Telegram Web Link
የአንድ ወር ተግባራዊ የህይወት መምሪያ ስልጠና።

-የህይወትን አላማ ማግኘት
-የስሜት ብልህነት
-ችግሮችን መፍታት
-ጭንቀትንና ፍርሀትን መቀነስ ማስወገድ እና ሌሎችም ስልጠናዎችን ያካተተ ነው።

ልምድ ባላቸው ሳይኮሎጂስቶችና የህይወት ክህሎት አሰልጣኞች ይምጡ ይሰልጥኑ።

ሁሉንም ስልጠናዎች ለተካፈለ በነፃ የንግግር ክህሎት ስልጠና ሰርተፊኬትን ጨምሮ ያገኛል።

ለበለጠ መረጃ
0946333951
0912664084 ይደውሉ።

ህዳር 20 ይጀምራል

👇👇👇👇
@temuabiy
@temuabiy
@temuabiy
ለውብ ቀን!
💚

ከዶ/ር ክዋሜ ንክሩማህ አይረሴ ንግግሮች
---------------------------------------------------------
“አፍሪቃዊ የሆንኩት አፍሪቃ ውስጥ በመወለዴ ሳይሆን አፍሪቃ እኔ ውስጥ በመወለዷ
ነው።”
* * *
“ የእኛ ዓላማ ‘የአፍሪቃ አንድነት አሁን! ’ ነው። የምናባክነው ጊዜ አይኖርም። ያለን
አማራጭ አሁኑኑ አንድ መሆን አለያም መጥፋት ነው። እናም በተባበረ አቋምና ጥረታችን
እዚሁ የአፍሪቃን አህጉራዊ መንግሥት መሠረት እንጥላለን ብዬ አምናለሁ።”
* * *
“ነፃነት አንድ ህዝብ ለሌላኛው እንደ ስጦታ የሚያበረክተው ነገር አይደለም። ይልቁን እንደ
ባለቤት የሚጠይቁት እና ማንም ማንንም ሊነሳው የማይችለው ነው።”

"ናካይታ"💚

@wegoch
@wegoch
ለውብ ቀን!
💚

#ዛሬ እጅግ በጣም የማከብረውና የምወደው አሰፋ ጫቦ "የትዝታ ፈለግ " ከሚለው መፅሐፉ ላይ በጣም የወደድኩትን ጀባ ልላቹ ፈለኩኝ.....


“ እኔ የምፅፈው ማንንም ለማስደሰት አይደለም። ማንንም ለማሳዘንም አይደለም። ሙግት
ለመፍጠርም አይደለም። ውይይት ለማካሄድ ነው። አተካሮ ለመፍጠር አይደለም። የሰከነ
ሀሳብ ማንሸራሸር ቢቻል ብዬ ነው። ንትርክ ለመፍጠር አይደለም። ይህ “ውሃ ወቀጣ”
የሆነውን አመለካከት ውሃውን ቦይ ቀዶ፣ ዘር ሰጥቶ እንዲፈስ ለማድረግ ነው። መስኖ ሆኖ
ሀሳባችንን እንዲያሳድገው ለመሞከር ነው። በአጭሩ የሰከነ ውይይት (Civil discourse)
ለመፍጠር ነው።
“Do not shoot the messenger!! ” ይላል። መልዕክተኛውን ተኩሰህ አትጣለው
ለማለት ነው። መልዕክቱን ክፈተው፤ እየው። አዳምጠው። ካልገባህ የገባው ፈልግና ተረዳ
ለማለት ነው። …
… የምንፅፈው የምንናገረው “ለጋራ ቤታችን” ወይም ከዚያ ለተረፈው ቢሆን ጥሩ ነበር።
አብርሃም ሊንከን ‘with malice toward none, with Charity for all with
firmness in the right as God gives us the right to see ...’ እንዳለው
ብንሞክርስ! ‘ፊታችንን ያለ ቂም በቀል ወደ ሁሉም ብንመልስ፣ ሁሉንም እጅ ዘርግተን
ብናቅፍ፣ በሀቁ ላይ ፅናት ቢኖረንም ይህን ሀቅ እንድናይ አምላክ ዓይናችንን ቢከፍተው … ’
የኔ ትርጉም ነው! ”

– አሰፋ ጫቦ (“የትዝታ ፈለግ” መጽሐፍ፣ ገፅ 207)

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
‹‹ይሄ ጡት መያዣ የመቼ ነው?››
--------------------
(ሕይወት እምሻው)

መነሻ ሃሳብ- Sex and the City ተከታታይ ፊልም ከእኔ በፊት አለሌ ነበር፡፡ የወጣለት ሴት አውል፡፡ ከሸሚዙ እና ከካልሲው በላይ ሴት የሚቀይር፡፡ ቁርስ ላይ አንዷን አሽኮርምሞ፣ ምሳ ላይ ካንዷ ተነካክቶ፣ ለእራት ደግሞ ሌላዋን አብስሎ ከእሷ የሚያነጋ አይነት፡፡ ልጃገረድ ከባለትዳር፣ የቤት ልጅ ከሴት አዳሪ ሳይል፣ ከሴት ሳይመርጥ፣ ከቀሚስ ለባሽ ሳያዳላ የሚፈጅ የወንድ ማሽን፡፡ እንስትን ሁሉ የሚረፈርፍ የወንድ መድፍ፡፡ ያገኛትን ሴት ሁሉ በወንድነቱ የሚያርስ፣ ካጋጠመችው የሚገጥም…ከዚያ ደግሞ ወዲያው ጣእሙ እንዳለቀ ማስቲካ ተፍቶ ሌላ- አዲስ- የታሸገች- ያልነካትን ለማግኘት የሚቅበዘበዝ፡፡ ልክ እንደዛ
የድሮ የአራዳ ልጆች ዘፈን ቀን ሳይቀጣጠር ማታ ቆንጆ ይዞ የሚያድር አይነት ሴት አውል፡፡ ደጁ መዘጋት አያውቅም ነበር….ልክ እንደ ራስ ሆቴል ተሸከርካሪ በር ነበረው…አንዷ በዚያኛው በኩል እየገፋችው ስትወጣ ሌሎቹ ደግሞ በዚህኛው በኩል ገፍተው የሚገቡበት ተሸከርካሪ በር የነበረው አይነት ነበር…..እኔን ካገኘ ወዲህ ግን በፊት የሚያውቀው ሰው ሁሉ ግር እስኪለው ድረስ ተረጋጋ፡፡ ልቡ አረፈ፡፡ ቀልቡ ተሰበሰበ፡፡ አይኖቹ ካለእኔ አላይም አሉ፡፡ ገላውም ከእኔ ገላ ውጪ አልነካ አለው፡፡ በእኔ ቆረበ፡፡: ‹‹በፍቅርሽ ተጠምቄ አዲስ ሰው ሆንኩ›› ብሎ እስኪምል…ብሎ እስኪገዘት አዲስ ማንነት አበቀለ፡፡ ያለፈ ታሪኩ የሚያስተምረኝ፣ ጓደኞቼ የሚሉኝ ሌላ ቢሆንም አምነዋለሁ፡፡ ‹‹አንቺን አገኘና አሌለነቱ የሚለቀው ይመስልሻል…? አትሞኚ›› ቢሉኝም ፤ መንፈቅ በሞላው ፍቅራችን- ቀን በቀን ስንገናኝ ብዙ አይቼዋለሁ፡፡ እንዳላምነው ምክንያት ስላልሰጠኝ፣ ሰው ባለፈው ሕይወቱ - ሰው ባለፈው ስህተቱ ብቻ ሊመዘን እንደማይችል ለመረዳት የሚያስችል ፍቅርና ብስለት ስላለኝ አምነዋለሁ። ሆኖም ግን ትላንቱን ዛሬ ላይ እያመጡ፣ የዛሬ ውብ ማንነቱን በድሮ እሱነቱ
እያጠለሹ የሚፈትኑኝ ጠንቆች አልጠፉም፡፡ ምን እንደሆነ ባላውቅም ከአዲሱ ሰው ጋር ወደፊት ልራመድ ስል የድሮውን እየመለሱ የኋልዮሽ የሚጎትቱ
ፈተናዎቸ ደግሞ ከሰሞኑ በዙብኝ፡፡
ፈተና 1…. መቼ እለት ካልዲስ ቁጭ ብለን ካታንጋን በሚያስንቀው የካፌው ሰው ጩኸት መሃል የቻልነውን ያህል ጮክ ብለን እያወራን ለመሰማማት ፍዳችንን ስናይ… ….አንዲት እንደጉድ የምታምር ሁሉነገሯ ረጅም የሆነ ሴት ከየት መጣች ሳትባል
ወደ ተቀመጥንበት መጣችና ጀርባውን…አለ አይደል…የሆነ ከዚህ በፊት ብዙ
ጊዜ እንደነካችው…ብዙ ጊዜ እንደዳበሰችው አይነት- ልክ ባልሆነ- በጣም እንቀራረባለን- ይሄን ጀርባ ራቁቱን አይቼዋለሁ- ይሄን ጀርባ ራቁቱን
ስሜዋለሁ...- ይሄን ጀርባ ጭኖቼን ከፍቼ አቆላልፌበታለሁ- በሚል አኳሃን ስትነካው ክው ብሎ ተነሳ፡፡ ‹‹ጄ…ሪ!›› አለ ደንግጦ ዞሮ እንዳያት፡፡ ምንም ሳትናገር እዛ የመድሃኒት ቤት ማስታወቂያ ላይ እንዳለው- ዋንጫ ነገሩ ላይ እንደተጠመጠመው እባብ ተጠመጠመችበት፡፡ እሱን ከእሷ ለይቼ ማየት እስኪያቅተኝ ሁሉም ቦታ ላይ ተለጠፈችበት፡፡ እንዴት ነው ነገሩ? አልታይም እንዴ? በትግል ራሱን አላቀቀና- እንደምንም በመሃላቸው ሌላ ሰው የሚያስገባ ክፍተት ፈጠረና- በመርበትበት ወደ እኔ እያየ- ከዚያ ደግሞ እሷን መልሶ እያየ….‹‹
እንዴት ነሽ..?›› አላት፡፡ ‹‹እኔማ ደና ነኝ….አንተ እንዴታባህ ነህ?እ? እኔማ አለሁ እንዳማረብኝ…ሰው እንደቀናብኝ…አታየኝም?›› ብላ ደማቅ የሴት አዳሪ ሳቅ የሚመስል ሳቅ እየሳቀች (አይደለም…እያሽካካች) አንዴ- ከዚያ ደግሞ ሁለቴ ተሽከርክራ ሁለንተናዋን አሳየችው፡፡ ራሷን ኤክስፖ አቀረበች፡፡ እንዴት ነው ነገሩ? አሁንም አልታይም እንዴ? እሷን ትቶ ወደእኔ መጣና እጄን ይዞ ያለፈቃዴ- ያለ እቅዴ ጎትቶ አነሳኝና ‹‹ጀሪዬ….ሚስቴን ተዋወቂያት….›› ብሎ አጠገቧ አቆመኝ፡፡ ‹‹አትንበላጠጪብኝ- አትሸከርከሪብኝ- ሰው አለኝ- ተዋወቂልኝ- እወቂልኝ››
ማለቱ ነው፡፡ ኩራት ቢጤ እየተሰማኝ እጆቼን ዘረጋሁላት፡፡ በጣም ረጅም መሆኗ የታወቀኝ እጄን ቀጥታ ሳይሆን ሽቅብ መስደዴን ሳይ ነው፡፡ የማነስ፣ የመኮሰስ ስሜት ተሰማኝ፡፡ ጠዋት እንዳቀድኩት ከፍ ያለ ጫማ ባለማድረጌ በራሴ ተበሳጨኹ፡፡ ‹‹ኦ…ሃይ…ጄሪ እባላለሁ…›› ብላ እንደ ህፃን ወደ ታች እያችኝ፣ እንዳች የስሜት
ለውጥ ሳታሳይ ጨበጠችኝ፡፡ ስሜን ነግሬያትና የውሸት ፈገግ ብዬ በፍጥነት ወደ ወንበሬ ተመለስኩና ተቀመጥኩ፡፡ እሱም ልትነካው ስትጠጋ እየሸሻት- አስሬ ወደ እኔ እያየ- ሽምቅቅ እያለ አንድ ሁለት ነገር ከተባባሉ በኋላ ሂደችና ተመልሶ ተቀመጠ፡፡ ዝም ብዬ አየሁት፡፡ ‹‹በፊት…ድሮ….በጣም በፊት የማውቃት ልጅ ናት…›› አለኝ የጥፋተኝነት ስሜት
ባሸነፈው ድምፅ ‹‹የማውቃት›› ሲል ምን ማለቱ እንደሆነ እኔም እሱም እናውቃለን፡፡ እንደምንም ፈገግ አልኩና እጁን ያዝኩት፡፡ እሱም በእፎይታ ፈገግ ብሎ የቀዘቀዘ ስፕሪሱን ተጎንጭቶ ሊስመኝ ጠጋ አለ፡፡ ፈተና 2 ከጄሪ በኋላ በስንተኛው ቀን እንዲህ ሆነ፡፡ ወክ እናድርግና ሙቪ ምናምን እንግባ ተባለን ሴንቸሪ ሞል ስንደርስ የሙቪ ሰአት ስላልደረሰ በየፎቁ ባሉት ዋጋቸው የማይቀመስ ቄንጠኛ ቡቲኮች ወጣ ገባ እያልን እንደበራለን፡፡ ሁለተኛ ፎቅ ስንደርስ ከቡቲኮቹ አንዷ መስኮት ላይ የምትታየው መልከመልካም አሻንጉሊት የለበሰችው ጃምፕ ሱት ማረከኝና…የፋሽን ነገር አይሆንልኝምና፤ ‹‹ጆንዬ በናትህ…ይሄን ነገር ልየው…›› ብዬው ጎትቼው ገባን፡፡ ሌላ ነገር ሳላይ ጃምፕ ሱቴ ጋር ጠጋ ብዬ ስነካካው ሳየው…..ስንገባ እንደዋዛ አየት ያደርኳት ከረጅም ባልኮኒ ጀርባ ተቀምጣ ስልኳን ትጎረጉር የነበረች- ከአንገት በላይ ስትታይ ደቃቃ የምትመስል- በኋላ ተነስታ ስትመጣ ግን መለስተኛ ኮረብታ የሚያህል ቂጥ ያላት ልጅ ጮክ ብላ- ‹‹እኔ አላምንም ጆንዬ!›› እያለች ከመሄድ ይልቅ ለመብረር በሚቀርብ ፍጥነት ወደ እሱ መጣች፡፡ በፍጥነት ዞርኩ፡፡ ጆንን አየሁት፡፡ በአስራሁለት ሰአት- ያውም በጥቅምት ምሽት ፊቱ በላብ ተዘፍቋል፡፡ ‹‹እህህ…ሰርኬ!›› አለ ለእቅፍ የመጣችውን ልጅ በመጨበጥ ለማራቅ እየለፋ፡፡ ልጅቱ በሁኔታው ግራ ተጋብታ እጁን ይዛ እንደቆመች…በቀኝ እጁ እሷን ይዞ…ግራ እጁን ወደእኔ ዘረጋና ‹‹የኔ ማር…ነይ አንዴ…ሰርኬ…ሰርኬ ቆይ….ሚስቴን ላስተዋውቅሽ…..›› አለ፡፡ ‹‹እኔ አላምንም….አንተ አስችሎህ…ሆኖልህ አንድ ሴት አገባህ…ጆኒ…አላምንህም! ሃሃሃሃሃሃ!›› አለች ጮህ ብላ እየሳቀች፡፡ ስለጠራኝ መሄድ ፈለግኩ፡፡ እጆቹን ይዤ ዛሬም- ከድሮ ሕይወቱ -- ከድሮ ብልግናው- ከበፊት ማንነቱ ልፋጠጥ ፈለግኩ፡፡ የምወደው የዛሬውን አንተን ነው…በየቦታው የቀበርካቸው ያለፉ ስህተቶችህ ግድ አይሰጡኝም ብዬ አጠገቡ ልቆም ፈለግሁ፡፡ ልጅቱ….‹‹አንተ አስችሎህ አገባህ….አላምንም›› ስትል ግን በዚያ ሰአት ቡቲኩ ውስጥ ካሉ አሻንጉሊቶች በላይ በድን ሆንኩ፡፡ ወላ ባለ ጃምፕ ሱቷ አሻንጉሊት በእኔ ፈንታ ተጠርታ ቢሆን ኖሮ ተነስታ ትቀድመኝ ሁላ ነበር….እመብርሃንን
እላችኋለሁ…የተዘረጋ እጁን እያየሁ….ወደ እሱ መሄድ እየፈለግኩ አቃተኝ….ልቤ መሄድ እየፈለገ እግሮቼ ግን ገገሙብኝ፡፡
(ይቀጥላል)

@wegoch
@wegoch
@paappii
☝️
ለውብ ቀን
💚

ይሄን ያለው አገልግሎቱን በብቸኝነት ያለምንም መቆራረጥ ሆድ ለባሰው ድሀው
ህብረተሰብ ለዘመናት ሲያቀርብ የቆየው ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ነው

"ናካይታ"💚

@wegoch
@balmbaras
ጡት መያዣ የመቼ ነው?››
(ሕይወት እምሻው)
ክፍል ሁለት
---------
….እመብርሃንን እላችኋለሁ…የተዘረጋ እጁን እያየሁ….ወደ እሱ መሄድ እየፈለግኩ አቃተኝ….ልቤ መሄድ እየፈለገ እግሮቼ ግን ገገሙብኝ፡፡ አይኖቹን አየሁ፡፡ የተዘረጋ እጁን አየሁ፡፡ አሳዘነኝ፡፡ አንዴ ፈርዶብኝ የለ? ያለ የሌለ ጉልበቴን አስተባብሬ ሄድኩና ይህችኛዋንም ተዋወቅኳት፡፡ ከዚያ በሁዋላ የነበረውን አስር ደቂቃ ግን ለማንም አልመኘው፡፡ ልጅቷ አንዱን ወሬ አንስታ አንዱን እየጣለች አእምሮዬን አዛለችው፡፡ጆሮዬን አደማችው፡፡ ጉልበቴን አላመችው፡፡ ‹‹….ጠፋህ እኮ- ደግሞ እንዴታባህ አምሮብሃል በናትህ- በጣም ተስማምቶሃል- ስልክ የማታነሳው ምን ሆነህ ነው- በጣም ፈልጌህ ብቀጠቅጥ ብቀጠቅጥ- በጣም ተስማምቶሃል- አምሮብሃል-ይሄን ቡቲክ ከከፈትኩ እኮ አመት አለፈኝ- ከዱባይም ከቱርክም አመጣለሁ-ምን ዋጋ አለው ሰራ የለም- ይሀ አብይ ከመጣ ጀምሮ ዶላር የለ ሱቅ ታቅፈን ኪራይ መገፍገፍ ብቻ-ዝም ብሎ በቲቪ ወሬ እያወራ ኢኮኖሚውን ገደለው እኮ-ቢዝነስ እኮ ሞቷል- ኮንስትራክሽን ብትል ንግድ ብትል ሞቷል- ምን አስቦ ነው በናትህ- እወደው ነበር አሁን ግን ለአይኔ እንኳን አስጠላኝ- ቲቪ ላይ ሲመጣ ቅይር ነው የማደርገው- በጣም ተስማምቶሃል- ያው ቤት ከመቀመጥ ብዬ እመጣለሁ እንጂ ደህና ነገር የሚገዛው ሰው እኮ አዲሳባ የለም- ሃሃሃ ገብቶሃል- ቴስት የለው ብር የለው ሰዉ- ወይ ዘግቼው ልገላገል መሰለኝ- ደሞ የባንክ እዳ አለብኝ- በጣም ተስማምቶሃል አንተ ግን…..›› ወድጄው የነበረው ልብስ አስጠላኝ፡፡ ተንቀልቅዬ ሙቪ ምናምን ብዬ መምጣቴ አስጠላኝ፡፡ ጆንን መውደዴ አስጠላኝ፡፡ ጆንን መተዋወቄ አስጠላኝ፡፡ ሴት መሆኔ
አስጠላኝ፡፡ መፈጠሬ አስጠላኝ፡፡ ‹‹እንሂድ…ፊልማችን ሳይጀመር….›› አልኩት ትንፋሽ በማትወስድበት የወሬ ሰልፍመሃል እንደምንም ገብቼ፡፡ ‹‹እንዴ…የወደድሽውን ….ልብሱን ለኪዋ!›› አለችኝ ወደ እኔ ዞራ፡፡
‹‹አይ…ይቅርብኝ…››
‹‹ምነው ለምን?››
‹‹ጃምፕ ሱት አያምርብኝም ዝም ብዬ ነው….›› ጆንን ገለግለኝ በሚል ሁኔታ
አየሁት፡፡ ‹‹አንሂድ ሰርክዬ…ዝም ብለን እንይ ብለን ነው…ሙቪውም ሰአቱ ደርሷል ›› አለ እኔን እያየ፡፡ ‹‹ኦኬ….ዋናው እንኳን ተገናኘን….በቃ ቻው….›› አለችን፡፡ ልትስመው ስትንጠራራ ጨበጣትና እኔም የግብር ይውጣ ‹‹ቻው› ብያት ወደ
በሩ መንገድ ስንጀመር…. ‹‹ውይ ጆንዬ….ቆይ ሳልረሳው!›› አለች፡፡
ይህች ሴተዮ ለምን አትተወውም? ለምን አትተወንም? ‹‹እ….›› አለ ዞር ብሎ እያያት፡፡ እኔም ዞርኩ፡፡ ‹‹በናትህ በናትህ ያ የድሮ ፓስፖርቴ እኮ እስካሁን አንተ ጋ ነው…ያኔ ከዱባይ እንደተመለስን…..ቢሰረዝም ትራቭል ሂስትሪው ይጠቅመኛል…መልስልኝ? እ?›› አለች በልምምጥ እያየቸው፡፡ ጥያቸው ወጣሁ፡፡ ደርሶብኝ እጄን ሲይዝ ከነኩርፊያዬ ዞር ብዬ አየሁት፡፡ ድሮ የማውቃት ልጅ ናት ሊለኝ ነው፡፡ ያን እለት ፊልሙም ምሽቱም ጋዝ ጋዝ እንዳለኝ ተለያየን፡፡ ፈተና 3 በስንተኛው ሳምንት ካለ እኔ የትም መሄድ የማይሆንለት ፍቅረኛዬ የአንድ የበፊት ጥብቅ- አሁን ግን የተጠፋፉ-- ወዳጁን አዲስ ቤት ለማስመረቅ ሃውስ ዋርሚንግ ፓርቲ ይዞኝ ሄደ፡፡ ልቅ እና ሰፊ የሆነው ሳሎን በብዙ ሰዎች ቢሞላም አልተጨናነቀም፡፡ ልክ ሳሎኑ ውስጥ እንደገባን ጆን ወደኔ ዞር ብሎ ‹‹ሶል ማለት ያውልሽ…ስንት መከራ አይቶ ነው ይሄን ቤት የጨረሰው….ለዚህ ነው የተጠፋፋነው ከኔም ጋር…ቤንሻንጉል ነበር ለብዙ ጊዜ…ኮንስትራክሽን
ኮንትራት አሸንፎ….ነይ ላስተዋውቅሽ…›› አለኝና አንደሁሌም እጄን ይዞ ሰውየው
ጋር ወሰደኝ፡፡ አጠገቡ እንደደረስን ጮህ ብሎ ‹‹ሶል …ቤት ለእንቦሳ! በስድስት አመትህም ቢሆን ጨረስከው አይደል…..?›› አለው፡፡ ተቃቀፉ፡፡ ከዚያ ሲተቃቀፉ ለአፍታ የለቀቀውን እጄን እንደገና ቀብ አድርጎ ‹‹ዛሬ…እጅግ ልዩ ሴት ላስተዋውቅህ ነው….›› ብሎ በኩራት እያየኝ ወደ ሶል ሲያስጠጋኝ.. ሶል ችኩል ብሎ- ‹‹ውይ…ኤደንዬ…! ፋይናሊ ዊ ሚት! መቼም ስላንቺ አውርቶ አይጠግብም…..!›› ብሎ ቀኝ እጁን ለመጨበጥ አቀረበልኝ፡፡ እጄን የያዘው የጆን እጅ በላብ ተጠምቆ አዳለጠኝ፡፡ አቀረቀረ፡፡ እጁን ለቀቅኩና-
‹‹ቤት ለእንቦሳ! እኔ ግን ሊያ ነኝ…›› ብዬ ሁለቱንም እቆሙበት ትቻቸው ወደ
በረንዳ ወጣሁ፡፡
ያን እለት የመቻል ፅዋዬ የሞላ፣ የመረዳት አቅሜ የተሟጠጠ መሰለኝ፡፡
ታከተኝ- ስለ እውነት ታከተኝ፡፡ በፍቅረኛዬ የማያልቅ የጀርባ ታሪክ- ባሰለፋቸው
ሴቶች ተደቁሼ የወደቅኩ- መነሳትያቃተኝ- ችዬ መቀጠል የተሳነኝ መሰለኝ፡፡ በስንት ልምምጥ- በስንት ይሄ ሁሉ እኮ ያለፈ ታሪክ ነው- በስንት ባለፈ ያውም ባልደበቅኩሽ ማንነቴ አትቅጪኝ- በስንት እወድሻለሁ- ካላንቺ ሰው አልሆንም- በስንት እባክሽ- በስንት በናትሽ- በስንት በማርያም- በስንት አንጀት የሚበሉ ልመናዎች - በስንት በገብርኤሎች- ተጎትቼ- ተሸንፌ ተመለስኩ፡፡ ሳምንት እንኳን ሳያልፍ ቤቱ ሄጄ…ገራሚ እራት በልተን- ጣፋጭ ወይን ጠጥተን-
አሪፍ ፊልም ተቃቅፈን አይተን-ተሳስመን-ተሳስቀን-ተሳስመን-አውርተን-ተሳስመን- ፍቅር ሰርተን-ተሳስመን- ተሳስቀን-ፍቅር ሰርተን- አውርተን-ተሳስመን…..ለመተኛት ስንሰናዳ ጆን ተፈጥሮ ጠራችውና ሽንተ ቤት ገባ፡፡ እኔ ደግሞ በወይንም-በፍቅርም- በእርካታም የተፍታታም የደከመም ሰውነቴን ይዤ አልጋው ውስጥ ስገባ በቀኝ ኮመዲኖው ላይ የተቀመጠው ስልኩ ‹‹ድዝዝ…›› አለ፡፡ ድዝዙ አጭር በመሆኑ ቴክስት እንደሆነ ገመትኩ፡፡ ስልኩን አንስቼ- አይቼ-ወይ በርብሬ አላውቅም፡፡ ለዚህ ምክንያት- ለዚህ ሰበብ ኖሮኝ አያውቅም፡፡ አሁን ግን እይ እይ…በይ በይ…በርብሪ በርብሪ አለኝ፡፡ ባለፉት ሳምንታት የተከሰቱት ነገሮች እንደገፋፉኝ ገመትኩ፡፡ ራሴን ገሰፅኩና ኮምፈርቴን ለብሼ አልጋው ውስጥ ልሰምጥ ስል ግን ስልኩ እንደገና ‹‹ድዝዝ›› አለ፡፡
አይ…አላይም….
አይ…አልከፍትም…
አይ…አልበረብርም….
ብድግ አደረግኩና አየሁት፡፡ ሁለት ቴክስት ሜሴጆች እንደገቡ ይታያል፡፡
ፓስወርድ ይፈለጋል፡፡ ጆንን ካወቅኩት ጀምሮ ስልኩን ፊት ለፊቴ የሚከፍትበትን የመስቀል ቅርፅ ሰራሁ፡፡ ተከፈተ፡፡ ቴክስቱን ከፈትኩ፡፡ ስም አልባ ቁጥር ነው፡፡ ሁለቱም ትኩስ ቴክስቶች የመጡት ከዚሁ ቁጥር ነው፡፡ መጀመሪያ የመጨረሻውን አነበብኩት፡፡
‹‹ፕሊስ ጆኒዬ….ፕሊስ…›› ይላል፡፡
ፕሊስ?
ጆኒዬ? ከፍ ብዬ መጀመሪያ የተላከውን አነበብኩ፡፡ ‹‹ጆኒዬ…ብደውል ብደውል አታነሳም…ፕሊስ ያንን ቤትህ የተውኩትን ብራዬን ፈልጌ ነው….ኢት ኢዝ ቬሪ ኤክስፔንሲቭ….ተራ ብራ አይለም….እና ሲመችህ ወይ ደውለህ አቀብለኝ ወይ እኔ መጥቼ ፒክ ላርገው…›› አናቴን በዘነዘና የተመታሁ መሰለኝ፡፡
በልምምጥ ያመለጥኩት፣ በየጎዳናው ሲያሳድደኝ የከረመው የድሮው ጆን
አድብቶ አልጋው ውስጥ አግኝቶ የወቀጠኝ መሰለኝ፡፡ ዞረብኝ፡፡ በደመነፈስ ወደ ቁመሳጥኑ ሄጄ የታችኞቹን መሳቢያዎች ጎረጎርኩ፡፡ ከካልሲና ከውስጥ ሱሪዎቹ ውጪ ምንም አላገኘሁም፡፡ በስርአት የተቀመጡ ልብሶቹን አተራመስኩ፡፡ ምንም የለም፡፡ ከዚያ ሃሳብ መጣልኝ፡፡ ቼስት ድሮወሮቹ! የመጀመሪያውን ከፈትኩ፡፡ መአት ወረቀትና ያለቁ ዶዶራንቶች፡፡ ሁለተኛውን ከፈትኩ፡፡ መአት ወረቀትና አብዛኞቹ ያለቁ እስኪብርቶዎች፡፡ ሰባራ ፍሬሞች፡፡ የምረቃ መፅሄት፡፡ ያረጀ አጭር የፎቶ አልበም፡፡: የተበላሸ ሰአት፡፡ የተሰበረ መነፀር፡፡ ሶስተኛውን ከፈትኩ፡፡ ሌላ መአት ወረቀቶች፡፡ …..ቆይ ቆይ…ይሄ ከወረቀቶቹ ኋላ በጥቁር ፌስታል የተቀመጠው
ነገር ምንድነው?
ጎትቼ አወጣሁት፡፡ እንደ ዋዛ ተቋጥሯል፡፡ በቀላሉ ፈታሁት፡፡ ግብድያ ቀይ ዋንደር ብራ፡፡ ታላላቅ ጡቶችን የሚይዘው- ጫማ ውስጥ ሊገቡ የደረሱ የወደቁ ጡቶችን በተአምሩ ከፍ አድርጎ አገጭ የሚያደርሰው ዝነኛው
ቪክቶሪያ ሲክረሬት ዋንደር ብራ፡ እውነቷን ነው፡፡ ውድ ነው፡፡ ስንት ነበር ባለፈው አማዞን ለይ ያሳዩኝ? መቶ አርባ
ሁለት ዶላር….? ቆይ ቆይ…..ምንድነው? ሊያስመልሰኝ ነው እንዴ…..? ምን እንደበጠበጠኝ አውቃለሁ፡:፡ ጆን ትላልቅ ጡት ካላት ሴት ጋር እዚህ ቤት መተኛቱ አይደለም….ይሄ መኝታ ቤት ሁለት መቶ ጡቶችን አላየም? እሱ አይደለም፡፡ ልሸሸው የማልችለው ጥያቄ ፊት ለፊቴ ስለተገተረ ነው ለመሆኑ ይሄ ጡት መያዣ እዚህ ቤት ከተተወ ስንት ጊዜው ነው? ለምን እንደሆን እንጃ ወደ አፍንጫዬ አስጠግቼ አሸተትኩት፡፡ ጠረኑ ትኩስ ነው..ገ?ላ ገላ ይላል ወይስ ኮመዲኖ ኮመዲኖ የሚለው ትንሽ ምርመራ የጊዜ ሰሌዳ ይሰጠኛል…ከእኔ በፊት ነው በሁዋላ የመጣው ለሚለው አንገብጋቢ ጥያቄ መልስ ሰጥቶ ያረጋጋኛል ብዬ ነው ....ጠረኑን ማግኩት፡፡ ሻነል ነምበር ፋይቭ፡፡ የምወደው ሽቶ….በጣም ጠንካራ…ጠዋት የተቀባ የሚመስል ሻነል ነምበር ፋይቭ ሽቶ ከጡት መያዣው ይተናል፡፡ ሻንል ነምበር ፋይቭ ጠንካራ ሽቶ ነው…እንደ ርካሽ ሽቶ ቶሎ አይበንም…በቀላሉ አይለቅም….ያውም በፌስታል ተቋጥሮ ብዬ አሰብኩ፡፡ ከዚያ ደግሞ ምንም ያህል ጠንካራና ሃይለኛ ሽቶ ቢሆንም ከስድስት ወር በላይ -ከእኔና ከእሱ ፍቅር በላይ- እንዲህ እንደበረታ አይቆይም ብዬ አሰብኩ፡፡
እህ፡፡
እህ…..
.ምንድነው…? ሊያስመልሰኝ ነው እንዴ?
…ሊያስመልሰኝ ነው…ሊያስመልሰኝ ነው….ደቂቃ ሳይሞላ የበላሁትንም የጠጣሁትንም እጄ ላይ የነበረው ግብዲያው ውድ ጡት መያዣ ላይ ስለቀውና ጆን ወደ መኝታ ቤቱ ገብቶ መርዶ ባረዱት ሰው ሁኔታ ሲመለከተኝ እኩል ሆነ፡፡

@wegoch
@wegoch
@paappii
ለጁምኣችን!
💚


የሰው ልጅ የውበቱ ግማሽ ምላሱ
ነውና ንግግራችሁን አሳምሩ !!
.
.
.


በሰዎች ዘንድ ተወዳጅ ብቻ ከመሆን
በላይ የላቀው ጸጋ እምነት
የሚጣልበት ሰው ሆኖ መገኘት
መቻል ነው።

ነጂብ መሕፉዝ

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
ለቅዳሚታችን!


አንዳንዱ መተቃቀፍ ንፍቅና ነው !

ሸጊቱ ቅዳሜ!

"ናካይታ"💚

@wegoch
@wegoch
~~~~~~~
ማስመሰል 1
~~~~~~~
አወራለሁ... ለእኔ ትርጉም የማይሰጠኝን... እሷን ግን እያሳቃት ነው፡፡ ልባዊ ንግግሬ 'ዝምታ' ነበር... አብረን ሆነን ማውራት አልፈልግም! ምንም አለማሰብ ያምረኛል... እጇን እንደያዝኩ... እሷም ዝም ብትል ደስታዬ... አብርነታችን የፈጠረውን ለስላሳ ድምፅ ማዳመጥ... ከእርሱ ጋር ልከኛ ንቅናቄ መወዛወዝ... ምን እንደሆንኩ መናገር ሳይጠበቅብኝ ከትትት ብዬ መሳቅ ያምረኛል፡፡ የአብርነታችን ጉዞ በተራ ወሬ ሲደበዝዝ ይጨንቀኛል... ዝም ብላት ደስ ይለኛል... እሷም እንደዛው... የታክሲ ጥቅስ ያልተጫነው... አደባባይ ደረት ላይ ያልተሰጣ... ተራ ፖለቲካ ያልሆነ... ዘመንኛ ያልተቃኘ... የአክስቷ ልጅ የሌለችበት ወሬ ያምረኛል... እርሱ ደግሞ ስም አለው... ዝ - ም - ታ!
~
~
አዲስ ነገር የሌለው የአፍ መከፈት እና መዘጋት ትርጉሙ ምንድነው?
ማውራት ምንድነው? ሌላው ያወቀውን መለፍለፍ ነውን? የአደባባይ ቅብብሎሽ የተለመደ ነገር ግን እንደ አዲስ ከሰው ሰው የሚንሸራሸር ወዙን የጨረሰ መግባባት ነው? ደግሞ ለሌላው ማቀበል አይነት?
(በዚህ ሁሉ ጥያቄዎቼ መሀል ደስ የሚላትን እያወራሁ ነው... እየሳቀች ነው፡፡)
~
~
ለምን ሌላኛ ቋንቋ የሆነ አብሮነት አንፈለስፍም? ይሄንን ጅንጀና ማን አስተማረን? ምናልባት ታላቅ ወንድም? ምናልባት የቤት ሰራተኛቸው ከአንድ ስሙ ካልታወቀ ጎረምሳ ጋር ስታወራ ሰምታት ይሆን? አሳሳቋን ከማን ኮረጀች? ኮርጃ አበላሸችው ወይስ አሻሽላዋለች?
ሁላችንንም ቀድሞ አራዳ የሆነ የመሰለን ቀልቃላ ጓደኛዬ አፍ ላይ ሰምቼው ይሆን? ስላማረበት እንዲያምርብኝ? ያልተገለጠ ቅናት ቀንቼ? እሷስ መልሱን ከየት ተማረች? ሶስት ወልዳ ከወፈረች ጓደኛዋ? ከልጆቹ አባት ጋር ስትፍነከነክ? የተጠና ጉዞ አይመስልም?
~
~
(ይሄ ሁሉ ሲሆን የጠላሁትን አወራታለሁ... የምትጠላውን እየሳቀች ነው? ወደ እውነትነት የተቃረበ ውሸት መወሻሸት ነውና እውነቱ፡፡)
የውስጥ ሀሳባችን ቢሰላ ከማን ጋር እንኖር ነበር? ከመሸሸግ ውስጥ የሚወጣ... ከማስመሰል ፍሬ የሚሸመጠጥ... ከመዋሸት ጥግ ያለ ጉዞ ጣፍጦን ተከተልነው? ጥሞን ለመድነው?
(ይሄንን ሁሉ ሳስብ እጃችን መሀል ስስ ላብ አለ... ጣቶቿ ጣቶቼን እየከፋፈሉ ተጣምረዋል... እኔ... እሷ... እኔ ... እሷ... አይነት አሰዳደር ተጣምረዋል... ቀይ ጣት... ደሟን እያሳየ የቀላ መዳፍ... አወራለሁ ትስቃለች... የማን ላብ ነው? )
~
~
ከመቀራረብ በላይ የሚጥም ጉዞ የትኛው ነው? ለቀረቧት በሀሳብ ከመሸሽ የበለጠ ምሬት የትኛው ነው?
(ወሬውን አቋርጬ ይሄንን አሰብኩ... እየጠበቀችኝ ነው እስክናገር... በመጠበቋ ላይ ያልተጠና አዲስ ፊቷን አየሁ...)
ቀይ ናት!
ስ - ታ - ም - ር!
(በረከት ታደሰ)

@wegoch
@wegoch
2024/09/27 11:24:52
Back to Top
HTML Embed Code: