Telegram Web Link
💚
የእናቶች ፀሎት እና ልመና ጠብ የምትል አይደለችም!!

ያደለው ቅዱሳንን ተማፅኖ እንዲህ ቤቱ በተአምራት ይሞላል! ይባረካል ይፈወሳል።


የኢትዮጵያ እናቶች ፀሎት አገራችንን ይጠብቅ አሜን

💚
መልካም ሰንበቲት

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ለውብ ቀን
💚
"የሕይወትን የሚፈጥራት አሁን እየተሰማህ ያለው ነገር ነው"


በሕይወት ውስጥ እንዳለ ማንኛውም ነገር ስሜትህንም ጥሩ ወይም መጥፎ ሊሆን
ይችላል።


አሉታዊም አዎንታዊም ስሜቶች አሉህ። ሁሉንም አዊንታዊ ስሜቶች የሚመጡት ከፍቅር
ሁሉም መጥፎ ስሜቶች ደግሞ የሚመነጩት ፍቅር ከማጣት ነው።


የተሻለ ስሜት ስታሳይ ለምሳሌ ስትደሰት የተሻለ ፍቅር በመስጠት ላይ ነህ። የበለጠ ፍቅር
በሰጠህ ቁጥር ደግሞ የበለጠ ይሰጠሀል።


የተከፉ ስሜት ሲሰማህ ለምሳሌ የተገፋህ ሲመስልህ አሉታዊ ስሜት የመርጨት ዕድል
ይሰፋል የምትቀበለውም የበዛ አሉታዊነትን ይሆናል። በአሉታዊ ነገሮች በጣም የምትበሳጭበት
ምክንያት በአሉታዊ ኃይል የሆነው ፍቅር ስለሌለ ነው።

ውብ ቀን💚!!!

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ለውብ ቀን
💚
መኖር የምትችለው የሚያስፈልግህን እንጂ የምትፈልገውን ሁሉ እንዳልሆነ አስብ።
ቀንህ እንዲ በራ ጧት በተነሳህ ጊዜ ይሄንን አስብ
ሁሉ በአንተ እንዲኖር እንጂ ፣ አንተ በሁሉ ውስጥ ለመኖር አትሞክር። ሁሉ ወደ አንተ
የሚመጣበትን መንገድ ይኑርህ። አንተ ወደ ሁሉ ለመሄድ አትሞክር።
ሁሉ ለአንተ ተፈጠረ እንጂ አንተ ለሁሉ እንዳልተፈጠርክ እወቅ። የሚጠበቅብህን ህይወት
ኑር አንጂ፣ የምትፈልገውን ሁሉ ለመሆን አትጠብቅ።

ሸጋ ቀን💚!

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ባህል፣ቅርስ፣ወርስ.....የምንለው ኑሮ የሚያቀለውን ሳይሆን ሕይትን የሚያከብደውን ነው። እምነታችን ቀይዶናል፣እውነታችን አስርቦናል፣ልምዳችን ቸነፈር ሆኖብናል፣ታሪካችን አናንቆናል፣ውርሳችን ጦረኛነትን አስፍኖብናል። አሸነፍን እና ተሸንፈን ካልሆነ፣አንከባበርም።

yuval noah harari በጻፈው "Hormode-us" ውስጥ የሰው ልጅ ለብዙ ሺህ ዘመናት መላቀቅ ካቃተው አጥቂውን ከረሐብ፣ከቸነፈር፣እና ከጦርነት ነፃ መውጣቱን ያውጃል። ዛሬ የሰው ልጅ ከረሐብ ይልቅ በጥጋብ እንደሚሞት ይጠቅሳል። ከቸነፈር በላይ እራስን ማጥፋት እንደሚያሰጋው ይደመድማል። ከጦርነት ይልቅ በአሸባሪዎች ጥቃት የሚሞተው እንደሚልቅ ይጠቅሳል። ይሄ የሰው ልጅ የደረሰበት ከፍታ እኛን አለመመልከቱ ዙሪያችንን በመቃኘት ብቻ ማረጋገጥ ይቻላልን። ዛሬም ረሓብተኞች ነን ፣ዛሬም፣የኮሌራ ጉዳይ ሥጋታችን ነው፣ዛሬም፣ለጦርነት ነጋሪት በመጎሰም ተንቀሳቃሽ ምስል እንቀርጻለን.......

...የሰው ልጅ ሲያሸንፍ እኛ የት ሆነን የድል በዓሉን አከበርን?እንዴት መጠሪያው ውስጥ ተካተትን? ለምንስ ያለንበት መረዳት ተሣነን?በማፈሪያችን ኮራን?....

...አንዳንዴ እንደዚህ ማሰብ ጥሩ ነው!!

ምንጭ :- ፍትህ መፅሔት ሰኔ 20111ዓ.ም ((( አለማየሁ ገላጋይ )))

ሰላም እደሩልኝ!!!!💚

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ለውብ ቀን
💚


በሺዎች የሚቆጠሩ ሻማዎችን ከአንድ ነጠላ ሻማ መብራት ይቻላል። የሻማው መብራት
ግን አይቋረጥም።


ደስታንም ማጋራት ደስታ አይቀንስም

ውብ ቀን💚

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ሆሆ
(በእውቀቱ ስዩም)
"ወንድ ሆኖ የማያመነዝር ፤ ወታደር ሆኖ እማይሰነዝር ፤ ነጋዴ ሆኖ እማይዘረዝር የለም ! “ይላል ምኡዝ ::
እውነቱን ነው፤ከጥቂቶቻችን በቀር ብዙ ወንድ በህይወቱ ቢያንስ አንዴ በትዳሩ ላይ ያድጠዋል:: ድርያ በአርቲስት ላይ ይጋነናል እንጂ ፊትና ጭን ከተሰጠው፤ ገበሬ ነጋዴ ፓስተር ሼህ የንስሃ አባት ሳይቀር እንደሚወሰልት እናውቃለን:: መቸም የሴት ገላ ማቀፍ እንዴት እንደሚጥም የቀመሰ ያውቀዋል፤ ግን የሚያስከፍለው ዋጋ ከደስታው ጋር አይመጣጠንም፤ አንድ ጣሳ ደስታ ይሰጥህና አንድ በርሚል ጣጣ ያሸክምሃል!!
1
የሆነ ጊዜ ላይ አሜሪካ ውስጥ ባንድ ከተማ የተከሰተውን ዜና በራሴ መንገድ ስተርተው ይሄን ይመስላል፤
ሰውየው ሚስቱ ማታ ለስራ በሄደችበት ውሽማውን አምጥቶ በተቀደሰው አልጋ ላይ ይፈትጋታል፤ በፍትጊያ መሀል ኮቴ ሰምቶ ቀና ሲል ሚስቱን አያት፤ ውሽምየዋ እንደስፓይደር ውመን በመስኮት ዘልላ ነካችው፤ ባልየው ብቻውን ከሚስቱ ጋር ተፋጠጠ፤ ሚስትዮዋ ለሰይፍ ሩብ ጉዳይ የቀረው ቢላዋ ይዛለች፤ ባሉካ ለመሮጥ ተመኜ ፤ግን እግሩ ቀጤማ ሆነበት፤ በወዛደር አማርኛ እንግለፀው ከተባለ እድሩ የቡልዶዘር ጎማ ሆነበት፤ ሚስትየው ምንም አላለችም፤ አልጋው ላይ እመርር ብላ ወጣችና አገር አማን ነው ብሎ ቆሞ የሚጠብቀውን ብልቱን ጨብጣ ከስሩ መተረችው፤ ከዛ እንደ ቀይ ስር በቁንጮው አንጠልጥላው ወጣችና በቤቱ ጉዋሮ በሚገኘው ዱር ውስጥ ወርውራው ተሰወረች፤
ብዙ ሳይቆይ አምቡላንስ ስልቡን ሰውየ ይዞ ወድ ሆስፒታ መረሸ፤ ያሜሪካ ፖሊስ በቦታው ደርሶ ፤ ከሲአኤ ጋር በመተባበር አካባቢውን በብረት ለበስ መኪና አጥሮ ተቆርጦ የተጣለውን ወሸላ ፍለጋ ተሰማራ፤፤ ከላይ በሂሊኮፍተር ከታች በአነፍናፊ ውሻ የታገዘ ሰአታትን የፈጀ አሰሳ በሁዋላ የተቆረጠው ብልት የጉንዳን መንጋ ወርሶት ተገኘ፤፤ በመጨረሻ ዶክተሮች ወደ ስልቡ ባል ቀርበው፤ “የጠፋብህ ብልት ይሄ ነውን?” ብለው’ በመስቀልኛ ጥያቄ መርምረው አረጋግጠው፤ በቀዶ ጥገና ተከሉለት፤ትንሽ ከመንሻፈፉ በቀር በድሮው ቦታ ተተከለ ፤እረ እንዴውም ከዱሮው ሳይሻል አይቀርም፤ ሚስት ተብየዋን ደስ አይበላትና ሀኪሞች ፤ እንደ ክንዱ በፈለገ ጊዜ የሚዘረጋውና የሚያጥፈው አድርገው ተከሉለት፤
2
ይሄ ደሞ ባልንጀራየ የነገረኝ ነው፤
ዲሲ ውስጥ የሚኖሩ ባልና ሚስት ኢትዮጵያውን የተጋቡበትን አስረኛ አመት በማክበር እየተዝናኑ አመሹ፤ከዚያ ሚስትዮዋ” ቤብ፤ በፍቅራችን ላይ ቅመም የሚጨምር ነገር ላሳይህ " አለችና ከራቫቱን ፈታችለት፤ አያ ‘ቤብ ‘ ክራቫቱን እያስፈታ ፤ ከታች ስራ እንዳይፈታ፤ ቀበቶውን ፈታ፤
ከጥቂት ደቂቃ በሁዋላ አንድ የትራፊክ ፖሊስ መንገድ ዳር ቆሞ ቫይብሬት የሚያደርግ መኪና ስለተመለከተ ጠጋ ብሎ መስኮቱን አንኩዋኩዋ!
“is there any problem ? officer? “ አለ ባልየው ትንፋሹ እየተቆራረጠ::
“መኪና መሳረር ህገወጥ ስለሆነ ልቀጣችሁ ነው” አለና ፖሊሲ ባልየውን መቶ ዶላር ቀጣው፤ ሚስቲቱን ግን ሁለት መቶ ብር ቅጣት ጣለባት፤
ባልየው ትንሽ ቆይቶ ስለከነከነው ፖሊሱን ተከትሎ ደረሰበትና፤
“ቅጣቱስ ይሁን! ይበለኝ፤ የግሬን ነው ያገኘሁት፤ ግን በምን ምክንያት ነው እኔን መቶ ብር ቀጥተህ ሚስቴን ሁለት መቶ ቀጣሃት?’
ፖሊሱ እንዲህ መለሰ፤
“እ ሷ መኪና ውስጥ እንዲህ አይነት ነገር ስታደርግ ያገኘሁዋት ለሁለተኛ ጊዜ ነው፤ ለዝያ ነው እጥፍ ያስከፈልኩዋት”
ባልየው በድንጋጤ ታሞ ይሄው በጎፈንድሚ እያስታመምነው እንገኛለን፤

@Wegoch
@Wegoch
" ከገዛ ፍራቻችን ነፃ ስንወጣ፣ የኛ መኖር ሌሎችን ነፃ ያወጣል" ማንዴላ


»» የካንሰር ኮኮብ ያለቸው፣ ኔልሰን ሮሊላላ ማንዴላ 1918 ዓም፣ የአንደኛው የአለም ጦርነት ማለቂያ ላይ ተወልደው፣ በ2013 ዓም ያረፉት እኚ እውቅ ሰው፣ ዛሬ ልደታቸው ነው። የአለም የሰለምና የትግል ተምሳሌት ሲሆኑ፣ የሳውዝ አፍሪካ ፕሬስዳንት ከመሆን ጀምሮ የኖቤል የሰላም ተሸለሚ አንጋፋ ሰው ናቸው።

»» በኢትዮጵያ በመገኘትም ትልቅ ስልጠና እንዳገኙ በመፃፋቸው ላይ የተናገሩት እኚ እውቅ ካንሰራዊያን፣ የአፓርታይድን አገዛዝ ለመደርመስ ህይወታቸውን ሰተው ሲታገሉ የነበሩ የነፃነት አባት ናቸው ።


🎂🎂መልካም ልደት ማዲባ🎂🎂
🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉

@zodiac_zodiac
@zodiac_zodiac
@zodiac_zodiac


@wegoch
ከፖለቲካ ውጭ ብዙ እልፍ አእላፍ የህይወት ቅመሞች አሉ ። ችኮ መንቻኮ ፖለቲካችን
ለስላሳውን የሰውኛ ገፃችንን እየገፈፈው ነው ። ከገበሬው እስከ ከተሜው ከሽፍታው እስከ
መኳንንቱ ከማይሙ እስከ ሊቁ በአንድ አግዳሚ ወንበር እኩል ጎን ለጎን አስቀምጦ
እንዳይደማመጥ አድርጎ የሚያስጮህ የሁሉ መንገደኛ ሙያ ፖለቲካ ይባላል ።
በየማጀታችን እንደ ኩፍኝ ገብቶ አፍኖናል ። ሰውነታችንን እየነጠቀ በሰውነት ድርቀት
እያቆራመደን ነው ። ሁሉም ሰው የሚተያየው በፖለቲካ አይን ብቻ ሆነና የፍቅር የመዋደድ
የመነፋፈቅ ያገር ልጅነት ወዝ ሁሉ ተሟጥጦ ጠፋ ። አሁን ሰው ሰው የሚሸት ነገር ነው
ረሃባችን ። ፖለቲካችን ያውም የሴራ ፖለቲካችን እካካ ነገር ነው ። ቀልብያችንን አግርሮ
ነፍስያችንን አድርቋል ። እናም ሳቂታዋንና ገራገሯን የህይወትን ገፅ እንባጃለን ።

ሸጋ ምሽት💚

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
...................አይበቃንም ወይ?
......................................................................
..እናንተዬ ምን የሚሉት ልክፍት ነው ግን የተጠናወተን?
ምነው ትንሹም ከተማና መንደር ብራቃችን ሆኖ ተባልተን ካልሞትን አልንሳ?! አባይን ያላየ ምንጭ ያመሰግናል ሲባል እኛ ጭራሽ ምንጯንም ካላደፈረስን ብለን ታገልንኮ... ፍራንክፈርትን፣ ዱባይን፣ ኒውዮርክን፣ ኳታርን፣ ቤጂንግን፣ ፓሪስ፣ ሎንደንን ወዘተ የሚያህሉ አዲስ አበባንም ሆነ መቀለ፣ ሐዋሳንም ሆነ ባህርዳር፣ አዳማንም ሆነ ጎንደር ደራርበው ... እኛ ምናካብደውን ከተማ የገጠር ከተማ አስመስለው የሚቦንሱ እልፍ ከተሞች በሞሉባት ዓለም የኔ ነው በሚል ደዌ ተባልተን ልናልቅ እኮ ነው።
.... ያለችንንም አሳድገን ከቀደምቶቹ እኩል እንደመሰለፍ እንደ ወለፈንዲ ዱርዬ ልጅ የሙጥኝ በልቼ ልሙት! አብሬ አልጠቀምም ብለን የምንስቆነቆነው፣ የምንገፈታተረው፣ የምንባላው ምን የሚሉት ልክፍት ቢይዘን ነው እናተዬ?
...እውነት በጣም ያሳፍራል! ይህቺ ሐገር በኢኮኖሚ ብቻ ሳይሆን በአዕምሮ ንቃት ደረጃም ኋላ ተሰላፊ እንደሆነች ምስክር መጥራት አላስፈላጊ ነው።
... ኧረ ትንሽ እንፈር! ኧረ ሼም ነው! ቅንጣት የአዕምሮ ንቃት ይኑረን! እውነት እስኪ ከሆሆታ ወጥተን ቆም ብለን እናስብ! ዓለም በአሁኑ ሰዓት ብሔርና ጎሣ የሚለውን ድሪቶ አውልቃ እወቀትና ችሎታ ላይ ሐዲዷን ዘርግታለች 'ኮ።
...እውቀትና ችሎታው ካለህ ከአዲስ አበባም ሆነ ከሐዋሳ ብዙ እጥፍ የሚልቁ ከተሞች ውስጥ በነፃነት ሰርተህ፣ ሐብት አፍርተህ፣ ወልደህ ከብደህ የምትኖርበት ዘመን ላይ እኮ ነን። ያደጉት ሐገራት ልጆቻቸው በእውቀት በልፅገው አዲስ ነገር እንዲፈጥሩ በሚራቀቁበት ዘመን ልጆችን ድንጋይና ዱላ እየሰጡ ለጥፋት ማሰለፍ ምን የሚሉት ልክፍት ነው? አናሳፍርም ወይ?
የድህነትና መገዳደል ጉዞ አይበቃንም? የኔ ነው የኔ ነው ከምንልስ የኛ ነው ብንል አናተርፍም?
... ሰው እንደፈለገ ተንቀሳቅሶ በአህጉራት መካከል ወር ከወር በሚሰራበት ዓለም በየጫካውና የገጠር መንደሩ መ�ስመር እያሰመሩ ውጣልኝ ማለት ምን የሚሉት ኋላ ቀርነት ነው? እኮ ንገሩኝ ምን የሚሉት ልክፍት ነው? እናንተዬ ይሄ ትልቅ የሞራል ውድቀት እኮ ነው! እደግመዋለሁኝ... ትልቅ ውድቀት!
***እባካችሁን ኢትዮጵያን የሚመጥን የሰውነት ስብዕና ላይ እንድረስ፤ ያለችን ከኛም አልፎ ለሌላ የምተርፍ አንጡራ ሐብት ያላት፣ ሌላውን የሚያስቀና የባህል፣ የነፃነትና መንፈሳዊነት ማማ የሆነች ድንቅ ሐገር ነች።
.... እነ ኢትኤልና ዮቶር-አብ በጥበብ ዓለምን ያስገበሩባትን ብፁዕ ምድር... የሰፈር፣ ተራ፣ ጠባብ፣ ከሰውነት የወረደ አስተሳሰብ ይዘን አናበላሻት። የአውሮፓና አሜሪካው የከተማ ልህቀት ቢቀርብን እንኳን ሐዋሳን እንደ ኬፕ ታውን፣ አርባ ምንጭን እንደሞምባሳ፣ መቀለን እንደ ሲንጋፖር፣ አዳማን እንደ ካይሮ፣ አዲስ አበባን እንደ አቡጃ ለማላቅ፤ የእኔ ብሔር የኔ ብሔር የሚለውን ትርኪሚርኪ ጥለን እንኳንስ የገዛ የሐገርህ ተወላጅ ወንድምህ ቀርቶ የዓለም ዜጎች መጥተው የሚሰሩባት፣ የሚጎበኟትና የእኔ በሆነች ብለው የሚቀኑባትን ኢትዮጵያ ለመፍጠር ረጅም እቅድ ይዘን እንጓዝ፤
"በዘመናዊ ሰፊ ዐለም ውስጥ ይህቺን የመሰለች ምርጥ ሐገር ይዘን የኋሊት አንጓዝ!"
ከዚህ በላይ ምን ልል እንደምችል አላውቅም!

..............(ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ አዕምሮ)


@Wegoch
@EliasGebru
ለጁምኣችን
💚
"ፍቅርን ስትሸከም ነገር ሁሉ ለአንተ እዉነትና ወደእውነት ብቻ የሚወስድ ይሆናል።"


ለጁማዐችን ወደ ሱፊዎች መንደር ስንሄድ ይህን እናገኛለን


የፍቅር መኖሪያው ልባችን ነው። ፍቅር ልዩና የሚያስደስት ስቃይ የተሞላ የፈጣሪ ስጦታ
ነው።


ፍቅርን በልቡ ተሸክሞ የሚዞር እሱ ሚስጥሩን ለማወቅም የሚቸግረው አይሆንም። ፍቅርን
ስትሸከም ነገር ሁሉ ለአንተ እዉነትና ወደእውነት ብቻ የሚወስድ ይሆናል።


በፍቅር ውስጥ ከእውነት በቀር ሌላ ነገር የለም
ለዚህም ነው አፍቃሪዎች በእውነት ባህር እየተሸነፉ ሲሰምጡ የምናየው።

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ለምሽታችን
💚
በምናያቸው ነገሮችና በእውነታው መካከል ሠፊ ልዩነት አለ

ፕሌቶ


የሥሜት ህዋሶቻቹ የሚያቀብሎዋችሁን መርጃዎች
የመጨርሻ እውነት ነው ብላችሁ አትቀበሏዋቸው ።


ምክንያቱም የስሜት ህዋሶቻችሁ ዘላለማዊ የሆነውን ተለዋዋጭ አድርጎባቹሃል ።


ፍፁማዊን ጉድለት ያለው በቦታ ግዜ የማይወስነውን በቦታና ጊዜ የሚወሥን እንዱን ብዙ
አድርገው አወናብደዋቹሃል።


ሰው ሰው ስንል በህዋሣት አማካኝነት የምናየውን በቁመት በመልክና በሁኔታ የተለያዩ
ግለሠቦችን ብቻ ማለት አይደለም ሰው እከሌ ሣይሆን ሁለትናዊ የሆነ ሊዳሠሥ
የማይችል፣ ግለሠቦች ከሚያሣዩት ተለዋዋጭና ግላዊ ጠባይ የተላቀቀ የሠውን ዘላለማዊ
ቅርፅ በሚገልፅ አምሮአዊ መለኮታዊ አለም ውሥጥ የሚመደብ ህያው ህልውና ነው ።

@wegoch
@wegoch
@balmbaras
ለቅዳሚታችሁ
💚
"ሰው የመከራን መኖር በስሜቱ በማወቁ ብቻ ራሱን በመከራ ውስጥ ያኖራል"
ብለዝ ፓስካል (1623-1662 ዓም) የነበረ የፈረንሳይ ፈላስፋ ጸሓፊና ሒሳብ ተመራማሪ
ነበር።

ፓስካል የሰውን ልጅ የታላቅነት ምልክት ወደ ሚያሳየን ሐሳቡ ለዛሬ ለቅዳሜታችን እውነት
እና እምነት ከሚለው መፅሀፍ ውስጥ ይህን የፓስካልን ሀሳብ እነሆ በረከት፦
ለፓስካል የሰው ልጅ ታላቅነት መገለጫው ለመከራ የተፈጠረ መሆኑን ከማወቁ ላይ ነው፡፡


“ዛፍ ለመከራ የተፈጠረ መሆኑን አያውቅም” የሚለው ፓስካል
“ሰው የመከራን መኖር በስሜቱ በማወቁ ብቻ ራሱን በመከራ ውስጥ ያኖራል ፤ ነገር ግን
በዚያ ዕውቀት ውስጥ ታላቅነትን ያገኛል” ይለናል፡፡
ይህንኑ ሲያብራራልን፡- “መከራ ውስጥ መኖራችንን የምንረዳው መከራው ሊሰማን ስለቻለ
ነው፤ ስንሞት ብቻ የመከራ ልምምድ ከእኛ ውስጥ ያበቃል፤ የፈረሰ ቤት መከራን
አያውቅምና፡፡
ሰው ብቻ መከራን ማወቅ ይቻለዋልና በሕይወቴ አያሌ ስቃዮችን ለማሳለፍ ቻልኩ፤ እንዲሁ
ደግሞ የሰው ታላቅነት በአስተሳሰቡ ውስጥ ይገኛል” በማለት ፓስካል ታላቅነታችንን
መሠረት ያስቀምጠዋል፡፡
“ሰውን ያለ እግር ፣ ያለ እጅና ያለ ራስ (ምንም እንኳን ራስ ከእግር በላይ አስፈላጊ መሆኑን
የሕይወት ልምድ ቢነገረንም) ማሰብ እችላለሁ፡፡
ነገር ግን ሐሳብ የሌለውን ሰው ለማሰብ የማልችለውና ከድንጋይና ከእንስሳ ለመለየትም
የሚያስቸግረን ነው” የሚለን ፓስካል ይንና ሰው ማሰብ በመቻሉ ብቻ ደግሞ ታላቅነትን
ማግኘት እንደማይችል ማወቅ ይገባዋል የሚል ሐሳብ ያመጣል፡፡
“የሰው ልጅ ታላቅነትና ክብር በሐሳቢ ላይ የተመሰረተ መሆኑን አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን ይህ
ሐሳቡ ደግሞ ምንድነው? እንዴትስ ከንቱ ሊሆን ይችላል? ብሎ መጠየቅ ይገባል” የሚለው
ፓስካል “ሐሳቡ አስደናቂና ታላቅ የሚሆነውን ያህል ከንቱና የማይረባም ሊሆን ይችላል
እኮ! ሐሳባችን በተፈጥሮ ዓይን ታላቅ ሲሆን በስሜትና ባህርያችን ምክንያት ደግሞ አያሌ
ጉድለቶች አያጡትም፡፡
በጥቅሉ የሰው ልጅ ተፈጥሮውን የሚነግሩት ሁለት ነገሮች ቢኖር ደመነፍስ እና ማሰብ
ናቸው፡፡ ነገር ግን ማሰብ የሰው የታላቅነት ምልክት ብቻ መሆኑን አንዘንጋ” ይለናል፡፡
እነዚህ ላይ የሰው ሐሳብ ከንቱነት የሚገለጥበትን ደረጃ ፓስካል ሲገልጠው፡- “ሰዎች
የእግዚአብሔርን እና የተፈጥሮን ሕግ ካወገዙ በኋላ ራሳቸው ላወጡት ሕግ ሲገዙ ማየት
ይገርመናል፡፡
የሰው ከንቱ ሐሳብ መገለጫው በራሳቸው ጥቃቅን ሐሳቦች እየተገዙ ሲጓዙ የፈጣሪን እና
የተፈጥሮን ትክክለኛና የተቀደሱ ሕጎች እረገጡ መሆናቸውን ካለማወቃቸው ላይ ነው”
በማለት ፓስካል የዛሬውን ጉዞ “ሶስት ዓይነት ሰዎ” በማለት ባስቀመጠው ሐሳቡ
ይቋጭልናል፡፡


“ በዚህ ምድር ላይ ሦስት ዓይነት ሰዎ አሉ፦


የመጀመሪያዎቹ እግዚአብሔርን የሚያገለግሉና እሱንም ያገኙ ሲሆን፤ ሁለተኛው ዓይነቶች
ደግሞ እሱን በመፈለግ የሚደክሙና ነገር ግን ያላገኙት ናቸው፤ የመጨረሻው ዓይነቶች
እሱን ሳይፈልጉ የሚኖሩ ነገር ግን ያገኙት ናቸው፤
የመጀመሪያዎቹ አዋቂና ደስተኞች ሲሆኑ ሁለተኛዎቹ ሞኞችና በመከራ ውስጥ የሚገኙ
ናቸው፤ በመጨረሻ የምናገኛቸው ደግሞ ደስተኞች ያልሆኑ ነገር ግን አዋቂዎች ናቸው”
ይለናል፡፡

ሸጋ ሸጊቱ ቅዳሜ!!!!💚💚💚

@wegoch
@wegoch
@wegoch
ለሰንበቲታችሁ
💚
"ለመንፈሳዊ ፍላጎታቸው ንቁ የሆኑ ደስተኞች ናቸው"
መንፈሳዊ ነገሮችን የተጠሙ ደስተኞች ናቸው መንግሥተ ሰማያት የእነሱ ነውና።
“የሚያዝኑ ደስተኞች ናቸው፤ መጽናኛ ያገኛሉና።
ገሮች ደስተኞች ናቸው፤ ምድርን ይወርሳሉና።
“ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ደስተኞች ናቸው ይጠግባሉና።
“መሐሪዎች ደስተኞች ናቸው፤+ ምሕረት ይደረግላቸዋልና።
“ልባቸው ንጹሕ የሆነ ደስተኞች ናቸው አምላክን ያያሉና።
“ሰላም ፈጣሪዎች ደስተኞች ናቸው ፤ የአምላክ ልጆች ይባላሉና።
“እነሆ፤ የእግዚአብሔር ማደሪያ በሰዎች መካከል ነው
እንባን ሁሉ ከዐይናቸው ያብሳል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሞት ወይም ሐዘን ወይም ልቅሶ
ወይም ሥቃይ አይኖርም።

መልካም ሰንበቲት💚

@wegoch
@wegoch
@wegoch
2024/09/27 23:22:19
Back to Top
HTML Embed Code: