Telegram Web Link
73 '

ቶተንሀም 2 - 5 ሊቨርፑል

ማዲሰን        ዲያዝ
 ኩሉሴቭስኪ    ማክ አሊስተር
                          ስቦዝላይ
                          ሳላህ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
83 '

ቶተንሀም 3 - 5 ሊቨርፑል

ማዲሰን         ዲያዝ
 ኩሉሴቭስኪ    ማክ አሊስተር
ሶላንኬ            ስቦዝላይ
                            ሳላህ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
85 '

ቶተንሀም 3 - 6 ሊቨርፑል

ማዲሰን         ዲያዝ
 ኩሉሴቭስኪ    ማክ አሊስተር
ሶላንኬ            ስቦዝላይ
                            ሳላህ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሊቨርፑል መሪነቱን አጠናክሯል !

በአስራ ሰባተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሊቨርፑል ከቶተንሀም ጋር ያደርጉትን ጨዋታ 6ለ3 በሆነ ውጤት አሽንፈዋል።

የሊቨርፑልን የማሸነፊያ ግቦች መሐመድ ሳላህ 2x ፣ ሉዊስ ዲያዝ 2x ፣ ስቦዝላይ እና ማክ አሊስተር ማስቆጠር ችለዋል።

ለቶተንሀም ግቦችን ዶምኒክ ሶላንኬ ፣ ኩሉሴቭስኪ እና ጄምስ ማዲሰን ከመረብ አሳርፈዋል።

ግብፃዊው ተጨዋች መሐመድ ሳላህ በውድድር አመቱ በሊጉ 2️⃣5️⃣ የግብ ተሳትፎዎችን በማድረግ ቀዳሚው ተጨዋች ሆኗል።

የሊቨርፑሉ የፊት መስመር ተጨዋች መሐመድ ሳላህ በውድድር ዘመኑ አስራ አምስተኛ የሊግ ግቡን በማስቆጠር ኮከብ ግብ አግቢነቱን እየመራ ይገኛል።

መሐመድ ሳላህ ግቦች የሊቨርፑል የምንግዜም አራተኛው ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ መሆን ችሏል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

1⃣ ሊቨርፑል - 39 ነጥብ
1️⃣1️⃣ ቶተንሀም - 23 ነጥብ 

ቀጣይ መርሐ ግብር ?

ሐሙስ - ሊቨርፑል ከ ሌስተር ሲቲ

ሐሙስ - ኖቲንግሃም ፎረስት ከ ቶተንሀም

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ክፍት ጨዋታ እንደሚሆን እናውቅ ነበር “

የሊቨርፑሉ የፊት መስመር ተጨዋች መሐመድ ሳላህ የቡድናቸው የተከላካይ ክፍል መሻሻል እንዳለበት ገልጿል።

“ ክፍት ጨዋታ እንደሚሆን እናውቅ ነበር “ ያለው መሐመድ ሳላህ አክሎም “ ቡድናችን የተከላካይ ክፍሉ መሻሻል አለበት ሶስት ግቦች ተቆጥረውብናል “ ብሏል።

የኮንትራት ማራዘም ሁኔታውን በተመለከተ የተጠየቀው መሐመድ ሳላህ በጉዳዩ ላይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
የቤቲካ የገና ስጦታ ተመልሷል!
ጨምሯል፣አድጓል፣ያንበሸብሻል!!
በየሳምንቱ ጓደኞቻችሁን በዕለተ ሰኞ በምንለቀው የፌስቡክ ፖስታችን ስር ታግ ያድርጉ፣ ይሸለማሉ!
በየሳምንቱ 5 አሸናፊዎች!
በየሳምንቱ ስማርት ስልክክክክክ እንዲሁም በመጨረሻም ለ2 ደንበኞች የ50,000 ብርርርር ሽልማት!! ሌሎችም ብዙ ስጦታዎች ከቤቲካ!

ለዚህ ሳምንት ፣ በየፌስቡክ ፖስታችን ስር ብቻ ያሉ ታግ የተደረጉ ቁጥሮች የሚመዘገቡ ይሆናል!
አሁኑኑ https://web.facebook.com/BetikaET ላይታግ ያድርጉ!

ቤቲካ የአሸናፊዎች ቤት!
Forwarded from HEY Online Market
🔹Mackbook M2 Air

•02 CC 139,000 Birr
•15 CC 129,000 Birr
•50 CC 119,000 Birr

Contact us :
0953964175 @heymobile

@Heyonlinemarket
#SerieA 🇮🇹

የጣልያን ሴርያ መርሐግብሮች በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት ቀጥለው ሲካሄዱ የሊጉ መሪ አታላንታ በአሸናፊነቱ ቀጥሏል።

የሊጉ መሪ አታላንታ ከኢምፖሊ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 3ለ2 በማሸነፍ መሪነቱን ያጠናከረበትን ውጤት አስመዝግቧል።

ጁቬንቱስ በበኩሉ ትላንት ምሽት ከሞንዛ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ1 ማሸነፍ ችሏል።

አታላንታ በዚህ የውድድር ዘመን ከአምስቱ ታላላቅ የአውሮፓ ሊጎች በርካታ ጨዋታዎችን ያሸነፈው ክለብ ሆኗል።

በአሰልጣኝ ጋስፔሪኒ የሚመራው አታላንታ ከሴርያው ካለፈው መስከረም ወር ወዲህ ምንም ጨዋታ አልተሸነፈም።

አታላንታ በሴርያው አስራ አንደኛ ተከታታይ ድሉ በማስመዝገብ ድንቅ የውድድር አመት በማሳለፍ ላይ ይገኛል።

የሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ምን ይመስላል ?

1️⃣ አታላንታ :- 40 ነጥብ
2️⃣ ናፖሊ :- 38 ነጥብ
3️⃣ ኢንተር ሚላን :- 34 ነጥብ ( 2 ቀሪ ጨዋታ )
4️⃣ ላዝዮ :- 34 ነጥብ
5️⃣ ፊዮሬንቲና :- 31 ነጥብ
6️⃣ ጁቬንቱስ :- 31 ነጥብ

ኮከብ ግብ አግቢዎች ደረጃ ?

- ማቲዮ ሬትጉዮ :- 1️⃣2️⃣ ጎሎች
- ማርከስ ቱራም :- 1️⃣1️⃣ ጎሎች
- ሞይስ ኪን :- 9️⃣ ጎሎች
- አዴሞላ ሉክማን :- 9️⃣ ጎሎች

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
አሸናፊዎች ተለይተዋል።

ትክክለኛ ምላሽ ቀድመው የሰጡት ከስር የተገለፁት የቤተሰባችን አባላት ናቸው።

ትክክለኛ ምላሽ የሰጡትን በመፈለጉ ሂደት የተዘለለ እና ያልታየ ካለ ማሳወቅ ይቻላል። Edit የተደረገ መልስ ተቀባይነት አይኖረውም።

ስጦታ የሚበረከትላቸው ቀድመው የመለሱ ሶስት አሸናፊዎች ብቻ ናቸው።

የማንችስተር ሲቲ እና አስቶን ቪላ

1ኛ. @iku_chelsea
2ኛ. @STUM10
3ኛ. Aman

የአርሰናል እና ክሪስታል ፓላስ ጨዋታ

1ኛ. Habtish sunpair
2ኛ. @Zekijon12
3ኛ. @S567i0

የባርሴሎና እና አትሌቲኮ ማድሪድ

1ኛ. @Miku03_26
2ኛ. Mia
3ኛ. @Tamicore

የቼልሲ እና ኤቨርተን ጨዋታ

1ኛ. @Nahomass
2ኛ. @nmoney_line
3ኛ. @Yeuthmanisultan

የማንችስተር ዩናይትድ እና በርንማውዝ

1ኛ.Ⓜ️♎️
2ኛ. nati
3ኛ. alex process

የሪያል ማድሪድ እና ሲቪያ

1ኛ. Fuad
2ኛ. @Senayt21
3ኛ. @YonasTilahu

የሊቨርፑል እና ቶተንሀም

1ኛ. @samir8100aa

🔴 አሸናፊዎች @Kidusyoftahe ስልክ ቁጥር በማስቀመጥ ሽልማታቸውን መውሰድ የሚችሉ ሲሆን ሽልማቱ በነገው ዕለት የሚደርሳቸው ይሆናል።

@tikvahethsport
TIKVAH-SPORT
“ የወከለኝ ክልል እንኳን አልመረጠኝም “ “ ምርጫው ፍትሀዊ አይደለም “  የተከበሩ አቶ ዱቤ ጁሎ ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንትነት ምርጫ ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ተወክለው በእጩነት የተወዳደሩት የተከበሩ አቶ ዱቤ ጁሎ “ ምርጫው ፍትሀዊ አይደለም “ ብለዋል። “ ምርጫው አልቋል አትሂድ ተብዬ ተነግሮኝ ነበር “ ያሉት የተከበሩ አቶ ዱቤ ጁሎ በጉባኤው ያጋጠመኝም ይሄው ነው በማለት…
“ የምመጣው መቶ በመቶ እምባ ለማበስ ነው “ አትሌት ስለሺ ስህን

“ ምርጫው ፍትሃዊ ነው “

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት በመሆን የተመረጠው አትሌት ስለሺ ስህን ትላንት የተካሄደው ምርጫ ፍትሀዊ ነው በማለት ተናግሯል።

“ ጊዜ ወስደው ተጠንቅቀው ሰርተዋል “ ሲል የምርጫውን ሂደት የገለፀው አትሌት ስለሺ ስህን “ ለእኔ ምርጫው ፍትሀዊ ነው “ ወደ ሀላፊነት እንድመጣ የማንም እጅ የለበትም ብሏል።

“ አትሌቲክሳችንን እና ሀገራችንን የሚመጥን ሥራ ለመስራት ዝግጁ ነኝ “ የሚለው ፕሬዝዳንቱ “ የምመጣው መቶ በመቶ እምባ ለማበስ ነው “ ሲል ተደምጧል።

" ከገብሬ ጋር ባልወዳደር ደስ ይለኝ ነበር ፤ ስለራሳችን ማጋነን እንዳይሆን እንጂ አትሌቲክሱን ፤ ቤቱን በደንብ የምናውቀው እኔና ገብሬ ነን፤ገብሬ እንግዲህ ያግዘኛል ብዬ አስባለሁ።“ አትሌት ስለሺ ስህን

አትሌት ስለሺ ስህን በትላንቱ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ጠንካራ ተፎካካሪ የነበረውን አትሌት ገብረእግዚአብሔር ገ/ማርያም በሶስት ድምፆች በመብለጥ ማሸነፉ ይታወቃል።

ምንጭ :- ጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ በሌላ አቅጣጫ ሪከርድ እያስመዘገብን ነው “ ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ቡድናቸው " ይሄ ጥሩ ነው " የሚባል ነገር የለውም በማለት ያለበትን ወቅታዊ ሁኔታ ገልጸዋል።

" ውጤቱ የለም እንጂ ጥሩ እየተጫወትን ነው ብዬ የምናገረው ነገር የለኝም “ የሚሉትጋርዲዮላ ሁሉም ቁጥሮች መጥፎ ናቸው ውጤቱን ማየት በቂ ነው ብለዋል።

“ እስካሁን በርካታ ሪከርዶችን ስንሰብር ቆይተናል አሁን ደግሞ በተቃራኒ አቅጣጫ ሌሎች ሪከርዶችን መስበር ጀምረናል እውነታው ይሄው ነው።" ጋርዲዮላ

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
አንቾሎቲ ተጨዋች ማስፈረም ይፈልጋሉ !

የሪያል ማድሪዱ ዋና አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ በጥር የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት አዲስ ተጨዋች ማስፈረም እንደሚፈልጉ ተገልጿል።

የክለቡ ሪያል ማድሪድ ቦርድ በበኩሉ በጥር የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ተጨዋች የማስፈረም ፍላጎት እንደሌላቸው ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።

በጉዳት ምክንያት በርካታ ተጨዋቾቹን ያጣው ሪያል ማድሪድ በቀጣይ ቡድኑን ለማጠናከር ወደ ዝውውር ገበያው እንደሚወጣ ሲዘገብ እንደነበር ይታወሳል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
የላሊጋ የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ታውቋል !

አስራ ስምንተኛ ሳምንቱ ላይ የደረሰው የስፔን ላሊጋ የ 2024/25 የውድድር ዘመን የወርሀ ታህሣሥ የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ይፋ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት የአትሌቲኮ ማድሪዱ ዋና አሰልጣኝ ዲያጎ ሲሞኒ የስፔን ላሊጋ የወርሀ ታህሣሥ የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ በመሆን መመረጥ ችለዋል።

አሰልጣኙ በወሩ አትሌቲኮ ማድሪድን እየመሩ ያደረጓቸውን ሶስት ተከታታይ የሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ ችለዋል።

አትሌቲኮ ማድሪድ የስፔን ላሊጋን በ 4️⃣1️⃣ ነጥቦች በመምራት ላይ ይገኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አርሰናል ተጨዋቹ ለሳምንታት ከሜዳ ይርቃል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የፊት መስመር ተጨዋች ቡካዩ ሳካ ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት ለበርካታ ሳምንታት ከሜዳ እንደሚርቅ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አረጋግጠዋል።

እንግሊዛዊው ተጨዋች ቡካዩ ሳካ አርሰናል ክሪስታል ፓላስን ባሸነፈበት ጨዋታ በጡንቻ ጉዳት ምክንያት ተቀይሮ መውጣቱ አይዘነጋም።

" ሳካ ያጋጠመው ጉዳት ጥሩ አይመስልም ከታሰበው የከፋ ሊሆንም ይችላል ለሳምንታት ከሜዳ ይርቃል “ ሲሉ ሚኬል አርቴታ ተናግረዋል።

ሌላኛው የፊት መስመር ተጨዋች ራሂም ስተርሊንግ በበኩሉ በጉዳት ምክንያት በተመሳሳይ ለሳምንታት ከሜዳ እንደሚርቅ ሚኬል አርቴታ ጠቁመዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቫሌንሽያ አሰልጣኙን አሰናብቷል !

ጥሩ ያለሆነ የውድድር አመት በማሳለፍ ላይ የሚገኘው የስፔን ላሊጋው ክለብ ቫሌንሽያ አሰልጣኝ ሩበን ባራን ከሀላፊነታቸው አሰናብቷል።

ቫሌንሽያ በዘንድሮው የውድድር አመት ካደረጋቸው የሊግ ጨዋታዎች በዘጠኙ ሲሸንፍ ማሸነፍ የቻለው በሁለቱ ብቻ ነው።

የስድስት ጊዜ የስፔን ላሊጋ አሸናፊው ቫሌንሽያ በአሁን ሰዓት በላሊጋው ደረጃ ሰንጠረዥ ግርጌ ላይ ይገኛል።

እ.ኤ.አ. ከ 1987 ወዲህ ሳይወርድ በስፔን ትልቁ የሊግ እርከን ላሊጋ እየተወዳደረ የሚገኘው ቫሌንሽያ አሁን ላይ የመውረድ አደጋ ተጋርጦበታል።

ቫሌንሽያ በቀጣይ የሊጉ መርሐግብር ከሪያል ማድሪድ ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ሩበን አሞሪም የራሽፎርድን ሁኔታ በራሳቸው ይፈታሉ !

አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም የማርከስ ራሽፎርድን ሁኔታ በራሳቸው እንዲፈተቱ ከክለቡ ሀላፊዎች ፍቃድ እንደተሰጣቸው ቢቢሲ ዘግቧል።

ሰር ጂም ራትክሊፍም ሆኑ የክለቡ ሀላፊዎች በማርከስ ራሽፎርድ የወደፊት ቆይታ ዙሪያ ጣልቃ እንደማይገቡ ተገልጿል።

አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ማርከስ ራሽፎርድን በተከታታይ ሶስት ጨዋታዎች ከቡድናቸው ስብስብ ውጪ ማድረጋቸው አይዘነጋም።

ማርከስ ራሽፎርድ በ 350,000 ፓውንድ ከክለቡ ከፍተኛ ተከፋይ ተጨዋቾች አንዱ ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኦስካር ወደ ብራዚል ሊመለስ ነው !

ብራዚላዊው የቀድሞ የቼልሲ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኦስካር ወደ ቀድሞ የልጅነት ክለቡ ሳኦ ፓውሎ ለመመለስ መቃረቡ ተገልጿል።

የ 33ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኦስካር ከቻይናው ክለብ ሻንጋይ ፖርት ጋር ከተለያየ በኋላ ያለ ክለብ ይገኝ ነበር።

ኦስካር በቻይና ሊግ በነበረው የሰባት አመታት ቆይታ 175 ሚልዮን ፓውንድ መሰብሰቡ ተገልጿል።

ኦስካር አሁን ላይ ሳኦ ፓውሎን ለሶስት የውድድር አመታት ለመቀላቀል ከስምምነት መድረሱን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
በኦልድትራፎርድ አይጦች ማስቸገራቸው ተገለጸ !

በማንችስተር ዩናይትዱ ኦልድትራፎርድ ስታዲየም አይጦች ማስቸገራቸውን ዴይሊ ሜይል አስነብቧል።

የአካባቢው የንፅህና ተቆጣጣሪዎች በኦልድትራፎርድ ጉብኝታቸው ወቅት በስታዲየሙ አይጥ ማግኘታቸው ተገልጿል።

ይህንንም ተከትሎ ክለቡ ከነበረው የንፅህና ቁጥጥር አምስት ኮከብ ደረጃ ሁለት ደረጃዎች መቀነሳቸው ተዘግቧል።

አብዛኞቹ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ክለቦች አምስት ኮከብ የንፅህና ጥራት ደረጃዎች እንዳሏቸው ተነግሯል።

ማንችስተር ዩናይትድ በበኩሉ ችግሩን ለማስተካከል ከአካባቢው የፀረ ተባይ ተቆጣጣሪዎች ጋር እየሰሩ መሆኑ ተነግሯል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
አርሰናል በሳካ ቦታ ማንን ሊጠቀም ይችላል ?

እንግሊዛዊው የመድፈኞቹ የፊት መስመር ተጨዋች ቡካዩ ሳካ በጉዳት ምክንያት ለሳምንታት ከሜዳ ይርቃል።

የቡካዩ ሳካን ጉዳት ተከትሎ ወደ ዝውውር ገበያው ይገቡ እነደሆነ የተጠየቁት ሚኬል አርቴታ “ ያሉንን ተጨዋቾች ለመጠቀም ነው ሀሳቤ “ ብለዋል።

አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አክለውም የቡካዩ ሳካ ጉዳት ከባድ ሊሆን እንደሚችል በመጠቆም ከውድድር ዘመኑ መጠናቀቅ በፊት ይመለሳል ብዬ እጠብቃለሁ ብለዋል።

በቀጣይ ጨዋታዎች ቡካዩ ሳካ በሚሰለፍበት የቀኝ የፊት መስመር ቦታ የተለያዩ ተጨዋቾች መሰለፍ እንደሚችሉ አሰልጣኙ ጠቁመዋል።

በቀጣይ በቀኝ የፊት መስመር ቦታ ጄሱስ ፣ ሀቨርትዝ ፣ ትሮሳርድ ፣ ማርቲኔሊ እና ንዋኔሪን ሊጠቀሙ እንደሚችሉ አርቴታ ተናግረዋል።

ጋብሬል ማርቲኔሊ የመጀመሪያ ተመራጭ ሊሆን እንደሚችል የጠቆሙት አርቴታ “ እሱ ከዚህ በፊት ተሰልፎ ጥሩ ነገር አሳይቷል ጥሩ አማራጭ ነው “ ብለዋል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/12/26 05:49:17
Back to Top
HTML Embed Code: