Telegram Web Link
ንዴት ቻልሽ? አልኩ ኮካዬን እያጣጣምኩ፡፡
- ለነፃነት ታጋይ ነበርኩ…የደርግ ወታደሮች አስተማረኝ፡፡ ምርኮ ወታደር፡፡ …ኢትዮጵያዊ ከሆንሽ ደግሞ በነፃ እጋብዛለሁ…የበራድ ቡና አለ ይዤልሽ እመጣለሁ….አለችና ጥላኝ ሄደች፡፡ ኮካዬን አስቀምጬ እንደ ማነከስ እያለች ስትሄድ አየኋት፡፡ ጊዜ ግን የሚገርም ነገር አይደለም? መኖር ግን የሚደንቅ ነገር አይደለም? እኔ፣ አባቴ የኢሰፓ አባል የነበረ ኢትዮጵያዊት፣ እኔ የጥላሁን ገሰሰን ‹‹አባረህ በለው ያንን አመፀኛ ተገጣይ ወንበዴ፣ ልኩን አሳየው አስኪደው በዳዴን›› በህጻንነት ጆሮዬ እያዳመጥኩ ያደግኩ ኢትዮጵያዊት እኔ፣ በጉረምስናዬ ዘመን ከኤርትራ ጋር ስንዋጋ የክፍሌ ልጆች ለኢትዮጵያ ሊሞቱ በሰልፍ ሲሄዱ ቆሜ ያነባሁ ኢትዮጵያዊት፣ እኔ፣ አሸባሪው ሻእቢያ፣ የሻእቢያ ተላላኪዎች፣ የአስመራ መንግስት ቡችሎች…የሚሉ የፕሮፓጋንዳ ቃላትን ስሰማ የጎለመስኩ ኢትዮጵያዊት.. በአንዲት ሚጢጢ የኤርትራ የገጠር ከተማ፣ ኤርትራን ለመገንጠል ከታገለች የሻእቢያ ወታደር ቁርስ ቤት ተቀምጬ ስልስ በኮካ እየበላሁ፣ ኢትዮጵያዊ ‹‹ጥቁር እንግዳ›› በመሆኔ ደግሞ ነፃ ቡና ልጋበዝ ነው፡፡ በእኔ እና በእሷ መሃከል ሰባ ሺህ ስዎች ረግፈዋል። በእኔ እና በእሷ መካከል ሃያ የጠብ አመታት አልፈዋል። በእኔ እና በእሷ መካከል ሊነገር የሚቀፍ በደል እና ስቃይ ተከናውኗል። ግን ያ ሁሉ አልፎ ቡና ልትጋብዘኝ ነው። ጊዜ ግን የሚገርም ነገር አይደለም? መሰንበት ግን የሚደንቅ ነገር አይደለም?
(ይቀጥል ይሆናል…)

@paappii
@wegoch

By hiwot emishaw
‹አንድ የጋምቤላ ተወላጅ ሽማግሌ ስለወቅቱ የሀገራችን ችግር የተናገሩትን ላስታውስህ . .
.
ሁለት ወንድማማቾች ወደ ትምህርት ቤት እየሄዱ ነበር፤ ትናንሾች ናቸው፤ ከሁለቱ አንዱ በእጅ ሳንቲም ይዟል፤ ሳንቲሙን በፍቅር ይዞ፣ እንዳይጠፋበት ተጠንቅቆ ወደ ትምህርቱ እየሄደ ቢሆንም፣ ያለመታደል ነገር ሆኖ ሲሮጥ 50 ሳንቲሟ ከእጁ አመለጠች። ልጁ ደንግጦ የጠፋበትን ሳንቲም ፍለጋ ኳተነ። ወንድሙ ግን ያቺ ሳንቲም የት እንዳለች ያውቅ ነበር። ሳንቲሟንም እንዳያት ሄዶ በእግሩ ቆመባት። ለወንድሙ ደብተርህን ልያዝልህ፤ ሳንቲሟን አንተ ፈልግ ብሎት በሳንቲሟ ላይ እንደቆመ ለብዙ ጊዜ ተገትሮ ቀረ፤ ወንድሙ ለአንድ አፍታ ዘወር እንዲልለት ቢፈልግመረ ወንድምየው ግን ሳንቲሟ የወደቀችው እዚያው አካባቢ እንደሆነች ስለሚያውቅ ፍለጋውን ቀጠለ። በዚህ የተነሳ ለብዙ ሰዓት እቆሙበት ቦታ ከባድ ፀሐይ መታቸው። ትምህርት ቤትም ረፈደባቸው። ፈተናውም አመለጣቸው።
ሁለቱ ወንድማማቾች የሆኑት ነገር፣በአሁኒቷ ኢትዮጵያ እየተተገበረ ነው። ችግራችን ምን እንደሆነ እናውቀዋለን። የጠፋብንን ነገር እናውቀዋለን። ግን አንዳችን ለሌላችን መፍትሄ ከማፈላለግ ይልቅ በችግሩ መፍትሄ ላይ ቆመንበታል። በዚህ የተነሳ አንዳችን ለሌላው መሰል ወንድማችን ብቻ ሳይሆን ለራሳችን እንቅፋት ሆነናል። ለዚህም ነው፣ በቅንነት ማጣት በሽታ ታውረን በመንገዳገድ ዘመናችንን እየጨረሰን ያለነው . . .›› ከ‹ያልተቀበልናቸው› መጽሐፍ የተወሰደ፣እንዳለጌታ ከበደ፡፡

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ወሎ :- "የአገር ድባብ "
ከተሰኘው በሌ /ኮ ጌታቸው መኮንን ሐሰን ጡሃ አማካኝነት መጋቢት 1984 ዓም
ከታተመው መፅሐፍ መካከል ነው ያገኘሁት :: ምናልባት ሌሎቻችሁ ያላነበባችሁት ካላችሁ
ተቋደሱት ብየ ነው ::
"ወሎና መርካቶ "
አንድ ፀሐፊ ወሎን የመርካቶ ተምሳሌ አርጎ ያቀረበው ፅሑፍ በአንድ ወቅት የመገናኛ
ብዙሀንን ትኩረት አሰባስቦ መቆየቱ ይታወቃል ;; ይህ ግን የዋዛ አልነበረም :: ወሎ እንደ
መርካቶ የተለያዩ አመለካከትና እምነት ያላቸውን : በተለያዩ የዕድሜ ክልል የሚገኙትንና
የበርካታ ብሔረሰቦችን አባላት በአንድ ዓይነት ሁኔታ የሚያስተናግድ በመሆኑ ነው ::
ይህንንም እንደሚከተለው በመጠኑም ቢሆን ማየት ይቻላል ::
አምስት ዓይነት አበይት ቋንቋዎች የሚናገር ብሄረሰቦች በወሎየነት ስሜትና ዕምነት
ተፈቃቅረው ያላንዳች ኮሽታ በወሎ በሰላም ይኖራሉ :: እነርሱም አማራ : አገው : ኦሮሞ :
ትግራይና አፋር ናቸው :: አነስተኛ ቁጥር ያላቸው አርጎባዎችም በወሎ ይገኛሉ ::
እኒሁ በአጠራር የተለያየ የብሄረሰብ ስም ያላቸው በማህበራዎ ሕይወት ግን ከሞላ ጎደል
ተመሳስለውና ተፈቃቅደው ስለሚኖሩ አብዛኛውን ጊዜ በተለይም በወሎ የሚገኙት ደማቅ
ከተሞች ሳይቀር እገሌ "ወሎየ " እንጂ የብሄር ወይም የብሄረሰቡን አባል ነው ሲባል
አይሰማም :: ርስበርስም በአምቻና በጋብቻ ስለተሳሰሩ በአብዛኛው የሚንጽባርቁት
የአንድነትን ስሜት ነው ::
በዋግ አውራጃ የሚገኘው ሕዝብ ቢያንስ የሶስት ቋንቋዎች ተናጋሪ ነው :: እነዚህም
አማርኛ : ትግርኛና አገውኛ ናቸው :: በደሀና ወረዳ በሚገኙት ምክትል ወረዳዎች (በቀደሞ
አጠራር ) አብዛሀኛዎቹ የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ሲሆኑ በተላጌ ምክትል ወረዳ የሚገኙት ብቻ
አገውኛ ይጠቀማሉ :: በሰቆጣ ወረዳ ደግሞ የጀረባና የዝቋላ ምክትል ወረዳ ህዝቦች
አገውኛ ብቻ ሲጠቀሙ በቀሩት ምክትል ወረዳዎች ደግሞ አማርኛና አገውኛ ይናገራሉ ::
በመሠረቱ የወሎን ሁኔታ በዚህ ተምሳሌነት ማየት ይቻላል :: በአንድ ቀበሌ (አነስተኛ
ክልል ) እንኳን የተለያየ ቋንቋ የሚናገሩ ብሄረሰቦች ሊኖሩ የሚችሉበት :: ይሕ እንዳለ ሆኖ
የአንዱ ወረዳ ሕዝን ከሌላው ወረዳ ሕዝብ በብዙ ኪሎሜትር የሚለያይ ቢሆንም በዝምድና
: በጋብቻ : በአበልጅነትና በርስት ተካፋይነት (የርስት ተካፋይነት ከ 1970 ዐም ወዲህ
ቀርቷል ) እግጁን የተሳሰሩና የሚተዋወቁ ናቸው :: አንዱ ሌላውን በድንገት ከመንገድ
ቢያገኘው ተዘያይሮ (ተጨባብጦ ) ከየት እንደመጣና የነማን ዘመድ እንደሆነ መናገር
የተለመደ "ግብረገባዊ ግዴታ " ነው :: ሌላው ቀርቶ ጭራሽ ከራቀ አገር የመጣ ሰውን
እንኳን አንዱ ከመንደግ ካገኘው ሳይዘይረው ወይም ሰላምታ ሳይሰጠው አያልፍም :: ዝም
ብሎ ካለፈ ግን ሽፍታ ወይም ባለጌ ነው ተብሎ ይገመታል ::
ስለሆነም በሌላውና በአንዳንድ የአገራችን ክፍል በጎሰኝነት ስሜት የሚታየው የመጎሳሰም
ሁኔታ በወሎ አለመታየቱ ወሎን ብቸኛና ዕውቅ ይደርገዋል :: እኔአማራ ነኝ : እኔ ኦሮሞነኝ :
ትግሬ ነኝ : ወዘተ ... ከሚለው ይልቅ ወሎየ ነኝ የሚለው ስሜት በእጅጉ ያይላል :: እኒሁ
የተለያዩ ጎሳዎችም በዋግ አውራጃ ተመሳሌነት እንደቀረበው አብዛሀኛውን ጊዜ በመጋባትና
በመዋለድ ቋንቋቸውንና ባህሎቻቸውን ተጋርተው በሰላምና በመፈቃቀድ ይኖራሉ ::
በወሎ የሁለት አበይት ሀይማኖት ተከታይ ሕዝብ ይኖራል :: አብዛሀኛው የወሎ ሕዝብ
የእስልምና ሀይማኖት ተከታይ ሲሆን አብዛኛዎቹ እስላሞች ደግሞ ሐረጋቸው የአማራ
መሆኑን ይናገራሉ :: እንደሚታወቀው በሌሎች የኢትዮጵያ ክልሎች የሚገኙት አብዛኛዎቹ
አማራዎች ክርስቲያኖች ናቸው :: እጅግ የሚገርመውና የሚያስደንቀው ደግሞ በሀይማኖት
ምክንያት ምንም አይነት ያለመግባባት ስሜት አለመታየቱ ብቻ ሳይሆን የሀይማኖት መዳቀል
ወሎየውን የየትኛው ሀይማኖት ተከታይ እንደሆነ ለመገመት እንኳን በማያስችል የመገኘቱ
ሁኔታ ነው :: ጎረቤቷ እስላም የሆነች ክርስቲያን ወደ ቤተክርስቲያን ለማስቀደስ ስትሄድ
እስላሟ ልጅዋን ይዛ የራስዋን ጡት እያጠባች ተጠብቅላታለች :: በዚሁ አንጻር እስላሟ
ወደ መወሊድ ወይም ወዳጃ ስትሄድ እስላሟ እንድምታደርገው ክርስቲያኗ ልጅዋን
እያጤባችና ቤቷን እየጠበቀችላት ትቆያለች ::
በአጠቃላይ በሐይማኖት ምክንያት በሚኖሩት በዓላት : ድግሶችና ማናቸውም ዓይነት
የመቀራረቢያ ዝግጅቶች እስላም L ክርስቲያን ሳይባባሉ ባንድነት ይሳተፋሉ :: ጤበል
ቅመሱ የሚል ክርስቲያን ጠላ ብቻ ሳይሆን ለእስላሙም ቡቅሪ የማዘጋጀት ነገር የተለመደ
ነው :: የዚህ የተሳሰረ ግንኙነት ውጤትም በወሎየዎች የስም አሰያየም እንኳን
እንደሚታየው እገሌ ክርስቲያን ነው እስላም ነው ብሎ ለመግመት እንኳን ያዳግታል :: :ከበደ
መሐመድ : መኮንን ሐሰን L ካህሳይ አሊ : ገመቹ አህመድ : ወዘተ ... የሚሉትን ስሞች
ይዘን ብንመረምር ርሱ ክርስቲያን ቢሆን አባቱ እስላም ወይም ርሱ እስላም ቢሆን በአባቱ
ክርስቲያን ይህ ካልሆነ ደግሞ በአያቱ የሌላውን ሀይማኖት ጉዳይ እንኳ አንድ ቢያደርገው
እንጂ ሊነጣጥለው የማይችል መሆኑን ያስገነዝባል :: በብሄረሰብም ረገድ ተመሳሳይ ሁኔታ
አለ ::
በጠቅላላእ የጎሳና የሀይማኖት ጉዳይ በወሎ ሕዝብ መካከል አንዳችም xግር
ያልፈጠረበትና ሊፈጠርበትም የማይችል ሲሆን እስካሁንም በመተሳሰርና በአንድነት ስሜት
በመኖር ላይ ይገኛል :: ይህንንም የኢትዮጵያ ሕዝብ በአርአያነት ሊከተለው የሚገባ ነው ::
በጣም የሚገርመውና የሚያስደንቀው ጉዳይ ቢኖር በክርስትና ሀይማኖት እጅግ ጥንታዊው
ቤተክርስቲያን በወሎ የመገኘቱን ያህል የቁርአን ጥንታዊ መፅሐፍትና ታሪካዊ መስጊዶችም
በወሎ የመገኘታቸው ሁኔታ ነው ይህም ሁለቱንም ሀይማኖትች በወሎ ጥንታዊ መሰረት
እንዲይዙ አድርጓቸዋል ::
በወሎ ያለውን የአነጋገር ፈሊጥ ወይም የቋንቋ መዳቀል ሁኔት በጥልቀት ለመረመረው ሰው
የተለያየ የሀይማኖትና ብሄረሰብ ቋንቋ ተደበላልቆ ልዩ የመግባቢያ ቋንቋ መፍጠሩን ማጤን
ይቻላል ።
((ጸሃፊው ጌታቸው መኮንን ሃሰን ወሎ ተወልዶ ያደገ የደርግ ከፍተኛ መኮንን የነበረ ከ100
መጽሃፍት በላይ የተረጎመ ጠንካራ ሰው ነበር።)

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
።።።።።።።።።።።
እስቲ ዛሬ እንኳን ከተሻለህ ስለ ኢትዮጵያ አስብ ሰላም ሲኖርህ በ ሀገርህ ትከበራለህ ሰዉን ምታፈናቅል ከሆነ ግን እድሜ ልክህን በ ምድር ላይ እንደ ቃኤን ተቅበዝባዥ ትሆናለህ።

ደሞ ሳልነግርህ ፖለቲካ ድራማ ነው እነሱ ተመካክረው ተከታታይ ድራማ አይምሮህ ላይ እየሰሩብህ ነው አብይም ኦነግም ግንቦት 7 ትም ደብረጺኦንም ገዱም ጀዋርም ታማኝም ኢሀዲግም ሃይለኛ ትወና እየተወኑ ነው አንተ ምንም ሳይጎልህ ትጫረሳለህ እረፍ በቃ ኢትዮጵያዊ ሁን

1 ሚስጥር ልንገርህ መንግስትም ሆነ የ ፖለቲካ ፓርቲዎች ኢትዮጵያ ውስጥ የተማረ ቢቻ እንዲኖር ስለሚፈለግ ያልተማረዉን ህዝብ ሊጨርሱ ቆርጠው ተነስተዋል እንዴት አልክ ካልክ . እስካሁን በተካሄዱ የርስ በርስ ጦርነት ተጎጅው ማነው ገበሬው ያልተማረው ሆ ሲሉ አብሮ ሆ ሚለው ምንም ያልሆነዉስ የ ከተማው ነዋሪ እንደኔ ፌስ ቡክ ላይ ተቀምጦ የሚፈልገውን የሚጽፍ ስለዚ ንቃ ተማር አትስማቸው ምንም አልጎደለብህም ሰው ስላፈናቀልክ ምንም የተለየ ጥቅም አታገንም ትርፉ ኪሳራ ነው ቂምን ማትረፍ ስራ ስጡኝ እንጅ እሄ የኔ ክልል ነው አትበል የ ድራማቸው የ ሟች ገጸ በሃሪ አትሁን ወንድሜ
ደሞ ደሞ ሚኒልክ ጡት አስቆረጠ ምትል እስከዛሬ ለምን እቺ ጥያቄ አልተነሳችም ዛሬ ምን ተገንቶ አቆጠቆጠች በል ? ይሁንስ ብንል ዶክተር አብይ አሁን ማር እያስቆረጠ ነው? እንዴ ? ሱማሌን ቤኔሻንጉልን ቡራዮን ካስታወስክ በቂ ነው እስካሁን ከጠራዉልህ ሁሉም ቦታ የሚኖር አብዛጛው ገበሬ ነው ላንተ የ ጦር ኬዳ ስም እያወጣ ያጫርስሃአ ቄሮ ፋኖ ዘርማ ታፈሰ ምናምን እያለ አትስማ አንተ ከነሱ በላይ ማሰብ የምትችል የ ሰዉ ሊጅ ዘር ፍጥረት ነህ አስብ ሚኒልኪ ካጠፉት በላይ አብይ እያጠፋ ነው ፍቅራችን እንጂ ህገመንግስቱ አያኖረንም ቢሆንልን የዕምነት መጸሀፍትን ባነበብን ሁላችንም መጤዎች ነን ከ 100 አመት በሁላ አንዳችህንም አንኖርም ስለዚ ልጆቻችን በሰላም እንዲኖሩልን ከ ፖለቲካ እንውጣ ሰርተን እንደግ አድገን እናሳድግ የምር ያለፈዉ አልፏል በዘር እራስህን አትገድብ ከዘረኝነት ውጣ ሰው መሆንህን አስብ ልክ እንደኔና እንደጓደኞቼ ሀገራችን ለዘላለም ትኑር።

(ደረጄ ሸዋዬ)
@wegoch
@wegoch
@gebriel_19
የቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ኮንሰርት 3 ቀን ቀረው !!!


የመግቢያ ትኬት መግዛት የሚፈልግ ካለ 0912 65 97 53
<< ጥበብ ካልገባህ እንደእርያ መሆንህ ነው >>

ጠቢብ እንዲህ አለ ፡- <<በጨለማ ማየት እችላለሁ .....!! >> የጠቢቡን አባባል ያልተረዳ ሰነፍ ደግሞ ጠየቀ፡-<<በጨለማ ማየት ከቻልክ ታድያ ለምን መብራት ይዘህ ትሄዳለህ ? >> ጠቢቡ ከሰነፍ የሚጠብቀው ጥያቄ ነውና ሳይደነቅ መለሰለት ፡- << እንዳንተ ዓይነቱ በጨለማ ማየት የማይችል መጥቶ እንዳይገጨኝ ነው >> አለው።


ጠቢብ መሆን ባይቻል የጠቢብን ብርሃን ማየት ይቻላል።

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ከመፅሐፍት የተወሰዱ አጫጭርና አስተማሪ ፅሑፎችን መገኛው።
👇👇👇👇👇
@ethio_deraseyane
@ethio_deraseyane
@ethio_deraseyane
የቤታችን ነው!!!!!

ልጅቱ ባል አገባች አሉ ። የወፌ ብር አበባ እየተባለ ተዘፈነ ።ሎጋው ሽቦ ጭፈራው ደመቀ ። ድግሱ ተበላ ። ""ድንግል ነኝ ፤ ህግ አለኝ " ብላ የተገባችው ልጅ አለኝ ያለችው ህግ ሳይገኝላት ቀረ ። አቶ ባል ሙሽራው ጫጉላ ቤት አጋድሞ ሙሽሪትን በአለንጋ ጠብሶ ጠብሶ ወደ ቤተሰቦቿ ሸኛት ። እያለቀሰች ቤት ደረሰች ። እናትም ደንግጠው "" ልጄን ምነው ??ምነው ??እያሉ ጠየቋት ። ሙሽሪትም """ሙሽራው ህግ የለሽም ብሎ ደበደበኝ"" ብላ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች ። እናት ሆየ ምን ቢሉ ጥሩ ነው፤ ""ሲጀመር በቤታችን ከእናቴ ጀምሮ ህግ የለንም አትይውም ነበር ። ያልፈጠረብንን ከየት ይመጣል አትይውም ነበር ። እናማ ወዳጆቼ በቤታችን ህግ የለንም ከማለታችን በፊት ህግ ይከበር ለማለት ነው ።



@balmbaras
@wegoch
@wegoch
#አረ_እናስብበት_ፊታችን_ወደ_ቅርሳችን

እኔ ሐበሻ አሁንስ እየገረመኝ ነው በሠሞኑ ጥቂት ጊዜዎች ውስጥ #ርዕስና_ዜናመሆን እንደሚሆድ ምንም እንደማይሆድ ተረድቻለው ለአይጥዋም ሆሆሆ ለአንበሳውም ሆሆሆ ተብሎ ይቻላል እንዴ ጓድ።
ዛሬ ቤተ መንግስት ጋር ለተደረገው ሠላማዊ ሠልፍ ቃሊት ያለው ባለሱቅ እንደዘጋ ሲነገረኝ ቤተ መንግስቱ ቃሊቲ ሄደ ብዬ ተሳስቀን አልፈናል ወዳጅ ሁሉም ነገር እኮ ልክ አለው ስትፈራም ስትደፍርም ድንበር ሳታልፍ ሊሆን ይገባል አልጫ ፈሪም አንበሳ ደፋርም መሆን ዋጋ ያስከፍላሉ እና።
ቅድም ታክሲ ውስጥ ጎኔ የተቀመጠውን ምነው Network ጠፋ ብለው ባክ ፓርላማ የከበደ ፀብ ነበር ሚኒስተሮቹ ተጨራረሱ እኮ እሱን ለመደበቅ ነው አለኝ ከዛ ሳጣራ የሠልፉ ጉዳይ ነው ይመስለኛል ሰውየው የሚያውቀው የጦሩ ፓርላማ ይኖረው ይሆናል ወገን ግን ተዉ ቆም ብለን እናስብ ሠዎች እስኪ በዚ የሠበር ዜና ጋጋታ ጊዜ #ስለላሊበላ አልሰማንም እና ነው አደጋው ምን ያህል እንደከፋ ቅርሳችን ምን ያህል መጥፋት መጣሂ እጣው እንደሆነ ስለምን አናወራም ስለሌሎችስ ንቀን ትላንትን አንቋሸን የዘመናችን የግብራችን እርካሽ ቂም እና ጥላቻችን እያጠፋቸው ያሉትን ቅርሶቻችን ለምን አናይም ጎበዝ አረ የሚበጀንን እንሻ ወዳጅ
ስለከተማችን ንፅህና
#ታሪክ_መስራት_ባንችልም_ታሪክ_እንጠብቅ
ስለሀገራችን አንድነት እንደተደራሽነታችን ብናወራ ብንፅፍስ
በቃ ሠበር ዜና የሠበረውን ማህበራዊነት ጥሩ ወጌሻ ብንፈልግስ አረ ቆም ብለን እናስብ

ቅጥ ያጣውን በመሸ ሠበብ የገነነውን የታክሲዎች የዋጋ ጭማሪ ብናስተውል ዛሬ የተጠቀምነው facebook ነገ ከታክሲ ውጪ መልስ አጥተን እንደማንጠቀም አትርሱ

እስኪ በሽታዎች ስላመጡት የከፋ የታማሚያን ቁጥር እንጨነቅ እያየን ነው በየመንገዱ መኪና ቆሞ እስክንበሳጭ የምንለመነው ነገርን ከእንጭጩ አለመሆኑ ነው ብቻ

#አህያውን_ፈርቶ_ዳውላውን ሆነ ጊዜው ወይ ኢትዮጵያዬ

#ኢትዮጵያ_ከሠበር_ዜና_ውጪ_ለዘላለም_ትኑር!!!
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
#ተክለ_ዮሀንስ

@gebriel_19
@wegoch
@wegoch
ደስታን የሚፈጥርልህ ጨዋታ ብቻ ሳይሆን አጫዋችህም ጭምር ነው!!!!😍😍😍😍😍


ቅዳሜያችን፣
የቅኔ ጎርፍ የሚጎርፍባት፣ የእሁድን እረፍት እያሰብን
የምንወዳቸውን መፅሃፍት
የምናነብባት፣ ነፍስያችንን በቅጡ ለማዳመጥ ፋታ
የምንወስድባት፣ ከወዳጅ ዘመድ የምንዘያየርባት ደርባባ
ቀናችን ናት!!!!!

@Balmbaras
@wegoch
@wegoch


ሸጊቱ ቅዳሜ ትሁንላቹ...ወርቆቼ!!!!!!💚💛❤️💚❤️💚❤️
የበሰበሰ ጥርስ
(ካህሊል ጂብራን)

📗📗📒📒📕📕

በአፌ ውስጥ በስብሶ የሚያስቸግረኝ አንድ ጥርስ አለኝ በቀን ሰላማዊ ሆኖ ይውላል ። ምሽቱ ሲገፋ፣ የጥርስ ሃኪሞቹ እንቅልፍ ሲጥላቸው እና መድሃኒት ቤቶቹ ሲዘጉ ግን ይጠዘጥዘኝ ይጀምራል ።

አንድ እለት ትዕግስት ተሟጠጠና ወደ አንድ የጥርስ ሃኪም ሄጄ ያንን ስቃይ ያበዛብኝንና የምሽቴን ፀጥታ ወደ ማቃሰት እና ማጓራት በመለወጥ እንቅልፍ የነሳኝን ጥርስ እንዲነቅልልኝ ነገርኩት ።

📖📖📖

የጥርስ ሃኪሙ ራሱን ከግራ ቀኝ እየወዘወዘ " ጥርሱን ማዳን ስንችል መንቀሉ ቂልነት ነው " አለኝ ። ከዚያም ጎንና ጎኖቹን በስቶ ቀዳዳዎቹን በማፅዳት ወደ ቀድሞ ሁኔታው ሊመልሰው እና ከብስባሴው ሐራ ሊያወጣው ያለውን መንገድ ሁሉ ተጠቀመ ። መብሳቱን ከጨረሰ በኋላ በንፁህ ወርቅ ሞላውና " የበሰበሰው ጥርስህ አሁን ከጤነኞቹ የበለጠ ጠንካራና ብርቱ ነው " አለኝ በኩራት ። አመንኩት ። ከፈልኩትና ስፍራውን ለቅቄ ሄድኩ ።

📖📖📖

ነገር ግን ገና ሳምንቱ ሳይገባደድ የተቀሰፈው ጥርስ ወደ ህመሙ ተመለሰና የነፍሴን ጥዑም ዜማ ወደ ለቅሶና ስቃይ ለወጠብኝ ። እናም ወደ ሌላ የጥርስ ሃኪም አመራሁና
" ምንም ጥያቄ ሳይጠይቀኝ ይህንን ጥርስ አውጥተህ ጣልልኝ ። የደረሰበትና ያልደረሰበት ግልግልን እኩል አያውቃትም! " አልኩት ።

ትዕዛዜን በማክበር ጥርሴን ነቀለልኝ ። ከዚያም ጥርሴን እያየ " ይህ ጥርስ እንዲነቀል በማድረግህ መልካም አድርገሃል " አለ ።

📖📖📖

በአፍ ማህበረሰብ ውስጥ እስከ መንጋጋ አጥንት ድረስ የበሰበሱ ብዙ በሽተኛ ጥርሶች አሉ ። ይሁንና ማህበረሰቡ እነዚህን የተበላሹ ጥርሶች ለማስነቀልና ከስቃዩ ለመገላገል ምንም ጥረት አያደርግም ። ራሱንም በወርቅ ፍቅፋቂ ይሞላል ። አብዛኞቹ የበሰበሱትን የማህበረሰብ ጥርሶች በሚያብለጨልጭ ወርቅ እንደሚያክሙ የጥርስ ሃኪሞች ናቸው ።

እንደዚህ ተጠጋግነው በመደለል የሚኖሩ ብዙዎች ናቸው ስቃይ ህመምና ሞት ዕጣ-ፈንታቸው ናቸው ።

📖📖📖

....ሃገር አፍ ውስጥ ብዙ የበሰበሱ እና ቆሻሻ ፣ ያመረቀዙና የሚሸቱ ጥርሶች አሉ ። ሃኪሞቹ ከመንቀል ይልቅ በወርቅ ፍቅፋቂ አክመዋቸዋል ። ህመሙ ግን እንዳለ ነው ።

የበሰበሰ ጥርስ ያለው ሃገር የታመመ ጨጓራ እንደሚኖረው እርግጥ ነው ። በዚህ ያለመፈጨት ችግር ውስጥ የሚገኙ ብዙ ሃገራት አሉ ።

...ሃገር ዳቦውን በበሰበሰ ጥርሱ እንደሚያኝክ እና አንዳንዱም ጉርሻ ከተመረዘ ምራቅ ጋር በመዋሃድ በሽታውን በሃገሩ ጨጓራ ውስጥ እንደሚያሰራጭ ስትነግሯቸው " አዎ ግን የተሻሉ የጥርስ ሙሌቶች እና ማደንዘዣዎች እየፈለግን ነው " ይሏችኋል ....

📖📖📖

ምንጭ 👉 " የጥበብ መንገድ " መጽሐፍ ከገጽ 16 - 18 ካለው የተቀነጨበ
ደራሲ 👉 ካህሊል ጂብራን
፨ ገበያ ላይ ከተገኘ ልታልፉት የማይገባ ቆንጆ መጽሐፍ ነው " የጥበብ መንገድ " ፩ እንዲሁም ፪

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
እኔም ልቀቁዋቸው፤ኧረ የፍትህ ያለህ እላለሁ፡፡ የዝምታው መጠን ረዘመ፡፡ የታሰሩበት
ጊዜም፣ እየተደረገባቸው ያለው የመብት ጥሰትም ተገቢ አይደለም፡፡ የታሰሩበት ምክንያትም
አጥጋቢ አይደለም፡፡ አጥፊ ሆነው ከተገኙም የይቅርታው መንፈስ ይህን ያህል ሊርቃቸው
አይገባም፡፡ ይቅርታ ለማን እንደሚገባው፣ ለማንስ መነፈግ እንዳለበት የተምታታብን
ይመስላል፡፡ የከተማው አስተዳደር መጀመርያ በየትምህርት ቤቱ ዙርያ በየጊዜው
ቁጥራቸው እየጨመረ ያሉትን የተከፈቱ ጫት ቤቶችና ሺሻ ማጨሻ መደብሮች ላይ
ጡንቻውን ያሳይ፡፡
አዲስ አበባ የሚታመሙላት እንጂ ተጨማሪ ሕመም የሚሆኑባት ከተማ አይደለችም፡፡
ለአዲስ አበቤዎች አለጊዜው ፈተና መስጠት ተጨማሪ ጠበሳ ማሳደርና የሚያመረቅዝ
ቁስል ማሳረፍ እንጂ ፈጽሞ ለለውጥ አያነሳሳም፡፡

((( እንዳለጌታ ከበደ )))

@balmbaras
@wegoch
@wegoch
ማክሰኞን በሳቅና በሳቅ ልናሸንፋት ተነስተናል!!!!!!!


ቀኑ ለሰው ተሰራ እንጅ ሰው ለቀኑ አልተሰራም!!!!!!! እናም
ቀኑ የእኛ ቀን ይሆን ዘንድ ግድ ይለዋል!!!!!!
ሰው በልቡ እንዳሰበ እንደዚያው ይሆናልና ሳቅ በሳቅ
በሆነው ሃሳባችን ቀኑን ወደ ሳቅ ጅረት ለመለወጥ
ቆርጠን ተነስተናል!!!!!!
እናም ልክ እንደነዚህ ሸጋ ልጆች
ፍልቅልቅ ፣💚
ድምቅምቅ፣💛
ፍክትክት፣❤️
ሽብርቅርቅ፣💚💛❤️
ፍንድቅድቅ፣ ያለ ሳምንት አንድዬ ይሰጠን ዘንድ ማን

ከልካይ አለው???? ማንም!!!!!!!!!!

@balmbaras
@wegoch
@wegoch

👇👇👇👇 ከዚህ በታች ሲነሽጠን በራሳችን ድምፅ የሙሉቀን መለሰን ሸጋ ሙዚቃ እንዲህ ዘፈነው💚💛❤️👇👇
2024/09/29 19:25:17
Back to Top
HTML Embed Code: