Telegram Web Link
Forwarded from WANAW SPORT
🎁 #ይገምቱ#ይሸለሙ!

🏆  በዛሬው ምሽት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 6ኛ ሳምንት ተጠባቂ ፍልሚያ ማን ያሸንፋል?

⚽️ ማንቺስተር ዩናይትድ
ወይስ ቶተንሀም ⚽️

💬 ግምትዎን #በገፃችን ኮሜንት ላይ ብቻ ያስቀምጡልን!

⚠️ የውድድሩ ህጎች፦
👉🏾 የጨዋታውን አሸናፊ ክለብ እስከ የግብ መጠኑ #በትክክል ቀድመው የሚገምቱ #2 ተከታታዮቻችን የዋናውን ማልያዎች ይሸለማሉ።
👉🏾 የዋናውን ማህበራዊ ገፆች መከተል፣ መወዳጀትና ማጋራት ይጠበቅቦታል።
👉🏾 የተስተካከሉና ተደጋጋሚ መልሶች በፍፁም ተቀባይነት የላቸውም።
👉🏾 አንድ ተሳታፊ ከሁለት ጊዜ በላይ አይሸለምም፡፡

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
🅱️🔠🔠🔠🔠🔠🅱️🔠🔠🔠

🍏Original iPHONE, Samsung & Tab watch’s አዳዲስ እንዲሁም ያገለገሉ ስልኮችን በተመጣጣኝ ዋጋ እና ያሎት ስልክ ላይ በመጨመር ከበቂ ዋስትና እና ጥገና ጋር እኛው ጋር ያገኛሉ ።

📢Telegram Channel
📱https://www.tg-me.com/+rKw6vNZJp49kOWM0
ቀድመው ይደውሉ 👇
Contact us ☎️
📲+251911120707
+251904818881
📍ቦሌ መድሃኒአለም
" ከሊጉ አሰልጣኞች ጋር ጓደኛ አይደለሁም “ ቴንሀግ

የቀያይ ሴጣኖቹ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ከየትኛውም የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ አሰልጣኝ ጋር ጓደኛ አለመሆናቸውን ገልጸዋል።

" ከየትኛውም የፕርሚየር ሊግ አሰልጣኝ ጋር ጓደኛ አይደለሁም ባልደረቦች ብቻ ነን ፣ ከጨዋታ በኋላ የመገናኘት ባህል አለ ነገርግን የሚዲያ ግዴታ ነው እየጠፋ ያለ ነገር ነው “ ሲሉ ኤሪክ ቴንሀግ ተናግረዋል።

“ ከምክትል አሰልጣኞች ጋር በጋራ ነው የምንሰራው የጋራ ስራ ነው በእቅዶቹ እንስማማለን የመጨረሻውን ውሳኔ እኔ አሳልፋለሁ እቅዱ የጋራ ነው።" ቴንሀግ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ

12:30 ማንችስተር ዩናይትድ ከ ቶተንሀም

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሀሪ ማጓየር ጉዳት አጋጥሞታል !

እንግሊዛዊው የማንችስተር ዩናይትድ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሀሪ ማጓየር በልምምድ ወቅት ጉዳት እንዳጋጠመው ተገልጿል።

በዚሁ ጉዳት ምክንያት ማንችስተር ዩናይትድ ዛሬ ከቶተንሀም ጋር የሚያደርገው ተጠባቂ ጨዋታ እንደሚያመልጠው ተነግሯል።

በዛሬው ጨዋታ የቀያይ ሴጣኖቹን የኋላ መስመር ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ እና ማትያስ ዴሊት ከዲያጎ ዳሎት እና ማዝራዊ ጋር ይመሩታል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አስቶን ቪላ ነጥብ ተጋርቷል !

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ስድስተኛ ሳምንት መርሐግብር አስቶንቪላ ከኢፕስዊች ታውን ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቋል።

የአስቶን ቪላን ግቦች ኦሊ ዋትኪንስ እና ሮጀርስ ከመረብ ሲያሳርፉ ለኢፕስዊች ታውን ዴላፕ 2x አስቆጥሯል።

የሊግ ደረጃቸው ?

5️⃣ኛ. አስቶን ቪላ :- 13 ነጥብ
1️⃣5️⃣. ኢፕስዊች ታውን :- 4 ነጥብ

ቀጣይ መርሐግብር ምን ይመስላል ?

እሁድ አስቶንቪላ ከ ማንችስተር ዩናይትድ

ቅዳሜ ኢፕስዊች ከ ኤቨርተን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ሁሉም አጨዋወት ደካማ ጎን አለው “ ቴንሀግ

የቀያይ ሴጣኖቹ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የዛሬ ተጋጣሚያቸው ቶተንሀምን የአጨዋወት ዘይቤ እንደሚወዱት ገልጸዋል።

“ የቶተንሀምን አጨዋወት እወደዋለሁ ጠንካራ እና የሚሰብ ጨዋታ ነው የሚያደርጉት ነገርግን ሁሉም አጨዋወት የራሱ ድክመቶች አሉት “ ሲሉ ኤሪክ ቴንሀግ ተናግረዋል።

“ በፈርናንዴዝ እተማመናለሁ በየአመቱ ተመሳሳይ ነው በአመቱ መጨረሻ ፈርናንዴዝ በሊጉ ከሁሉም በላይ የግብ እድል ፈጥሮ ብዙ ግብ ያስቆጥራል “ ቴንሀግ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
3 ' ማንችስተር ዩናይትድ 0 - 1 ቶተንሀም

ጆንሰን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
11 ' ማንችስተር ዩናይትድ 0 - 1 ቶተንሀም

                             ጆንሰን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
42 ' ማንችስተር ዩናይትድ 0 - 1 ቶተንሀም

                             ጆንሰን

🟥 የማንችስተር ዩናይትዱ አምበል ብሩኖ ፈርናንዴዝ ቀይ ካርድ ተመልክቷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የእረፍት ሰዓት !

በሳምንቱ ተጠባቂ መርሐ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ ከቶተንሀም ጋር እያደረጉ የሚገኙትን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት እየመሩ ወደ መልበሻ ቤት አምርተዋል።

የቶተንሀምን የመሪነት ግብ ጆንሰን ከመረብ አሳርፏል።

🟨 የቢጫና ቀይ ካርድ የተመለከቱ ተጫዋቾች እነማን ናቸው ?

- በመጀመሪያው አጋማሽ በማንችስተር ዩናይትድ በኩል ማዝራዊ ፣ ማውንት እና ዲያጎ ዳሎት በቶተንሀም በኩል ጆንሰን የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክተዋል።

🟥 በተጨማሪም የማንችስተር ዩናይትዱ አምበል ብሩኖ ፈርናንዴዝ ቀይ ካርድ ተመልክቷል።

የጨዋታው የኳስ ቁጥጥር ምን ይመስላል ?

- በመጀመሪያው አጋማሽ ቶተንሀም 63% - 37% የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ነበራቸው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ብሩኖ ፈርናንዴዝ ምን ያህል ጨዋታ ያመልጠዋል ?

የቀያይ ሴጣኖቹ አምበል ብሩኖ ፈርናንዴዝ ከቶተንሀም ጋር እየተደረገ በሚገኘው ጨዋታ የቀይ ካርድ መመልከቱ ይታወቃል።

ብሩኖ ፈርናንዴዝ በቀጣይ ክለቡ የሚያደርጋቸው ሶስት የሊጉ መርሐ ግብሮች እንደሚያመልጡት ይጠበቃል።

በዚህም መሰረት :-

- አስቶን ቪላ ከ ማንችስተር ዩናይትድ

- ማንችስተር ዩናይትድ ከ ብሬንትፎርድ

- ዌስትሀም ከ ማንችስተር ዩናይትድ በሚያደርጉት ጨዋታዎች ለቡድኑ ግልጋሎት የማይሰጥ ይሆናል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
47 ' ማንችስተር ዩናይትድ 0 - 2 ቶተንሀም

                             ጆንሰን
ኩሉሴቭስኪ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
54 ' ማንችስተር ዩናይትድ 0 - 2 ቶተንሀም

                             ጆንሰን
                             ኩሉሴቭስኪ

- የቶተንሀም ተጓዥ ደጋፊዎች አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግን “ ጠዋት ትሰናበታለህ " የሚል ዝማሬ እያሰሙ ይገኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
77 ' ማንችስተር ዩናይትድ 0 - 3 ቶተንሀም

                             ጆንሰን
                             ኩሉሴቭስኪ
ሶላንኬ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
85 ' ማንችስተር ዩናይትድ 0 - 3 ቶተንሀም

                             ጆንሰን
                             ኩሉሴቭስኪ
                             ሶላንኬ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማንችስተር ዩናይትድ ሽንፈት አስተናግዷል !

ማንችስተር ዩናይትድ ከቶተንሀም ጋር ያደረጉትን የፕርሚየር ሊግ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር 3ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፈዋል።

የቶተንሀምን የማሸነፊያ ግቦች ዶምኒክ ሶላንኬ ፣ ብሬናን ጆንሰን እና ኩሉሴቭስኪ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የሚመራው ማንችስተር ዩናይትድ በውድድር ዘመኑ ሶስተኛ የሊግ ሽንፈቱን አስተናግዷል።

ፖርቹጋላዊው አማካይ ብሩኖ ፈርናንዴዝ በማንችስተር ዩናይትድ ቆይታው የመጀመሪያ ቀይ ካርድ ተመልክቷል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

8️⃣ኛ ቶተንሀም :- 10 ነጥብ
1️⃣2️⃣ኛ ማንችስተር ዩናይትድ :- 7 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታዎች ?

እሁድ አስቶን ቪላ ከ ማንችስተር ዩናይትድ

እሁድ ብራይተን ከ ቶተንሀም

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ስር ክለቡ ወደ ኃላ እየተጓዘ ነው “

የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋቾች በዛሬው ጨዋታ ቡድኑ ካስመዘገበው ውጤት በኃላ ሀሳበቸውን አካፍለዋል።

የቀድሞ ተጫዋች አሽሊ ያንግ “ ዩናይትዶች በሜዳ ላይ ያላቸውን አልሰጡም “ ሲል “ ምንም አይነት ፍላጎት አላሳዩም “ ብሏል።

አሽሊ ያንግ በተጨማሪም “ ቡድኑን በሜዳ ላይ የሚመራ ተጫዋች የለም ፣ ቶተንሀም በሜዳው የሚጫወት ይመስል ነበር “ በማለት ተናግሯል።

ጋሪ ኔቭል በበኩሉ “ የመጀመሪያ አጋማሽ የቡደ‍ኑ እንቅስቃሴ መጥፎ ነበር “ ሲል ተደምጧል።

የቀድሞ የመሐል ተከላካይ ሚኬል ሲልቬስተር የክለቡን ወቅታዊ ሁኔታ ሲተች “ ክለቡ በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ስር ወደ ኃላ እየተጓዘ ነው “ ሲል ሁኔታውን ገልፆል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
2024/10/01 22:29:16
Back to Top
HTML Embed Code: