#HaramayaUniversity

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በአካባቢ ሳይንስ የዶክትሬት ዲግሪ ፕሮግራም ሊጀምር ነው።

የዩኒቨርሲቲው ግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ በአካባቢ ሳይንስ የሦስተኛ ዲግሪ ፕሮግራም መስጠት ለመጀመር የውስጥ ስርዓተ ትምህርት ግምገማ አካሒዷል።

የፕሮግራሙ መጀመሩ፥ ከፍተኛ የምርምር ክህሎት ያላቸውን ምሁራን በማፍራት አንገብጋቢ የአካባቢ፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የብዝሀ ህይወት እና ዘላቂ የሀብት አያያዝ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል መሆኑን የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ፕሮግራሞች ዳይሬክተር መሰረት አምዴ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ኮሌጁ አስፈላጊውን ሒደት በመከተል በግምገማው ወቅት የተሰጡ አስተያየቶችን በማካተት ፕሮግራሙን ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
#ExitExamCertificate

ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ያላለፉ ተማሪዎች የምስክር ወረቀት ቅፅ አዘጋጅቶ ለሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ልኳል።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ብሔራዊ የቅድመ-ምረቃ የመውጫ ፈተና ከሰኔ 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እየተደረገ እንደሚገኝ ይታወቃል።

በቅድመ-ምረቃ መውጫ ፈተናው የአፈጻጸም መመሪያ መሰረት፥ የመውጫ ፈተና ውጤት በተማሪዎች ሰርተፍኬት (Temporary Degree) ወይም ትራንስክሪፕት ላይ አልፏል (PASS) ወይም ወድቋል (FAIL) በሚል እንዲቀመጥ ሚኒስቴሩ አዟል።

በዚህም የመውጫ ፈተና ያላለፉ ተማሪዎች የሚሰጡ ኮርሶችን ማጠናቀቃቸውን የሚያረጋገጥ ሰርተፊኬት የሚሰጣቸው ሲሆን፤ ጊዜያዊ ዲግሪ የሚሰጠው ተፈታኙ/ተፈታኟ የመውጫ ፈተናውን በድጋሚ ወስዶ/ወስዳ የማለፊያ ነጥብ ሲያስመዘግብ/ስታስመዘግብ ብቻ እንደሚሆን በሰርተፊኬቱ ይገለጻል።

(የትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ እና የመውጫ ፈተና የውጤት ሰርተፍኬት ፎርማት ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ህሕክምና ኮሌጅ በተለያዩ የጤና መስኮች ያሰለጠናቸውን 312 ተማሪዎች አስመርቋል።

ተመራቂዎቹ በህሕክምና ቅድመ-ምርቃ፣ በስፔሻሊቲ እና በሰብ-ስፔሻሊቲ ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

@tikvahuniversity
መንትዮቹ ተመራቂዎች!

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌንየም ሕክምና ኮሌጅ ዛሬ ካስመረቃቸው 312 ተማሪዎች መካከል መንትዮቹ ዶክተሮች ይገኙበታል።

ዶ/ር ኃይማኖት ወልደሩፋኤል እና ዶ/ር ረድኤት ወልደሩፋኤል 🎓 👏

@tikvahuniversity
27ኛ ዙር ሙሉ የሒሳብ መዝገብ አያያዝ (Modern Accountancy) ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን። 

👉 ተግባርን ከንድፈ ሀሳብ ያስተሳሰረ ስልጠና
👉 መሠረታዊ አካውንቲንግ እና ኦዲት አሰራር፣ ሙሉ የአካውንቲንግ ሒሳብ አሰራር በፒስቺሪ ተደግፎ እና የግብር አያያዝ ትምህርቶችን አካቶ የሚሰጥ
👉 የሥራ ላይ ስልጠና (Internship) የተመቻቸለት

☎️   0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1:
ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Telegram: https://www.tg-me.com/sagetraininginstitute
TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
#Residency_GAT_Registration

በ2017 ዓ.ም በጤና ሚኒስቴር ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የተመደባችሁ የሕክምና ስፔሻሊቲ ሬዚደንሲ አመልካቾች የትምህርት ማስጀመሪያ የገለጻ ፕሮግራም ረቡዕ ሚያዝያ 1/2017 ዓ.ም ይሰጣል።

ገለጻው በዩኒቨርሲቲው ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አዳራሽ አስተዳደር ሕንጻ አንደኛ ፎቅ፣ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሚያዝያ 1/2017 ዓ.ም ጠዋት 3፡00 ይሰጣል።

አመልካቾች ዩኒቨርሲቲው የሚሰጠውን የድኅረ-ምረቃ ፈተና (GAT) ለመውሰድ መመዘገብ ይኖርባችኋል።

ለ'GAT' ይመዝገቡ፦

https://Portal.aau.edu.et ይግቡ።

➫ Exam Application የሚለውን ይጫኑ።

➫ Test Taker Registration የሚለውን ቅፅ ይሙሉ።

➫ የፓስፖርት መጠን ፎቶ ያለው ፎቶ ያስገቡ።

➫ Submit የሚለውን ይጫኑ።

➫ ሲስተሙ የሚሰጠዎን መለያ ቁጥር ይያዙ።

➫ ቴሌብር በመጠቀም የምዝገባ ክፍያ 750 ብር ይክፈሉ።

➫ አድሚሽን ቲኬትዎን በማውረድ ፕሪንት ብለው ይያዙ።

የ'GAT' ፈተና ከሚያዝያ 6-10/2017 ዓ.ም ይሰጣል።

@tikvahuniversity
🔥 Code. Compete. Conquer!
Safaricom Talent Cloud Capstone Challenge!
🔥

Ready to push your limits? Safaricom Talent Cloud brings to you the Capstone Project. If you are in Addis Ababa, team up and turn your idea into an MVP in just 6 weeks.

💰 Win BIG! 💰
🥇 Grand Prize: ETB 140,000
🥈 Second Place: ETB 85,000
🥉 Third Place: ETB 50,000

🔔 Are you are skilled in one of the following?

● Mobile (Kotlin/Flutter)
● Frontend (React)
● Backend (Java/Node.js)
● Fullstack
● DevOps
● UX/UI
● Product Ownership/Scrum Master

Form Your Dream Team! 🤝
● Assemble your 4–6-member squad and let one person apply, registering everyone.
● Note: All applicants must complete the TestGorilla assessment which will be sent through email!
Guided by expert advisors, you will collaborate, innovate, and compete for the prize.

Apply Here

Deadline: April 09, 2025
#Update

የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና (EHPLE) ከሚያዝያ 1-3/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል።

እያንዳንዱ ተፈታኝ 200 ጥያቄዎች ይቀርቡለታል፦ 100 ጥያቄዎች በጠዋት መርሐግብር እና 100 ጥያቄዎች በከሰዓት መርሐግብር፡፡

ተፈታኞች ፈተና ማዕከል እንዲደርሱ የሚጠበቀው ጠዋት 1፡30 እና ከሰዓት 7፡00 ላይ መሆኑ ተገልጿል፡፡

(የፈተና መርሐግብር፣ የጊዜ ሰሌዳ፣ የሚያስፈልጉ ሰነዶች እንዲሁም ወደ ፈተና ማዕከል ይዞ መምጣት የተከለከሉ ነገሮች እና ሌሎች መረጃዎች ከላይ ተያይዘዋል፡፡)

ለተጨማሪ መረጃ፦
952 ወይም 0115186275 / 0115186276

@tikvahuniversity
#AmboUniversity

በ2017 ዓ.ም አምቦ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ሬዚደንት ሐኪሞች ምዝገባ ሚያዝያ 5 እና 6/2017 ዓ.ም እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ሙሉ የትምህርት ማስረጃ፣ የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ፣ የቀድሞ የሥራ ተቋም መልቀቂያ እና ጉርድ ፎቶግራፍ ስካን በማድረግ በዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር ፖርታል estudent.ambou.edu.et ላይ መጫን ይጠበቅባችኋል፡፡

ትምህርት ከመጀመሩ በፊት ኦፊሽያል ትራንስክሪፕት ለአምቦ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት በፖ.ሳ.ቁ. 240 ማስላክ ይጠበቅባችኋል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ የትምህርት ማስረጃችሁን ዋናውንና የማይመለስ አንድ ኮፒ መያዝ ያስፈልጋል፡፡

@tikvahuniversity
#WachemoUniversity

በ2017 ዓ.ም ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ሬዚደንት ሐኪሞች ምዝገባ የሚካሄደው ሚያዝያ 1 እና 2/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ ሰነዶች፦

➫ የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ (በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ስፖንሰር ለተደረጋችሁ)፣
➫ ከ8-12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት እና ከ9-10ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት፣
➫ የመልቀቂያ ደብዳቤ ይሰሩበት ከነበረው ተቋም፣
➫ ሁለት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ
➫ የመጀመሪያ ዲግሪ ኦፊሽያል ትራንስክሪፕት ለዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በፖ.ሳ.ቁ. 667 እንዲሁም በኢሜል [email protected] ማስላክ ይኖርባችኋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦ ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ሕንጻ ቁ. 144

@tikvahuniversity
#Update

ከሚያዝያ 1-3/2017 ዓ.ም የሚሰጠውን የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ አመልካቾች፥ የፈተናው አሰጣጥ ቅድመ ገለጻ (Orientation) እና የሙከራ ፈተና (Mock Exam) ማክሰኞ መጋቢት 30/2017 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት የሚሰጥ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
2025/04/08 02:01:44
Back to Top
HTML Embed Code: