Telegram Web Link
አማድ ዲያሎ የደሞዝ ክፍያ ጭማሬ ያገኛል !

የማንችስተር ዩናይትዱ የፊት መስመር ተጨዋች አማድ ዲያሎ በክለቡ በሚፈራረመው አዲስ ውል ከፍተኛ የደሞዝ ጭማሬ እንደሚያገኝ ተገልጿል።

አማድ ዲያሎ በቅርቡ በማንችስተር ዩናይትድ ቤት የረጅም ጊዜ ኮንትራት ለመፈራረም ከስምምነት መድረሱ በአሰልጣኝ ሩበን አሞሪም መገለፁ አይዘነጋም።

ቀያዮቹ ሴጣኖች በቡድኑ አይነኬ ከሚሏቸው ጥቂት ተጨዋቾች መካከል አማድ ዲያሎ አንዱ መሆኑ ተገልጿል።

በተጨማሪም ፈረንሳዊው ተከላካይ ሌኒ ዮሮ ሌላኛው በማንችስተር ዩናይትድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ተጨዋች መሆኑ ተነግሯል።

@tikvahethsport          @kidusyoftahe
#EthPL 🇪🇹

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አስራ ሶስተኛ ሳምንት መርሐግብር ኢትዮጵያ ቡና ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ድሬዳዋ ከተማ ያለፉትን ሶስት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም በአቻ ውጤት ተለያይተዋል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

4️⃣ ድሬዳዋ ከተማ :- 18 ነጥብ
6️⃣ ኢትዮጵያ ቡና :- 16 ነጥብ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
“ ኳሷ ከሊጉ የተለየች ነበረች “ አርቴታ “ እንደምናልፍ ሙሉ እምነት አለኝ “ የመድፈኞቹ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቡድናቸው ትላንት ቢሸነፍም ኒውካስል ዩናይትድን በሜዳው አሸንፎ ለፍፃሜ መድረስ እንደሚችል ገልጸዋል። አሰልጣኙ አክለውም ቡድኑ በካራባኦ ካፕ ጥቅም ላይ እየዋለች የምትገኘውን ኳስ በደንብ መላመድ እንዳለበት አሳስበዋል። ሚኬል አርቴታ በንግግራቸውም “ ኒውካስልን በሜዳው…
“ ከዚህ በፊት ስለ ኳሱ የተሰጠ አስተያየት የለም “

የእንግሊዝ ፉትቦል ሊግ ቃል አቀባይ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የካራባኦ ካፕ መጫወቻ ኳስ ላይ የሰጡት አስተያየት የመጀመሪያ መሆኑን ገልጸዋል።

አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የካራባኦ ካፕ ኳስ ለጨዋታ አስቸጋሪ እንደሆነ ከትላንት ምሽቱ ሽንፈት በኋላ ገልፀው ነበር።

አወዳዳሪው አካል በበኩሉ ኳሱን ከካራባኦ ካፕ በተጨማሪ ሌሎች ታላላቅ የአውሮፓ ሊጎች በስኬት እየተገለገሉበት ነው ብሏል።

“ ሴርያ እና ላሊጋም ኳሱን ይጠቀማሉ “ ያሉት የ " EFL" ቃል አቀባይ በተጨማሪም በእንግሊዝ የታችኛው ሊግ ውድድሮች ጥቅም ላይ እየዋለ ነው ብለዋል።

ቃል አቀባዩ አክለውም “ ሁሉም በዚህ አመት የተጫወቱት ክለቦች በተመሳሳይ ኳስ ነው ከአርቴታ በፊት የቀረበ ቅሬታ የለም “ ሲሉ ተደምጠዋል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ሲቲ ተጨዋቾች ለማስፈረም እየሰሩ ነው !

ማንችስተር ሲቲ የኢንትራክት ፍራንክፈርቱን የፊት መስመር ተጨዋች ኦማር ማራሙሽ ለማስፈረም በመስራት ላይ መሆናቸውን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።

ማንችስተር ሲቲ ለግብፃዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኦማር ማራሙሽ የአራት አመት ውል ማቅረባቸው ተገልጿል።

ማንችስተር ሲቲ በተጨማሪም የሌንሱን የመሐል ተከላካይ አብዱኮድር ኩሳኖቭን ለማስፈረም ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸው ተነግሯል።

በአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የሚመራው ማንችስተር ሲቲ በዚህ ወር ሁለቱንም ተጨዋቾች ወደ ቡድኑ ለመቀላቀል ከፍተኛ ጥረት ላይ መሆኑ ተዘግቧል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

5:00 ቶተንሀም ከ ሊቨርፑል

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
እረፍት

ቶተንሀም 0 - 0 ሊቨርፑል

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ባርሴሎና ለፍፃሜ ደርሰዋል !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ከአትሌቲክ ቢልባኦ ጋር ያደረገውን የስፔን ሱፐር ካፕ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የባርሴሎናን የማሸነፊያ ግቦች ጋቪ እና ላሚን ያማል ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ባርሴሎና ማሸነፉን ተከትሎ የስፔን ሱፐር ካፕ ፍፃሜ ተፋላሚ መሆኑን ማረጋገጥ ችሏል።

ባርሴሎና በፍፃሜው የሪያል ማድሪድ እና ማዮርካን አሸናፊ የሚገጥሙ ይሆናል።

ባርሴሎና በተከታታይ ሶስት አመታት ለስፔን ሱፐር ካፕ ፍፃሜ ደርሰዋል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
86 '

ቶተንሀም 1 - 0 ሊቨርፑል

ቤርግቫል

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
90 '

ቶተንሀም 1 - 0 ሊቨርፑል

ቤርግቫል

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ሊቨርፑል ሽንፈት አስተናግዷል !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑሉ ከቶተንሀም ጋር ያደረገውን የካራባኦ ካፕ ግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

የቶተንሀምን የማሸነፊያ ግብ ሉካስ ቤርግቫል ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ስዊድናዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሉካስ ቤርግቫል የቶተንሀም የመጀመሪያውን ግብ አስቆጥሯል።

ከአራት ወራት በኋላ ሽንፈት የገጠማቸው ሊቨርፑሎች በውድድር ዘመኑ ሁለተኛ ሽንፈታቸው ሆኖ ተመዝግቧል።

ሁለቱ ቡድኖች የካራባኦ ካፕ ግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታቸውን ከአንድ ወር በኋላ በሊቨርፑሉ አንፊልድ ስታዲየም የሚያደርጉ ይሆናል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
ታላቅ የገና ስጦታ እስከ ጥር 4 የሚቆይ ቅናሽ

Exchange Available (ባሎት PlayStation ላይ  ጨምረው መቀየር ይችላሉ)

FC24  ,  FC25    CIDI GAME

FC25 NEW PACKED =8,000
FC24 NEW PACKED =4,200

አድራሻ፦
ቁጥር 1  መገናኛ ሱቅ የአድራሻ ለውጥ በቅርቡ ስለምናደርግ ከመምጣቶ በፊት አስቀድመው ይደውሉ
   
ቁጥር 2   ቦሌ Celavi burger አጠገብ ዘንባባ ህንፃ  ምድር ላይ


ስልክ፦ 0910529770 ወይም                  0977349492
0914646972  ይደውሉ
Telegram channel ፦
https://www.tg-me.com/CanPlaystation

                       👍Update Your Life
" የመልስ ጨዋታውን በጉጉት እንጠብቃለን " ቫን ዳይክ

የሊቨርፑሉ አምበል ቨርጅል ቫን ዳይክ በምሽቱ ጨዋታ ዳኛው ስህተት መስራታቸውን በሰጠው አስተያየት ገልጿል።

“ ሉካስ ቤርግቫል በቀይ ካርድ መውጣት ዳኛው ስህተት ሰርቷል ነገርግን ስህተቱን ሊያምን አልቻለም “ ሲል ቫን ዳይክ ተናግሯል።

ቫን ዳይክ አክሎም “ ጨዋታውን የተሸነፍነው በዚህ ምክንያት ነው ማለት አልፈልግም ነገርግን በቀይ መውጣት ነበረበት “ ብሏል።

“ ገና የመጀመሪያ ዙር ነው ቀሪ ዘጠና ደቂቃ አለ የመለስ ጨዋታውን በአንፊልድ ለማድረግ በጉጉት እንጠብቃለን “ ቫን ዳይክ

@tikvahethsport @kidusyoftahe
“ የዳኝነት ህጉ ለቶተንሀም አግዟል “ አርኔ ስሎት

የሊቨርፑሉ ዋና አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ቡድናቸው ትላንት ምሽት በተሸነፈበት ጨዋታ በነበረው ዳኝነት ደስተኛ እንዳልነበሩ ገልጸዋል።

“ ዳኛው በጨዋታው ጎል ለምን እንደተሻረ ለህዝብ ከሚናገር ይልቅ ሁለተኛ ቢጫ ለምን እንዳልመዘዘ ቢናገር ጥሩ ነበር “ ሲሉ አርኔ ስሎት ተናግረዋል።

አርኔ ስሎት አክለውም “ እሁድ ቶተንሀም ከኒውካስል ሲጫወት ዳኝነቱ ከእነሱ በተቃራኒ ነበር ዛሬ ከእነሱ ጎን ሆኖ ነበር " ብለዋል።

የቶተንሀም አሰልጣኝ አንሄ ፖስቴኮግሉ በበኩላቸው “ እነዚህ ህጎች ናቸው ወዳጄ “ ሲሉ አርኔ ስሎት ከተቆጠረው ግብ በኋላ ስላሳዩት ብስጭት ተናግረዋል።

ሉካስ ቤርግቫል በቀይ ባለመውጣቱ እድለኛ ነበር ወይ ተብለው የተጠየቁት አሰልጣኙ “ በፍጹም “ ያሉ ሲሆን ህግ ነው ምንም ማድረግ አይቻልም ብለዋል።

@tikvahethsport      @kidusyoftahe
ሮድሪጎ ቤንታንኩር በምን ሁኔታ ላይ ነው ?

ዩራጋዊው የቶተንሀም አማካይ ሮድሪጎ ቤንታንኩር ቡድናቸው ትላንት ሊቨርፑልን ባሸነፈበት ጨዋታ ከባድ የጭንቅላት ጉዳት አስተናግዶ ነበር።

ተጨዋቹ ጨዋታው በጀመረ ገና በ 15ኛው ደቂቃ ነበር ያጋጠመውን የጭንቅላት ጉዳት ተከትሎ ራሱን በመሳቱ ከሜዳ በእርዳታ ታግዞ የወጣው።

የ 27ዓመቱ ተጨዋች ቤንታንኩር ራሱን እንደሚያውቅ እና ሰዎችን እንደሚያነጋግር ክለቡ ቶተንሀም ስለ ሁኔታው በሰጠው አስተያየት አረጋግጧል።

ተጨዋቹ ለተጨማሪ የህክምና ምርመራዎች ወደ ሆስፒታል ማቅናቱን ክለቡ አያይዞ ገልጿል።

@tikvahethsport      @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ዌስትሀም አሰልጣኝ ለመሾም ተስማማ ! ዌስትሀም ዩናይትድ እንግሊዛዊውን አሰልጣኝ ግራም ፖተር በሀላፊነት ለመሾም ከስምምነት መድረሳቸውን ዘ አትሌቲክ አስነብቧል። ዌስትሀም ከደቂቃዎች በፊት ስፔናዊውን አሰልጣኝ ጁሊያን ሎፕቲጌ ከአሰልጣኝነት ማሰናበታቸውን በይፋ ማስታወቃቸው ይታወሳል። አሰልጣኝ ግራም ፖተር በዌስትሀም ዩናይትድ የሁለት አመት እና ግማሽ አመት ውል መፈረማቸው ተገልጿል። አሰልጣኝ…
ዌስትሀም ዩናይትድ በይፋ አሰልጣኝ ሾመ !

ስፔናዊውን አሰልጣኝ ጁሊያን ሎፕቲጌ ከሀላፊነት ያሰናበተው ዌስትሀም ዩናይትድ አዲስ አሰልጣኝ መሾማቸውን አስታውቀዋል።

ዌስትሀም ዩናይትድ እንግሊዛዊውን አሰልጣኝ ግራም ፖተር የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ አድርገው በሀላፊነት መሾማቸውን ይፋ አድርገዋል።

አሰልጣኝ ግራም ፖተር ዌስትሀም ዩናይትድን ለሚቀጥሉት ሁለት አመታት እና ግማሽ አመት ለማሰልጠን ፊርማቸውን ማኖራቸው ይፋ ሆኗል።

አሰልጣኝ ግራም ፖተር ዌስትሀም ዩናይትድ ነገ ምሽት ከአስቶን ቪላ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ስራቸውን እንደሚጀምሩ ተገልጿል።

@tikvahethsport    @kidusyoftahe
" በቼልሲ ምክንያት የተሻለ ሰው ሆኛለሁ " ግራም ፖተር

ዌስትሀም ዩናይትድን በሀላፊነት የተረከቡት አሰልጣኝ ግራም ፖተር ከሹመቱ በኋላ ከጋዜጠኞች ጋር የመጀመሪያ ቆይታቸውን አድርገዋል።

አሰልጣኙ በቆይታቸውም :-

- " በትክክለኛው ጊዜ ትክክለኛውን ነገር መምረጥ ነበረብኝ ክለቡን ካነጋገርኩ በኋላ ዌስትሀም ለእኔ ትክክለኛ ክለብ መሆኑን አውቄያለሁ።

- ከቼልሲ ጋር ከተለያየሁ በኋላ ሀያ ወራትን አሳልፌያለሁ በጣም ጥሩ የእረፍት ጊዜ ነበረኝ።

- ከቼልሲ ባገኘሁት ልምድ ምክንያት አሁን የተሻለ ሰው ሆኛለሁ ብዬ አስባለሁ።

- አጥቅቶ የሚጫወት እና ጥሩ እግርኳስ የሚጫወት ቡድን እንፈልጋለን ነገርግን ነገሮችን አመጣጥነን መጓዝም ያስፈልጋል።

- ትላንት ምሽት ከመደሰቴ የተነሳ ጥሩ እንቅልፍ አልተኛሁም ነበር።" ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport    @kidusyoftahe
ማድሪድ የተጫዋቹን ግልጋሎት አያገኝም !

ሪያል ማድሪድ ዛሬ ምሽት ከማዮርካ ጋር በሚያደርጉት  ጨዋታ የወሳኝ ተጨዋቻቸውን ግልጋሎት እንደማያገኙ ተገልጿል።

በጨዋታው ክሮሽያዊው አማካይ ሉካ ሞድሪች በኢንፌክሽን ህመም ምክንያት እንደማይሳተፍ ተነግሯል።

ሎስ ብላንኮዎቹ ዛሬ ምሽት 4:00 ከማዮርካ ጋር የስፔን ሱፐር ካፕ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል።

@tikvahethsport    @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ዎልቭስ ተጨዋች ለማስፈረም ተስማማ ! የፕርሚየር ሊጉ ክለብ ዎልቭስ የሬምሱን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ኢማኑኤል አግባዶ ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል። ዎልቭስ ተጫዋቹን በ 18 ሚልዮን ዩሮ ክፍያ እና ተጨማሪ ታይቶ የሚጨምር 2 ሚልዮን ዩሮ የዝውውር ሒሳብ ለማስፈረም ከስምምነት ደርሰዋል። የ 27አመቱ ኮትዲቯራዊ ተከላካይ ኢማኑኤል አግባዶ ዎልቭስን በአራት አመት ኮንትራት ለመቀላቀል…
ዎልቭስ ተጨዋች አስፈረመ !

የፕርሚየር ሊጉ ክለብ ዎልቭስ የሬምሱን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ኢማኑኤል አግባዶ ማስፈረማቸውን በይፋ አስታውቀዋል።

ዎልቭስ ተጫዋቹን በ 18 ሚልዮን ዩሮ ክፍያ እና ተጨማሪ ታይቶ የሚጨምር 2 ሚልዮን ዩሮ የዝውውር ሒሳብ አስፈርመዋል።

ፕሮፌሽናል እግርኳስን ከ 5️⃣ አመት በፊት በቱኒዚያ የጀመረው የ 27አመቱ ተከላካይ ኢማኑኤል አግባዶ ለዎልቭስ የአራት አመት ውል ፈርሟል።

ኮትዲቯራዊ ተከላካይ ኢማኑኤል አግባዶ በዎልቭስ የሚከፈለው ገንዘብ በሬምስ ከሚያገኘው በወር 75,000 ዩሮ ወደ 240,000 ከፍ እንደተደረገለት ተገልጿል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
አል ሂላል የኔይማርን ውል ማደስ አይፈልጉም !

የሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ሂላል የብራዚላዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ኔይማር ውል ማራዘም እንደማይፈልጉ ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።

ኔይማር በሚቀጥለው ክረምት በአል ሂላል ያለው የሁለት አመት ኮንትራት እንደሚጠናቀቅ ይታወቃል።

አሁን ላይ አል ሂላል ኔይማር በሚያጋጥሙት ተደጋጋሚ ጉዳቶች ምክንያት በቀጣይ ውሉን የማራዘም ፍላጎት እንደሌላቸው ተዘግቧል።

ኔይማር በቀጣይ ወደ ሀገሩ ብራዚል ይመለሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ እና በብራዚል የራሱን ትልቅ ክለብ እንደሚገዛ ተገልጿል።

ኔይማር ከሳውዲ አረቢያ ያገኘውን ከፍተኛ ሀብት ብራዚል ውስጥ የራሱን ክለብ ለመግዛት እንደሚጠቀመው ተነግሯል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
2025/01/10 12:37:01
Back to Top
HTML Embed Code: