Telegram Web Link
ላሚን ያማል ለሳምንታት ከሜዳ ይርቃል !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና የፊት መስመር ተጨዋች ላሚን ያማል በጉዳት ምክንያት ለሳምንታት ከሜዳ እንደሚርቅ ክለቡ ይፋ አድርጓል።

ላሚን ያማል ባጋጠመው ጉዳት ምክንያትም ከሁለት እስከ ሶስት ሳምንታት ከሜዳ እንደሚርቅ ክለቡ አስታውቋል።

ይህንንም ተከትሎ ላሚን ያማል የስፔን ብሔራዊ ቡድንን የማይቀላቀል ይሆናል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ሳውዲ አረቢያ ያለሁት ለገንዘብ አይደለም " ሮናልዶ

ፖርቹጋላዊው የአምስት ጊዜ ባሎን ዶር አሸናፊ ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሳውዲ አረቢያ ያመራው ለገንዘብ አለመሆኑን ገልጿል።

“ ብዙዎች ወደ ሳውዲ አረቢያ ያቀናሁት ለገንዘብ እንደሆነ ያወራሉ “ የሚለው ሮናልዶ ነገር ግን እኔ እዚህ ያለሁት እግር ኳስ ለመጫወት አሁንም ፍቅር ስላለኝ ነው ብሏል።

ክርስቲያን ሮናልዶ አክሎም ሳውዲ አረቢያ ያለሁት ሁልጊዜም ማሸነፍ ስለምፈልግ በማለት ተናግሯል።

የሳውዲ ፕሮ ሊግ ከፍተኛ ፉክክር እየታየበት መምጣቱን የገለፀው ተጨዋቹ " ሊጉ አሁን ላይ ለምርጥ ተጨዋቾች ጭምር ፈታኝ ነው።"ሲል ተደምጧል።

@Tikvahethsport           @kidisyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
🌍 #Wanaw_International 🌍

From the streets of Addis to dressing the greatest on the field—Wanaw is proud to be part of the game at every level. Moving forward, always!

Follow Us
:
Website | Instagram | Facebook | TikTok | X | Youtube | Telegram

🏅 ዋናው ወደፊት...
የፕርሚየር ሊጉ ዳኛ ምርመራ ተከፈተባቸው !

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ዳኛ ዴቪድ ኩት በማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጨውን የተንቀሳቃሽ ምስል ቅጂ ተከትሎ ምርመራ ተከፈተባቸው።

ዋና ዳኞው በተሰራጨው የቪዲዮ ቅጂ ሊቨርፑልን እና የቀድሞ አሰልጣኛቸውን የርገን ክሎፕን ሲሳደቡ እና ሲተቹ ተስተውለዋል።

ይህንንም ተከትሎ የሊጉ ፕሮፌሽናል ዳኞች ማኅበር [PGMOL] ቪዲዮውን መመልከቱን እና በ 49ዓመቱ ዳኛ ዴቪድ ኩት ላይ ምርመራ መጀመሩን አስታውቋል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የፕርሚየር ሊጉ ዳኛ ምርመራ ተከፈተባቸው ! የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ዳኛ ዴቪድ ኩት በማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጨውን የተንቀሳቃሽ ምስል ቅጂ ተከትሎ ምርመራ ተከፈተባቸው። ዋና ዳኞው በተሰራጨው የቪዲዮ ቅጂ ሊቨርፑልን እና የቀድሞ አሰልጣኛቸውን የርገን ክሎፕን ሲሳደቡ እና ሲተቹ ተስተውለዋል። ይህንንም ተከትሎ የሊጉ ፕሮፌሽናል ዳኞች ማኅበር [PGMOL] ቪዲዮውን መመልከቱን እና በ 49ዓመቱ ዳኛ…
የፕርሚየር ሊጉ ዳኛ ዴቪድ ኩት ታገዱ !

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ዳኛ ዴቪድ ኩት በማህበራዊ ሚዲያዎች የተሰራጨውን የተንቀሳቃሽ ምስል ቅጂ ተከትሎ መታገዳቸው ተገልጸ።

ዋና ዳኞው በተሰራጨው የቪዲዮ ቅጂ ሊቨርፑልን እና የቀድሞ አሰልጣኛቸውን የርገን ክሎፕን ሲሳደቡ እና ሲተቹ ተስተውለዋል።

አሁን ላይ የፕርሚየር ሊጉ ፕሮፌሽናል ዳኞች ማኅበር የ 49ዓመቱ ዳኛ ዴቪድ ኩት ማገዱን አስታውቋል።

ማህበሩ በዳኛው ላይ የሚያደርገውን ሙሉ ምርመራ መቀጠሉን እና በቀጣይ ተጨማሪ ማብራሪያዎችን እንደሚሰጥ አሳውቋል።

@Tikvahethsport       @kidusyoftahe
“ 100 ሚልዮን ከቀረበ ይሸጣል “

የፖርቹጋሉ ክለብ ስፖርቲንግ ሊስበን ፕሬዝዳንት ቫራንዳስ ለቪክቶር ዮከሬስ የውል ማፍረሻ ከቀረበ እንደሚሸጡት ገልጸዋል።

" በዮከሬስ ቆይታ ዙርያ ዋስትና አልሰጥም " ያሉት ፕሬዝዳንቱ " እሱን የሚፈልግ ክለብ የውል ማፍረሻውን ካቀረበ እና ተጨዋቹ መሄድ ከፈለገ ይሄዳል።" ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ አክለውም ተጨዋቹ በጥር የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ስፖርቲንግ ሊስበንን ይለቃል የሚል እምነት እንደሌላቸው ተናግረዋል።

ስዊዲናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ቪክቶር ዮከሬስ በስፖርቲንግ ሊስበን ቤት ያለው ውል ማፍረሻ 100 ሚልዮን ዩሮ መሆኑ ተገልጿል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሩድ ቫን ኔስትሮይ ከዩናይትድ ይለቃል !

ባለፉት ጨዋታዎች ማንችስተር ዩናይትድን በጊዜያዊ አሰልጣኝነት የመራው ሩድ ቫን ኔስትሮይ በቀጣይ ከክለቡ ጋር እንደሚለያይ ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።

ሩድ ቫን ኔስትሮይ ባለፈው ክረምት የአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ምክትል አሰልጣኝ በመሆን የቀያዮቹን ሴጣኖች የአሰልጣኝ ቡድን አባላት መቀላቀሉ ይታወቃል።

ቫን ኔስትሮይ የኤሪክ ቴንሀግን መሰናበት ተከትሎ ዩናይትድን በአራት ጨዋታዎች ሲመራ ሶስቱን በአሸናፊነት ተወጥቶ በአንዱ አቻ ተለያይቷል።

አዲሱ የክለቡ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ዛሬ በካሪንግተን ተገኝተው ከተነጋገሩ በኋላ ቫን ኔስቶሮይ እንዲቀላቀላቸው እንደማይፈልጉ ማሳወቃቸው ተነግሯል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሞርጋን ሮጀርስ ለእንግሊዝ ጥሪ ቀረበለት !

የአስቶን ቪላው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሞርጋን ሮጀርስ ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ጥሪ እንደተደረገለት ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።

በአስቶን ቪላ ቤት ጥሩ ጊዜን እያሳለፈ የሚገኘው የ 22ዓመቱ አማካይ ሞርጋን ሮጀርስ ለሶስቱ አናብስት ለመጀመሪያ ጊዜ ጥሪ ተደርጎለታል።

እንግሊዝ በቀጣይ ከግሪክ እና ከሪፐብሊክ አየርላንድ ጋር የአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ ጨዋታዋን የምታደርግ ይሆናል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
እንግሊዝ ተጨዋቾቿ ከስብስቡ ውጪ ሆኑ !

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ ላሉበት ጨዋታዎች ጥሪ ካደረገላቸው ተጨዋቾች መካከል #ስምንት ተጨዋቾች ቡድኑን መልቀቃቸው ተገልጿል።

የሶስቱን አናብስት ስብስብ በጉዳት የለቀቁ ተጨዋቾች

- ቡካዮ ሳካ
- ዴክላን ራይስ
- ጃክ ግሪሊሽ
- ፊል ፎደን
- አሌክሳንደር አርኖልድ
- ኮል ፓልመር
- ሌቪ ኮል ዊል እና ራምስዴል መሆናቸው ተገልጿል።

በሌላ በኩል ሞርጋን ሮጀርስ ፣ ጃሮድ ቦውን ፣ ብራንዝዌት ፣ ጄምስ ትራፎርድ እና ሊቭራሜንቶ ለብሔራዊ ቡድኑ ጥሪ ቀርቦላቸዋል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ጄርሚ ዶኩ ከቤልጂየም ስብስብ ውጪ ሆነ !

የማንችስተር ሲቲው የፊት መስመር ተጨዋች ጄርሚ ዶኩ የሀገሩ ቤልጂየም ብሔራዊ ቡድን ስብስብን ለቆ መውጣቱ ተገልጿል።

ጄርሚ ዶኩ የብሔራዊ ቡድኑን ስብስብ የለቀቀው በበቂ አካላዊ የብቃት ደረጃ ላይ ባለመገኘቱ ምክንያት እንደሆነ ተዘግቧል።

ፊል ፎደን ፣ ጃክ ግሪሊሽ ፣ ማኑኤል አካንጂ እና ማቲውስ ኑኔስ በተመሳሳይ የብሔራዊ ቡድናቸውን ስብስብ የለቀቁ ሌሎች የማንችስተር ሲቲ ተጨዋቾች ናቸዉ።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
Tab A9+ , 128GB, 29,999 Birr
Tab A8, 64GB , 31,000 Birr
Tab S6 lite, 64GB, 40,000 Birr

Contact us:
0936222222 @heymobile1
0925927457 @eBRO4

@Heyonlinemarket
" ሰዎች እንዲጠራጠሩን እንፈልጋለን " ሩበን ዲያስ

የማንችስተር ሲቲው ተከላካይ ሩበን ዲያስ በቡድናቸው ወቅታዊ ብቃት የተነሳ ሰዎች ያሳደሩባቸው ጥርጣሬ ይበልጥ ጠንካራ እንደሚያደርጋቸው ተናግሯል።

" ሰዎች እንዲጠራጠሩን እንፈልጋለን " ያለው ሩበን ዲያስ " የእነሱ ጥርጣሬ እኛን የበለጠ ያጠነክረናል " በማለት ተናግሯል።

" ለበርካታ ጊዜያት አሁን በምንገኝበት የውጤት ቀውስ ውስጥ ገብተን ወደ አሸናፊነት ተመልሰናል ይሄንን አሁንም እንደምናደርገው እርግጠኞች ነን።" ሩበን ዲያስ

ተጨዋቹ አያይዞም ከሀገራት ጨዋታ መልስ ካጋጠመው ጉዳት አግግሞ ለጨዋታዎች ብቁ መሆን የሚችልበት እድል እንዳለ ገልጿል።

@Tikvahethsport               @kidusyoftahe
“ ትልቅ ነገር ማሸነፍ ከፈለግክ ጫናውን መቀበል አለብህ “

የመድፈኞቹ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሚኬል ሜሪኖ ቡድናቸው እየቀረበበት የሚገኘውን ጫና መቋቋም እንዳለበት ገልጿል።

“ ትልቅ ቡድን መሆን ከፈለግክ እና ትልቅ ዋንጫዎችን ማሸነፍ ከፈለግክ የሚቀርበውን ጫና መውደድ አለብህ “ ሲል ሚኬል ሜሪኖ ተናግሯል።

" ከምርጥ ተጨዋቾች ጋር መጫወት መውደድ አለብን ፤ ትልቅ ውድድሮችን ማሸነፍ አለብን የቡድኑ አስተሳሰብ ሁልጊዜም ያለውን የመስጠት ነው።" ሜሪኖ

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
" ባሎን ዶር ያሸነፍኩት ባሳየሁት ወጥ ብቃት ነው " ሮድሪ

ስፔናዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሮድሪ በቀጣይ ካጋጠመው ከባድ ጉዳት በማገገም በዚህ የውድድር አመት ወደ ሜዳ ሊመለስ እንደሚችል ጠቁሟል።

ሮድሪ ምን አለ ?

- "የውድድር አመቱ ረጅም ነው በዚህም መሰረት ከታሰበው ጊዜ ቀድሜ በዚህ አመት ወደ ሜዳ ልመለስ እችላለሁ።

- ባሎን ዶርን ያሸነፍኩት ባሳየሁት ወጥ ብቃት ነው ይሄ በእግር ኳስ በጣም ከባድ ነገር ነው ባለፈው አመት በወጥነት ደረጃ የሚስተካከልኝ ተጨዋች አልነበረም።

- ለባሎን ዶር ሽልማት መምረጥ ብችል ዳኒ ካርቫሀልን ሁለተኛ እንዲሁም ቪኒሰስ ጁኒየርን ሶስተኛ አደርጋለሁ።

- በማንችስተር ሲቲ ያለኝን ኮንትራት ማራዘም ቅድሚያ የምሰጠው ነገር አይደለም አሁን ላይ ትኩረቴ ካጋጠመኝ ጉዳት በማገገም ላይ ነው።" ብሏል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
ላምፓርድ ኮቬንትሪን ለማሰልጠን ጠይቋል !

እንግሊዛዊው አሰልጣኝ ፍራንክ ላምፓርድ የሻምፒዮን ሺፑን ክለብ ኮቬንትሪ ሲቲን በአሰልጣኝነት ለመረከብ ማመልከቻ ማስገባቱ ተገልጿል።

የሻምፒዮን ሺፑ ክለብ ኮቬንትሪ ሲቲ ከቀናት በፊት የቡድኑን ዋና አሰልጣኝ ማርክ ሮቢንስ አሰናብተዋል።

ፍራንክ ላምፓርድ አሰልጣኙን በመተካት ኮቬንትሪ ሲቲን ለማሰልጠን ጥያቄ ማቅረቡን የክለቡ ፕሬዝዳንት ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንቱ ሲናገሩም ላምፓርድን ጨምሮ በርካታ ትልልቅ አሰልጣኞች አመልክተዋል ነገርግን እስካሁን ከውሳኔ አልደረስንም በቀጣይ እንገመግማለን ብለዋል።

@Tikvahethsport    @kidusyoftahe
የባርሴሎና እና ማድሪድ ታሪካዊ ተጨዋቾች !

የሪያል ማድሪድ ታሪካዊ ተጨዋቾች ከባርሴሎና ታሪካዊ ተጨዋቾች ጋር የእግርኳስ ጨዋታ ሊያደርጉ መሆኑ ተገልጿል።

የሁለቱ ክለቦች ታሪካዊ ተጨዋቾች ጨዋታ እሁድ ታህሣሥ 6/2017 ዓ.ም ጃፓን ቶኪዮ ላይ እንደሚደረግ ይፋ ሆኗል።

አንድሬስ ኢኔስታ ፣ ዣቪ ፣ ማሼራኖ እና ራፋ ማርኩዌዝ ጫማቸውን ከሰቀሉ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ለባርሴሎና ታሪካዊ ተጨዋቾች እንደሚሰለፉ ተገልጿል።

@Tikvahethsport          @kidusyoftahe
ማርቲን ኦዴጋርድ ወደ ክለቡ ይመለሳል !

የመድፈኞቹ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ማርቲን ኦዴጋርድ የሀገሩ ኖርዌይ ብሔራዊ ቡድን ስብስብን በመልቀቅ ወደ ክለቡ እንደሚመለስ ተገልጿል።

ማርቲን ኦዴጋርድ በሀገሩ ብሔራዊ ቡድን የህክምና ባለሙያዎች ከተካሄደለት ምርመራ በኋላ ወደ ክለቡ እንዲመለስ መደረጉ ተዘግቧል።

ተጨዋቹ ጉዳዩን አስመልክቶ " ከህክምና ባለሙያዎች ጋር ካደረግኩት ውይይት በኋላ ጨዋታዎችን ለማድረግ በቂ ሁኔታ ላይ እንዳልሆንኩ ተገልፆልኛል" ብሏል።

"ለሀገሬ መጫወት ያስደስተኛል ሆኖም አሁን ላይ ይሄን ማድረግ አልችልም በቡድን አጋሮቼ እምነት አለኝ በቀጣይ ጨዋታዎች ለእነሱ መልካሙን እመኛለሁ" ማርቲን ኦዴጋርድ

@Tikvahethsport        @kidusyoftahe
ሮናልዶ አንድ ሺ ግቦችን ማስቆጠር ያስባል ?

የአምስት ጊዜ የባሎን ዶር አሸናፊው ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ በቀጣይ 1,000 ግቦችን የማስቆጠር ኢላማውን ላያሳካ እንደሚችል ጠቁሟል።

“ ስለረጅም ጊዜ እቅድ ማሰብ አልፈልግም “ ያለው  ሮናልዶ ምናልባት 1,000 ግቦችን ላያስቆጥር እንደሚችል ገልጿል።

“ 1,000 ግቦችን ካስቆጠርኩ በጣም ጥሩ ነው ካልሆነም አሁንም የአለም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ነኝ።“ ሲል ክርስቲያኖ ሮናልዶ ተናግሯል።

@Tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
🤖 #Wanaw_Bot 🤖

💬 ምላሽ ቶሎ እየደረስዎት አይደለም? በማይተኛው #የዋናው ቴሌግራም ቦት ጊዜዎን ቆጥበው ትዕዛዝዎን በፍጥነት ያስገቡ!

📌 ወደ ዋናው ቦት ለመሄድ 👉
Wanaw Bot

Call us!
📞 8289


Follow Us
Website | Instagram | Facebook | TikTok | X | Youtube | Telegram

🏅 ዋናው ወደፊት...
✈️ ሽንፈት አልባ በረራዎች ✈️
ያለሃሳብ ይወራረዱ፣ይብረሩ፣ በአቪዬተር ያሸንፉ!
በየመሃሉ ላልተሳኩ ውርርድዎ 10% ተመላሽ ከቤቲካ!
እስከ ጥቅምት 10 ድረስ በየሳምንቱ!
አሁኑኑ Betika.et ላይ ይወራረዱ!
ቤቲካ የአሸናፊዎች ቤት
2024/11/15 09:22:07
Back to Top
HTML Embed Code: