Telegram Web Link
በዚህ አዝግሙልኝ

''ባህላዊ ምሽት'' የተሰኘ ፁኹፍ ላንብብላቹማ
ሌሊሳ ግርማ ነው ፀሃፊው
ክፍል ፩
አቅራቢ:- @Mykey21

@Wegoch
@Wegoch
@Wegoch
#የእሳት ላይ ቁጥሮች

       ክፍል - ፫

ከተዘጉት በሮች ውስጥ ብዙ ጩኸቶች እየተሰሙ ነው ሁሉም በአንድ ነገር ተስማምተዋል የመጡበት ነገር አደለም ለሀገራቸው ለማንም እንደማይጠቅም ተረድተዋል
ከዚ በፊትም አፋኙን መንግስት ያውቁታል
 ተስፋ ቆርጦ በዝምታ ከዝምታ ገዳም የገባ አለ
እጁን ዘርግቶ ልመናውን ወደ ላይ አድርጓል
ከተዘጋው በር ውስጥ አነስተኛ የምሁራን በአት የገዳም ኑሮ መስሏል
የዘጉ ምሁራኖች በፀሎት ላይ ናቸው
ቀናቶች እየተቆጠሩ ሄዱ....
አሁን በናጋዚ ሰማይ ምንም አይነት ጩኸት የለም የዝምታ ሰማይ ከምሁራኑ ፀሎት ጋር ተደምሮ ናጋዚ የምሁራኖች ገዳም ተብሎ መሰየም ነው የቀረው
ከናጋዚ ሰማይ ውጪ የቤተሰቦቻቸውም ዝምታ በርትቷል የመገናኛ ብዙሀኖቹም በደረሳቸው ከባድ ማስጠንቀቂያ የማናቸውንም ቤተሰቦች መቀበል አቁመዋል
ቤተሰብም ከበአቱ ተቀላቅሎ ከቤቱ አነስተኛ ገዳም ገድሟል
እጁን ዘርግቶ ለጠፉበት ሰዎች ፍለጋውን ለአምላክ ሰቷል
በናጋዚ የምሁራን ገዳም ለቤተሰብ ይፀለያል በቤቱ የገደመው ልጄን ባይ ቤተሰብ ለልጁ ይጸልያል
የሁለት ስጋዎች ወግ ከአንድ የመንፈስ ገዳም ተገናኝቷል
እራሳችሁን ለትልቅ ነገር አዘጁ ለመጨረሻ ጊዜ የሰሙት ድምፅ ከጆሮአቸው ያቃጭላል ያ ትልቅ ነገር መጨረሻው ሞት እንደሆነ ተረድተዋል
ሁሉም አንድ ነገር ይጠብቃል ምክንያቱን ለመስማት ጓጉቷል ቋምጧል ተጨንቋል ተጠቧል
በናጋዚ ሰማይ ነገሮች የተለመዱ ይመስላሉ
ከገዳምያኑ ፀሎት ቀጥሎ በትልቅ ፀጥታ ውስጥ ትልቅ ነገር እየተነደፈ ነው
ዘቦቹ የሚያስፈልጋቸውን እየጠየቁ ከበአቱ ላሉ ምሁራን ያቀብላሉ
ግማሹ መጽሀፍ ቅዱስ ግማሹ መዝሙረ ዳዊቱን ግማሹ ዝምታው ሲውጠው ማስተንፈሻ ወረቀት መጽሀፍት
የሁሉም ተመሳሳይ ጥያቄ ፂም መላጫና እስኪርፒቶ ሆኑአል
ከሚቀርብላቸው ምግብ ጀርባ የሚሰጣቸውን ሹካና ማንኪያ መመለስ ካቆሙ ሰንበት በት ብለዋል
ፀሎታቸው ሰመረ መሰል የዘቦቹ ልቦና ተሰውሯል አስተዋይ በሌለበት አለም የነጋዚ ገዳማውየን በጥልቅ ዝምታ ትልቅ ነገር አስበዋል
አፋቸውን ከፍተው የተቀበሏቸው በሮች መቼ ሰተት ብለው እንደሚከፈቱ ናፍቀዋል
የተኙበትን አልጋዎች ብረት ፈታተዋል ከወለል እያደሩ ለአላማቸው ቁመዋል
ከፀሎቱ ቀጥሎ በሚገናኙበት ግንብ  ባለው ሽንቁር መልእክት ያስተላልፋሉ ሁሉም ለሚጠብቁት ቀን ተዘጋጅተዋል ሳይተዋወቁ በመንፈስ አንድ ሆነዋል በወኔ ተሞልተዋል
ዛሬ ቀናቸው ትመስላለች የቁርስ ስነ ስርአት እንዳለቀ የተዘጉት በሮች ሰተት ብለው ተከፈቱ
ከልብሶቻቸው ውሰጥ ብዙ ነገሮች ተከማችተዋል አንድ ነገር እየጠበቁ ነው በገደሙበት አለም ከአምላክ አንድ ነገር የተላከላቸው እስኪመስል ድረስ በራስ መተማመናቸው ጨምሯል ቀስ እያሉ ከበሮቻቸው ወደ ነጩ አዳራሽ ተመሙ
ዛሬ እንደ ቀድሞ ጩኸት የለም ሁሉም በትኩረት ሚደረገውን እየተመለከቱ ነው
የናጋዚ ዘቦች ከማማው ቦታቸውን ይዘዋል ሁለት አልሞ ተኳሾች ከማማው በላይ ተሰድረዋል
አይኖች ወዲያ ወዲያ ይላሉ የዝምታ ንግግሮች በሁሉም ጆሮዎች ገብተዋል
ከመላእክት የመጣው የማምለጫ ስልት ዛሬ ሊተገበር ከጫፍ ደርሷል
ከገደሙበት አለም መልስ ስለተላከላቸው ዛሬ ደሞ ነፍስ የማዳን የጀግና ተልእኮ ውስጥ ገብተዋል
ከምሁርነት ወደ ብህትውና ከብትህውና ወደ ጦር ዘመቻ ለመግባት አሰፍስፈዋል
ልጄን ስትል የነበረችው ሴት ዛሬ ልጇን ለማቀፍ የሚያስችላትን ነገር ለማድረግ ወስናለች
ያ እንባ ዛሬ የለም ወኔዋ ልቧን ሞልቶ ሊፈነዳ ደቂቃዎች ቀርተውታል
ሁሉም በአንድ ልብ
በስጋ መሪ የሌለበት ጦርነት በመንፈስ ግን መሪው ሲለምኑት የነበረው አምላካቸው እንደቆመላቸው አምነው ተዘጋጅተዋል
      ሰላም የሀገሬ ልጆች ትኩረታቸው ከድምጽ ማጉያው ላይ ተተከለ የባለፈዋ ሴት ደግማ መታለች
       እንዴት ከረማችሁ  መልስ የለም
ዛሬ ለምን ሁላችን ከዚ ከናጋዚ እንደተገናኘን እንነጋገራለን
ትልቁ አላማ ዛሬ ግልፅ ይደረግላቸዋል መልሳ ድምጿ እስከወዲያኛው ሄደ
የናጋዚ ገዳማውያን ለመጨረሻ ጊዜ ይሆናል ይሄን ድምፅ የሚሰሙት
     ሰአቱ ደርሷል.......
ሹካዎች የመመገቢያ ሳህኖች ከፂም መላጫ ውስጥ የወጡ በብዕር ላይ የታሰሩ ምላጮች
ከአልጋ የተነቀሉ ጠንካራ ብረቶች ከሁሉም በላይ በመሪያቸው ላይ ያላቸው እምነትን ይዘው ተዘጋጅተዋል
አዎ ሰአቱ እየተሽከረከረ ነው የሞት ትግል ሽረት በናጋዚ ሰማይ...

      ብላቴናው በእሳት ገፆች ላይ
    
@wegoch
@wegoch
@wegoch
ሰከን ብላ ከዋለችው ቅዳሜ ለምሽታችኹ ትኾን ዘንድ ይቺን ስሙማ!

''ባህላዊ ምሽት'' የተሰኘ ፁኹፍ ላንብብላቹ
ክፍል ፪
ሌሊሳ ግርማ ነው ፀሃፊው
@Mykey21

@Wegoch
@Wegoch
@Wegoch
Audio
የሶስተ ሲኖትራክ ወገ
#እሱባለው_የኔነህ

@wegoch
@wegoch
#የእሳት ላይ ቁጥሮች
 
     ክፍል - ፬

ከድምፅ ማጉያው መታ ከጠፋችው ሴት በሁዋላ ሁሉም አይኖቹን ወደ በሩ አማትሯል በሮች ሊውጧቸው እንዳልተዘጋጁ ባለመከፈታቸው ፍንጭ ሰጡ ዘቦቹም ከማማው ላይ አልተንቀሳቀሱም ቀጣይ ነገር እንዳለ ተረድተዋል
የጠቢብ ቅኔው ዝምታው ነው በዝምታ ሁሉን በአይኖቻቸው እየተከታተሉ  ነው
  ሰላም ውድ የሀገሬ ልጆች እንኳን ወደ ናጋዚ በሰላም መጣችሁ ጎርነን ያለ የወንድ ደምፅ ተሰማ
ቆይታችሁ ጥሩ እንደሆነ አልጠራጠርም አወራሩ የቀልድ ንግግር እንጂ ለቁም ነገር የመጣ አይመስልም
አሁን እዚ ምን እንዳገናኘን ለምን እንደተገናኘን ምነግራችሁ ይሆናል
የናጋዚ ድርጅት የኢትዮጵያ የመጪው ተስፋ ለልጅቿ ለህዝቧ ለወደፊት እጣዋ ለወደቀው ጥበቧ ለተራበው ህዝቧ መዳኒት ለሚሻው ህመምተኛዋ ለሰላሟ ትልቅ አሻራ ለመጣል የተቋቋመ ድርጅት ነው
እናንተም ለመጪዋ ኢትዮጵየያ የየራሳችሁን አሻራ እንድታስቀምጡ ነው ወደዚ የመጣችሁት ከዚች ቀን ጀምሮ ሁላችሁም በየድርሻችሁ በናጋዚ ስር ሆናችሁ ታገለግላላችሁ ማለት ነው
አጥንታችሁን ከስክሳችሁ ደማችሁንም ቢሆን አፍሳችሁ ላብችሁን አንጠፍጥፋችሁ ኢትዮጵያን አንድ እርምጃ ከፍ የማድረግ ሀላፊነት በእናንተ ላይ ተጥሏል
 በእናንተ ዋጋ የኢትዮጵያ ህዝብ እጁን ወደ ላይ በተስፋ ብቻ መዘርጋት አቆሙ ወደ ናጋዚ ይዘረጋል ተስፋ ብቻ አሳይተንም አንነሳውም የጠየቀውን ስለምንሰጥ እናንተም ሀሳብ አይግባችሁ እዛ መጸሀፍ አሳትማችሁ ሸጣችሁ በተራ ሆስፒታል የማይደን  በሽተኛ ከሚያደክማችሁ በምታስተምሩበት የማይገባው ከሚያደነቁራችሁ እዚ ሆናችሁ ሁሉንም ብታደርጉ ነው ሚሻላችሁ እዛ ከምትለቃቅሙት ገንዘብ በላይ እዚ ሆናችሁ ብዙ ነገሮች ታገኛላችሁ ከእንግዲህ ጀምሮ ለራስ መኖር አቁማችሁ ለሀገርና ለወገን ስለምትኖሩ እኛ ደሞ ለቤተሰቦቻችሁ ትልቅ ነገር እናደርግላቸዋለን እንከባከባቸዋለን የምፀት ሳቅ ከድምፅ ሚጉያው ተሰማ ድምፁም ወዲያ ተቋረጠ
የንግግሩ ነገር እንዳለቀ ከማማው ላይ ደረጃዎቹን እየደሰቁ ዘቦቹ መውረድ ጀመሩ ሰአቱ መድረሱን ልቦናቸው ነገራቸው ሁሉም እርስ በእርስ ተያየ
የማምለጥ ሰአት ደርሳለችና የሞት ሽረት ትግል ለማድረግ ተዘጋጁ
የእስከ ዛሬው የናጋዚ የምሁራን ገዳም ሱባኤ ዛሬ መልስ ያገኛል
ሁሉም ተስፋውን በለመነው አምላክ ላይ አድርጓል ሀይሉንም በሹካዎች በምላጮቹ በተገነጠሉት ብረቶች ላይ እንዲሆን ተማፅኗል
ሀገር በማቅናት የተልፈሰፈሰ እጅ ዛሬ ሲቀለብ ከኖረ ፈርጣማ ጋ ሊጋጭ ነው
በሮቹም እንደተለመዱት ሰተት ብለው ለመዋጥ አፎቻቸውን ከፈቱ
ዘቦቹ በማማው እስኪወርዱ ምሁራኑ ሁለት ሁለት ሆነው ተጠባብቀው ቆሙ
ቀጥል አለ ቀድሞ ወደ አዳራሹ የወረደው የናጋዚ ዘብ
ከፊቱ የሚገኘውን አንዱን ገፍተር እያደረገ
በመቅፅበት  ከሰውነቱ መዞ ያወታውን ሹካ በአይኖቹ ትክክል ሰካቸው
የጦርነቱ ማብሰሪያ ጩኸት በዘቡ እሪታ ተጀመረ
ከየት መጣ ሰይባል ዘቦቹ ላይ ጥቃት መፈፀም ተጀመረ
በያዙት ምላጭ አንገቶቻቸውን ይተለትሉ ጀመር ለመመገቢያ በተሰጣቸው ሹካ አይኖቻቸውን ይጠነቁሉ ገቡ ከአልጋው ባወረዱት ብረት የዶመዶመው ጭንቅላታቸው ላይ ማሳረፍ ቀጠሉ ዘቦቹም የዋዛ አደሉም ከማማው ያሉት ተኳሾች በፍጥነት መልስ ሰጡ በኢላማቸው የገባውን ምሁር ይለቅሙ ጀመር ጊዜው ስላልነበር እንጂ ለምሁራኖቹ የተዘጋጁ ነፍሰ በላዎች ነበሩ በትንቅንቁ ፈተና የሆነባቸው ምሁራኖቸቹን ለቅሞ መጣል ነበር
ጠመኔ የያዘ እጅ ዛሬ ስለት ይዞ ነፃነቱን የቀማውን ሰው ይተለትል ጀምሯል በጠመኔ ብናኝ የነጣው እጅ ዛሬ በደም ተጨማልቋል
በብዕር ቀለም ጠቅሶ ስንቱን እንዳልፃፈ ዛሬ በስለት ደም እየጠቀሰ ከመሬት ይጥል ጀምሯል
በጥይት እየተበሳሱ የሚወድቁ ምሁራን እየበዙ መጡ
አልሞ ተኳሾቹ መሳሪያውን ያንጣጡት ጀመር
ይተጋተጉት ገቡ
በጀርባው እየወደቀ በደረቱ እየተሳበ የሞት ትግል ሽረት ማድረጉ አልቆመም
ተኳሾቹ ያልጠበቁት ዱብዳ ስለወረደባቸው የራሳቸውንም ሰዎች ይልጡ ገቡ
ከዘቦቹ የተረፉት ወደ ማማው አመሩ አንዱን ተኳሽ ጉሮሮውን ቀደው ጣሉት
የናጋዚ ሰማይ የጦርነት ሜዳ ሆነ ብዙ ምሁራኖች ከመሬት ወድቀዋል የከፈሉት ውለታ ሳይመለስ በሞት ብድራቸው ተከፍሏል
ሌላኛውን ተኳሽ ዘለው ሰፈሩበት በያዘው ስናይፐር ከአፈር ደባለቁት መፅሀፍ ይዞ እድሜውን የጨረሰ ምሁር ዛሬ ለነፃነቱ ስናይፐሩን ታጥቋል
ከረፈደ የደረሱ ይመስላሉ የሚያቃስት ደምፅ ፊቱ የተተለተለ ለሞት የሚያጣር ድምፅ ከልቡ በገባው ጥይት እስትንፋስ ያቆመ እሬሳ ነጩ አዳራሽ በደም ተሞልቷል 7 ምሁራን ብቻ በህይወት መትረፍ ቻሉ በህይወት ያሉትን ዘቦች ከተኳሾቹ በቀሙት ስናይፐር ወደ ሞት መላክ ጀመሩ 
በፀሎት የተላከው የማምለጫ ስልት ለ7 ሰዎች ብቻ ሰርቷል ከሁሉ በላይ የፀለዩት እነሱ ናቸው መሰል
በደም የተጨማለቀ ሰውነታቸውን ይዘው የተዘጋውን በር በያዙት መሳሪያ እየከፈቱ መውጣት ጀመሩ ከሰባቱ ሰዎች ልጄ ስትል የነበረችው ሴት እግሯን ተመታ በአንድ ወጣት ተደግፋ እያፈገፈገች ነው     ተርፋለች
ዞሮ ማየት የለም የናጋዚ ሰማይ በሞት መልአኮች ተከቧል ወደሱ የገባ አፈፍ እየተደረገ ይወሰዳል
የዘቦቹ ደም ከምሁራኖቹ ደም ጋ ተቀላቅሎ አንድ ነን የሚል ምልክት የሰራ ይመስላል
በጦርነት የተጀመረ ልዩነት በሞት አንድ ሆኗል...

       ብላቴናው በእሳት ገፆች ላይ

@wegoch
@wegoch
@wegoch
#ወግ_ብቻ
.
..........በድሮ ጊዜ አንድ አግኝቶ ያጣ ባለፀጋ ሰውዬ በአገሪቱ አሉ የተባሉ ባለሀብት ሰው ጋር ይሄድና

"ጌታዬ አግኝቼ ያጣው ነኝ፤ በደጉ ዘመን ከቤቴ ምንም ጠፍቶ አያውቅም፡፡ አሁን ክፉ ዘመን መጣና ከነቤተሰቤ የምልሰው የምቀምሰው አጣው ይርዱኝ" አላቸው፡፡

ባለጠጋው ሰውም እውነት አግኝተክ ያጣህ ከሆነ ይሄን ጥያቄ መልስ "ከዶሮ ብልቶች የሚጣፍጠው የቱ ነው?" አሉት፡፡

ነዳያኑም "ቆዳዋ" አለ፡፡

ባለጠጋውም "እውነትም አግኝተክ ያጣክ ነህ፤ በሉ ከእህሉ ስፈሩለት፤ ከከብቶቹም የሚበቃውን ያህል ስጡት ብሎ አሰናበተው፡፡

ይህ ሰው ወደ ቀየው ሲመለስ አንድ ወዳጁ ይሄን ሁላ ሀብት ከየት እንዳገኘ ይጠይቀዋል፡፡ ተመፅዋቹም ሁሉን ነገር ነገረው፡፡ ከዛ ባልንጀራው እንደሱ ሀብት ለመቀበል ወደ ባለጠጋው ሰው ሄደ፡፡

እዛም እንደደረሰ "ጌታዬ አግኝቼ ያጣው ነኝ፤ በደጉ ዘመን ከቤቴ ምንም ጠፍቶ አያውቅም፡፡ አሁን ክፉ ዘመን መጣና ከነቤተሰቤ የምልሰው የምቀምሰው አጣው ይርዱኝ" አላቸው፡፡


ባለጠጋው ሰውም እውነት አግኝተክ ያጣህ ከሆነ ይሄን ጥያቄ መልስ "ከበሬ ብልቶች የሚጣፍጠው የቱ ነው?" አሉት፡፡

ነዳያኑም "ቆዳው" አለ፡፡

ባለጠጋውም አንተ አጭበርባሪ ነክ ብሎ በባዶ ሰደደው፡፡

የፈለገ ብንቸገር መዋሸት ግን አይሆኑ ውድቀት ላይ ይጥለናል፡፡
#ሰናይ_ቀን_ና_ሌሊት
@wegoch
@wegoch
#ወግ_ብቻ
ፍርፋሪ ታሪክ
¤¤¤¤¤¤¤
"ከጅምሩ ማን ፍጠር አለህ እንዲህ ያለ ነገር?ይሄ ነው ፍርድህ? ዛሬስ አትወርድም፣አትጽፍም ከግንባሩ ላይ ኃጢያቱን የሚያጽፍ ድፍን የቆዬ ጎረምሳ ተሰልፏል..."
"ተው አርዮስ! ተው! ከፈጣሪ አትጋፋ!...አዋቂ ነው...ተው"
"ድንቄም አዋቂ! ሲታወቅ እንዲህ ከሆነ እውቀት በአፍንጫዬ ይውጣ።አይገርምህም!"
"ለአንዲት ጋለሞታ ፈጣሪህን...ትክዳለህን!"

"ጋለሞታ? ጋለሞታ አልህ?...የት አየህ ስትዘሙት?...የት?...አዘሟች ከሌለ ዘማዊት ትፈጠር ይመስል።እንደወይራ፣እንደቀጋ አትበቅል ዘማዊት..."
"ይወራል።...ድፍን መቂ እሱኑ ነው የሚያወራው"
"እና አመንህ አንተ?"
"ምን አማራጭ ይኖራል? ሰው ተኩኖ።...ሁሉ አምኗል እኔ ማነኝና ሰው ያመነውን አላምን የምለው?"
"አልገባኝም?"
"አይገባህም።አንተ ብቻ ከሰው፣ከቀየው ተነጥለህ፣ለዘማዊት ሴት ጥብቅና የሚያስቆምህ ነገር።ብቻህን ከአድባር ትጋጫለህ?...ሴት ጠፋ?ከሸርሙጣ?"
"ዝም በል አንተ!!...ምፅዋ ሸርሙጣ አይደለችም።"
"ነች!"
"አይደለችም! ምፅዋ ሸ...ር...ሙ...ጣ... አይደለችም!! ትሰማኛለህ...አንተ ካላባለግኃት አንዲት ምስኪን ሯጭ ከመሬት ተነስታ ሸርሙጣ አትሆንም።"
"ትጠረጥረኛለህ?"
"አላምንህም"
"አሕመድንስ ትጠረጥራለህ? ከእርሳቸው አፍ ነው ቀድሜ የሰማሁት።"
"እሳቸው ቅዱስ ገብርኤል ናቸው? የማልጠረጥራቸው?"
"እና እርሳቸውንም ጠርጥረህ?"
"እንክት! ምፅዋዬ እኮ ናት!"
"በል ወግድልኝ ልሂድበት መንገዴን!እውነትም አሪወስ!...ያሳደጉህ የእናትህ ጡትሽ ሳይሆን ስምህ እንደሆነ ገና ዛሬ ገባኝ!"
"የምን መንገድ?...የሰው መንገድ አበላሽቶ ...ወዴት?"
"የማን መንገድ ተበላሸ? አንተ ኩሩሩ ወግድልኝ!"
"የምፅዋ።የምስኪኗ...በወሬ ገፍታችሁ የጣላችኋት።...ህልሟ መንገዷ አልነበረም? እ!"
"የምን ህልም አላት ደግሞ ሸርሙጣ? ምን ትሰራበታለች ቢኖራትስ?"
"አንተም አለህ አይደል፤አይደል እሷ? ሯጭ ነበረች ታውቃለህ።... አቦ ሸማኔ የሚያሳድድ ፍጥነት ነበራት።...የጥንቸል ሳንባ ምታስተፋ ነበረች ይህን አንተም ታውቃለህ....ምን ያረጋል!"
"ጋለሞቶች።"
"አልገለሞተችም።....አንተ ውሻ እንዳልዘነጥልህ በዚህ ከዘራ!"
"ኧረ በህግ...በህግ አምላክ!...ምን ታረግበት ነው እሱ...ኧረ ኡ!...ኡ!...ኧረ በህግ!..."
"ልጄን!...አይኔን!...በማህፀኗ...እንደያዘች...አስኮበለላችኋት...ምፅዋዬን አሸሻችኋት"
"ተው አሪዎስ!...ተው አንተ ከሐዲ!...ባለውለታህን?"
"የት ብዬ ልፈልጋት እሺ አሁን?...ንገረኝ!...እ!..."
"እንካ ቅመስ ይችን ለምፅዋዬ!!...እ!...ይህችን ደግሞ በማህፀኗ ይዛ ለተሰደደችው ልጄ...እንካ!!"
"ኡ!...ኡ!...ኡ!...ኧረ የሰው ያለህ!!!"
"የት ብዬ ነው የምፈልጋት አሁን?...እ!...ምፅዋዬ...የበኩር ልጄን እናት?"
*
*
*
*
*
*
ዘንባባ
©ምግባር ሲራጅ
ከገፅ 133-134
©ከጥበብ ማረፊያ የቴሌግራም ገፅ
@wegoch
@wegoch
'' ስለ ኀዳር በሽታ ''
(የሐያኛው ክፍለ ዘመን መባቻ ከተሠኘው እና መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ እንደፃፉት)


@Wegoch
@Wegoch
@Wegoch
#የእሳት ላይ ቁጥሮች

   ክፍል - ፭

ከሞት መንጋጋ ጫፍ ያመለጡት ምሁራን እያፈገፈጉ ነው
ሞትን ሰላም ብለውት ሊያቅፋቸው ሲል ነው ለትንሽ ያመለጡት በእውቀት ከድህነት ከላዋቂነት ጋር ይፋጁ የነበሩ ዛሬ ለነፃት ተዋግተው በእድል ተርፈዋል
ከሞት ለአንድ ስንዝር ታክል አምልጠው ወተዋል
የሳምንታቱ ሱባኤ ለሰባቱ ሰዎች ብቻ ነው የሰራው ሌሎቹ መሰዋትነትን ተቀብለው አልፈዋል
በናጋዚ ሰማይ ትተዋቸው በሞት የተለዩአቸውን ጓዶቻቸውን እያሰቡ ማምለጡን ተያይዘውታል
ለምን የሚለው ጥያቄ ሙታኖቹንም ጨምሮ ሰባቱ ሰዎችን አንድ ያደረገ ጥያቄ ሆኑአል
ወደ ሗላ ማየት የለም
 ቁስለኛዋን በየተራ እየተቀባበሉ ይደግፏታል በጣም ውብ ናት ውበቷም ሳይሆን አይቀርም እንዲ እንዲሳሱላት ያደረገው
የሷ ቁስል ከሁሉም ባሰ እንጂ ፊቱ የበለዘ አፍንጫው በዘቦቹ ቡጢ የተሰበረ
ጥርሱ የወለቀ ሰውነቱ የተገሸለጠ አለ
አይዟችሁ እንደርሳለን የአንድ ሰው ድምፅ ብቻ ነው ሚሰማው
ማን የት ከየት ወዴት እንደሚሄድ አያውቅም ከመካከላቸው በእድሜ ከሁሉም ሚበልጡ ሰው መንገዱን ያወቁት ይመስላል በራስ መተማመናቸው ለሁሉም ደስታ ፈጥሯል
ወደ የት እንደሚሄዱ በአባ ተስፋ ስላሴ መሪነት ይነገራቸዋል
አባ ተስፋ ስላሴ በኢትዮጵያ ታዋቂ ሊቅ ናቸው በታሪክ በስነ ፈለገ ትልቅ ቦታ ይሰጣቸዋል ወደ ናጋዚ ሲገቡ አስኬማቸው በዘቦቹ ወድቆ አሁን የክህነት ስልጣናቸውን ለጊዜውም ቢሆን አተዋል
ሁለቱ ወንድማማቾች ዶክተር ናትናኤል ታምሩ እና ደራሲ ዮቶር ታምሩ ከ7 እደለኞች መካከል ናቸው
እግሯን በጥይት ተመታ ደሟን እያዘራች ምታፈገፍገው ፊያሜታ አብርሀም ትባላለች ሚስጥራዊ ምልክቶችን ፈቺ እና ሰአሊ ናት
ጥበበኛው ሰአሊ ስምኦን ካሳሁንም ሰባቱን ተቀላቅሏል የኮምፒውተር ባለሙያው ቢንያም ቃኘው ስር ስራቸውን እየተከተለ ነው
ሁሉም ይተዋወቃሉ በተለያዩ መድረኮች የጥበብ ዝግጅቶች የስነ ፅሁፍ ምሽቶች የስዕል አውደርዮች ላይ ተገናኝተው ያውቃሉ ለዛም ነው እርስ በእርስ በመተማመን በጋራ ማምለጡን የተያያዙት
ከሰባቱ ሰዎች የማይታወቅ አንድ ሰው አለ ሁሉም እርስ በእርስ ይተዋወቃሉ ይሄን ሰው ግን አያውቁትም ኤልያስ ሽመልስ ይባላል በአዲስ አበባ ብዙ ባንኮችንና ድርጅቶችን በመዝረፍ ይታወቃል ስሙን መላ የኢትዮጵያ ህዝብ ከጆሮ አስገብቶታል መልኩን ግን ማንም አያውቀውም
እርሱም ማን ይሁኑ ማን ለምን ከነሱ ጋር አብሮ እንደሚሮጥ እራሱ አያውቀውም
እሩጫው ቀጥሏል ማፈግፈጉ አይሏል
ድካም ውሀ ጥም እረሀብ ...
ሞት ሁሉን ያስረሳቸው ይመስል ምንም ነገር አይሰማቸውም
አባ ተስፋ ስላሴ ከፊት ሆነው ይመራሉ ስድስቱ እድለኞች ይከተላሉ
ካገኙት ወንዝ ውሀ እየተጎነጩ ሳር ቅጠሉን እየበሉ ከሶስት ቀን በሁዋላ ጉዞአቸው ተገታ
ደርሰናል አሉ አባ ተስፋ ስላሴ ማምለጡ ማቆሙንና ዋስታና ያለው ቦታ እንደ ደረሱ ከፊታቸው እየተነበበ
በቆርቆሮ ከታጠረው ጊቢ ውስጥ አንዲት የቆጥ ቤት ትታያለች  ነው ምትታየው
የከብቶች ጩኸት የወፎች ዝማሬ የኩሬ መንፎልፎሎች ብቻ ነው ሚሰማው
ሶስት ቀን ሙሉ በዝምታ ነው ያሳለፉት
አባ ቀድመው ወደ በሩ አመሩ አንዲት ትንሽዬ ልጅ መታ በሩን ከፈተችው የይግቡ ፈገግታ ከፊቷ እየተነበበ
ሁሉም ወደ ግቢው ዘለቁ
ከግቢው ካለው የቆጥ ባሻገር ወደ አምስት የሚጠጉ ቤቶች በግቢው ውስጥ አሉ ከአንደኛው ቤት ሁሉም ተከተቱ
ቁስለኛዋን ከመደብ አስተኟት አባ ለቁስለኛዋ እርዳታ ማድረጊያ ብዙ መሰርያዎችን ይዘው መጡ
ዶክተር ናትናኤል ስራውን በአግባቡ ሰራ ከቁስለኛዋ ባሻገር የራሱን ቁስል ጨምሮ የሁሉንም ቁስሎች አከማቸው
ማምለጣቸውን ሲያረጋግጡ ረሀቡ ጠናባቸው
ትኩስ ወተት ከአንባሻ ጋር ቀረበላቸው
ያጣድፉት ጀመር ቁስለኛዋን ኤልያስ እየመገባት ነው
ትኩረት ሁሉ ወደ አዲሱ ሰው ነው
ስምህን ማን ልበል አለ ደራሲ ዮቶር ለአዲሱ ሰው ጥያቄውን ወረወረለት ከረጅም ጊዜ በሁዋላ ወደ ጆሮ የተወረወረች ድምፅ ተሰማ
ኤልያስ ሽመልስ እባላለሁ ......

      ብላቴናው በእሳት ገፆች ላይ

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ወግ ብቻ pinned a voice message
#የእሳት ላይ ቁጥሮች

  ክፍል - ፮

ስሙን እነደነገራቸው መብረቅ የወረደ ይመስል ሁሉም ደነገጡ ኤልያስ የሚለው ስም ከጆሮአቸው እነደገባ ሚበሉትነ እሀል ትን አስባላቸው
አዎ የሀገሪቱ ዋነኛ ዘራፊ ማፈፍያ ከመካከላቸው መገኘቱ አስደንግጧቸዋል
ዮቶር ከፊቱ ምንም አይነበብትም ታድያ ከእኛ ጋ ለምን ቀላቀሉህ
እሱን እኔም አላውቅም በወተት ያራሰውን አንባሻ ለፊያሜታ እያጎረሳት አይኖቹን ከአይኗ አልነቀለም ብዙ አመት ሚተዋወቁ ነው ሚመስሉት
ሁሉም የቀረበላቸውን አንባሻ በወተቱ እያወራረዱ ስልቅጥ አድርገው በሉ ሶስት ቀን ሙሉ ጠብ ያላለ አንጀት ዛሬ ተንፈስ ብሏል
በሉ ተነሱ ማሳያችሁ ነገር አለ መነጋገርም አለብን ለትልቅ ጉዳይ ታስፈልጉኛላችሁ  አባ ተስፋ ስላሴ ከቤቱ ቀድመው ወተው ቀደ ቆጧ አመሩ ሁሉም ተከተሏቸው ሌባው ኤልያስም ፊያሜታን ተከትሎ ደግፍ ተከተላቸው የቆጧን በር ከፍተው ከፊት ለፊታቸው ያለውን ፍርግርግ ብረት አንሸራተው ከፈቱት
ሁሉም ወደ በሩ ዘለቁ አባ ፍርግርጉን መልሰው ከረቸሙት ሳይተታሰብ ቁልቁል ተምዘገዘገ ከአባ በስተቀር ሁሉም ተደናግጠዋል አይዟችሁ አሉ በአባት አንደበታቸው
የገቡባት ቆጥ ባልተታወቀ ሁኔታ እንደ አሳንሰር ወደ ታች ተምዘግዝጋ ቆመች
ፍርግርጉን አንሸራተው ከፈቱት
ሁሉም ወደ ታች ወረዱ ድቅ ድቅ ጨለማ ውጧቸዋል አባ ከነሱ ነጠል ብለው የሆነ ነገር ሲያንሸራትቱ ጨለማው በደማቅ ብርሀን ተሞላ
ሁሉም የሚያዩትን ማመን አልቻሉም እንዴት ወደ ዚ እንደመጡም ምንም ሚያቁት ነገር የለም
አለም ላይ ብዙ እውቀትን ያሳደዱት ምሁራን እንዲህ ያለ ትልቅ ቤተ መጽሀፍት አይተው አያውቁም ቁስለኛዋ ህመሟን እረስታ በምታየው ነገር እየተደመመች ነው ሌባውም ምን ጉድ ነው ብሏል ሌሎችም እንደዛው
በትላልቅ ምሰሶዎች ላይ ከተሰሩት መደርደሪያዎች ላይ የታሪክ የስነ ፈለግ የህክምና የሳይኮሎጂ የሀይማኖት የመዳኒት ቅመማ የቴክኖሎጂ የመሳሰሉት በየዘርፉ ተሰንደው ተቀምጠዋል ከማማው ላይ ያሉትን ለማውረድ ትላልቅ መሳላሎች ቦታ ቦታ ይዘዋል
አፋቸውን ይዘው እያልጎመጎሙ  አንገቶቻቸወን እየሽከረከሩ አይኖቻቸውን እያርገበገቡ ወደ አዳራሹ መጠጋት ጀመሩ
ከሰፊው አዳራሽ መሀላ ላይ ካለው ትልቅ ግርግዳ ላይ #ሻርማይክ የሚል ፅሁፍ በሮዝ አበባ ላይ ተስሎ ይታያል
ሁለቱ ሰአልያን ከመፅፀፍቶቹ በላይ የስዕሉ አሳሳል መስጦ አስገርሟቸዋል
በዚ አዳራሽ ከገባንበት ጨለማ እንወጣለን ከጨለማው ያስገቡንን እኛ ወደ ጨለማ እንከታቸዋለን
እንኳን ደህና መጣችሁ አባ ተስፋ ስላሴ ደስ የሚል ፈገግታ ለገሷቸው
ውሎ እያደር ሁሉም ተግባቡ ቁስለኛዋም ቁስሏ ደርቋል ሰባቱም ውሎ አዳራቸውን ከመሬቱ ስር ካለው ቤተ መፅሀፍት አድርገዋል
ሌባውም አመሉ ለቆት ከመፅሀፍት እውቀት መስረቅ ጀምሯል
ሰባቱ እድለኞች ከመሬት ስር ካለው ቤተ መፅሀፍት ትልቅ ሀሳብ እያሳቡ ነው መንግስት በነሱና በተሰዉት ምሁራን ላይ ያደረሰውን በደል ዋጋ ለማስከፈል ተዘጋጅተዋል
የቤተሰቦቻቸውን ናፍቆት ዋጥ አርገው ለአላማቸው ቆመዋል
የሀገራቸውን ልዩ ልዩ ቅርሶች ከመንግስት እጅ እየነጠቁ ተቋሙን ወና ለማስቀረት ወስነዋል
ከቱሪዝም ሚመጣውን ገንዘብ በአፍንጫው ይውጣ ብለው ካዝናውን ለማራቆቶ ተዘጋጅተዋል
ከአንድ አመቱ ትውስታ ሁሉም ተመልሰዋል......
ያለፈውን አንድ አመት የሆኑትን እያስታወሱ ከሬዲዮ በሰሙት ዜና እየተዝናኑ ነው
ከጠረጴዛው ላይ ያለችውን ሬዲዮ ፊያሜታ ጠረቀመቻት የእግሯ ጠበሳ ቦታውን እንደያዘ ነው ህመሟን የልጇን ናፍቆተት እያሰበች ታዝናለች   ሌሎቹም እንደዛው
እሳቱ ፍም ሆኖ ቅዝቃዜውን እያመጣው ነው
የሻርማይክ ቡድን አባላት ከፍሙ ስር ሆነው የአንድ አመት ትውስታቸውን መልሰው እየቃኙት ነው ቀጣይ ለታሰበለት ትልቅ እቅድ ሁሉም ቆርጠው ተነስተዋል
አባ ተስፋ ስላሴ የእያንዳንዱ ቅርስ መገኛ ቦታ እና ምንነት በመንገር የስድስቱንም ህይወት በማትረፍ እንደመሪነ ይቆጠራሉ
ሴቷ ጠቢብ ፊያሜታ አብርሀም የእያንዳንዱን ድርጅት የቤት ካርታ ንድፍ በማውጣት የማምለጫ እና የመውጫ በሮችን ትጠቁማለች
ሰአሊው ስምኦን ካሳሁን እስከዛሬ የተሰረቁትን ውድ ስዕሎች ተመሳሳይ እየሳለ ትልቅ የማጭበርበር ስራ በመንግስት ተቋማት ላይ ይሰራል
ሁለቱ ወንድማማቾች ኢላማ የተደረጉትን ድርጅቶች በመሄድ በ የደህንነት ካሜራዎችን የደህንነት መቆጣጠሪያ መሳሪያዎች የተጠመዱ አላምሮች ጨረሮችን ፈልፍለው በማወቅ ትልቅ ሚና ይጫወታሉ
የኮምፒውተር ባለሙያው ቢንያም ቃኘው የደህንነት ካሜራዎችን የተለያዩ መሳሪያዎች የባለስልጣናት ስልኮችን በመጥለፍ ጥበቃውን ያፀዳዋል
ኤልያስ ሽመልስ ወደ ተመረጡት ቦታዎች በመሄድ ያካበተውን የዝርፊያ ችሎታ በመጠቀም የኢላማውን መጨረሻ ያሳምረዋል
ሰባቱም ድርሻቸው ትልቅ ነው
የሚቀጥለው ኢላማ ምደነው ፊያሜታ ጥያቄዋን ወረወረች.....

      ብላቴናው በእሳት ገፆች ላይ

@Wegoch
@wegoch
@wegoch
#የእሳት ላይ ቁጥሮች

  ክፍል - ፯

በፊያሜታ ጥያቄ ሁሉም የተስማሙ ይመስላሉ ከእሳቱ ፊት ለፊት ወደ ተቀመጡት አባ ተስፋ ስላሴ አይኖቻቸውን ላኩ
ረጋ ብለው የነበሩት አባ ቡዙም ማሰብ አልፈለጉም
ይበቃናል .. ደገፍ ካሉበት ወንበር ወረድ ብለው እጆቻቸውን ጉልበታቸው ላይ ጣል አደረጉ
ምኑ ነው ሚበቃው መነፅሮቹን እያስተካከለ ቢንያም ጠየቀ
ከእንግዲህ በዚ መሸገግ ይበቃናል ንፁህ ብርሀን የቤተሰቦቻችን ፍቅር ያስፈልገናል ስለዚህ ሁላችንም ወደየ ቤተሰቦቻችን መመለስ አለብን
ማንም አልተቃወማቸውም ሁሉም በሀሳባቸው የተስማሙ ይመስላሉ
ቆይ ያቺ ደግ እናትህ አልናፈቀችህም ባንተ ናፍቆት ስትጎሳቆል አታሳዝንህም የአባ ንግግር የቢንያም አይኖችን ጠንቁለው ገብተው እንባ አስቀረሩት
እናንተስ አባታችሁን ማየት አትፈልጉም ለሁለቱ ወንድማማቾች ጥያቄያቸውን ወረወሩ ሁለቱም እርስ በእርስ በአይኖቻቸው ተያዩ
አንተስ ሰአሊው ከውድ ባለቤትህ እና ከልጆችህ ጋ ተመልሰህ መኖር አልፈለክም
ፊያሜታ አንቺስ ካለ አባት የሚያድገው ውብ ልጅሽ አልናፈቀሽም አቅፈሽ ግንባሩም ለመሳም አልጓጓሽም
አንተስ ከበፊቱ የተሻለ ህይወት የእርጋታ ኑር ቤተሰብ መስርተህ መኖር አልፈለከም ኤልያስ ከአባ ይህን ቃል እንደሰማ አይኖቹን ወደ ፊያሜታ ላካቸው
በፍቅሯ የወደቀው ገና እግሯን ተመታ ከእቅፉ የገባች ግዜ ነው ውበቷ አሳስሮ ይዞታል ብልሀቷ ቅልጥፍናዋ ሴትነቷ ገዝቶታል እሷም ለሱ ደስ የሚል ስሜት አላት ሁሌ ባከናወኑት ስራ ሲደሰቱ አብረው ከጨለማው ገብተው ያወጋሉ ይጫወታሉ ከእቅፉ ገብታ ከልቡ ላይ ትተኛለች ትርታውን እየሰማች የኔ ሌባ ትለዋለች
የመጨረሻ ምኞቱ እሷን አግብቶ መኖር ሆኑአል
አባ ዝቅ ካሉበት ጉልበታቸው ቀና ብለው ደገፍ አሉ ስለ እሳቸው ቤተሰቦች እያሰቡ ነው
ሁሉም በሀዘን በናፍቆት የሗሊት ሸመጠጡ
ግን.....         አባ ሁሉንም ከገቡበት ትካዜ አነቋቸው
ግን አንድ የመጨረሻ ስራ መስራት አለብን የእስከዛሬዎቹን መፃህፍት ቅርሶች ስእሎችም ከወሰድንባቸው ቦታዎች መልሰናቸዋል ከመንግስት እጅ ያወጣናቸውንም ቅርሶች ከዝርፊያ ስለሆነ ያዳነው በራሳችን ቦታ አስቀምጠናቸዋል
አሁን ግን ለህዝባችን ለሀገራችን ምንሰራው አንድ ስራ አለ በተለይ ህክምና አተው መዳኒት አተው ለሚጎሳቆለው የሀገራችን ህዝም መፍትሄ የሚሆን ስራ ነው
በባለፈው ሳምንት ከአንድ ገዳም የተሰረቀ #እፀ-ደብዳቤ የሚል የብራና መፅሀፍ በጀርመኖች እጅ ገብቷል እነሱም በኤንባሲያቸው በትላልቅ የደህንነት ባለሙያዎችና በተደራጀ የሴኩሪቲ መስመር እየተጠበቀ ነው ከሶስት ቀን በሁዋላ ነው ይዘውት ወደ ሀገራቸው ሚበሩት በዚች ትንሽ ቀን ከእጃቸው ወስደን በመፅሀፉ ላይ ትልቅ ምርምር አድርገን ህክምናና መድሀኒት ለሚሻው ህዝባችን በባህል ሀኪሞቻችን ታግዘን መድሀኒት እንሰጠዋለን
መቼም በፋብሪካ እንስራው ብለን ለመንግስት ተብዬው ብናመለክት መልሶ ወደ ናጋዚ ነው እንደማያጉረን ምንም ማረጋገጫ የለንም
ስለዚህ ይህን ትልቅ መፅሀፍ ከእጃቸው ላይ መውሰድ አለብን
ያው እንደለመዱት ከእኛ አፍ ወስደው በስማችን መፅደቁን ለምደውታል ከአለም በመዳኒት ቅመማ ቁንጮ የሆነችው ጀርመን ተብዬ መናጢ ከእኛ ዘርፋ በወሰደችው መፅሀፍት ነው አሁን ደሞ በዚ መፅሀፍ አሁን ላሉት በሽታዎች ወደ ፊት ለሚመጡት ጭምር ሙሉ የመድሀኒቱን ቅመማ በመፅሀፉ ላይ ሰፍሮ ይገኛል
ቢያንስ ለመዳኒት ምታወጣውን ገንዘብ በባህል ሀኪሞቻችን እናድንላት
ለህዝባችን ለእናት ኢትዮጵያችን......

        ብላቴናው በእሳት ገፆች ላይ

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ልብ ሰባሪ የአለማችን 4 ንግግሮች

1 በሶሪያ ጦርነት የቆሰለው ህፃን ለዶክተሩ «እኔ ወደ ፈጣሪ መሄዴ ነው
የሆነውን ሁሉ እነግረዋለው»

2 ኢራቅ ሞሱል ውስጥ ቆስላ እየሮጠች ካሜራማኑ ሲቀርፃት «አጎቴ እባክህ
ቪዲዮ አትቅረጸኝ ምክንያቱም ሂጃብ አለበስኩም»

3 አንድ ህፃን በፍልስጤም እጅግ በጣም ይራብና «ፈጣሪ ሆይ እባክህ በቶሎ ወሰደኝ አንተ ከወሰድከኝ በገነት ውስጥ አልራብም እዛ እበላለሁ»

4 በአፍጋኒስታን ጦርነት እጁ ክፉኛ የቆሰለው ህፃን ለሕክምና ዶክተር ጋ
ወስደውት ለዶክተሩ «ዶ/ር እጄን ስትቆርጠው ልብሴን አትቂረጠው ተጠንቀቅ ምክንያቱም እኔ ሌላ ልብስ የለኝም እና» አለው ።

በጦርነት ምክንያት እጅግ ፈታኝ የሆነ ድህነት በሶሪያ፣ አፍጋኒስታን ፣ ፍልስጤም እና ኢራቅ በርትቷል። እንፀልይላቸው ከነሱም የጦርነት አስከፊነትን እንማር።

@wegoch
@wegoch
@paappii

#afendi mutaki
በትዕግስት በሪሁን

፳፬-፰-፲፪

ለዘመናዊነቱ ወደር የማይገኝለት ሆስፒታል ውስጥ እገኛለው። የእንግዳ መቀበያው ጋር ተሠይሜያለው። በትክክል መረዳት ያልቻልኩት እዚህ ቦታ ምን እየሰራው እንደሆነ ነው። አጠገቤ የተቀመጡትን ሰዎች ገልመጥ ገልመጥ ብዬ ለመመልከት ሞከርኩ። የማውቀው ሰው አጣሁ። ሀኪሞቹም ቢሆኑ ከዚህ በፊት የማውቃቸው አይደሉም። ታዲያ ምን እየሰራሁ ነው? ጥያቄውን ለእራሴው ሠነዘርኩ። ዝምታ...... ግራ መጋባት.....
"ኧረ ዶክተር አልቻልኩም.... ኧረ ውይይይይ.." ከሃሳቤ ያነቃኝ በዊልቸር እየተገፋ በአጠገቤ ያለፈ ታካሚ ነበር። ትንሽ ስላስበረገገኝ ወደ ሰውየው አፈጠጥኩ። ወጣት ነው በ፳ዎቹ መጨረሻ ላይ የሚገመት። ጉዳቱ እንዳሰብኩት እንዳልሆነ ያወኩት ሙሉ የአካል ክፍሎቹ እንዳሉ ስረዳ ነው። ከጩኸቱ መግነን እሣት የለበለበው አሊያም ከባድ የመቆረጥ አደጋ የደረሰበት ነበር የመሰለኝ። ነገር ግን ጉዳዩ ሌላ ነው። ወጣቱ ሆዱ አካባቢ የተወጠረ ነገር ተመለከትኩ ከእግሮቹ መካከልም ፈሳሽ ይፈሳል። እንዴ ምንድንነው ነገሩ??.... አእምሮዬ ውስጥ የተፈጠረውን ሃሳብ ማመን አልፈለኩም። ሁኔታውን ወደጎን አድርጌ ሌላ ነገር ለማሰብ ሞከርኩ። ኮሪደሩ ላይ አንዲት ሴት በችኮላ እየተራመደች በአጠገቤ አለፈች። አነስ ያለ ዘመናዊ ዘንቢል አንጠልጥላለች ፔርሙዝ ይታየኛል።
" የደረሰ ወንድ አሁን በዚህ አለፈ?" አለች ጠደፍ እያለች
እንግዳ ተቀባይዋ እርጋታ ተላብሳ መለሰችላት
" ወደ ማዋላጃ ክፍል ገብቷል.... ነገር ግን ማንም ሰው መግባት አይችልም እባክሽ እዛ ጋር አረፍ በይ" በቀኝ እጇ እኔ ወደተቀመጥኩበት አመላከተቻት።

የፈጣሪ ያለህ!!!! ምንድነው የምሰማው? ቅድም ያየሁትን ተጠራጠርኩ። አይ ደግሞ እርግጠኛ ነኝ ወንድ ስለመሆኑ። ምን እየተፈጠረ ነው? ከቀድሞው በባሰ ግራ ተጋባሁ። የምጠይቀው ሰው ለመፈለግ በድጋሚ ዙሪያገባዬን ቃኘው። ከንቱ ልፋት።

" የአቶ ዘሪሁን ቤተሰቦች..." አንዲት ነርስ እኛ ወዳለንበት እየተመለከተች ተጣራች
" አቤት... አ.ቤት እኔነኝ... ማለቴ ባለቤቱ ነኝ" አለች የቅድሟ ሴት ከመቀመጫዋ እየተነሳች ትንሽ መርበትበት ይታይባታል።
"እንኳን ደስ አለሽ ባለቤትሽ በሠላም ተገላግሏል" ረዘም ያለ እልልታ.... እልልልልልልል .. በዙሪያችን ያሉት ሁሉ ምንም እንዳልተፈጠረ ሁሉ የእንኳን ደስ አለሽ መልእክት አዘነቡላት።
' መእዛ ምን እየሰራሽ ነው?' አእምሮዬ ስሜን ጠርቶ የጠየቀኝ መሰለኝ። እውነትም ምን እየሰራሁ ነው? ውሉ ባልገባኝ እና ምን እየተከናወነ እንደሆነ በማላውቅበት ቦታ ምን እያረኩ ነው? ተነስቼ መውጣት እንዳለብኝ ወሠንኩ። ከቦታው በፍጥነት መልቀቅ ስለፈለኩ ወደ አሳንስሩ አመራሁ ብዙ አላስጠበቀኝም። በውስጡ ፪ ሰዎች ይዟል ከኔ በላይ ካለው ፎቅ እንደመጡ ተመለከትኩ።
" ...ጌች ግን ታድሏል ሲመኝ እንደነበረው ወንድ ልጅ ተገላገል አይደል?" አለ ጠቆር ረዘም ያለው ወጣት
" እንዴ በጣም እንጂ ትላንት እራሱ ድካሙን ረስቶ ደስታ በደስታ ነበር" አለ የሰውየው ደስታ ተጋብቶበት
" እንኳን አደረገለት.. በሠላም መገላገሉ በራሱ ትልቅ ነገር ነው ለነገሩ ሃኪም ቤቱም ለማዋለጃ ብቻ በመሆኑ ጥሩ ነገር ያቀርባሉ" አለ የመጀመሪያው ሰው
እየመጣሽ ተኚ... አለ ያገሬ ሰው... ጭራሽ? የቅድሙን ወላድ በስህተት አሊያም በስንት አንድ ጊዜ በሚከሰት ክስተት የተፈጠረ ነው ብዬ ላምን በደረስኩበት ጊዜ ሌላ መርዶ? ሌላ አእምሮዬን የሚወጥር ነገር?
" መአዚ በቃ አመኚ ወንዶች መውለድ ጀምረዋል" አለኝ ውስጤ በለሆሣስ። አማተብኩ " ደግሞስ እስከመቼ እናንተ ሴቶች ብቻ የዚህ ነገር ተሸካሚ ትሆናላችሁ? እኩልነቱም ቢሆን በሚታይ ነገር ያምራል" አእምሮዬን ዝም ማስባል አልቻልኩም። በሩጫ ከሆስፒታሉ ቅጥር ወጣሁ።

* * * * * * * * * * * * * * * * ረቂቅ እና አጋሮቿ ያዘግጁት ዝግጅት ላይ ዘግይተን ነበር የደረስነው። ረቂቅ የረዱ የአጎት ልጅ ናት። ' የሴቶች መብት አቀንቃኝ ከሚባሉት ዋነኛዋ ናት። የ 'feminism'(ሴቶች የወንዶች ያህል መብት ይኑራቸው) ፅንሰሃሳብም ከሚያራምዱ ሰዎች ቀንደኛዋም ናት። ረቂቅ የመክፈቻ ንግግር አድርጋ ከመድረክ ከመውረዷ ነበር የደረስነው። ሃሳቡን ባልደግፈውም በረዱ ውትወታ እዚህ ተገኝቻለው።
"በቅድሚያ አላማችንን ደግፋችሁ እዚህ ለተገኛችሁ በሙሉ ላቅ ያለ ምስጋና አቀርባለው.." ሞቅ ያለ ጭብጨባ ተሠማ። ''ወይ መደገፍ" አልኩኝ በልቤ
ቀላ ያለችው ሴት ንግግሯን ቀጥላለች
".... እንደሚታወቀው ዓለም የወንዶች ሆና ኖራለች። ከዚህ በኋላ ግን ይህ ሁኔታ አይኖርም! በእኛ እና መሠል ሴቶች ይቀየራል!" አሁንም ጭብጨባ
"... ዛሬ ፩ ብለን የምንጀምርበት ቀን ቢሆንም ለረጅሙ ጉዞአችን ብዙ ስንቅ የምንቋጥርበት ነው። በወንዶች የተያዙብንን የበላይነቶች በሙሉ የምናስመልስበትን ስንቅ የምንቋጥርበት። መብታችንን የምናስከብርበትን መንገድ አሐዱ የምንልበት። የወንዶች ፈላጭ ቆራጭነት የሚያበቃበት፣ ከታዛዥነት የምንወጣበት ጊዜ ነው።" ጭብጨባው ቀጥሏል

" ስለ ምን ታዛዥነት ነው የምታወራው? ባል የቤት ራስ መሆኑ ምኑ ላይ ነው ክፋቱ? ልባም ሴት ሆኖ ባልን እንደሚፈልጉት አድርጎ መስራት ሲቻል..."

" እስከሚያልቅ መቆየት አለብን?" አልኳት ፊቴን ወደ ረዱ አዙሬ
" መአዚዬ የአዳራሹን ጉዳይ ስላስፈፀምኩላት መጨረሻ ላይ ለምስጋና ስለምትጠራኝ ነው ትንሽ ብቻ 'ፕሊስ' " አለችኝ ረዱ።

ሌሎች ብዙ ሰዎች መድረኩ ላይ እየተፈራረቁ ንግግር አደረጉ። የሚያስደነግጡ፣ ከተፈጥሮ ያፈነገጡ ሃሳቦችን አደመጥኩ። ቢቻል የማይለወጠውን የተፈጥሮ ትዕእዛዝ ለመለወጥም እቅዱ እንዳላቸው እየተፈራረቁ አሠሙን።
.
.
.
.
.
.
.
አዎ! እራሱ ነው። ይኼ የ 'ፌሜኒዝም' ስብሰባ የፈጠረብኝ ነገር ነው። አእምሮዬን ሳልሰጣችው እንዴት ይኼን ያህል ተቆጣጠሩኝ? የእቅዳቸው ደራሲ እስክመስል ድረስ፤ የህልማቸው አቀናባሪ እስክሆን ድረስ እንዴት ይህን ያህል ምስል አእምሮዬ ፈጠረ??? አማተብኩ። የትላንት ምሽቴን ቅዠት አስቤ ተሣለምኩ።
ጌታሆይ ተፈጥሮህን ጠብቅ።

@Wegoch
@Wegoch
@Wegoch
ይህ የአብዮተኞች ድምፅ ነው፡፡

የባለቅኔው ልጅ ሜዳ ወድቆ እኛ ቤት ደፍተን ቤት መተን አንገጥምም!!!



አዳሜ እና ሄዋኔ ትሰሙ እንደሆነ ስሙ!!! እዚህ ጋር ያንተን ላይክና ኮሜንት ለመሰብሰብ የሚፃፍ ትርክት የለም! ይልቅዬ ኪስህን አስዳብስሃለሁ! መፍትሄ አፈላላጊ አድርጌ እሾምሃለሁ ፡ ከችግር ፈጣሪነት አረንቋ ትላቀቃለህ !!!

ዳይ ዳይ ዳይ ሙስሊም ነሽ ክርስቲያን ነሽ ጦማሩን በሚገባ ተከታትለሽ የሚጠበቅብሽን ታደርጊያለሽ /ውልፍት እንዳትይ!/

እንደው የማያገባህ ጉዳይ ውስጥ ገብቼ እዘላብዳለሁ የምትል ካለህም መሰነባበቻ ቆመጥ ይሳብብሃል ወደ ጥልቁ ፅልመትም ትወረወራለህ፡፡

°°°°°°°°°°°••••••••••°°°°°°°°°°

ይህ የማየው ሰው ማነው ካላችሁ የታላቁ ኢትዮጵያዊ ባለቅኔ ሙሉጌታ ተስፋዬ /አያ ሙሌ/ ልጅ ዳንኤል ነው ሸህ አብዱ ፡፡

ስለ ሙሉጌታ ተስፋዬ በኔ አንደበት ለማውራት ይከብደኛል ፡ ይልቁኑ አዋቂ ዘያሪዎች ያወጉትን ከኮሜንት መስጫው ሳጥን ሊንኩን አኖራለሁ፡፡ ግን ይሄንን ብቻ ልንገርህ አንተ ካህሊል ጂብራን ትላለህ አንተ እነ ሩሚን ምናምን ጠቃቅሰህ ደረትህን ልትነፋብኝ ትችላለህ እኔ ግን እልሃለሁ ቅድሚያ ባለኝ የሃገሬ ምጡቅ ላይ ኩራቴ ያይላል ፡፡ የኛ ባለቅኔ ነው ሙሉጌታ ፡ አፍህን ሞልተህ መኩሪያዬ የምትለው ነፍስያው የምትጥም የከተበው የማይነትብ ባለ ብሩህ አዕምሮ ባለቤት! ( በሱ ስራዎች የዝናን ማማ የተቆናጠጣችሁ አርቲስቶቻችን እስኪ በሉ መስክሩ)


✿ እንግዲያው ወደ ቁም ነገሩ እንምጣ ✿

እርሱ ሳለ እንዳሻው ይቦርቅ የነበረ አባቴ መከታዬ ነህ እያለው ከእርሱ ጋር ቅኔውን ሲደረድር የቆየው ልጁ ዛሬ እንደቆሻሻ ተጥሎ ይገኛል፡፡ የባለቅኔውን ሙሉጌታ ተስፋዬን የአዕምሮ ጭማቂ ለህዝብ ያጠጡ አርቲስቶቻችንም በመከራ የሚጠቀማትን ዳቦ በሻሂ ሲምግ በሶ ብጥብጡን ሲጠቀም እያዩ ያልፋሉ!!!

☞ እሺ ስለማያውቁት ነው ብለን ቨቀናነት እናስብና እወቁልን ብለን እየጮህን ነው፡፡

☞ ይሄ አብዮት ስያሜው #የግጥም_አብዮት ሆኖ ሳለ የግጥም አባቶችን ውለታ አለመክፈል ይከብደዋልና ሊጮህ ተገዷል፡፡

☞ እርግጥ ነው ፡ የወደቀን የሚወድ እምብዛም የለም ( ብር ካልሆነ ለማንሳት ገድም አንል)

✿ ወድ አብዮተኞቻችን ሆይ አሁን ጥያቄው አጭር እና ግልፅ ነው ፡ ይህ ሰው ሶማሌ ተራ ላይ ድንጋይ ትራሴ ብሎ ተጎሳቁሎ ይገኛል ፡፡ የሚበላውን እህል የከፈተውን ጉሮሮ ከሚዘጋ ፈጣሪ ዘንድ እንጂ በራሱ የሚያገኝበት መንገድ የለውም፡፡ አባቱን በማጣቱ ምክንያት በደረሰበት ጫና ምክንያት ከጭንቀት አልፎ ድብርት ከድብርት አልፎ ድብታ ውስጥ ገብቷል፡፡ እውነት ለመናገር ያ በብዙ ሰዎች ይከበብ የነበረው የበርካታ ዝነኞችን ፊት ይቃኝ የነበረ አይን ዛሬ በብቸኝነት ሲከበብ የአዕምሮ ቀውስ ቢገጥመው አይገርምም!

✿ በልዩ ቀና ኢትዮጵያዊነት መንፈስ ንቁ! እዚህ መንደር በርካታ ፈጣሪ ፀጋውን ያበዛላችሁ ሰዎች እንዳላችሁ ጠንቅቄ አውቃለሁ፡፡ እውነት ለመናገር የጥቂቶቻችሁ እገዛ ብቻ ይህን ምስኪን ይታደገዋል፡፡

✿ ይህ አብዮት የግጥም ልጅ ወድቆ ቤት አይደፋም ቤት አይመታም ! ይሄ የምታዩት ሰው መጠለያ አጥቶ እኛ ከፀጋዬ ቤት ወል ቤት ከወል ቤት ሰንጎ መገን እየዘለልን አንገጥምም!!!!

ወደን ሳይሆን በግዳችን ይሄን ግዳጅ እንወጣለን ፡ ያኔ ነው ከፍታችን! በሉ በሉ የምን መቆም ነው ለጊዜው ጥቂት ብር ወርውሩ ጊዚያዊ ማደሪያ ቤቱ ይሰራለት ዘንድ የሚበላው የሚለብሰው እንዳይቸግረው ጠግቦ ያድር ዘንድ ብቻ!!!


እንግዲህ በኔ ቅዱስ ታደሰ ንጉሴ እንዲሁም ፍቃዱ ስማቸው መኮንን ከእናንተ የሚገኘውን ሳንቲም በማሰባሰብ ከሌሎች አብዮተኛ ገጣሚ ጓዶች ጋር በመሆን ለጊዜው የሚያስፈልገውን ለማድረግ በሚል ብቻ እንቀሳቀሳለን ፡፡ ሳትሰስቱ በሚመቻችሁ በኩል አለሁ በሉ፡፡

➊ ቅዱስ ታደሰ ንጉሴ ☞ 1000160263664 /የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ/

➋ፍቃዱ ስማቸው መኮንን☞19859107 /አቢሲኒያ ባንክ/


አረ ቀስስስስስ አትሻሙ ፡ እዚህ ጋር እኛ አነስተኛ #ቤት ለማሰራት፣ የሚበላው እንዳይቸግረው እና የሚለብሰውን እንዳያጣ ለማድረግ ጥቂት ሰው ነው የምንፈልገው!


ወዳጄ #ዋናው ዋናው ዋናው ስራ በቀጥታ ጉዳዩ #ለሚመለከታቸው ሰዎች አሳውቁና #እንዲሰበስቡት ይሁን ፡፡ የባለቅኔው ውለታ ያለባችሁ ተፍ ተፍ በሉ ሳይካትሪስትም ያሻዋልና አለሁ አለሁ በሉ ፡፡

ወዳጄ አዳምጠኝ ይሄ የከፋ ነገር አይደለም እጅግ በጣም ቀላል ነገር ነው ፡ እጅህን አትሰብስብ ፡ ነገ ላይ ራሱን አቅንቶ ታላቅ ነገር የሚሰራ ሰው ሜዳ ላይ ወድቆ እጅህ ቆርሶ እንዳይበላ፡፡

★የፍቅር ዘማች ወለየዎች ከወዴት ናችሁ?!

★ኢትዮጵያውያን አርቲስቶቻችን ውለታው የለባችሁም ወይ? ትላንት ሙሉጌታ ሳይሞት እንዲህ ባረኩ ኖሮ የምትሉትን ጉዳይ ለምን በልጁ ክሳችሁት አዕምሯችሁ እረፍት አያገኝም?!!!

እዚህ አብዮት ውስጥ ሰው ልትገል ደም ልታፋስስ የገባህ ካለ አሁኑኑ ለቀህ ውጣ፡ እንሆ አብዮቱ ሰው ሰው የሚሸቱ ስራዎችን የሚሰራ ነውና ሰው ለማዳን የምትሻ አብረኀን ዝለቅ ፡ ጣፋጩን ፍሬ ትበላለህ 🙏

#ሼር/SHARE እያደረጋችሁ ለመላው ኢትዮጵያውያን የማድረስ ግዴታችሁን ተወጡ፡፡ እንደ ሜቄዶኒያ ያላችሁ #ግብረ_ሰናይ ተቋሞች እያያችሁ አትለፉ !



"በመዋረድ ቀን፣ የለም ዘመድ፥
ዘመድ እንኳ ቀን ሲጎድል፣ ይኾን የለም ወይ ባዕድ፣
የሥጋ ኑሮህ ሲሟላ፣ ሲትረፈረፍልህ ማዕድ፣
ከነገድህ ያልኾነው፣ ከዘርህ የማይወለድ፣
የሚዛመድህ ብዙ ነው፣ ባዳም ይኾንሃል ዘመድ፣

ቀን ሲጎድል ግን፣ እንዲህ ነው፤

ሐዋርያውን ቢጠይቁት፣ ዐላውቀውም ብሎ ካደ፣
ፈጣሪውን ተወና፣ ከባዕድ ጋር ተዛመደ፤
ዘመድስ ዮሐንስ ነው፣ የነጎድጓድ ልጅ ብርቱ፣
መቃብር እስኪወርድ ድረስ፣ አልተለየምና ከእናቱ፤

ግጥም(በግዕዝ)☞የቅኔ ሊቅ አምባሳደር ብርሃኑ ድንቄ
ትርጉም ☞ በመምህር ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

ዳይ ዳይ ዝም ብለህ አትይ ሼር እያደረክ የበኩልህን ተወጣ ይህን አስከፊ ጊዜ ተጋግዘን እንሻገር ፡፡

ሀሉም ቢተባበር __ የት ይደረስ ነበር 🙏🙏🙏
#የግጥም_አብዮት

@wegoch
@wegoch
#የእሳት ላይ ቁጥሮች

   ክፍል - ፰

ሁሉም ለትልቁ እና ለመጨረሻው አላማ ዝግጁ ሆነዋል ይሄ እንዳለቀ ከሚናፍቋቸው ቤተሰቦቻቸው ጋር ሚገናኙበት ቀን እሩቅ እንደማይሆን ተስፋ አድርገዋል
እቅዱንም አሳክተው መድሀኒት ለሚሻው ህዝባቸው ትልቅ ነገርን ሊያደርጉለት እንደሆነ ወስነዋል
#ፊያሜታ በተዘረጋላት መረብ ከጀርመን ኤንባሲ አዲሷ ወጥ ቤት ሆና ተገኝታለት
#ዮቶር ከኤንባሲው ቢሮዎች ሰተት ብሎ ገብቶ አዲሱ የቢሮው የማሽኖች እና የኮምፒውተሮች ጠጋኝ በሚል የካሜራዎችን ሲስተም የደህንነት ሁኔታዎን በስሩ ተቆጣጥሯል
#ስምዖንም አዲስ ለተገነባው ህንፃ በቀረበለት ኮንትራት መሰረት ልዩ ልዩ ስዕሎችን ለኤንባሲው እያቀረበ ነው
#ዶክተር ናትናኤል በኤንባሲው ለሚደረጉት ካርኒቫሎችና የእራት ግብዣዎች ቆጃንጆ ኮረዳዎችን ከነጮቹ እቅፍ ይከታል
ሁሉም በተለያየ መንገድ ለአንድ አላማ ቆመዋል...
በልብሶቻቸው ላይ በተገጠሙት ካሜራዎችና ድምፀ መቅርፆች የኤንባሲውን ቅጥር ከእግር እስከ እራሱ እየቀረፁ ከመሬቱ ስር ላለው ቢንያም ያደርሱታል ይህ እቅድ ከበፊቶቹ ሚለየው ለመጨረሻው ተግባር ኤልያስ ብቻ አይደለም ወደ ቦታው የሚያመራው በዚ እቅድ ስድስቱም ሰዎች ከቦታው መገኘት አለባቸው
ጉጉታቸውን እንባቸውን ናፍቆታቸውን አዲሱ ሚጀምሩት ህየይወታቸውን ሁሉም በዚ እቅድ ላይ ተሳትፈው ሊያገባድዱት ወስነዋል በናጋዚ ሰማይ ምንም ከሞት ጋ ቢፋጠጡ ለዚ አላማ እንደተመረጡ አውቀዋል
#ስምኦን ዙሪያ ገባውን ባስጌጣቸው ስዕሎች አዲሱን ህንፃ በሙሉ ሞልተውታል በእያንዳንዱ ስዕሎች ላይ የተገጠሙት ካሜራዎች ሁሉንም እንቅስቃሴዎች ወደ መሬቱ ስር ያስተላልፋሉ
#ፊያሜታ የመግደሉም የማዳኑም ነገር በእጇ ገብቷል መርዢ የሚል ትዕዛዝ ካገኘች የኤንባሲውን በሊታዎች ጠቅልላ ታስተኛቸዋለች
#ደራሲው ዮቶር ገቢ ወጪውን ይከታተላል በሚሰራቸው ማሽኖች ላይ በሚገጥማቸው ድምፀ መቅርፆች የኤንባሲውን ጩኸቶች አስከ ትናንሽ ሹክሹክታዎች ወደ መሬቱ ስር ያስተላልፋል
#ናትናኤል በውቦቹ ሴቶች ታግዞ ቡዙ ነገሮችን ይሰበስባል
ዛሬም ለአዲሱ ህንፃ ምርቃት በሚል ብዙ ታዳሚዎቸች ከቦታው ተሰባስበዋል
ሻርማይኮችም ቦታ ቦታቸውን ይዘዋል .....
ሰአሊው አስውቦ ለሳላቸው ስዕሎች ከኤንባሲው ሰዎች ትልቅ አድናቆት ተችሮታል
ወጥ ቤቷ ፊያሜታም ለዛሬው ምሽት የሚቀርበውን የምግብ አይነት አዘጋጅታ የቀደሙ ወጥ በረቶቹን አስንቃ ለዛሬው ማታ ጉድ ጉድ ትላለች
ዮቶርም በቅልጥፍናው ከብዙ የኤንባሲዎቹ ሰዎች ጋ ተግባብቷል
ዶክተሩም በሚያመጣቸው ውብ ሴቶች ምክንያት ከነጮቹ ጋ ወዳጅነት ፈጥሯል
ዛሬ ሁሉንም ነገር አከናውነው ወደ አለማቸው መመለስ አለባቸው..
ከመሬቱ ስር ያሉት ሰዎች የእኩለ ሌሊቱን ሰአት እየጠበቁ ይገኛሉ አይኖቻቸውን መረጃ ከሚያሳዩቸው እስክሪኖች ላይ አልነቀሉም
ከኤንባሲው ካሉት ሰዎች የሚላኩላቸውን ምስሎች ትኩረት ሰተው እየተከታተሉ ነው
አባ ተስፋ ስላሴም ናጋዚ የቀማቸውን አስኬማቸውን ዛሬም አልጫኑትም ከመሬቱ ስር ያለው ሙቀት ዛሬ በርትቷል በአስኬማ ይሸፈን የነበረው ውብ ፀጉራቸውን እየነኩ ላባቸውን ይጠርጉታል ሁሉም እንዳለቀ እሳቸው አስኬማቸውን መልሰው ለመድፋት ወስነዋል
አባ ከገዳሙ በደረሳቸው መረጃ መሰረት Mr isaac የተባለውን ነጭ በትኩረት ከእስክሪኖቹ ላይ እየፈለጉ ፎቶውን እያስተያዩት ነው......

                  ይቀጥላል..
      ብላቴናው በእሳት ገፆች ላይ

@wegoch
@wegoch
@wegoch
#ወግ_ብቻ
. . .
ማነሽ ባለሳምንት

ሳቅ የጥዋ ማህበር ጠባይ አለው። በአንዱ ላይ ለአስራአንድ ተሆኖ ይሳቃል። ሌላው ይቀጥላል የጥዋ ማህበሩን ለማውጣት። ሲል ሲል ዙሩ እኔ ጋ ደረሰ።

የፌዙ መነሻ ቤቴ ሰርሳሪ መግባቱ ነው። ጫት ቃሚው ሁሉ "እኔ የሰማሁት" እያለ አወራ፤ አውካካ። ወሬው ስብጥርጥር ነው። ለያዥ ለገናዥ ያስቸገረ። እኔ እንዲመች አድርጌ ላቅርብላችሁ። (ለዚህ መምህርነቴ ጠቅሞኛል።)

አንድ
-------
መካሻ አጎት ቤት ሰርሳሪ ገባ። የሰረሰረበትን ድጅኖ እንደያዘ የቤቱን ዙሪያ ገባ ቢመለከት ምንም የረባ እቃ አጣ። እቃ ከጠፋ በልቼ ልሂድ ብሎ ሌማቱን ቢከፍት ባዶ ሆኖ አገኘው። ፓስታ ቀቅሎ ይሆናል ብሎ ድስቱን ቢከፍተው ሸረሪት አድርቶበት አየ። በዚህም፦
ሀ - በሀዘኔታ አለቀሰ ያሉ አሉ፤
ለ - ቀስቅሶ ይሄን ድጅኖ ሸጠህ ብላ ብሎ ሰጠው ያሉ አሉ።
ሐ - አምስት ብር ቀዳዳ ሰሀን ላይ አስቀምጦለት ወጣ ያሉ አሉ።

ሁለት
--------
መካሻ አጎት ቤት ሰርሳሪ ገባ። ሌሊቱን ሲለፋ አድሮ ሊነጋጋ ሲል ቀድዶ ገባ። በድካም እያለከለከ ቢመለከት እሱ ከቀደደው የማይተናነስ ሌላ ነባር ቀዳዳ በትይዩ ግድግዳ ላይ ተመለከተ። በልፋቱ ተናደደ። ይበልጥ ያናደደው ደግሞ ቤቱ ውስጥ ምንም ባለመኖሩ ነበር። ስለዚህ የመካሻን አጎት ቀስቅሶ፦
ሀ - መከረው ያሉ አሉ፤
ለ - ሰደበው ያሉ አሉ፤
ሐ - ገረፈው ያሉ አሉ።

በዚች ቀልድ ጥሎሽነት ከወሪሳዎች ጋር እንዳልለይ ሆኜ ተቀላቀልኩ። አንድ አካል አንድ አምሳል ሆንኩ። በብላ ተባላ ዘመን የብላ ተባላ ሠፈር ሠፈርተኛ ሆንኩ። . . .
---------------------
ዓለማየሁ ገላጋይ
ወሪሳ
ገፅ 21 - 22
@wegoch
@wegoch
@wegoch
Forwarded from ግጥም ብቻ 📘 (👋ገብርዬ)
በ +251934039346
ወይም @cher46 ላይ ፎቶ በመላክ ሦዕል ማሳል ይቻላል።

ሦዕል ለ ስጦታ ጥሩ አማራጭ ነው።
#ሥዕል_ብቻ የቴሌግራም ገፅ

@seiloch
@seiloch
#የእሳት ላይ ቁጥሮች

 ክፍል - ፱

ከመሬቱ ስር አትኩሮቱ ቀጥሏል ሁሉም ትኩረታቸው ከአባ እጅ ላይ ወደ ሚገኘው ፎቶ ላይ ሆኑአል
ከኤንባሲው ካሉት የሻርማይክ አባላት የሚላከት ምሰሎች አንዱም ከፎቶው ጋ ሊመሳሰል አልቻለም
ናትናኤል ያሰፈራቸው ሴቶች ዛሬ ይበልጥ ውበት ጨምረዋል ቀለበት ያሰረውንም አፈፍ እያደረጉ በውበት ማርከዋል
ጭፈራው ሙዚቃው ደስታው ቀጥሏል
ለሻርማይኮች ግን ገና ነው እንደተለመደው ከድል ሲመለሱ በእሳቱ ዙሪያ ሰብሰብ ብለው በአባ ጊቢ ካሉት ላሞች ትኩስ ወተት እየተጎነጩ አባ ሸክ አርገው በሚያርዱላቸው ጠቦቶች ጥብስ እየተዝናኑ ማክበር ናፍቀዋል
ከእግር እስከ እራሱ የኤንባሲውን ቅጥር ቢያካልሉትም ፎቶ ላይ ያለው ሰው በአካል አልተገኘም
ፊያሜታ ሰአቱአን እየጠበቀች ነው በጀርመኖች ስርአት ከምግብ በሗላ ወይን የመብላት ፕሮግራም ይዘጋጃል እሷም የወይኑን ሰአት በጉጉት እየጠበቀች ነው
በእያንዳንዱ የወይን ፍሬ ላይ በጥንቃቄ በስሪንጅ ወግታ ባስገባችው አድካሚ እፅ ለእቅዱ ትልቁን ሚና ተጫውታለች
ከመሬቱ ስር ያሉት አባላት አይኖቻቸውን ነቅለዋል ከኤንባሲው ያልተገኙ እንግዶች እንዳሉ ስለተረዱ አባ እና ኤልያስ ወደ ኤንባሲው ለመሄድ ተነስተዋል ቢንያም እነሱ እዛ እስኪደርሱ አዲስ መረጃ ካለ ለእነሱ እንዲያሳውቅ ከመሬቱ ስር ከእስክሪኖቹ ጋ ተፋጡአል
መንፈቀ ሌሊቱ እየተጋመሰ ነው ጨዋታው ሞቅታው እየጨመረ ነው የደከመው ከሳበችው አንዱአን እቅፍ አድርጎ ወደ መጋለቢያው ይወስዳታል
በድካም ላይ ሌላ ድካም........
አሁን ያልመጡትን እንግዶች ለመቀበል ተዘጋጅተዋል
አባ እና ኤልያስም ወደ ኤንባሲው በተከፈተላቸው በሮች ገብተዋል
መንፈቀ ሌሊት አለፈ አዳዲስ ፊቶች በኤንባሲው በዝተዋል ከደቂቃዎች በፊት ሁለት ሰዎች በክብር ሞቅ ባለ ጭብጨባ ወደ ኤንባሲው የክብር ቦታ ገብተዋል እነሱን ተከትለውም በዛ ያሉ ታጣቂ ጋርዶች ከኤንባሲው ዘልቀዋል
የሙዚቃው ድምፅ ቀነስ እያለ መጣ...
ወደ መድረኩ አንዲት ሴት ወጣች ማይካሮፎኑን መታ መታ አደረገች
ሰላም እንዴት አመሻችሁ    የተጋተችው መጠጥ አድክሟታል
ወደ ዚህ መድረክ አንድ ትልቅ እንግዳ ልጋብዝ እወዳለሁ ለሀገራቸን ትልቅ ስጦታ ይዘውላት ለሚሄዱት Mr isaac
ኤንባሲው በሰከሩ ነጮች እና በጥቂት ሀበሾች ጭብጨባ ተሞላ
ወደ መድረኩ Mr isaac የተባለው ሰው ወጣ በእጆቹ በቀይ ጨርቅ የተጠቀለለ ነገር ይዟል
ሻርማይኮች እርስ በእርሰ ተያዩ
እኔ እንኳን ብዙ ላወራ አይደለም እየተዝናናችሁ ስለሆነ ብዙም አልቆይም ድምፁን ጠረግ እያደረገ
ዛሬ አንድ ትልቅ ነገር ለሀገራችን ጀርመን ይዘን ልንሄድ ስለሆነ መርቃችሁን እንድትሸኙን ነው
ቀዩን ጨረቅ እየፈታ.....
በጣም የቆየ የሚመስለ የነተበ ብራና ከቀደ ጨርቁ አወጣ ቀጠለ...
ሀገራችን ካለችበት የህክምና ብቃት ወደ ተሻለ ደረጃና በመድሀኒቱ ቅመማ ከአለም ቁንጮ የሚያደርገንን ጥበብ
ዛሬ ከደጎቹ ከልዩዎቹ ኢትዮጵያውያን ለኛ በስጦታ መልክ ስለተሰጠን ደስታዬን ለመግለፅ ስለወደድኩና ለማመስገን ስለፈለኩ ነው
አመሰግናለሁ ....
አባ ዘለው ቢያንቁት ደስታቸው ነበር ሰርቆ እና ገዳም በርብሮ አስበርብሮ ያገኘውን ጥበብ በስጦታ አስመስሎ ሲያወራ ተበሳጭተዋል
ደጎችና ልዩ የሆኑት ኢትዮጵያውያንን ደሞ በሱ አፍ በመጥራቱ ጭራሽ ንዴታቸው ገነፈላበቸው
ሰአቱ መድረሱን ስላወቁ ለመረጋጋት ሞከሩ
የወይኑ ሰአት የደረሰ ይመስላል ፊያሜታ እና አጋር ሰራተኞች ለእራቱ ተብሎ በተዘጋጀላቸው ልብሶች ተውበዋል
ከወጥ ቤት እየወጡ ወይኖቹን ለእንግዶቹ ማዘገን ጀመሩ
ውቧ ፊያሜታ ለምሽቱ የታደሙትን ሴቶች ታስነንቅ ጀመር ወይኑን ከውብ ፈገግታዋ ጋ እየሰጠች ጋርዶቹን ጭምር አዘገነች
Mr isaac ከሚስቱ እጅ እየተወረወረለት ወይኑን ወደ አፉ ያስገባ ጀመር
ከሻርማይክ አባላት ውጪ አብዛኛው ሰው ወይኑን እያጣጣመ ነው.....

              ሊፈፀም ሰአቱ ደርሷል
       ብላቴናው በእሳት ገፆች ላይ

@wegoch
@wegoch
@wegoch
የማለዳቹ ይቺን ስሙማ

''በሸርተቴ ሞራል ሰበራ''

አዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ የተገኘ ፁኹፍ ነዉ።
ፀኀፊ :- ኤፍሬም እንዳለ
የፁኹፉ ድምፅ :- ሚኪያስ ልየዉ @Mykeyliyew

(በንባቡ ላይ ስለተጠቀሰዉ የፀኀፊዉ የስም ስህተት በቅድሚያ ይቅርታ እጠይቃለኹ ፀኀፊዉ ''ኤፍሬም ስዩም'' ሳይኾን ''ኤፍሬም እንዳለ'' ነው)።

@Wegoch
@wegoch
@wegoch
2024/11/05 23:14:21
Back to Top
HTML Embed Code: