Telegram Web Link
#ወግ_ብቻ
.
አንድ ቀን ጋሽ ስብሐት በጠና ታሞ ልንጠይቀው ሄድን። የጠያቂዎች ጋጋት በዝቶበት ስልችት ብሎት ኖራሯል። ከመሃከላችን አንዱ በጥያቄ ያጣድፈዋል። ጋሽ ስብሐት ብስጭት አለ። ስሙን ጠራው ፣ "እባክህ በሩን ከውጭ ትዘጋልኝ ...

*

ጋሽ ስብሐትን ቃለመጠይቅ ለማድረግ አንድ ጋዜጠኛ ወደ ቤቱ ሄደ። ጋሽ ስብሐትም እንግዳውን ተቀብሎ ሻይ ጣደ።
ጋዜጠኛው ስለ ስራዎቹና ስለ ጋሽ ስብሐት አንተ እኮ እንዲህ ነህ እያለ መለፍለፍ ጀመረ። ሻዩ ፈላ። ጋሽ ስብሐት ሁለት ብርጭቆ አቅርቦ ሻዩን መቅዳት ጀመረ።

የጋዜጠኛው ብርጭቆ ሞልቶ መፍሰስ ጀመረ። " እንዴ ጋሽ ስብሐት እየፈሰሰ እኮ ነው። "
" አንተም በኔ መረጃ ሞልተህ እየፈሰስክ ነው። ታዲያ ምንድን ነው ልጠይቀኝ የመጣኸው? "

*

ጋዜጠኛ:- ጋሽ ስብሐት በዓሉ ግርማን እንዴት ትገልጸዋለህ?
በዓሉ ግርማ ዛሬ ቢኖር የኔን ስም አታውቀውም ነበር። እግዜርም ይሄን አውቆ በጊዜ ቀጨልኝ።
@wegoch
@wegoch
@wegoch
ለጊዜ ተዋቸው!


በአንድ ትንሽ መንደር ውስጥ የሚኖር አንድ ሰው ነበር። ታዲያ ይህ ሰው፣ በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ በኑሮው ከሚገጥመው ችግር የተነሳ፣ ሁልጊዜም በህይወቱ ደስተኛ አልነበረም። አንድ ቀን ግን ከሚኖርበት ሥፍራ በቅርብ ርቀት የምትገኝ ከተማ ዘንድ፣ አንድ ታላቅ የኃይማኖት አባት ከአጃቢዎቻቸው ጋር እንደመጡ ይሰማል። ይህን ጊዜም እኚህን አባት ማግኘት አለብኝ ብሎ ይወስናል።

በመሸም ጊዜ እኚህ አባት ያሉበት ሥፍራ ይደርስና፡ እሳቸውን ለማግኘት ቁጭ ብሎ መጠባበቁን ይይዛል። ከረጅም ቆይታ በኋላም እኒያን አባት ያገኝና ጥያቄውን ይጀምራል። "አባቴ ሆይ፥ በህይወቴ ፍፁም ደስተኛ አይደለሁም፤ በቃ ሁሌም በችግር የተከበብኩኝ ሰው ነኝ... በዚህ በኩል የሥራ ጭንቀት፣ በዚህ ደግሞ የጤና ቀውስ፣ በዛላይ የቤቴ ውስጥ ችግር... ብቻ ተደማምሮ እረፍት ነስቶኛል፣ ደስታም ርቆኛል፤ እባክዎትን አንዳች የመፍትሄ ሀሳብ ይስጡኝና፡ ደስተኛና የሰላም ኑሮ እንድኖር ይርዱኝ!"

ሽማግሌውም ፈገግ ብለው፤ "ልጄ፥ ለችግርህ ነገ ጠዋት ላይ መፍትሄ እሰጥሃለሁ፤ ነገር ግን አሁን ባዝህ፣ ጥቂት የኔን ሥራ ልትሠራልኝ ትችላለህን?፤ ሰውዬውም በዚህ ይስማማል። እሳቸውም ቀጥለው፦ "በጉዞአችን የያዝናቸው መቶ ግመሎች በዚህ ይገኛሉ፤ እናም ዛሬ ምሽት የነርሱን ነገር፡ አደራውን ላንተ ሰጥቻለሁ፤ ሁሉንም ግመሎች እመሬት ላይ ካስቀመጥክ በኋላ ወደ መኝታ መሄድ ትችላለህ"። ይህንንም ብለው ወደ ድንኳናቸው ሲያቀኑ፣ ሰውዬውም የታዘዘውን ሊያደርግ ምሽቱን ግመሎቹ ዘንድ አመራ።

በቀጣይ ቀንም ሽማግሌው ማልደው ወደ ሰውዬው በማቅናት "ልጄ፥ ሌሊቱን ጥሩ ተኝተህ አደርክ?" ብለው ይጠይቁታል። ሰውዬው ግን ኅዘን በተሞላበት ስሜት ሆኖ "አባቴ፥ ለዐፍታ እንኳን እንቅልፍ ሳይወስደኝ ነው ሌሊቱ የነጋው። ብዙ ለፋሁ፣ ብዙም ጣርኩኝ፡ ይሁንና በአንድ ጊዜ ሁሉንም ግመሎች እንዲቀመጡ ማድረግ አልቻልኩም። አንዳንዶቹ ራሳቸው ይቀመጣሉ፤ አንዳንዶቹ ግን ላስቀምጣቸው ብሞክርም እንኳን አይቀመጡም፤ አንዱ በዚህ በኩል ሲቀመጥ፡ በሌላ በኩል ያሉት ይነሣሉ"።

ይህን ጊዜ ሽማግሌው ፈገግ እያሉ እንዲህ አሉ፦ "ካልተሳሳትኩኝ፡ ይህ የሆነው ትላንት ማታ ነው አይደል?"

- ራሳቸውን በራሳቸው ያስቀመጡ ብዙ ግመሎች ነበሩ!?

- ብዙዎቹ ደግሞ በአንተ ጥረት ሊቀመጡ ችለዋል!?

- ቀሪዎቹ ልታስቀምጣቸው ሞክረህ እንኳን አልተቀመጡም፤ ከቆይታ በኋላ ግን በጊዜ ውስጥ ራሳቸውን አስቀምጠው አግኝተሃቸዋል!?

ሰውዬውም፦ "አዎ! አዎ!...ትክክል!" ብሎ መለሰ።

ሽማግሌውም ቀጠሉና፦ "ስለዚህ አሁን አንድ ነገር ተረዳህን?፤ በህይወት ያሉም ችግሮች እንዲሁ ናቸው...

- አንዳንዶቹ በራሳቸው መፍትሄ ያገኛሉ።

- አንዳንዶቹ በአንተ ጥረት መፍትሄ ያገኛሉ።

- አንዳንዶቹ ደግሞ በአንተ ጥረት እንኳን አይፈቱም፤ እነዚህን ችግሮች ለጊዜ ተዋቸው። ትክክለኛው ጊዜ ሲደርስ በራሳቸው ይፈታሉና/መፍትሄ ያገኛሉና/።

ትላንት ማታ፣ ምን ያህል ብትሞክር በአንድ ጊዜ ሁሉንም ግመሎች ማስቀመጥ እንዳልቻልክ ትምህርት ወስደሃል። አንዱን ግመል በዚህ ጋር ስታስቀምጥ በሌላ በኩል ያሉት ይነሣሉ። ልክ እንዲሁ፤ እዚህ ጋር አንዱን ችግር ፈታሁ/ተፈታ ስትል እዛ ደግሞ ሌላ ችግር ተነስቶ ይጠብቅሃል። ህይወት እንዲህ ነውና!። ችግሮች የህይወት አካል ናቸው፤ አንዳንድ ጊዜ ጥቂት፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ በርካታ ችግሮች ይኖራሉ። ይሄ ማለት ግን ስለነሱ ሁሌ ማሰብ አለብህ ማለት አይደለም። እነሱን ለጊዜ እየተወክ ወደፊት ተጓዝ። በእያንዳንዱ እርምጃም ወደ ዓላማ-ህይወት (Purpose of life/self- realization/) ማደግን ተማር።

ልብ በል፤

• አንዳንድ ጊዜ፤ ደስታን ለማወቅ በኅዘን፣ ዝምታን ለማድነቅ በጩኸት፣ የመኖርን ዋጋ ለማወቅ ባለመኖር መንገድ ልታልፍ ግድ ነው።

ይኸውልህ፤ ህይወት በተቃርኖ የተሞላች ነች። እያንዳንዱ ስኬት ከሸክም ጋር ነው የሚመጣው። ትልቅ ቤት ማግኘት ስኬት ሲሆን፣ ብዙ የሚጸዳ መኖሩ ሸክም ነው። ልጅ መውለድ ስኬት ሲሆን፣ በእኩለ ሌሊት መነሳቱ ሸክም ነው። ባለስልጣን መሆን ስኬት ሲሆን፣ የህዝብን ጩኸት ማስተናገዱ ሸክም ነው።

ብዙ ጊዜ የምንሠራው ስህተት- ስኬቱን ያለ ሸክም ከመፈለግ የሚመጣ ነው። ይህ ግን እውነታው አይደለም። የሚመጡት በጥቅል (package) ነው። ዋናው ነገር፣ ሸክሙም እያለ በስኬቱ/በበረከቱ መደሰትን መማሩ ላይ ነው!!
@wegoch
@wegoch
@wegoch
መፅሐፍትን መቅዳት ትጉህነት ነው

ስለ ቅኔ ሳስብ በዘመኔ ማንበብ ከቻልኩዋቸዉ ጥቂት መፅሐፍት መኀከል አንዱን ላንሳ ''ኀሠሣ'' ይሠኛል ፀኀፍትዋ ሕይወት ተፈራ ናት። ቀድሞ ነገር ''Mine to Win'' ብላ በ እንግሊዝኛ ቋንቋ ነበረ የፃፈቸዉ ፥ ኃላ ላይ ታድያ ሕይወት ታደሰ የተባለች ሰዉ ይኽንኑ መፅሐፍ ወደ አማርኛ ቋንቋ ተርጒማ በድጋሚ ለንባብ አብቅታው ነበረ። ስለ መፅሐፉ ለማለት ብዙ ይፈልጋል እና እሱን እንመለስበታለን አኹን ግን እንደዉ ከመፅሐፉ ላይ ከተለያዩ ገፆች ያገኘዋቸዉን ፁኹፎች እቀዳለኹ ትጒህም ነኝና ፥ ለማነሳቸዉ ኹለት ገፆች ላይ የሰፈሩ ሐሳቦች ይረዳን ከኾነ ዘንድ ይኽ መፅሐፍ ባንድ ቅኔን ለመማር ከፍተኛ ፍላጎት ስላሳየ ተዋነይ ስለተባለ ወጣት ያተኩራል ስለ ቅኔ ህይወቱ ብቻም ሳይኾን እንዴት የፈለገዉን ነገር ማግኘት ስለመቻሉ ፣ ቀድሞ ነገር ፍላጎቱ የት ድረስ እንደነበረ ፣ ፈተናዎቹን እንዴት ባስቸጋሪ ኹኔታ ውስጥ  ቢኾን እንኳን ማለፍ ስለመቻሉ ከኹሉም ከኹሉም ደግሞ ቅኔን ለመማር ለማወቅም ያለዉን ውጣ ውረድ እና ኹናቴ በጉልህ አድርጋ ሕይወት ተፈራ ያሳየችበት መፅሐፍ ነው። እንዳልኳቹ ይኽ ከመፅሐፉ ስለምኖስደዉ ኀሳብ እንደ መኳተኛ ነውና ወደ ፁኹፉ ላዝግም

ገፅ 26 ላይ ያገኘኹትን ላስቀድም
 ( ተዋነይ'ን አጎቱ ዐወቀ በሚመክረዉ ጊዜ )

'' ገና ስትፀነስ በህይወት ዘመንኽ ትልቅ ቦታ የመድረስ ምርጫ ተመነሻዉም የተሰጠኽ መኾኑን ተገንዘብ። ፈጣሪ ሕይወት ሰጥቶኻል ፥ ሕይወትህን ደርዝ እምታስይዘዉ ግን አንተ ነኽ። ቢያንስ መሞከር አለብኽ። ወኔ ማለት መለወጥ 'ምትችለዉን ነገር መለወጥ መቻል ነው።

ገፅ 110 ላይ ደግሞ ተዋነይ ይኽን ይለናል

ቅኔ ለመቁጠር ግብዓት የኾኑትን ማኀበራዊ ደንቦች ፣ ልማዶች ፣ የሰዉ ልጅ ባህርይ እንዲኹም ተፈጥሯዊውን ዓለም በተመለከተ ጥልቅ ዕውቀት አቀበለኝ።
    የወንድ ልጅ ቁንጮ ፣ የልጃገረድ ጋሜ ፣ የአበባ መዓዛ ፣ የሴት ልጅ ውበት ፣ የመነኩሴ ብፅዕና ፣ ሞፈርና ቀንበር ፣ የጨቅላ ሞት ፣ የሴት ለጋስነት ፣ የወደቀ ዛፍ ፣ እሾኻማ ጽጌ ፣ ተፍለቅላቂ ኮከብ ፣ ብራ ቀን ፣ የማለዳ ንፋስ ሽውታ ፣ የወፍ ላባ ኩሽኩሽታ እንዲኹም ነጎድጓዳማ ሰማይ ኹሉ ጥልቅ ትርጉም ያዘሉ ተምሳሌቶች ናቸው።
      __________//_____

ኸዚኹ ገፅ ላይ የተቀረዉን እቀዳለኹ መቅዳት ትጒህነት ነውና።

@Wegoch
@Wegoch
@Wegoch
ይህቺን የካህሊል ጂብራንን ጽሑፍ አንብቡና በፍቅር ውደቁ ::

የተሰበሩ አክናፍ (The Broken Wings)
( ካህሊል ጂብራን )


የፍቅር ምትሃታዊ ጨረር መንፈሴን በመዳበስ ዐይኖቼን የከፈተልኝ በ18 ዓመት ዕድሜዬ ነበር፡፡ መንፈሴን በውበቷ ያነቃቃችውና ወደ ፍቅር አፀድ የመራችኝ ሴት ደግሞ ሰልማ ካራሚ ነበረች፡፡

ውበትን አመልክ ዘንድ ራሷን ምሳሌ በማድረግ የፍቅርን ሀሁ ያስተማረችኝ ሰልማ ካራሚ ናት፡፡ የእውነተኛ ሕይወትን ግጥም ለመጀመሪያ ጊዜ ያዜመችልኝም እርሷ ነበረች፡፡

ማንም ወንድ የመጀመሪያ ፍቅሩን አይረሳም፡፡ የትውስታው ሕመም ልቡን እየጐዳው እንኳን የመጀመሪያ ፍቅሩን መላልሶ ያስታውሳል፡፡ የእያንዳንዱን ወንድ ብቸኝነት ወደሙሉ ሐሴት የምትቀይር ‹‹ሰልማ›› በሁሉም ሕይወት ውስጥ አለች፡፡ የወጣቱን ቀዝቃዛ ልብ በፍቅሯ በማሞቅ የደነዘዘ ምሽቱን በሙዚቃ የምትቀይር ‘ሰልማ' በሁሉም ሕይወት ውስጥ አንዴ ትከሰታለች፡፡


የቅዱስ መጽሐፍትን ምሥጢር ለመረዳት አእምሮዬ በተወጣጠረበት ወቅት ነበረ የሰልማ ውብ ከናፍር ለጆሮዬ ፍቅርን ሹክ ያሉት፡፡ ሕይወቴ ባዶ ነበር - ልክ አዳም በገነት እንደነበረው! ከዚያም ሰልማን እንደ ብርሃን ማማ ከርቀት አየኋት፡፡ እርሷ የልቤ ሄዋን ናት፡፡ ልቤን በአስደናቂ መረዳት ሞልታ የሕይወትን ትርጉም አሳየችኝ፡፡


የመጀመሪያዋ ሄዋን በራሷ ፍላጐት አዳምን ከገነት አስወጥታዋለች፡፡ የእኔዋ ሰልማ ግን በጣፋጭ ፍቅሯ አማካኝነት በራሴ ፍላጐት ወደገነት እንድገባ አደረገችኝ፡፡ ሆኖም የመጀመሪያውን ሰው የገጠመው እኔንም ገጥሞኛል፡፡ አዳምን ከገነት ያስወጣው እሳት የሆነ ቃል እኔንም ሳላጠፋና የተከለከለውን ፍሬ ሳልቀምስ ከገነት አባረረኝ፡፡

ዛሬ - ከዓመታት በኋላ - የቀረኝ ነገር ቢኖር የዚያ ውብ ሕይወት የሚያሳምም ትውስታ ብቻ ነው፡፡ ልቤን በሃዘን ፤ ዐይኖቼን በእንባ እየሞላ ያሰቃየኛል፡፡ የእኔዋ ውድ ሰልማ ሞታለች፡፡ የተሰበረ ልቤና በጥድ ዛፍ የተከበበ መቃብሯ ብቸኛዎቹ መታወሻዎቿ ሆነዋል፡፡ የሰልማ ምስክር ሆነው የቀሩትም ባዶው ልቤና መቃብሯ ናቸው፡፡


መቃብሯን የሚጠብቀው አስፈሪ ፀጥታ የሳጥኗን ውስጥ ምሥጢር ለፈጣሪ እንኳን አሳልፎ አይሰጥም፡፡ በሥራቸው አካሏን መጠው የሚመገቡት የዛፍ ቅርንጫፎችም ምሥጢሯን አይተነፍሱትም፡፡ የልቤ ሲቃ ብቻ ነው ፍቅር ፣ ውበትና ሞት የሠሩትን ድራማ የሚገልፀው፡፡

በቤሩት የምትኖሩ ወጣት ጓደኞቼ ሆይ - በመቃብሩ ሥፍራ ስታልፉ የእግራችሁ ዳና እንዳይረብሻት በዝግታ ተራመዱ፡፡ የሰልማ መቃብር ጋር ስትደርሱም አቅፎ ላስተኛት መሬት እንዲህ በሉልኝ፡- ‹‹በባህር ማዶ የፍቅር እሥረኛ የሆነው የጂብራን ተስፋዎች በሙሉ እዚህ አርፈዋል፡፡ እዚች ቦታ ላይ ደስታውን አጣ ፤ እንባውን አደረቀ ፤ ፈገግታውንም ረሳው፡፡››

የጂብራን ሃዘን ከመቃብሩ ጐን ካሉት ዛፎች ጋር ያድጋል፡፡ መንፈሱም ከፍ ብሎ ከዛፎቹ በላይ የሰልማን መሞት በሃዘን ያስታውሳል፡፡ ትናንትና ውበትን የዘፈኑት የሰልማ ከናፍር ዛሬ ከምድር በታች የተሸሸጉ ምሥጢራት ሆነዋል፡፡


‹‹ኦ - ወዳጆቼ! ባፈቀራችኋቸው ደናግል ስም እለምናችኋለሁ፡፡ በዚህ ስታልፉ ለተረሳችው ፍቅሬ አበባ አስቀምጡላት፡፡ አንድ አበባ ማኖር በፅጌሬዳ ላይ እንደምትፈጠር የማለዳ ጤዛ የንጋት አብሳሪ ነውና፡፡›


( ' መናፍቁ ካህሊል ጂብራን ' ከተሰኘው መጽሐፍ የተቀነጨበ )

@wegoch
@wegoch
@paappii
[' #Every_onE_has_a_storY ']
.
(#አሌክስ_ይህ )
.
.
.
ታቅዶ : በሚሖነውና : ያለ : እቅድ : በሚከሰተው : ገጠመኝ : መሓል : ደስታ : የሚባለው : ተወዳጅ : የስሜት : እንክብል : በተስፋ : ቅጠል : ተጠቅልሎ : ይገኛል :: መውደቅ : መነሳቱ : ማጣት : ማግኜቱ : ውሎን : ኣሪፍ : ህይወትን : ጣፋጭ : ያደርጋል : ጥሩ : የሚመስለው : ሑሉ : ጥሩ : ብቻ : ዐይደለም : መጥፎ : የሚመስለው : ኁሉም : መጥፎ : ብቻ : ኣይደለም
. . .
በህይወት : ውስጥ : ሑሉም : ነገር : የታቀደና : ቀድሞ : የሚታወቅ : ቢሖን : ኖሮ : ህዪወት : ሲበዛ : ኣሰልች : እና : ብዙም : የማትጣፍጥ : ትሖን : ነበር . . . በህይወት : ውስጥ : ምንም : ኣይነት : በእቅድ : የሚሖን : ነገር : ባይኖር : ኖሮ : ኣብዛኛው : የሕይወት : ገጠመኝ : ኣደጋ : የበዛበትና : ከባድ : ይሖን : ነበር . . .
. . .
ሑሉም : የራሱ : ታሪክ : ሑሉም : የራሱ : ገደል : ዐለዉ : ስለዚሕ : ሰዎችን : ኣትናቅ : ከማይገባቸው : ያለፈ : ቦታም : ኣትስጣቸው : ክፉ : ተግባርን : ሑሉ : ዐውግዝ : ከክፉ : ነገሮች : ኁሉ : ራቅ : ሰው : ነሕና : በሰዎች : ላዪ : ግን : ኣትፍረድ : ክፉ : ኣስተሳሰብ : እንጂ : ክፉ : ሰው : ኣልነበረም : ሖኖም : ግን : ክፉ : ሃሳብ : ካላቼው : ሰዎች ጋር : መዋል : ክፉ : ከማድረግ : ኣይተናነስም : መቼቱ : ይለያዪ : እንጂ : ኁሉም : ሰው : የሚያስደስት : ገጠመኝ : የሚያሳምም : ትውስታ : ኣለዉ : ሑሉም : ሰው : የተነገረም : ያልተነገረም : ታሪክ : ዐለው : የተፃፈና : ያልተፃፈ : የሚያስደስት : የሚያሳዝን : ሌላም : ሌላም. . .
. . .
የጊዜ : መልክ : ዥንጉርጉር : ነው : ኣንዱ : ትናንት : ኣቀርቅሮ : በተራመደበት : ጎዳና : ዛሬ : በኩራት : ይራመድበታል : ኣንዱ : ትናንት : በልበ : ሙሉነት : በሄደበት : መንገድ : ዛሬ : ኣንገቱን : ደፍቶ : ያልፍበታል : ሑሉም : ኃይል : በጊዜ : ውስጥ : ነው : ጊዜ : ባንተ : ሲሖን : ሃዘንህን : በልክ : ላንተ : ሲኆንም : ደስታህ : ረብ : ይኑረው
. . .
ኁሉም : የደስታ : ስሜቶችህ : ዘላቂ : እንዳልሖኑ : ኁሉ : ሑሉም : ፈተናዎችህ : በጊዜ : ውስጥ : እንደ : ጤዛ : ተነው : ይጠፋሉ : ኣንዳንድ : ነገሮችን : ከጊዜ : ይልቅ : የኣንተ : ጥረትና : ውሳኔ : የሚፈታቸው : ሲሖኑ : ኣንዳንድ : ሑኔታዎች : ደግሞ : በጊዜ : ብቻ : የሚፈቱ : መሖናቸውን : መረዳት : ኣለብሕ : ስለዚህ : ነገሮች : ‘ለምን : ኣሑኑኑ : ኣልሖኑም’ : ብለሕ : ሙጥኝ : ኣትበል : ትናንት : ያስጨነቀሕ : ዛሬ : እንደሌለ : ሑሉ : ዛሬ : የሚፈትንህም : ነገ : ላዪ : ኣይኖርም : ኣብዝቶ : መጨነቅ : ህይወትን : ማባከን : ሲሖን : ኣብዝቶ : ግድየለሽ : መሖንም : ኅይወትን : ጣዕም : ኣልባ : ያደርጋል : ትናንት : ያልነበረህ : ጸጋ : ዛሬ : እንዳለኅ : ሑሉ : ዛሬ : ያለህ : ፀጋም : ነገ : ላይኖር : ስለሚችል : ባለህ : ነገር : ኣመስግን : ተደሰትም:: #GooD_EveninG
.
.
.
.
.
እና ደ`ሞ #Its_My_Dam

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ከዛሬ ጀምሮ ጥቁር ነኝ
ባንጋባም አብረን ሶስት አመት የኖርን ፣አንድ ልጅ የወለድኩለት ባለቤቴ እዚህ
ውጪ ሐገር ብዙ የኖረ: በአባቱ አፍሪካ በናቱ ደግሞ ኢትዮጵያዊ ነው። አቤት ፀባይ! ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስይዞ በጥሬው ካለወለድ ሊበደር የሚችልበት ወርቅ አመል አለው። ሌላውማ አይነሳ። --እና ትናንትና ለወንድሜ በዋትስ አፕ ደውየለት እናቴ በዝና የምታውቀውን ባሌን በካሜራ አየችው እና እጇን ማራገብ ጀመረች -- 'ወቸው ጉድ! ብለሽ ብለሽ ደሞ ቅዱስ ሚኻኤል ረግጦት : በጦሩ የሚያስፈራራው ሰው ጋር ትኖሪ ጀመር ? አለችኝ። (ወንድሜ ትከሻዋን በስሱ ገፋ እያደረገ ዝም በይ ነገር ይላታል ።) አብሬ የኖርኩትን ሰው እንደ አዲስ ዞር ብየ አየሁት ። ለሃያ ምናምን ጊዜ ገንዘብ ስንልክላት እኮ እንኳን ለእኛ ቤት ለክልሎች ሁሉ አዳርሰን ስናበቃ; ተርፎን ለጅቡቲ የደፋነው ምርቃት አሸክማን ነበር። ውለዱ ክበዱ አይለያችሁ ምናምን --- ብላን ነበር ። 'ወይ ሰው' አልኩ የገዛ እናቴን። ባለቤቴ ወደ ካሜራው ቀረብ አለ እና ፈገግ ብሎ በአክብሮት 'ሃው ዱዩ ዱ ' አላት 'ምን አለ ደግሞ ?' አቤት አቤት አፍንጫ! አቤት የአፍንጫ ገደል! አቤት አፈጣጠር! አይይ የኢትዮጵያ ሰው ጉዴን ስማ ! ጉዴን ስማልኝ የቶቢያ ሰው!--- አለች 'ባክሽ እማየ ደሞ ታበዥዋለሽ የኢትዮጵያ ሰው ምን ያርግሽ ? የኢትዮጵያ ጠላቶች በእሱ የአፍንጫ ቀዳዳ የሚገቡ መሰለሽ እንዴ ? ' ብግን ብያለሁ። ምንም ቢሆን አንድ ልጅ ወልጄለታለሁ ። ተስማምቶኝ ነው የምኖረው።
እናቴ እያበሸቀችኝ ነው።
"ኤዲያ ! ያገርሽን ሰው የወንዝሽን ሰው አጣሽ እና ነው ይሄንን ዘር የሚያበላሽ
ይይይይ ደግ አላረግሽም ። እናት ነኝ እኔ ካልነገርኩሽ ማን ይነግርሻል ? ለካ ባለፈው አቃዠኝ አባተተኝ የግብርኤል ፀበል ላኩልኝ የምትይው ለካ ከዚህ ጋር እየኖርሽ ነው ? " ብላኝ አረፈች ። መጮህ አማረኝ። እማ! አፍሪካዊ ነው እኮ ! በአንድ አህጉር በአንድ ካርታ ውስጥ ነን --- " የምለው ጠፋብኝ። "ተይ ተይ! የምን ካርታ ? " አለች በቁጣ። ይሄ ካርታ እና ቁማር ድሮም ትውልዱን ያበላሸው ። ስንቱ መሰለሽ በካርታ ሰበብ
መቅኖ አጥቶ የቀረው?" እያለች ተብከነከነች ሶፋው ላይ ጋደም ያለችው ልጄ ጭቅጭቃችንን ሰምታ ተነሳች ። ባለቤቴ ቢያባብላት ዝም እልል ስላለች በዛውም ለቤተሰብ እንዳሳይ ከእቅፌ ላይ አኖራት። 'እህእ የማን ልጅ ናት?' አለች ። እናቴ በግርምት። አንጀቴ ተንተከተከ ' የማን ትሆናለች? የእኛ ነቻ። ' አልኳት። 'እህእ የእናንተ ልጅ? የእ-ናን-ተ ልጅ ቱቱፍ ቱፍ ቱፍ ቱፍ--- አለች '
እየመረቀቻት መስሎኝ ተፅናናሁ።
'ስሟን ማን አልሻት?' ' ብርቱካን '
እናቴ በሳቅ ተንፈራፍራ ልትሞት፣ ወንድሜም ሳቅ ሲያፍነው ይሰማኛል።
ጥላቻ በነፍሴ ሲሰራጭ ተሰማኝ።
'እኔ ምልሽ ?' 'እ ' አልኳት 'እናንተ ምትኖሩበት እውጭ ሐገር : ጥቁር ብርቱካን አለ እንዴ? ' አለች። አዞረኝ ፣ አጥወለወለኝ ፣ ስልኩን ዘጋሁት ። ኢትዮጵያ የአፍሪካ መዲና ! አዲስ አበባ የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫ እና መተኛ ናት :- (ምነው ስብሰባ ተሰብስበው ብዙዎቹን ሲያንቀላፉ አይደል የምናያቸው?) መቀመጫ ላይ ተቀምጠን ካወጋን በሁዋላ ታዲያ: ስንግባባ ደግሞ አብረን ብንተኛ ምን ችግር አለው?' እንግዲህ ብር ን ወንዶ ብርቱካኔን መጥላት የለም። ሁለተኛም ለቤተሰቦቼ አልደውልም ። እኔ በጥቁርነቴ አምናለሁ እነሱ ደግሞ ፀይም እንደሆኑ ይቀጥሉ።
አዲዮስ።

@wegoch
@wegoch
@paappii

#abeba birhanu
#ወግ_ብቻ
.
......የዜን መሪ የነበረው ሪዮካን ተራ በተራራ ግርጌ ባለው አንድ
ትንሽ ጎጆ ውስጥ በጣም ቀለል ያለ ሕይወት ይመራ ነበር ፡፡ አንድ ቀን ምሽት አንድ ሌባ ጎጆውንለመዝረፍ ይመጣል። ነገር ግን ጓዳ ጎድጓዳው ውስጥ ምንም ነገር እንደሌለ ያያል ፡፡

ሪዮካን ከሄደበት ተመልሶ ሲመጣ ሌባውን ይይዘዋል፡፡ “እኔን ለመጎብኘት ረዥም መንገድ መጥተህ ሊሆን ይችላል ፣ እናም ባዶ እጅህንማ አትመለስም! እባክህ ልብሶቼን በስጦታ ውሰድ፡፡” በማለት ለሌባው ችሮታን ያደርግለታል። ሌባ ግራ ተጋብቶ ነበር ፡፡ የተቸረውን ልብሶች ወስዶም ይሸሻል ፡፡

ሪዮካን ደማቋን ጨረቃ እየተመለከተ ራቁቱን ተቀምጦ “ድሃ ነፍስ! ፣ ያቺን ውብ ጨረቃ ብሰጥህ እመኛለሁ” ሲል ጮክ ብሎ ተናገረ ፡፡

ሱራፌል አየለ
@wegoch
@wegoch
@wegoch
መፅሐፍትን መቅዳት ትጉህነት ነዉና ተያይዤዋለዉ

የጨረቃና የፀሐይ ግርዶሽ
እንደ ሳይንስ ጥናት አንዳንድ ጊዜ ፣ ጨረቃ እና መሬት በአንድ መስመር ላይ ይገናኛሉ። ይህ በሚኾንበት ጊዜ የመሬት ጥላ ጨረቃ ላይ ያርፍና ጨረቃ ትጋረዳለች ወይም የጨረቃ ጥላ መሬት ላይ ያርፍና ፀሐይን እንዳናይ ትጋርድብናለች። እንዚህ ክስተቶች ግርዶሽ ይባላሉ።
 
አንድሮሜዳ መፅሐፍ ገፅ194



የፀሐይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ መጻሕፍት 
ኢትዮጵያውያን ስለ ፀሓይና ስለ ጨረቃ ግርዶሽ በተናገሩበት ትርጓሜ ሚጠነ ብርሃናት በተባለ መጽሐፋቸዉ ላይ ስለ ፀሓይ ግርዶሽ የራሳቸዉን የምርምር አመክንዮ አኹን ካለዉ ሳይንስ ለየት ባለ መልኩ እንዲህ ሲሉ አስቀምጠዋል:-

መፅሐፉ ላይ በግዕዝ ቋንቋ ከሰፈረዉ ፁኹፍ ስር የቀረበዉን የአማርኛ ትርጓሜ እቀዳለኹ

በእንዳንድ ሀገር እንጂ በዓለም ኹሉ የማይኾን የፀሓይ የመጨለም ልማድን ጨረቃ የልማዱን ጒድለት በማያደርግ ጊዜ ክበቡ ያለ ብርሃን ባዶ ጠፍ ይኾናል ፤ የፀሓይ ሠረገላዉ ከላይ ሲኾን የጨረቃ ሠረገላዉ ከታች በኩል ነው ፤ በየዘመኑ ወይም በብዙ ዓመታት የጨረቃ ክበቡ ከፀሓይ ጋር በቀጥታ ወደ ተያየበት የጨረቃው ዙሪያው እንደ ደመና ያጋረዳል ፤ ክበቡም ያለ ብርሃን ባዶ ይኾናል ፤ በሰማይ ላይ በተጋረደ ጊዜ በዚያ ሀገር በግልጽ የፀሓይ መጨለም ይኾናል ፤ በዚያ ሀገር ፀሓይ አይታይምና ከደመና ይልቅ ክበቡ ግዙፍ ናውና ብርሃን እንደማይሰውረው እንደ ዐየር ነፋስ ረቂቅ አይደለምና ፤ በፀሓይ ክበብ ልክ ታላቅና ሰፊ ነውና) ብለው ጽፈው ነበር።

አንድሮሜዳ መፅሐፍ ገፅ 200

@Wegoch
@Wegoch
@Wegoch
እነ አባ አይቼው
( በእውቀቱ ስዩም)
እኛ የድርሰት ስራ እምንሞክር ሰዎች ስራችን ቅጥፈት ነው፤ ስንቀጥፍ ደግሞ ቅጥፈት መሆኑን አንደብቅም፤ ግን ቅጥፈቱን ስታነቢው ፤እየተዝናናሽ እግረመንገድሺን ደሞ ቄስ ወይም ፈላስፋ የማይነግርሽን የህይወት ሀቅ ልታገኚበት ትችያለሽ’! ድርሰት ማለት እውነትን እነግራለሁ ብለው ቃል ሳይገቡ እውነት መናገር ነው!
ይህ ወግ ስለ ድርሰት አይደለም! ሀቅ እናገራለን ብለው ሚድያ ላይ ስለሚያጭበረብሩ ሰዎች ነው ፤
ባገራችን ሶስት ዋና ዋና ያጭበርባሪ መደበቂያ ዋሻዎች አሉ፤ ያገር( ወይም የብሄር)ፍቅር ስሜት ፤ ሃይማኖት እና የእድሜ ባለፀግነት!
የሌለ እየተተረተርህ ፤ ቀዳዳነትህ ላይ ትንሽ ያገር ፍቅር ነስነስ ካደረግክበት ማንም አይናገርህም፤ ለምሳሌ አንዱ ብድግ ብሎ “የጥንት አባቶቻችን ጆቢራ ተፈናጠው ጨረቃ ላይ ወጥተው እንደነበር ጥንታዊ መዛግብት ያረጋግጣሉ “ ብሎ ቢቀድ አብዛኛው እድምተኛ እልል ብሎ ይቀበለዋል፤ ላርመው ወይም ልሞግተው ብለህ ብትነሳ ባልተወለደ አንጀታቸው ያበራዩሃል ፤
የፈጣሪን ስም አብዝተህ ካነሳህ ፤ አሁንም አሁንም ከማልህ፤ ጆሮ ጭው እሚያረግ ውሸት ብትናገር የሚሞግትህ የለም፤
እንዲሁም አረጋዊ ከሆንክ፤ ጋቢ ለብሶ ደጅ ላይ ቁጭ ማለት ደረጃ ላይ ከደረስህ እንደመጣልህ መበርነን ትችላለህ ! በደንብ ተተርትረህ ከመሸበት ታድራለህ! የሆነ ሰውየ አለ ፤ በያ ትውልድ ታሪክ ውስጥ እዚህ ግባ እሚባል ሚና የለውም፤ ዋለልኝ አይሮፕላን ሲጠልፍ እሱ ካፌ ቡሌ ሲጠልፍ ነበር! አሁን መቸም ሙታን ተነስተው፤ አይመሰክሩኝም ብሎ ነው መሰል በየሚድያው ቻክኖሪስን የሚያስንቅ ገድሉን ሲቀድ አየዋለሁ !
ድሮ በልጅነታችን ወላጆቻችን አደብ ሊያስገዙን ሲፈልጉ “ አባ ጅቦ መጣልህ “ ይሉን ነበር፤ ከዚያ ጎለመስን ! አያጅቦ መጣልህ በadult version “ ኢሉምናቲ እና 666” ሆኖ ከች አለልን ! ባለፈው አንዱ ጉድ፤ ቻናሉ ላይ ላይቭ ተጎልቶ “ ላይቭ ላይ ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ሰዎች ትታዩኛላችሁ ፤ ወይ አንድ ሰው ይቀነስ ! ወይ አንድ ሰው ይጨመር! አለበለዚያ ልቀጥል አልችልም”፤ ሲል አየሁት !
ሰፊው ህዝብ ደሞ ኑሮው የፈጠረበት ፍርሃት ሳያንሰው እኒህ ፍሪኮች የፈበረኩትን ፍርሃት እየተበደረ ይቦካል! ኮሮና በቢልጌትስ የተፈጠረው በክትባት ሰበብ አእምሮአችን ውስጥ ቺፕስ ለማስቀመጥ ነው ይልሃል ደሞ ! ባለቺፕሱ ምን አጠምድ ብሎ ነው አንተ አእምሮ ውስጥ ቺፕስ እሚያስቀምጠው? ለቺፕሱም ይታዘንለት እንጂ!
ደብረ ማርቆስ ውስጥ፤ ድሮ፤ አንድ ሰው አገር እሚያስለቅቅ ውሸት ከተበረነነ “ አባ አይቼው “ የሚል ቅፅል ይሰጠው ነበር ፤ አባ አይቼው በቀዳዳነት ክብረወሰን የሰበረ ሰው ነበር ፤ ” አንድ ቀን ቀዳማዊ ሃይለስላሴ በመኪና ሲሄዱ አዩኝና መኪና አቁመው ሊፍት ሰጡኝ፤” ብሎ ላንድ ጠላ አጣጩ ነገረው ፤ እዚህ ላይ ቢያቆም ጥሩ ነበር ፤ “ የሁዋላ በር ከፍቼ ልገባ ስል “ ቀጠለ አባ አይቼው “ ጃንሆይ አጠገባቸው ወደ ተቀመጠችው ምሽታቸው እየተመለከቱ ፤አይቼው ጋቢና! መነን ወደ ሁዋላ ብለው ትዛዝ ሰጡ፤”
ሀሰት የሚወገዝበት ዘመን ነበርና የአባ አይቼው ተወግዘው ቀልለው ሞቱ፤ ዛሬ ቢኖሩ ኖሮ በየቻናሉ እየቀረቡ እንደ ልባቸው ተረርር እያደረጉ ከብረውና ተከብረው ይኖሩ ነበር
.
@wegoch
@wegoch
#የሰኔ መቅሰፍቶች

ክፍል -፯

የሰኔ ወር ሊያልቅ ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተውታል ከሰምኑ ትልቅ ሰላም ቢሰማቸውም አሁን የመጨረሻዎቹ ቀናቶች ሙሉ በሙሉ መቅሰፍቱን ይዘው እንደሚመጡ ገምተዋል
ሰውነታቸው መንምኗል ፊታቸው ገርጥቷል
ከቤተሰቡ ሁሉን የረሳችው ፊያሜታ ትመስላለች የሆነ አካል ሹክ ብሎ እንደነገራት ልቧ አምኗል
መቅሰፍቱ አልፏል
ካላለፈም ያው እንደተለመደው.....
ዛሬም ቤተሰቡ ሰብሰብ እንዳለ ነው
ዜናው ወሬው ሁሉ ጨረቃ ስልጣኗን ስላሳየችበት ግርዶሽ ሆኑዋል
ዛሬም ነግቶ መጨለሙ ከንደ አዲስ ይወራ
ቤተሰቡም ነግቶ ሲጨልም የኛም ነገር አከተመ ብለው ከሽብር ገብተው ነበረ
ጨረቃዋ ፀሀይን ጋርዳ ቀስ ብላ ቦታዋን ስትለቅ ቤተሰቡም ባልጠበቀው ደስታ ውስጥ እራሱን አጊቶታል
ያቺ እንደ ሶስት አመት የረዘመችው ሶስት ሰአት ግን ከማንም ሰው ትዝታ ውስጥ አጠፋም
ፊንሀስ የግርዶሹ ለት ከመፈጸሙ ከአንድ ቀን በፊት የነበረውን ሁኔታ እያስታወሰ ስቅቅ እስኪለው ይረብሸዋል የህይወት ነገረም ምን ያህል አስፈሪ ነገር እንደሆነ ሲያስብና ጭንቀቱ ምን ያህል እንደ ነበረ ሲያስብ ፈገግ ይሰኛል ሰውነቱን ለቀቅ አድርጎ ተመልስ ያስታውሰው ጀመር
ቤተሰቡ ሙሉ በሙሉ የመቅሰፍቱ ቀን መድረሱና ከግርዶሹ ጋ በቀጠሮ መምጣቱን አምነው ተቀብለዋል
ነገ ተመልስ ጨልሞ ይበራል ያንን ብርሀን በአይኔ አየው ይሆን....
ጭንቅላቷን እግሮቿ ውስጥ ከታ እግሮቿን በእጆቿ ጥብቅ አድርጋ ቆልፋቸዋለች
በቃ ሊያልቅ ነው ሊያበቃ ነው...
የተደፋችበት ሰአት ከመርዘሙ የተነሳ ሰውነቷ እርስ በራሱ ተሳስሯል ፀጉሯ ተነቃቅሎል የፊቷ ንዳድ እራሶን እየሰበቀ ይለበልበው ጀምሯል
ሲነጋ ያበቃል ነገ ከጨለመ ለኛ ቤተሰብ አይነጋም ያበቃል ፊያሜታ ከአልጋው ጀርባ ተጣብቃ ምሽቱን በእንባ እያሳለፈችው ነው
ቤተሰቡም ልጆቹን ይዞ ከነሱ ጋር የመጨረሻውን ምሽት ለማሳለፍ ወስኗል
የሁሉም ልብ በአንድ ሆኖ ለነገው ይመታል
በግድ የሚከፈቱ ጥርሶች ህፃናቱን በትንሹም ቢሆን ደስ አሰኝቷቸዋል
ፊንሀሴ በሀሳብ አለም ውስጥ ያለበትን ቦታ እረሴቶታል
ከእግሮቹ በላይ ሀሳቦቹ ስለፈጠኑበት እግሮቹኔ ማቆም አልቻለም
ዛሬ ከቤቴ ብወጣ ምንም አልሆንም ነገ ናት የኔ ቀን ዛሬን በምንም አልሆንም ተስፋ ከቤቱ ወጥት ጉዞውን ጀምሯል
አሁንም ይሄዳል አንገቱን ከግራ ወደቀኝ እየመለሰ በመስኩ መሀል ይራመዳል
ነገ የሚወዳት ጨለማ ፀሀይን ስትጋርድ ለቤተሰቡሜ ትልቅ ፅልመት ይዛ እንደምትመጣ አውቋል
አሁንም ግን ይወዳታል ከመስኩ አይኖቹን አንስቶ ጨረቃን ከሰማዩ ፈለጋት በዳመናው የጠቆረው ሰማይ መጣው መጣው ሚለው ዝናብ በመብረቁ መምጣቱን ሲያስገመግም ፊንሀስንም ከሀሳቡ አነቃው
ትንፋሹን ሀሳቡ የያዘበት ይመስል ወደ ውስጥ አየር ስቦ በረጅሙ ተነፈሰ
ብዙ እንደተጓዘ አውቋል ምሽቱሜ ለአይን መያዝ ጀምሯል
ተመልሶ ዞሮ ወደ ቤተሰቡ ገሰገሰ
ምን አልባት የሚራመድባት መስክ ለመጨረሻ ጊዜ የሚጓዝባት መንገድ ትሆናለች
ዝቅ ብሎ የመስኩኔ ሳር በእጁ ዳበስ አደረገው ስንብት መሆኑን ሳሩም ሳያውቀው አልቀረም
ነገ ነግቶ ሲጨልም ለቤተሰ በእርግማኑ ለተመረጡ ሰዎች የዘላለም ፅልመትን ያለብሳል
ፊያሜታ ባለችበት ዘንበል ብላ ከወለሉ ላይ ጋደም ብላለች
ፊንሀስም ከጉዞው ሲመለስ ያልጠበቀው ፀጥታ አስገርሞታል
ሁሉም ለትልቁ ሞት ልምምድ እንዲሆነው በትንሹ ሞት ውስጥ መቆየትን መርጧል
ፊንሀስም ወደ አልጋው ሄደ
የእህቱ እግሮች የአልገረውን ጫፎች አልፈው ተመለከታቸው
እሱም ከወለሉ ጋደም ብል ትንፋሿን ይቆጥረው ጀመር
አይንቹ ክድን ሲሉ ቁጥሮቹም አቆሙ

ይቀጥላል.....
ብላቴናው በእርግማን ገፆች ላይ

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ምንምነት ውስጥ ምንም ነገር አለ።


ሀሳብ አለ።
… እሚታሰብ እሚንሰለሰል ። ሳትፈልገው ሚፈልግህ…… ሳታልመው
እሚያልምህ…… በአንተ ዙሪያ እየዘወረ እሚዘውረወህ…… ሀሳቡን
ተረድተህ ለመሰደር ብትባዝንም ምንጩንና ፍንጩ የማይገለጥልህ
ግዜ አለ……… ታወጣ ታወርድና ይህን ሀሳብህን ለሚካፈልህ ጓደኛ
ትሻለህ… …ለመረዳት ሀሳብህን ለመካፈል የመጣው ጓድህ " ምን
ገጠመህ ጓዴ? " ይልሀል። የገጠመህ እክል አታውቀውም ግን
ጨንቆሀል……ግን ደብቶሀል…… ግን ያባዝንሀል…… የተምታታ ስሜት
ውስጥህ ሰርፇል። እንዲህ ነው ብለህ ተንፍሰህ ነገሩን ሀሳቡን
ማቅለል ያዳግትሀል።

……ያሳለፍካቸውን ቀናት እየተመለስክ ውሎህን አዳርህን
እያስታወስክ የተገበርካቸውን ትሰልላለህ ። ምንም አታገኝም ወይም
ከስሜቱ ጋር እየታገልክ መንስኤው ይጠፋሀል። ዝም ብሎ ውስጥህ
ይነጫነጫል ንጭንጭህን ተባዕት ወይም እንስት በታገኝ
አግኝተውህ የውስጥህን ስላልተነፈስክ ይከብዳቸዋል።እንዲህ
ይገጥማል ሀቅ ነው ። መንስኤ አለው ወይም ደርሰህ ተደብተሀል።፤

☞ ………ምንም ባልነው ነገር ምንም ያላልነው ነገር ይፈተላል።
ምንም ማለት ባዶ አይደለም ባዶ ያልነውም ምንም አይደለም ማለት
አይደለም። ባዶነትም አንድ ምንነት ነውና።ግን ምን ሆኛለሁ? ምንም
አልሆንኩም አልልም ባዶ ሆኛለሁና።

እናም
☞ ማንኛውም ሀሳብ ሀሳብ ሆኖ… ሀሳብነቱ ገዝፎ ሀሳብን አጨንግፎ
እሱ ሲያንሰራራ… …አንሰራርቶ ሀሳብ ሀሳብነቱን የሚረዳ ሀሳቡ
ደርሶበት ያረፈበት ሰው ላይ ነው።

ደግሞም
ምንም ነገር ውስጥ ምንም ነገር አለ
ምንም ነገር ያለምንም ነገር አይነሳምና።

@wegoch
@wegoch
አንድ ቀን አንድ ወጣት ወደ አንድ አገር ለመሄድ በጉዞ ላይ ሳለ
ምሽት አሸነፈውና በጅብ ከመበላት ብሎ ከፊት ለፊቱ
የምትታየው ትንሽ መንደር አመራ ከመንደሩ ደርሶ "የመሸብኝ
እንግዳ ነኝ አሳድሩኝ?" ሲል ይማፀናል።
የቤቱን ባለቤት አብርሃምን መሆን የሚጥር እንግዳ ተቀባይ
ነበርና "ይግቡ" በማለት እንግዳውን ወደ ጠባብ እልፍኙ
ይጋብዘዋል። ወጣቱም ወደ ቤት ገብቶ ትንሽ እንዳረፈ ለእግሩ ውሀ
ተሰጥቶት ከታጠበ ብኋላ እራት ይቀርብለትና ይበላል።
የቤቱ ጌታ ለወጣቱ ልጅ መኝታ ሲያስብ የመኝታ ቦታ ስለሌለ ትንሽ ጊዜ
ያስብና አንድ ሀሳብ ይመጣለታል። ይህም ሃሳብ ሌላ አማራጭ ስለሌለው
ከልጃገረድ ልጁ ጋር እንዲተኛ ይወስናል። "እንግዳው ልጄ እዚህ አልጋ
ላይ ከልጄ ጋር ተኛ" ይለውና አልጋውን ሁለት ቦታ በትራስ ይከፋፍልና
ያስተኛዋል።
እንግዳው ልጅም በተመደበለት ቦታ አንድ ጊዜ እንኳን ሳይንቀሳቀስ ለሊቱ
ነጋ። ጠዋት ቁርስ በልቶ ከቤት ተሰናብቶ መንገዱን ሲቀጥል
ማታ አብሯት የተኛችው ልጅ አበባ ስትኮተኩት በአጥር ያያታትና
"እህት መሄዴ ስለሆነ በአጥር ዘልየ ልሰናበትሽ" ሲላት
ትሰበራለህ ስትለው "ግድ የለሽም አልሰበርም" ይላታል።
ልጅቱም "እህ.... ማታ ትራስ መዝለል ያቃተህ አሁን እንዴት
አጥር ልዝለል ትላለህ?" ትለዋለች
:
አንዳንድ ሰዎች አለመቻልና መተው ሲደባለቅባቸው አያለሁ።
መተው አለመቻል አይደለም። ሰው የቻለውን ሁሉ አያደርግም
ማድረግ ያለበትን ብቻ ነው ማድረግ ያለበት። የሚችለው ነገር
ቢሆን እንኳ ማድረግ ከሌለበት ይተወዋል። ያቅተዋል ሳይሆን
ይተወዋል ብሎ ይመልስላታል።
.
ምን ለማለት ፈልጌ ነው
:
:
:
ያ እንግዳ አክባሪ ሰው ያሰመረው ትራስ የእምነት መስመር
ነው። የመታመን አጥር ነው። አጥሩ ይርዘምም ይጠር ብቻ
ታጥሯል። ያንን አጥር ማክበር የእምነት ወሰንን አለማለፍ እንጂ
አለመቻል አይደለም።
.
ሰው መጮህ ስለቻለ ዝም ብሎ አይጮህም፣ሰው መሳቅ ስለቻለ
ያለ ምክንያት አይስቅም፣ሰው መልበስ ስለቻለ ያገኜውን
አይለብስም . . . ለራሱ በተረዳውና ባመነበት መንገድ መስመር
ያበጃል። ካሰመረው መስመር ላለማለፍ የሚችለውንም
ይተዋል።
ማድረግ ስላልቻለ አይደለም መስመር ማለፍ ስላልፈለገ ነው
እንጂ ! ! !

@wegoch
@wegoch
@wegoch
🏹🏹🏹🏹🤺🤺🤺🐅🐅🐅🐅🐅

🔱አንድ ንጉስ ከ አጃቢው ጋር በመሆን ለ አደን ይወጣል። ለ አደን ሲወጡ ንጉሱ ወጥመድ እያጠመደ እያለ ወጥመዱ አምልጦት እጁን ቆረጠው።
በዚህም አጃቢው በማዘን "አይዞህ ንጉስ ሆይ ሁሉ ነገር ለበጎ ነው!" ይለዋል።
በዚህም ንጉሱ በንዴት እየጦፈ "የኔ እጅ መቆረጥ ነው ለበጎ?" ይለውና እስር ቤት ያሳሰረዋል።
ከብዙ ጊዜ በሗላ ንጉሱ ብቻውን ለአደን እራቅ ብሎ ወደሚገኝ ጫካ ሄዶ በአደን ላይ ሳለ ሰው አርደው ለጣዖት መሰዋት የሚያደርጉ ጨካኝ ሰዎች ይይዙትና አርደው ለጣኦታቸው መሰዋት ሊያደርጉት ሲሉ ቆራጣ እጁን አዩት።

በእነሱ ህግ መሰረት መሰዋት የሚያደርጉት ሰዉ ሙሉ ጤነኛ መሆን አለበት፡፡ በዚህም እየተናደዱ ለቀቁት።
ንጉሱ አጃቢው ያኔ 'ሁሉ ነገር ለበጎ ነው! ያለው ትዝ አለው' እየሮጠም ወደ አጃቢው እስር ቤት ሄዶ ስላሰርኩክ ይቅርታ አርግልኝ!.......... ብሎ ታሪኩን አጫወተው።
አጃቢውም "ማሰርክ ለበጎ ነበር! እኔም መታሰሬ ጠቅሞኛል።" አለው።
ንጉሱ-"እንዴት?"
አጃቢ-"ባልታሰር ኖሮ ከአንተ ጋር እሄድ ነበር ከዛ የያዙክ ሰዎች አንተ ቆራጣ መሆንህን ሲያውቁ ይለቁህና አኔን አርደው መሰዋት ያረጉኝ ነበር"አለው።

ባለን አመስግነን የተሻለ ለማግኘት ስንጥር የሚገጥሙንን ውጣ ውረዶች ይበረቱብን ይሆናል። ይሄ ደግሞ ያለ እና ለእና ብቻ የሚሆን አይደለም። ስለሆነም በማማረር ፈንታ 'ነገር ሁሉ ለበጎ ነው' ብለን ውጣ ውረዱን በፅናት እንለፍ።
😊😊😊 ፅኑአን እንሁን😊😊😊

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ከስራ በሁዋላ አየሁዋት ሄድኩና"
(በእውቀቱ ስዩም)
ኢትዮጵያ ውስጥ ስራ እንዲከበር ያደረገ ደርግ ነው፤ ከዛ በፊት ስራ የተናቀ
ተግባር ነበር፤
“ዋይ ዋይ ባላባት
እንግዲህ ቀረ ሳይሰሩ መብላት “ ይሉ ነበር የዩኒቨርስቲ ፋኖዎች!
ደርግ ስራን አስከበረ፤ አንዳንዶች እንደውም ባንድ ጊዜ ሁለት ስራ ደርበው
እሚሰሩ ነበሩ ! ለምሳሌ አትሌት ምሩፅ ይፈጠር ሩጫ ልምምድ ሲያደርግ
እግረመንገዱን በየቤቱ ፖስታ ያድል ነበር! በደርግ ብር ኖቶች ላይ ያሉትን
ምስሎች ተመልከቷቸው ! ሰፌድ የምትሰፋ ሴት፤ የሚመራመር ሳይንቲስት ! ቡና
የሚለቅም ገበሬ! የቦዘነ የለም!
መንግስቱ ሃይለማርያም እልል ያለ አምባገነን ነበር ፤ በስራ ግን ቀልድ
አያውቅም! የሆነ ጊዜ ላይ መንጌ፤ አለማየሁ እሸቴንና ጥላሁን ገሰሰን ወደ ቢሮው
አስጠራቸው !
“ ወጣት አለማየሁ! “
“አቤት ጓድ ሊቀመንበር “
“እጅ እግሩ ተቆርጦ አከላቱ ጎሎ
ይኑር አባብየ እየበላን ቆሎ
አርባራቱን ታቦት ጠርቶና ለምኖ
ብለው የዘፈንከው ምን አስበህ ነው? አባትህ ካልሰራ ማን የቆላውን ቆሎ ነው
የሚበላው?"
“ ጓድ ሊቀመንበር ይሄን ዘፈን የዘፈንኩት ካብዮቱ በፊት ባድሃሪው ስርአት ውስጥ
ነው! አሁን ንቃቴ ከጨመረ በሁዋላ የገዛ ዘፈኔን ሳደምጠው ሼም
ይጨመድደኛል” አለ አሌክስ ዞማ ፀጉሩን በጣቶቹ እየቆፈረ !
“ ሂስህን ከዋጥህ ላይቀር፤ ነገሮችን አስተካክለህ ብትዘፍነው ምን
ይመስልሃል?”
“ ጥሩ አሳብ ነው ጓድ ሊቀመንበር ! ምኑጋ ላስተካክለው? ”
መንጌ በመስኮቱ አሻግሮ ትንሽ ሲያስብ ከቆየ በሁዋላ ፤” እጅ እግሩ ተቆርጦ
የሚለው ስንኝ በጣም ዘግናኝ ነው ! የምር አባትህ ከሆነ ትንሽ አስተያየት
አድርግለት ! ወይ እጁን ወይ እግሩን አስቀርለት ! "
“ የትኛውን ላስቀርለት?” አለ አሌክስ !
“ እንደኔ እንደኔ እጁን ብታስቀርለት ጥሩ ነው፤” ቀጠለ መንጌ
” የለመነውን ቆሎ ለመያዝ ራሱኮ እጅ ያስፈልገዋል፤ እንደ ሁኔታው አይተን፤
ብሄራዊ ውትድርና ላይም ልናሳትፈው እንችላለን ፤ ሻእቢያ ናቅፋ ላይ የረፈረፈችን
እግር የሌላቸው ሸሽተው እማያመልጡ ወንበዴዎችን የቀበሮ ጉድጏድ ውስጥ
ወትፋ ነው፤ ‘ ይገርምሃል መጀመርያ ፈንጅ በእግራቸው ያስጠርጏቸዋል! ከዛ
ደግሞ በባሊ ተሸክመው ወስደው ሽምቅ ውጊያ ላይ ያሰማሯቸዋል! አገር
መገንጠል የተለማመዱት የገዛ ወንድሞቻቸውን እግር በመገንጠል ነው!
ርጉሞች!"
ቀጥሎ መንጌ ወደ ጥላሁን ገሰሰ ዞር ብሎ " እሺ ጃል ጥላሁን! ወዳንተ
ስመለስ፤
" ያላየሁሽለታ በማዘን፤ በጭንቀት በድቀት ተክዤ
ሌሊቱን ሳልተኛ እያደርኩኝ፤ ቀኑን እውላለሁ ፈዝዤ "
ብለህ የዘፈንከውን አዳምጫለሁ! አሁን ያለንበት ሁኔታ የሙሉ ጊዜ አፍቃሪነትን
የምናበረታታበት አይደለም!! ወጣቱ ቀን በስራ ተስማርቶ ማታ ላይ በሃሳብ
መፍዘዝ መብቱ ነው! በተረፈ ኢትዮጵያ ሌትም ቀንም በፍቅር የሚጃጃል ወጣት
የምትሸከምበት ጫንቃ የላትም! የወዝ አደር እንጂ የውዝዋዜ አደር ፓርቲ
ለመገንባት አልተነሳንም! ተግባባን?”
ከጥቂት ሳምንታት በሁዋላ ጥላሁን ገሰሰ “ ፈልጌ አስፈልጌ “ የሚለውን ዘፈን
ሰራ! ዘፈኑ የመንጌ ተፅእኖ እንዳለበት ለማወቅ እኒህን ስንኞች ብቻ ማየት
ይበቃል!
“ አየሁዋት መርካቶ ሲሉኝ ትናንትና
ከስራ በሁዋላ አየሁዋት ሄድኩና
ከስራ በሁዋላ ብቅ ብል በማታ
የለችም ካዛንችስ እሱዋ የት ተገኝታ
እሷ የት ተገኝታ

@wegoch
@wegoch
@paappii
ከየት እንጀምር ?
#ዳንኤል ክብረት)
.
ወዳጄ ሆይ ለምን ከሌለህ ነገር ትጅምራለህ? በሰው ላይ ኀዘን የሚጨምረው፣ ተስፋ መቁረጥም የሚያደርሰው፣ የበታችነትንም የሚያመጣው፣ ቅዠትንም የሚያባብሰው ከሌለ ነገር መጀመር ነው፡፡ እስኪ ራስህን አስበው? ስላላገኘሃቸውና ስላልደረስክባቸው፤ ስላመለጡህና ስላልተደረጉልህ ነገሮች ከማሰብ በእጅህ ስላለውና ስለደረስክበት ነገር ለምን አታስብም፡፡
በአንተ እጅ ያለው ነገር በአንተ እጅ ከሌለው ነገር ይበልጣል ወይስ ያንሳል? በእጄ ያለው ትንሽ ነገር ነው፣ በእጄ የሌለው ግን ዓለም በሙሉ ነው፤ ታድያ እንዴት በእጄ ያለው በእጄ ከሌለው ነገር ሊበልጥ ይችላል? እንደምትል አይጠረጠርም፡፡ ሲገመትም እንደዚያው ነው፡፡
እንደ እውነቱ ግን በእጅህ ያለው ነገር በእጅህ ከሌለው ነገር ይበልጣል፡፡ እንዴት? አልክ፡፡ በመጀመርያ ደረጃ በእጅህ ያለው ነገር ያንተ ነው፡፡ በእጅህ የሌለው ግን ገና ያንተ አይደለም፡፡ ያንተ የሆነው ያንተ ካልሆነው ነገር ይበልጣል፡፡ ምክንያቱም ያንተ በሆነው ነገር መጠቀም ትችላለህ ያንተ ባልሆነው ነገር ግን ልትጠቀም አትችልም፡፡ ያንተ በሆነው ነገር ልታዝዝ ትችላለህ፤ ያንተ ባልሆነው ነገር ግን ልታዝ አትችልም፡፡ ያንተ የሆነውን ነገር ማግኘትህን ርግጠኛ ሆነሃል፡፡ ያንተ ያልሆነውን ማግኘትህን ግን ርግጠኛ መሆን አትችልም፡፡ ያንተ በሆነው ነገር ልትወስንበት ትችላለህ፤ ያንተ ባልሆነው ነገር ግን ልትወስን አትችልም፡፡ ያንተ የሆነውን ነገር ለሌላው መስጠት ትችላለህ፤ ያንተ ያልሆነውን ግን መስጠት አትችልም፡፡ ካለህ ነገር ላይ ቆመህ የሌለህን ማየት ትችላለህ፤ ከሌለህ ነገር ላይ ቆመህ ግን ያለሀን ነገር ማየት አትችልም፡፡
እናም ወዳጄ ስትቆጥር ካገኘኸውና ከሆነልህ ነገር ጀምረህ ቁጠር፡፡ ባላገኘኸው ነገር ከምትበሳጭ ባገኘኸው ነገር ተደሰት፡፡ ባልሆንከው ነገር ከምታዝን በሆንከው ነገር ሐሴት አድርግ፡፡ ባልያዝከው ነገር ከመበሳጨት በያዝከው ነገር ሥራበት፡፡ ባልሆንከው ማንነት ከመቃዠት በሆንከው ማንነት መኖር ጀምር፡፡
ይህ ማለት ምን ይመስልሃል?
ስትጓዝ እያረጋገጠክ ተጓዝ፡፡ መጀመርያ ያለህን ዕወቀው፣ ከዚያም ባለህ ነገር ምን ያህል እንደ ተጠቀምክበት ርግጠኛ ሁን፡፡ ላለህ ነገር ዋጋ ስጠው፡፡ ያንተ የሆነውን ነገር አክብረው፡፡ ያን ጊዜ የሌለህን ታገኘዋለህ፡፡ የሌላውን ሰው ትዳር አይተህ፣ እርሱን ተመኝተህ፣ እንደዚያ በሆንኩ እያልክ በሌለህ ነገር ከማዘን፤ እስኪ በአንተ ትዳር ውስጥ ምን መልካም ነገሮች አሉ? የትኞቹን ተጠቅመህባቸዋል? የትኞቹን አድንቀሃቸዋል? ለየትኞቹስ ዋጋ ሰጥተሃቸዋል፡፡ የሌለህን ብቻ የምታይ ከሆነ ያለህን ማወቅ አትችልም፡፡ ስለ ሌለህ ነገር ብቻ የምታስብ ከሆነ ባለህ ነገር መጠቀም አትችልም፡፡ አሁን የምትሠ ራበትን ሞያ ወይም ቢሮ ወይንም መስክ በሚገባ ተጠቅመህበታል? ሠርተህበታል? ከዚያስ ማግኘት ያለብህን አግኝተሃል? ወይስ ሌላ ሞያ የምትፈልገው፣ ሌላ ቦታ መቀጠርም የምትመኘው፣ ሌላስ መስክ ላይ መዋል የምትጓጓው ሰዎች አደረግነው ሲሉ ስለሰማህ ነው፡፡
ብዙ ሰዎች ታች ከፍል በተማሩት ምንም ሳይሠሩበት ወደ ላይ ይወጣሉ፡፡ በመጀመርያ ዲግሪያቸው አንዳች ሳይፈይዱ ሁለተኛና ሦስተኛ ይይዛሉ፡፡ አኗኗራቸውንና አስተሳሰባቸውን ስታየው ግን ታች ክፍል ናቸው፡፡ ለምን ይመስልሃል? መጀመርያ በያዙት ነገር ሳይረኩና ሳይጠቀሙ፣ የያዙትን ነገር ፈጽመው ማወቃቸውን ሳያረጋግጡ ሰው ስላደረገው ብቻ ሌላውን አደረጉ፡፡
በቤታችን ውስጥ ይህኮ የለንም ብለን የገዛናቸው የማንጠቀምባቸው አያሌ ዕቃዎች አሉ፡፡ በየቁም ሳጥናችን ውስጥ ስለሌለን ብቻ የገዛናቸው የማንለብሳቸው ብዙ ልብሶች አሉ፡፡ ምናልባት ግን እነርሱን ከመግዛታችን በፊት ምን እንዳለን ብናስብ ኖሮ እነርሱን የሚተካ ወይንም የሚያስከነዳ ነገር በቤታችን ነበረ፡፡ እስኪ ሰዎችን ስማቸው፡፡ እዚህ መሥሪያ ቤት የተቀጠሩ የሚሠሩበትን እያማረሩ ያኛውን መሥሪያ ቤት ያደንቃሉ፡፡ እዚያ ያሉት ደግሞ ያሉበትን እየረገሙ እዚህ ያለውን ያመሰግናሉ፡፡ ለምን? ሁሉም ሌላ ያያሉ እንጂ ያላቸውን አያዩም፡፡
የት እንደምትሄድ ሳታውቅ አትሂድ፡፡ የት እንደምትሄድ ለመወሰን ደግሞ ከየት እንደተነሳህ ማወቅ የግድ ነው፡፡ ምናልባትምኮ አለመሄዱ ከመሄዱ የተሻለ ሊሆን ይችላል፡፡ እንዴት መሄድ ብቻውን ዓላማህ ይሆናል? ለአንዳንዶች መማር ብቻ ዓላማቸው ነው፡፡ ለአንዳንዶች ደግሞ ማግባት፡፡ ለአንዳንዶች መነገድ፡፡ ለአንዳንዶች ውጭ ሀገር መሄድ፡፡ ለአንዳንዶች ቤተ ክርስቲያን መሄድ፤ እነዚህ መንገዶች እንጂ መድ ረሻዎች አይደሉም፡፡ ሰውዬው መንገድ ሲሄድ አንድ ሽማግሌ ያገኛል፡፡
«አባቴ ይኼ መንገድ ይወስዳል?» ይላቸዋል፡፡
«የት ለመሄድ ፈልገህ ነው» አሉት ሽማግሌው፡፡
«የምሄድበትን አላውቀውም» አላቸው፡፡
«የምትሄድበትን ካላወቅከውማ የትኛውም መንገድ ይወስድሃልኮ» አሉት ይባላል፡፡

@wegoch
@wegoch
በእንተ ዲያስፖራ
(በእውቀቱ ስዩም)
ዲያስፖራ አይደለሁም፤ተመላላሽ ነኝ፤ “ ሲራራ “ የሚለው መጠርያ ይገልፀኛል::
እኔ እንደታዘብኩት ፤ዲያስፖራ ሁሉ አንድ አይነት አይደለም፤ መአት አይነት
ዲያስፖራ አለ! ለዛሬ ዋና ዋናዎቹን ላስታዋውቃችሁ !
የመጀመርያው ክፍል አድፋጭ ዲያስፖራ ነው፤ አሳምሮ የተማረ፤ ዘናጭ ስራ
ያለው፤ ፖለቲካን የሚያውቅ ግን በፖለቲካ ውስጥ መሳተፍ ውቃቤው
የማይፈቅድለት ! ወይ በእምየ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ተስፋ የቆረጠ ! የራሱን እና
ያገር ቤት ዘመዶቹን ኑሮ ከማቃናት የዘለለ አላማ የለውም ፤ ሰልፍ ላይ
ብትጠሪው አይመጣልሽም ! አበሻ ሬስቶራንት ብዙ አይታይም! እንጀራ ሲያምረው
ተራርቆ ያዝዛል ! ደፋሮች መድረክ ላይ አንፈራጥጠው ፤ ማይክ አንቀው ሲቀደዱ
ጥግ ይዞ እያየ ይስቃል፤ወይም ያሽሟጥጣል ! ለትምርት ቤት ፤ ለላይብራሪ
ወይም ለመጠጥ ውሃ ማሰርያ ካልሆነ በቀር መዋጮ አይሳተፍም ! ቁጥሩ ብዙ
ነው፤ግን በቀላሉ አይታይም!
ሁለተኛው መደብ የቱግ ቱግ መደብ ልንለው እንችላለን ! አልተማረም ! ወይ
ተምሮም ትምርት አልዘለቀውም! ግንባሩ ላይ ነጥሮ ተመልሷል! እድል፤
ከውልደት ወደ ስደት በቀጥታ የገፈተረችው ነው ! አዲሳባን እንኳን በቅጡ
አያውቅም! ፤ በቀጥታ ከይፋትና ጥሙጋ ወይም ከጭላሎ አሜሪካ ወይም
አውሮፓ የገባ ሊሆን ይችላል ! ከሩቢላ እንደወረደ የሰፈሩ ሰዎች ወይም ዘመዶቹ
ይቀበሉታል፤ እዛው ሰፈራቸው ውስጥ ማደርያ ይፈልጉለታል፤ ከዛ እዛው ሰፈሩ
ውስጥ ሲጥር ሲግር ኖሮ አርጅቶ ይሞታል! ሰፊውንና ውስብስቡን የኢትዮጵያ
ማህበረሰብ የማወቅ እድል አልነበረውም ! ስለዚህ ስለሌላው ህብረተሰብ
ያለው እውቀት ካሉባልታና ከሚድያዎች ቀደዳ የተቃረመ ነው !
በኑሮ ቺስታ ሊሆን ይችላል! ቤቱ ገብቶ “ ምን ይዤ ልመለስ ወደ ናቴ ቤት “
የሚለውን በድብቅ ያንጎራጉራል! አገሩ መግባት እንደማይችል ስለሚያውቅ አገር
ቤት ያለውን ሰው ሲያስብ ደሙ ይፈላል! አገር ቤት ያለው ሰው ድርሻውን
የወሰደበት ይመስለዋል! ፤ከእሱ ቡድን ውጭ ያለውን ከማርስ እንደወረደ እንግዳ
ፍጡር ይመለከታል ! የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ስትጠራው ሁለት ሰአት ቀድሞ
ይደርሳል፤ ! ባንዲራ በየአይነቱ- በጨርቅ መልክ፤ በፈሳሽ መልክ ሳይቀር
ሊኖረው ይችላል! ኑሮው እሮሮ አንደበቱ ተናዳፊ ነው! ዲያስፖራ ከሚባል”
ዳሞትራ “ ቢባል በደንብ ይገልፀዋል!
ብዙ ጊዜ ሚድያዎችን የሚያጣብበው በዚህ ምድብ ውስጥ ያለው ነው !
እንግዲህ ሁኔታውን አይተህ፤ ፍረድበት ፤ወረድበት፤ ወይም እዘንለት!
ምራቂ፤
ያገር ቤት ነዋሪ በዲያስፖራ ሲናደድ “ እዛ በርገርህን እየገመጥህ እኛን
ታፋጀናለህ ይላል! የማፋጀቱን ምንጭ ከላይ ጠቅሻለሁ:: አሁን የበርገሩን ነገር
ልናገር!
ብዙ ተመላልሻለሁ ! በርገር የሚበላ ዲያስፖራ አንድ ቀን አይቸ አላውቅም፤
እንዲያውም ከዲሲ ከቶሮንቶና ከአምስተርዳም በላይ በርገር የምትቀለብ ከተማ
ብትኖር አዲሳባ ናት
ኮረና ጭር ሳያደርጋቸው በፊት፤ ውሃ ልማት ፤ ቦሌ መድሀኒያለም እና ገርጂ
ውስጥ የተከፈቱ ቀያይ በርገር ቤቶች በደንበኛ ተጨናንቀው ጠጠር መጣያ
እንኳን አልነበራቸውም ! ዲያስፖራው ግን እንጀራን በያይነቱ አማርጦ የሚበላበት
ገበያ ዘርግቷል ! አበሻ እንደ ልብ በማይገኝበት ከተማ የተቀረቀርን ሰዎች እንኳን
ቢያንስ በወር አንዴ አገር አቆራርጠን ሄደን እንቀምሳለን!
ሚኒስቶታ ውስጥ አቶ ገረመውንና ኦቦ ጋሩማ በፖለቲካ ምክንያት ሊደባደቡ
ይችላሉ! ዲላ ሬስቶራንት ውስጥ ስታገኛቸው ግን አንድ ናቸው ! ሁለቱም የጤፍ
ምርኮኞች ናቸው ! ሁሉን አሰባሳቢ ባንዲራ ካለ እንጀራ መሆን አለበት !

@wegoch
@wegoch
@paappii
Forwarded from ቅንድል ኢትዮጵያ (Ermiyas Dejene)
#ቅንነት_ድል_ያደርጋል!

ቅንነት ይነገራል ፣ ቅኖች ይመሰገናሉ ፣ ምክንያታዊ ዳሰሳዎች በሀገርና በአለም ትዕይንቶች ላይ ይቀርባሉ፡፡
መነሻችንም መድረሻችንም ቅንነትን ያነገበ በምክንያታዊነት የሚመራ በሀገር ፍቅር የተሞላ ትውልድ ማፍራት ነው፡፡

# ቅንድል_ኢትዮጲያ

https://bit.ly/3f3uU57
Forwarded from ቅንድል ኢትዮጵያ (Ermiyas Dejene)
ቅንድል_መፅሔት_ቅፅ_2_ቁጥር_3_KendelM_edited70.pdf
6.2 MB
#ቅንድል _ዲጂታል_መፅሔት

★ቅፅ-፪ ቁጥር-፫

ወቅታዊና ትኩስ እውነቶች በሀገሬ ዐምድ

አጃኢብ ያስባለው የሀይማኖት አባት

ኢትዮጲያዊ ቅኖች ይመሰገኑበታል፡፡

አሸላሚ ጥያቄዏች የተካተቱበት

ያንብቡትና ብዙ ያትርፉበት


የበፊት ዕትሞችን ለማግኘት ይሄን ይጫኑ
2024/09/24 19:28:51
Back to Top
HTML Embed Code: