Telegram Web Link
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#ለአርሶ_አደሩ_እንድረስለት !

በወረባቦ ወረዳ ውስጥ የተከተሰው የአንበጣ መንጋ አርሶ አደሩ ደክሞ ለፍቶ ያፈራውን ሰብል ወደ ጎተራው ሳያስገባ አንበጣ መንጋው እያወደበት ይገኛል።

ይህንን የሰብል ጉዳትም ለመቀነስ በሰው ሃይል የኬሚካል ርጭት ፣ በባህላዊ መንገድ የመባረር እና በሂሊኮፍተር ኬሚካል ርጭት ቢደረግም የአንበጣ መንጋውን መቆጣጠር አልተቻለም።

በመሆኑም የሲቪክ ማህበራት የመንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና ባለሀብቶች በአንበጣ መንጋው ሰብላቸው የወደመባቸው አርሶ አደሮች እንዲደግፉ የወረባቦ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሳዳም ሽመልስ ጠይቀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
"በትግራይ ክልል ለሚገኙ ተማሪዎች 2.8 ሚሊዮን ማስክ ይከፋፈላል" - ትምህርት ሚኒስቴር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ

የትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል (Face Mask) ስርጭትን በተመለከተ ክልሎች ለተማሪዎቻቸው ተረክበው እንዲያሰራጩ የሚገልጽ እና ድልድሉንም አስመልክቶ የጊዜ እና የመጠን ዝርዝር ያለው ደብዳቤ ለክልል ትምህርት ቢሮዎች ጽፏል፡፡

በዚህ ደብዳቤ ውስጥ የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ አልተካተተም፡፡ ይህም በበርካቶች ዘንድ ጥያቄ ፈጥሯል፡፡

ጉዳዩን በተመለከተ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ጠይቀን ተከታዩ መረጃ ተሰጥቶናል ፦

- የተደረገው ድልድል የትግራይ ክልል ተማሪዎችን ጭምር የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ እንዲያገኙ ተደርጎ የተሰራ ነው፡፡

- በደብዳቤው ላይ ማካተት ያልተቻለው የፌዴሬሽን ምክር ቤት በቅርቡ ባሳለፈው ውሳኔ ምክንያት ነው፡፡

- አሁን ላይ በመላ ሀገሪቱ ላሉ 26 ሚሊዮን ተማሪዎች የማስክ አቅርቦት እንዲሟላ እየተሰራ ይገኛል፡፡

- ለትግራይ ክልል ለሚገኙ ተማሪዎችም ይህንን ሥርጭት ለማድረስ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከወረዳዎች እና ከዞኖች ጋር ግንኙነት ጀምሯል፡፡ ሥርጭቱም በዚያው በኩል የሚካሄድ ይሆናል፡፡

- አጠቃላይ ወደ 50 ሚሊዮን ማስክ በዝግጅት ላይ ነው፡፡ ከዚህም ውስጥ 2.8 ሚሊዮን የሚሆነው በትግራይ ክልል ለሚገኙ ተማሪዎች የሚከፋፈል ይሆናል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ጥቅምት 1/2013 ዓ/ም

የኢትዮጵያ ኮቪድ-19 መረጃዎች ፦

#Somali

በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 142 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 7 ሰዎች በኮቪድ19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 104 የላብራቶሪ ምርመራ ተራደርጎ 39 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Amhara

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 1,154 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 99 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። ከ99ኙ መካከል 64 ከምዕ/ጎጃም ዞን ፣ 16 ከባህር ዳር ከተማ ይገኙበታል።

#DireDawa

በድሬዳዋ 142 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 47 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቷል።

#Tigray

በትግራይ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 468 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 19 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

#Oromia

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 471 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 169 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት 3,913 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 365 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። የ6 ሰዎች ህይወት አልፏል።

#Harari

በሐረሪ ባለፉት 24 ሰዓት 120 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 53 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል።

#SNNPRS

በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 645 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 50 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል።

#Sidama

በሲዳማ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 184 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 18 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል።

@tikvahethiopiaBOT
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#ATTENTION📣

በድሬዳዋ የተከሰተ አንበጣ መንጋ በ10 ሺህ ሄክታር ሰብል እና ግጦሽ ሳር ላይ ጉዳት ማድረሱን የአስተዳደሩ የግብርና ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ለኢዜአ አስታውቋል።

መነሻውን ከሶማሌ ላንድ ያደረገ የአንበጣ መንጋ ከመስከረም 21 ቀን 2013 ዓም ጀምሮ ነው በድሬዳዋ በ22 ገጠር ቀበሌዎች የተከሰተው።

በ4 ሺህ ሄክታር ማሳ ላይ የሚገኝ የበቆሎና ማሽላ ሰብል ላይ ጉዳት አድርሷል፤ በተጨማሪ 6 ሺህ ሄክታር የግጦሽ ሳር ሙሉ ለሙሉ አውድሟል።

በተወሰኑ ቦታዎች ላይ በደረሰ የአተር ሰብል፣ በቲማቲምና ፍራፍሬ ተክሎች ላይ ጉዳት አድርሷል።

አንበጣ መንጋውን በባህላዊ መንገድ ጭስ በማጨስ እና ድምፅ በማሰማት እና በኬሚካል ርጭት ለመቆጣጠር ጥረት ቢደረግም ከአቅም በላይ መሆኑን ተነግሯል።

ከዚህ ቀደም አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ የኬሚካል መርጫ አውሮፕላኖች ጥገና ላይ መሆናቸው ችግሩን ያባባሰው መሆኑን ተገልጿል። (ENA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#አስቸኳይ_መልዕክት !

በሓፀቦ አከባቢ የአንበጣ መንጋ እየታየ ስለሆን በሰብል ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ቦታው በመገኘት የአርሶ አደሩ የመከላከል ስራ እንድትቀላቀሉ ተጠይቋል - (AXUM UNIVERSITY)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#COVID19Ethiopia

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 7,383 የላብራቶሪ ምርመራ 866 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ10 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 633 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 84,295 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 1,287 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 38,316 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#UPDATE

በአርሜኒያ እና አዛርባጃን መካከል ተደርጎ የነበረው የተኩስ አቁም ስምምነት ከአንድ ቀን በላይ መዝለቅ አልቻለም።

አዛርባጃን በዛሬው ዕለት እንዳስታወቀችው የተኩስ አቁም ስምምነት ከተደረሰ ከአንድ ቀን በኋላ ለዛሬ እሁድ አጥቢያ የአርሜኒያ ኃይሎች በሰነዘሩት ጥቃት 7 ሰዎች ተገድለዋል።

ጥቃቱ የተሰነዘረው በአዛርባጃንዋ የጋንጃ ከተማ የመኖርያ መንደሮች ላይ ነው ተብሏል።

በጥቃቱ ከተገደሉት ውጭ ህጻናትን ጨምሮ ሌሎች 33 ሰዎች መቁሰላቸውን የአዛርባጃን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በትዊተር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።

ነገር ግን የአርሜኒያ ኃይሎች ውንጀላውን አጣጥለው ይልቁኑ የተኩስ አቁም ስምምነቱን በመጣስ የአዛርባጃን ኃይሎችን ተጠያቂ ማድረጋቸው የፈረንሳይ ዜና ምንጭ ዘግቧል።

በሩስያ አደራዳሪነት በሁለቱ ሀገራት መካከል ተደርጎ የነበረው የተኩስ አቁም ስምምነት ለሁለት ሳምንት የሚቆይ እንደነበር የፈረንሳይ ዜና ምንጭ ዘገባ ያመለክታል። (DW)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
የቀወት ወረዳ ወጣቶች እና የአማራ ክልል ልዩ ኃይሎች የአንበጣ መንጋ መከላከል ስራ በውድቅት ጨለማ እየተጋፈጡት ይገኛሉ።

በአሁኑ ሰዓት ከፍተኛ የአንበጣ መንጋ በቀበሌዎች በመስፈሩና እያደረሰ ያለው የሰብል ውድመት ከፍተኛ በመሆኑ ለነገ ተብሎ የሚታለፍ ባለመሆኑ በባህላዊ ዘዴ የኬሚካል ርጭት ስራ እየተሰራ ይገኛል።

አንበጣ መንጋው በተከሰተባቸው አካባቢዎች የሚገኙ የፀጥታ አካላት የአንበጣ መንጋውን የመከላከል ስራን እየሰሩ ይገኛሉ።

ምንጭ፦ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
በጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ግብዣ ፕሬዜዳንት ኢሳያስ ዛሬ ኢትዮጵያ ይገባሉ !

የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለሶስት ቀን የስራ ጉብኝት ዛሬ ኢትዮጵያ ይገባሉ።

በጉብኝቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ኡስማን ሳሌህና የፕሬዜዳንቱ አማካሪያ የማነ ገብረአብም ተካተዋል።

#YemanGMeskel
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#ZamZamBank

ዘምዘም ባንክ ለዓመታት ሲያደርግ የነበረው ዝግጅት አጠናቆ ዛሬ ጥቅምት 2 ቀን 2013 ዓ/ም በይፋ ሥራውን ሊጀምር እንደሆነ ሪፖርተር አስነብቧል።

ባንኩ በኢትዮጵያ 'ከወለድ ነፃ ባንክ' አገልግሎት በመስኮት ደረጃ እንዲሰጥ ምክንያት በመሆን የሚጠቀስ እና የመጀመርያው ከወለድ ነፃ ባንክ ለመሆን ሲንቀሳቀስ የቆየ ባንክ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#UPDATE

ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጅማ ገቡ!

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጅማ ሲደርሱ በዚያው የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አቀባበል እንዳደረጉላቸው etv ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ኮሮና ቫይረስ የገንዘብ ኖቶች ላይ ፣ የስልክ ስክሪኖች ላይ እና በማይዝጉ ብረቶች ላይ ለ28 ቀናት ሳይሞት ቆይቶ በሽታ ሊያስተላለፍ እንደሚችል ተመራማሪዎች ይፋ አደረጉ።

የአውስትራሊያ ብሔራዊ ሳይንስ ኤጀንሲ ይፋ ያደረገው ጥናት ሳርስ-ኮቭ-2 የሚል ሳይሳዊ መጠሪያ ያለው ኮሮናቫይረስ ከተገመተው በላይ ለረዥም ጊዜ በቁሶች ላይ እንደሚኖር ያረጋገጠ ነው።

ኮሮናቫይረስ በብዛት የሚተላለፈው ሰዎች ሲያስሉ ፣ ሲያስነጥሱ ወይም ሲነጋገሩ እንደሆነ ይታወቃል። ይሁን እንጂ ይህ አዲሱ የተመራማሪዎች ግኝት ቫይረሱ ከቁሶች ወደ ሰዎች የሚተላለፍበት መጠንም ከተገመተው በላይ ሊሆን ይችላል ተብሏል።

ምንጭ፦ BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ የሰዎች ህይወት አለፈ!

በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ ዱሃዝባጉና ቀበሌ መነሻው የሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ።

የክልሉ መንግስት ፤ ለሰዎች ሞት መንስኤ የሆነው የግለሰቦች ግጭት ነው ብሏል።

በዱሃዝባጉና ቀበሌ አንድ ግለሰብ የሠው መሳሪያ ለመንጠቅ ሙከራ ባደረገበት ወቅት ፣ ባለ መሳሪያው ራሱን ለመከላከል ባደረገው ጥረት መሳሪያ ሊነጥቀው የመጣውን በስለት መሳሪያ የመቁሰል ጉዳት አድርሶበታል ተብሏል።

ይህን ተከትሎ ጉዳት የደረሰበት ግለሰብ ቤተሰብ በበቀል ስሜት ተነሳስተው ባደረሱት ጥቃት የንጹኃን ዜጎች ሕይወት እንዳለፈ ተገልጿል።

የክልሉ መንግስት ምን ያህል ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ አልገለፀም።

ጥቃት አድራሾቹ ግለሰቦች በቁጥጥር የዋሉ ሲሆን ፣ የክልሉ እና የፌዴራል የጸጥታ አካላት ችግሩ እንዳይሠፋ ለማድረግ በጋራ እየሠሩ ናቸው ተብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
2024/09/22 14:26:59
Back to Top
HTML Embed Code: