Telegram Web Link
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
Forwarded from WANAW SPORT
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሰዎ!

ዋናው የስፖርት አልባሳት ብራንድ

Instagram | Facebook | TikTok

🏅ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
#EthPL

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የ 2017 የውድድር ዘመን ሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ፋሲል ከነማ ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የመቐለ 70 እንደርታን ግብ ያሬድ ብርሀኑ ከመረብ ሲያሳርፍ ቢኒያም ላንቃሞ ፋሲል ከነማን አቻ ማድረግ ችሏል።

ቀጣይ መርሐ ግብራቸው ምን ይመስላል ?

ሰኞ ⏩️  ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ መቐለ 70 እንደርታ

ማክሰኞ ፋሲል ከነማ ከ ስሁል ሽረ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ዩናይትድ ከፈለገኝ እመለሳለሁ “ ሶልሻየር

የቀድሞው የቀያይ ሴጣኖቹ ተጨዋች እና አሰልጣኝ ኦሌ ገነር ሶልሻየር ማንችስተር ዩናይትድ በድጋሜ አድል የሚሰጣቸው ከሆነ እንደሚቀበሉ ገልጸዋል።

“ ሌሎች አሰልጣኞች ስለያዙት ቦታ መናገር አልፈልግም “ ያሉት አሰልጣኝ ኦሌ ገነር ሶልሻየር “ ነገርግን ማንችስተር ዩናይትድ በድጋሜ እንዳሰለጥን ከጠየቀኝ እቀበላለሁ “ ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ የቡድኑ ችግር በቂ ግብ አለማስቆጠሩ ነው “ ቴንሀግ

የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ቡድናቸው እሁድ ከቶተንሀም ጋር ከሚያደርገው ጨዋታ በፊት ከጋዜጠኞች ጋር ቆይታ አድርገዋል።

ኤሪክ ቴንሀግ ካነሷቸው ሀሳቦች መካከል :-

- " አዲስ ከጉዳት የተመለሰ ተጨዋች የለንም በቶተንሀም ጨዋታ የሚኖረን የቡድን ስብስብ በመጨረሻ ጨዋታችን ካለን ጋር ተመሳሳይ ነው።

- የቡድኑ ችግር በቂ ግብ አለማስቆጠር ነው ማስቆጠር የሚችሉ ተጨዋቾች አሉን ነገርግን ከምንፈጥራቸው የግብ አድሎች አንፃር በበቂ ሁኔታ አላስቆጠርንም።

- ሁሉም ቡድን ጠንካራ እና ደካማ ጎን አለው ቶተንሀም አጥቅቶ የሚጫወት ቡድን ነው ጥሩ መሆን አለብን።

- ከቶተንሀም ጋር የምናደርገው ጨዋታ ጠንካራ እና አዝናኝ ይሆናል።

- እስካሁን ሁለት ዋንጫዎችን አሳክተናል በዚህ አመት ተጨማሪ ዋንጫዎችን ማሸነፍ እንፈልጋለን።" ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EthPL

በ 2017 የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ቀጣይ መርሐ ግብራቸው ምን ይመስላል ?

ሰኞ ⏩️  ኢትዮጵያ መድን ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ

እሮብ ኢትዮጵያ ቡና ከ ሀዋሳ ከተማ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የዩናይትድ እና ቶተንሀምን ጨዋታ ማን ይመራል ?

የፊታችን እሁድ በማንችስተር ዩናይትድ እና ቶተንሀም መካከል የሚደረገውን የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ስድስተኛ ሳምንት መርሐግብር የሚመሩት ዳኛ ታውቀዋል።

እሁድ አመሻሽ 12:30 በኦልድትራፎርድ ስታዲየም የሚደረገውን ተጠባቂ ጨዋታ ክሪስ ካቫናህ በመሐል ዳኝነት እንደሚመሩት ይፋ ተደርጓል።

ጨዋታውን ማን ያሸንፋል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቶተንሀም ድል አድርጓል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም ከካራባህ ጋር ያደረገውን የዩሮፓ ሊግ የመጀመሪያ ጨዋታ 3ለ0 በሆነ ውጤ ማሸነፍ ችሏል።

የቶተንሀምን የማሸነፊያ ግቦች ብሬናን ጆንሰን ፣ ፓፔ ሳር እና ዶምኒክ ሶላንኬ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ቶተንሀም በጨዋታው ገና በስምንተኛው ደቂቃ ተከላካያቸው ራዱ ድራጉሲን በቀይ ካርድ መውጣቱን ተከትሎ በአስር ተጨዋቾች ጨዋታውን ለመጨረስ ተገደዋል።

በሌላ ጨዋታ ሮማ ከስፔኑ ክለብ አትሌቲክ ቢልባኦ ጋር ያደረገውን የዩሮፓ ሊግ የመጀመሪያ ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቋል።

የሌሎች የዩሮፓ ሊግ ጨዋታዎች ውጤት ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
iPhone 16 Promax
iPhone 16 Pro
iPhone 16 Plus
iPhone 16
Available Now!

0925927457 @eBRO4
0953964175 @heymobile
@heyonlinemarket
⚽️አጓጊው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ስድስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች!

👉 ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት ለመከታተል ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!

👉 የዲኤስቲቪን ዲኮደር በ1,199 ብር ከ1 ወር ነፃ የሜዳ ፓኬጅ ጋር ያገኛሉ።

የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://bit.ly/2WDuBLk

#PremierLeagueAllonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvSelfServiceET
እንኳን ለብርሀነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ!

መልካም የመስቀል በዓል!
ጁቬንቱስ ግብ ያልተቆጠረበት ክለብ ሆኗል !

የሴርያው ክለብ ጁቬንቱስ ከአምስቱ ታላላቅ የአውሮፓ ሊጎች ባደረጋቸው የሊግ መርሐ ግብሮች ምንም ግብ ያላስተናገደ ብቸኛው ክለብ መሆኑ ተገልጿል።

ጁቬንቱስ በዘንድሮው የውድድር ዘመን ባደረጋቸው አምስት የጣልያን ሴርያ ጨዋታዎች ምንም ግብ ሳይቆጠርበት መውጣት ችሏል።

ጁቬንቱስ ሶስቱን የሴርያ ጨዋታዎች ምንም ግብ ሳያስቆጥር በአቻ ውጤት ሲያጠናቅቅ ሁለቱን በማሸነፍ በዘጠኝ ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ከጠበቅኩት በላይ ነው ያገኘሁት “ ሚኬል አርቴታ

የመድፈኞቹ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የቡድኑን ወጣት አማካይ ኢታን ንዋኔሪ ከጠበቁት በላይ ሆኖ ማግኘታቸውን ገልጸዋል።

አርሰናል ቦልተንን ባሸነፈበት ጨዋታ ግብ ማስቆጠር የቻለው ኢታን ንዋኔሪ “ የዋናው ቡድን አካል ነው በቀጣይ የጨዋታ ጊዜ ያገኛል “ ሲሉ ሚኬል አርቴታ ተናግረዋል።

አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አክለውም የ 17ዓመቱ እንግሊዛዊ አማካይ ኢታን ንዋኔሪን ከጠበቁት በላይ ሆኖ እንዳገኙት ገልጸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EthPL 🇪🇹

በ 2017 የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የውድድር ዘመን ሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ስሑል ሽረ ከሀዋሳ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የስሑል ሽረን ግብ ፋሲል አስማማው ከመረብ ማሳረፍ ሲችል መሐመድ ሱሌይማን በመጨረሻ ደቂቃ በራሱ ላይ ያስቆጠረው ግብ ሀዋሳ ከተማን አቻ አድርጓል።

ከአመታት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የተመለሱት ስሑል ሽረዎች ከመጀመሪያ ሁለት ጨዋታዎች አራት ነጥቦች በመሰብሰብ በግብ ክፍያ በልጠው የሊጉ መሪ መሆን ችለዋል።

ቀጣይ መርሐግብር ምን ይመስላል ?

ማክሰኞ ፋሲል ከነማ ከ ስሁል ሽረ

እሮብ ⏩️ ኢትዮጵያ ቡና ከ ሀዋሳ ከተማ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኒውካስል የተጫዋቹን ግልጋሎት ላያገኝ ይችላል !

ኒውካስል ዩናይትድ ነገ ከማንችስተር ሲቲ ጋር በሚያደርገው የሊግ ጨዋታ የአሌክሳንደር አይሳክን ግልጋሎት ላያገኝ እንደሚችል አሰልጣኝ ኤዲ ሀው ገልጸዋል።

“ አይሳክ አሁንም ጣቱ ላይ የጉዳት ስሜት አለው ለማንችስተር ሲቲ ጨዋታ መድረሱ አጠራጣሪ ነው ሳምንቱን ሙሉ ልምምድ አልሰራም “ ሲሉ አሰልጣኝ ኤዲ ሀው ተናግረዋል።

ኒውካስል ዩናይትድ ነገ 8:30 በሴንት ጄምስ ፓርክ ስታዲየም ከማንችስተር ሲቲ ጋር ተጠባቂ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ካላፊዮሪን ሴርያ ውስጥ ማቆየት አለመቻላችን ያሳዝናል “ የጁቬንቱስ ሀላፊ

የጣልያኑ ክለብ ጁቬንቱስ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ጊንቶሊ አርሰናልን የተቀላቀለው ሪካርዶ ካላፊዮሪ ሴርያ ውስጥ አለመቆየቱ እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል።

“ ካላፊዮሪን ሴርያ ውስጥ ማቆየት አለመቻላችን በጣም ያሳዝናል “ ሲሉ የገለፁት ስፖርቲንግ ዳይሬክተሩ “  የእሱ መልቀቅ ለእኛ ለምንፈልገው ክለቦች ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ለሊጉ መጥፎ ነው “ ብለዋል።

መድፈኞቹ ሪካርዶ ካላፊዮሪን 38 ሚልዮን ፓውንድ በሚደርስ የዝውውር ሒሳብ ከቦሎኛ ማስፈረማቸው አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሊቨርፑል ግብ ጠባቂው ወደ ሜዳ ይመለሳል !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ቁጥር አንድ ግብ ጠባቂ አሊሰን ቤከር ልምምድ መስራቱን አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ገልጸዋል።

“ አሊሰን ልምምድ ሰርቷል ለጨዋታ ብቁ ነው ብለን እናስባለን እሱን በድጋሜ በማግኘታችን ደስተኞች ነን “ ሲሉ አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ተናግረዋል።

ብራዚላዊው ግብ ጠባቂ አሊሰን ቤከር በጉዳት ምክንያት ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ለሊቨርፑል ግልጋሎት እንዳልሰጠ ይታወሳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባርሴሎና ከዩኤፋ ቅጣት ተጥሎባቸዋል !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ከሞናኮ በነበረ የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ደጋፊዎቹ የዘረኝነት ባህሪ አሳይተዋል በሚል ከአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ቅጣት እንደተጣለባቸው ተገልጿል።

በዚህም መሰረት ባርሴሎና በቀጣይ ከሜዳው ውጪ ለሚያደርገው አንድ የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ትኬቶች እንዳይሸጥ እና 10,000 ዩሮ ቅጣት እንደተጣለበት ተነግሯል።

ይህንንም ተከትሎ ባርሴሎና በቀጣይ ከሜዳው ውጪ ከሬድ ስታር ቤልግሬድ ጋር የሚያደርገውን የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ያለ ተጓዥ ደጋፊ ለማድረግ ይገደዳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ኒውካስል የተጫዋቹን ውል ማራዘም ይፈልጋል ! ኒውካስል ዩናይትድ የእንግሊዛዊውን የፊት መስመር ተጨዋች አንቶኒ ጎርደን ኮንትራት ማራዘም እንደሚፈልጉ ተገልጿል። በአሰልጣኝ ኤዲ ሀው የሚመራው ኒውካስል ዩናይትድ አንቶኒ ጎርደን ከእረፍት ሲመለስ ኮንትራቱን ለማራዘም ንግግር ለመጀመር ማሰባቸው ተነግሯል። ኒውካስል ዩናይትድ ተጨዋቹ በመጀመሪያ አመቱ በክለቡ ላሳየው ጥሩ ብቃት መሸለም እንደሚፈልጉ ተዘግቧል።…
ኒውካስል የተጫዋቹን ውል ለማራዘም ተስማማ !

ኒውካስል ዩናይትድ የእንግሊዛዊውን የፊት መስመር ተጨዋች አንቶኒ ጎርደን ኮንትራት ለማራዘም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

በአሰልጣኝ ኤዲ ሀው የሚመራው ኒውካስል ዩናይትድ የአንቶኒ ጎርደንን ኮንትራት እስከ 2029 ለማራዘም መስማማቱ ተነግሯል።

እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጨዋች አንቶኒ ጎርደን በአዲሱ ውል መሰረት የኒውካስል ዩናይትድ ከፍተኛ ተከፋይ እንደሚሆን ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/30 20:24:49
Back to Top
HTML Embed Code: