Telegram Web Link
ለጁምኣችን
💚💚💚

☞ ደስታ የሚጀምረው ከፍቅር ግንኙነት ከስራ ከገንዘብ አይደለም ከራስ ነው


ደስተኛ
ሁናችሁ ዋሉ

ውብ ቀን💚

@wegoch
@wegoch
እንደውም እንደውም የ ከተማው መስተዳድር ምልክት የኢሉምና'ጢ' ነው!
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ርዕሱ ላይ ያለው 'ጢ' በምክንያት ነው የገባው፡፡
ቅድም ደክሞኝ ነበር፡፡ እንዲሁ ስንከራተት ነበር የዋልኩት (በእግሬ)፡፡ ከተወለድኩ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ እግረኛ ነኝ... የሰው ልጅ በመራመድ ብዛት እንደ ላጲስ የሚያልቅ ቢሆን የእኔ እግር አንገቴ ጋር የሚደርስ ይመስለኛል፡፡ ብቻ ደክሞኝ ነበር... ከግቢ ወጥቼ ወደ ሰፈር ለመሄድ እንደ ብዙሀኑ የሀገሬ ሰው ተሰለፍኩ... ከመንገደኛ ጋር ተገለማመጥኩ... የአላፊ አግዳሚ ፊት አየሁ... ፀሀይ ደበደበኝ (ጥብስ ጥብስ የምሸት ይመስለኛል አንዳንዴ ፀሀይ ሲመታኝ...) መጨረሻ ላይ ሸገር ባስ ውስጥ ገባሁ፡፡ የሸገር ባስ የመጨረሻው ወንበር ሁሌ ይገርመኛል፡፡ ከ ተሳፋሪዎች ጋር በየደቂቃው አይን ለአይን ትተያያለህ... የተቀመጡት ሁሉ ቅንድብ ቅንድብህን እያዩህ ይመስልሀል፡፡ አንዳንዴ የሆነ ስሜታዊነት ይመጣብኝና 'ንግግር አድርግ አድርግ' የሚል ስሜት ያንቀኛል፡፡ ከዚህ ሁሉ ሶስተኛ አለም ማህበረሰብ ፊት ለፊት ስትቀመጥ ልጁን የዳረ ደጋሽ ነው የምትመስለው፡፡ ለሚያይህ ሁሉ ጥሩ ፊት ማሳየት ግዴታህ ይሆናል፡፡ ገብቼ የሆነ ቦታ መርጬ ተቀመጥኩ... ወሬ ለመስማት የሚመች ቦታ... መንገድ ስንጀምር ሬድዮ ተከፈተ፡፡ ተሳፋሪዎች ከመስኮት ወዲያ አይናቸውን ተከሉ፡፡ አንዳንዴ ተሳፍረህ ስትሄድ ሹፌሩ መስማት የሚፈልገውን ነገር እስፒከሩ መጨረሻ ድረስ ከፍቶ የማትፈልገውን ነገር ያሰማሀል (በእኔ ቋንቋ አንድ ሰው የአርባ ምናምን ሰው ጆሮ አስገድዶ ይደፍራል!) ብቻ ሬድዮው ስለ 666 ኢሉሚናንቶች ምናምን የሰማነውን ይደግምልናል፡፡ ተሳፋሪው ውይይት ጀመረ፡፡ "አይ ዘመን!" አለች ከአጠገቤ የተቀመጠችዋ ወፍራም ሴትዮ... ስትመቻች አንገቴ በመስኮት ይሾልካል... ይቺ ሴትዮ መልስ ሳይሆን ዳይት እንደሚያስፈልጋት ተረዳሁ፡፡
"ይኸው አሁንማ አጥለቀለቁን" አለ ስራ ሊፈልግ እንደወጣ የሚያስታውቀው ላባም ወጣት፡፡
"አሁን እኛ ጋር ጠቅልለው ገብተዋል አሉ... መሬት ስር ቆፍረው ነው የሚኖሩት አሉ፡፡" አለ ብረት ባልያዘው እጁ ላቡን እየጠረገ፡፡
"አይገርምም?" አለችኝ ወፍራሟ ሴትዮ ወደ እኔ ዞር ብላ
"አዎ! አንቺን ለምታክል ቶን ሴት ከእኛ እኩል ማስከፈላቸው እጅግ ገርሞኛል" ልላት አሰብኩ፡፡ ግን ግራ እጇን በሙድ ጣል ብታደርግብኝ ሞራሌንና የህይወት ጉዞዬን በቀላሉ ልታደናቅፈው እንደምትችል ገባኝ፡፡
"በጣጣጣጣጣጣም!" አልኳት፡፡
ስራ ፈላጊው ወጣት ዶክመንት የያዘበትን ሽሮዋማ ዶሴ ብብቱ ስር ከቶ ስለ ምልክታቸው ፣ አላማቸው ፣ እና መገኛ ስፍራቸው እየተወራጨ ያስረዳል (ስራ ያገኘ እየመሰለው ይሆን?)
"... ይሄ የፍየሉ ቀንድ ነው!" አለ ሁለት ጣቶቹን አንስቶ (አይደለም የኔ ወንድም እርሱ የአንተ ሁለት ጣት ነው፡፡ )
ብቻ ብዙ ነገሮችን በኢሉምናንትነት ፈረጀ፡፡ የሀይሌ ገብረስላሴን ፈገግታ ጨምሮ 666 ነው አለ፡፡
ሁሉም በጉዳዩ ተወያየ፡፡ ሁሉም የማያውቀውን የሚገምተውን ከአደባባይ የለቀመውን እውቀት ሳያስፈቅድ አካፈለን፡፡ ከአጠገቤ ያለችውም ሴትዮ ስለ ዘመኑ ክፉነት አስገድዳ አስረዳችኝ... ተገድጄ አመንኩላት... (ምናለ ለእንደኔ አይነት ምስኪኖች አብይ ቢያስብልን? ነፃ ቢያወጣን ከዚህች ቶን የምታክል ሴትዮ!) አሁን ምን አስባለው መሰለህ... መንገድ ሄዶ ሄዶ ለሁለት ከተከፈለ ኢሉምናጢ ነው! በሁለት አይንህ አፍጥጠህ ካየኸኝ ኢሉምናጢ ነህ! ብቻ እነርሱ ወደኛ ሳይመጡ እኛ እየሄድንባቸው መሰለኝ፡፡ ፒያሳ ያለው የሚንልክ ሀውልት ፈረሱ ኢሉምናጢ ነው(ምክንያቱም ቂጡ ለሁለት ተከፍሏል!)፡፡ በጣም የሚያስቀኝ ግን እንደ መረዳጃ እድር ተሰብስበው ተቀላቀሉ ምናምን የሚለው ነው፡፡ ምን ያህል እንደ ሰለቸኝ ይሄ ወሬ! እንደውም እንደውም የ ከተማው መስተዳድር ምልክት የ ኢሉምናጢ ነው! ለምዶብን የለ?

(በረከት ታደሰ)

@wegoch
@wegoch
ለቅዳሚታችን
💚

ደስተኛ ሰዎች ወደየትኛውም አቅጣጫ ይመልከቱ፣ የትም ቦታ ይሁኑ፣ ምንም ይሁኑ
አብዛኛው ሰው የማይመለከተውን ውበት የማየት ተክህሎ አላቸው፡፡ አብዛኛው ሰው
ፍልሚያውን ብቻ በሚያይበት ቦታ መልካም አጋጣሚዎችን ያያሉ፤ አብዛኛው ሰው እጥረትን
ብቻ በሚያይበት ቦታ ትርፍ ያያሉ ለዚህ ሁሉ ነገርም ምስጋና ያቀርባሉ ። ምስጋና ለደስታ
----------------------------------------------


እንስቃለን!!!!

በቅዳሜ ሰማይ፤
በደጋጎቹ ሃገር ፤
በማር ዘነብ ቀዬ፤ በላይኛው ወሎ፤
ፍንሽንሽ ፍልቅልቅ፤
ፍንድቅድቅ ብለናል፤ እንደ ፋፎ ቆሎ።

((( ጃ ኖ )))💚💛❤️


የሸገነ፤ የተሸባረቀ፤ የተገማሸረ ቅዳሜ
ጀባ ብለናል!!!!!!!!!💚💛❤️

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
🇪🇹🇪🇹🇪ዘጠነኛው የብርሃን ዕለት የመጀመሪያው ማክሠኞ ነሀሴ 7። ይምጡና አብዝተው ያትርፉ እንድቅትዮን በ አዲስ አበባ ትያትር እና ባህል አዳራሽ(ፒያሳ) ።
ልዩ እና እውቅ የጥበብ ሰዎች ግጥም እና ወግ በባህላዊ ሙዚቃ ታጅበው ያቀርባሉ።

እማይቀርበት ልዩ የጥበብ ምሽት!


@getem
@wegoch
@tebeb_mereja
Qur'ann 75:4
Yes,We are able to put together in perfect order the very tips of his
fingers.

Masha Allah.


አይደለም ጣቶቹን (ፊት እንደነበሩ )
በማስተካከል ላይ ቻዮች ስንኾን
(እንሰበስባቸዋለን)

ሱረቱል አል ቂያማህ ቁጥር 4


ለበይክ አሏሁመ ለበይክ
ለበይከ-ላሸሪከለከ-ለበይክ
ኢነል ሃምደ-
ወኒዕመተ
ለከረል ሙልክ-
ላ ሸሪከ-ለክ!!
-
አረፋ የመስዋዕትነት፣ የመታዘዝና የምህረት በዓል ነው።
ሁሉም ነገር በቦታውና በጊዜው ያምራል።
ለእስልምና እምነት ተከታዮች ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንኳን ለአረፋ በዓል አደረሳችሁ ❤️❤️❤️

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
እልህ የወለደው የተቀጣሪ መስፈርት
^^^^*^^^^^^^^*^^^^^^^*^^^^^^^^
{®ዳንኬብ}

‹‹ በዚህ ሀገር ላይ ፈልገህ የማታገኘው ነገር ቢኖር ስራ ነው፡፡ ›› አለ ጫንጮ የፍለጋ ምሬቱን ፊቱ ላይ እያንጫጫ፡፡
‹‹ ስራ እንኳ አይጠፋም ግን ካልናቅክ ነው፡፡ ›› አለ ጎረቤታችን አሰፋ የመንደሩን ቦዘኔ በዓይኑ ጠቅ እያደረገ፡፡
‹‹ ያልተነካ አሉ እትዬ መሰሉ ›› ወደ እናቴ ጠቆመችና ‹‹ ስንት አመት ፈለግና! መች አገኘን? እርሶ አንድ ቀን በፍለጋ ቢንከራተቱ ኑሮ … ›› የጀመረችውን መጨረስ ትታ ፀጉሯን መጠቅለል ተያያዘችው፤ ብቸኛዋ ስራፈት እህታችን ማኪ
‹‹ ኤዲያ አስመሳይ መችና የት የፈለጋችሁትን ነው? ›› አሰፋ ለክርክርና ለወቀሳ ሲያኮበክቡ ታዩኝ፡፡
ይኼን የምክክር መድረክ የክርክር ሊያደርጉት መሰለኝ፤ ለነገሩ የምክክር መድረክ ብለው ስሙን አሽሞነሞኑት እንጅ የምክር መድረክ ነው፡፡
አንድ እኔን … ዘንድሮ የተመረኩትን ለመምከር፤ ታዲያ እኔ መጠየቅም፣ መናገርም አልተፈቀደልኝም፡፡ ቶሎ እንዲጠናቀቅ ሲባል ድምፄ ታቅቧል፡፡ ለዛሬ ተቀባይ ነኝ፡፡ በሂደቱ ላይ ቅሬታ ቢኖረኝ እንኳ በዝምታ ማለፍ እንዳለብኝ የመድረኩ አዘጋጅ ሳሚ ቀድሞ አሳውቆኛል፡፡
ሳሚ እንደ ሊቀወንበርነቱ (ይቅርታ እኛ ቤት ወንበር እንጅ መንበር ስለሌለ ነው) ዝም ካሰኘ በኋላ ምክሩን ቀጠለ
‹‹ ስራ ምታፈላልግባቸውን ዘዴዎች ልንገርህ… ያው ጊዜው የቴክኖሎጂ እና የኢንፎርሜሽን በመሆኑ በየቢሮዎች በየተቋማቶች እየሄድክ ስራ መጠየቅ አይኖርብህም፤ መቅጠር ሲፈልጉ የቅጥር ማስታወቂያዎችን በቦርዶች ላይ ይለጥፋሉ፡፡ ከዛ አለፍ ሲል ጋዜጣውንም መፅሄቱንም የሞላው የስራ ማስታወቂያ ስለሆነ መፅሐፍ መደብር አልያም ቤተመፅሐፍ ገብተህ ማገላበጥ ነው፡፡ ከዛ ሻል ሲል ስማርት ስልክህን ወጣ አድርገህ ቴሌግራምህን ትከፍትና vacancy channelኦችን መቀላቀል ነው ሚጠበቅብህ፡፡ ከዛ በየቀኑ፣ በየሰዓቱ፣ በየደቂቃው upload እያደረግክ የምትፈልገውን የስራ ዓይነት መኮምኮም ነው፡፡ Appም አለ Install አድርገህ፤ የተመረቅክበትን የትምህርት ዘርፍ አስገብተህ፤ Register ታረጋለህ፡፡ ከዛ ባንተ ዘርፍ የስራ ቅጥር ሲወጣ አንድ አንድ ብርህን እየሞሸለቁ መረጃ ይልኩልኃል ››
ይህን ሁሉ እየተጠቀመ ለ3 ዓመት ስራ ያላገኘው ሳሚ ስራ እንደማገኝበት ተስፋ አድርጎ የስራ ማግኛ ዘዴዎች ብሎ ጠቆመኝ፡፡
የምክክር መድረኩ በተቋጨ በማግስቱ ስራ ፍለጋ ወጣሁ፡፡ ስራ መናቅ አያስፈልግም፤ መስፈርት ካሟላው ሰተት ብሎ መወዳደር ነው፡፡
ሙሉ ቦርድ አስሼ ሟሟላት የቻልኩት መስፈርት የጥበቃን ብቻ ነበር፤ ማስታወቂያውን ፎቶ አንስቼ ጋዜጣ ማገላበጡን ተያያዝኩት፡፡ ያው ቅድሚያ ለሴት እንደሚሰጡ ግልፅ ቢሆንም እስኪያዳሉ መስፈርቱን ላሟላ የቻልኩት ሁለተኛ ስራ አስተናጋጅነት ነበር፡፡ ቦታው ግን ካለሁበት ሀገር ውጭ ስለሆነ እዛ ሄጄ በዳሌ ሲቪያቸው እኔን ጎልተው የሚቀጠሩ ሴቶች በዓይኔ ውል ሲሉብኝ ብርንም፣ ንዴትንም፣ ተስፋንም ለመቆጠብ ስል ተውኩትና ከራሴ ጋር ሙግት ያዝኩ፡፡
‹ እንደው የዘበኛውን አለፍኩ ልበል፤ በሳምንቱ የተሻለ የቅጥር ማስታወቂያ ቢለጠፍ መጠበቁን ትቼ ለመወዳደር መክነፌ የማይቀር ነው፡፡ ስለዚህ የተሻለ ልፈልግ … ›
ተውኩት!!!
ስራ ሳልንቅ የተሻለ ልፈልግ እያልኩ አንድ ወር ሙሉ ያለስራ ተቀመጥኩ፣ ቆምኩ፣ ዞርኩ፡፡ በቃ ልወዳደር ብዬ እወስንና ነገ ከዚህ የተሻለ ማስታወቂያ እንደሚለጠፍ መንፈሴ ሹክ ሲለኝ ውሳኔዬን እቀይራለሁ፡፡ … ነገም እንደዚሁ
እንዲህ እያልኩ ዛሬ ላይ ደረስኩ፤ ብዙ የስራ ቅጥሮችን ከትናንት ጋር ጥያቸው እየመጣሁ፡፡
እዚህ ሀገር ላይ ተፈልጎ የማይገኘው ስራ ሳይሆን ነገ የተሻለ ስታይ ጥለኸው የማትሄድ፣ ንቀህ የማትተወው ስራ እንጅ፤ ለዚህ ብቸኛ አማራጩ በተመረቁበት መቀጠር ነው፡፡ እሱም ከተገኘ!!

እልህ የወለደው ውሳኔ ከውስጤ ፈንቅሎ ወጣ፡፡
‹ ስራ አይናቅም፤ የተሻለ እስኪመጣ፣ በተማርክበት እስኪገኝ ግን ይጠበቃል፡፡ እልህ መጣጭ፣ ትዕግስት ጨራሽ፣ ተስፋ መጣጭ ቢሆንም፡፡
ከዛ ይልቅ ግን የራሴን የተቀጣሪ መስፈርት ለምን አላዘጋጅም? አው መስፈርትን ለቀጣሪ ብቻ ማን ነው የሰጠው፤ እኔም ምቀጠረው እኔ የምፈልገውን መስፈርት ለሚያሟላ ነው፡፡ አበቃ!!! ›
መስፈርቴ፡
ነገ ከተቀጠርኩበት ስራ የተሻለ ባገኝ ጥዬው ለመሄድ የስራ መልቀቂያ በማስገባቴ የማይከፋና የሰራሁበትን በቀን አስቦ ሊከፍለኝ የሚችል ከሆነ ለመስራት ፍቃደኛ ነኝ፤ በዚህ የሚስማማ ማንኛውም ድርጅት ሊቀጥረኝ ይችላል፡፡

@wegoch
@wegoch
ለአረፋችን
❤️❤️❤️


አረፋ ደረሰ።
አልሃምዱሊላህ እንኳን በሰላምና በጤና አደረሰን።
ይህን ፎቶ የተነሳሁት ወሎ ውስጥ ነው ከሚሴ # ሾንኬ ልዩ ቀበሌ። የተቀመጥንበት
መስጂድ 1000 ዓመት ገደማ ያስቆጠረ ሲሆን በትልቅ ተራራ አናት ላይ ይገኛል።
ከተራራው አናት እስከታች ድረስ አርጎባዎች ብቻ ይኖራሉ። ከዚህ ተራራ ሳይወርዱ ከላይ
የጠቀስኩትን ያክል ዘመን ኑረዋል። ሁሉን ነገር ከጎበኘሁና ከቀረጽኩ በሁዋላ ከማይክ
ውጭ (mic off) እኒህን የማህበረሰቡ አስተዳዳሪ አባት አንድ ጥያቄ ጠየኳቸው...
"በርግጥ ድሮ እስልምናን ለመጠበቅና ራሳችሁንም ለመከላከል በማሰብ ነው እዚህ
ከፍታማ ስፍራ ለመኖር የመጣችሁት ነገር ግን አሁን ይሄ ቦታ ምንም የሌለበት ድንጋያማ
ተራራ ነው ምናለ ወረድ ብላችሁ ሜዳው ላይ ብትኖሩ? የተሻለ ስራስ ብትሰሩ?......(የጥያ
ቄ መዓት!)"
"አይ ልጄ እኛ ለመብላት አይደለም የምንኖረው ይቺኑ በተራራው ላይ ያመረትናትን ማሽላ
በቀን አንዴም ቢሆን እየቀመስን አላህን ለመዘከርና ዲኑን ለመጠበቅ ነው...."
እኔን ትክ ብለው ሲያዩኝ በጥዋቱ ጸጉሬን ለመፈረዝ የታጠብኩበት ሻምፑና ፈሳሽ ቅባት
ግምባሬን የሀብታም ቅቤ ቅል አስመስሎታል...."አንተና የከተማ ሰውማ ይህን ጮማ
እየበላችሁ እንዲህ እያብረቀረቃችሁ ዋሉንጂ...(ለቀልድ ያክል)" አሉኝ። በዚህ የለየለት
ተራራ ወገብና አናት ላይ በግምት ከ200 እስከ 300 አባወራ ይኖራል....በቂ የሆነ ምርት
አለመኖሩን ገምቼ ሆዴ እየተንሰፈሰፈብኝ..."ቆይ ግን እንደው ይህን ተራራና ገደል
መንግስትና መብራት ሀይል ባያውቁትም አልፎ አልፎም ቢሆን የእህል እርዳታ
አይመጣላችሁም? ደግሞም ለመንግስት ግብር ትከፍላላችሁ አይደል?..(የጥያቄ መዓት)"
አከታትዬ ጠየኳቸው...
ፈገግ እያሉ "አይ ልጄ እሱማ የት ይቀራል ተራራ ነው ብሎ ማን ይምርሃል...(ሳቅ) እርዳታ
ሚባል ነገር እንኳ የለም አይተንም አናውቅ"
ሰውየው ቅጥነታቸውንና የግምባራቸውን እጥፋት ሳይ ቁርጥ አባቴን መሰሉኝ! አይገርምም!
ሰው እንዲህ ከነ አነጋገሩ ይመሳሰላል...! እናላችሁ...ይህ መንደር ይገርማል ኢትዮጵያዊ
የሆነ ሁሉ ቢያየው በሰዎቹ አኗኗርና በተራራው ከፍታ በመገርም አንድ ቀን
እንደሚያመሰግነኝ አልጠራጠርም! ቦታው ከነመስጊዱና ከነሙሉ መንደሩ በዩኔሶኮ
በቅርስነት ተመዝግቧል። ጋዜጠኞቻችን የኢድ በዓል በመጣ ቁጥር ምግብ የተትረፈረፈን
ይመስል በየቤቱ እየገባችሁ የድግስ መዓት ከምታሳዩንና ያልቸገረንን ድቤ ከምታስደልቁብን
መሰል ታሪካዊና መንፈሳዊ ቦታዎችን አቅዳችሁ ብትሰሩ መልካም ነው። [እኔን
ጨምሮ...ሃሃሃ] ሙስሊሙ ማህበረሰብም ከሳዑዲው ሀጂ መልስ እንዲህ አይነት
ቦታዎችን የመጎብኘት ልምዱ ቢኖረው እምነታችንንም አገራችንንም እንጠቅማለን ለማለት
ያህል ነው። ጊዜያችሁን የተሻማሁባችሁ አፉ በሉኝ! መልካም በዓል ይሁንልን። ኢድ
ሙባረክ!

(( ያሲን መሀመድ )))

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
ኢድ ሙባረክ!

እንኳን ለ1440ኛው ዓመተ-ሒጂራ የኢድ-አል-አድሃ (ዓረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፡፡ 🙏🏽

#መልካም_በአል

@getem
@seiloch
@wegoch
የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ "ምርጫው በተያዘለት ቀን ይካሄዳል" ማለቱን ተከትሎ፣ ሚዲያዎቻችን እንዲህ ሲሉ ይከርማሉ፡፡
.
ናሁ ቲቪ- አቶ ልደቱ አያሌውን አቅርቦ ኢንተርቪው ያረገዋል፡፡ ልደቱም ያቺን "
ስንቱን ነገር ጠብጥበን እናቀዋለን" የምትል ሳቁን እየሳቀ " ህ- እዚህች ሀገር ላይ ምርጫ ማካሄድ የልብ ህመምተኛን ማራቶን እንደማስሮጥ ነው፡፡ መሀል ላይ ልቢቱም ሰውዬውም ይፈነዳሉ፡፡ አሁን ተጠያቂ የሚሆነው ማነው- እሺ ብሎ የሮጠው ሰው ወይስ ለልብ ህመምተኛ ማራቶን የፈቀደው አስሯጭ? እኔ ልንገርህ አደለም፣ ቀጣዩ አመት እንኳን ምርጫ በርጫ እንኳን ተደብቀን ነው፡፡ ፒፒፒፒ ሪሪሪሪ..."
.

OMN በባለቤቱ በጃዋር አማካይነት "እጅግ ሚዛናዊ" የሆነ መግለጫ ይሰጣል፡፡ " አንድ መንግስት ምርጫ ማካሄድ ግዴታው ነው፡፡ አብይን አይደለም እኔን እንኳን ሳንመረጥ አንድ ቀን ስልጣን ላይ እንዳንቆይ የሚያረግ ወጣት ነው የፈጠርነው፡፡ ምርጫ ባይካሄድ ቄሮ ዝም ይል ይመስልሃል? ይሄንን የለውጥ አመራር እጁን ይዞ ወደ አራት ኪሎ እንዳስገባው፣ እጁን ይዞ ደሞ ቃሊቲ ያወርደዋል፡፡ ስለዚህ ማወቅ ያለብን አሁን ኢህአዴግ የወሰነው ለህልውናው ብሎ እንጂ በሌላ መልኩ አይታይ፡፡ ፒሪሪሪ ፓራራራ.."

.
በረራ ጋዜጣ በርዕሰ አንቀጿ ይህንን ትላለች " ታሪካዊ ውሳኔ፡፡ አዴፓና ጀሌዎቹ ( what in God's name is jelewchu
tho?) የአማራውን ትግል ለማዳከም ቀን ከሌት በሚሰሩበት በዚህ ወቅት፣ የገዢው ፓርቲ አመራር ይህንን ውሳኔ ማሳለፉ ታሪካዊ ነው፡፡ በቁጥር የማይገለፁ
የአብን ከፍተኛ፣ ማዕከለኛ እና ዝቅተኛ አመራሮች በታሰሩበ፣ ቀርቷል የተባለው
የሽብርተኛ አዋጅ ህግ የጠጣውን አቧራ አራግፎ ዳግም የማፈኛ ማጣቀሻ በተደረገበት ማግስት እንዲሁም የአዲስ አበባ ባላደራ እንዳይንቀሳቀስ እጅግ
የተለያዩ አሻጥሮች እየተካሄዱበት ባለበት በዚህ ወቅት የአማራውን ህዝብ በከፊል እንኳን የማይወክለው አዴፓ በስራ አስፈፃሚዎቹ በኩል ይህንን ውሳኔ
ማሳለፉ ለታሪክ መዝገቦች ብቻ የሚተው አደለም፡፡ አማራውን የሚወክሉት ሀይላት አሁን ከመቼውም በላይ ወደ አንድ መምጣት ያለባቸው ወቅት ነው...
ፒሪሪሪ ፓራራራራ..."

.
ፍትህ መፅሄት "በቅድሚያ ሀገር ሰላም ይሁን"፣ "የሽግግር መንግስት ጊዜው ደርሷል" የሚል ርዕሰ አንቀፅ ታስነብበናለች፡፡
.

ኢቲቪ "የተተከሉት ችግኞች ለቀጣዩ ምርጫ እንደሚደርሱና የዛፎቻቸውን ጥላ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሚያደርጓቸው የምረጡኝ ዘመቻዎች መሰብሰቢያ ቦታ ሊጠቀሙባቸው እንደሚችሉ ተገለፀ" ይለናል፡፡

.
ፌስቡካችን "በማን ሊያሸንፍ ይችላል" የቅድመ ትንበያ ሴራ ትንተና ፏ ትላለች፡፡
.

# ወሬያችን የተሰኘው "# እጅግ_ተወዳጅ " የ-ዩቲዩብ ሾው በብርጋና ቲዩብ
አምስተኛ ክፍሉን ይለቃል፡፡
.

እኛም- እንወጣለን፣ እንወርዳለን- የድንገቴ ሀብት ጎርፍ ጠራርጎ ሳይወስደን ሌላ ሳምንት ያልፋል፡፡


@wegoch
@wegoch
@paappii

#biniam teshome
Forwarded from ግጥም ብቻ 📘 (ልዑል)
ተስፋ የግጥም ስብስብ መፅሀፍ ምረቃ
በ አስታውሰኝ ረጋሳ (አስቱ)

አርብ ነሀሴ 10
ክ 11:00 ጀምሮ
በ አዲስ አበባ ቲያትር እና ባህል አዳራሽ (ማዘጋጃ) ፒያሳ

@getem
@tebeb_mereja
@tebeb_mereja
ሰው ሆኖ አለመቻል አይቻልም።
ተመስገን አብይ እባላለሁ። የአ.አ ዩኒቨርስቲ የስነልቦና ተማሪ ነኝ። ሰዎችን ሊያነቃቁና ሊለውጡ የሚችሉ ስልጠናዎችን እሰጣለሁ። መልካም ሀሳቦቼንም የማካፍልበት አሪፍ ቻናል አለኝ። እናንተም ቻናሌን እንድትቀላቀሉኝ በእክብሮት እጋብዛለሁ።

@temuabiy
@temuabiy
@temuabiy
ለውብ ቀን
💚💚💚

በትንሹ ትልቁን አትጋርድ


በእውቀታቸው የተከበሩትና በትህትናቸው የሚወደዱት
መንፈሳዊው መምህር የማለዳውን ትምህርት ለተማሪዎቻቸው
ሰተው እንደጨረሱ ተማሪዎቻቸውን አሰናብተው በጥሞና ቆመው አድማሱን አሻግረው
በሃሳብ እያስተዋሉ እያለ ከተማሪዎቻቸውአንዱ
"መምህር አንድ ጉዳይ አስጨንቆኝ ልጠይቅ ነው የመጣሁ" በማለት ከሄዱበት የሃሳብ
አለም መለሳቸው


መምህሩም ወደ ተማሪያቸው ዞር ብለው እያዩት "ጉዳዩ
አስጨንቆህ ሳይሆን በጉዳዩ አንተ ተጨንቀህ ነው ፡፡ የሆነስ
ሆነና ምን እንደሆነ ንገረኝ"


ተማሪውም "እንዴት መሰሎዎ መምህር የቅዱስ ቃሉ ሚስጥር እንዲገለጥልኝ እሻለሁ
ይሁን እንጂ እለት በእለት እንዳላጠና እንቅፋት ገጥሞኛል . . ."


መንፈሳዊው መምህር በጣቶቻቸው ጢማቸውን ሳብ ሳብ
እያደረጉ "እንቅፋት እንደገጠመህ አመንክ ፡፡


መልካም እንቅፋቱ ምንድነው?


ተማሪው ቀጠለ "የምኖረው ከወንድም እህቶቼ ጋር እናትና
አባቴን ጨምሮ በአንድ ትንሽ ጎጆ ቤት ውስጥ ነው እናም ቃሉን ለማጥናት ጥሞናና ጸጥታ
የማገኝበት የአፍታ ጊዜ ስለሌለተቸግሬያለሁ ፡፡ ምን ባደርግ ይሻላል?


ችግሩን በደንብ አድምጠው የተረዱት መምህርም የተማሪያቸውን ትከሻ በፍቅር አሸት
አሸት እያደረጉ
"እስቲ አንድ አፍታ ወደጉዋሮ ዞር ዞር እንበል ምናልባት አንዳች
ነገር ይገለጥልን ይሆናል" ብለው ወደ ውጭ አብረው ወጡ ፡፡


"እስቲ ቀና ብለህ ወደ ሰማይ ተመልከት" አሉት


"ምን ይታይሃል? "


"ወሰን የሌለው ሰፊ ሰማይ" ተማሪው መለሰ
"አሁን ደሞ እጅህን አይኖችህ ፊት ጋርደህ ወደላይ ተመልከት


ምንድነው የሚታይህ?


እጄ ብቻ


በደንብ አይተህ ንገረኝ ብለው በቆመበት ትተውት ጥቂት
እርምጃ እንደተራመዱ


መምህር ከእጄ መዳፍ እና ጣት ውጭ ምንም አይታየኝም
እርምጃቸውን ሳያቋርጡ አየህ ልጄ ወሰን አልባውን ትልቁን
ሰማይ ማየት ያልቻልከው በትንሿ እጅህ አይንህን ስለሸፈንክ ነው ልክ እንደዚሁ
ከቤተሰባችህ ጋር በትንሽ ጎጆ መኖርህን
መንፈሳዊውን እውቀት ልብህ እንዳትረዳ ጋረድክ ፥ በነሱ
ጨዋታና አንድ ላይ አብሮ በመኖር ፍቅር ውስጥ የቅዱስ ቃሉን ፍቺ መገለጥ ፈልግ . . .


በትንሹ ትልቁን አትጋርድ

ውብ ቀን!💚

@wegoch
@wegoch
Forwarded from ግጥም ብቻ 📘 (ልዑል)
ተስፋ የግጥም ስብስብ መፅሀፍ ምረቃ
በ አስታውሰኝ ረጋሳ (አስቱ)

አርብ ነሀሴ 10
ክ 11:00 ጀምሮ
በ አዲስ አበባ ቲያትር እና ባህል አዳራሽ (ማዘጋጃ) ፒያሳ

@getem
@tebeb_mereja
@tebeb_mereja
2024/09/27 17:25:15
Back to Top
HTML Embed Code: