Telegram Web Link
" ለአዲስ ፈተና ዝግጁ ነኝ " ራሽፎርድ

የማንችስተር ዩናይትዱ የፊት መስመር ተጨዋች ማርከስ ራሽፎርድ በቀጣይ ለአዲስ ፈተና ዝግጁ እንደሆነ ገልጿል።

ስለ ማንችስተር ዩናይትድ የወደፊት ቆይታው የተጠየቀው ማርከስ ራሽፎርድ " ለአዲስ ፈተና ዝግጁ ነኝ ብዬ አስባለሁ " በማለት ተናግሯል።

“ ማንችስተር ዩናይትድን የምለቅ ከሆነ ከእኔ ስለ ማንችስተር ዩናይትድ መጥፎ ነገር አይሰማም ሁልጊዜም በዩናይትድነቴ እቀጥላለሁ።“ሲል ራሽፎርድ ተናግሯል።

“ ሌሎች ተጨዋቾች ክለቡን እንዴት እንደለቀቁ አውቃለሁ እኔ እንደነሱ መሆን አልፈልግም የምለቅ ከሆነ በራሴ በይፋ የማሳውቅ ይሆናል።“ ራሽፎርድ

“ ከማንችስተር ደርቢ ውጪ መሆኔ ያበሳጫል ነገርግን ተከስቷል ጨዋታውን አሸንፈናል ወደፊት እንቀጥላለን " ያለው ራሽፎርድ " ምርጡ አቋሜ ገና አልመጣም " ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ይቅናዎት!
ኦዶች ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍ ተደርገዋል።
ታዲያ ምን ይጠብቃሉ? ለማሸነፍ በተመቻቹ ኦዶች ይወራረዱ!
አሁኑኑ Betika.et ላይ ብቻ!
ቤቲካ የአሸናፊዎች ቤት!
Forwarded from HEY Online Market
Gaming PC (Core i9)

🔸Z-Book, Core i9
10th Generation
1TB Storage/ 32GB RAM
Nvidia RTX 5000 (16GB)

🔹HP OMEN, Core i9
13th Generation
1TB Storage/ 16GB RAM
Nvidia RTX 4060 (8GB)

🔸Nitro-5, Core i9
Core i9-13th Gen
1TB Storage /16GB RAM
Nvidia RTX 4060 (8GB)

Contact Us
0953964175 @heymobile
@heyonlinemarket
የዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዎች !

2:00 ሪያል ማድሪድ ከ ፓቹካ ( ፍፃሜ )

4:30 አርሰናል ከ ክሪስታል ፓላስ ( ካራባኦ ካፕ )

4:45 ኒውካስል ከ ብሬንትፎርድ ( ካራባኦ ካፕ )

5:00 ሳውዝሀምፕተን ከ ሊቨርፑል ( ካራባኦ ካፕ )

5:00 ሞናኮ ከ ፒኤስጂ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኢታን ንዋኔሪ ወደ ፊት መስመር አጥቂነት ?

ሴፔናዊው የአርሰናል አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ወጣቱ ተጨዋቻቸው ኢታን ንዋኔሪ በፊት መስመር አጥቂነት የመጫወት አቅም አለው የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል።

የ 17ዓመቱ ተጨዋች ኢታን ንዋኔሪ በአሁን ሰዓት በክለቡ በቀኝ የአጥቂ አማካይ ቦታ ተሰልፎ ግልጋሎት እየሰጠ ይገኛል።

መድፈኞቹ ከኤቨርተን አቻ በተለያዩበት ጨዋታ የቡድኑን አምበል ማርቲን ኦዴጋርድ በመተካት በቦታው ተሰልፎ መጫወት ችሏል።

አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በቀጣይ ጥቂት አመታት ወጣቱን ተጨዋች ኢታን ንዋኔሪ በአዲስ ሚና ለማብቃት ማሰባቸውን ገልጸዋል።

አሰልጣኙ ተጫዋቹን ቡድናቸው በሚታማበት የዘጠኝ ቁጥር ተጨዋች ቦታ ዝግጁ ለማድረግ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

ወጣቱ ተጨዋች ኢታን ንዋኔሪ በዚህ አመት ለአርሰናል አራት ግቦችን ማስቆጠር የቻለ ሲሆን በቡድኑ ከእሱ የበለጠ ግብ ያስቆጠሩት ቡካዩ ሳካ እና ሀቨርትዝ ናቸው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
“ ምንም የተከለከለ ነገር አልተጠቀምኩም " ሙድሪክ የቼልሲው ተጨዋች ማይካሎ ሙድሪክ የተከለከለ ንጥረነገር አለመጠቀሙን በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባሰፈረው መልዕክት ገልጿል። የሰጠው ናሙና የተከለከለ ንጥረነገር መጠቀሙን እንደሚያሳይ የእንግሊዝ ኤፍኤ እንዳሳወቀው ያረጋገጠው ሙድሪክ “ እኔ ግን ተጠቅሜ አላውቅም " ሲል ተናግሯል። የተነገረው ነገር እንዳስደነገጠው የገለፀው ተጨዋቹ “ እንዴት ሊሆን…
ሙድሪክ የፖግባን ጠበቆች ቀጥሯል !

ዩክሬናዊው የቼልሲ ተጨዋች ማይካሎ ሙድሪክ ያልተፈቀደ ንጥረነገር መጠቀሙ በምርመራ መታየቱን ተከትሎ በጊዜያዊነት ከእግርኳስ መታገዱ ይታወቃል።

ማይካሎ ሙድሪክ አሁን ላይ ፈረንሳዊው ተጨዋች ፖል ፖግባ በቅርቡ ተመሳሳይ ነገር አጋጥሞት የረዱትን ጠበቆች መቅጠሩን ቴሌግራፍ አስነብቧል።

የህግ ተቋሙ ፖል ፖግባ ተጥሎበት የነበረው የአራት አመት እግድ ወደ አስራ ስምንት ወር ዝቅ እንዲል መርዳታቸው ተገልጿል።

ሙድሪክ ንጥረነገሩን መጠቀሙ በምርመራ ቢታወቅም አውቆ ምንም ነገር እንዳልወሰደ እና እንዴት ሊሆን እንደቻለ ከክለቡ ጋር እያጣራ እንደሚገኝ ማሳወቁ ይታወሳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ተጨዋቾች ወደ ሜዳ ውሻ ይዘው ይገባሉ !

የኤሲ ሚላን እና ሄላስ ሄሮና ተጨዋቾች በሳምንቱ መጨረሻ በሚያደርጉት ጨዋታ ሰባት የውሻ ቡችሎችን ሜዳ ውስጥ ይዘው እንደሚገቡ ተገልጿል።

ሄላስ ሄሮና ተጨዋቾቹ የውሻ ቡችሎችን ይዘው የሚገቡት በእንሰሳት ጣቢያ የሚገኙት ቡችሎቹ ባለቤት እንዲያገኙ ለመርዳት መሆኑን አስታውቋል።

የሁለቱ ክለቦች አምበሎች እንዲሁም ከሁለቱም ቡድኖች ተጨማሪ አምስት ቡችሎችን ይዘው ወደ ሜዳ እንደሚገቡ ተነግሯል።

ጨዋታው በሚልዮን የሚቆጠር ተመልካች ያለው በመሆኑ እንስሳቱ የሚወዳቸውን ቤተሰብ ያገኛሉ የሚል አምነት አለን ሲል ክለቡ አሳውቋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
" ለአዲስ ፈተና ዝግጁ ነኝ " ራሽፎርድ የማንችስተር ዩናይትዱ የፊት መስመር ተጨዋች ማርከስ ራሽፎርድ በቀጣይ ለአዲስ ፈተና ዝግጁ እንደሆነ ገልጿል። ስለ ማንችስተር ዩናይትድ የወደፊት ቆይታው የተጠየቀው ማርከስ ራሽፎርድ " ለአዲስ ፈተና ዝግጁ ነኝ ብዬ አስባለሁ " በማለት ተናግሯል። “ ማንችስተር ዩናይትድን የምለቅ ከሆነ ከእኔ ስለ ማንችስተር ዩናይትድ መጥፎ ነገር አይሰማም ሁልጊዜም በዩናይትድነቴ…
" ራሽፎርድ ቢቆይ ደስተኛ ነኝ " ሩበን አሞሪም

የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ማርከስ ራሽፎርድ በማንችስተር ዩናይትድ ቤት ቢቆይ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ማርካስ ራሽፎርድ ትላንት " አዲስ ፈተና ለመጋፈጥ ዝግጁ ነኝ ዩናይትድን የምለቅ ከሆነ ስለ ክለቡ ከእኔ መጥፎ አይሰማም " ሲል ተናግሮ ነበር።

ሩበን አሞሪም በበኩላቸው ስለ ራሽፎርድ ቆይታ ተጠይቀው " ቢቆይ ደስተኛ ነኝ ክለቡ ትልቅ ተሰጥኦ ያለው ተጨዋች ያስፈልገዋል እሱ ደግሞ ይህ አለው " ብለዋል።

" ራሽፎርድ የሚስፈልገው በምርጥ አቋሙ መጫወት ነው የማስበው እንደዛ ነው እሱን ማገዝ እፈልጋለሁ " ሲሉ አሰልጣኙ ጨምረው ተናግረዋል።

ሩበን አሞሪም አክለውም ማርከስ ራሽፎርድ ትላንት ከሰጠው ቃለ ምልልስ በኋላ አግኝተው እንዳላነጋገሩት አረጋግጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቼልሲ የተጫዋቹን ውል ለማራዘም ተስማማ !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የወጣት ተጫዋቹን ጆሽ አቼምፖንግ ኮንትራት ለረጅም ጊዜ ለማራዘም ከስምምነት መድረሳቸውን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።

የ 18ዓመቱ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች በሰማያዊዎቹ ቤት እስከ 2029 ክረምት ድረስ ለመቆየት ፊርማውን እንደሚያኖር ተገልጿል።

እንግሊዛዊው ተጨዋች በቼልሲ ቤት ያለው ውል በ 2026 የሚጠናቀቅ መሆኑን ተከትሎ በክለቡ ያለው ቆይታ የተረጋገጠ አልነበረም።

ተጨዋቹ በአሁኑ ሰዓት በአሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ስር ልምምድ በመስራት ላይ መሆኑ ሲገለፅ በቀጣይ የኮንፈረንስ ሊግ ጨዋታ እንደሚሰለፍ ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ባርሴሎና ከፍተኛውን ገቢ አግኝቷል !

የስፔን ላሊጋ ባለፈው የ 2023/24 የውድድር አመት ክለቦች ከቴሌቪዥን መብት ያገኙትን ገቢ ይፋ አድርጓል።

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ከቲቪ መብት 162.5 ሚልዮን ዩሮ ጊቢ በማግኘት ቀዳሚውን ስፍራ መያዛቸውን ላሊጋው አስታውቋል።

የስፔን ላሊጋው አሸናፊ ሪያል ማድሪድ በበኩሉ ከውድድር አመቱ የቴሌቪዥን መብት 159.5 ሚልዮን ዩሮ በመቀበል ሁለተኛ ደረጃን መያዛቸው ተገልጿል።

አትሌቲኮ ማድሪድ በበኩሉ 117.9 ሚልዮን ዩሮ በማግኘት ሶስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጣቸው ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዩናይትድ የተጫዋቹን ግልጋሎት አያገኝም !

ማንችስተር ዩናይትድ ነገ ከቶተንሀም ጋር በሚያደርገው ተጠባቂ የካራባኦ ካፕ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ የተጫዋቹን ግልጋሎት አያገኝም።

እንግሊዛዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሜሰን ማውንት በጉዳት ከጨዋታው ውጪ መሆኑን አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም አረጋግጠዋል።

ተጨዋቹ ማንችስተር ዩናይትድ ማንችስተር ሲቲን ባሸነፈበት ጨዋታ በጉዳት ምክንያት ተቀይሮ መውጣቱ የሚታወስ ነው።

በተጨማሪም የመስመር ተጨዋቹ ኑሴር ማዝራዊ በጨዋታው መድረሱ አጠራጣሪ መሆኑን ሩበን አሞሪም ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የላሊጋ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ?

የስፔን ላሊጋ የ 2024/25 የውድድር ዘመን የወርሀ ታኅሣሥ የወሩ ምርጥ ተጨዋች አምስት እጩዎች ይፋ ተደርገዋል።

በዚህም መሰረት :-

ሳንድሮ

ጁድ ቤሊንግሀም

አንቷን ግሬዝማን

ሳንሴት እና

ራፊንሀ በእጩነት መቅረብ የቻሉ ተጨዋቾች ናቸው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ሙድሪክን እናምነዋለን “ ኢንዞ ማሬስካ

የሰማያዊዎቹ አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ክለቡ በተከለከለ ንጥረነገር ምክንያት በጊዜያዊነት ከእግርኳስ ከታገደው ማይካሎ ሙድሪክ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

አሰልጣኙ ሲናገሩም " ሙድሪክን እናምነዋል ድጋፍም እናደርግለታለን “ ሲሉ ከተጨዋቹ ጉን መሆናቸውን ተናግረዋል።

ኢንዞ ማሬስካ አክለውም በቼልሲ ቤት እስከ 2030 ኮንትራት ያለው ማይካሎ ሙድሪክ የእግር ኳስ ህይወቱ መጨረሻ ይሆናል ብለው እንደማያምኑ ገልጸዋል።

ሙድሪክ በቀጣይ ከኤፍኤው ምን ሊገጥመው ይችላል ?

የእንግሊዝ ኤፌኤ የተጫዋቹን የክስ ሂደት ከፀረ አበረታች ቅመሞች ህግ ጥሰት ጋር የሚያገናኘው ከሆነ ሙድሪክ የረጅም ጊዜ ቅጣት እንደሚጠብቀው ተገልጿል።

የ 23ዓመቱ ተጨዋች ሙድሪክ ምናልባትም የአራት አመታት እገዳ ቅጣት ሊጣልበት እንደሚችል ጉዳዩን በሚመለከት የወጣው የኤፍኤው ህገ ደንብ ይገልፃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" የአለም ምርጡ ተጨዋች ነኝ " ቪኒሰስ

የሪያል ማድሪዱ የፊት መስመር ተጨዋች ቪኒሰስ ጁኒየር ሰዎች ነገሮችን እንዴት ማድረግ እንዳለበት እንዲነግሩት እንደማይፈልግ ተናግሯል።

የፊፋ የአለም ምርጥ ተጨዋች ሽልማት ባለቤቱ ቪኒሰስ ጁኒየር ሲናገርም “ በእርግጥም የአለም ምርጡ ተጨዋች ነኝ " ሲል ተደምጧል።

“ ማንም ሰው ነገሮችን እንዴት ማድረግ እንዳለብኝ ሊነግረኝ አይችልም " የሚለው ቪኒሰስ ጁኒየር “ እኔን ዝቅ ለማድረግ እና ለማሳነስ ብዙ ለፍተዋል ነገርግን አልቻሉም " ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማርከስ ራሽፎርድ ከቡድኑ ስብስብ ውጪ ነው !

እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጨዋች ማርከስ ራሽፎርድ ቶተንሀምን ከሚገጥመው የማንችስተር ዩናይትድ ስብስብ ውስጥ እንዳልተካተተ ተገልጿል።

አርጀንቲናዊው ተጨዋች አሌሀንድሮ ጋርናቾ በበኩሉ ወደ ቡድኑ ስብስብ መመለሱ ተነግሯል።

ሁለቱ ተጨዋቾች በሳምንቱ መጨረሻ ከተደረገው የማንችስተር ደርቢ ጨዋታ ውጪ ተደርገው እንደነበር የሚታወስ ነው።

አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ጋርናቾ እና ራሽፎርድ በሚኖረን ልምምድ ላይ ጥሩ ነገር የሚያሳዩ ከሆነ ለጨዋታው ይመረጣሉ ብለው ነበር።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

4:30 አርሰናል ከ ክሪስታል ፓላስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሪያል ማድሪድ የዋንጫ አሸናፊ ሆኗል !

የስፔኑ ክለብ ሪያል ማድሪድ የ 2024 የፊፋ ኢንተርኮንቲኔንታል ካፕ ዋንጫ አሸናፊ ሆነዋል።

ሎስ ብላንኮዎቹ በኳታር ከሜክሲኮው ክለብ ፓቹካ ጋር ያደረጉትን የፍፃሜ ጨዋታ 3ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የሪያል ማድሪድን የማሸነፊያ ግቦች ኪሊያን ምባፔ ፣ ሮድሪጎ እና ቪኒሰስ ጁኒየር ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ በሪያል ማድሪድ አሰልጣኝነት አስራ አምስተኛ ዋንጫቸውን በማሳካት ስኬታማው የሪያል ማድሪድ አሰልጣኝ ሆነዋል።

ሉካ ሞድሪች ከሪያል ማድሪድ ጋር ሀያ ስምንተኛ ዋንጫውን ሲያሳካ በክለቡ ታሪክ በርካታ ዋንጫዎችን ማሳካት የቻለው ተጨዋች ሆኗል።

ቪኒሰስ ጁኒየር ከሪያል ማድሪድ ጋር አስራ አራተኛ ዋንጫውን አሸንፏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" የተሰለፉ ተጨዋቾች ይገባቸዋል " አርቴታ

የመድፈኞቹ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በዛሬ ምሽቱ ጨዋታ በቋሚነት የተሰለፉ ተጨዋቾች እንደሚገባቸው ገልጸዋል።

“ ዛሬ እንዲጫወቱ የመረጥናቸው ተጨዋቾች ሁሉም ይገባቸዋል “ ሲሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ተናግረዋል።

አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በምሽቱ ጨዋታ ባለፉት ጨዋታዎች እድል ያልሰጧቸውን ተጨዋቾች በቋሚነት አሳልፈዋል።

ራሂም ስተርሊግ ፣ ንዋኔሪ ፣ ኬራን ቴርኒ እና ጋብሬል ጄሱስ ጨዋታውን በቋሚነት ለመጀመር የተመረጡ ተጨዋቾች ናቸው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2025/01/01 07:07:13
Back to Top
HTML Embed Code: