Telegram Web Link
ምክር እስከመቃብር
(ከኣልፎ ሂያጁ ማስታወሻ የተቀነጨበ)
(በእውቀቱ ሥዩም)
.
እንደምነሽ ሸገር
እንደምነሽ ሸገር
የቤት ኣከራየ የጋሽ ጣሰው ኣገር
እየመጣሁ ነው፡፡ወደ ኣዲስ ኣበባ እየመጣሁ ነው፡፡እናቶች
ኣባቶች ልጆች ኦርጅናሎች ሰልቫጆች! እኔ ሳልመጣ ውጊያውን
እንዳትጀምሩት ኣደራ፡፡ ኣጭርና ጣፋጭ ይሁን እንጂ
በማንኛውም ትግል ላይ ለመሳተፍ ዝገጁ ነኝ፡፡የጥይት መከላከያ
ቆብ ሹራብና ሱሪ እንዲሁም ፈንጅ የማይበትነው ጫማ
ከተሰጠኝ ኣንድ ሻለቃ እመራለሁ፡፡ኣነሰ ከተባለ ኣንዲት ኮረብታ
እቆጣጠራለሁ፡፡ በጦር ምህንድስና ላይ እሳተፋለሁ፡፡ ባሩድ
ኣገነፋለሁ፡፡ የታንክ ጎማ እነፋለሁ፡፡በሰላሙ ቀን ለሞባይል፤
በቀውጢው ቀን ለሽጉጥ ማስቀመጫ የሚሆን ሰገባ እሰፋለሁ፡፡
ይሄም ኣላዋጣ ካለ የኤፍሬም ይሳቅን ቡድን የሚፎካከር
ኣስታራቂ ቡድን ኣቋቁሜ” ኣንተም ተው ኣንተም ተው፤
ያስታረቅሁበትን ኪሴ ውስጥ ክተተው” የሚል ኣገልግሎት
እሰጣለሁ፡፡ቃሌ ነው፡፡የተናገርኩት ከሚጠፋ በቅርቡ የገዛሁት
ጋላክሲ ሙባይል ይጥፋ(በዝች ንግግር ውስጥ የተደበቀ ጉራ
እንዳለ እናንተ ሳትሉኝ ኣውቀዋለሁ)
ገና ለገና ካሜሪካ ሊመጣነው በማለት ማጅራቴን ለመመታት
እያሟሟቃችሁ ያላችሁ ዱርየዎች እንዲሁም ከዱላ የተረፈች
ማጅራቴን በማሸት ትርፍ ለማጋበስ የተሰናዳችሁ ወጌሻዎች
ተስፋ ቁረጡ ፡፡ ቤሳቢስትን የለኝም፡፡(ማጅራት መምታት ሲነሳ
ፋሲል ደመወዝ ትዝ ኣለኝ፡፡እንኳን እግዜር ማረህ ልለው ብደውል
ከዲሲ በርሮ ኣትላንታ እንደገባ ነገረኝ፡፡ለኮንሰርት ይሁን
ለስልታዊ ማፈግፈግ ኣልነገረኝም፡፡ ወይ ኣበሳ!እኛ
ኢትዮጵያውያንኮ ምስኪን ነን ፤ ኣገር በቀል- ዱላ ሸሽተን ስንሄድ
የውጭ ኣገር ዱላ ይጠብቀናል፡፡
ኣሜሪካ ሁለት ወር ስቆይ ያተረፍኩት ነገር ቢኖር ግብዣና ምክር
ነው፡፡ዲታው ቢራ ጋብዞ ወደ ኣገርቤት ይዣት የምመለስ ቦርጭ
ያወጣልኛል፡፡ቺስታው ቦርጬ እንዴት እንደምቀንስ ይመክረኛል፡፡
ኣሜሪካ ፍሪሽ የሆነ ሰው ኑሮው ምክር እስከመቃብር ነው፡፡
ከኢትዮጵያ ወደ ኣሜሪካ ገንዘብ የተላከለት የመጀመርያው ሰው
ሳልሆን እቀራለሁ?
ለምሳሌ ጺም ለመቆረጥ ኣስር ዶላር መከስከስ ነበረብኝ፡፡
ፈርዶብኝ ኣሜሪካ ስገባ ጺሜ ያለወትሮው ቶሎቶሎ ማደግ
ጀመረ፡፡ኣዲኣበባ እያለሁ ጺም ኣልነበረኝም፡፡እንዲያውም” ይሄ
ልጅ ጺሚ የሚባል ነገር የለውም ስልብ ነው እንዴ?” የሚል
ኣሜት በመንደራችን ይናፈስ ነበር፡፡ስልብ ኣለመሆኔን ለማሳየት
ኣንድ ሁለት ቀን መንገድ ዳር ሸንቻለሁ፡፡
እንደልማዴ ከቀናኝ የሚጋብዘኝ ከፈረደብኝ የሚመክረኝ ኣላጣም
በማለት Fenton መንገድ ላይ ወደሚገኝ ያበሻ ምግብ ቤት
ጎራ ኣልኩ፡፡ ኣንዱ መድረክ ላይ የሱዳን ዘፈን ይዘፍናል፡፡
ከተስተናጋጆች ውስጥ ኣንድም የሚያዳምጠው የለም፡፡ሁሉም
ሙባይሉ ላይ ኣቀርቅሯል፡፡የታደለው ከፍቅረኛው በቫይበር
የተላከለትን የክንፈር ምስል እያየ በደስታ ይዋኛል ፡፡
ያልታደለው”የትምርት ቤት ክፍያ እየደረሰብኝ ስለሆነ ቶሎ
ላክልኝ እንጅ”የሚል ካገር ቤት የተላከ መልክት እያነበበ
ተክዟል፡፡ ሌላው ግድግዳው ላይ በተንጠለጠለው ቲቪ ላይ
የሚተላለፈውን ያሜሪካ እግርኳስ እየተመለከተ ምድር ጠቦታል፡፡
ያሜሪካ እግርኳስ ቢሏችሁ እንደ ዋናው እግርኳስ እንዳይ
መስላችሁ፡፡ ኣንዱ ጠብደል ጥቁር ሙልሙል ኳስ ይዞ
ይሮጣል፡፡ሌላው ኣሳድዶ ይደርስበትና ዘርጥጦ ይጥለዋል፡፡ ለኔ
ይህ ጨዋታ ሳይሆን ህጋዊ እውቅና ያለው ኣምባጓሮ ነው፡፡
በዚህ መሃል ዘፋኙ “ከ እኔ ጋ ናችሁ?” እያለ ኣስሬ ቢጣራም
ማንም ተጉዳይ ኣልጣፈውም፡፡ ልምምድ ላይ ያለ ይመስል
ለራሱ ዘፍኖ ወረደ ፡፡ስላሳዘነኝ ባንኮኒውን እንደመቋሚያ ተደግፌ
በጥሞና ኣዳመጥሁት፡፡ድምጹ ከዛፍ ላይ ኣምፖል ያረግፋል፡፡
ቢሆንም ዘፈኑን ኣለቅጥ ያስረዝመዋል፡፡የሱን የሱዳን ዘፈን ታግሶ
መጨረስ ሱዳንን በእግር እንደማቋረጥ ነው፡፡
ጥግ ላይ ክበበው ገዳ ተቀምጧል፡፡ ወንበር ስቤ ኣጠገቡ
ተሰየምሁ፡፡ ራት ይጋብዘኛል ብየ ስጠብቅ ከራት ጋር የተያያዘ
ገጠመኝ ጋበዘኝ፡፡
ክበበው ገዳ ጎረምሳ እያለ የለቅሶ ቤት እራት ኣያመልጠው
ነበር፡፡ እንድያውም እንዲያባላኝ እያለ ቃሪያ በኪሱ ይዞ መዞር
ጀምሮ ነበር፡፡ ኣንድ ለቅሶ ላይ ታድያ እራት ሲቀርብ ክበበው
ከቤቱ ይዞት የመጣውን ቃርያ ከኪሱ ኣውጥቶ ኮርሸም ሲያደርግ
የተመለከተ የሰፈር ልጅ ወደ ኣስተናጋጆች እያጨበጨበ “እዚህ
ጋ ቃርያ ኣልደረሰኝም” ብሎ ጮከ፡፡
ኣለፍ ብሎ፤ የጃንሆይ ኣምባሳደር ዘውዴ ረታና ያሬድ ጥበቡ
ቁጭ ብለዋል፡፡ያሬድ ተራሮችን ያንቀጠቀጠ ትውልድ ሲሆን
ዘውዴ የተንቀጠቀጠው ተራራ ነው፡፡ኣሁን ዲማሚቱና ተራራውም
ባንድ ጠረጴዛ ዙርያ ተቀምው ሳያቸው ገረመኝ፡፡
ከማጅራቴ ኣካባቢ “ልትጽፍ ነው የመጣህ ኣይደል”የሚል
ሹክሽክታ ሰማሁ፡፡ወይንሸት ናት፡፡ ባለፈው ኣመት ከባህል
ቡድናችን ጋር ስትመጣ ኮከብ ድምጻዊ ነበረች፡፡ኣሁን እዚሁ
ቀርታ ኮከብ ኣስተናጋጅ ሆናለች፡፡ኣፍንጫዋ ላይ የወርቅ ቡግር
የመሰለ ሎቲ ለጥፋለች፡፡እዚህ ኣገር ሴቶች ሎቲ
የሚያንጠለጥሉት ጆሮኣቸው ላይ ሳይሆን ኣፍንጫቸው ላይ ነው፡፡
ስለወይንሸት በሌላ ምእራፍ እተርካለሁ፡፡
በሩ ኣጠገብ ተኬን ኣየሁት፡፡ ተኬ በደርግ ዘመን ካይሮ ላይ
ከጠፋው የብሄራዊ ቡድናችን ገንዘብ- ያዥ ነበር፡፡ኢትዮጵያ
ከግብጽ ጋር ባደረገችው በግጥምያ ዋዜማ ላይ በረኛውን
ጨምሮ ብዙ ተጫዋቾች ስለኮበለሉ እሱ የበረኛውን ቦታ ተክቶ
ተሰልፏል፡፡ ከተቃራኒ ቡድን የተለጋች ኳስ ወደእሱ ኣቅጣጫ
ስትመጣ በገንዘብ ቆጠራው ለምዶበት ጣቱን በምላሱ እያጣቀሰ
ሲርበደበድ ፤ ኣስራ ሰባት ጎል ገበቶበታል፡፡ (ምንጭ፡
የይድነቃቸው ተሰማ ሪፖርት)ተኬ ጉዳዩ ሲነሳበት
ያማርራል፤“ይሄ ውለታ ቢስ ህዝብ የገባብኝን ኣስራ ሰባት ጎል
እንጂ ያዳንሁትን ሰባት መቶ ጎል ኣላሰበልኝም” ይላል፡፡ካገሩ
ወጥቶ መቅረት ኣሳብ ፈጽሞ ኣልነበረውም፡፡ይሁን እንጅ ይህን
ሽንፈት ይዞ ጓድ መንግስቱ ፊት መቆም የሚያመጣውን ነገር
ኣስቦ በዛው” ነካው“፡፡
ኣሁን በሩ ኣጠገብ ቁጭ ብሎ ”ብሉ ሙን“ ቢራ ይጠጣል፡፡
የቢራ ጠርሙሱን በጥርሱ ከፍቶ ቆርኪውን ጠረጴዛ ልይ ተፋው፡፡
ቢራ መክፈቻ ቢቀርብለትም ተጠቅሞበት ኣያውቅም፡፡እግዜር
መንጋጋን የፈጠረው ሲርብህ ኣጥንት እንድትቆረጥምበት
ሲጠማህ የቢራ ጠርሙስ እንድትከፍትበት ነው ይላል፡፡

@wegoch
@wegoch
#ቅንድል_ዲጂታል_መፅሔት
አለምን በስጋት እየናጠ ስላለው COVID-19 በስፍት የተዳሰሰበት ፣ ሀገሪኛ ወጎች ፣ የስነ ልቦና ግኝቶች ፣ የቅን ተምሳሌት እንግዶች ፣ የጥበብ ቱሩፍት ፣ አጃኢብ ያስባሉ የአለም ድንቅ ትዕይንቶች እና ዕልፍ ገፆች በወጣት ፀሀፊዎች ከልብ ተቃኝተውበታል፡፡

#ያንብቡትና_ያትርፉበት!

#ቅፅ-2 #ቁጥር-1👇👇


@kendelM
@kendelM
ቅንድል_ዲጂታል_መፅሔት_ቅፅ_2_|_Kendel_edited10.pdf
6 MB
ቅንድል ዲጂታል መፅሔት
#ቅፅ-2 #ቁጥር-1

#አዲስ ይዘት፣
#ልዩ አቀራረብ
#ሚያሸልሙ_ጥያቄዎች_የተካተቱበት



💵ፓኬጅ ከገዙ 60 ሳንቲም ብቻ💵

ቅን ፣ ምክንያታዊ እና ሀገር ወዳድ ትውልድ ለኢትዮጵያ !!!
@KendelM
@KendelM
#የደሜ ዜመኞች

ክፍል - ፲
ቀጥያለሁ...
(የሞቴ መምጣት ደርሳለችና የፍቅሬን ንሰሀ ስሙልኝ)
ቀጥያለሁ.....

የፍቅሬ ሀገር ድንበር ስለሌለው መሰረትና አጥር ሳይከልለው ወደ አርያም ሊፈረጥጥነው
ተጠርቷላ
መልአከ ምትም ከፊቴ ተገትሮ ና እንጂ  እየጠበቀችህ ብሎ እጁን ዘርግቶልኛል
እኔም ከእጁ ለመግባት ቸኩያለሁ ግን ንሰሀዬን ልነግራችሁ ወደድኩኝ
                    ማ ዘንድ ይደር
                   ሰው አሳዝኖ ሰው ላይሆን ነገር
                   ምን አስጀመረው የማይሆን ነገር
                   ልቤ አንቺን ትቶ ከማን ዘንድ ይደር
                  ልማልልሽ ወይ በቶ መስቀሌ
                  ከራሴ ጋር ነው ብጣላሽ ጥሌ
ትዝ ይለኛል የፊያሜታዬ ልደት ሰኔ 19 ነበር ምን አድርጌ እንደማከብርላት ግራ ግብት ብሎኝ ነበር ብዙ ጊዜ ፈጣን ትሁን እንጂ ፀጥታ ነፍሱአ ነው ልደቷን እኔ እና እሷ ብቻ እንድናከብረው ፈለኩኝ በምቶደው በፀጥታ አለም ውስጥ ሆነን
ትምህርቱ ሊያልቅ የ1 ሳምንት ጊዜ ብቻ ነበር የቀረው እናም ሁሉም ነገር መለየት መለየት ብቻ ነው ሚሸተው
የኛም ቢዝነስ ከምላችሁ በላይ አድጓል ግን በዛው ልክ ማላውቃቸው ሰዎች ቢዝነሴን እንድተውና ከስራቸው ገለል እንድል እየነገሩኝ ነበር
አልሰማም ብያለሁ እኔም
ሰኔ 18 ላይ ነኝ ነገ የንግስቴ የውልደቷ ቀን ነው ማንንም ሳላማክር ሁሉን ነገር በራሴ ለማድረግ ወስኛለሁ
ገና በጠዋቱ ፊያዬ እየሮጠች መታ ከእቅፌ ውስጥ ገባች ጊዮርጊስ ሄጄ ፀሎት አድርጌ መጣሁ አለቺኝ ምን ታየሽ ባክሽ አልኩአት ትናንሽ አይኖቹአን አንስታ ገላመጠቸኝ
ሁሌ ሳናዳት እንዲህ ነው ምታደርገው   
ይሄን ደሞ ላንተ ብላ ከወደ አንገቷ እጆቹአን አስገባች የሚያምር ቶ መስቀል ወደ አንገቴ አስጠጋችልኝ እንዳይጠፋብኝ አስሬው እኮ ነው አለቺኝ
መስቀሉን ስማ አሰረቺልኝ መቼም ላልየህ ቃሌ ነው የኔ አባት ቃሏ ሰርስሮኝ ወደ ውስጤ ዘለቀ
እንባ ቀረሽ ስሜት ውስጥ ገብታ እኔንም ይዛኝ ዘለቀች
ዛሬ ስሜቷ ሁሉ ዝብርቅርቅ ሆኑአል
ሁሌ ወደ ምንቀምጥባት ቦታ ወስጄ አወራት ጀመር
ትዝ ይለኛል ይሄን ዜማ ከሰጠችኝ መስቀል ጋር አያይዤ እዘፍንላት ጀመር
                  ልቤ አንቺን ትቶ ከማዘንድ ይደር
                  ልማልልሽ ወይ በ ቶ መስቀሌ
                 ከራሴ ጋር ነው ብጣላሽ ጥሌ
የሰጠችኝን መስቀል እየዳበሰች ከእቅፌ ውስጥ ገብታለች
ደሞ ነገ የንግስቴ ልደት ነው
ሁሌ ደስ ሲለኝ በደስታዬ ሀይል ዳመናውን ማዘው ይመስል ዛሬም ስሜቴን ተረድቶ በነጎድጓዱ መጣው ይለኝ ጀምሯል
ካፊያ ከሰማዩ ሲጀምር ይዣት ልነሳ ተነሳሁ  አይሆንም አለቺኝ ምወደው ዝናብ ከላይ ከእቅፌ ስር ደሞ ንግስቴ ተኝታለች
በእቅፌ ስር ነች ቶ መስቀሌን በጣቶቿ እየዳሰሰች በትንፋሿ አንገቴን ታሞቀው ጀምራለች
ምን ቁር ምን ብርድ ምን ዶፍ አሁን በኔ ላይ ስሜት አያመጡም የሷ ትንሽ ትንፋሽ የልቤን እሳት ይለኩሰዋል
ያ ውብ ፀጉር በዝናቡ ጠብታዎች ውበቱ ጨምሯል ጠብታዎቹ ቁጭ ቁጭ ብለው ለፀጉሯ ማጌጫ የተቀመጡ ጌጦች መስለዋል ሁሉ ነገራች በስብሷል ዝንቡ ክፉኛ ቢያረጥበንም በፍቅር እቅፍ ውስጥ ሙቅ ቤት ሰርተናል
ፈራሁ አለቺኝ ዝም ብለሽ እቀፊኝ አልኩአት      ለካ
እንባዋን ከዝናቡ ጠብታውች እጋ እኩል እያፈሰሰቸቻው ነው
ስቅ ሲላት ሳግ ወደ ላይ ስሜቷን ሲያወጣው እኔም ማልቀሷን አወኩኝ
ምድነው የሆነሽቢኝ ፈራሁ ፈራሁ ብቻ ነው መልሷ
ከፊቴ የማላውቃቸው ሁለት ልጆች ኢስኮ ታች ሜዳ ላይ በጣም ተፈልገሀል አሉኝ መጣሁ አልኳቸው ከሁኔታቸው የግዴት ትዕዛዝ ነው ሚመስለው
ደርሼ ልምጣ አልኩአት አትሂድ አለቺኝ አሁን ነው ምመለሰው ብላትም እባክህ ሆነ መማፀኑአ ተነሺ እሺ አብረን ሄደን እንመለሳለን አልኩአት
ዛሬ ከበስተጀርባዬ ሚቆም ማንም ሰው አልነበረም ሚከተለኝ ህዝብ ዛሬ ከኋላዬ የለም አጆቹአን ይዤ አለሜን እያስከተለኩኝ ወረድኩ
በጨቀየው ሜዳ ወደ 12 የሚጠጉ ልጆች ተሰብስው ቆመዋል በዛ ዝናብ እኔን ቀመው እየጠበቁ ነው አንድማ ማውቀው ፊት የለም
እኔ ከጨቀየው መሬት አለሜን አስከትዬ ጭቃው እየዛኩ ወደ ነሱ ተጠጋው ፎቁ ላይ ያለው ተማሪ ከሜዳው ሚደረገውን ድርጊት ተገርሞ ይመለከታል እጇን አጥብቄ ይዤዋለሁ
ድንገት ከወደ ጭንቅላቴ ከፍ ያለ ምት ተሰማኝ እጆቹአን ለቅቄ ከመሬት ወደኩኝ ጩኸቷ ከጆሮዬ ያቃጭላል ሰውነቴ ብዙ ምቶችን እያስተናገደ ነው ዝናቡ ከላይ የነሱ ቡጢ ከሰውነቴ ይወርድ ጀመረ ኢስኮ እያለች የነበረችው ፊያዬ ዋይ ዋይታዋ ቀነሰብኝ ድምጿ ከጆሮዬ ሲጠፋ የተማሪው ጩኸት ሲያስተጋባ ተሰማኝ ዱላው እየቀነሰ ዝናቡ ሀይሉን ጨምሯል
ደም የሞሏው ፊቴ በዝናቡ እየታጠበ ይነፃ ጀመር ከምንም በላይ የጭንቅላቴ ህመም አይሎብኛል አይኔን ከሜዳው ላይ ጥዬ ብዥታዬን አጠራ ጀመር እሷን መፈለግ ጀመርኩ
ከፊቴ ውድቅ ብላለች ያ ውብ ገላ ከጨቀየው ሜዳ ላይ ተንጋሎ ወድቋል
በተሰባበሩት እጆቼ አይኔን እጠርግ ገባሁ እየዳሁ አጠገቧ ደረስኩ ቅድም ስዳብሰው የነበረው ፀጉር በጭቃ ተለውሷል
በእጆቿ ሆዶአን ይዛዋላች አሁንም ይበልጥ ተጠጋሁዋት
ከዝናቡ አልፍ አንድ ዘለላ እንባ ከአይኗ ስትፈስ አየሁ
 ሆዷ ደም ለብሷል ሆድ እቃዋ ተገልብጧል
ኢ ኢ ኢ ስስስኮ አለቺኝ ምድነው እናቴ እጆቼ ግንባሮቿ ላይ ጣልኩት
ቶሎ እንድትመጣ እሺ አባቴ አለቺኝ በደም እጇ ከአንገቴ የተንጠለጠለውን የሰጠችን መስቀል በደም ለወሰቻቸው
ተማሪው ሜዳው ላይ ደርሷል ወዴት እንደምመጣ ባላቅም እሺ እንኩአን ሳልላት አፋፍሰው ወሰዱአት
እኔም በተማሪዎቹ ድጋፍ ተነስቼ እከተላት ጀመረ በታክሲ ተጭኜ ዝም ብዬ መጓዝ ጀመርኩ የተማሪዎቹን የለቅሶና የሀዘን ድምፅ እየሰማሁ ከአንድ ሆስፒታል ደጃፍ ደረስኩ
በነሱ ድጋፍ ከውስጥ ዘለኩ የት እንዳስገቡአት እንጃ ብቻ ሁለት ነርሶች ወደ እኔ መጡ ሊወስዱኝ ፈለጉ አይሆንም አልኩኝ  ቶሎ ና እሺ ቶሎ ና የመጨረሻ ድምጿ ከጆሮዬ ያስተጋባል ቃናዋ በህሊናዬ ያንሻብብ ጀመር
ነርሶቹ እንደያዙኝ እሪታና ጩኸት ሲበዛ የአለሜ ቃና በድምፃቸው ተዋጠ ነርሶቹ በሰሙት ጩኸት ለቀቁኝ
ሞታለች የሚል ድምፅ ስሰማ እኔም ሌላ ምት ወደ ጭንቅላቴ ሲመጣ ታወቀኝ ከመሬት ወደኩ ጭንቅላቴ ሲከፈል የጎን አጥንቴ ሲደቅ ተሰማኝ
እናንተዬ ልቤ እየቀነሰችብኝ ትንፋሽ እያጠረኝ ነው እጆቼ ንዝረታቸው ጨምሮ ምፅፈው ሁሉ እየተደለዘ ነው እፍን ምልስ እፍን ምልስ
ሞቷን ስነግራችሁ እኔም ልሄድ ነው መሰለኝ
ደሜ ወረቄትን ሸፍኖታል ድምፅ አልባው እንባዬ እየወረደ ነው ልሄድ ነው በቃ ልሄድ ነው ልቤ እየያዘገመች ነው እጆቼም ዝለውብኛል
እይኔ መስለምለም ጀምሯል ብዥ ብዥ ሆኖብኝ መስመሬን እየሳትኩ ነው ምፅፈው
ከዚ ወዲ ፋታ ለመውሰድ ብዬ ዜማ ስለማላጫውትላችሁ እቺን ብቻ ስሙልኝ እሺ ወደ እኔ ቶሎ ኑ እሺ እናንተም እዛ ስንገናኝ ብዙ ነገር ነው ማጫውታችሁ
መልአከ ሞት መጨረሴን አውቋል መሰል ቀኝ እጄን ለቀም አድርጎ ይዞኛል
በግማሽ ሞት እና በግማሽ ሂወት ውስጥ ነኝ
በግራው አይኔ ካለሁበት አለም ወጥቼ አዲስ ነገርች እያየሁ ነው
በቀኜ ደሞ በደም የተጨማለቀውን ገፄን
እቺን ስሙልኝ አደራ ቶሎ ኑ በሷ ቃል ነው እኔም ምሰናበታችሁ
ዜማዋ ልትጀምር ነው
          የት ነው የምትኖሪው ያለሽበት ቦታ
           ምንኛ ሀያል ነው ይህ ያንቺ ትዝታ
          ደቂቃዎች ሴኮንድ እንዴት ልለይሽ
                 የትዝታዬ ምንጭ ውሀ
            ውሀ ጥሜ ነ
እጅሽን ዘርግተሽ ባማረ ፈገግታ
እያልሽ ስጠሪኝ ና የኔ ትዝታ
ኡኡኡ ሰቀቄኔ ሆንሽብኝ ትዝታ
አይጠፋም ዘወትር ቁመናሽ ከፊቴ
ወዴት ነው ያለሽው በዛብኝ ናፍቆቴ
እንደምነሽ ልበል ባለሽበት ቦታ
ከልቤ ከትመሻል አልረሳሽም ላፍታ
ምኒሊክ ወስናቸውን እያጫወትኩላችሁ ነው አዎ ሁሉን ከትውስታዬ አጥቼ እሷን ብቻ ሳስብ ኖሬያለሁ አሁን ደሞ ወደ ጠራቺኝ ቦታ ልሄድ ነው ቶ ሎና ብላኛለች ልፍጠንባት ልዘግይባት ባላውቅም
እግዚአብሔርን እንዴት አምጣልኝ ብላ ብትለምነው እንዲ ቶሎ መልስ የሰጣት
ቶ መስቀሌን በቀኝ እጄ እፈታ ጀምሬያለሁ ምንም ክፉ ትዝታዬን ይሼ ወደ እሷ መመለስ አልፈልግም እዛ በመላእክቶች ታግሼ ፍለጋዬን ቶሎ እጀምራለሁ
ና ስላለቺኝ ከመግቢያው በር ላይ ቁጭ ብላ እንደምጠብቀኝ አምናለሁ
ለሀጢያቴ ወደ ሲኦል ባመራ እንኳ ከሷ ጋ ከሆነ ሁሉም ነገር እሷ ካለች ገነቴ ይሆናል
እሷ ስትሰናበተኝ በደም በተለወሰው እጇ መስቀሌን ቀብታዋለች እኔም ስነሳ መስቀሌን በደም ከተጨማለው ገፄ ላይ ጥዬዋለሁ
እሷን ስሰናበት የሰማሁት ነጎድጓድ አሁንም እኔን ሊሸኝ ነው መሰል ያንባርቅ ጀምሯል ፈራሁ ትለኝ የነበረው ሰአት እኔንም ያስፈራኝ ጀመር
ነፍሷን አርጥቦ የወሰደው ዝናብ የኔንም ነፍስ አርጥቦ ሊያበሰብስ ነው መሰል መዝነቡ ጀምሯል የምድሩን በደሌና ሀዘኔን ዝናቡ ሊያጥብልኝ ነው መሰል ዝናቡም ቀጥሏል
ነፍሴ በምወደው ዝናብ ታጅባ ልታመራልኝ ነው
ነጎድጓዱም ከሰማዩ ድንበር ቆሞ እንኳን ደህና መጣህ ሊለኘ ነጎድጓዱም ብርቅታውን ያጮኸው ጀምሯል
ልቤም ቆም መታ ቆም መታ ትላለች አይኔም ከጭለማው ገብቶ ብርሀኑን አቷል አፍንጫዬም ከጨለመው አለም ገባ መሰል በፊት ማውቀው ቃና አልሸትህ ብሎኛል ሁሉም ልዩ ሆኖብኛል
ቀኝ እጄን አፈፍ አደረገኝ ብዕሬም ወደቀ
ቃሌን ልስጣችሁ በቃ
ቶሎ ኑ እሺ

ተፈፀመ
✍️ብላቴናው

@wegoch
@wegoch
@wegoch
#ወግ_ብቻ
......ሳያስቡት፣ በድንገት ገደል ውስጥ የወደቁት ሁለት እንቁራሪቶች ከገደሉ
ለመውጣት መዝለል የጀመሩት ወዲያው ነበር፡፡ ግና….ምን ቢዘሉ ምን ቢፈርጡ
የገደሉ አፋፍ የማይደፈር ሆነ፡፡

ሁለቱ እንቁራሪቶች ባለ በሌለ ኃይላቸው ወደላይ መወንጨፉን ተያያዙት፡፡
እዚህ ገደል ውስጥ መቆየት ማለት ሞት መሆኑን ደመነፍሳቸው ይነግራቸዋል፡፡
ስለዚህም…መቸም መዝለል ያባት ነውና እንጥፍጣፊ ጉልበታቸውን አሟጥጠው
ህይወታቸውን ለማዳን ሽቅብ ይዘሉ ጀመር፡፡
የገደሉ አፋፍ ግን የማይደፈር ሆነ፡፡ እነሱም ግን የሚበገሩ አልሆኑም፡፡
መዝለል መፍረጡን፣ በዕልህ ሽቅብ እንጣጥ ማለቱን ቀጥለውበታል፡፡ በዚህ
መሃል የሁለቱን እንቁራሪቶች የመዝለል የመፍረጥ የእልህ ሲቃ የሰሙ ሌሎች
በአቅራቢያ ያሉ እንቁራሪቶች ወደገደሉ አፋፍ ቀርበው ቢያስተውሉ የሁለት
ምስኪን ብጤዎቻቸውን የሞት ሽረት ትግል ተመለከቱ፡፡ እልህ አስጨራሽ የሞት ሽረት ትግል ! የነዚህ ምስኪኖች ጥረት ከንቱ ሆኖ የታያቸው አሁን የመጡት እንቁራሪቶች ብዙም ሳይቆዩ ቅስም ሰባሪ አስተያየታቸውን መሰንዘር ጀመሩ፡፡

“አይ አትልፉ፣ መቼም ቢሆን ከዚህ ገደል ውስጥ አትወጡም” ሲሉ ጮሁ የገደሉን አፋፍ ሞልተው ቁልቁል የሚመለከቱት እንቁራሪቶች፡፡ ሁለቱ ምስኪኖች ግን
ለዚህ ቅስም ሰባሪ አስተያየት ጆሮም ሳይሰጡ የሽቅብ ዝላያቸውን ተያያዙት፡፡
ግ ና ብ ዙ ም ሳ ይ ቆ ይ ከ ሁ ለቱ እንቁራሪቶች አንደኛው የመዳን ተ ስ ፋ ው እየተሟጠጠ አቅም ይከዳው ጀመር፡፡ ከገደሉ አፋፍ ያሉ ብጤዎቹ የአትችለውም ሀሳብ ወኔውን ሰለበው፡፡ አቅም ከዳው፡፡ በተስፋ መቁረጥ እንደነገሩ አንዴ ዘሎ ተመልሶ በፈረጠበት በዚያው አሸለበ፡፡
ይኼኛው እንቁራሪት ግን የዋዛ አይደለም፡፡ የጓደኛው እንዲህ እንደቀልድ
በወደቀበት ማሸለብ ቢደንቀውም እሱ ግን መዝለሉን አላቋረጠም፡፡ ያለ የሌለ ኃይሉን አጠራቅሞ የሞት ሞቱን ሽቅብ መወንጨፉን ቀጠለ፡፡ እልህ አስጨራሽ ነበር፡፡ በስተመጨረሻ ግን ሆነ ተሳካለት፡፡ ኃይሉን አሰባስቦ አንዴ ሽቅብ ተወንጭፎ የገደሉ ከንፈር ላይ ጉብ አለ፡፡ ከገደሉ ወጣ፡፡ የ“አትችለውም፣ አትልፋ” ቅስም ሰባሪ ጩኸታቸውን ሲያዥጎደጉዱ የነበሩት ገደሉ አፋፍ የተሰበሰቡት ብጤዎቹ በእንቁራሪቱ ድል እጅጉን ተደንቀዋል፡፡ ምን ያለው ጀግና ነው በሚል አተያይ እያስተዋሉት በመኃላቸው አቋርጦ አለፈ፡፡ ግን… ከመሀከላቸው አንዱም ቢሆን ፈጽሞ ያልገመተው ነገር የዚህን እንቁራሪት መስማት ያለ መቻል ነበር፡፡ አዎን…ባለድሉ እንቁራሪት መስማት አይችልም ነበር፡፡ እናም፣ ለእሱ፣ የዛ ሁሉ እንቁራሪት የገደል አፋፍ ጩኸት አንዱም ጆሮው አልደረሰም፡፡ ይልቁንም፣ ከሁኔታቸው የሚያበረታቱ ብጤዎቹ ሆነው ነበር የታዩት፡፡ ስለዚህም እንቁራሪቱ አጀብ፣ በዚህ ጀግና እንቁራሪት ወኔ እንደተደመመ መስማት የተሳነውም ጀግናው እንቁራሪትም ገደሉ አፋፍ ላይ ሆነው ባይሰማቸውም፣ አበረታትተውኛል ባላቸው እንቁራሪቶች መሃል በልቡ እያመሰገናቸው በድካም እንደዛለ ጉዞውን ቀጠለ፡፡
@wegoch
@wegoch
@wegoch
የግል ስሜትና ብሄራዊ ምልክት
(በእውቀቱ ስዩም)
.
ባገራችን ህዝብ ከገዥ ጋር ተማክሮ የመረጠው ብሄራዊ ምልክት ኖሮ አያውቅም ፤ ያገር ገዥዎች የሆነ የስልጣን ምልክት ይመርጣሉ፤ ያ ምልክት በውድም ሆነ በግድ ብሄራዊ ምልክት ሆኖ ይቀራል ፤ገዥው አምራቹን ህዝብ( ገበሬውን፤አንጣሪውንና ነጋዴውን) አማክሮ የመረጠው ምልክት መኖሩን የሚያስረዳ ታሪክ ካለ አቅርብልኝ! የእድሜ ልክ ተማሪነኝና ሀሳቤን ለመቀየር አላቅማም!
አንበሳ የአራዊት ንጉስ ነው ተብሎ ይታሰብበት በነበረበት ዘመን ነገስታት አምሳላቸው አድርገው መርጠውታል፤ አንድም፤ የክርስቶስ ምልክት ስለሆነ የክርስትያን ነገስታት ምልክት ሆኖ ቆይቷል
ይሁን እንጂ ሁሉም ነገስታት ተመሳሳይ ልማድ አይከተሉም ነበር ፤ለምሳሌ ዳግማዊ ቴዎድሮስ አንበሳ ማህተም የነበረው ሲሆን ተተኪው አጤ ተክለጊዮርጊስ ነብርን በምልክትነት መርጧል:: ንግስተ ነገስታት ዘውዲቱ ርግብን (የኖህ ርግብ) የማህተሟ ምልክት አድጋለች ፤
ታሪክን ትንሽ ብንበረብር በቀጥታም ሆነ በእጅ አዙር ከአዋፋት ጋር የተቆራኙ ጌቶች ማግኘታችን አይቀርም፤ የካፋ ነገስታት እንደ ጥንታዊ ግብፃዉያን በላባ ያጌጠ ዘውድ ነበራቸው ፤ላባው ከየትኛዋ ወፍ አይነት እንደተነቀለ አላወቅሁም፤ ንጉስ ምኒልክ የሀረሩን ኢሚር አብዱላሂን በጦርነት አሸንፎ ከያዛቸው ምርኮዎች መካከል ለማዳ ውሻና ለማዳ ወፍ ይገኙበታል፤
“የምኒልክ ነገር
ይመስለኛል ተረት
አሞራው በቀፎ
ውሻው በሰንሰለት” ብላ የዘፈነችው ገንቦኛ የወፉን አይነት ለይታ አልነገረችንም፤ ግን የተሸናፊውን ያክል አሸናፊው የማረከው ብርቅ ወፍ ቢሆን ነው!
የጠቅላይ ምኒስትር አብይ አህመድ ጣዖስ የዘመኑን መንፈስ የሚያስረሳ ክርክር ቀስቅሳለች ፤ አንዳንዱ በሚያነሳው ክርክር ላይ አንዳች ፍሬ አይጠፋውም ፤ ስራ ከምፈታ ልጄን ላፋታ ብሎ የተሰማራም ሞልቱዋል ፤ ስለ ጣኦስም ሆነ ስለ አንበሳ ትርጉዋሜ በሰፊው እመለስበታለሁ ፤
አይበልብኝና ስልጣን ላይ ብወጣ የአንበሳንም ሆነ የጣኦስን ሀውልት አላፈርስም፤ በነበረው ላይ የራሴን ብሄራዊ ምልክት እመርጣለሁ ፤ ከበሬ ሌላ ማንን ልመርጥ እችላለሁ? የሚወዱኝ ለምልክቱ ጥሩ ጥሩ ትርጉም እየሰጡ ይደግፉልኛል፤ በውቄ ለመጀመርያ ጊዜ አርሶ አደሩን የሚያከብር ብሄራዊ ምልክት አስተዋወቀ እያሉ ያወድሱኛል፤ የሚጠሉኝስ? “በሬ” የሚለው ቃል ባንድ አዳር ስድብ አድርገውት ያድራሉ፤ ችግሩ ከምልክቱ አይደለም፤ ለምልክቱ ባለቤት ካለን አስተያየት ነው፤ ስሜት ከአእምሮ በላይ እንደሚበረታ ለማስረዳት ሾፐናወርንና ብጤዎችን መተንተን አይጠበቅብኝም ! እነዚህን ያገራችን ተረቶች ብቻ ማየት ይበቃል;
-ሰውን ሲወዱ ከነ ንፍጡ !
-ጠላት ይቀባል ጥላት !

@wegoch
@wegoch
#ወግ_ብቻ
.
.......አንድ ሰው በባህር ብቻውን በመርከብ እየተጓዘ እያለ
በመዓበል ተመታና መርከቡ ተሰባብሮ በባህሩውሰጥ ሰመጠች ሰውዬው እንደምንም እራሱን አድኖ አንድ ደሴት ላይ ያርፍና ጎጆ ነገር ሰርቶ ለቀናት ለብቻው እዛች ደሴት ላይ ይኖራል ,,,,,,,,ምግብ ዓሳ እያጠመደ እየተመገበ ብዙ ቆየ። አንድ ቀን ዓሳ ሊያጠምድ ወደ ባህሩ እየሄደ በመሀል እዛች ባህር ላይ ጭስ ይሸተዋል ዞር ብሎ ሲመለከት
ያቺ ጎጆው እየነደደች ነው ,,,,,,,እየሮጠ ቢመለስም ጎጆዋን ሊያድናት አልቻለም ለካ ዓሳ ለማብሰል ያቀጣጠለው እሳት ተያይዞ ጎጆውን አንድዷታል አለቀሰ ፈጣሪውን ወቀሰ እንዴት እዚህ ባህር ላይ ለብቻዬ ጥለከኝ ከቤተሰቦቼ ነጥለኸኝ ስታበቃ በስንት ልፋት የሰራዋትን ጎጆ ታቃጥልብኛለክ ብሎ አለቀሰ አማረረ,,,,,,,, ከደቂቃዎች በኋላ አንድ ድምፅ ሰማ ወደ
ድምፁ ፊቱን ሲያዞር አንድ ትልቅ መርከብ አየ ተደሰተ ,,,,,, የመርከቡ ሰዎችም መጥተው ጭነው ወሰዱት
ከዚያም ለመርከብ ሰዎች ጠየቃቸው !
እንዴት አገኛችሁኝ እዚህ አካባቢ እዚህ ባህር ላይ ማንም አይመጣም እኮ እናንተ እንዴት መጣችሁ ?
አላቸው ,,,,, መርከበኞቹም እኛም በዛኛው በኩል ዞረን እየሄድን ነበር ከዚያ በኩል ጭስ አየንና እዚህ ሰው ይኖራል ብለን መጣን አንተ አገኘን አሉት። አቤት ጌታዬ ለካ ከዚህ ከስቃይ ልታወጣኝ ፈልገህ ነው ትንሿ ጎጆዬን ያፈረስከው ወደ ትልቁ ቤቴ ልትወሰደኝ ነው ። አለ
አንዳንዴ የሆነ ነገር ስናጣ ሲበላሽብን ፈጣሪንም ሰውንም ስናማርር እንኖራለን ግን ካጣነው ነገር ከጎደለብን ነገር ጀርባ ብዙ ጥሩ ነገር ልናገኝ እንደምንችል እንዘነጋለን በችግራችን ጊዜ መጠጋት
ያለብንን አንድዬን እንረሳለን ከዚያም አልፈን የሁሉ ነገር ፈጣሪውን እንኮንነዋለን ።ያጣነውን የሰጠን እግዚአብሔርን አእምሯችን ከሚያስበው በላይ ሊሰጠን እንደሚችል ማመን አለብን። እግዚአብሔርን እንደ ቅዱሳን በእምነት መፅናትን ያድለን። አሜን
@wegoch
@wegoch
@wegoch
Forwarded from Mikiyas Liyew Mykey
''ደቦ''
የጉዞ ማስታወሻ
በ ''ሄኖክ ስዩም''
ክፍል ፩
(፷ ደራሲያን ከተሳተፉበት መፅሐፍ ዘንድ ያገኘነው ፁኹፍ ነው)

@Wegoch
@Wegoch
@Wegoch
Forwarded from Mykey (Mikiyas Liyew Mykey)
ሸማኔዎች ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ስራቸውን ሰርተው ከተለያዩ ቦታዎች (ከሰበታ፣ ከአስኮ፣ ከኮልፌ፣ ከአንቆርጫ፣ ከኮተቤ ወዘተ) እሁድ ሽሮሜዳ አምጥተው ይሸጣሉ!

አሁን ግን ከኮሮና ቫይረስ መከላከል ስራ ጋር በተያያዘ ተለዋጭ ቦታ ስላልተሰጣቸው ችግር ላይ ናቸው፣ እንደውም በዱላ እየተደበደቡ ይበተናሉ።

የቤተሰብ አስተዳዳሪዎች አሉ፣ ብዙዎቹ በኪራይ ቤት ይኖራሉ። "ሰርተን መሸጫ ስላጣን ድምፃችንን አሰሙልን" ስላሉኝ ይህንን መረጃ አጋራሁ።

ጋዜጠኛ ኤልያስ መሠረት(AP)
ፎቶግራፍ:- ሚኪያስ ልየው(ከእነእርሱስ Project)
@Eliasmeseret
@Mykeyonthestreet
''ደቦ''
የጉዞ ማስታወሻ
በ ''ሄኖክ ስዩም''
ክፍል ፪
(፷ ደራሲያን ከተሳተፉበት መፅሐፍ ዘንድ ያገኘነው ፁኹፍ ነው)
አቅራቢ @Mykey21

@Wegoch
@Wegoch
@Wegoch
#የእሳት ላይ ቁጥሮች

    ክፍል - ፩

ከሰሞኑ በመላው የዜና አውታሮች በሬዲዮ ጣቢያዎች አንድ አይነት ነገር ነው ሚሰማው
ሁሉም ዜናዎች #ሻርማይክ በሚል ስም እራሱን በሚያንቀሳቅሰው ቡድን ላይ ሆኑአል ዘገባቸው
ከሬዲዮዋ የምቶጣውን ድምፅ በእሳቱን መሞቂያ ዙሪያ ያሉት 7 ሰውች እየሰሙት ነው ምንም አይነት ስሜት ከፊታቸው አይነበበም
ሬዲዮዋ ቀጠለች ....
የቅርስ ተቋሙ በስልክ ባደረሱን መረጃ በሀገራችን ውስጥ ከ12 በላይ ገዳማትና ሁለት የቅርስ ተቋማት ላይ ከፍተኛ የሆነ ዘረፋ ተፈፅሟል ጋዜጠኛው ፈጠን ብሎ
በሁሉም ገዳማትና በተሰረቁት ተቋማት ላይ #ሻርማይክ የሚል ፅሁፍ በሮዝ አበባ ላይ ታትሞ እንደተቀመጠ መረጃው ደርሶናል ፖሊስ በሰጠን መረጃ መሰረት እስካሁን ማን ይሁን በማን ምንም አይነት ፍንጭ አለመገኘቱንና በተለየ መልኩ ዘረፋው እንደተካሄደ ገልጿል
በተጠናከረ መልኩ አሳዶ ለመያዝ ቃልም ገብቶልናል
በመጽሀፍ ከተሞላው ቤት ውስጥ አንድ ጠረጴዛ ላይ የተቀመጠች አንድ ሬዲዮና ድምጿን ሞቅ እያረገ ወደ ጆሮ ከሚያስገባው የእሳት ማሞቂያ በቀር ሌላ ምንም ነገር የለም
የቤቱ ዝምታ አስፈሪ ሆኑአል 7 ወንበሮች ላይ 7 በፀጥታ ተውጠው የተቀመጡ ሰዎች ከሬዲዮዋ ምቶጣውን ድምፅ ከዜና አንባቢው እየመነተፉ በእሳት ነበልባሉ እያሞኩ ከጆሩአቸው ይከታሉ
እስከዛሬ ጠብቀው ያቆዩት ቅርስ ይመስል ተንከባክበው የጠበቁት ይመስል በሸረሪትና በአይጥ አር በተሞላ ጉሮኖ ውስጥ ሲኖር ለምን እንደዚ አላንገበገባለው   ቲሽ.....
የቤቱን ዝምታ ተሰበረ ወጣቱ መነፅሮቹን ወደ ላይ በጣቶቹ እየገፋ ንግግሩን ሊቀጥል ሲል
ሬዲዮዋ ቀደመችው...."
ከአበባውና ከታተመው ሻርማይክ የሚል ፅሁፍ ጀርባ ምን ይሆን ያለው ጋዜጠኛው እስከ ወዲያኛው ሄደ
ሀገር ማለት ሰው ነው
ሰው ነው ሀገር ማለት ለሬዲዮ ማስተዋወቂያ የምትውለዋ ዘፈን ትስረቀረቅ ገባች
ሀገር ሀገር   ሀገር ሰው ነው እያሉ ነው እዚ የሚጫወቱብን
 ሰዉ እንኳን ሀገር ሊሆን ምንም ስሜት በውስጡ ሳይኖር በዚች ሀገር ተብላ በተሰየመች ረቂቅ መሬት ላይ ይኖራል ወጣቱ ልጅ ቀጥሎ አሁንም አፉን ያዘ
ሬዲዮዋ ቀጠለች
ከሰሞኑ ሁኔታ ጋር ተያይዞ ህዝቡ በነገሩ ስለተቆጣ በመንግስት ላይ ተቃውሞውን እያሰማ ይገኛል
በገዳማቶቻችንና በያዙት ቅርስ ላይ ሚደረገው ስርቆት ይብቃ መንግስት በቶሎ ዘራፊዎቹን ለህግ ያስረክብ
አንድ ወጣት በወኔ ከራዲዮዋ ዘራፍ ይላል
ተወልዶ እዚ እስኪደርስ ሄዶ ያልግበኘውን ቅርስ አሁን ሲዘረፍ እሪ ይላል ይሄኔ ወደ አንዱ ገዳም ይዘህ ሄደህ ታሪኩን ከምትነግረው ትንሽ ክለብ ውስጥ ከተህ አንድ መጠጥ ብጋብዘው ለሱ ደስታ ነው
ደሞ ያወራል እኮ ልክ ነኛ
 ወጣቱ የስድስቱን ሰዎች ዝምታ ለመስበር እየጣረ ነው
ሬዲዮዋ ቀጠለች የእሳቱ ሙቀት ለምታወጣው ዜና ቆንጆ አሟቂ ሆኖላታል ከሁሉ በላይ የሞቀው ወጣቱ ልጅ ነው
ነገሩ ልዩ ሁኔታን ፈጥሯል ሻርማይክ ሮዝ አበባ እና የዘራፊው ቡድን ሁሉም አይኖች ሬዲዮዋን የአንዲት ሴት እጅ ጠረቀማት
#ከአንድ አመት በፊት
ወደ ፖሊስ መምሪያዎች የሚመጡ የአፋልጉኝና የጠፋብኝ መረጃዎች ተበራክተዋል
ከሁሉም ልዩ ያደረገው ጠፉ እየተባሉ መረጃ የሚሰጥባቸው ሰዎች ተመራማሪዎች የታሪክ ምሁራን ደራሲዎች የኮምፒውተር ባለሙያዎች መሆናቸው ነው ፖሊስ ከነገሩ በስተጀርባ ማን እንዳለ ስለሚያውቅ ለነገሩ መልስ ከመስጠት ተቆጥቧል
መንግስተ ባደራጀው አዲስ ስርአት ለሀገር ጠቃሚ የሆኑ ምሁራንን ከያሉበት እየወሰደ ወደ አዲሱ #ናጋዚ ብሎ ወደ ሰየመው ማጎሪያ እያስገባቸው ይገኛል
የቤተሰብ ዋይ ዋይታ የምሁራኑ እናቶች እንባ የቤተሰቦቻቸው ጩኸት ተበራክቷል
ፖሊስም በለመደው መልሱ በቅርቡ ተጨባጭ ማስረጃ እስክይዝ ጠብቁኝ ይላቸዋል
በቅርቡ የሁለቱ ምሁራን አባት አቶ ታምሩ የፖሊስን በር አንኳክተዋል ልጆቼ ብለዋል
ዶክተር ናትናኤል ታምሩ እና ደራሲ ዮቶር ታምሩ ከጠፉ ሁለት ቀን እንደሞላተው አስረድተዋል እሳቸውም የአባት አንጀታቸውን ታቅፈው ሄደዋል
#የናጋዚ ተቋም ባጨቀው የምሁራን ብዛት ወለሉ ሳይቀር እውቀት እውቀት ብሏል
የት ነን ......
   
      ብላቴናው በእሳት ገፆች ላይ

@wegoch
@wegoch
@wegoch
እንደው ይጠቅማልና ይኼን ልዩ ወሬ ስሙማ
አቅራቢው:-ወንድሙ ሃይሉ (ሸገር ራዲዮ)
.
.
.
.
.
@Wegoch
@Wegoch
@Wegoch
''ደቦ''
የጉዞ ማስታወሻ
በ ''ሄኖክ ስዩም''
ክፍል ፫
(፷ ደራሲያን ከተሳተፉበት መፅሐፍ ዘንድ ያገኘነው ፁኹፍ ነው)
''በአፅንኦት የተተረከ''
የኋላውን ዝምታ ለማስከን ያኽል :- የጋሽ ሙላቱ አስታጥቄ ጃዝ ስራዎች
አቅራቢ @Mykey21

@Wegoch
@Wegoch
@Wegoch
ታጋቹ ማስታወሻ
( በእውቀቱ ስዩም)
ቀሳ ከወጣሁ ጊዜ ጀምሮ ቤቴ ውስጥ ያገኘሁት ምግብ ሩዝ ብቻ ነው ፤ ሰኞ ሩዝ በቲማቲም- ማክሰኞ ሩዝ በጅንጅብል- ረቡእ ሩዝ እንደወረደ፤ ወዘተ…ባጭሩ በሩዝና በሪዝ ተከብቤ ሰነበትሁ ማለት ይቻላል፤ አንዳንዴ ምግብ የቀየርኩ እንዲመስለኝ የምበላበትን ቦታ እቀያይራለሁ፤ ሳሎን ውስጥ ሁለት ማንኪያ እጎርስና የተረፈውን በረንዳው ላይ ተቀምጨ እጨርሰዋለሁ፤
ሩዝ ጠዋት ማታ ከመብላቴ የተነሳ ወደ ማጅራቴ ሲሸሽ የነበረው ፀጉሬ ተመልሶ ቅንድቤ ድረስ ግጥ—ም አለ ፤ የህንድ አክተር ለመምሰል የቀረኝ በሱሪ ላይ ቀሚስ መደረብና ባየር ላይ የሚበር ሞተር ሳይክል መንዳት ነው፡ ፡
የሆነ ግልገል ጉንዳን ጠረጴዛየ እምብርት ላይ ከተበተኑት የሩዝ ቅንጣቶች መካከል አንዲቱን መርጦ ተሸክሞ ሲያዘግም ተመለከትኩ ፤ኩንታል መሸከሙ ነው፤ አይ ጉንዳን! አሁን ጉንዳንን የመሰለ ታታሪ ፍጡር በሚኖርበት አለም የሰው ልጅ የላባደሮችን ቀን ያከብራል ? ልይዘው ሞከርኩ ፤የጣቶቼን ጥላ ሲያይ ኩንታሉን እንደተሸከመ መሮጥ ጀመረ፤ አምልጠህ ሞተህል ባክህ! !ባውራ ጣቴና በነገረኛ ጣቴ መካከል አጣብቄ ያዝኩት ፤ የሞተ መስሎ ፀጥ አለ፤ ለካ አስመሳይነት የሰው ልጆች ባህርይ ብቻ አይደለም፤ ትወናውን አድንቄ በተሸከመው የሩዝ ቅንጣት ላይ አንዲት የቲማቲም ፍሬ መርቄለት ለቀቅሁት፤
ባለፈው ለለውጥ ያክል የሱካር ድንች ለመቀቀል ሞከርኩ፤ የአሜሪካ የሱካር ድንች አንዱ ፍሬ የድሮ ካውያ ያህላል ፤ ችግሩ በቀላሉ አይበስልም፤ እንዲያውም ካሜሪካ ሱካር ድንች፤ የኢትዮጵያ በሬ ሸኮና ቀድሞ ይበስላል፤ ቤት ጠርጌ ፤ምንጣፍ ቀይሬ፤ ኮርኔስ ራሱ ቀይሬ ተመልሼ መጥቼ ሳየው፤ አልበሰለም፤ ምን ጉድ ነው! ከዛ ገላየን ተታጥቤ፤ ብብቴንና በስተራስጌ የሚገኘውን ሁሉ ተላጭቼ ለባብሼ ሳበቃ ብረትድስቱን ከፈትኩት፤ ድንቼ መብሰሉን ለማረጋገጥ በሹካየ ወጋ አደረግሁት፤ እንዴየየየየ! የሹካው ጥርስ ተጣመመ፤ በጣም ተናደድሁና አውጥቼ በመስኮት በኩል ወረወርኩት፤ ድው! የሆነ ሰውየ oh Fuck! ብሎ ሲወድቅ አየሁት፤ ልጅ እያለሁ እናቴ “ ምግብ መወርወር ጡር ነው “ ትለኝ ነበር፤ እረ ጦርም ነው እማየ ፤ ይሄው አንድ ምስኪን ፖስታ አመላላሽ ፈረንጅ ለትንሽ ገድየ ነበር!
በክቡር ዳኛ Frank Caprio ፊት ቀርቤ ፤የፈነከትኩት ሰውየ እስኪሻለው ድረስ አልጋው አጠገብ ተቀምጨ በእንግሊዝኛ እንዳስታምመው ፈረዱብኝ! ሁለት ወር ሙሉ ተጎድቼ እንደከረምኩ ያወቅሁት በሆስፒታሉ ውስጥ የሚቀርበልኝን መኖ ሳይ ነው-ቆስጣ፤ የወይን ዘለላ፤ በማር የተጠበሰ ዳቦ! ግሪክ ሳላድ! እረ ወገን! ላስታማሚው እንዲህ አይነት ምግብ ከቀረበ ለታማሚው ምን እንደሚቀርብ ኢማጂን እንግዲህ!
ባልተያያዘ ዜና ፤
እንደ ዶክተር አቢይ አህመድ ያለ ብልጥ ሰው ግን አለ? ፤ ሰልስትና (ከሶስት ቀን በፊት) ተቃዋሚዎችን ፓርላማ ውስጥ ሰብስቦ ሲያወራ ማስኩን ካፍንጫው ሸርተት አድርጎ ከንፈሩ ላይ አስቀምጦት አየሁ ፤ ብዙ ሰው ስትራቴጂ መሆኑ የገባው አልመሰለኝም ፤የተፎካካሪ ፓርቲ ሊቀመንበሮች " አንተ ብቻ ነህ እንዴ አፍንጫህን የማናፈስ ነፃነት ያለህ ?ብለው በእልህ ማሳካቸውን ገለቡት ፤ አብቹየም ሁሉም አፍንጫውን ማጋለጡን ከተመለከተ በሁዋላ ፈገግ ብሎ በልቡ፤ “ጎበዝ! እንግዲህ ይቺን ቫይረስ እንቃመሳታ ፤ እኔ ጎልማሳ ስለሆንኩ አገግሜ እነሳለሁ ፤ ለእናንተም ደግሞ አካላዊ ርቀቱን ያስጠበቀ ቀብር አስከባሪ ይዘጋጃል” ካለ በሁዋላ የምትከተለዋን ዘለሰኛ ማስታወሻው ላይ አሰፈረ፤
ጎልማሶች ከመከራ ስንማር ፤
ለሼባዎች ነፍስ ይማር !

@wegoch
@wegoch
@wegoch
Forwarded from Mykey (Mikiyas Liyew Mykey)
ጣዕም ያላቸው ወዞች!
ኹሌም ቀኑን ለምታከብሩት ለእናንተ ይኹን

ከእነእርሱስ ፕሮጀክት © Mikiyas Liyew
@Mykeyonthestreet
2024/09/26 23:15:44
Back to Top
HTML Embed Code: