Telegram Web Link
45 '

ሊቨርፑል 1-1 ሌስተር ሲቲ

ጋክፖ                 አንድሬ አዬው

@tikvahethsport       @kidusyoftahe
እረፍት

ሊቨርፑል 1-1 ሌስተር ሲቲ

ጋክፖ                 አንድሬ አዬው

@tikvahethsport       @kidusyoftahe
50'

ሊቨርፑል 2-1 ሌስተር ሲቲ

ጋክፖ                 አንድሬ አዬው
ጆነስ

@tikvahethsport       @kidusyoftahe
82 '

ሊቨርፑል 3-1 ሌስተር ሲቲ

ጋክፖ                 አንድሬ አዬው
ጆነስ
ሳላህ

@tikvahethsport       @kidusyoftahe
ሊቨርፑል መሪነቱን አጠናክሯል !

በአስራ ስምንተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሊቨርፑል ከሌስተር ሲቲ ጋር ያደርጉትን ጨዋታ 3ለ1 በሆነ ውጤት አሽንፈዋል።

የሊቨርፑልን የማሸነፊያ ግቦች መሐመድ ሳላህ ፣ ኮዲ ጋክፖ እና ከርትስ ጆንስ ማስቆጠር ሲችሉ ለሌስተር ሲቲ አንድሬ አየው ከመረብ አሳርፏል።

ግብፃዊው የሊቨርፑል ተጨዋች መሐመድ ሳላህ በውድድር ዘመኑ አስራ ስድስተኛ የሊግ ግቡን በማስቆጠር ኮከብ ግብ አግቢነቱን እየመራ ይገኛል።

መሐመድ ሳላህ በውድድር ዘመኑ በሊጉ 2️⃣7️⃣ የግብ ተሳትፎዎችን በማድረግ ቀዳሚው ተጨዋች ሆኗል።

ሊቨርፑል የፕርሚየር ሊጉን መሪነት ወደ ሰባት የነጥብ ልዩነት ከፍ ማድረግ ችለዋል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

1⃣ ሊቨርፑል - 42 ነጥብ
1️⃣8️⃣ ሌስተር ሲቲ - 14 ነጥብ 

ቀጣይ መርሐ ግብር ?

እሁድ - ዌስትሀም ዩናይትድ ከ ሊቨርፑል

አሁድ - ሌስተር ሲቲ ከ ማንችስተር ሲቲ

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዎች !

4:30 ብራይተን ከ ብሬንትፎርድ

5:15 አርሰናል ከ ኢፕስዊች ታውን

🔴 የዛሬው የይግምቱ ሽልማቶቻችን የአርሰናል ጨዋታ ነው።

🔴 የዛሬ ሽልማታችን 4:00 ላይ ወደ ቤተሰቦቻችን የሚደርስ ይሆናል።

🔴 መገመት የሚቻለው በተጠቀሰው ሰዓት ላይ ብቻ ነው።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
“ ፕርሚየር ሊጉን ማሸነፍ እፈልጋለሁ “ ሳላህ

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል የፊት መስመር ተጨዋች መሐመድ ሳላህ በዚህ አመት የፕርሚየር ሊጉን ዋንጫ ማሸነፍ እንደሚፈልጉ ተናግሯል።

“ በዚህ አመት በቡድኑ ውስጥ ያለው ስሜት የተለየ ነው ዋንጫውን እንድናሸንፍ እፈልጋለሁ አላማችን ዋንጫውን ማሳካት ነው።“ ሲል መሐመድ ሳላህ በአስተያየቱ ተናግሯል።

መሐመድ ሳላህ አክሎም ለደጋፊው “ መልካም የገና እና አዲስ አመት በዓል ይሁንላችሁ “ ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።

" የሊጉ ኮከብ ግብ አግቢ መሆን ያስደስታል ነገርግን ዋናው አስፈላጊ ነገር የቡድኑ ድል ነው ዋንጫውን እንደምናሸንፍ ተስፋ አለን።" ሳላህ

ግብፃዊው ተጨዋች መሐመድ ሳላህ በአንፊልድ ስታዲየም ባደረጋቸው 1️⃣4️⃣2️⃣ የሊግ ጨዋታዎች 1️⃣0️⃣0️⃣ኛ ግቡን ማስቆጠር ችሏል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
“ መሪ ብንሆንም የሊጉን ከባድነት እናውቃለን “ አርኔ ስሎት

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ዋና አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ቡድናቸው ትላንት ምሽት ያሳየው እንቅስቃሴ እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል።

“ አጠቃላይ በቡድን እንቅስቃሴ ደስተኞች ነን “ ያሉት አርኔ ስሎት “ በጨዋታው የተጫወትነው መጫወት በምንፈልገው መንገድ ነው “ ሲሉ ገልጸዋል።

አርኔ ስሎት አክለውም “ የሊጉ መሪ ነን እናውቃለን ነገርግን ፕርሚየር ሊግ ምን ያህል ከባድ እንደሆነም እናውቃለን “ ሲሉ ተናግረዋል።

“ ከሁለት ወራት በፊት ከማንችስተር ሲቲ ያለን የነጥብ ልዩነት አንድ ነበር አሁን አስራ አራት ሆኗል ይህ ጉዳት እና ቅጣት ካጋጠመ በሊጉ ምን እንደሚገጥም ያሳያል።“ አርኔ ስሎት

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
“ የሚገጥመን ፈተና ገና አልተጠናቀቀም “ አሞሪም

የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ቡድናቸው ችግር እንደሚገጥመው ቀድመው መናገራቸውን ገልጸዋል።

አሰልጣኙ በቅርቡ ኤቨርተንን 4ለ0 ካሸነፉ በኋላ በሰጡት አስተያየት “ ከባድ ችግር ከፊታችን እየመጣ ነው “ ብለው ተናግረው ነበር።

ከምሽቱ ሽንፈት በኋላ “ አስቸጋሪ ጊዜ እንደሚመጣ ቀድሜ ተናግሬያለሁ “ ያሉት ሩበን አሞሪም ይህም የመጨረሻው አይሆንም ፤ ጊዜ ያስፈልገናል “ ብለዋል።

ስለ ራሽፎርድ ከቡድኑ ውጪ መሆን የተጠየቁት አሰልጣኙ “ እያደረኩ ያለሁት ለክለቡ ጥሩ የሆነውን ነው አላቆምም “ ሲሉ መልሰዋል።

ዩናይትድ በቀጣይ እነማንን ያገኛል ?

ማንችስተር ዩናይትድ በቀጣይ

- ኒውካስል ዩናይትድ
- ሊቨርፑል እንዲሁም
- አርሰናል ( ኤፌ ካፕ ) በተከታታይ የሚገጥሙ ይሆናል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ማቲውስ ኩንሀ ወደ አርሰናል ?

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የብራዚላዊው የዎልቭስ የአጥቂ አማካይ ማቲውስ ኩንሀ የረጅም ጊዜ አድናቂ መሆናቸውን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።

መድፈኞቹ ተጨዋቹ በዚህ አመት እያሳየ የሚገኘው ጥሩ እንቅስቃሴ እንዳስደነቃቸው እና ሁኔታውን በመከታተል ላይ እንደሚገኙ ተነግሯል።

አርሰናል ተጨዋቹ ላይ ፍላጎት ያሳዩ እንጂ እስካሁን ለማስፈረም ቅድሚያ ከሚሰጧቸው ተጨዋቾች ዝርዝር ውስጥ እንዳላካተቱት ተነግሯል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
“ አንቶኒን ለማስፈረም ብዙ ክለቦች እየጠበቁ ነው “ ወኪሉ

የብራዚላዊው የማንችስተር ዩናይትድ የፊት መስመር ተጨዋች አንቶኒ ወኪል በርካታ ክለቦች አንቶኒን ለማስፈረም እየጠየቁ እንደሚገኙ ተናግሯል።

“ አንቶኒን በጥር ለማስፈረም በርካታ ክለቦች ጠይቀዋል “ ያለው ወኪሉ ክለቦቹ ለተጨዋቹን ሁኔታ ማወቅ ይፈልጋሉ ጠንካራ ፍላጎት ነው ያላቸው በማለት ተናግሯል።

ወኪሉ አክሎም ማንችስተር ዩናይትድ አንቶኒን የመሸጥ ወይም በውሰት የመስጠት ፍላጎት ይኑረው አይኑረው እንዳላሳወቃቸው ገልጿል።

ብራዚላዊው ተጨዋች አንቶኒ ከአመታት በፊት ማንችስተር ዩናይትድን በትልቅ የዝውውር ሒሳብ ቢቀላቀልም በሚገባው ልክ ቡድኑን እያገለገለ አይገኝም።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የላሊጋ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ? የስፔን ላሊጋ የ 2024/25 የውድድር ዘመን የወርሀ ታኅሣሥ የወሩ ምርጥ ተጨዋች አምስት እጩዎች ይፋ ተደርገዋል። በዚህም መሰረት :- ሳንድሮ ጁድ ቤሊንግሀም አንቷን ግሬዝማን ሳንሴት እና ራፊንሀ በእጩነት መቅረብ የቻሉ ተጨዋቾች ናቸው። @tikvahethsport     @kidusyoftahe
የላሊጋ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ታውቋል !

አስራ ዘጠነኛ ሳምንቱ ላይ የደረሰው የስፔን ላሊጋ የ 2024/25 የውድድር ዘመን የወርሀ ታኅሣሥ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ይፋ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት እንግሊዛዊው የሪያል ማድሪድ አማካይ ጁድ ቤሊንግሀም የላሊጋ የታኅሣሥ ወር ምርጥ ተጨዋች ተብሎ በአብላጫ ድምፅ መመረጥ ችሏል።

ጁድ ቤሊንግሀም በወሩ ባደረጋቸው የላሊጋ ጨዋታዎች አራት ጎሎችን አስቆጥሮ ሁለት አመቻችቶ አቀብሏል።

ቱርካዊው የሎስ ብላንኮዎቹ አማካይ አርዳ ጉለር በበኩሉ የ 23ዓመት በታች የላሊጋ የታኅሣሥ ወር ምርጥ ተጨዋች ሽልማት መቀበል ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኬንያ አሰልጣኝ ቤኒ ማካርቲን ልትሾም ነው !

የኬንያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞውን የማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ቡድን አባል አሰልጣኝ ቤኒ ማካርቲ በሀላፊነት ለመሾም መቃረቡ ተገልጿል።

ብሔራዊ ቡድኑ ከሳምንታት በፊት ከቱርካዊው አሰልጣኝ ኤንጂን ፊራት ጋር ከሶስት አመታት በኋላ ተለያይተዋል።

የሀራምቤ ኮከቦቹ አሁን ላይ ቤኒ ማካርቲን ዋና አሰልጣኝ አድርገው ለመሾም ከስምምነት መድረሳቸው ተነግሯል።

ደቡብ አፍሪካዊው አሰልጣኝ ቤኒ ማካርቲ የሀራምቤ ኮከቦቹን የሚረከቡ ከሆነ ለመጀመሪያ ጊዜ ብሔራዊ ቡድን በአሰልጣኝነት የሚመሩ ይሆናል።

አሰልጣኝ ቤኒ ማካርቲ የኬንያ ብሔራዊ ቡድንን በ 2025 መጀመሪያ ጀምሮ ማሰልጠን ይጀምራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተጠቁሟል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
የመድፈኞቹን ጨዋታ በነፃ በቻናል 223 SS Premier League በቀጥታ ይከታተሉ! እርሶ ብቻ ዲኮደርዎን ያብሩ ፤ በ ዲኤስቲቪ ፈታ ይበሉ!

ከታኅሣሥ 18 እስከ 20 ሁሉንም ቻናሎች፤ ሁሉንም መዝናኛዎች፤ ያለአንዳች ክፍያ ይዝናኑ!

ዲኮደርዎን ያብሩ!

#DStvEthiopia #ሁሉምያለውእኛጋርነው #በሽበሽበዲኤስቲቪ
የቤቲካ የገና ስጦታዎች
በየቀኑ የ1000 ነጻ በረራ የሚያስገኙ ቻሌንጆች እናንተን እየጠበቁ ነው።
ከዚህ የተሻለ የበዓል ስጦታ የትም አይገኝም! በቤቲካ ብቻ!
ሁሉንም በአንድ ላይ በቤቲካ ያገኛሉ። ታዲያ ምን ይጠብቃሉ?
ይወራረዱ፣በትልቁ ያሸንፉ ፣ከስጦታ እና ጉርሻዎቹ የድርሻዎን ይውሰዱ።
ቤቲካ - የአሸናፊዎች ቤት
ዳኒ ኦልሞ ባርሴሎናን በነፃ ሊለቅ ይችላል !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ስፔናዊውን አማካይ ዳኒ ኦልሞ ለቀሪው የውድድር አመት በላሊጋው ለማስመዝገብ ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት እንዳላገኘ ተገልጿል።

ባርሴሎና ካለበት የፋይናንስ ችግር ጋር በተያያዘ ዳኒ አልሞን በቀጣይ ማስመዝገብ እንደማይችሉ ሲዘገብ ነበር።

አሁን ላይ ባርሴሎና ዳኒ ኦልሞን በላሊጋው ለማስመዝገብ አራት ቀናት እንዳሉት ተዘግቧል።

ባርሴሎና ዳኒ ኦልሞን በሚቀጥሉት አራት ቀናት ማስመዝገብ የማይችል ከሆነ ተጨዋቹ በነፃ ባርሴሎናን እንደሚለቅ ተገልጿል።

@tikvahethsport      @kidusoyoftahe
ማድሪድ የስታዲየሙን ስያሜ ሊቀይር ነው !

የስፔን ላሊጋው ክለብ ሪያል ማድሪድ የስታዲየሙን ሳንቲያጎ በርናቦ ስያሜ ማስተካከያ ሊያደርግበት መሆኑን ማርካ ዘግቧል።

ይህንንም ተከትሎ ሪያል ማድሪድ "ሳንቲያጎ" የሚለውን ስያሜ በማስቀረት "በርናቦ“ ስታዲየም ብቻ በሚል ለመቀየር ማሰቡ ተገልጿል።

ሎስ ብላንኮዎቹ የስታዲየሙን ስያሜ " በርናቦ ስታዲየም " በሚል ለመቀየር ያሰቡት ከገበያ ንግድ ጋር በተያያዘ ምክንያት መሆኑ ተነግሯል።

ሪያል ማድሪድ ስታዲየሙን በክለቡ ውስጥ በተጨዋችነት እና ፕሬዝዳንትነት ትልቅ አሻራ ባሳረፉት ስፔናዊ የቀድሞ ተጨዋች ሳንቲያጎ በርናቦ ስም እንደሰየመ የሚታወቅ ነው።

@tikvahethsport      @kidusoyoftahe
ሳንቲ ካዞርላ በኤምሬትስ ስታዲየም ይገኛል !

የቀድሞ የመድፈኞቹ ተጨዋች ሳንቲ ካዞርላ ዛሬ የአርሰናል እና ኢፕስዊች ታውንን ጨዋታ ለመታደም በኤምሬትስ ስታዲየም ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።

ስፔናዊው ተጨዋች ሳንቲ ካዞርላ ከአርሰናል ጋር ከተለያየ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በኤምሬትስ ስታዲየም እንደሚገኝ ተነግሯል።

የ 40ዓመቱ ተጨዋች ሳንቲ ካዞርላ በአሁን ሰዓት በስፔን ሁለተኛ ሊግ ለሪል ኦቬዶ በመጫወት ሲገኝ በውድድር ዘመኑ መጨረሻ ጫማውን እንደሚሰቅል ይጠበቃል።

የመድፈኞቹ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ሳንቲ ካዞርላ ጫማውን ሲሰቅል የአሰልጣኝ ቡድናቸውን እንዲቀላቀል እንደሚፈልጉ ሲናገሩ ነበር።

@tikvahethsport      @kidusoyoftahe
📽 😍 የምርጥ አስሩን ቆይታ እንከታተል!

የ#1Wedefit ዲጂታል የሙዚቃ ውድድር ኮከቦቻችን ያደረጉትን አስደሳች ቆይታ የመጀመሪያው ክፍል በYouTube ቻናላችን ላይ እንድትከታተሉ እንጋብዛችኋለን! 👉🏾
https://youtu.be/Z_Fymkjk0Po?si=b-hyA4jQhahrOV-I

#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#FurtherAheadTogether #DigitalMusicChallenge
2025/01/03 22:30:57
Back to Top
HTML Embed Code: