Telegram Web Link
Forwarded from HEY Online Market
•PlayStation 5, 73,000 Birr
•Playstaion 5 Slim, 78,000 Birr

•PlayStation 4 Slim, 35,000 Birr
•PlayStation 4 Pro, 43,000 Birr

•Playstaion portal, 35,000 Birr
•Meta Quest 2, 55,000 Birr
•Meta Quest 3, 83,000 Birr

Contact
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
አል ኢትሀድ ለተጫዋቹ የቀረበውን ጥያቄ ውድቅ አደረገ !

የሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ኢትሀድ ዌስትሀም ዩናይትድ ንጎሎ ካንቴን ለማስፈረም ያቀረቡትን የዝውውር ጥያቄ ውድቅ ማድረጋቸው ተገልጿል።

ዌስትሀም ዩናይትድ ለንጎሎ ካንቴ ዝውውር 15 ሚሊየን ፓውንድ የዝውውር ሒሳብ ቢያቀርቡም በአል ኢትሀድ ጥያቄው ውድቅ መደረጉ ተነግሯል።

አል ኢትሀድ የ33 አመቱን ንጎሎ ካንቴ የመሸጥ ፍላጎት #የሌላቸው ሲሆን ዌስትሀም ዩናይትድ አሁንም ከስምምነት ላይ ለመድረስ በንግግር ላይ መሆናቸው ተዘግቧል።

ዌስትሀም ዩናይትድ ንጎሎ ካንቴን ለማስፈረም 25  ሚሊየን ፓውንድ እና ከዛ በላይ የዝውውር ሒሳብ እንደሚያስፈልጋቸውም ተጠቁሟል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
“ ግሪንውድን ስለሰጡን ዩናይትድን እናመሰግናለን “ ዲ ዘርቢ

ጣልያናዊው የማርሴይ ዋና አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዘርቢ አዲሱን ፈራሚያቸው ሜሰን ግሪንውድ ታላቅ ተጨዋች ማድረግ እንደሚፈልጉ በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል።

“ ስለ ግሪንውድ የሚሰማው ሁሉም ነገር ስላለፈው ነገር ነው “ ያሉት አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዘርቢ እሱን ታላቅ ተጨዋች ማድረግ እና ቡድኑን በእሱ ላይ መገንባት እንፈልጋለን ብለዋል።

አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዘርቢ ቀጥለውም ማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋቹን ስለሸጠላቸው ማመስገን እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጆኢል ማቲፕ ወደ ባየር ሌቨርኩሰን ?

የወቅቱ የጀርመን ቡንደስሊጋ አሸናፊ ባየር ሌቨርኩሰን ካሜሮናዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ጆኢል ማቲፕ ለማስፈረም መቃረባቸው ተገልጿል።

ጆኢል ማቲፕ ከሊቨርፑል ጋር ከስምንት የውድድር አመታት ቆይታ በኋላ በውድድር አመቱ መጨረሻ መለያየቱ አይዘነጋም።

በአሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ የሚመራው ባየር ሌቨርኩሰን የ 32ዓመቱን ተከላካይ ጆኢል ማቲፕ በነፃ ወደ ቡድናቸው ለመቀላቀል ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አርሰናል ተጨዋች ለማስፈረም ተስማማ ! የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ጣልያናዊውን የቦሎኛ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሪካርዶ ካላፊዮሪ ለማስፈረም ከተጨዋቹ ጋር ከስምምነት መድረሱ ተገልጿል። መድፈኞቹ ለተጨዋቹ ባቀረቡት እስከ 2029 የሚቆይ የአምስት አመት ኮንትራት ከስምምነት መድረሳቸው ተነግሯል። አርሰናል በተጨዋቹ ዝውውር ሒሳብ ዙሪያ ከቦሎኛ ጋር ንግግር በማድረግ ላይ መሆናቸው ሲገለፅ ክለቡ…
አርሰናል ከቦሎኛ ጋር ለስምምነት መቃረቡ ተገለጸ !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ጣልያናዊውን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሪካርዶ ካላፊዮሪ ለማስፈረም ከቦሎኛ ጋር ለስምምነት መቃረባቸው ተገልጿል።

መድፈኞቹ ከዚህ በፊት ተጨዋቹን እስከ 2029 በሚቆይ የአምስት አመት ኮንትራት ለማስፈረም በግል መስማማታቸው ይታወቃል።

አርሰናል ክለቡ ጋር ጥሩ ንግግር ማድረጋቸው የተገለፀ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በቀጣይ ተጫዋቹን የማስፈረም ሙሉ እምነት እንዳላቸው ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ዴሊትን የማስፈረም ሀሳብ ከእኔ አልመጣም “ ኤሪክ ቴን ሀግ

የማንቸስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ስሙ ከክለቡ ጋር በስፋት እየተያያዘ ስለሚገኘው የባየር ሙኒክ ተከላካይ ማትያስ ዴሊት አስታያየታቸውን ሰጥተዋል።

" ከሁለት አመት በፊት ማትያስ ዴሊትን ለማስፈረም እፈልግ ነበር ነገርግን እሱ ባየር ሙኒክን ተቀላቅሏል " ያሉት ኤሪክ ቴንሀግ አሁን ግን እሱን የማስፈረም ሀሳቡ ከእኔ የመጣ አይደለም ሲሉ አረጋግጠዋል።

" ማትያስ ዴሊትን በደንብ እንደማውቀው አልክድም ነገርግን ወደዚህ ይመጣ እንደሆነ በቀጣይ የሚታይ ጉዳይ ነው " ሲሉ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ተናግረዋል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች ማትያስ ዴሊትን ለማስፈረም ከተጨዋቹ ጋር መስማማት ቢችሉም ከባየር ሙኒክ ጋር በዝውውር ሒሳብ ዙሪያ እስከ አሁን ከስምምነት ላይ መድረስ እንዳልቻለ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጄደን ሳንቾ በዩናይትድ ስብስብ ውስጥ ተካቷል !

በዛሬው ዕለት ከሬንጀርስ ጋር የወዳጅነት ጨዋታውን የሚያደርገው ማንችስተር ዩናይትድ እንግሊዛዊውን ተጨዋች ጄደን ሳንቾ በስብስቡ ውስጥ ማከተቱን ይፋ አድርጓል።

በተጨማሪም አዲሱ ፈራሚ ሌኒ ዮሮ በማንችስተር ዩናይትድ የቡድን ስብስብ ተካቶ ወደ ስኮትላንድ ማምራቱ ይፋ ሆኗል።

ሁለቱም ተጨዋቾች ምሽት 12:00 ሰዓት ከሬንጀርስ ጋር በሚደረገው ሁለተኛ የቅድመ ውድድር የወዳጅነት ጨዋታ ተሰልፈው ይጫወታሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ከአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ጋር አለመግባባት ውስጥ የነበረው ጄደን ሳንቾ ለመጨረሻ ጊዜ ለማንችስተር ዩናይትድ ተሰልፎ የተጫወተው ከአመት በፊት እንደነበር ይታወሳል።

በዛሬው የማንችስተር ዩናይትድ ስብስብ ማርከስ ራሽፎርድ ፣ ሀሪ ማጓየር ፣ አንቶኒ እና ሊንድሎፍ አለመካተታቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አርሰናል ከቦሎኛ ጋር ለስምምነት መቃረቡ ተገለጸ ! የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ጣልያናዊውን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሪካርዶ ካላፊዮሪ ለማስፈረም ከቦሎኛ ጋር ለስምምነት መቃረባቸው ተገልጿል። መድፈኞቹ ከዚህ በፊት ተጨዋቹን እስከ 2029 በሚቆይ የአምስት አመት ኮንትራት ለማስፈረም በግል መስማማታቸው ይታወቃል። አርሰናል ክለቡ ጋር ጥሩ ንግግር ማድረጋቸው የተገለፀ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በቀጣይ…
#Update

አርሰናሎች ጣልያናዊውን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሪካርዶ ካላፊዮሪ ማስፈረም ከጣልያኑ ክለብ ቦሎኛ ጋር ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

መድፈኞቹ ተጫዋቹን 38 ሚልዮን ፓውንድ በሚደርስ የዝውውር ሒሳብ ለማስፈረም ከቦሎኛ ጋር መስማማታቸው ተነግሯል።

ተጨዋቹ ከእረፍት በተመለሰ በኋላ ለክለቡ ቦሎኛ ሀላፊዎች አርሰናልን በመቀላቀል ህልሙን እንዲያሳካ እንዲለቁት ጥያቄ ማቅረቡ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ጃሬድ ብራንዝዌት ኤቨርተንን ላይለቅ ይችላል ! የመርሲሳይዱ ክለብ ኤቨርተን አማካይ አማዱ ኦናና ወደ አስቶን ቪላ ማምራት በማንችስተር ዩናይትድ የሚፈለገውን ጃሬድ ብራንዝዌት ዝውውር ሊያስቀረው እንደሚችል ተገልጿል። አማዱ ኦናን በ50 ሚልዮን ፓውንድ ለአስቶን ቪላ ለመሸጥ የተቃረበው ኤቨርተን ከፍተኛ የዝውውር ሒሳብ ካልቀረበላቸው ጃሬድ ብራንዝዌትን በዚህ ክረምት ላይሸጡት እንደሚችሉ ተነግሯል። …
ኤቨርተን ተጫዋቹን እንደማይሸጥ አሳወቀ !

የመርሲሳይዱ ክለብ ኤቨርተን ተከላካያቸው ጃሬድ ብራንዝዌትን በዚህ ክረምት የመሸጥ ፍላጎት እንደሌለው ለማንችስተር ዩናይትድ ማሳወቁ ተገልጿል።

ማንችስተር ዩናይትድ አሁን ላይ ተጫዋቹን ለማስፈረም የሚፈልጉት የተጠየቀው የዝውውር ሒሳብ የሚቀንስ ከሆነ ብቻ መሆኑ ተዘግቧል።

ኤቨርተን በበኩሉ ተጫዋቹን ለመሸጥ ሊያስብ የሚችለው የጠየቀው 70 ሚልዮን ፓውንድ ከቀረበለት እንደሚሆን ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አርሰናል የወዳጅነት ጨዋታውን አሸንፏል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ዛሬ በልምምድ ማዕከሉ ከሊግ አንዱ ክለብ ሌይተን ኦሪየንት ጋር የወዳጅነት ጨዋታ አድርጎ 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፉ ተገልጿል።

ለመድፈኞቹ ግቦቹን ጋብሬል ጄሱስ እና ስሚዝ ሮው ማስቆጠራቸው ተገልጿል።

አርሰናል ቀጣይ ሳምንት ሐሙስ በአሜሪካ ከበርንማውዝ ጋር የቅድመ ውድድር የወዳጅነት ጨዋታውን የሚያደርግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
ዋናው 🤝 የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

🇪🇹 ዋናው ስፖርት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከካፍ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ልዩ የካፍ 'B' ላይሰንስ የአሰልጣኞች ስልጠና አጋር በመሆኑ ታላቅ ኩራት ይሰማዋል።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
🔥⚽️ ትኩስ የስፖርት ዜናዎችን በቀላሉ በSMS እናግኝ! 💬

ከሳፋሪኮም ቁጥራችን 'A’ ብለን ወደ 30001 SMS በመላክ አሁኑኑ Elite ስፖርትን እንቀላቀል ! በቀን 2ብር ብቻ!

በElite ስፖርት በሽ ዜናዎች⚡️

🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ:
https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን
https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom
#SafaricomEthiopia
#1Wedefit
#Furtheraheadtogether
" እዚህ እንድደርስ የረዱኝን ሁሉ አመሰግናለሁ " ቀነኒሳ በቀለ

ኢትዮጵያዊው የረጅም ርቀት ሯጭ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ የ " ESPN " አፍሪካ ሚዲያ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ምርጥ አፍሪካዊ ስፖርተኛ ተብሎ መመረጡ ይፋ ተደርጓል።

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ሚዲያው ለሰጠው እውቅና ትልቅ ክብር እንዳለው በፌስቡክ ማህበራዊ ትስስር ገፁ ሲገለፅ " እንደዚህ አይነት ክብር ማግኘት ያስደስታል በአትሌቲክስ ህይወቴ የረዱኝኝን ሁሉ አመሰግናለሁ " ብሏል።

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በአትሌቲክስ ህይወቱ ሶስት የኦሎምፒክ ፣ አምስት የአለም ሻምፒዮና እንዲሁም አስራ አንድ የአለም ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና ወርቅ ሜዳልያ እና ሌሎች ድሎች ባለቤት ነው።

አትሌት ቀነኒሳ በቀለን በመከተል ኬንያዊው የረጅም ርቀት ሯጭ ኤሉድ ኪፕቾጌ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።

ካሜሮናዊው እግርኳስ ተጨዋች ሳሙኤል ኢቶ በምርጫው ከእግርኳስ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቅ ችሏል።

በሴቶች ኢትዮጵያዊቷ የረጅም ርቀት ሯጭ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ በሴቶች ሁለተኛ በሁለቱም ጾታ ደግሞ አምስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችላለች።

ሚዲያው ምርጥ አፍሪካዊ ስፖርተኛ ምርጫውን ያደረገው እ.ኤ.አ. ከ 2000 ወዲህ የስፖርት ህይወታቸውን በጀመሩ ስፖርተኞች መሆኑን አስረድቷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሳንቾ ከወራት በኋላ ለዩናይትድ እየተጫወተ ነው !

እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጨዋች ጄደን ሳንቾ ማንችስተር ዩናይትድ ከሬንጀርስ ጋር እያደረገ በሚገኘው የወዳጅነት ጨዋታ ከወራት በኋላ በክለቡ ማልያ ተሰልፎ በመጫወት ላይ ይገኛል።

ኤሪክ ቴንሀግ ስለ ሳንቾ በሰጡት አስተያየት " ሁሉም ጥፋት ያጠፋል " ሲሉ " ዩናይትድ ጥሩ ተጨዋች ያስፈልገዋል ሳንቾ ደግሞ ምርጥ ተጨዋች ነው ፣ መመለሱ ጥሩ ነገር ነው።"ብለዋል።

በትላንትናው ዕለት ክለቡን በይፋ የተቀላቀለው ሌኒ ዮሮ በበኩሉ የማንችስተር ዩናይትድ የመጀመሪያ ጨዋታውን በማድረግ ላይ ይገኛል።

" ሌኒ ዮሮን በማስፈረማችን በጣም ደስተኞች ነን እሱ ትልቅ አቅም ያለው ተጨዋች ነው።" ሲሉ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ስለ አዲሱ ፈራሚያቸው ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/04 07:37:16
Back to Top
HTML Embed Code: