Telegram Web Link
ቼልሲ ግብ ጠባቂ ማስፈረም ይፈልጋል !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በቀጣይ ተጨማሪ ግብ ጠባቂ ለማስፈረም በመመልከት ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።

በአሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ የሚመሩት ሰማያዊዎቹ በአሁን ሰዓት የ 22ዓመቱን የቪያሪያል ግብ ጠባቂ ፊሊፕ ሆርጌንሰንን ለማስፈረም ከፍተኛ ፍላጎት ማሳየታቸው ተነግሯል።

ቼልሲ የግብ ጠባቂውን ዝውውር የሚያጠናቅቁ ከሆነ ያለፈውን አመት በውሰት በሪያል ማድሪድ ቤት ካሳለፍ ኬፓ አሪዛባላጋ ጋር ስድስተኛ ግብ ጠባቂያቸው ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" በርካታ ተጨዋቾች ሲቲን መቀላቀል ይፈልጋሉ " ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በርካታ ተጨዋቾች ወደ ቡድናቸው መምጣት ቢፈልጉም ከክለቦቻቸው ጋር ለመስማማት እንደተቸገሩ ገልፀዋል።

" ብዙ ተጨዋቾች ወደ ማንችስተር ሲቲ መምጣት ይፈልጋሉ ነገርግን እኛ እነሱን ለማስፈረም ከክለቦቻቸው ጋር ልንስማማ አልቻልንም።"ሲሉ ፔፕ ጋርዲዮላ ተናግረዋል።

ክለቦች ማንችስተር ሲቲን ከፍተኛ የዝውውር ሒሳብ እየጠየቁ መሆኑ ተጨዋች ለማስፈረም አስቸጋሪ እንዳደረገባቸው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ገልጸዋል።

ማንችስተር ሲቲ ለማስፈረም ከጠየቃቸው ተጨዋቾች መካከል ከፈረሙት ተጨዋቾች ያልፈረሙት ተጨዋቾች በእጅጉ እንደሚበልጡ ፔፕ ጋርዲዮላ አሳውቀዋል።

ፔፕ ጋርዲዮላ አክለውም በማንችስተር ሲቲ በመቆየታቸው ደስተኛ እንደሆኑ እና በመጪው የውድድር አመት ተጨማሪ ዋንጫዎችን ማሸነፍ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዴቪድ ዴህያ የዝውውር ጥያቄዎች ቀርበውለታል !

ባለፈው አመት ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ከተለያየ በኋላ ያለ ክለብ የሚገኘው ስፔናዊው ግብ ጠባቂ ዴቪድ ዴህያ አሁን ላይ የዝውውር ጥያቄዎች እንደቀረቡለት ተገልጿል።

ከአስራ ሁለት አመታት በኋላ ከቀያይ ሴጣኖቹ ጋር የተለያየው ዴቪድ ዴህያ ከሳውዲ አረቢያ እና አሜሪካ በርካታ ጥያቄዎች እንደቀረቡለት ተነግሯል።

በተጨማሪም ዴቪድ ዴህያ ከጣልያን ሴርያ ክለቦች የዝውውር ጥያቄ እንደደረሰው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" የትኛውንም ተጨዋች ማጣት አንፈልግም " ኤዲ ሀው

የኒውካስል ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ኤዲ ሀው በክረምቱ የዝውውር መስኮት ወሳኝ ተጫዋቾቻቸውን መልቀቅ እንደማይፈልጉ ገልጸዋል።

" እኛ የትኛውንም ተጨዋች ማጣት አንፈልግም " የሚሉት ኤዲ ሀው ስሙ ከሊቨርፑል ጋር በስፋት ሲያያዝ የነበረውን የፊት መስመር ተጨዋቻቸው አንቶኒ ጎርደን ማቆየት እንደሚፈልጉ አሳውዋል።

" አንቶኒ ጎርደን ለእኛ ቁልፍ ተጨዋች ነው ፣ ትክክለኛውን ውሳኔ ለመወሰን አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ገብተን ነበር ሆኖም ጎርደን በክለቡ ይቆያል" ሲሉ ኤዲ ሀው ተናግረዋል።

ኒውካስትል ዩናይትድ ከፋይናንሻል ፌር ፕሌይ ህግ ጋር በተያያዘ እንደ አንቶኒ ጎርደን ፣ ብሩኖ ጉማሬሽ እና አሌክሳንደር አይሳክ ያሉ ቁልፍ ተጨዋቾችን ሊሸጡ እንደሚችሉ ሲገለፅ እንደነበር አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ፕርሚየር ሊጉን ለማሳካት ተቃርበናል “ አርቴታ

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቡድናቸው የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ዋንጫን ለማሸነፍ በእጅጉ ተቃርቧል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል።

ለቅድመ ውድድር ዝግጅት ቡድናቸውን ይዘው ወደ አሜሪካ ያቀኑት አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በቀጣይ የመጀመሪያ ግባቸው ዋንጫዎችን ማሸነፍ እንደሆነ ተናግረዋል።

" ቡድኑን በሁሉም ቦታዎች ለማጠናከር ጠንክረን እየሰራን ነው " ያሉት አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ " የአርሰናል ስኬት ተፎካካሪ መሆን ብቻ ሳይሆን ዋንጫዎችን ማሸነፍ መሆን አለበት " ብለዋል።

ሚኬል አርቴታ ቀጥለውም "  እኛ በጥሩ መንገድ ላይ ነን " ሲሉ " ባለፉት ሁለት አመታት ያሳየነው ጥሩ ነገር ዋንጫ ለማሸነፍ በቂ አልነበረም ይህንን በመቀየር ዋንጫዎችን ማሸነፍ እንፈልጋለን " ብለዋል።

አርሰናል ባለፉት ሁለት የውድድር አመታት የሊጉን ዋንጫ ለማሸነፍ በእጅጉ ተቃርቦ በአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በሚመሩት ማንችስተር ሲቲዎች በመጨረሻው ሰዓት ማጣቱ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የአሌክሳንደር አርኖልድ የሊቨርፑል ቆይታ ?

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል አዲሱ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ሪቻርድ ሂውዝ በቀጣይ ቅድሚያ ሰጥተው የሚሰሩት የአሌክሳንደር አርኖልድን ውል ማራዘም እንደሚሆን ተገልጿል።

አሌክሳንደር አርኖልድ በአሁን ሰዓት በእረፍት ላይ መሆኑ ሲገለፅ በቀጣይ በአዲሱ አሰልጣኝ አርኔ ሴሎት ስር ለመስራት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው ተነግሯል።

የስፔኑ ክለብ ሪያል ማድሪድ የአሌክሳንደር አርኖልድን ኮንትራት ሁኔታ በመከታተል ላይ እንደሚገኙ ሲዘገብ ነበር።

እንግሊዛዊው የመስመር ተጨዋች አሌክሳንደር አርኖልድ በሊቨርፑል ቤት ያለው ኮንትራት በ2025 እንደሚጠናቀቅ ይታወቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የማንችስተር ዩናይትድ የዝውውር ሁኔታ ?

ማንችስተር ዩናይትድ የዝውውር መስኮቱ ከመጠናቀቁ በፊት ተጨማሪ የፊት መስመር አጥቂ ለማስፈረም ሊንቀሳቀስ እንደሚችል ሲገለፅ በክለቡ ዝርዝር ውስጥ ኢቫን ቶኒ እና ካልቨርት ሌዊን እንደሚገኙ ተገልጿል።

ለረጅም ጊዜ አድሪያን ራብዮን የማስፈረም ፍላጎት የነበራቸው ቀያዮቹ ሴጣኖች አሁን ላይ ተጨዋቹ ያለ ክለብ ቢገኝም ለማስፈረም እንቅስቃሴ እንዳላደረጉ ተዘግቧል።

ዩናይትድ የመሐል ሜዳ ክፍሉን ለማጠናከር ሶፍያን አምራባትን እና የሪያል ሶሴዳዱን ማርቲን ዙቢሜንዲ በአማራጭነት መያዛቸው ተነግሯል።

ማንችስተር ዩናይትድ በቀጣይ ለቪክቶር ሊንድሎፍ የዝውውር ጥያቄ ከቀረበ ለመመልከት ዝግጁ መሆናቸው ተጠቁሟል።

ስኮትላንዳዊው አማካይ ስኮት ማክቶሚናይ በበኩሉ በክለቡ እንደሚፈለግ የተገለፀ ሲሆን ጥሩ ሒሳብ ከቀረበ ለመመልከት ሊያስቡ እንደሚችሉ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እስማኤል ሳር ወደ ፓላስ ለማምራት ተስማማ !

የፕርሚየር ሊጉ ክለብ ክሪስታል ፓላስ ሴኔጋላዊውን የፊት መስመር ተጨዋች እስማኤል ሳር ከማርሴይ ለማስፈረም በግል ከተጨዋቹ ጋር መስማማታቸው ተገልጿል።

ማርሴይ ክሪስታል ፓላስ ያቀረበውን የመጀመሪያ ሒሳብ ውድቅ ማድረጋቸው ሲገለፅ በሁለቱ ክለቦች መካከል ንግግሮች መቀጠላቸው ተዘግቧል።

ማርሴይ እስማኤል ሳርን ባለፈው አመት ከሻምፒዮን ሽፑ ክለብ ዋትፎርድ በ 25 ሚልዮን ዩሮ ማስፈረማቸው አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
በሜሰን ግሪንውድ ውል ውስጥ ምን ተካቷል ? የላሊጋው ክለብ ሄታፌ እንግሊዛዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ሜሰን ግሪንውድ ከማንችስተር ዩናይትድ በቋሚነት ለማስፈረም በማሰብ ላይ መሆናቸው ተገልጿል። ማንችስተር ዩናይትድ ሜሰን ግሪንውድን ለሄታፌ በውሰት ሲሰጥ በውሉ ውስጥ ከተጨዋቹ የወደፊት ሽያጭ ለሄታፌ 20% ክፍያ የሚያስገኝ ህግ ማካተቱ ተነግሯል። ሄታፌ ሀያ በመቶ ክፍያውን የሚያገኘው ማንችስተር ዩናይትድ…
ሄታፌ ከግሪንውድ ሽያጭ ተጠቃሚ ይሆናሉ !

የስፔኑ ክለብ ሄታፌ የፊት መስመር ተጨዋች ሜሰን ግሪንውድ ከማንችስተር ዩናይትድ በውሰት ውል ሲያስፈርሙት ባካተቱ የወደፊት ሽያጭ ውል ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተገልጿል።

ሄታፌ በዚህ ውል መሰረት የ 22ዓመቱ ተጨዋች ግሪንውድ ወደ ማርሴይ ካደረገው ዝውውር 20% ገቢውን እንደሚያኙ ተነግሯል።

ማንችስተር ዩናይትድ ከማርሴይ ለዝውውሩ 26.7 ሚሊየን ፓውንድ የተቀበሉ ሲሆን ለሄታፌ 5.34 ሚሊየን ፓውንድ መክፈላቸው ተጠቁሟል።

በተጨማሪም ማንችስተር ዩናይትድ ሜሰን ግሪንውድን ለማርሴይ ሲሸጠው ከተካተተው 50% የወደፊት ሽያጭ ገቢ ላይ ሄታፌ 20% ተካፋይ እንደሚሆን ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የፓሪስ ኦሎምፒክስ ደረሰ!

ከሐምሌ 19 እስከ ነሐሴ 5 በዲኤስቲቪ  ሙሉ የቀጥታ ስርጭት በ9 ቻናሎች ይተላለፋል!

ብርቅዬ አትሌቶቻችንን በፓሪሱ ኦሎምፒክስ ለመቀላቀል ጊዜው አሁን ነው!

እናሸንፋለን ድሉን እናያለን!

የፓሪስ ኦሎምፒክስን በ350 ብር በጎጆ ፓኬጅ ይከታተሉ! ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/dg1

#ParisOlympics #2024Olympics #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
Forwarded from WANAW SPORT
🇪🇹 ዋናው 🤝 የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና 🇪🇹

ዋናው ስፖርት ከሰኔ 22 ጀምሮ በድሬዳዋ ከተማ አስተናጋጅነት በ40 ክለቦች መካከል ሲከናወን ቆይቶ ባሳለፍነው እሁድ በጉባ ከተማ አቶቲ አሸናፊነት የተጠናቀቀው የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና የወንዶች ውድድር አጋር ስለነበር የተሰማውን ልባዊ ኩራት ይገልፃል።

Wannaaw Ispoort Adoolessa 22 irraa eegalee Qopheessummaa Magaalaa Dirree Dawaan Kilaboota 40 gidduutti gaggeeffamaa kan ture Shaampiyoonaa Kilaboota Naannolee Itiyoophiyaa Dorgommii dhiirotaan dilbata darbe Olaantummaa Magaalaa Gubbaa Atooteen kan xumurame Miiltoo ta’uu isaatiin garaadhaa akka boonu ibsa.

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
አርሰናል ከተጨዋቹ ጋር ተለያይቷል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ታዳጊ የፊት መስመር አጥቂያቸው ቺዶ ኦቢ ማርቲን በክለቡ ውሉን እንደማያራዝምና ከቡድኑ ጋር እንደሚለያይ አሳውቀዋል።

የ 16ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ቺዶ ኦቢ ማርቲን በማንችስተር ዩናይትድ እንዲሁም ሌሎች ክለቦች እየተፈለገ ይገኛል።

ባለፈው አመት በአርሰናል አካዳሚ ጥሩ ጊዜን ያሳለፈው ተጨዋቹ በቀጣይ በነፃ ዝውውር የሚቀላቀለውን ክለብ እንደሚያሳውቅ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ዩኤፋ ምርመራ መጀመሩን ይፋ አደረገ ! የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር የስፔን ብሔራዊ ቡድን ተጨዋች ከቀናት በፊት በማንችስተር ሲቲው ተጨዋች ሮድሪ እየተመሩ ያሰሙትን ዝማሬ እየመረመረ እንደሚገኝ ገልጿል። ዩኤፋ ምርመራውን የከፈተው ስፔን የአውሮፓ ዋንጫ ድሏን ማድሪድ ውስጥ በምታክብርበት ወቅት ተጨዋቾቹ " ጂብላርታር ስፔን ነው " እያሉ እንግሊዞች ላይ ቀልደዋል በሚል መሆኑ ተነግሯል። በሰዓቱ ሮድሪ…
ሮድሪ እና ሞራታ ክስ ቀረበባቸው !

የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር የስፔን ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች የሆኑት ሮድሪ እና አልቫሮ ሞራታ ላይ ክስ ማቅረቡን አስታውቋል።

ሁለቱ ተጨዋቾች ከዩኤፋ ክስ የቀረበባቸው ባለፈው ሳምንት ስፔን የአውሮፓ ዋንጫ ድሏን በምታከብርበት ወቅት ባሰሙት ዝማሬ ምክንያት መሆኑ ተነግሯል።

ዩኤፋ አሁን ላይ ባወጣው መግለጫ ሁለቱ ተጨዋቾች ላይ ካቀረበው ክስ ውስጥ ስፖርታዊ ውድድሮችን ለሌላ ስፖርታዊ ያልሆነ አላማ በማዋል የሚል ይገኝበታል።

የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ዲሲፕሊን ኮሚቴ በቀጣይ በተጨዋቾቹ ላይ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ተያይዞ ተገልጿል።

ተጨዋቾቹ ስፔን የአውሮፓ ዋንጫ ድሏን ማድሪድ ውስጥ በምታክብርበት ወቅት " ጂብላርታር ስፔን ነው " እያሉ በመዘመራቸው ምክንያት ቅሬታዎች ሲቀርቡባቸው ነበር።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ዴቪድ ዴህያ የዝውውር ጥያቄዎች ቀርበውለታል ! ባለፈው አመት ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ከተለያየ በኋላ ያለ ክለብ የሚገኘው ስፔናዊው ግብ ጠባቂ ዴቪድ ዴህያ አሁን ላይ የዝውውር ጥያቄዎች እንደቀረቡለት ተገልጿል። ከአስራ ሁለት አመታት በኋላ ከቀያይ ሴጣኖቹ ጋር የተለያየው ዴቪድ ዴህያ ከሳውዲ አረቢያ እና አሜሪካ በርካታ ጥያቄዎች እንደቀረቡለት ተነግሯል። በተጨማሪም ዴቪድ ዴህያ ከጣልያን ሴርያ…
ዴቪድ ዴህያ በኤሪክ ቴንሀግ መናደዱ ተገለጸ !

ስፔናዊው ግብ ጠባቂ ዴቪድ ዴህያ ማንችስተር ዩናይትድን ለመልቀቁ ምክንያት ናቸው ባላቸው አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ እና የቀድሞ የክለቡ ሀላፊ ጆን ሙርታፍ መናደዱ ተገልጿል።

ዴቪድ ዴህያ ሁለቱ ግለሰቦች በክለቡ ከሌሉ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ ቢመለስ ደስተኛ እንደሚሆን ለእሱ ቅርብ ለሆኑ ሰዎች መናገሩም ተጠቁሟል።

ዴህያ በቀጣይ አዲስ ክለብ መቀላቀል ቢፈልግም ከማንችስተር ዩናይትድ ውጪ ለእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ክለብ ተሰልፎ መጫወት እንደማይፈልግ መግለፁ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/04 21:24:55
Back to Top
HTML Embed Code: