ፌስቡክ ሆይሆይታ ና ሆያሆዬ ባሻገር ጦርነቱ ላይ በምናብ በመገኘት ለመዘካከር ነውና ሳትሰለቹ አንብቧት።

መጀመሪያ ላይ ስለአድዋ ጦርነት መንስኤ ሲነሳ የውጫሌው ውል አንቀፅ አስራ ሰባት እንደሆነ በሰፊው ሲነሳ እንሰማለን
ውሉ ችግሩ ምንድነው? መቼ ተፈራረሙ? ውጫሌ የት ነው?

....ውጫሌ በወሎ ወረኢሉ ውስጥ የምትገኝ መንደር ስትሆን ይህን ውል የኢጣልያ መንግስት እና የኢትዮጵያ መንግስት በሚያዚያ 25 ቀን 1881 ዓ.ም በውሉ አስተርጓሚ በግራዝማች ዮሴፍ ንጉሴ የተከናወነ ውል ነው።
ውሉ ጠቅላላ 20 አንቀፅ ሲኖረው ለጦርነቱ መነሻ የሆነው አንቀፅ 17 ነው።

እስኪ አንቀፁን በሁለቱም ትርጉም እንመልከተውና ለጥቀን ሌላውን እንቀጥል:-
#በአማረኛ_የተፃፈው
"የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት ከአውሮፓ ነገስታት ለሚፈልጉት ጉዳይ ሁሉ የኢጣሊያ መንግስት አጋዥነት መላላክ ይቻላቸዋል።"

.... ይላል።
#በኢጣሊያኛ_የተፃፈው_ደግሞ
"የኢትዮጵያ መንግስት ከውጭ አገር መንግስታት ጋር የሚያደርገውን ግንኙነት በኢጣሊያ መንግስት አማካኝነት ማድረግ ይገባቸዋል።"
...የሚል ነበር።

ጣሊያኖች ይህን ውል ከተዋዋሉ በኃላ ለ12 የአውሮፓ መንግስታትና ለዩናይትድስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ጭምር October 11 ቀን 1889 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ
#ኢትዮጵያ_በኢጣሊያ_ስር_ነች እያሉ አሳወቁ።
በትምህርት ቤት መማሪያ ደብተሮችም ላይ ሁሉ ኢትዮጵያ በኢጣሊያ ጥገኝነት ስር ናት የሚል ታተመ።

ይህ ለአድዋ ጦርነት መነሳት ምክኒያት ና ዋነኛ መንስኤ የሆነው ጉዳይ ሊታወቅ የቻለው አለቃ አፅመ ጊዮርጊስ የተባሉ ቋንቋ አዋቂ አፄ ምሊኒክ በሰጧቸው ትዕዛዝ መሰረት የውሉን ሰነድ በመመርመር የውሉ 17ኛው አንቀፅ የያዘውን ትርጉም መዛባት በመግለፅ ጉዳዩ ኢትዮጵያ የምትጎዳበት ስለመሆኑ ጭምር በማስረዳት በሰጡት ቃል ነው።

............. ይህን ያህል ስለ17ኛው ውል መሳሳት አቅጣጫ ከያዝንና ካየን የትርጉሙ መጭበርበር እንዴት ከአለቃ አፅመ ጊዮርጊስ ለአፄ ምሊኒክ እንደደረሰ እንቃኝ።
አለቃ አፅመ ጊዮርጊስ ባልታተመ (ይህ የወንድማችን ቅፅ አንድ እስከወጣበት ጊዜ ድረስ) መፅሀፋቸው እንደገለፁት ለአፄ ለምሊኒክ እንዲህ ሲሉ በደብዳቤ አመለከቱ :-
<< የተፃፈው ውል ኢጣሊያ አገር የሚሄደው ማለፊያ ነው።
ብቻ 17ኛውን ክፍል ይመልከቱት።ዛሬ በሚዛን ብትመዘን የብር ተመን አትሆንም ካንድ ዓመት በኃላ ግን ከሺህ ቶን ፈረሱላ እርሳስ ይልቅ ትከብዳለች። >>

... ይህ ደብዳቤ እንደ ደረሳቸው ምኒሊክ አንቶኔን አስጠርተው እንደገና ጠየቁት።
አሁንም ግልፅ ባልሆነ አነጋገር አጭበረበራቸው። እንዲህም አለ << ታዲያ ይህ ምን ክፋት አለበት (17ኛው ክፍል) እኛ የርስዎ አሽከርዎ ፖስተኛ መሆናችን ነው እንጂ።>>... | አለቃ አፅመ ጊዮርጊስ የኦሮሞ ህዝብ ታሪክ (ያልታተመ)|

....... የውሉ ዋና ፀሀፊ ፒዬትሮ አንቶኔሊ ከአፄ ምሊኒክ ከእቴጌ ጣይቱና ከመኳንንቱ ፊት ቀርቦ ይህን የውጫሌ ውል እምቢ ካሉ ጦርነት መነሳቱን እንዲያውቁት ያስፈልጋል ብሎ ሲደነፋ እቴጌ ጣይቱ ደግሞ እጥፍ ጊዜ ቱግ ብለው ተቆጡና፤
" የዛሬ ሳምንት አድርገው። በዚህ የሚደነግጥልህ የለም ሂድ የፎከርክበትን አድርግ። እኛም የመጣውን እናነሰዋለን። እግሩን ለጠጠር ደረቱን ለጦር ሰጥቶ አገሩን የማያድን ሰው በዚህ የሌለ አይምሰልህ።
የገዛ ደሙን ገብሮ ለገዛ አገሩ መሞት ጌጥ ነው እንጂ ሞት አይባልም። አሁንም ሂድ አይምሽብህ የፎከርክበትን በፈቀደህ ጊዜ አድርገው። እኛም እዚህ እንቆይሃለን።.....
እኛ ለራሳችን እንበቃለን የሀገራችንንም ክብር እንጠብቃለን። አንፈራችሁም! በፈቀድነው ጊዜ ከመሬታችን ከሀገራችን ተራራ እንደ ድንጋይ እንፈነቅላችኃለን።" አሉት።

እርሱም ከአዳራሹ ሊወጣ ከሞከረ በኃላ እንደገና መለስ ብሎ
"የምንገጥመውኮ ጦርነት ነው፤ ወንዶቹስ በሆነላቸው እንኳን ሴቲቱ" አላቸው።
"የእኔ ሴትነትና ያንተ ወንድነት የሚለካው እዚያው ጦር ሜዳ ነውና እንዳትቀር።"ብለው መለሱለት።
እንግዲህ የአጭቤው(አጭበርባሪው)አንቶኔሊ አንቶዬ(ስምህን ቄስ ይጥራው አንተ ሰላቢ😀 ለነገሩ....😀😀)
በንቀት እና በወኔ ሙላት የተመላለሱትን ቃለ ምልልስ አይተናል።

የጣይቱን ፉከራ በጦርነቱ ውስጥ በሰራችው ገድል የምናውቀው ነው መቼስ።
ያው ዘመን እየመጣ ዘመን በሄደ ቁጥር እነእቴጌን መሰል ሴቶችን ማጣት የሀገር ህመም ነው። መቼስ ዘንድሮ እንደሆነ ፎክረውና ብልሃት ምሰው ከሚያሸንፉ ይልቅ ቁራጭ ጨርቅ በላያቸው ላይ ለጥፈው ወንዱን እያፈዘዙ አንዴ ከቆመ ዛፍና መኪና ጋር እያጋጩ አንዴ ቦይ ውስጥ እየከተቱ ሆኗል ብልሃቱ። (ቱ ደሞኮ እኛኑ ነው 😂)
እኔስ ስንቴ ነው አንገቴን እስኪያመኝ እየሾፍኩ ቆሎ በትኜ ጣቢያ ያደርኩት 😀 " መገን" አለ ወሎ።

የአንቶኔሊን ንቀት ታክል በዘመኔ ላይ መማረር ቢኖርብኝም ይሁን ይመቻቸው ብያለሁ።
የዚህችን ክፍል መዝጊያ ከመፅሀፉ ውስጥ ባገኘዋት ፈገግ በምታስብል ገጠመኝ ልዝጋና በቀጣዩ ቀን በሌላ ክፍል ልመለስ....

...... አንቶኔሊ ከስብሰባው ሲወጣ ምኒልክ ለጋሲዮን ድረስ የሚሄድበት በቅሎ ስጡት ብለው ተሰጠው። አንቶኔሊ በቅሎ ለሰጠው አሽከር አንድ መቶ ብር ሰጠ።
አሽከሩም የተሰጠውን ብር ይዞ አዳራሽ ገብቶ ለምኒልክ ነገረ።
ራስ መኮንን ነበሩና " ጉርሻ ከሆነ ይበዛል። ጃንሆይ ለሰጡት በቅሎ ከሆነም ያንሳልና ይመለስ!" አሉ። ምኒልክም ስቀው ለአሽከሩ "ጉርሻ ነውና ውሰደው" አሉት።

........... ዛሬ የአድዋን ድል መዳረሻ ቀናት አስመልክቼ በቅንጭብ ያቀረብኩት ክፍል ይህን ይመስላል በቀጣይ አንዳንድ የጦርነቱን ነጥቦች እናያለን ሀሳብ አስታየታችሁን ፃፉልኝ።
የተሳሳትኩትም ካለ አርሙኝ ያጠፋሁትም ካለ ይቅርታ እጠይቃለሁ።🙏

ለዚህ ፅሁፌ በዋነኝነት ኃብረ ኢትዮጵያ በሚል ርዕስ በ2008 ዓ.ም በቴዎድሮስ በየነ የታተመውን ቅፅ አንድን ተጠቅሜያለሁ።
ቸር ቆይታ!!!
- ለማድብን እጅጉ ( ቃሲም )
- ለበፍቃዱ አረጋ
#እና
- ለቃለአብ ሲሳይ (ናታኒም)
ምስጋናዬ ይድረስልኝ
©
#ሲራክ ወንድሙ @siraaq
@wegoch
@wegoch
#ወግ_ብቻ
.
አድዋ እና ሰበቡ
©በሲራክ ወንድሙ
ክፍል ፪
አድዋና ሰበቡ በሚል ርዕስ ለአድዋ በዓል መዳረሻ የምናወጋት ወግ እና ጥቁምታ ዛሬም ቀጥለናል። በዚህ ክፍል ስለ ታላቁ የአድዋ ጦርነት አዋጅና የጦርነቱን ሁነት አጠር መጠን አድርገን እናይ ዘንድ ወድጃለሁ።

እንደቀደመው ክፍል ይህንንም ክፍል ለማሰናዳት ህብረ ኢትዮጵያ ቅፅ ፩ በሚል ርዕስ በቴዎድሮስ በየነ በ2008 ዓ.ም የታተመውን የታሪክ መፅሀፍ አገላብጫለሁ።
የአፄ ምሊኒክ አድዋ ጦርነት የክተት አዋጅ የሚለውን መንደርደሪያ አድርገን እንሻገር።

አዋጁ እንዲህ የሚል ነበር።
" አዋጅ አዋጅ የደበሎ ቅዳጅ
የሰማህ ላልሰማ አሰማ
እግዚአብሔር በቸርነቱ እስካሁን ጠላት አጥፍቶ አገር አስፍቶ አኖረኝ።
እኔም እስካሁን በእግዚአብሔር ቸርነት ገዛሁ። እንግዲህ ብሞትም ሞት የሁሉ ነውና ስለኔ ሞት አላዝንም። ደግሞ እግዚአብሔር አሳፍሮኝ አያውቅም።
እንግዲህም ያሳፍረኛል ብዬ አልጠራጠርም።
አሁን አገር የሚያጠፋ ሃይማኖት የሚለውጥ ጠላት በእግዚአብሔር የወሰነልንን የባህር በር አልፎ መጥቷልና እኔም ያገሬን ከብት ማለቅ የሰውን መድከም አይቼ እስካሁን ዝም ብለው ደግሞ እያለፈ እንደ ፍልፈል መሬት ይቆፍር ጀምር።
አሁን ግን በእግዚአብሔር ረዳትነት አገሬን አሳልፌ አልሰጠውም። ያገሬ ሰው ፤ ካሁን ቀደም የበደልሁህ አይመስለኝም። አንተም እስካሁን አላስቀየምከኝም። ጉልበት ያለህ በጉልበትህ እርዳኝ። ጉልበት የሌለህ ለልጅ ለምሽትህ ለሀይማኖትህ ስትል በሀዘን እርዳኝ።
ወስልተህ የቀረህ
#እንደሁ ግን ትጣላኛለህ።
አልተውህም። ማሪያምን ለዚህ አማላጅ የለኝም።
ዘመቻዬ በጥቅምት እኩሌታ ነውና የሸዋ ሰው እስከ ጥቅምት እኩሌታ ድረስ ወረኢሉ ከተህ ላግኝህ።"

|መስከረም 7 ቀን 1888 ዓ.ም
#ሸዋ አዲስ አበባ|
(የአዋጁ ፅሁፍ ምንጭ ገብረ ስላሴ ወልደ አረጋይ ታሪክ ዘመን ዘዳግማዊ ምኒልክ ገፅ 225......)
እንዲህ በሚል አይረሴ የአዋጅ ጥሪ ህዝቡ አብሮ ድሉን እንዲቀዳጁ ጋበዙ።

በዚህ የአዋጅ ጥሪ ውስጥ እምዬ ምሊኒክ የመንፈስ ጥንካሬያቸው ፣ በአምላካቸው ላይ ስላላቸውና ስለነበረባቸው ጥብቅ ቁርኝትና የመንፈስ ቅርበት እንዲሁም ከሚመሩት ህዝብ ጋር ስላላቸውና ስለነበራቸው ግንኙነት እንዲሁም መተማመን ሲያወጉ ድሉ የራሳቸው እንደሆነ ግን ድሉ የሚመጣው በመተባበርና በአንድነት እንደሆነ ሲያትቱ እንሰማለን።

ከዚህም በተጨማሪ ዛሬ በኛ ዘመን የት ገዳም እንደመነነ ፣ የት መሬት እንደተቀበረ ወይም የት እንደተሰወረ የማናውቀው ኢትዮጵያዊ ጨዋነት የተላበሰ አዋጅ ነበር። ልብ ይሞላል ነብስ ከፍ ያደርጋል።

የሆነው ሆነና እንደጥቁምታ ያ የተሰወረብን ጨዋነትን ስታገኙ ለምንዱባን ሳንቲም መወርወር እንደማይወድ ስስታም ባለፀጋ አትለፉት!። ያዙ!!
ምናልባት ካለብን የስብዕና እና የብልሹ ባህሪ ችግራችን ያወጣናል።
ያው ሞኝ እየመሰለን ስለምናልፈው ነው።

ለማንኛውም ወደ ቀጣዩ ስንለጥቅ በቅንፍ ውስጥ ስናልፍ ለማለት ነው። ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ጥቅምት 2 ቀን 1888 ዓ.ም ሰራዊታቸውን አስከትለው ወደ አድዋ ለመዝመት ከአዲስ አበባ ጉዞ ጀመሩ።

ወደ አድዋ የዘመተው የኢትዮጵያ ወገን የጦር ቁጥር ጥቂት አከራካሪ ቢሆንም
#ኤጭ የሚያስብል ደረጃ አልደረሰም።
እስኪ ከግምቱ ጥቂት እንቅመስ፦
ቶኪ የተባለው ፀሀፊ የኢትዮጵያ ወታደር 70.000 - 80.000 ይደርሳል ሲል አንቶኔሊ ደግሞ ከ110.000 - 120.000 ነው ይላል። ባራቴሪ እንዳለው ደግሞ ከ75.000 - 80.000 ይደርሳል ብሏል።ኢልግ ፣ ዌልብ እና ካፒቴን ክሎሼት የተባሉ የታሪክ ፀሀፊዎችም እንዲሁ የእውቀታቸውን ግምት ወርውረዋል።

.... ጦርነቱ እንደታወቀና የክተት አዋጁ ከታወጀ በኃላ የጎጃም ፣ የጎንደር ፣ የወሎና የላስታው ከ300 - 500 ኪ.ሜ ያህል የሀረር ፣ የባሌ ፣ የአርሲ ፣ የከምባታ ፣ የሲዳማ ፣ የጅማ ፣ የከፋ ፣ የወለጋና ፣ የኢሉባቡር ጦር ከ 1000 - 1500 ኪ.ሜ ድረስ ያለውን አገር አቋርጦ ተጉዟል። (በነገራችን ላይ የተነሳው ሰራዊት ሁሉ ከጦርነቱ ቦታ አልደረሰም። ሰራዊቱ በከፊል ገና ጉዞ ላይ እንዳለ ጦርነቱ ተጠናቆ እንደነበረ ኢልግ የተባለ የታሪክ ፀሀፊ ይናገራል።)

...አጭር ሱሪና ጥብቆ ለብሶ በዚያ ላይ ነጠላውን ደርቧል።
የሚራመደው በባዶ እግሩ ከድንጋይና ከእንጨት እንቅፋት ጋር እየታገለ ውስጥ እግሩን እሾህ ...በሙቀት ጊዜ ረጫሞ እያቆሰለው ፤ ለራሱም ቆብ ስለሌለው የፀሀይ ሀሩር ...የሌሊት ቁር ይፈራረቁበት ነበር።

ቢታመም ያገር ባህል መድሃኒት ከመጠቀም በቀር ደንበኛ ህክምናም አያገኝም ነበር።
በጉዞ ላይ እያለም ራሱ የባህሉን መድሃኒት እንደልብ ማግኘት ይቸግራል እንደነበር ይነገራል።
.....ጦርነቱ የአፍሪካ የነፃነት እንቁ የጥቁር ህዝቦች የተስፋ ምድርና የጀግኖች እናት በተባለችው የእምዬ ምኒልክ ሀገር የሆነችው እምዬ ኢትዮጵያ አሸናፊነት በታላቅ ድል ተጠናቀቀ።
አንድ ቀን ብቻ የፈጀው ይህ ጦርነት የተካሄደው አድዋ (ትግራይ ውስጥ ) በእለተ እሁድ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም ነበር።

የታላቁ የአድዋ ጦርነት ለሉአላዊነቷና ለነፃነቷ በተከፈለ የደምና የአጥንት መሰዋዕትነት በዚህ መንገድ ተጠናቀቀ።
አድዋ የእልፍ የአውሮፓ ጎልያዶችን እብሪት አፈር ዲሜ ያበላ ጠጠር ነው። ( ጠጠር ስል ተምሳሌቱን ለማጉላትና ጨዋታውን ለማድራት እንጂ ድሉን ለማሳነስ የተጠቀምኩት ቃል እንዳልሆነ ይታሰብልኝ 🙏)
መላው የአውሮፓ ጎልያዶችን አንገታቸውን የደፉበት እጃቸውን በአፋቸው ያስጫነ ታላቅ ድል ነው።

እኛ አይመስለንም እንጂ ድፍን አፍሪካን ያነቃቃ የጥሪ ደወልም ነበር።
ኑ ቤቴ ግቡ አጥንቴን ጋጡ ደሜንም ጠጡ እናንተን አንችልም ንገሱብን ባሉ ለአፍሪካ ሀገሮች ንጉሳቸው እንደሚከሰስ ሀይሉ እንደሚረታ የተረዱበት ችቦና ደመራ ነው አድዋ።

አድዋ እልፍ ነው። ነጥቡ አንድ ብቻ አይደለም።
በእርግጥ ድል አድርጎ ድሉን ለናቀው የኛን መሳይ ትውልድ አድዋ ምንም ነው።
የካቲት ሀያ ሶስትን ጠብቆ ባንዲራ ለብሶና ፎቶ ተነስቶ አድዋ አድዋ ከማለት በቀር እያንዳንዱ ሰው ለነገይቱ ኢትዮጵያ አቅሙ በፈቀደ መርዳት ፣ ማሰብና መታተር አይደለም ተስፋው።
እንደገና የካቲትን መጠበቅ ነው። እጣችን!
የአያቱን "መቃብር ቆፋሪ" እንደምትለዋ ወግ!

አድዋ ረቂቅ ነው ያኔ ሆነን ዛሬን ማየት ቢቻለን አድዋ ለኛ ባልተገባ ነበር።
እኔ በግሌ ለአድዋ የተከፈለውን መሰዋዕትነትና ሀገር ማዳን ሳስብ ዛሬ በፍቃደኝነት ራሱን ለአውሮፓ የሚያንበረክክ እና የሚያስገዛ ትውልድ እያለ ያ ሁሉ ዋጋ መክፈል ለምን እላለሁ።
ዛሬ ፊታችን ቢቆሙ መልሳችን ምንድነው?
የቀረው ቢቀር ፍቅር ይሉት መንፈስ ባጣ ዘመን የጣዲቄ ህመም ያመኛል።

የቀረው ቢቀር እምዬ ምኒልክ ከጦር ከመሪዎቻቸው መካከል ከፈረሱ ላይ ገበየሁን ባጡ ጊዜ ያለቀሱት እምባ የታመሙት ህመም ያመኛል።
የቀረው ቢቀር ቀድሞ ቀድሞ ኃላ የቀረው ትውልድ ስልጣኔ ባለው ስይጣኔ ፣ እውቀት ባለው ድድብና ሲኮራ ያመኛል።
የቀረው ቢቀር....!
.......
የቀረው ይቅርና ይህን መፅሀፍ ሳነብ እምባ ካስቀረሩኝ ፣ ቅንነት እና እዝነትን ካስጨበጡኝ ነጥቦች አንዱን ላንሳና በጥቁምታ ልሰነባበት።
@wegoch
@wegoch
@siraaq
👇👇👇
ይቀጥላል
☝️☝️
.... የቀጠለ
...በመጋቢት 23 ቀን 1888 ዓ.ም እምዬ ምኒልክ ለሙሴ ሽፍኔ የፃፉትን ደብዳቤ እንመልከት። እንዲህ ይላል። " በጥጋባቸው አድዋ ላይ ተዋግተው ድል ሆኑ። እኔ ግን በድንቁርነታቸው ብዛት የነዚያን ሁሉ ክርስቲያን ደም በከንቱ መፍሰሱን እያየሁ ድል አደረኳቸው ብዬ ደስም አይለኝም።"አሉ።
እምዬ ሰው የመሆን ጥግ ኢትዮጵያ የመሆን ውሃ ልክ ናቸው።

ምናልባት በኔ እሳቤ ኢትዮጵያ መሪ ያጣችው ከሳቸው በኃላ እንደሆነ ይሰማኛል።
በመሪ ስም እንደ እረኛ ከኃላ ሆነው ነድተው ነድተው ሀገሪቷን የት እንደከተቱ ለማስረዳት መነሳት ለቀባሪ ማርዳት ነው።

መቼስ አምላክ ተማፅኖዋን ሰምቶ እርስ በእርስ ድል አይሉት ውርደት እየደጋገምን ራሳችንን ከማቆሸሽና የድግግሞሽ ጦስ አውጥቶ የሚነዳ ሳይሆን የሚመራ መሪ ይስጣት እላለሁ።ደሞ አሜን በሉ ( ከፈለጋችሁ አትበሉ እናንተ ባትሉ እኔ እላለሁ)

..... ዛሬ አድዋና ሰበቡ ፪ በሚል ርዕስ ያዘጋጀውትን ፅሁፍ እንዲህ አየነው።
በቀጠሉት ቀናቶች ውስጥ ስለ አንዳንድ የአድዋ ጀግኖች ፣ በጥቂቱ እናነሳለን በተለይ በተለይ በግሌ በጣም ስለሚገርሙኝ አዝማሪዎች ከእዛም ከዚህም በቃረምኩት የንባብ እና የማድመጥ ቃሬሚያ በመነሳት አንዳንድ ነገር ልል እችላለሁ።
የአብዬ ፀጋዬን ግጥም ጨምሮም በተለያዩ ፀሀፊያን የተፃፉ ግጥሞችን እና ሙዚቃዎችን(የጂጂንም አድዋ) እያነበብን ፤ እያደመጥን እንዘካከራለን።

ይህን ሁሉ ብዬ ወስልታችሁ ፅሁፌን ያላነበባችሁ እንደሁ ውጊያዬ በቃል ነው።😀
በተረፈ ሀሳብ አስታየታችሁን ፃፉልኝ።
የተሳሳትኩትም ካለ አርሙኝ ያጠፋሁትም ካለ ይቅርታ እጠይቃለሁ።🙏

ለዚህ ፅሁፌ በዋነኝነት ኃብረ ኢትዮጵያ በሚል ርዕስ በ2008 ዓ.ም በቴዎድሮስ በየነ የታተመውን ቅፅ አንድን ተጠቅሜያለሁ።
ቸር ቆይታ!!!
©ሲራክ ወንድሙ
@siraaq
ለወንድሜ ማድብን እጅጉ (ቃሲም ) ምስጋናዬ ይድረስልኝ!🙏
@wegoch
@wegoch
@wegoch
EMINƎM

Had a dream i was king, i woke up still king!
ሲጨንቀኝ ተስፋ መቁረጥን ስገፋ መውደቅን ስከፋ ማልቀስን
አላስተማርከኝም።
ሳላውቅህ ሳላገኝህ አንስቶ ህልሜን አምነዋለሁ። ገና ፈላ እያለሁ ነው።
ትምህርት ቤት ውስጥ ዞር ብዬ አይቻት የማላውቅ ቢጫ ልጅ በህልሜ
መጣች አመለጠኝ አፈቀርኳት ቀልድ እንዳልያዝኩ የገባኝ እስካድግ
ሊለቀኝ አለመቻሉን ሳይ ነበር። 7ዓመት ቆይቼ ስፈራት የኖርኳትን ልጅ
ስካር አጀግኖኝ ነገርኳት። ተሳቀብኝ ሁላ። በዛ ዕድሜ ያለ ወጠጤ
ሊሰማው እንደሚችለው ተሰማኝ። እንደማልወደድ አመንኩ። ቀድሞም
"ደስ ሲል" ያለኝ አልነበረም። የገባኝ መሰለኝ ልፈቀር እንደማልችል
ተሰማኝ። ደደብኩ። ጨለማ ውስጥ መቀመጥ በሬን ዘግቼ መዋል ሰው
አለማግኘት ጀመርኩ። ስልኬን ሸሸሁት። መፃህፍትና የያዟቸውን የፍቅር
ታሪኮች እደበቃቸው ጀመር። የስብሐትን "ወጣት ነህ" መርህ እንኳ
አፈርኩበት።
ከቀናት በሁዋላ ወደቀልቤ መመለስ ስጀምር አደመጥኩህ። የሆንኩትን
ቀድመህ አውቀኸዋል። አረጋጋኸኝ። ሰቅለዋት እንጂ ወርደህ አይደለም
አልኸኝ
"They say the competition is stiff
But I get a hard dick from this shit, now stick it in"
"ትፈቀራለህ ትወደዳለህ የምናባህ Inferiority complex ነው።" "የምን
ጡቴን ተቆረጥኩ ቁላዬን ተሰለብኩ ብሎ ማለቃቀስ ነው። መጀመሪያ
መብራቱን አብራው" ስትለኝ ረጅም ጊዜ ጨለማ ውስጥ እንደሰነበትኩ
አወቅኩ። ለአባቴ ስል እንኳ ብርሐን ለማየት ያልፈቀድኩ እኔ ለራሴ ስል
አበራሁት።
"But don't let 'em say you ain't beautiful oh
They can all get fucked. Just stay true to you"
ከራሴ ፍቅር ያዘኝ። የማልወደድ እኔን አስወገድኩ። አዲስ እኔን ሰራሁ።
ያስተማርከኝ ይወዱሃልን አይደለም 'የማይወዱህ ይበዱ'ን ነው። 'አንተ
ለራስህ በቂ ነህ'ን ነው። ያኔ ነው ለመጀመሪያ ጊዜ ፍቅር እስከመቃብር
ላይ እንዳለችው ውድነሽ በጣሙ ራሴን በመስታወት አይቼ "አፈቅረኛለሁ"
ያልኩት። አባቴ ይሙት ከዚያ አንስቶ ለመኖር ብቻ እኖራለሁ እንጂ
ለመወደድ አልኖርኩም።
ራሴን አልፌ ማየት ስጀምር በወጠጤ ጉልበቴ ባልጠና ጡንቻዬ
መንግስት የሚባል የደደቦች ስብስብን ልቃወም አሰኘኝ። የምርጫ
ምልክት እየዞርኩ መገንጠል የኮሚዩኒቲ ፖሊሲንግ የምሽት ተረኞች በር
ስር ኢህአዴግ ይበዳ አታሸንፉም የሚል ወረቀት ማስቀመጥ ጀመርኩ።
ጓደኞቼ አብረውኝ ነበሩ። ከብዙ ጣጣ በሁዋላ ልንቀላቀላቸው ያሰብናቸው
ድውያን ከምጠላው መንግስት በምንም እንደማይለዩ ተረዳሁ። አቋረጥኩ።
አመለጠኝ። ጓደኛዬ አምልጦኝ ሄደ። ያዙት። አሰሩት። ሃገር ምድሩ ባንተ
ጦስ ነው አለኝ። "ደደብ ነህ ክፉ ነህ ከሃዲነህ" አሉኝ። አስራሁለት እንኳን
ያልተፈተንኩ ግልፍተኛ ብቻ ነበርኩ። ይሄ እንደሚመጣ እንኳ አላሰብኩም።
ለቅሶ በረከተብኝ። ያየሁትን አላዩም የጓደኛዬን ጀርባ እያየሁ
የምሰቃያቸውን ሌሊቶች አያውቁም። ሁሉም ወረደብኝ። በድጋሚ አመንኩ።
ጥፋተኛ ነኝ አልኩ። ከነበርኩበት ገጠር ስመለስ ከተማው በሙሉ የአስራ
ስምንት ዓመት እኔ ላይ አብሮ ጠበቀኝ። እንባዬ ለራሴ ያቃጥለኝ ነበር።
በፍፁም ፍቅር የሚወደኝ ወንድሜ የጠራኝን ልደት እሱ እንኳን እያለቀሰ
አካልበው አስወጡኝ። አሁን ደግሜ አላለቀስኩም። ዓለም ቢተወኝ
የማትተወኝ አንተ እንዳለህ አውቃለሁ። አይስቅም ይሉሃል እየሳቅክ
ተቀበልከኝ። በሬን ዘጋሁ። መብራቴን አጠፋሁ። በጆሮዬ ተጠግተህ
ትንፋሽህን ሁላ እስክሰማው በፍፁም እልህ እኒህን ሁሉ አልክልኝ።
It's a little too late to say that you're sorry now
You kicked me when I was down
But what you say just (don' hurt me)
That's right bitch
And I don't need you (no more)
Don't wanna see you
Ha, bitch you get (NO LOVE)
You showed me nothing but hate
You ran me into the ground
But what comes around goes around
I don't need you (no more)
ልክ ነህ'ኮ ግን ግን ቢሆንም ቢሆንም ብቻዬን ነኝ አልኩህ "አንተ ደደብ
ላንተ መሰለኝ የማወራው" አልኸኝ።
"I ain't never giving in again
Caution to the wind, complete freedom
Look at these rappers, how I treat them
So why the fuck would I join 'em when I beat 'em"
ቀጥሎ ምን ይባላል። "አሜን ነው" እያልኩ መኖር ጀመርኩ። ሁሌም
ለጥያቄዎቼ መልስ አንተ ጋር አለ። ለህመሜ ፈውስ አጥተህለት
አታውቅም። "ኢየሱስን ተቀበል" ለሚሉኝ ሁሉ አፌን ሞልቼ
"ይሄው የኔ ኢየሱስ ማን ነው የእስራቴን ገመድ የበጠሰው ማን ነው
ያዳነኝ Eminem አይደለም ወይ እላቸዋለሁ" ሁሌም ባንተ ብርቱ ነኝ
ጌታዬ።
የተወደዳችሁ ቅዱሳን if Eminem's songs can't help you to move
on sorry no one can
ሰብዕናዬን በጭብጨባና ጋጋታ ላይ እንዳልመሰርት ሆኜ ተሰርቼበታለሁ።
እኔ እስካለሁ የእኔ ንግስናም ሆነ አምላክነት ይቀጥላል። Eminem ይባረክ
Be king think not why be a king when you can be a god!

©ክቡር ሰይጣን 🖤🖤🖤

@Mahletzerihun
@wegoch
@wegoch
የትዳር አጋራችንን እግዜር ነው የሚሰጠን ብላችሁ የምታምኑ ሰዎች .... እስኪ አንዴ ጠጋ በሉ! የምራችሁን ነው?

እግዜር ለአዳም ሄዋንን የሰጣትኮ ሴት በምድር ስላልነበረ ነው!

ምድር በሰው ዘር ከሁለቱም ወገን ተሞልታ ራስሽን ፈልገሽ አጊንተሽ የሚስማማሽን ባል ፈልገሽ የምትመርጪበት ማሰቢያ እና ልብ ሰጥቶሽ .... አሁን ቤተሰብ እንኳን ለልጁ ሚስት ወይ ባል በማያጭበት ዘመን እግዜርን ማስቸገር አግባብ ነው?

እኔ የምሬን ነው እሺ አግብተሽ ... ተፋታሽ ... ከዛ እግዜር ሰጠ እግዜር ነሳ ልትዪ ነው ወይስ የሰይጣን ስጦታ ነበር ልትዪ?

አንተኛው ራሱ አስር ገርል ፍሬንድ ጠብሰህ እግዜርን ራሱ አምታተኸው ስታበቃ .... አስራ አንደኛዋን እግዜር ሰጠኝ ልትል ነው? (አስሮቹ ሳምፕል ናቸው?😜)

ስናገባ 'እግዜር ነው የሰጠኝ' ስንጣላ 'ይሄ የተረገመ ሰይጣን!!' (ሰይጣን ራሱ እኮ ግራ ገባው)

እስኪ እቤታችሁ ቁጭ በሉና ሄዋን አንኳክታ ትመጣ ከሆነ ጠብቁ.... ድህነት ብቻ ነው የሚያንኳኳባችሁ!!

አንቺም ወንድ በደረሰበት አትድረሺና 'ባሌ በመኪና ይምጣ' 🤪ብለሽ ፀልዪ እስኪ .... ተው እንጂ ....

ደሞ አንዳንዶች አለን እንጂ "እገሌን የእኔ ካደረግክልኝ!" ብለን የምንፀልይ ... ከዛ ደግሞ በአመቱ ሌላ እገሌ .... ፈጣሪ ራሱ ዝርዝሩ ብዝት ብሎበት .... ለፈርኦን እንዳለው 'ኸረ ህዝቤን ልቀቂ!' ነው የሚለው !!

አታፍሩምኮ ንጉስ ሰለሞንን በ700 ሚስቶች እና በ300 እቁባቶች ጌታ ነው የባረከው ትሉኝ ይሆናል😜😜😜

ከሆነ በጊዜ ንገሩኝ እስኪ ... በቀረው የእርጅና ዘመኔ አንድ አስሩን ላደራጃቸውና ተስማምተው በፍቅር እንዲያስተዳድሩኝ ፆም ፀሎት ልግባ 🤣🤣🤣🤣

እህህ የምር እረፉኣ? ስለ ሚስት ራሱ 700 ሚስትና 300 እቁባት የነበሩት ጠቢቡ ሰለሞን ያለውን ጥቅስ እየጠቀሳችሁ ..... ብልህ ሚስት ... አስተዋይ ሚስት....

ከ1000 ውስጥ የትኛዋ ነበረች አስተዋይዋ? በስማቸውስ ያውቃቸው ይሆን እንኳን በስብእናቸው?

ንግስተ ሳባ ናታ በሉ ደሞ ...

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Meri feleke
«በሕጋዊ መንገድ ሰው መግደያ ዘዴ» - ሥጦታ?!

* * * *
ከጥቂት ቀናት በፊት ጓደኛዬ ቤት ሄጄ በካርቶን የታሸገ ኩኪስ ውሰድ አለኝ።
«ለምንድነው የምትሰጠኝ?» አልኩት። ተግባብተናል፣ በነጋታው ለሳምንት ከከተማ ይወጣል። «ስለማልኖር ይበላሻል» አለና ሐቋን ተናገረ። ሰማንያ ምናምኑም ብሔሮች በየቋንቋቸው "የሥጦታ ፈረስ ጥርሱ አይታይም" እያሉ ነግረው ነው ያሳደጉን። ለምን? እንዴት? ምናምን አንልም፣ መቀበል አለብን ነው መሠለኝ 路♂ ባለፈው አንድ ሀኪም ወዳጄ ነፃ ምርመራ ላርግልህ ሲለኝ ያወራነው ነገር ነው ይሄንን ያስታወሰኝ። እምቢ አልኩ። ለምን? እኔንጃ፣ "አለብህ" የሚለኝን ነገር እያሰብኩ መሰለኝ። ናሲም ታለብ የተባለው ፀሀፊ "በሕጋዊ መንገድ ሰው መግደያ ዘዴ አለ!" ይላል። ይሄን ዘዴው ሲያብራራው እንዲህ ይላል፣ በግርድፉ . . . የሆነን ሰው ሞት ማፋጠን ከፈለግክ የግል ዶክተር ስጠው። መጥፎ ዶክተር ስጠው እያልኩህ አይደለም፣ እሱ የፈለገውን ዶክተር ይምረጥ፤ አንተ ገንዘቡን ክፈልለት። የትኛውም ዶክተር ይሆናል። ምናልባት የቱንም ሕግ ሳትጥስ ግድያ መፈፀም የምትችለው በዚህ መልኩ ነው። ስለጤናህ ዳታ/መረጃ ሲኖርህ ሕክምና ትጨምራለህ፣ መታከም አለብኝ ትላለህ። እንደ neurotic ሰው ያደርግሀል። የግል ዶክተርህም ምንም ሳይሰራ ደሞዝ እንደተቀበለ እንዲሰማው አይፈልግም። ስለዚህ የሚያይብህን ጥቃቅንና tolerable ሕመሞች ሁሉ ይነግርሀል። አንተም የሆነ ህመም እንዳለብህ እያወቅክ ዝም አትልም። መድሀኒት ትፈልጋለህ። (የማይክል ጃክሰን ዶክተር በተመሳሳይ ጥፋት መከሰሱን ይጠቅሳል) በጣም የተራቀቀ ሕክምና ማግኘት የሚችሉ ሀብታሞችና የሀገር መሪዎች ለምን እንደተራው ሰው በቀላሉ እንደሚሞቱ አስበህ ታውቃለህ? ከሁኔታቸው እንደምናየው ከበዛ የሕክምና ድጋፍና ከበዛ የመድሀኒት አጠቃቀም ነው የሚሆነው።' የተራቀቀ የዳታ መሰብሰቢያ ክፍል ያላቸው ፖሊሲ አርቃቂዎቻችንም ተመሳሳይ ችግር ይፈጥራሉ ይላል ታለብ፤ የሚሰሟትን ድምፅ እንደ መረጃ እየቆጠሩ ያልተገባ ምላሽ በመስጠት ቀውስ ውስጥ ይከቱናል። የዳታ ዘመን ነው፣ በብዛት ይገኛል። ነገር ግን ዳታ ሲበዛ መርዛማ መሆኑ አይወራም። ዳታ ላይ ያለን አተያይ ወሳኝ ነው ይለናል። ዳታዎችን በየቀኑ ስናይ የሚያስደነግጠን፣ ለምላሽና ለውሳኔ የሚያስነሳን ነገር ብዙ ነው። ይሄንን ተመሳሳይ ዳታ ተጠራቅሞ በዓመት አንዴ ብናይ ግን ተመሳሳይ ኹኔታ ውስጥ አንገኝም። የፌስቡክ አጀንዳ፣ የመንግሥት አማካሪዎች፣ የመንግሥት ውሳኔዎች ወዘተ በጩኸት ላይ የተመሰረቱ ናቸው። ዛሬ የሆነ ነገር ተፈፀመ ይባላል። ያቺን የዕለት ዜና ወይም ዳታ ይዘን እርምጃ እንዲወሰድ፣ የሆነ ነገር እንዲደረግ እንጮሀለን። ነገ ሌላ ነገር እንሰማለን፣ የዚያኔ ደግሞ ሌላ እርምጃ እንዲወሰድ እንጮሃለን። ጩኸት በጩኸት ነው። ቆም ብለን ባለፈው ዓመት ወይ ሁለት ዓመት የጮህንባቸውን አንድ ሺህ አጀንዳዎች ስናስብ ግን አብዛኞቹን ረስተናቸዋል። ወጥ በሆነ መልኩ አድጓል፣ አሽቆልቁሏል፣ እስካሁን አለ ወዘተ ብለን ልንናገርላቸው የምንችላቸው ነገሮች በጣም ጥቂት ናቸው። ነገር ግን ሺሆቹንም ጩኸቶች ሰምቶ በረባ ባልረባው የፖሊሲ ሀሳብ ያቀረበ አማካሪና ውሳኔ ሰጪም እንዳለ ከተፈጠሩትና ከሆኑት ነገሮች መረዳት እንችላለን። ይህ ኹኔታ ከሥነ-ሕይወታዊ (ባዮሎጂካል) እኛነታችን ጋር ማያያዝ እንችላለን። ብዙ መረጃ ብዙ ጭንቀት ውስጥ ይከታል። የቅርብ ጊዜ የሕክምና ጥናቶች የፆምን የጤና ጥቅም በሰፊው ሲገልፁ አይተናል። ሆርሞኖች በብዛት የሚመነጩት ምግብ ሲወሰድ ነው። ሆርሞኖች ወደተለያዩ የሰውነታችን ሥርዓቶች መረጃ ያደርሳሉ፣ ሲበዙ ሰውነታችንን ግራ ያጋቡታል። ብዙ ዜና እኛን ግራ እንደሚያጋባን ነው ብዙ ሆርሞንም ሰውነታችንን ግራ የማጋባት ሥራ ይሰራል። ሚዲያውም ያበደ ነው። የጠራና የነጠረ ጠቃሚ መረጃ ሳይሆን በየቀኑ ሰዓታቸውን እና ገፃቸውን የሚሞላ ጩኸት ነው የሚለቁብን። በየቀኑ በሀገራችን 1000 ሰዎች ተገቢውን ቀላል ሕክምና ማግኘት ባለመቻላቸው፣ ወይም በረሃብ፣ ወይም ደግሞ በሌላ መንግሥትና ሕዝቡ ትንሽ ጥረት አድርገው ሊያስቀሯቸው በሚችሏቸው ተራ ምክንያቶች ይሞታሉ እንበል። ሚዲያዎቻችን የሚነግሩን ግን ስለ አንድ ሺሁ ሞት ሳይሆን ስለ ሁለት ለየት ባለ ሁኔታ ስለሞቱ ወይም ስለተገደሉ ሰዎች ነው። የየዕለት ጩኸት ነው የሚሰጡን። የሚያስደነግጡንና በቀላሉ ኡኡ የሚያስብሉንን ሁለት አሰቃቂ ግድያዎች ወይም ኹነቶች ነው የሚተርኩልን።
* * * *

አንድ የሕግ ድራማ/ፊልም ላይ ያየሁት ታሪክ ጭብጥ ከዚሁ ይያያዛል፣ ትልልቆቹን የመድኃኒት አምራች ኩባንያዎች "ሕመም ሻጮች" ናቸው ይላቸዋል። የገፀባህሪውን አገላለፅ ወደፌስቡክ ከሞላ ጎደል ወደፌስቡክ እንዲህ ላውርደው . . .
«እረፍት አልባ የእግር ልክፍት» ሲባል ሰምታችሁ ታውቃላችሁ? ቁጭ ብላችሁ
ወይም ተኝታችሁ በእንቅልፍ ልባችሁ እግራችሁን የሚያስነቀንቅ ልክፍት ነው። ከእንቅልፍ አያነቃም ወይም አያደክምም፣ ጉዳትም የለውም። እንደችግር አይታችሁትም አታውቁ ይሆናል። ነገር ግን የመድሃኒት አምራች ኩባንያዎች በጣም ከባድ ህመም እንደሆነ ይነግሯችኋል። መድኃኒት ሰርተውለታል። ችግሩ ካለባችሁ እሱን መውሰድ አለባችሁ። ስለዚህ ልክፍት ሰምታችሁ የማታውቁ ከሆነ ምናልባት «የትኩረት ማጣት ቀውስ» ችግር ሰለባ ሆናችኋል። የትኩረት ማጣት ቀውስ አሳሳቢ ችግር ቢሆንም ለሱም መድኃኒት ሰርተውለታል። መውሰድ አለባችሁ። «feeling depressed» ብላችሁ ትለጥፋላችሁ። ምናልባት በዚህ ሌሊት ይሄንን ረዘም ያለ ጽሁፍ እያነበባችሁ ነው። የእንቅልፍ ማጣት ችግር አለባችሁ
ማለት ነው። ምናልባት ያልተኛችሁት ቀን የበላችሁት ምግብ ሆዳችሁን አሳምሟችሁ ይሆናል። የሆድ ቁርጠት መድሃኒት አለላችሁ። እዚህ ፌስቡክ ላይ የተለያየ ደፋርና ገራሚ ጽሁፎች ፖስት ታደርጋላችሁ፣ ነገር ግን ከሰው ስትቀላቀሉ የሚያስደነግጥ፣ የሚያስሸሽ የsocial anxiety ችግር አለባችሁ። መድሀኒት አለው። በአጠቃላይ ሁላችሁም የማታውቁት ብዙ ዓይነት ሕመም አለባችሁ! አያሳስብም
እንደዕድል ሆኖ ለሁሉም ሕመሞች መድሐኒት አለ!! መውሰድ አለባችሁ!!
* * * *
ሁላችንም የምናውቀውና የማናውቀው በሽታ አለብን። ፌስቡክ የሚባል ነፃ ሕክምና ስናገኝ ለሁሉም ሕመማችን መፍትሔ ለማግኘት የተለያዩ ነገሮች
እናደርጋለን። ያደረግናቸው ነገሮች፣ የወሰድናቸው መድኃኒቶች ደግሞ ብዙ ነገር አሳጥተውናል። ጭንቀት፣ ጥል፣ መከፋት፣ ማፈር፣ ጓደኛ ማጣት፣ መጥላት/ መጠላት፣ ወዘተ አትርፎልናል።
ደግሞ . . . ለሁሉም በሽታዎቻችን መድኃኒት አለ። ፖለቲከኞችና አክቲቪስቶች መድኃኒቱን ይሸጡልናል። ችግሮቻችንን ይነግሩናል። ነገር ግን ለሚነግሩን ችግራችን «መፍትሔ ነው» ብለው ያሰቡትና ያዘጋጁት መድሃኒት መኖሩን ሲያውቁ ብቻ ነው ችግሮቻችንን የሚነግሩን። እስከዚያው ድረስ ትክክለኛ
ችግራችንን ቢያዩም አይነግሩንም። መፍትሔ ብለው የሚሸጡልንን መድሀኒት
አላዘጋጁማ። እሱ ደግሞ አያዋጣም።
ዘፋኙ እንዲህ ይላል .

«ላንቺም ለእኔም ከቶ ማይበጁ ጥጥ ሸምነው ጋቢ እየቋጩ
ያሞጋገሱሽ ምን እንኳን ቢመስልም ነጠላቸው ብርድ አያስጥልም።
እንኳንስ ለኛ ላገሩ ሊያውቁ
ለራሳቸው ከቶ የት አወቁ
ባንቺ ዝምታ ጎን እየታከኩ
ጎጇችንን ስሩን ነካኩ
እናትዬ ጥንስሱን እይው እታለሜ ድግሱን ለይው..
-
የተሰጣችሁን ሁሉ ያለጥያቄ የማትቀበሉ፣ ድግሱን የምትለዩ ያድርጋችሁ!

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Gemechu merara fana
ተ/ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሠሠ እንዴት እንዳዋረደኝ......

እነሆ ዩኒቨርስቲ ለመግባት ወደ አዲስ አበባ የመሄዴ ነገር እውነት ሆነ፡፡
(በጎርኪ ስታይል በመምጣቴ ይቅርታ) በመጨረሻው ምሽት ዘመድ
አዝማድ ተሰብስቦ ምን መማር
እንዳለብኝ ሃሳብ ያዋጡ ጀመር፡፡
ሸምገል ያሉት ዘመዳችን ዝንብ መከላከያ ጭራቸውን
በኮንዳክተር ሙድ ግራ ቀኝ ካወናጨፉ በኋላ እንዲህ አሉ፡፡
“… እንግዲህ አገር ቆርጠህ መጓዝህ ካልቀረ ደህና ነገር ተምረህ ነው
መምጣት!! ሲሆን ሲሆን ህክምና ብትገባ ደግ ነው፡፡ ወባ እንኳ ካቅሟ
ሰው ሆና ስንቱን ስትረፈርፍ ታያት
የለም? ይህ ሁሉ አኪም በመጥፋቱ ነው፡፡ ትምርቱን ስትጨርስ የት
እቀጠራለሁ ብለህ ከቶም እንዳትሰጋ! አንተ ተማር እንጂ ሃገሬውን
አስተባብረን መተዳደሪያህን አንድ ጋሻ ጥቅጥቅ ያለ ለም መሬት፣
እየተፈራረቁ የሚያርሱ ቀንጃዎች፣ የመጀመሪያ እህል ዘር ከሚስትና ከጎጆ
ጋር እናሰጥሃለን..” ሲሉ ቀሰቀሱ፡፡
አብዛኛው ሰው በጭብጨባ ደስታውን
ገለጠ፡፡
ሌላው የቅርብ ዘመዳችን እጁን መዘዘና አደግድጎ ሃሳብ ሰጠ፡፡
“… እህህህ እንግዲህ ምክክርም አይደል የያዝነው? ምንም እንኳ አሁን
አባታችን በሰጡት አሳብ ላይ ሌላ መደመር ከድፍረት የሚቆጠር ቢሆንም
ዘመድ ተብለን መሰየማችን ቅሉ አስተያየት እንድንሰጥ ያስገድደናል፡፡
እሳቸው እንዳሉት እክምና ብትገባ በጎ ነው፡፡ እሱ አልሆን ታለ ግን
እንደምንም ብለህ መንዲስ ብቶን ይሻላል ባይ ነኝ፡፡ እንግዲህ መንዲስ
ሲኮን መንገድ ትቀይሳለህ፣ እስባልት ትዘረጋለህ፣ሌላው ቢቀር እህች
ጎረቤታችን ያለችው ቡካይ ጅረት እንኳ ልብ በቅቷት ስንቱን እንደ ግንድ
እያየን እያንከባለለች ወሰደችው? ልብ በል እንግዲህ በበጋኮ ዘለን
የምንሻገራት ቦይ ናት ክረምት ሲመጣ ወንዝ ነኝ ብላ ሰውን ያህል ነገር
እያንዘፋዘፈች የምትወስድ፡፡ ይሄ ሁሉ ለምን ሆነ ታልክ ዛዲያ ድልድይ
ስላልተሰራላት ነው፡፡ አቻምና እንኳ እኛ ና ባሻገር ያሉ መንደሬዎች
ተረባርበን ወደል የሚያህል ግንድ እየቆረጥን ድልድይ አጋድመን ነበር፡፡
ውሃ በላውና በስብሶ የአያ ደባልቄን ልጅ እሻገራለሁ ሲል ተጠርምሶ አብሮ
ወሰደው፡፡ እና እንግዲህ ላሳጥረውና መንዲስ ኮነህ
ከመጣህ እኔ በበኩሌ ተመሬቴ የማርሰውን የእኩል ሰጥሃለሁ፡፡..” አለና
ተቀመጠ፡፡
ደማቅ ጭብጨባ ተከተለው፡፡ በስተመጨረሻ ተነሳችና
“… እኔ እንኳ ጠበቃ ቢሆን እመርጣለሁ፡፡ ወገን እሰቡ እንጂ! አዳሜ
ድንበራችንን እየገፋ የሚያርሰው፣ ምሎ ተገዝቶ በታቦት ሸምጋይ ገንዘብ
ተተበደረን በኋላ ሽምጥጥ
የሚያደርገን፣ ወረዳ ሹመኞች ሳይቀሩ ግብር እያሉ አጠፌታ የሚያስከፍሉነ
ለምን ነው? የመንግስትን ደንብ አያውቁም ብለው አይደለም? እኔ
በበኩሌ የተበላሁ ገንዘብ አስር ልጅ
አሞናሙኖ ያስድረኝ ነበር፡፡ አሁንም የሆነ እንደ ሆነ ነገረ ፈጅ ሁኖ ሲሆን
እስከዛሬ የተቦጠቦጥነውን እንዲያስመልስልን ያም ባይሆን ለወደፊቱ
እንዲከላከልልን ነው፡፡..” ብላ
ቦታዋ ተመለሰች፡፡
የሚገርመው ግን አንድም ቦተ ስለኔ አሳብ የጠየቀኝ ሰው የለም፡፡ ግራ
ቀኙን እንደ ፍርድ ቤት ሰምቼ ገባሁና ተኛሁ፡፡
በጥቂት ቀን አዲሳባ ገባሁና ትያትር መማር ጀመርኩ፡፡ ይህንን ከ4 ዐመት
ህጻን ወንድሜ በቀር ለማንም አልተናገርኩም፡፡ ለሱም ልነግረው የቻልኩት
ገመና ድራማ በሚተላለፍበት ግዝ ሹገር ዳዲ ሆነው ሚተውኑት ጋሽ
ተስፋየን ስለወደዳቸው መምህሬ ናቸው ብየ ስለ
ነገርኩት ነው፡፡ በተረፈ ሶስት አመት ሙሉ በጓጉንቸር ቁልፍ እንደከረቸሙት
የከርቸሌ በር ተጠርቅሜ ኖርኩ፡፡
በየአጋጣሚው ምን እንደምማር ሲጠይቁኝ በስልት እያፈገፈግኩ
አመልጣቸዋለሁ፡፡ ከኔ አልመጠ ቢላቸው ዘመዶቼ ራሳቸው መላ ይመቱ
ጀመር፡፡ ህክምና የተመኙልኝ አዛውንት
“..ይህ ልጅ እክምናውን ነው የመረጠ፡፡ ማስረጃውም….” አሉና
ከብብታቸው አንድ ፎቶ መጅርጠው አወጡ ፎቶው እኔ ነጭ ጋውን ለብሼ
የተነሳሁት ነበር፡፡ እንዴት እሳቸው እጅ
ሊገባ እንደቻለ ደነቀኝ እንጂ ፎቶው ለአንድ ኮርስ ማሟያ የሞሌርን “
የፌዝ ዶክተር” የተሰኘ ተውኔት ስተውን የተነሳሁት ነበር፡፡ እንዲህ እንዲህ
እያልኩኝ መመረቂያዬ ተደገሰ፡፡
በአጋጣሚ ዘመድ ሁሉ ተሰብስቦ ምርቃቴን ሲያከብር ተስፋየ ገሰሰ በቲቪ
ብቅ አሉ “…የጓዴ መምህር!!” አለና ህጻኑ ወንድሜ ጮኸ! ግራ ቀኝ
ሲያፋጥጡኝ ትያትር መማሬን ነገርኳቸው፡፡ አባቴ ክፉኛ አዘነ፡፡
“… ምነው ልጄ አዲሳባ እሚያህል አገር ድረስ ሄደህ ቅሌት ተምረህ
ትመጣ?! አይይይ አለዛሬም አላዋረድከኝ! ምሰህ ቀበርከኝ እንጂ! እኔ
ደግሞ እንደ ሰዎቹ ሞያ ተምረህ
መጣህ መስሎኝ 10000 ብሬን ሆጭ አድርጌ መደገሴ!! አሄሄ ምን
አደርጋለሁ! ራስን አይገርፉ!..”
እያለ አቅማማብኝ፡፡
ህክምና የተመኙልኝ አዛውንት እንዲህ ብለው ለአዝማሪ ግጥም ሰጡ
አኪም ይሁን ብየ ዳር አገር ሰድጄ፣
ቀሎ ወርዶ መጣ ደጀን ያልሁት ልጄ።

©ጥላሁን ሀገሬ

@MahletZerihun
@Wegoch
@Wegoch
እንኳን ለ 125ናው የአድዋ በዓል አደረሳችሁ
ሥዕል #ለይኩን_ግርማ
.
@seiloch
@getem
@wegoch
አነስተኛ የሰው ቁጥር ከምታስተናግድ ካፌ ቁጭ ብለው እያወጉ ሳለ…በረጅም ደቂቃዎች የተሰላ ምስጠት በሚመስል የትካዜ ፊት ዝምታ ውስጥ ቆየ።በቅርብ እርቀት የተቀመጠው ጓደኛው ሻዩን ጎንጨት አረገና ጉሮሮውን ሲጠራርግ ከትካዜው መለሰውና "እኔ ምለው" ብሎ ጀመረ… የምስጠቱን ውጤት ሊያቀርብ ይመስል …


"እኔ ምለው…ምንም ይሁን ምን ዛሬም በጥያቄ ጎዳና ላይ ነኝ፡፡ ጥያቄ በዘመን ርዝመት መልስ ያገኛል ብለውኝ ነበር።መልስ ካላገኘ ግን በጊዜ ሂደት ጥያቄ ራሱ መልስ የማይፈልግ የሕይወት ክፍል ይሆናል።? …ጥያቄ ጠይቄ በአራት ነጥብ እንዳልዘጋው ጥያቄ ነው፤የሰዋሰው ህግን ያናጋው ይመስለኝና ጠያቂነቴን ለመቀጠል እጠይቃለው።እሺ ቆይ ስለጥያቄዎቼ ብጠይቅ በጠያቂነቴ እጠየቅ ይሆን?አለ።

ከሁለቱም በስተቀኝ የተቀመጠው አጠር ያለው ጓደኛቸው ቀደም አለና "ወዳጄ ልምከርህ… ምክር አይጠየቅም።እኔ ለመናገር መጠየቅ አለብኝ ብዬ አላስብም።ጠይቄም ባገኘውት መልስ ተጠያቂነትን ስለማልፈልግ ድምፄን አቅበዋለው።
አለመጠየቅ ከአዋቂነት እንደ ሰበሰበኝ ለሚያስቡም እኔ ማውቀው አለማወቄን ነው እያልኩ ማፅናኛን ለራሴ ስችር ሰምተውኛል።ዛሬ ተቀባይ ነኝ።አልጠይቅም…በሂደቱ ላይ ቅሬታ ቢኖረኝ እንኳ በዝምታ ማለፍን አምኛለው።
ወይም አላውቅምን ዋጋ እሰጠዋለው።በመልሶች ውስጥ ሌላ ጥያቄ አይጠፋምና አላውቅም የሚል ቃል ሀብት ነው"።
የቀረበውን የብርጭቆ ውሀ በአንድ ትፋሽ ጨልጦ ሲያበቃ በረጅሙ ተንፈስ አለና ቀጥሎ "ወይ እስቲ እግዜርን ጠይቀው" አለው። ባለ ትካዜው "እግዜርማ ብዙ ጠያቂ አለው "ብሎ አለፈው።

ባለ ሻዩም በመሀል " ገባና ሲመስለኝ «ለምን?» ወይም «እንዴት?» የሚሉ ጥያቄዎች ህብር ፈጥረው ያመጡት
ሐብት አለ።
ውስጡን የጥያቄዎች ማዕበል
የማይንጠው ሰው ለህይወት የሚያበረክተው አዲስ ነገር ቅንጣት አይኖረውም ብዬ አስባለው።ጥያቄ ጅማሬ ነው።መጠየቅ ቢያመሳስለንም አቻ መልስ መፈለግ ያለያየናል… ክብደቱ መልስ ፍለጋው ላይ ያይላልና።
እናም ጠይቅ!
አሁን ከአንድ ስኬታማ ወንድ በስተጀርባ በለው ጎን ማን አለ ብለህ ብጠይቅ አንድ ጠንካራ ሴት ብለው የመጀመሪያውን መልስ ይሰጡሀል።ሀብታም ዘመድም የሚል አይጠፋም።ግና ከእያንዳንዱ ስኬት ከራቀው ወንድ ጀርባ አንድ ሰነፍ ሴት ልትኖር እንደምትችል ማንስ ነገረን… ካልጠየቅን " አለው።ተሳሳቁ።ሳቃቸው ሲረግብ

አልጠያቂው አልጠይቅ መፈክሩ የሆነው አጭሩ ጓደኛቸው በተራው ጣልቃ ገባና " እና እንደው እንደ ብዙሀኑ ለጥያቄው ከቀረቡት መልሶች ውስጥ መልሱ አልተሰጠምን አክበህ ማለፍ አቅቶህ ነው?መልስ ያጣስ ጥያቄ እንዳለ ዘንግተህ ነው ?ብሎ ሳያስበው ጠያቂ ሆኖ ጨረሰ።

ቀን ፪፬/፬/፪፼፩፫

@wegoch
@wegoch
@wegoch

#Heaቨን
(Maggie)

"እንደናንተ ዘመን ተሻጋሪ ...ባለ ብዙ ፍሬ ...ከንፁህ ልብ የተቀዳ ... በማስመሰል በውድድር እና በይሉኝታ ያልተፈተለ ..... ገንዘብ ውበት ዝና ና ክብር ሚባሉ ኮተቶችን ያልደረተ.... ድንገት ብልጭ ብሎ ደግሞ ድርግም የማይል....... የደረቀ ነፍስን የሚያለመልም.. አመድማ ገፅን የሚያወዛ.... ከእውነተኛ ማንነት የተጨለፈ መዋደድ.... መገኛው ወዴት ነው?" ብዬ ጠየቅኳቸው.. .....ገጠር ሄጄ የነበረ ግዜ.. ....... ከአያቴ የመጨረሻ ልጅ ከእታፈሱ ጋር ምንጭ ውሀ ልንቀዳ የሄድን ግዜ እንደሳቸው እድሜ ጠገብ ዛፍ ስር ቁጭ ብለው ያገኘዋቸውን የቀዬው ነዋሪ አዛውንትን
...
....
የህይወት ትልቁ ክፍል ላይ ተስፋ ቆርጫለው... ፍቅር ላይ!

.. ፍቅር ሸቀጥ ከሆነብኝ ከራረመ... በወንድ ኪስ ውስጥ እና በሴት ልጅ ውበት ስር የቀብር ስነስርዐቱን የፈፀመ ርካሽ ሸቀጥ!....(በተለይ በዚ ዘመን)

ዝግመተለውጡን የጀመረው ከራስ ነው!.... በነፈላስፎቹ ዘመን ፍቅር በጭንቅላት ይለካ ነበር.
ለጥቆ ወደ ልብ ወረደ! እራሱ ፍቅር(ክርስቶስ) መጥቶ ፍቅርን አነገሰው. ሰልሶ... ወደብልት ወረደ! የኛ ዘመን ላይ!.....የፍቅር ቀን በሚል የገበያ ስምኮ ሚደረገውን ብናገር ለቀባሪው ማርዳት ነው ሚሆንብኝ... እስቲ ተውት!......
አራትኛ ወደጉልበት አምርቷል... ይኸው ለጉድ የጎለተኝ መድሀኒያለም ክብሩ ይስፋና.... የኔ አልሆነችምና ፊቷ መበላሸት አለበት ብሎ አሲድ ሲደፋባት አይቻለው.....

:::::;;;;;;;:::::::::::::

ወደቀድሞው ልመለስማ

ሽማግሌው ....እድሜን ስክነትን ጥበብን ትዕግስትን እና ጥልቅ ማስተዋልን... መሬት ላይ ወድቆ አቧራን ቃም እንዳደረገ እርጥብ ልብስ ቅመውት....ፍፁም በተረጋጋ መንፍስ እንዲህ አሉኝ
.
.
"ልጄ.... ባሁኑ ዘመን ሁሉም ሰው ፍቅርን አድናቂ ብቻ ስለሆነ ነው! ዳር ቆሞ ብቻ ማድነቅ! የሰው ድግስ ላይ ከዳር እንደቆመ የበይ ተመልካች በምኞትና በህልም አለም እንደሚደሰት... መናኛ ሰው!.... ፍቅርኮ እጃችን ላይ ነው!
የተሳካላቸው ሰዎችን ስታይ ምነው እነሱን ባደረገኝ! ምነው ፈጣሪዬ መልካሙን ልክ የነሱ ያለውን የሞቀ ፍቅር በሰጠኸኝ.....ታድለው.. ትላለህ እንጅ... "እኔም አንድ ቀን..." ብለህ እጅህ ላይ ያለውን ፍቅር ለመዘርዘር አታልምም!
...... ታካች ትውልድ! .... እንኳን ሰውን ውሻን ለማልመድ መስዋዕት ትከፍላለህኮ! .... ምስያህን ለማልመድ ግን እንደው እንሰናከላለን.

በዛላይ.... እናንት ያሁን ዘመን ልጆች... በሳይንሱ በቀለሙ በጥበቡ... በሁሉም ላይ እንደተሳለ ሰይፍ ናቹ.... ግን... ፍቅር ላይ ይቀራዋል! ምድር ራሱ የቆመችው ፍቅር ሚባል መቋሚያ ተደግፋ ነው.
..... ፍቅርን "ባለቤት መሆን" ወይ በላባቹ እንዳደረጃቹት ቤት ንብረት"የእኔ ብቻ ሀብት! የኔ ንብረት" በሚል ስም ሸብልላቹ ያፈቀራቹት ወገን ድንገት ተቅፋቹ ገሸሽ ያለ እንደሆነ በፍቅር ላይ ተስፋ ትቆርጣላቹ!..... "ተከዳው!" "አወይ ሰው ማመኔ" ትላላቹ.....

ቀድሞ ነገር የጀመራቹት መች ፍቅር ሆነና?! ....ግብይት ይ?"

የጥጥ ማሳ የመሰለ ራሳቸውን ዳበስ አድርገው.... ቀጠሉ

"ወፊቱን በወጥመድህ ይዘህ ቤትህ ጎጆ ሰርተህ ጥሬ ወሀ እና መሰል ነገሮችን እየሰጠህ በድሎት ብታሳድጋትም እሷ ግን ከዛ ጎጆ መውጣትህ ሁሌ ትናፍቃለች

.. በተመሳሳይ... ይችኑ ወፍ ለቀህ እሯሷው የሯሷን ጎጆ ሰርታ ብትኖር ግን እጎጆዋ ለመመለስ እጅጉን ትናፍቃለች.... አየህ...
የሙጥኝ ብለህ ፍቅርን ስትይዝ እንደባህር ዳር ድንጊያ ያሟልጭሀል.... ነፃነቱን ስተሰጠው ግን... ቅንጭብ እንዳዋደደው ወረኧት የሙጥኝ ይልብሀል"

ሰው እጅግ የተወሳሰበ ፍጥረት ነው... መልአካዊ አመልና እንስሳዊ አመል አለው......... በመልአካዊው ያፈቅርበታል በእንስሳዊው ይበቀልበታል.........
ለዛኮ ነው ወንጌል ስሙ ቁርዐን ቅሩ መጣፍቅዱስ አንብቡ የሚባል.....
የምትወድዳት ሴት ውስጥ ያለውን እንስሳ ለመግደል መጀመርያ አንተውስጥ ያለውን አውሬ መግደል አለብህ!
ያኔ ማንንም የሚያ ስ ቀና እጡብ ድንቅ ፍቅር ትመሰርታለህ..."

ቀጭን ኩታቸውን ወደ ትከሻቸው እያጣፉና ሱፍ እንደተዘራበት ጥቁር መሬት በነጭ ጢም የተወረረ ፊታቸውን ዳስሰው

"እየውልህ.... ልጄ.... ... ክርስቶስ ፍቅሩን የገለጠው ቆስሎ ነው... አንተም ቁሰል ድማ አካልህን እጣ ወይ ደግሞ እንዲያ እንደክርስቶስ ያለውን አይነት ስ ቃይ ተሰቃይ አይደለም ያልኩት.... ትግስትን ገንዘብ አድርግ..... ማስተዋልን አስከትል.... ፍቅር ስሜት ብቻ አንዴ ቦግ አንዴ እል ም እንደሚል ተራ የሚሆነው.... ለሰጠኸው ፍቅር ምላሽ ስተጠብቅ ግዜ ነው. አፍቅር.... አንተውስጥ ያለው ፍቅር አገር ያህላል.... ትጎዳለህ እሱ እርግጥ ነው... ግን ጉዳትስ ቀን ጠብቆ ይክስሀል..... ፍስሀን በሰውነትህ ኮለል ያደርግልሀል...... ብቻ ታገስ .... "ቦ ጊዜ ለኩሉ!" አይደል ያለው ጠቢቡ!......... ስጥ ስጥ ስጥ..... ተስጠኸው አጥፎ ደርቦ የሰጥሀል.....ታድያ የሚሰትበትን ግዜ አታስላ.... እሱው በፈቀደው ቀን ይስጥህ."

ተመስጬ ነበር.....ካሉት ውስጥ አንድ ሀሰት የለበትም.

አንድ ነገር ተረዳው......... ግብዞች እንደሆንን... ወድደን ለካ በዛ ፋንታ መወደድን እንጠብቃለን??......

እታፈሱ እንስራውን ሞልታ ጨርሳ እንዳሻክማት ጠራችኝ...... ሽማግሌውን እጅ ነስቼ ሄድኩ

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Magi 🖤
"የመነኩሴውን ታሪክ ታውቂዋለሽ አይደል "…

"አላውቀውም ንገሪኝ" አልኳት

" እ…አንድ ሰው ሚስት ለማግባት ፈለገና ምክር ፍለጋ አንድ የሚያውቃቸው መነኩሴ ጋር ሄደ።መነኩሴውም የመጣበትን ምክንያት ጠየቁትና ሰዉየውም 'ቆንጆ፣ምርጥ ዘር ያላት፣የተማረች፣ፀባየሸጋ ሁሉን ያሟላች ሴት ፈልጋለው' ቢላቸው እሳቸውም 'ልጄ ለምን መነኩሳለው ...ህሄን ሁሉ የምታሟላ ብትገኝማ እኔም አገባት ነበር' አሉ አሉ።"

ፈገግ አልኩ…

በንዴት ቀጠለች

"አጋዥ፣ትሁት፣ለጋስ፣ታማኝ፣አፍቃሪ፣ይቅር ባይ፣አስተዋይ፣በተጨማሪም በሱ ቁንጅና መስፈርት ቆንጆ በአንድ ጊዜ  እንድሆን ይፈልጋል … ይሄስ እሺ ግን መድከምን ፣ መሳሳትን(ጠብቆ) ይከለክለኛል።ግርም የሚለኝ  እሱ በጊዜ ቀነጫጭቦ የሚኖራቸውን ከኔ በድምር መፈለጉ ነው።ለራሱ አያውቅ ነዳይ ለመነ ለአዋይ አሉ

"ምነው" አልኳት ብሷቷን ላረግብ እያሰብኩ።

"የሆንኩትን አይደለም… ያልሆንኩትን ነው።ያልሆነውን ግን መሆን የሚፈልገውን እንድሆን ይለፋል።እሱ መሆኑ አይቀድምም?

ስቆሽሽ ካላፀዳኝ?ወይም የምፀዳበትን ካላቀበለኝስ? ...የስህተት ልጆች አይደለን…የተሳሳተች ሄዋን ውስጥ ፍፁም እኔን ለመቅረፅ ይዳክራል።

Love cleanses አይደል የምትሉት ምነው ለሱ ከሸፈበት?ሰነፍ ነው?የራሱ ሰው ላይ ስህተት ሲያገኝ ይጨንቀዋል?

ንፁህ ያለመቆሸሽ ዋስትና የለው… ንፁህ ማለት ቆሽሾ የጨረሰ ነው?ከዚያ ወድያ የማያድፍ ፍፁም?ጥጉስ እስከመጨረሻው ባለማደፍ መዝለቅ ነው?"
ብሷቷን በጥያቄዋች ደረደረችልኝ።

አፅናናለው ብዬ ሀሳብ አዋቅሬ "እንከን የለሽ ሴት ፍለጋ ስትወጣ አይደክምህም አትባክንም?" ብዬ ምነው በጠየኩት

searching for the perfect person while we are messes… ፐ what an easy way to get disappointed ... ብቻዬን አውርቼ አፌን አጣመምኩ።ማፅናናት ብቀጥልም ከኔ ዘንድ የቀረ ትምህርቴ ይህ ነበር።

ያልተደረሰበት ትልቅ የሚባል ስኬት፣የቁጥር መጨረሻ የለካው ገንዘብ፣ከሁሉ የላቀ ግዙፍ እምነት፣ የማይረታ የሚባል አንድነት ፣ በመጨረሻም ፍፁም የሚባል ፍቅር እና ሰው ከሰው ልጅ መንደር ያሉ አይመስለኝም፤ሁሉም አንፃራዊ ነው። ለተቀማጭ ሰማይ…) አሉ ብዞዋቻችን ተቀምጠን የተራመደውን ወልጋዳነት ለመናገር ስንቸኩል እኛው ተደናቀፍን እኮ

anyway be what you seek, what you seek is seeking you ብሏል Rumi …ያኔ ምርጫችን ቢቀናጣም ቢጤውን አያጣም።

just one last golden rule
"None of us can vow to be perfect. In the end all we can do is promise to love each other with everything we got.Because love is the best thing we do.
Said Ted(A fictional character who said it all )

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Heaቨን
#አሉላ_አባነጋ 🔥👑


ምን ተብሎ ነው ሚጀመረው? ማን ነው ነው የሚባለው? ምንድነው ነው
የምንለው? በምን ማዕረግ ነው የሚጠራው? ራስ'ስ ለአሉላ ምኑ ነው?
ጀነራልነት የአሉላን የሩብ ግማሽ ይገልፀዋል? በታሪክ የነበሩት ጀግኖች
ሁሉ ተደምረው አኪሊስ ጋኒከስ ስፓርታከስ ሊዎኒዳስ ዳዊት ጎልያድ ጌድዮን
ዮፍታሔ ሊጣመሩ ማይችሉት ሁሉ ተጣምረው አንድ ባትል ፊልድ ላይ
አሉላን ባዶ እጁን ቢገጥሙት መሪያቸውን በንቀት እያየ "I knew you
would lead these men to their death eventually, is this the
day you would do it?" ብሎ ኢሬቻቸውን ሚያበላቸው ይመስለኛል።
ከልጅነቱም aggressiveness ደሙ ውስጥ ነው። ገብረሚካኤል የነበረው
የክርስትና ስሙን አባቱ እንግዳ ቁቢ ንስሐአባቱ ወልደጊዮርጊስ ጋር ሄደው
"ቀይሩልኝ" ይሏቸዋል። ምነው ቢባሉ "ወልደ ገብርኤል አርጉለት ልጄ
እንደሚካኤል የዋህና ገራገር ሳይሆን እንደ ገብርኤል ቁጡና ቀልጣፋ
እንዲሆንልኝ ነው ምፈልገው" ብለው ነበር። ወንዳታ አሉላ። ወንዳታ
ገብርኤል።
ካሳ ምርጫ ለንግስና ሻፍዶ ከላስታው ዋግሹም ጎበዜ(ተክለጊዮርጊስ)
ጋር ሲፈሳፈስ አሉላ ማርኮ እንደ በግ እየጎተተ አመጣው። ከዛ ትግሬዎቹ
ምን በለው ፎከሩ
"ንጉስ ማራኪ ከነዘውዱ
የበዝብዝ አሽከር አሉላ ወንዱ"
አሉላ ግብፅን መሐዲስቶችን ጣልያንን በተለያየ የጦር አውድማ
ረምርሟቸዋል። አሁን በየንግግርህ መሃል ዶግ-አመድ እያልክ ወሬ
ምታሳምርበት figure of speech የመጣው ዶጋሊ ላይ 500 የጣልያን
ጭባ ወታደሮችን አመድ ካደረጋቸው በሁዋላ ነው። ያኔ ነበር አፄ ዮሐንስ
ቀኝ እጁን ነው ምቆርጠው ይምጣ ብቻ ሲሉት አሉላ ጀግናዬ የቀኝ
እጃቸውን ቀኝ እጅ ለመቁረጥ ከሆነላቸው ምን ቸገረኝ ብሎ ሲከንፍ መቀለ
የሄደለት። ከዛስ? ከስልጣን ገሸሽ አረገው። የጦር ስትራቴጂስቱን አሉላን
ምክር መስጠት አትችልም ብሎ። መሐዲስት የጎንደር አብያተ
ክርስትያናትን ማቃጠል ሲጀምር ጆ ጎጄውን ራስ አዳል ተሰማን(ንጉስ
ተክለሓይማኖትን) ላከው። ቀምሶ ተመለሰ። ምኒልክና ሌሎቹን አስተባብሮ
መሐዲስትን ሊፈጅ ወደ መተማ ተመመ። ሚላ ቢጠበቅ ቢጠበቅ ዝር
ሳይል ቀረ ላሽ አለው። ትግሬዎቹ በዚ አኮረፉት። ዮሐንስን ሱዳኖች
ቀልበውት አንገቱን ይዘው ሄዱ። አሉላ ምኒልክ ላይ ጥርሱን እንደነከሰ
የዮሐንስን ልጅ መንገሻን ሊያነግስ ደፋ ቀና አለ። ምን ምክሩን አልሰማ
ብሎ በፈጣጣው ተዋግቶ ቢሰዋም ጌታዬ ነበር የሚለው። ታማኝነቱ ሌላ
ታሪክ ነው። አሉላና ክህደት በአንድ ዋንጫ ጠጥተው አያውቁም።
ምኒልክ በኃይል በልጦ ራሱን ሹሞ ጠበቃቸው። ትግሬዎቹ ራስ አሉላ በዘር
ሐረግ የባላባት ልጅ ሆኖ ሳይሆን በላቡ በውጊያ ችሎታው በmerit የራስ
ወርቅ ያሰረ ብትፈልግ በመውዜር ቢያሻህ በቡጢ የሚከነትር ጀግና መሆኑን
ያውቃሉና አቄሙበት። ተናቆሩት። ርስ በርስ እባብ ለእባብ ሆኑ። ሸዋ
ሊያስታርቅ ቀጠራቸው። አሉላ 'ከሃዲው' ምኒልክ ጋር ሄደ። ወደደው።
ሊገድሉት ከሚያሴሩበት ዘመዶቹ አዳነው። ታዲያ ከሸዋ አልመለስም አለ።
ድፍን ሸዋ በምኒልክ አዝማችነት ለአሉላ ወንድነት ጀግንነት ገበረ። የዚህኔ
ነበር አሉላን የገበሬ ልጅ፤ ከሃዲ ብለው እነ ራስ መንገሻ label ያረጉት።
አሉላ ምን ቢሉት መስሚያው ድፍን ሆነ።
"ያደራ ልጄ ከተቀናቃኞቹ ጋር ተመሳጥሮ ሊያጠፋኝ ሲል ነፍሴን የታደግካት
ምኒልክ በሩቁ ስጠላህ በሩቁ ስንቅህ ኖሬያለሁ። በሩቁ ሆነህ ነፍሴን
አተረፍካት። ከእንግዲህ ከግቢህ አልወጣም" አሉ። ከትግራይ ራሶች አንዱ
የሆነውን ራስ ሐጎስንም
"ሐገሬ እንኳን በናንተ እጅ አልወደቀች። እንኳን ትክክለኛውን ጌታ አገኘች"
ብሎት ነበር ይሄን ነው royalty recognizes royalty የምንለው።
አደዋን አንስተህ አሉላን መግደፍ ድንግል ሰገጥ መሆን ነው። ዘመቻው
በጎራዴ በመድፍ እና በነፍጥ ተጀምሮ ያለቀ ከመሰለህ ሌጣ መሃይም
ነህ። አሉላ ባሻይ ዓውዓሎምን ለስለላ የጣልያን ሰፈር ልኮ fake news
አሰራጭቶ ጣልያኖችን ሌላ ታሪክ ውስጥ የከተተበት መንገድ ከሁሉም
የቀደመው ነው። የነጣይቱ የውሃ ጉድጓድ ከበባም ቀላል የሚሊተሪ
ስትራቴጂ አልነበረም።
አየህ ጌታዬ አሉላ አንድ ሰውና አንድ ማዕረግ የሚበቃው ፍጥረት
አይደለም። ብቻውን ጀምዓ ነው። ጀግና ያደንቃል። ዮሐንስን ጌታዬ
ብያለሁና ምኒልክን አልልም የሚል ሽልም ደደብ አይደለም። "ሳውቅህ
ገባኝ ምኒልክ ጭስ ነህ አገሬ አንተን በማግኘቷ ዕድለኛ ናት ይመችህ"
ነው ያለው።
ሌላው ፕላኔታችን የአሉላን የሩብ ግማሽ ጀግና አፍርታ አታውቅም።
ምድርን ወክሎ ከaliens ጋር መዋጋት ይችላል። I can take all of you
motherfucker all at once የሚል፤ ፍርሃት ሲያልፍም የማይነካካው
ጀግና ነው። አንዴ ይሄን ብዬ ነበር
"ቀን የጣለው ጀግና ሄዶ ቀን የቀናው ቢመጣ
አባቴ ይሙት ስልህ
በአሉላ ስም ብዬ ነው ዛሬም የፍርሃት ዛር የማስወጣ"
ስሙ ጠበል ነው ዘምዘም ነው የኢዩ ጩፋ ካራቴ ነው በፈለከው መንገድ
address ያደርግሃል። አገሪቱ ኃይማኖት ብትሆን አሉላ ገብርኤሏ ነው
ለዚች አገር ፊትም ያላለፈ ሁዋላም የማይገኝ መልዐከ ዑቃቤዋ፤ የሌሊት
ጠባቂዋ ግብር የማይበላ ዛሯ ነው።
አሉላ
ምኒልክ
አሉላ
ምኒልክ
አሉላ
ምኒልክ

©ክቡር ሰይጣን 🖤🖤🖤

@MahletZerihun
@wegoch
@wegoch
እንደ ሀገር፣ እንደ ህዝብ ነፃ ለሆንበት ቀን እንኳን አደረሰን የቆየችልንን ሀገር ጠባቂ ትውልድ እንሁን ከተከፈለላት ዋጋ በታች አናድርጋት፤ ተሰብረው ያቀኑንን፣ ተገብረው ያቆዩንን፣ ባፈሰሱት ደም ነፃነትን ላጠመቁን አባቶች የሚገባውን ዘልአለማዊ ክብር ሰርተን እንችራቸው። በብዙ መስዋዕት የቆመን ማንነት ታግለን ልናፈርሰው አንችልም

"አድዋ ዛሬ ናት አድዋ ትላንት
መቼ ተነሱና የወዳደቁት"

የካቲት 2፫ ፲፱፹፰
አድዋ የጥቁር ህዝብ አኩሪ ታሪክ
እኔ ጥቁር ሰው ነኝ!!!

በእምኒ የጨረቃ

@wegoch
@wegoch
@wegoch
እኔ ነኝ ጤነኛ እነሱ?

ሬሳ በቀብር ፈንታ ሲቃጠል አይታችሁ ታውቃላችሁ ወይ?

እኔ ግን አይቻለሁ:: አጅቤ ወስጄ አስቃጥዬ ... አመዱን አጅቤ ... ምን አቻኮላችሁ ልነግራችሁ አይደል?

እኔ ሁለት ቀን ነው ያየሁት ... እቤታችን መጥቶ ... ለበዓል ... ተጫዋች .. ወጣት ነው! እነሱ
ቤተሰቦቹ ናቸው...

"ጆናስ እኮ ሞተ" ብሎ የሚነግረኝ አባቱ ራሱ ነው:: እኔን ነው ማየት ... ነጠላዬን አቀብሉኝ አልኩ:: እሱ እቴ ... ውስኪዬን አቀብሉኝ ብሎ በላይ በላዩ ይጨልጠዋል::

"ምን ሆነሽ ነው ኸረ ተረጋጊ!" አባትየው ነው በድጋሚ ..... የልጁን ሞት የረሱት መስለው ከወንድሙጋ ሌላ ወሬ ያወራሉ....

ልጁ
ይሄ ከተራራ ላይ ገመድ ወገባቸው ላይ አስረው የሚሽቀነጠሩትን ነገር ታውቁት የለ? እንደሱ ሲምዘገዘግ ነው ተፈጥፍጦ ...ትንሽ ቀን ሀኪም ቤት ተኝቶ የሞተው...

(እኔ ሀበሻ ነኝ! ምንም ሆኖ ይሙት ... ሰው ሞተ ከተባለ 'ወየው ልጄን... ወንድሜን ... አጎቴን ..." ነው! እነሱ 'እረፍ ስንለው አልሰማ ብሎ' ይላሉ:: 'ኸረ ሙት አይወቀስም ተው' እላለሁ በሆዴ ... (በነሱ ቆንቃ ማለት ስለማልችል ነው)

የቀብሩ ቀን ... (የመቃጠሉ ቀን ) ሬሳው በስነስርዓት በሳጥን ተደርጎ ጥቁር ሱፋችንን ግጥም አድርገን ቤተ ክርስቲያን ሄድን!! ... እንደማንኛውም ሬሳ የፀሎት ስነስርዓት ተደረገለት... ወላ ሀሌሉያ የሚለውን እንግሊዝኛ መዝሙር ዘመርኩላቸው ... (ሚስማር ሊያዘንቡብኝ ሆ! የመዝሙሩ ግጥምኮ ከእግዜር ጋር ፀብ አለው! )

የሆነው ሆኖ ሬሳው መቃጠያ ስፍራ ከመሄዱ በፊት ተሰናበቱት ሲባል ... የልጁ አያት አበባ ሊያስቀምጡ በሄዱበት ከእናቱጋ ተደጋግፈው ማልቀስ ጀመሩ.... ድምፄን እንዴት ልዋጠው? ህቅቅ ብዬ መነፋረቅ...

እናት የምመስለው እኔ ነኝ!! ሰው 'ምኑ ናት? ' እየተባባለ የሆነ ፊልም ይመስል ያፈጡብኛል:: ... ስንት ነገር አለ? ህእ ... ሀበሻኮ በአንድ ለቅሶ ለአንድ ሞት ብቻ አያለቅስም ... እነሱ ይሄን ያውቃሉ? አያውቁም!! ... የዛሬ 20 ዓመት የሞተ ወንድሜ... የዛሬ 14 ዓመት የሞተ አያቴ .... የዛሬ 6 ዓመት የሞተ ጏደኛዬ ... በእዛ እንባ ውስጥ ይሄ ሁሉ ሀዘን መኖሩን ያውቃሉ? አያውቁም....

ስንወጣ ሰው እናትና አባቱን ትከሻቸውን ጨበጥ እያደረገ ካለፈ በኃላ እኔጋ ሲደርሱ አበክረው ያፅናኑኛል::

የሚቃጠልበት ቦታ ሄደን ተቃጥሎ እስኪበቃና እስኪቀዘቅዝ ጊዜ ስለሚፈጅ ተመልሳችሁ ኑ ተብለን ሲለኮስ አይተን ሄድን!!

(በነገራችሁ ላይ ... ሬሳዬ እንዳይቀበር ይቃጠል ያለው ራሱ ሟች ነው:: እናትና አባቱ እንቢ ብለው ነበር ... እህቱ ቃሉ መከበር አለበት:: ብላ በዛ ላይ 18 ዓመት ስላለፈው መብቱ ነው ተብሎ ነው::)

ልናርፍ በሄድንበት እህትየው የባሰውን አመጣችው!!

"አመዴን ከወደቅኩበት ተራራ ላይ ወስዳችሁ በትኑት ብሏል:: እዛው ወስደን ነው የምንበትነው!"

አባትየው ምርር ብሎት

"በህይወት እያለም እረፍት ሰጥቶኝ አያውቅም! ይኸው ሞቶም ያንከራትተኛል! ምን አይነት የተረገመ ልጅ ነው?" (ልጁ ራሱ ግፉ)

እኔ አይኔን በልጥጬ ደንግጬ አያቸዋለሁ!! እነሱ ያፅናኑታል

"አይዞህ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ነው!! ቃሉን እናድርግለት"

አመዱን በሚያምር እቃ አስቀምጠው ሰጡን!! አመድ አጅቤ ትንሽ መንገድ ከሄድኩ በኃላ እኔ ወደቤቴ ተመለስኩ.... እነሱ አመድ ብተና ወደተራራው ተጏዙ....

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Meri feleke
ልንጋባ ሁለት ሳምንት ሲቀረን እጮኛዬ ጤነኛ እንዳልሆነ አወቅኩ!! (ርዕስ ነው)

"አታውቂም ነበር እንዴ?" ብለው የሚያዩኝ አስተያየት ራሱን ሊያጠፋ የነበረው ልጃቸው ሳይሆን እኔ የሆንኩ በሚያስመስል ሀዘኔታ አይን ነው።

"ምኑን? ምኑን ነው የማውቀው?"

"bipolar እንደሆነ አልነገረሽም?"

"ባይፖላር ምንድነው?"

እናቱና ወንድሙ 'ውይ ምስኪን አታውቅም!' የሚል አስተያየት ተያዩ። ያሉት ነገር ትርጉሙ ሳይገባኝ ግን ፍቅረኛዬ እንደ እርጅና የሚያስፈራ ነገር(ለእኔ ከእርጅና በላይ አስፈሪ ነገር የለኝም) እንደደበቀኝ ገባኝ።

ፍቅረኛዬ ነው! አብረን መኖር ከጀመርን ሶስት ወራችን! ማታ ከእንቅልፌ ስነቃ ከአጠገቤ አልነበረም። ለደቂቃዎች ጠበቅኩት። አልተመለሰም። አንዳንዴ እንቅልፍ ሲያስቸግረው እንደሚያደርገው ሳሎን ከሆነ ብዬ ሄድኩ። አልነበረም! የሳሎኑ ወደ ጓሮ የሚያስወጣ በር ክፍት ነው። እግሬ በደመነፍስ ተራመደ።

ቤታችን (ቤቱ) ውሃ ዳር ነው። የሳሎኑ ወደጓሮ የሚያስወጣ በር ወደ ውሃው ነው የሚመራው። ጨረቃዋ ፏ ብላ ምሽቱ የእኩለቀን ድምቀት ደምቋል። ዙሪያ ገባውን ቃኘሁ። በስሱ ከሚያፏጨው ንፋስ በቀር ምንም ተንቀሳቃሽ ነገር የለም። ዓይኔን ወደውሃው ላኩት። ውሃው ውስጥ የሚንቀሳቀስ ነገር ያየሁ መስሎኝ አተኮርኩ። ማመን አልፈለግኩም ወይም ባይሆን ተመኘሁ እንጂ ያየሁት የሰው ጭንቅላት ነበር። ከደቂቃዎች በኃላ ራሱ መሆኑን አረጋገጥኩ። ፍቅረኛዬ ነው!! ውሃው ውስጥ እየተራመደ ነገር ........ ውሃው አንገቱጋ ደርሷል::

እኔ ምን ነበር ያደረግኩት? ቆምኩ! ደነዘዝኩ! ተጣራሁ
"ፔር! ሀኒ..."

ውሃው ውስጥ ልገባም ጀመርኩ:: ከነየቤት ጫማዬ ..... የውሃው ቅዝቃዜ እርሱጋ ሳልደርስ የሚገድለኝ አይነት ነው:: እየገባሁ ደጋግሜ ተጣራሁ።

"ፔር ! ፔር! " እንደሀበሻነቴም 'እሪሪሪሪ ..... ኸረ ወየው ኡኡኡኡኡኡ.... የሰው ያለህ' ማለትም ያምረኛል።

የጎረቤታችንን ስም እየጮህኩ ተጣራሁ አንዴ የፍቅረኛዬን ..... አንዴ የጎረቤታቸንን ስም ... እጮሃለሁ! የምይዘው ግራ ገባኝ .... የእሳት አላርማቸው ራሱ እንደእኔ መጮሁን እንጃ ጎረቤት መብራት ሲበራ እሪታዬን ከበፊቱ አብልጬ አቀለጥኩት። መጥተው እሱን ሲያወጡት እኔ ግማሽ ውሃ ውስጥ እንደገባሁ ደንዝዤ ቆሚያለሁ። እግሬ መንቀሳቀስ አቃተው። ድንጋጤው ...... ከዜሮ በታች የሆነው የውሃው ቅዝቃዜ ....... ጭንቅላቴ ውስጥ አሁንም አሁንም የሚያቃጭለው ሀሳብ 'ራሱን ሊያጠፋ ነበር?' አማተብኩ። መጥተው እጄን ይዘውኝ ከውሃው ወጣሁ!!

ሀኪም ቤት ከደረስን በኋላ ተደውሎላቸው የመጡት ቤተሰቦቹ 'እንዴት አታውቂም?' ብለው ይገረሙብኛል።

የፍቅረኛዬ ህመም ምን እንደሆነ ሊያስረዱኝ ሳይንሳዊ ማብራርያ ይነግሩኛል። በግልብ ሀበሽኛ ቋንቋ ፍቅረኛዬ መለስተኛ እብድ ነው። ይኸው ነው!! የአዕምሮ አለመረጋጋት!

"በሆነ መንገድ ትሪትመንት ይኖረዋልኣ? የሚድን ነገር ነው?" አልኩት ዶክተሩን። እሱም እንደቤተሰቦቹ እንዴት አታውቂም በሚል ሀዘኔታ እያየኝ(መሰለኝ)

"በሚያሳዝን ሁኔታ አይደለም! ... እ እ ከስንት አንዴ በራሱ የመጥፋት ነገር አለው። ጨርሶ ባይድንም በመድሃኒትና በትሪትመንት ግን ኖርማል ቀን ይኖራቸዋል።" ብሎኝ ምን ማድረግ እንደሚገባኝ ይነግረኛል። ማድረግ አለብሽ ብሎ የሚነግረኝን ነገር ማድረግ መፈለጌን እንኳን ሳያውቅ

ልንጋባ ቀን ቀጥረናልኮ!

ምንድነው የማደርገው?

ክፉ ሴት ነኝ? ፍቅረኛዬ ራሱን ሊያጠፋ ከመሞከሩ ከሰዓታት በኋላ ያሳሰበኝ ቪዛዬ ነው! ካላገባሁት ወደሀገሬ ልመለስ ነው።

በለሊት ተነስቶ ራሱን ለማጥፋት የሚሞክር እብድ ከመሆኑ ውጪኮ ጥሩ ሰው ነበር።

አንዳንዴ ልክ እንደጦዘ ሰው እየተቅለበለበ አንዱን ቃል ከአንዱ እየደረበ ከማውራቱ ውጪኮ ደህና ሰው ነበር።

አንዳንዴ በጣም ከመደበሩ የተነሳ እቤት ውስጥ ሲንቀሳቀስ ሰው ሰራሽ ሮቦት እንጂ ስጋና ደም ያለው ሰው አይመስልም ነበር እንጂ ደህና ሰው ነበርኮ

ለሊት ለሊት ብዙ መተኛት ስለማይችል ግማሽ ለሊቶችን ብቻዬን ተኛለሁ እንጂ ደህና ሰው ነበርኮ!

አንድ ቀን የጦፈ ልፋት ላይ ሆነን ድንገት የሆነ ራዕይ እንደተገለጠለት ነገር አክሱሙን ነቅሎ እንደተንጋለልኩ ጥሎኝ እርቃኑን ከመኝታ ቤት ወጥቶ ሲሄድ ምን ሆኖ ነው ብዬ ብከተለው ምንም እንዳላቋረጠ መጠጥ ቀድቶ ሳሎን ቢቀመጥም ..... ደህና ሰው ነበርኮ

ይሄ ሁሉ የህመሙ ምልክት መሆኑን የማውቀው ዛሬ ነው። ሀበሻ ነኛ .... የአእምሮ መታወክ ... አለመረጋጋት ... እያለ ከማያለዝብ ማህበረሰብ ነው የመጣሁት!! ... እብደት እብደት ነው የማውቀው!! በደረጃና በምልክት ተከፋፍሎ አንድ ሀገር ስም እንዳለው አላውቅም!! ከአዕምሮ ጋር የተያያዘ ምንም ነገር ከተፈጠረ ... ፀሎት ... ፀበል ... ጠንቋይ ቤት ... ባስ ካለ እና ትንሽ ከዘመኑ ሀኪም ቤት .... ትንሽ ትንሽ ያለመረጋጋቱን 'እገሌ እኮ ወሰድ ያደርገዋል' እየተባለ በሳቅ የሚታለፍ ነው!

የተወሰኑ ቀናት ሆስፒታል ከቆየን በኋላ ወደ ቤት ተመለስን! ፈራሁት! በተራዬ የማልተኛው እኔ ሆንኩ! እሱን ጥበቃ ገባሁ!
እንደፈራሁት ገብቶታል።

"You are free to leave me" አለኝ የሆነ ቀን!

ምን ማለት ነው? ማንን ነው የሚያስኮንነው? ደሞስ ቪዛዬስ? ቀድሞስ የያዘ ይዞኝ እንጂ አካሄዱ መች ጠፋኝ? ሰበር ሰካ እያልኩ እፈተለከው!

ግን ከዛስ?

አልጨረስንም ............

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Meri feleke
#Hiking_trip to Mount Mogle

Mount Mogle or the Mogle hills are located 19kms West of Addis Ababa. The hills contain a spectacularly diverse landscape. With the elevation of around 3210 meters above sea level, it is the highest peak in the West side of the capital.

The beautiful group of mountains, various types of trees and birds make the place an ultimate destination for hikers.

Hiking Date :- March 14, 2021 (megabit 5, 2013)

#Hiking_Cost 500 ETB only and for foreign 25 dollar

Departure Spot-piyasa (Tayitu Hotel)🍁
Departure Time - 12:30 Am LT 🍂🌴🍁

🎉🎊Package includes🎋🎊

🚍 Transportation
🌲 Bottled water
🌺 entrance with Guide
🍂 photography 📷
💐 Breakfast and lunch
🌷 Family Chilling & Talent performance ( if any)🙊🙊

🧗‍♂️ Trip grade: Medium
👉 Score Level: 8/25
👉 elevation: 3210 meter
👉 walking hour: 5-6 hour (8 km of walking)

suitable for:
- beginner
- walking of average fitness
- basic skill required

NB.
🚫 Sanitizer & facemask mandatory!

Brought to you by
💥#Sunset_Hiking_Group

for more join the
🔸channel @sunsethiking🍁
🔹the group @sunsethike🍁
🔻📷 @sunsetphotography🍁

🎫 tickets available at
@Paappii (0922303747)
ልንጋባ ሁለት ሳምንት ሲቀረን እጮኛዬ ጤነኛ እንዳልሆነ አወቅኩ (ክፍል ሁለት)

"ተሻለህ? እንዴት ነው የሚያደርግህ?"ይባላል?

"እንደ እብድ እንደእብድ ነው የሚያደርገኝ!" እንዲለኝ ነው?

እንደእውነቱ ከሆነ የሚያደርገውስ እኔ እነደማውቃቸው እብዶች አይደለም። የሚያደርገው ብቸኛ ነገር ጉልበቱን አቅፎ መተኛት ነው።

በግድ ይጎርሳል ..... ተፈጥሯዊ ግዴታ ስለሆነ እግሩን እየጎተተ ሽንት ቤት ይሄዳል። በቀን ውስጥ ከጥቂት ቃል ያለፈ ከአፉ አይወጣም።

ከሱ እንዲህ መሆን በላይ ልፋት ማቆማችን አሳሳቢ ነገር ሆኖ ባይሆንም እስከመቼ እንደምፆም ማወቁም አይከፋምኮ🤪 አብሯት ብዙ አልባሌ ነገር እንዳደረገ ሰው ሳይሆን ዛሬ እቤቱ እንደመጣች እንግዳ ነው የሚያየኝ። ቀኑ መርዘሙ ለሊቱ ደግሞ መባሱ ከአጠገቤ ዞር ሲል ካለማመኔ ሽንቱን ሁሉ ቆሜ ላሸናው ምንም አይቀረኝም።

የዛን ያህል ክፉ ሴት አታድርጉኝ! ፍቅረኛዬ ባይሆን ..... አብሬው ባልተኛ ......ወደፊቴን አብሬው ባላስብ ..... በአንድ ጣራ አብሬው ባልኖር ...... ይሄ ሁሉ ባይሆን እናንተ ስታነቡት እንዳዘናችሁለት እኔም አዝኛለሁ። ቤተሰቦቹ ; ጎረቤቱቹ ; ጓደኞቹ መጥተው 'እንዴት ነው?' ብለው ጠይቀውት እንደሚሄዱት፣ ስልክ እንደሚደውሉት እንደሱኮ እኔም የዛን ያህል ሀዘኔታና ፍቅር አለኝኮ

ግን ቀሪውን ዘመኔን ልሰጠው? በትዳር ስም ራሴንም ምንም የማያውቅ ልጄንም የየእለት ሰቀቀን ውስጥ ለመክተት የሚያስደፍር ቸርነትም ፍቅርም የለኝም። የዛን ደረጃ ፍቅር ማፍቀር የሚችለው ማፍቀሪያዬ ቆይቷል ከጥቅም ውጪ ከሆነ ......

ኸረ እንደእውነቱ ከሆነ በየትኛውም መጠን የሚሆን ፍቅር የለኝም!

አዎ ላገባው ነው። አዎ አብሬው እየኖርኩ ነው። አብረን ከመኖራችን በፊትም ለአንድ አመት የኔ ፍቅር የኔ ህይወት ተባብለናል። አላፈቅረውም ማለት እጠላዋለሁ ማለት አይደለም? 🤷🏽 መሃል ላይ የሆነ ስሜት አለ አይደል? ደስ ይለኛል! ከዛ ባለፈ ግን መሽለኩያዬ ነው። ማምለጫዬ ነው! ማለቴ ነበር!

እሱ ዛሬ ብድግ ብሎ ሰርጉን ሰርዤዋለሁ ቢል አንደኛ አይገርምም ያመዋላ!

ሁለተኛ ኖርዌጅያን ነው። እንኳን ሰርጉን ራሱንም በፈቃዱ ከመኖር ቢሰርዝ ከአንድ ቀን ቀብር ያለፈ ግርግር የለውም።

እኔስ?
እኔ እሱን ሳገባ ለእርሱ የሁለት ሰው ጥምረት እንደሆነው አይደለም ለኔ።

እሱ ቤት ስገባ የልጄን የወደፊት ህይወት ... የቤተሰቤን ድህነት ..... ያቺ የምወዳት ጎረቤቴን የበዓል ወጪ ሳይቀር በትከሻዬ አዝዬ ከነብዙ ጓዜ ነው የማገባው!

እሺ እኔስ በቃ ሰርጉን ሰርዝኩት አልኩኝ 'ልጄ ቀስ ብላ ትከፍላለች' ብሎ በብድር መሬት የገዛ አባቴን ምንድነው የምለው?

'ልጄን ሰው ካደረግክልኝ ሙክት አስገባለሁ!' ብላ ለመድሀንያለም የተሳለች እናቴን ምንድነው የምላት?

ለሚያውቃቸው እኩዮቹ ሁሉ 'እናቴ ውጪ ሄደች መጥታ ፈረንጆቹጋ ትወስደኛለች!' ብሎ የተቀደደ ልጄን ምንድነው የምለው?

'አይዞሽ እህታለም እኔ አለሁልሽ የግል ትምህርት ቤት አስገባሻለሁ' ያልኳትን ታናሽ እህቴን ምንድነው የምላት?

ለእነሱ መክፈል ያለብኝ መስዋዕትነት ከእብድ ጋር መኖር ከሆነ የምገባበትን ማጥ በወጉ ማወቅ ስላለብኝ ስለህመሙ ጎግል ማድረግ ጀመርኩ። ሳልዋሻችሁ መጀመሪያ የጎለጎልኩት ካገባሁት በኋላ እንደለመደው ራሱን ሊያጠፋ ቢሞክርና ቢሳካለት የኔ እጣ ፋንታ ምን እንደሚሆን ነው። ቋሚ የመኖርያ ፈቃድ ለማግኘት 3 ዓመት አብሬው የመኖር ግዴታ አለብኝ።

እንደክፉ ሴት አትዩኝ። እሺ በቃ ትንሽ ትንሽ ክፉ ነኝ። ከሞተ ወረቀቴን ይሰጡኛል። ለሆነ ሰከንድ ቢሞት ሁሉ ምንም እንደማይመስለኝ አሰብኩ። አምኛለሁ እሺ በደንብ ክፉ ነኝ!

በአለም ላይ 45 ሚሊየን ህዝብ የባይፖላር ህመም ተጠቂ መሆኑን ሳነብ በተመሳሳይ ምልክቶች የማውቃቸውን ሰዎች ሁላ እጠረጥር ጀመር። ራሴን ሁላ ስሜቶቹ ተሰምተውኝ ከሆነ ፈተሽኩ 'እብድ እኮ ለራሱ አይታወቀውም'ብዬ ተውኩት

በአለማችን ታዋቂ የሆኑ በዚህ ህመም ተጠቂ የነበሩና የሆኑ ሰዎችን ስም ዝርዝር ሳነብ የእብዶች ዓለም ነውሳ ዓለማችን?

በጣም ጥቂቶቹን ላስቆጥራችሁ ከመሪዎች የአሜሪካውን አብርሃም ሊንከን Abraham Lincoln የእንግሊዙን ዊንስተን ቸርችል (Winston Churchill)

ከሙዚቀኞች በፍቅር የምወዳት ኒና ስሞንን ጨምሮ Nina Simone, Selena Gomez,,Mariah Carey , Amy Winehouse, Demi Lovato ዘፋኞቹ ላይ ይበረታል ልበል? ብዙ ናቸው

በቁጠኝነቱ የሚታወቀው ታዋቂው ቦክሰኛ mike tayson

ታዋቂው የፊልም ፀሃፊ ዳይሬክተርና ተዋናይ Mel Gibson የዘመኔ ወንድ ልጆች እንደሱ ለመሆን ካራቴ የሚማሩለት አክተር ቫንዳም Claude Van Damme

እሺ ማነው ጤነኛ? የእብዶች ዓለምማ ነው!

ዶክተሩጋ ደውዬ ላገኘው እንደምፈልግ ነግሬው አገኘሁት። ይሄ ደግሞ ክፋቴን ሲያበዛው

"አንቺ ወደህይወቱ ከመጣሽ በኃላ ደስተኛ እንደሆነው ደስተኛ ሆኖ አያውቅም። ለ20 ዓመት ህክምናውን የምከታተለው እኔ ነኝ። አንቺን ካገኘ በኋላ ድኛለሁ ብሎ ለራሱ ስላመነ መድሃኒቱን አቋርጦ ነው" ይለኛል!!

ምን ውስጥ ነው ራሴን የዘፈቅኩት?

አሁንም አልጨረስንም ......

@wegoch
@wegoch
@paappii

#Meri feleke
ልንጋባ ሁለት ሳምንት ሲቀረን እጮኛዬ ጤነኛ እንዳልሆነ አወቅኩ (ክፍል ሶስት)

(ተፋፍረን እንጂኮ ሁላችንም አብደናል)

እንዴ የፈረንጅ አማች ሲከፋ ከሀበሻ ይብስ የለ እንዴ?

"በሱ ፋንታ ምናለ አንቺን ቢያቆራምድልኝ!" አንሾካሽካለሁ

"Pardon?" ትላለች ወደ አፌ ጆሮዋን አሹላ

"እዚሁ ነው እናቴ እዚሁ ነው!"

"Excuse me?"

ኡፈይ እቺ ደግሞ አላስተነፍስ ልትለኝ ነው እንዴ? እህቱኮ ናት! ወንድሟን አለሁልህ ልትለው ለተወሰነ ቀን መጥታ ልትደፋኝ በነገር። ቀድሞውኑም እንደማላፈቅረው ገብቷታል። 'እሰይ የታባሽ !' አይነት ሙድ ታሸሙራለች። የኔ መጨናነቅ ደስ ያላት ነው የምትመስለው።
'በላሁ ብለሽ ተቆረጠምሽ!' አይነት የነገር ዳርዳርታ
ጨዋታ ትጫወታለች::

"ስለሰርጉ ተነጋገራችሁ?"

"አልተነጋገርንም ምናልባት ቀኑን መቀየር ሊኖርብን ይችላል" አልኳት

"ሀሳብሽን የምትቀይሪ መስሎኝ ነበር።" እና ይህቺ የሀበሻ አማች አይደለችም?

"ለምን ብዬ?"

"አይ ያለበት ሁኔታ ከከበደሽ ብዬ ነው።" (ከባዱን ይስጥሽ እላታለሁ በልቤ)

የሰርጉን ቀን ላልተወሰነ ቀን አራዘምነው። እሱም መድሀኒቱን መቃም ቀጠለ። ከቀን ወደ ቀን ድባቴው ለቀቅ እያለለት መጣ።

የሆነኛው ቀን ከእህቱ ጋር እቤት ትቼው ወጣሁ እና አንዲት የምግባባት ታይላንዳዊት ጋር ሄድኩኝ። የማሳጅ ቤት አላት። የተፈጠረውን ነገር አንድ በአንድ ነገርኳት። እኔን ክፉ ናት አላችሁ? በሷ ሂሳብ እኔ ለመላዕክትነት እቀርባለሁ።

"ምን ትሰሪያለሽ ታዲያ? መድሀኒቱ ህመሙ የሚነሳበትን የጊዜ ጋፕ ያረዝምልሻል እንጂ ዘላለምሽን ወይም ሶስት ዓመት ከእብድ ጋር ነው የምትኖሪው ይልቅ በቀረሽ ጊዜ ዞር ዞር ብለሽ የሚያገባሽ ፈልጊ!" አለችኝ። ባል ከምስር ውስጥ የሚለቀም ጠጠር ነው ወይ ፈለግ ፈለግ ተደርጎ የሚገኘው? በዛ ላይ አብዛኛው ኖርዌጅያን አግባ ከሚባል ሲኦል ግባ ቢባል ኪሱ ውስጥ እጁን ከቶ እያፏጨ ይገባል።

"ከየት ነው የምፈልገው?"

"ቲንደር አካውንት ክፈቺ (የታወቀ የዴቲንግ ሳይት ነው) ወንዱ እዛ አፉን ከፍቶ አይደል እንዴ የሚውለው? ከፈለግሽ ደግሞ ማሳጅ ቤት እየመጣሽ እኔጋ ዋዪ ሀብታሞቹ ይመጣሉ::"

"ከዛስ? በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ አግባኝ ብለው ማን ይሰማኛል?"

"አንቺ (እንዴት ያለሽው እንከፍ ነሽ አይነት አስተያየት ከፀጉሬ እስከጥፍሬ እያየችኝ) ይሄን የመሰለ ሰውነት ይዘሽ .... ቆንጆ ነሽ ... በዛ ላይ ስማርት ነሽ ...ጨዋታውን ተጫወቺ (አባባሏ ስድድድ ያለ ስድነት አለው ) አጊንቶ ነው። ካላገባኸኝ ቪዛዬ ሊያልቅ ስለሆነ ልሄድብህ ነው ትዪዋለሽ አለቀ!"

"እሺ ባይለኝስ? ከሁለት ያጣ ሆንኩ ማለት አይደል?"

"አንቺ (አሁንም አጠራርዋ እንዴት ያለሽው ገንገበት ነሽ አይነት ነው) አንድ አምስቱን አጫውቺ ከአምስቱ አንዱ ይፈርምልሻል!"

"መድሀንያለምዬ አምስቱን እያጫወትኩ ተመልሼ ፍቅረኛዬ ቤት ነው የምገባው?"

"ምን? ከቤት ስትወጪ ምልክት ያደርግበታል? ወይስ ይለካዋል?"

"እኔ ለሱ አይደለም ለራሴ? ጭንቅላቴ አይቀበለውም!"

"እንግዲህ ምርጫው ያንቺ ነው!"

እቤት ስገባ እሱ ከእህቱ ጋር ሳሎን ቁጭ ብለዋል።

"እንኳን ወጣሽ ከኔ የባሰ ድብርት ውስጥ ገባሽ!" አለኝ። ዛሬ ደግሞ በደንብ ነቃ ያለ ይመስላል።

"እ ለለውጥ አሪፍ ነው!" አልኩት።

ዶክተሩ እንዳስረዳኝ ይሄን የድባቴ ጊዜ ካለፈ መድሀኒቱን በስርዓት ከወሰደ ደህና ይሆናል። ላልታወቀ ያህል ጊዜ..... ደግሞ ድጋሚ እስኪነሳበት ....

ህመሙ ከገነት ሲኦል አይነት የስሜት ለውጥ ነው። እጅግ ከፍተኛ የሆነ የፈንጠዝያ ስሜት ከብዙ ተያያዥ ስሜቶችና ቅዠቶች ጋር ለቀናት ወይም ለሳምንታት ይቆይና ከዛ ደግሞ ከፍተኛ የሆነ የድብርት ስሜት ራስን እስከማጥፋት የሚያስደርስ ራስን መጥላትና አለመፈለግ ስሜት ለቀናት ለሳምንታት ይከተላል

"ይቅርታ! " አለኝ እህቱ ስትሄድ ጠብቆ "ስላልነገርኩሽ ይቅርታ"

"እሺ ለምንድነው ግን ያልነገርከኝ?"

"አንቺ ዓይኖች ውስጥ ብቻ ነው ጤንነቴን የማየው። አንቺ ስታዪኝ ብቻ ነው ሙሉነት ... እንደማንኛውም ሰው ጤንነት ይሰማኝ የነበረው። ሌሎች በዙሪያዬ ያሉ ሰዎች ሲያዩኝ አይናቸው ውስጥ አቅም አልባነቴን አየዋለሁ። ተስፋ ቢስነቴን አየዋለሁ። አንድ ምንም እንዳልጎደለሽ አድርጎ የሚያይሽ ያውም የምታፈቅሪው ሰው በህይወትሽ ሲኖር ደስ ይላል። ለመኖር ፈለግኩ .... ዓይንሽ ተስፋ ሰጠኝ .... ለመኖር ጓጓሁ .... አለመናገር መረጥኩ!" አለኝ። አይኑ ሳያነባ ድምፁ እያለቀሰ።

ግራ ገባኝ .... የምር ግራ ገባኝ። ልጄ አልቅሶ ሲያበቃ እንቅልፍ ሲወስደው በእንቅልፍ ልቡ ህህቅ ብሎ ሲቃ ሲያሰማ አንጀቴ እንደሚላወሰው አንጀቴ ተላወሰብኝ። አጠገቡ ሄጄ አቀፍኩት ትከሻው ላይ አገጬን አድርጌ ግራ የገባው ሀሳብ ሳስብ ከቆየሁ በኃላ

"መቼ ነው ለመጀመሪያ ጊዜ ያወቅከው?" እንዴት ብዬ እንደምጠይቀው ግራ ገባኝ ብቻ ገብቶታል። አይኑን ቡዝዝ አድርጎ

"ከአባቴ ሞት በኋላ አባቴን እንደገደልኩት ሳስብ ለሳምንታት ዲፕረስድ ሆንኩ::" እያለኝ እህቱ መጣች

ምንድነው ያለው? አባቴን ገድዬው ነው ያለው? ገድዬው ሲጥ ገድዬው?

አሁንም በድጋሚ አልጨረስንም

@wegoch
@wegoch
@paappii
2024/09/23 19:21:17
Back to Top
HTML Embed Code: