Telegram Web Link
“ ከሌላ ክለብ ብጫወት እመርጥ ነበር “ ቴንሀግ

የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ነገ በዩሮፓ ሊግ አሰልጣኝነት የጀመሩበትን ክለብ ትዌንቴ መግጠም ከባድ እንደሚሆንባቸው ገልጸዋል።

“ ከሌላ ክለብ ብጫወት እመርጥ ነበር “ ያሉት አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የምትወደውን ነገር መጉዳት ጥሩ አይደለም በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

አሰልጣኙ አያይዘውም ሉክ ሾው ከብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ እረፍት በኋላ ወደ ሜዳ ሊመለስ እንደሚችል ጠቁመዋል።

በክሪስታል ፓላስ ጨዋታ ራሽፎርድን ተጠባባቂ በማድረጋቸው መተቸታቸው “ አግባብ አይደለም “ ያሉት ኤሪክ ቴንሀግ " ሰው የመተቸት መብት አለው ግን ማብራሪያ ከሰጠሁ እኔን ማመን አለብት “ ብለዋል።

ቡድናቸው በዚህ አመት የዩሮፓ ሊግ ዋንጫን ማሸነፍ አላማው መሆኑን አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ አክለው ገልፀዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የዚነዲን ዚዳን ልጅ ጫማውን ሰቅሏል !

የፈረንሳዊው አሰልጣኝ ዚነዲን ዚዳን ልጅ ኢንዞ ዚዳን በ 29ዓመቱ ከእግርኳስ ራሱን ማግለሉን በይፋ አስታውቋል።

በአማካይ ስፍራ የሚጫወተው ኢንዞ ባለፈው አመት ከስፔን ሶስተኛ ዲቪዚዮኑ ክለብ ፉንላብራዳ ጋር ከተለያየ ወዲህ ክለብ አለማግኘቱን ተከትሎ ጫማውን ለመስቀል መወሰኑ ተገልጿል።

ተጨዋቹ በእግርኳስ ህይወቱ 203 ጨዋታዎች በማድረግ አስራ ሶስት ግቦች አስቆጥሮ ሀያ አራት አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

ተጨዋቹ በቀጣይ ከእግርኳስ በመራቅ በግል ስራ ለመሰማራት መወሰኑን የስፔን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
🔊 ለስፖርት ትጥቅ ፍላጎትዎ #ዋናው ብለው ያግኙን!

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ወይም በቴሌግራም ቦት @WanawSportBot ይዘዙን።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
TIKVAH-SPORT
የኒውካስል ካራባኦ ካፕ ጨዋታ ተራዘመ ! ኒውካስል ዩናይትድ ነገ ከዌምብለደን ጋር ሊያደርገው የነበረው የካራባኦ ካፕ ሶስተኛ ዙር ጨዋታ ለሌላ ጊዜ መራዘሙ ይፋ ተደርጓል። ጨዋታው የተራዘመው በዌምብለደን ቼሪ ሬድ ሪኮርድስ ስታዲየም በገጠመ የጎርፍ አደጋ ምክንያት ስታዲየሙ ጉዳት ስለደረሰበት መሆኑ ተገልጿል። አሰልጣኝ ኤዲ ሀው ጨዋታውን አስመልክቶ ዛሬ ጠዋት ሊሰጡ የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ መሰረዙ…
ኒውካስል ለተጋጣሚው የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል !

ኒውካስል ዩናይትድ ስታዲየሙ በጎርፍ አደጋ ለተጎዳበት የካራባኦ ካፕ ሶስተኛ ዙር ተጋጣሚው ዌምብለደን ክለብ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጋቸው ተገልጿል።

ሁለቱ ክለቦች ዛሬ ሊያደርጉት የነበረው የካራባኦ ካፕ ጨዋታ የዌምብለደን ቼሪ ሬድ ሪኮርድስ ስታዲየም በገጠመው የጎርፍ አደጋ ምክንያት መራዘሙ ይታወቃል።

ኒውካስል ዩናይትድ ዌምብለደን ስታዲየሙን ማስጠገኛ እንዲሆነው 15,000 ፓውንድ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጋቸው ተገልጿል።

ጨዋታው በቀጣይ በኒውካስል ዩናይትድ ስታዲየም ሴንት ጄምስ ፓርክ እንደሚደረግ ሲገለፅ ዌምብለደን ከስታዲየሙ ገቢ 45% እንደሚያገኙ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ባሎን ዶር ከቪንሰስ ሌላ የሚገባው የለም “ ኔይማር

ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኔይማር ቪንሰስ ጁኒየር የባሎን ዶር ሽልማት እንደሚገባው በሰጠው አስተያየት ገልጿል።

“ ቪንሰስ ጁኒየር ባሎን ዶር እንዲያሸንፍ አግዘዋለሁ “ የሚለው ኔይማር “ ከቪንሰስ ሌላ የሚገባው እጩ የለም “ በማለት ተናግሯል።

“ ቪንሰስ ጁኒየር ባሎን ዶር የሚገባው ተጨዋች ነው ምክንያቱም እሱ ተፋላሚ ነው ፤ አሁን ላይ የሁላችንም አርአያ መሆን ችሏል።“ ሲል ኔይማር አስተያየቱን ሰጥቷል።

“ ቪንሰስ ጁኒየር በህይወቱ ብዙ ችግሮች አጋጥመውታል ነገርግን የሚጠበቅበትን ሁሉ ተወጥቷል ትችቶቹን ሁሉ አሸንፏል።“ ኔይማር

የባሎን ዶር ሽልማት ስነ-ስርዓት ሰኞ ጥቅምት 18/2017 ዓ.ም ሲካሄድ ቪንሰስ ጁኒየር ፣ ሮድሪ ፣ ቤሊንግሀም እና ዳኒ ካርቫል የአሸናፊነት ግምት አግኝተዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ሮድሪ ባሎን ዶር ይገባዋል “ አሰልጣኝ ጆዜ ቦርዳላስ

የስፔኑ ክለብ ሄታፌ አሰልጣኝ ጆዜ ቦርዳላስ ሮድሪ የዘንድሮው የባሎን ዶር ሽልማት እንደሚገባው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

“ ሮድሪ አስደናቂ የውድድር ዘመን አሳልፏል “ ያሉት አሰልጣኝ ጆዜ ቦርዳላስ “ የባሎን ዶር ሽልማት ይገባዋል እንደሚሰጠው ተስፋ አደርጋለሁ “ በማለት ተናግረዋል።

ነገ ከባርሴሎና ጋር ስላለባቸው ጨዋታ ያነሱት አሰልጣኙ “ እኛ ባርሴሎናን አንፈራም ሌሎች ክለቦችንም እንዲሁ “ በማለት ገልጸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ በአለም አቀፍ ደረጃ ዩናይትድ ከሙኒክ ትልቅ ነው “

የማንችስተር ዩናይትድ የመስመር ተጨዋች ናስር ማዝራዊ ክለቡን በአነስተኛ የዝውውር ሒሳብ መቀላቀሉ ጫናዎች እንደቀነሱለት ገልጿል።

“ ለእኔ ጥሩ ስራ ሆኖልኛል ምክንያቱም ውድ ዋጋ አልወጣብኝም ጥሩ ጅማሮም አለኝ ፤ ለደጋፊዎቹ ጥሩ ፊርማ ነው ብለው ለማሰብ ቀላል ሆኖላቸዋል።“ሲል ናስር ማዝራዊ ተናግሯል።

ከዩናይትድ እና ባየር ሙኒክ ትልቁ ማን ነው የሚል ጥያቄ የቀረበለት ተጨዋቱ “ ለማወዳደር ከሞከርክ አንዱን ትልቅ አንዱን ትንሽ ማድረግ አትችልም ነገርግን በአለም አቀፍ ደረጃ ዩናይትድ ትልቅ ክለብ ነው “ ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማድሪድ ለኤንድሪክ ጎል እስከ መቼ ይከፍላል ?

ሪያል ማድሪድ ብራዚላዊውን ወጣት አጥቂ ኤንድሪክ ከፓልሜራስ ሲያስፈርሙ በኮንትራቱ ውስጥ ግብ ሲያስቆጥር ክፍያ የሚፈፅሙበት ውል መካተቱ ይታወቃል።

የፓልሜራስ አካዳሚ ዳይሬክተር ጇ ፓውሎ ስለ ውሉ ሲያብራሩ ኤንድሪክ ለሪያል ማድሪድ ጎል ሲያስቆጥር እና አመቻችቶ ሲያቀበል ገንዘብ እንቀበላለን ብለዋል።

ዳይሬክተሩ ሲናገሩም ኤንድሪክ አምስት ጎሎች ሲያስቆጥር 1.5 ሚልዮን ዩሮ ያስገኝልናል ብለዋል።

ይህ ክፍያ የሚቀጥለው ኤንድሪክ የሚያስቆጥራቸው ግቦች 60 ሚልዮን ዩሮ እስከሚደርሱ መሆኑን ዳይሬክተሩ አያይዘው ገልጸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፎች !

3:45 ቼልሲ ከ ባሮው

3:45 ማንችስተር ሲቲ ከ ዋትፎርድ

#CarabaoCup

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
5 '

ማንችስተር ሲቲ 1-0 ዋትፎርድ

ዶኩ

ቼልሲ 0-0 ባሮው

#CarabaoCup

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ሮድሪ ለአጭር ጊዜ ከሜዳ ይርቃል “ ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ሮድሪ በጉዳት ምክንያት ከሜዳ የሚርቀው ለአጭር ጊዜ ሊሆን እንደሚችል ገልጸዋል።

አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ አያይዘውም “ የሀኪሞችን የመጨረሻ ውጤት እስካሁን እየጠበቅን ነው “ ሲሉ ስለ ሁኔታው አስረድተዋል።

ሮድሪ ትላንት ምሽት ለተጨማሪ ምርመራዎች ወደ ስፔን ባርሴሎና ማቅናቱ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
10 '

ቼልሲ 1 - 0 ባሮው

ንኩንኩ

ማንችስተር ሲቲ 1-0 ዋትፎርድ

ዶኩ

#CarabaoCup

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
15 '

ቼልሲ 2 - 0 ባሮው

ንኩንኩ

ማንችስተር ሲቲ 1-0 ዋትፎርድ

ዶኩ

#CarabaoCup

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
30 '

ቼልሲ 3 - 0 ባሮው

ንኩንኩ
ፋርማን ( በራስ ላይ )

ማንችስተር ሲቲ 1-0 ዋትፎርድ

ዶኩ

#CarabaoCup

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
40 '

ማንችስተር ሲቲ 2-0 ዋትፎርድ

ዶኩ
ኑኔስ

ቼልሲ 3 - 0 ባሮው

ንኩንኩ
ፋርማን ( በራስ ላይ )

#CarabaoCup

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
48 '

ቼልሲ 4 - 0 ባሮው

ንኩንኩ
ፋርማን ( በራስ ላይ )
ኔቶ

ማንችስተር ሲቲ 2-0 ዋትፎርድ

ዶኩ
ኑኔስ

#CarabaoCup

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
77 '

ቼልሲ 5 - 0 ባሮው

ንኩንኩ
ፋርማን ( በራስ ላይ )
ኔቶ

ማንችስተር ሲቲ 2-0 ዋትፎርድ

ዶኩ
ኑኔስ

#CarabaoCup

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
88 '

ማንችስተር ሲቲ 2-1 ዋትፎርድ

ዶኩ ኢንስ
ኑኔስ

ቼልሲ 5 - 0 ባሮው

ንኩንኩ
ፋርማን ( በራስ ላይ )
ኔቶ

#CarabaoCup

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/27 07:21:20
Back to Top
HTML Embed Code: