Telegram Web Link
" ደጋፊው ግሪንውድን ከፈለገ ገንዘብ ያዋጣ "

የጣልያኑ ክለብ ላዝዮ ፕሬዝዳንት የሆኑት ክላውዲዮ ሎቲቶ የክለቡ ደጋፊ ለተጨዋች ፊርማ ገንዘብ መክፈል እንዳለበት ገልጸዋል።

ግሪንውድን ከማንችስተር ዩናይትድ ለማስፈረም እያደረጉ ስለሚገኙት ጥረት የተናገሩት ክላውዲዮ ሎቲቶ " ደጋፊዎች ግሪንውድን ማስፈረም ከፈለጉ ገንዘብ መክፈል አለባቸው " ሲሉ ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንቱ አያይዘውም ለግሪንውድ ዝውውር 25 ሚልዮን ዩሮ እና ከወደፊት ሽያጭ 50% የሚያስገኝ የዝውውር ጥያቄ ለማንችስተር ዩናይትድ ማቅረባቸውን ገልጸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
•PlayStation 5, 73,000 Birr
•Playstaion 5 Slim, 78,000 Birr

•PlayStation 4 Slim, 35,000 Birr
•PlayStation 4 Pro, 43,000 Birr

•Playstaion portal, 35,000 Birr
•Meta Quest 2, 55,000 Birr
•Meta Quest 3, 83,000 Birr

Contact
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
Modern Sport - Al Ahly
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
ኢትዮጵያ የምታዘጋጀው የሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ ማጣሪያ መቼ ይካሄዳል ?

በሀገራችን ኢትዮጵያ የሚካሄደው የዘንድሮው የሴካፋ ሀገራት የካፍ ሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ ማጣሪያ ውድድር የሚደረግበት ቀን እና ተሳታፊ ክለቦች ይፋ ተደርገዋል።

ውድድሩ ከነሐሴ 11/2016 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 29/2016 ዓ. ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

በውድድሩ ዘጠኝ ክለቦች ተካፍለው አሸናፊው ክለብ ምስራቅ አፍሪካን ወክሎ በካፍ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድሮች የሚሳተፍ ይሆናል።

በውድድሩ እነማን ይሳተፋሉ ?

- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ( ኢትዮጵያ )

- ካዋምፔ ሙስሊም ( ዩጋንዳ )        

- ሲምባ ኪውንስ ( ታንዛኒያ )

- ኬንያ ፖሊስ ቡሌት ( ኬንያ ) 

- ዋርየርስ ክዊንስ ( ዛንዚባር )

- ፋድ ጅቡቲ ( ጅቡቲ )           

- ዬ ጆይንት ስታርስ ( ደቡብ ሱዳን )

- PVP ቡየንዚ ( ቡሩንዲ )                       

- ራዮን ስፖርት ( ሩዋንዳ )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ህልሜን አሳክቻለሁ " ምባፔ

ፈረንሳዊው የሎስ ብላንኮዎቹ የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ በክለቡ የህክምና ምርመራውን ለማድረግ በማድሪድ ተገኝቷል።

ሪያል ማድሪድን በመቀላቀሉ ስለተሰማው ስሜት ከጋዜጠኞች ጥያቄ የቀረበለት ኪሊያን ምባፔ " ህልሜን ነው ያሳካሁት " ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

ሪያል ማድሪድ በዛሬው ዕለት ከሰዓታት በኋላ በሳንቲያጎ በርናቦ ስታዲየም 80,000 ደጋፊዎች በተገኙበት ለኪሊያን ምባፔ ይፋዊ አቀባበል ያደርጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት ከሀላፊነታቸው ለቀቁ !

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ወሠና አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት ከብሔራዊ ቡድኑ ሀላፊነት መልቀቃቸውን በይፋ አስታውቀዋል።

አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ላለፉት ስምንት አመታት በሀላፊነት ሲመሩ በአለም ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ እንዲሁም በተከታታይ በአውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ ተፋላሚ መሆን ችለዋል።

አሰልጣኙ ከሀላፊነታቸው ከለቀቁ በኋላ " እንግሊዝን ማሰልጠን ለእኔ ሁሉም ነገር ነው ፣ በነበረው ቆይታ ያለኝን ሁሉ ሰጥቻለሁ አሁን ደግሞ ለሌላ ምዕራፍ ጊዜው ነው " ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ማራቶን ካቋረጥሽ ፈርሚ ከተባለ እጅግ የሚያሳዝን ነው " ኃይሌ ገብረ ሥላሴ

ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ በፓሪስ ኦሎምፒክ ማራቶን ውድድር " አላቋርጥም ብለሽ ፈርሚ " የተባለ አትሌት አለ መባሉን " እውነት ከሆነ እጅግ የሚያሳዝን " ሲል ገልፆታል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ረ/ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ስለ ጉዳዩ ከቀናት በፊት ተጠይቃ "  በፍጹም ልክ አይደለም ቅር ብሎኛል ግን ደግሞ ልጅቷ በራሷ ተማምና ሄዳ መፈረሟ በእሷ እንድደሰት አድርጎኛል።"ብላለች።

ከብሔራዊ ቴሌቪዥን ጋር በነበራቸው ቆይታ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ የሰጡት የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ የቴክኒክ እና ህዝብ ግንኙነት ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ቢልልኝ መቆያ " አሉባልታ ነው " ሲሉ የገለፁ ሲሆን " አልተባለም " በማለት ማረጋገጫ ሰጥተዋል።

አቶ ቢልልኝ አያይዘውም " መረጃው አትሌቷን የሚጎዳ እና ለሌሎች ሀገራት ሞራል የሚሰጥ ነው ፣ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የሚሰራውን ያውቃል " ብለዋል።

ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ በበኩሉ " ስሰማው በጣም ደንግጫለሁ አይደለም ማስፈረም በቃልም አላቋርጥም በይ ካሏት ተገቢ አይደለም ሊታሰብም አይገባም " ሲል ከሸገር ኤፍ ኤም ስፖርት ጋር በነበረው ቆይታ ተናግሯል።

ይህንን የተባለችው አትሌት ትግስት " ካሸነፈችው የአለም ሪከርድ ወይም ኦሎምፒክን ብታስመርጣት ኦሎምፒክን የምትመርጥ ነች " ሲል ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ገልጿል።

የአለም የማራቶን ሪከርድ ባለቤቷ አትሌት ትግስት አሰፋ ለማራቶን ከፍተኛ ዝግጅት ላይ ስትገኝ ሙሉ ወጪ በመሸፈን የህክምና ባለሙያና አሰልጣኟን ወደ ፓሪስ ይዛ በመሄድ የፓሪስ ማራቶን የሚደረግበት ቦታን መመልከት መቻሏ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" በማድሪድ ፍቅር መውደቅህን አውቃለሁ " ፔሬዝ

የሪያል ማድሪዱ ፕሬዝዳንት ፍሎረንቲኖ ፔሬዝ በሳንቲያጎ በርናቦ ስታዲየም እየተደረገ በሚገኘው የኪሊያን ምባፔ አቀባበል ስነስርዓት ላይ ንግግር በማድረግ ላይ ናቸዉ።

ፕሬዝዳንት ፍሎረንቲኖ ፔሬዝ ምን አሉ ?

- " ኪሊያን ምባፔ እዚህ በመሆንህ አመሰግናለሁ አንተ በሪያል ማድሪድ ፍቅር መውደቅህን አውቃለሁ ገና በ18ዓመትህ አለም ዋንጫ አሸንፈሀል።

- ሪያል ማድሪድ ኢንተርናሽናል ክለብ ነው በአለም ላይ ታዋቂ ነው ፣ ሪያል ማድሪድ ውስጥ ሌላ ምርጫ የለም ማሸነፍ ብቻ ነው።

- ኪሊያን ምባፔ እዚህ ያለኸው እኛ ብቻ ሳንሆን አንተም መምጣት ስለፈለግክ ነው።

- አሁን የምትለብሰው አስራ አምስት የሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫዎችን የያዘውን ነጩን ማልያ ነው።"ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ለማድሪድ ህይወቴን እሰጣለሁ " ምባፔ

የሪያል ማድሪድ ተጨዋች በመሆን በመታወወቅ ላይ የሚገኘው ኪሊያን ምባፔ ለክለቡ ህይወቱን እንደሚሰጥ በስነስርዓቱ ላይ በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

ኪሊያን ምባፔ ምን አለ ?

- " የሪያል ማድሪድ ተጨዋች የመሆን ህልም ነበረኝ ማሳካት ችያለሁ አሁን እዚህ ነኝ አሁን በትልቁ ክለብ ትልቅ ደረጃ ላይ መድረስ እፈልጋለሁ።

- እዚህ ቦታ ለመገኘት በርካታ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን አልፌያለሁ አሁን በአለም ምርጡ ክለብ ውስጥ እገኛለሁ።

- ለወጣቶች ማለት የምፈልገው የማይሆን ህልም እንደሌለ ነው አሁን እኔ ደስተኛው ሰው ሆኛለሁ።

- ለሪያል ማድሪድ ሙሉ ህይወቴን እሰጣለሁ ሪያል ማድሪድ በእግርኳስ ታሪክ ውስጥ ምርጡ ክለብ ነው።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ከቪንሰስ ጋር እስከምጫወት ጓጉቻለሁ " ምባፔ

በዛሬው ዕለት በይፋ የሪያል ማድሪድ በመሆን ደጋፊውን የተዋወቀው ኪሊያን ምባፔ ቪንሰስ ጁኒየር ማድሪድን እንዲቀላቀል እንደጠየቀው በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

ሪያል ማድሪድን እንዲቀላቀል ቪንሰስ ጁኒየር መልዕክት በመላክ በተደጋጋሚ እንደጠየቀው የገለፀው ኪሊያን ምባፔ " ከእሱ ጋር እስክጫወት ጓጉቻለሁ ፣ እንዲሁም ከቤሊንግሀም እና ሌሎች ኮከቦች ጋር " ብሏል።

" ቪንሰስ ጁኒየር ልዩ ተጨዋች ነው " የሚለው ኪሊያን ምባፔ እርስበርስ ለመላመድ ችግር አይኖርብንም ትልቅ ተጨዋቾች እንዴት አብረው እንደሚጫወቱ ያውቃሉ ከእሱ ጋር መጫወት ምንም ችግር የለብኝም " ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
🎙 ለአካዳሚ ሰልጣኞች የሚሆኑ ትጥቆች ለእናንተ!

👉🏾 #አሁኑኑ ይዘዙን!

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ወይም በቴሌግራም ቦት @WanawSportBot ይዘዙን።

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
የፓሪስ ኦሎምፒክ 10 ቀን ብቻ ቀረው!

ከሐምሌ 19 እስከ ነሐሴ 5 በዲኤስቲቪ  ሙሉ የቀጥታ ስርጭት በ9 ቻናሎች ይተላለፋል!

ብርቅዬ አትሌቶቻችንን በፓሪሱ ኦሎምፒክስ ለመቀላቀል ጊዜው አሁን ነው! ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ የአትሌቶቻችንን ብቃት እና ወኔ በጎጆ ፓኬጅ በ350 ብር ይከታተሉ! 

እናሸንፈለን ድሉን እናያለን!

የፓሪስ ኦሎምፒክስን በ350 ብር በጎጆ ፓኬጅ ይከታተሉ! ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/dg1

#ParisOlympics #2024Olympics #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
TIKVAH-SPORT
" አለምአቀፍ የኦሎምፒክ ደንቦች ተጥሰዋል " ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በቅርቡ በዝግ ባደረገው ምርጫ አለምአቀፍ ህጎችን መጣሱን በመግለፅ " ህግ መከበር አለበት " ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል። በኦሎምፒክ ኮሚቴው ምክትል ፕሬዝዳንት ሆኖ የተመረጠው ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ " የኦሎምፒክ ኮሚቴው መሪዎች ስራ መልቀቅ ከነበረብን ከሶስት አመታት…
“ በይፋ ራሴን ከኦሎምፒክ ኮሚቴ አግልያለሁ “ ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ

“ የተከበሩ ዶክተር አሸብር የትም ሂዱ ብለውናል የትም እንሄዳለን “

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አባል የነበረው ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ በወረቀት ላይ ብቻ ከተካተትኩበት የኦሎምፒክ የኮሚቴ አባልነት በይፋ መልቀቄን ህዝብ ይወቅልኝ ሲል ተናግሯል።

አሁን ያለው የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አባል የስራ ዘመኑ ሊጠናቀቅ ስምንት ወይም ዘጠኝ ወራት እንደሚቀሩት የገለፀው ኃይሌ " እኔ በወረቀት ላይ ብኖርም ጥዬ የወጣሁት ግን ከቶኪዮ ኦሎምፒክ በፊት ነው " ብሏል።

ከሶስት አመታት በፊት ከአባልነት መልቀቁን ለህዝብ ያላሳወቀው የባሰ ብጥብጥ ውስጥ እንዳይገባ በመስጋት መሆኑን ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ከሸገር ኤፌ ኤም ጋር በነበረው ቆይታ ገልጿል።

" በድጋሜ ያለ አግባብ ሌላ ምርጫ ማድረግ እና ሌላ ስህተት ግን ተቀባይነት የለውም ያንጊዜ ማድረግ የነበረብኝ ነው አሁን ከአባልነት መልቀቄን በይፋ አሳውቃለሁ።" ሲል ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ተናግሯል።

ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ አያይዞም በቅርቡ በዝግ በተደረገው ምርጫ ጋር በተያያዘ የተነሳውን ውዝግብ ለአዲሷ የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ አቅርበው መልስ እየተጠበቀ መሆኑን አስረድቷል።

" የተከበሩ ዶክተር አሸብር የትም ሂዱ ብለውናል የትም እንሄዳለን " ያለው ኃይሌ " በኋላ ግን ለምን ሄዳችሁ ለምን ይህንን አደረጋችሁ እንዳይሉ እፈራለሁ ፣ እንኳን ይሄን 42 ኪ.ሜ በሞት እና በህይወት ውስጥ ሆነን ሮጠናል " በማለት ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
" ደጋፊው ግሪንውድን ከፈለገ ገንዘብ ያዋጣ " የጣልያኑ ክለብ ላዝዮ ፕሬዝዳንት የሆኑት ክላውዲዮ ሎቲቶ የክለቡ ደጋፊ ለተጨዋች ፊርማ ገንዘብ መክፈል እንዳለበት ገልጸዋል። ግሪንውድን ከማንችስተር ዩናይትድ ለማስፈረም እያደረጉ ስለሚገኙት ጥረት የተናገሩት ክላውዲዮ ሎቲቶ " ደጋፊዎች ግሪንውድን ማስፈረም ከፈለጉ ገንዘብ መክፈል አለባቸው " ሲሉ ተናግረዋል። ፕሬዚዳንቱ አያይዘውም ለግሪንውድ ዝውውር…
የላዝዮ ደጋፊዎች ፕሬዝዳንቱን ተቃውመዋል !

የጣልያን ሴርያው ክለብ ላዝዮ ደጋፊዎች የክለቡ ፕሬዝዳንት ክላውዲዮ ሎቲቶ የሰጡት አስተያየት ላይ ተቃውሟቸውን ገልጸዋል።

የላዝዮ ፕሬዝዳንት ክላውዲዮ ሎቲቶ በትላንትናው ዕለት በሰጡት አስተያየት " የክለቡ ደጋፊዎች ግሪንውድን ከማንችስተር ዩናይትድ ማስፈረም ከፈለጉ ገንዘብ መክፈል አለባቸው " ሲሉ ተናግረው ነበር።

የክለቡ ደጋፊዎች ዛሬ ቡድኑ የቅድመ ውድድር ልምምድ በሚያደርግበት ስፍራ " ለተጨዋቾች ግዢ እርዳታ " የሚል ፅሁፍ የያዘ የእርዳታ ማሰባሰቢያ ሳጥን በማስቀመጥ ተቃውመዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ማርሴይ ግሪንውድን ለማስፈረም ተስማማ ! ማርሴይ እንግሊዛዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ሜሰን ግሪንውድ ለማስፈረም ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል። ማንችስተር ዩናይትድ ለተጨዋቹ ዝውውር የቀረበለትን አጠቃላይ 31 ሚልዮን ዩሮ የሚደርስ የዝውውር ሒሳብ መቀበሉ ተነግሯል። በተጨማሪም ማንችስተር ዩናይትድ ከወደፊቱ የተጨዋቹ ሽያጭ ከግማሽ በላይ የሚሆነውን ገንዘብ ለመውሰድ ከስምምነት…
ግሪንውድ ማርሴይን ለመቀላቀል ተስማማ !

እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጨዋች ሜሰን ግሪንውድ የፈረንሳዩን ክለብ ማርሴይ ለመቀላቀል በቃል ደረጃ ከስምምነት መድረሱ ይፋ ተደርጓል።

ማርሴይ ከሳምንት በፊት ተጫዋቹን በ31 ሚልዮን ዩሮ ለማስፈረም ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ከስምምነት መድረሳቸው ይታወሳል።

የ 22ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ሜሰን ግሪንውድ በቀጣይ የህክምና ምርመራውን ለማድረግ እንደሚጓዝ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/05 05:27:28
Back to Top
HTML Embed Code: