Telegram Web Link
TIKVAH-SPORT
የቼልሲ ተጨዋቾች ብስጭት ውስጥ መሆናቸው ተገለጸ ! የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በርካታ ተጨዋቾች በአርጀንቲናዊው ተጨዋች ኢንዞ ፈርናንዴዝ ባህሪ ከፍተኛ ብስጭት ውስጥ ገብተው እንደሚገኙ ተገልጿል። ተጨዋቾቹ ኢንዞ ፈርናንዴዝ ለምን ይህን ያደርጋል የሚል ጥያቄ በመጠየቅ ላይ መሆናቸውን ለክለቡ መልበሻ ቤት ቅርበት ያላቸው የመረጃ ምንጮች ገልጸዋል። የክለቡ መልበሻ ቤት በዚሁ ምክንያት መከፋፈሉ…
ኢንዞ ፈርናንዴዝ ወደ ቡድኑ ልምምድ ተመለሰ !

አርጀንቲናዊው የቼልሲ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኢንዞ ፈርናንዴዝ በቅርቡ ከተፈጠረው ክስተት በኋላ ወደ ክለቡ ልምምድ መመለሱ ተገልጿል።

ኢንዞ ፈርናንዴዝ ወደ ቡድኑ ልምምድ ከተመለሰ በኋላ በአካል የቡድን አጋሮቹን ይቅርታ መጠየቁ ተገልጿል።

በተጨማሪም መፀፀቱን ለመግለጽ በቼልሲ የእርዳታ ፋውንዴሽን በኩል ፀረ ዘረኝነት ላይ ለሚሰሩ የበጎ አድራጎት ተቋማት ትልቅ ድጋፍ ለማድረግ ማሰቡን አሳውቋል።

ኢንዞ ፈርናንዴዝ በቅርቡ በአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ውስጥ ከኮፓ አሜሪካ ድል በኋላ ባሰሙት ዝማሬ ምክንያት ከፍተኛ ተቃውሞ እንደገጠመው አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አርቴታ አማካይ ማስፈረም ይፈልጋሉ !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ዋና አሰልጣኝ ሜኬል አርቴታ በቀጣይ አንድ አማካይ እንዲገዛላቸው እንደሚፈልጉ ተገልጿል።

መድፈኞቹ ለማስፈረም የመጀመሪያ ምርጫቸው የሪያል ሶሴዳዱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሚኬል ሜሪኖ መሆኑ ሲገለፅ ይሁን እንጂ እስካሁን ንግግር አለመጀመራቸው ተዘግቧል።

ተጨዋቹ በሌሎች ክለቦች እየተፈለገ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን በተጨማሪም ሪያል ሶሴዳድ ውሉን እንዲያራዝም ጥያቄ እንዳቀርቡለት ተጠቁሟል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቼልሲ እና ናፖሊ በንግግር ላይ ናቸው ! የጣልያኑ ክለብ ናፖሊ ቤልጂየማዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ሮሜሎ ሉካኩ ለማስፈረም ከቼልሲ ጋር በድርድር ላይ መሆናቸው ተገልጿል። በተቃራኒው ቼልሲዎች በበኩላቸው ናይጄሪያዊውን አጥቂ ቪክቶር ኦሲሜን ከናፖሊ ለማስፈረም በድርድር ላይ መሆናቸው ተነግሯል። ቼልሲዎች ቪክቶር ኦሲሜንን የመግዛት አማራጭ ባካተተ የረጅም ጊዜ ውሰት ውል እንደሚያስፈርሙት ሲገለፅ ናፖሊ…
“ ለኦሲሜን ክብር ሊኖራቹ ይገባል “ ወኪሉ

የናይጄሪያዊው የፊት መስመር አጥቂ ቪክቶር ኦሲሜን ወኪል ካሌንዳ ኦሲሜን ወደ ቼልሲ በውሰት ውል ያመራል ተብሎ መነገሩ ሀሰተኛ መሆኑን ገልጿል።

" ኦሲሜን የተካተተበትን የልውውጥ ዝውውር መረጃ  ተመልክተነዋል ፣ እሱ በቀላል የሚገኝ ተጨዋች ይመስል ነገሩን ቀላል ነው ያደረጉት ፣ ሀሰተኛ ዜና ነው " ሲል ወኪሉ በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

ወኪሉ አክሎም " በቀላሉ ይገኛል የሚሉት ቪክቶር ኦሲሜን በናፖሊ ታሪክ ሶስተኛው ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ነው ፤ ለእሱ ክብር ሊኖራቹ ይገባል " ሲሉ ተናግሯል።

ናፖሊ እና ቼልሲ ቪክቶር ኦሲሜንን የሮሜሉ ሉካኩ የዝውውር አካል ለማድረግ በንግግር ላይ መሆናቸው መዘገቡ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ምባፔ እንደ እኔ ጥሩ አጥቂ አይደለም " ሌዋንዶውስኪ

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና የፊት መስመር አጥቂ ሮበርት ሌዋንዶውስኪ የሪያል ማድሪዱ ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ ከእሱ የተሻለ ጨራሽ አጥቂ እንዳልሆነ ተናግሯል።

ኪሊያን ምባፔ በተለያዩ ቦታዎች ላይ የመጫወት አቅም እንዳለው የገለፀው ሌዋንዶውስኪ " ይሁን እንጂ እሱ እንደ እኔ ጎበዝ አጥቂ መሆኑን እርግጠኛ አይደለሁም " ብሏል።

ፖላንዳዊው አጥቂ ቀጥሎም “ የምባፔ ወደ ላሊጋ መምጣት ለእኔ ጥሩ መነሳሻ ይሆንልኛል በግብ ማስቆጠር አጨራረስ ከእሱ የተሻልኩ ነኝ ብዬ አስባለሁ “ ሲል ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
  🆕 አዳዲስ እንዲሁም በመጠኑ ያገለገሉ ስልኮችን ከተሟላ ዋስትና እና ጥገና ጋር ይዘን ቀርበናል📱ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይጎበኙ

📌 https://www.tg-me.com/sellphone2777

📞  0929008292

📩 inbox @bina27

📍አድራሻ- ቦሌ ከሸገር ህንፃ አጠገብ
ግብፅ ቀጣዩን ዙር ተቀላቀለች !

በ2024 የፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር እግርኳስ ጨዋታ ግብፅ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታዋን ከስፔን ጋር አድርጋ 2ለ1 ማሸነፍ ችላለች።

በዚህም መሰረት ግብፅ በምድቡ ምንም ጨዋታ ሳትሸነፍ በሰባት ነጥቦች የምድቡ የበላይ በመሆን ሩብ ፍፃሜውን መቀላቀል ችለዋል።

ግብፅ በታሪክ ለሶስተኛ ጊዜ ለኦሎምፒክ ሩብ ፍፃሜ ደርሰዋል።

የስፔን ብሔራዊ ቡድን ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ሩብ ፍፃሜ ደርሰዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ የባየር ሌቨርኩሰን ዝውውር ሁለት ደረጃ ከፍ ያልኩበት ነበር “ ዣካ

ስዊዘርላንዳዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ግራኒት ዣካ ባለፈው አመት ከአርሰናል ወደ ባየር ሌቨርኩሰን ያደረገው ዝውውር ደረጃው ከፍ ያለበት እንደነበር ተናግሯል።

ግራኒት ዣካ በንግግሩም “ ባለፈው አመት ከአርሰናል ወደ ባየር ሌቨርኩሰን ያደረግኩት ዝውውር ከደረጃ ዝቅ ያልኩቡት ሳይሆን ሁለት ደረጃዎች ከፍ ያልኩበት ነበር ፤ በዚህ አመት ከባለፈው የተሻለ መስራት አለብን “ ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሞሮኮ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቀለች !

በ2024 የፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር እግርኳስ ጨዋታ አፍሪካዊቷ ሀገር ሞሮኮ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታዋን ከኢራቅ ጋር አድርጋ 3ለ0 ማሸነፍ ችላለች።

የሞሮኮ ኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድን ሁለት የምድብ ጨዋታዎችን በማሸነፍ ምድቡን በበላይነት አጠናቆ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅሏል።

ሞሮኮ ግብፅን በመከተል በፓሪስ ኦሎምፒክ እግርኳስ ውድድር ሩብ ፍፃሜውን የተቀላቀለች ሁለተኛዋ አፍሪካዊት ሀገር መሆን ችላለች።

በምድቡ አርጀንቲና ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ኢንዞ ፈርናንዴዝ ወደ ቡድኑ ልምምድ ተመለሰ ! አርጀንቲናዊው የቼልሲ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኢንዞ ፈርናንዴዝ በቅርቡ ከተፈጠረው ክስተት በኋላ ወደ ክለቡ ልምምድ መመለሱ ተገልጿል። ኢንዞ ፈርናንዴዝ ወደ ቡድኑ ልምምድ ከተመለሰ በኋላ በአካል የቡድን አጋሮቹን ይቅርታ መጠየቁ ተገልጿል። በተጨማሪም መፀፀቱን ለመግለጽ በቼልሲ የእርዳታ ፋውንዴሽን በኩል ፀረ ዘረኝነት ላይ ለሚሰሩ የበጎ አድራጎት ተቋማት…
" የኢንዞን ይቅርታ ሁሉም ተጨዋቾች ተቀብለዋል " ማሬስካ

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ዋና አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ የክለቡ ተጨዋቾች ኢንዞ ፈርናንዴዝ ያቀረበውን ይቅርታ መቀበላቸውን በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።

ክለቡ የኢንዞ ፈርናንዴዝን ሁኔታ በርጋታ መመልከቱን የገለፁት አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ “ ኢንዞ ሁላችንንም በግል አአነጋግሮ ስለጉዳዩ በማብራራት መጥፎ አስቦ እንዳልሆነ አረጋግጦልናል “ ብለዋል።

" ሁሉም ተጨዋቾች ያቀረበውን ማብራሪያ በመቀበል ይቅር ብለውታል “ ያሉት አሰልጣኙ ከትናንት ምሽት ወዲህ ቡድን አብሮነቱን እያሳየ በጋራ እየሰራ ነው ብለዋል።

ፈረንሳዊው ተጨዋች ዊስሌይ ፎፋና በ "X" የማህበራዊ ትስስር ገፁ ከኢንዞ ፈርናንዴዝ ጋር በተያያዘ ቅሬታውን ያቀረበበትን መልዕክት አጥፍቶ ተስተውሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ስሚዝ ሮው የህክምና ምርመራውን አጠናቀቀ !

እንግሊዛዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኤሚል ስሚዝ ሮው ወደ ፉልሀም የሚያደርገውን ዝውውር ለማጠናቀቅ ያደረገውን የህክምና ምርመራውን ማጠናቀቁ ተገልጿል።

ኤሚል ስሚዝ ሮው የፉልሀም ሪከርድ በሆነ 37 ሚልዮን ፓውንድ በሚደርስ የዝውውር ሒሳብ ክለቡን እንደሚቀላቀል ተነግሯል።

ፉልሀም የ 24ዓመቱን ተጫዋች ኤሚል ስሚዝ ሮው በአምስት አመት ኮንትራት ያስፈርሙታል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አልቫሬዝ የሲቲ ቆይታው ያልተረጋገጠ መሆኑን ገለጸ ! አርጀንቲናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ጁሊያን አልቫሬዝ የማንችስተር ሲቲ የወደፊት ቆይታው ያልተረጋገጠ መሆኑን በሰጠው አስተያየት ገልጿል። ባለፈው አመት ብዙ የጨዋታ ጊዜ ማግኘቱን የገለፀው ጁሊያን አልቫሬዝ " ነገርግን በትልቅ ጨዋታዎች መጫወት እፈልጋለሁ ስለወደፊቱ ቆይታዬ ማሰቤን አላቆምኩም “ ብሏል። “ የኦሎምፒክ ውድድር ሲጠናቀቅ የራሴን…
“ አልቫሬዝ የሚፈልገውን አስቦበት ያሳውቀን “ ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው የፊት መስመር ተጨዋች ጁሊያን አልቫሬዝ ስለወደፊት ቆይታው ማሰብ ከፈለገ " አስቦበት ያሳውቀን " ሲሉ ፔፕ ጋርዲዮላ ተናግረዋል።

ጁሊያን አልቫሬዝ ከቀናት በፊት በማንችስተር ሲቲ ስለሚኖረው የወደፊት ቆይታው ቁጭ ብሎ ማሰብ እንደሚፈልግ ተናሮ ነበር።

በጉዳዩ ላይ ምላሽ የተጠየቁት ፔፕ ጋርዲዮላ “ አልቫሬዝ ብዙ ተጫውቷል ተጨማሪ መጫወት ይፈልጋል ጥሩ ነው ፤ ያስብበት እና ምን ማድረግ እንደሚፈልግ ያሳውቀን “ ሲሉ ተናግረዋል።

አልቫሬዝ በበኩሉ “ መጥፎ ነገር አልተናገርኩም ፣ ያልኩት ማሰብ እፈልጋለሁ ነው ይህ ደግሞ ያለ ነገር ነው ፣ ማንችስተር ሲቲ ውስጥ ምቾት እንደተሰማኝ ሁልጊዜ ተናግሬያለሁ ታላቅ ክለብ ነው።"ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Paris2024

ስፔናዊዎቹ የሜዳ ቴኒስ ተጨዋቾች ራፋኤል ናዳል እና ካርሎስ አልካራዝ በፓሪስ ኦሎምፒክ የሜዳ ቴኒስ ጥንድ ውድድር ሁለተኛ ዙር ጨዋታቸውን በድል ተወጥተዋል።

የፈረንሳይ ኦፕን በርካታ ጊዜ በማሸነፍ ባለሪከርዱ ራፋኤል ናዳል እና የወቅቱ የፈረንሳይ ኦፕን አሸናፊ ካርሎስ አልካራዝ ለመጀመሪያ ጊዜ በተጣመሩበት ውድድር ሩብ ፍፃሜ ደርሰዋል።

ራፋኤል ናዳል እና ካርሎስ አልካራዝ ከ ኔዘርላንዳዊዎቹ ዌስሌይ ኮሎፍ እና ግሬክስፖር ያደረጉት የሁለተኛ ዙር ጨዋታ 6-4 ፣ 6-7 እና 10-2 ተጠናቋል።

ስፔናዊያኑ ራፋኤል ናዳል እና ካርሎስ አልካራዝ በሩብ ፍፃሜው ከአሜሪካኖቹ ኡስቲን ክራጂኬች እና ራጄቭ ራም ጋር ይጫወታሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የሞሪንሆው ቡድን ፌነርባቼ ቀጣዩን ዙር ተቀላቀለ !

በአሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ የሚመራው የቱርኩ ክለብ ፌነርባቼ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ቅድመ ማጣሪያ ጥሎ ማለፍ ሶስተኛውን ዙር ተቀላቅለዋል።

የሁለተኛ ዙር የማጣሪያ የመልስ ጨዋታውን በሜዳው ከስዊዘርላንዱ ሉጋኖ ክለብ ጋር ያደረገው ፌነርባቼ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

ፌነርባቼ በድምር ውጤት 6ለ4 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ቀጣዩን ዙር ሲቀላቀል ኤዲን ዤኩ በሁለቱ ጨዋታዎች አራት ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።

ፌነርባቼ በሚቀጥለው ዙር ማጣሪያ ጨዋታ ከፈረንሳዩ ክለብ ሊል ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ዩናይትድ ተጨዋች ለማስፈረም እያነጋገረ ነው ! ማንችስተር ዩናይትድ የአርሰናሉን ታዳጊ የፊት መስመር አጥቂ ቺዶ ኦቢ ማርቲን ለማስፈረም ንግግር ላይ መሆናቸው ተገልጿል። የ 16ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ቺዶ ኦቢ ማርቲን አርሰናል በክለቡ እንዲቆይ ያቀረበለትን ጥያቄ አለመቀበሉ እና ክለቡን ለመልቀቅ መወሰኑ ታውቋል። ተጨዋቹ በዚህ ሳምንት ካሪንግተን ተገኝቶ እንደነበር መዘገቡ የሚታወስ ሲሆን ቀያዮቹ…
ዩናይትድ ተጨዋች ለማስፈረም ተስማማ !

በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የሚመራው ማንችስተር ዩናይትድ ወጣቱን የፊት መስመር አጥቂ ቺዶ ኦቢ ማርቲን ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

የ 16ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ቺዶ ኦቢ ማርቲን በቅርቡ ከሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ጋር መለያየቱ አይዘነጋም።

ተጨዋቹ ከተለያዩ ክለቦች ጥሩ የዝውውር ጥያቄዎች ቢቀርቡለትም ማንችስተር ዩናይትድን ለመቀላቀል መምረጡ ተነግሯል።

ያለፈውን አመት በአርሰናል አካዳሚ ጥሩ የሚባል ጊዜን ያሳለፈው ቺዶ ኦቢ ማርቲን በቀጣይ ማንችስተር ዩናይትድን በነፃ ይቀላቀላል ተብሏል።

ተጨዋቹ ማንችስተር ዩናይትድን እንዲቀላቀል በቅርቡ የክለቡን የአሰልጣኝ ቡድን የተቀላቀለው ሩድ ቫን ኔስቶሮይ የማሳመኑን ስራ መስራቱ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
Affordable Gaming PC (HP Victus)

🔸
Core 17 12th Gen
RTX 3050 TI (4GB)
104,000 Birr

🔹Core 17 13th Gen
RTX 4050 TI (6GB)
119,000 ETB

🔸Core 17 13th Gen
RTX 4060 (4GB)
139,000 ETB

Contact Us
0953964175 @heymobile
@heyonlinemarket
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
Partizan - Dyn. Kyiv
Borac Banja Luka - PAOK
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
“ ጋርዲዮላ በሲቲ እንዳደረገው ማድረግ እንፈልጋለን “ ሀንሲ ፍሊክ

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ሌሊት ከማንችስተር ሲቲ ጋር በአሜሪካ ያደረጉትን የወዳጅነት ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤ አጠናቀዋል።

በአሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ የሚመራው ባርሴሎና ማንችስተር ሲቲን በመለያ ምት 4ለ1 ማሸነፍ ችሏል።

ከጨዋታው በኋላ አስተያየታቸውን የሰጡት አሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ " ባርሴሎና ውስጥ ጋርዲዮላ በማንችስተር ሲቲ የገነባውን አይነት ማድረግ እንፈልጋለን “ ሲሉ ተናግረዋል።

አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በበኩላቸው ኤርሊንግ ሀላንድ ከእረፍት በኋላ ያልገባው መጠነኛ ጉዳት ስላጋጠመው መሆኑን ገልጸዋል።

ማንችስተር ሲቲ በቅድመ ውድድር ዝግጅት እስካሁን ካደረጋቸው መደበኛ ጨዋታዎች በሁለቱ ሲሸነፍ በአንዱ አቻ ተለያይቷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ትልቅ ዋንጫ የማሸነፍ ህልም አለኝ " ራሽፎርድ

የማንችስተር ዩናይትዱ የፊት መስመር ተጨዋች ማርከስ ራሽፎርድ ከቡድኑ ጋር ትልቅ ዋንጫዎችን የማሸነፍ ህልም እንዳለው በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

“ አሁንም ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ትልቅ ዋንጫ የማሸነፍ ህልም አለኝ “ የሚለው ማርከስ ራሽፎርድ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ እና የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫዎችን ማሳካት እፈልጋለሁ “ ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Paris2024

የ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር አምስተኛ ቀኑን ሲይዝ በዛሬው ውሎው አስራ ስምንት የወርቅ ሜዳልያዎች ለአሸናፊዎች ይበረከታሉ።

በውድድሩ ጃፓን የወርቅ ሜዳልያ ቁጥሯን ወደ ሰባት ከፍ በማድረግ የሜዳልያ ሰንጠረዡን መምራቷን ቀጥላለች።

በሜዳልያ ብዛት አሜሪካ አጠቃላይ ሃያ ስድስት ሜዳልያዎችን በመሰብሰብ ቀዳሚ ስትሆን አዘጋጇ ሀገር ፈረንሳይ አስራ ስምንት ሜዳልያዎች በማግኘት ትከተላለች።

በዛሬው ዕለት በጂምናስቲክ ፣ ብስክሌት ፣ ታንኳ ፣ በሴቶች ዳይቪንግ ፣ ፌንሲንግ ፣ ጁዶ ፣ ቀዘፋ ፣ ዋና ፣ ሹቲንግ እና ትርያትሎን ለሜዳልያ ከሚደረጉት ውድድሮች መካከል ዋነኞቹ  ናቸው።

ወቅታዊ የሜዳልያ ሰንጠረዡ ምን ይመስላል ?

1️⃣ ጃፓን :- 🥇🥇🥇🥇🥇🥇🥇🥈🥈🥉🥉🥉🥉

2️⃣ ቻይና :-🥇🥇🥇🥇🥇🥇🥈🥈🥈🥈🥈🥈🥉🥉

3️⃣ አውስትራሊያ :- 🥇🥇🥇🥇🥇🥇🥈🥈🥈🥈🥉

4️⃣ ፈረንሳይ :-🥇🥇🥇🥇🥇🥈🥈🥈🥈🥈🥈🥈🥈🥈🥉🥉🥉🥉

5️⃣ ደቡብ ኮርያ :-🥇🥇🥇🥇🥇🥈🥈🥈🥉🥉🥉

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሊቨርፑል በቀጣይ ተጨዋች ያስፈርማሉ ?

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል በዘንድሮው ክረምት የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት እስካሁን ምንም ተጨዋች አላስፈረሙም።

በአሰልጣኝ አርኔ ስሎት የሚመራው ሊቨርፑል በዚህ ክረምት ምንም ተጨዋች ያላስፈረመ ብቸኛው የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ክለብም ነው።

ሊቨርፑል በክረምቱ የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት መጨረሻ በተጨዋቾች ሽያጭ ላይ ተመርኩዘው ሁለት ወይም ሶስት ተጨዋቾች ለማስፈረም ማቀዳቸው ተዘግቧል።

አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ቡድናቸውን ለማጠናከር የመሐል ተከላካይ እና የመሐል ሜዳ ተጨዋች ማስፈርምን ቅድሚያ እንደሚሰጡ ተነግሯል።

በተጨማሪም ሊቨርፑል በቀጣይ ለማስፈረም የሚመርጣቸው ተጨዋቾች እድሜያቸው ከ 24ዓመት በታች የሆኑ እንደሚሆኑ ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/06 00:36:43
Back to Top
HTML Embed Code: