Telegram Web Link
#CopaAmerica2024

የኮፓ አሜሪካ የፍፃሜ ውድድር በመካሄድ ላይ ሲገኝ ኮሎምቢያ እና አርጀንቲና እያደረጉ የሚገኙት መርሐ ግብር ያለ ግብ 0ለ0 በሆነ ውጤት መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቋል።

የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ ባጋጠመው ጉዳት ተቀይሮ ሲወጣ በተጠባባቂ ወንበር ላይ በከፍተኛ ሀዘን ውስጥ ሆኖ ተይቷል።

የጨዋታው መጀመሪያ ሰዓት በደጋፊዎች ችግር ምክንያት ለሶስት ጊዜያት ሊቀያየር ችሏል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
አርጀንቲና ሻምፒዮን ሆነዋል!

የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን በሀገረ አሜሪካ የተዘጋጀውን የኮፓ አሜሪካ ውድድር አሸናፊ በመሆን አጠናቀዋል።

120 ደቂቃዎችን በፈጀው መርሐ ግብር አርጀንቲና በላውታሮ ማርቲኔዝ ብቸኛ ግብ ኮሎምቢያን 1ለ0 መርታት ችላለች።

በአሰልጣኝ ሊዮኔል ስካሎኒ የሚመሩት አርጀንቲናዎች ውድድሩን ለተከታታይ ጊዜ ማሸነፍ ችለዋል።

የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን የኮፓ አሜሪካን ሲያሸንፍ በታሪክ ለአስራ ስድስተኛ ጊዜ ሆኖ ተመዝግቧል።

ላውታሮ ማርቲኔዝ በኮፓ አሜሪካው አምስት ጎሎችን በማስቆጠር የውድድሩ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ሆኗል።

አርጀንቲና ኮፓ አሜሪካውን ማሸነፏን ተከትሎ በፊናሌሲማ የዋንጫ ጨዋታ የዩሮ አሸናፊዋን ስፔን የምትገጥም ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባሎንዶር ለሮድሪጎ ስጡት “

የአውሮፓ ዋንጫ አሸናፊዋ ስፔን ዋና አሰልጣኝ ሉዊስ ዴ ላፉንቴ ባሎን ዶር ሮድሪጎ እንደሚገባው ከድሉ በኋላ በሰጡት አስተያየት ተደምጠዋል።

አሰልጣኙ “ ባሎን ዶርን ለሮድሪጎ ስጡት “ ሲሉ ሲደመጡ የአለማችን ምርጡ ተጫዋቾች በስብስቤ ውስጥ አሉኝ “ በማለት የቡድኑን አባላት አድንቀዋል።

የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች ሮድሪጎ በበኩሉ “ ስፔናዊ ተጫዋች ባሎንዶር ቢያሸንፍ ደስ ይለኛል ፣ የስፔን እግር ኳስ ደረጃን አሳይተናል “ በማለት ተናግሯል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ኦባምያንግ ወደ ሳውዲ አረቢያ ሊያመራ ይችላል !

ጋቦናዊው የኦሎምፒክ ማርሴይ የፊት መስመር ተጨዋች ኦባምያንግ በቀጣይ ወደ ሳውዲ አረቢያ ሊግ ሊያመራ እንደሚችል እየተዘገበ ይገኛል።

ተጫዋቹን ለማስፈረም በቅርቡ ናቾን ከሪያል ማድሪድ በይፋ ያስፈረመው የሳውዲ ሊጉ ክለብ አል ቃዲሲያ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ ተገልጿል።

ማርሴይ ኦባምያንግን ማቆየት እንደሚፈልጉ ቢገለፅም የወደፊት ቆይታው የሚወሰነው በራሱ በተጨዋቹ እንደሚሆን ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሙለር ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ ሊያገል ነው ! የጀርመን ብሔራዊ ቡድን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ቶማስ ሙለር ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ ለማግለል ከውሳኔ መድረሱ ተገልጿል። የ 34ዓመቱ ተጨዋች ቶማስ ሙለር ለጀርመን ብሔራዊ ቡድን አንድ መቶ ሰላሳ አንድ ጨዋታዎችን ማድረግ ችሏል። ቶማስ ሙለር ከጀርመን ብሔራዊ ቡድን ጋር አንድ የአለም ዋንጫን ማሸነፍ ችሏል። @tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቶማስ ሙለር ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ አገለለ !

የጀርመን ብሔራዊ ቡድን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ቶማስ ሙለር ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ ማግለሉን በማህበራዊ ትስስር ገፁ ይፋ አድርጓል።

ከአስራ አራት አመታት በላይ ለጀርመን ብሔራዊ ቡድን ግልጋሎት የሰጠው ቶማስ ሙለር አንድ መቶ ሰላሳ አንድ ጨዋታዎችን ማድረግም ችሏል።

የ 34ዓመቱ ተጨዋች ቶማስ ሙለር ከጀርመን ብሔራዊ ቡድን ጋር አንድ የአለም ዋንጫን ማሸነፍ ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የሁዋን ጋምፐር ዋንጫ መቼ ይደረጋል ?

በካታላኑ ክለብ ባርሴሎና አዘጋጅነት ለሀምሳ ዘጠነኛ ጊዜ የሚካሄድው የሁዋን ጋምፐር ዋንጫ ውድድር የሚደረግበት ቀን ታውቋል።

የዘንድሮው የባርሴሎና የሁዋን ጋምፐር ዋንጫ ውድድር ተጋጣሚ የፈረንሳዩ ክለብ ሞናኮ መሆኑ ይፋ ተደርጓል።

ጨዋታው ነሐሴ 6/2016 ዓ.ም በስታድ ሉዊስ ኮምፓኒ እንደሚደረግ ተገልጿል።

@tikvahethsport           @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ዩናይትድ ተጫዋቹን ሊሸጥ ነው ! ማንችስተር ዩናይትድ ፈረንሳዊውን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ዊሊ ካምብዋላ ለስፔኑ ክለብ ቪያሪያል ለመሸጥ ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል። ቪያሪያል ተጨዋቹን በ10 ሚልዮን ዩሮ ለመግዛት ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ከስምምነት መድረሳቸው ተነግሯል። ተጨዋቹ በቀጣይ የህክምና ምርመራውን በማድረግ ቪያሪያልን በይፋ ለመቀላቀል ቀጠሮ እንደተያዘለት ተዘግቧል። @tikvahethsport    …
ዩናይትድ ከተጫዋቹ ጋር በይፋ ተለያየ !

ፈረንሳዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ዊሊ ካምብዋላ ማንችስተር ዩናይትድን በመልቀቅ የስፔኑን ክለብ ቪያሪያል መቀላቀሉ ይፋ ተደርጓል።

ማንችስተር ዩናይትዶች ከተጨዋቹ ዝውውር አጠቃላይ11.5 ሚልዮን ዩሮ የሚደርስ የዝውውር ሒሳብ እንደሚቀበሉ ተነግሯል።

ተጨዋቹ በማንችስተር ዩናይትድ ቤት አንድ አመት ውል ቀርቶት የነበረ ሲሆን ውሉን ለማራዘም የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ አድርጎ እንደነበር ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
•PlayStation 5, 73,000 Birr
•Playstaion 5 Slim, 78,000 Birr

•PlayStation 4 Slim, 35,000 Birr
•PlayStation 4 Pro, 43,000 Birr

•Playstaion portal, 35,000 Birr
•Meta Quest 2, 55,000 Birr
•Meta Quest 3, 83,000 Birr

Contact
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
Forwarded from WANAW SPORT
📢 ውብ ማልያዎች በተመጣጣኝ ዋጋ!

👉🏾 #ያናግሩን፣ ምርጫዎን ይዘዙን!

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ወይም በቴሌግራም ቦት @WanawSportBot ይዘዙን።

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
TIKVAH-SPORT
አርሰናል ተጫዋቹን በውሰት ሊሰጥ ነው ! የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የመሐል ሜዳ ተጨዋቹ ሳምቢ ሎኮንጋ በውሰት የላሊጋውን ክለብ ሲቪያ ለመቀላቀል ከጫፍ መድረሱ ተገልጿል። ሲቪያ የተጫዋቹን ሙሉ ደሞዝ ለመክፈል ከስምምነት መድረሳቸው ሲገለፅ እንዲሁም በሚቀጥለው አመት በ12 ሚልዮን ዩሮ የመግዛት አማራጭ እንደሚካተትላቸው ተነግሯል። ቤልጂየማዊው ተጨዋች ሎኮንጋ በቀጣይ የህክምና ምርመራውን በማድረግ…
አርሰናል ተጫዋቹ በውሰት አመራ !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሳምቢ ሎኮንጋ በውሰት የላሊጋውን ክለብ ሲቪያ መቀላቀሉ ይፋ ተደርጓል።

ሲቪያ ቤልጂየማዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሎኮንጋ በሚቀጥለው አመት በ12 ሚልዮን ዩሮ የመግዛት አማራጭ እንዳላቸው ተገልጿል።

ሲቪያ በውሰት ቆይታው የተጫዋቹን ሙሉ ደሞዝ እንደሚከፍሉ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሮናልድ አራውሆ ቀዶ ጥገና ሊያደርግ ይችላል !

የባርሴሎና እና ዩራጓይ ብሔራዊ ቡድን የመሐል ተከላካይ ሮናልድ አራውሆ ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት የቀዶ ጥገና ህክምና ሊደረግለት እንደሚችል ተገልጿል።

ተጨዋቹ ዩራጓይ ከብራዚል ባደረገችው የኮፓ አሜሪካ የምድብ ጨዋታ ወቅት ጉዳት አስተናግዶ በመጀመሪያው አጋማሽ ተቀይሮ ለመውጣት ተገዶ ነበር።

ሮናልድ አራውሆ ቀዶ ጥገናውን የሚያደርግ ከሆነ እስከ ታህሳስ ወር ከሜዳ ሊርቅ እንደሚችል ሲገለፅ የመጀመሪያው የኤል ክላሲኮ ጨዋታም ያመልጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጆርዳን ሻኪሪ ከብሔራዊ ቡድኑ ራሱን አገለለ !

የስዊዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ጆርዳን ሻኪሪ በ31ዓመቱ ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ ማግለሉን በይፋ አስታውቋል።

" በብሔራዊ ቡድኑ በነበረኝ የአስራ አራት አመታት ቆይታ የማይረሱ ቅፅበቶች አልፈዋል፣ አሁን ጊዜው የመሰናበቻ ነው ጥሩ ትዝታዎች አሁንም ይኖራሉ ሁሉንም አመሰግናለሁ።" ሲል ጆርዳን ሻኪሪ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አልቫሮ ሞራታ ኤሲ ሚላንን ለመቀላቀል ተስማማ !

የስፔን ብሔራዊ ቡድን አምበል አልቫሮ ሞራታ አትሌቲኮ ማድሪድን በመልቀቅ የሴርያውን ክለብ ኤሲ ሚላን ለመቀላቀል ከስምምነት መድረሱ ተገልጿል።

ተጨዋቹ በኤሲ ሚላን ቤት የአራት አመታት ኮንትራት ለመፈረም በቃል ደረጃ ከስምምነት መድረሱ ተነግሯል።

ኤሲ ሚላን አልቫሮ ሞራታን የውል ማፍረሻውን 13 ሚልዮን ዩሮ ከፍለው እንደሚያስፈርሙት ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ዩናይትድ የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ ሊቀጥር ነው ! ማንችስተር ዩናይትድ ያለፈውን የውድድር አመት በበርንሌይ ቤት ያሳለፉትን የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ ጄሌ ቴን ሮዌላርን በሀላፊነት ሊሾሙ መሆኑ ተገልጿል። የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኙ በቅርቡ ከበርንሌይ ጋር ከተለያዩ በኋላ አያክስን የተቀላቀሉ ቢሆንም ማንችስተር ዩናይትድ ካሳ ከፍሎ ለመውሰድ እየሰራ መሆኑ ተገልጿል። ያለፉትን አምስት አመታት በማንችስተር…
ዩናይትድ የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ ሾመ !

ማንችስተር ዩናይትድ ያለፈውን የውድድር አመት በበርንሌይ ቤት ያሳለፉትን የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ ጄሌ ቴን ሮዌላርን በሀላፊነት መሾማቸውን ይፋ አድርገዋል።

የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኙ በቅርቡ ከበርንሌይ ጋር ከተለያዩ በኋላ አያክስን የተቀላቀሉ ቢሆንም ማንችስተር ዩናይትድ ካሳ ከፍሎ እንዳስፈረማቸው ተገልጿል።

" እሱ በእንግሊዝ እግርኳስ ጥሩ ልምድ አለው ቡድኑን እንደሚያግዝ እርግጠኛ ነኝ በተለይ ግብ ጠባቂዎች ከሌሎች ጋር እንዲዋሀድ ይረዳል።"ሲሉ ኤሪክ ቴንሀግ ስለ አሰልጣኙ ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ፉልሀም ስሚዝ ሮውን ማስፈረም ይፈልጋል ! ፉልሀም እንግሊዛዊውን የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኤሚል ስሚዝ ሮው የማስፈረም ፍላጎት እንዳላቸው ተገልጿል። አሰልጣኝ ማርኮ ሲልቫ በቀጣይ የፊት መስመራቸውን ለማጠናከር ከሚመለከቷቸው ተጨዋቾች ቀዳሚው ኤሚል ስሚዝ ሮው እንደሚሆን ተዘግቧል። ፉልሀም ተጨዋቹን ለማስፈረም የዝውውር መስኮቱ ሲከፍት ጥያቂያቸውን ሊያቀርቡ እንደሚችሉ ተነግሯል።…
አርሰናል ለተጫዋቹ የቀረበውን ጥያቄ ውድቅ አደረገ !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ክሪስታል ፓላስ እና ፉልሀም ስሚዝ ሮውን ለማስፈረም ያቀረቡትን የዝውውር ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ ተገልጿል።

መድፈኞቹ ሁለቱ ክለቦች የዝውውር ሒሳቡን አሻሽለው እንዲቀርቡ በንግግር ላይ መሆናቸው ሲገለፅ ተጨዋቹ በበኩሉ ሁሉንም አማራጮች መመልከት እንደሚፈልግ ተነግሯል።

እንግሊዛዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኤሚል ስሚዝ ሮው በመድፈኞቹ ቤት ብዙም የጨዋታ ሰዓት ባለማግኘቱ ምክንያት ክለቡን ሊለቅ እንደሚችል ሲገለፅ እንደነበር ይታወሳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የኤደርሰን የማንችስተር ሲቲ ቆይታ ? ብራዚላዊው የማንችስተር ሲቲ ግብ ጠባቂ ኤደርሰን ከሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ኢትሀድ የዝውውር ጥያቄ እንደቀረበለት እና እያሰበበት እንደሚገኝ ተገልጿል። ኤደርሰን በክረምቱ የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ጥሩ የዝውውር ጥያቄዎች ከቀረቡለት ማንችስተር ሲቲን ለመልቀቅ ሊያስብ እንደሚችል መገለፁ ይታወቃል። ማንችስተር ሲቲ በበኩሉ ተጫዋቹ በክለቡ እንዲቀጥል እንደሚፈልጉ…
አል ናስር ለኤደርሰን የዝውውር ጥያቄ አቀረበ !

የሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ናስር ብራዚላዊውን ግብ ጠባቂ ኤደርሰን ለማስፈረም ለማንችስተር ሲቲ ይፋዊ የዝውውር ጥያቄ ማቅረባቸው ተገልጿል።

አል ናስር ለዝውውሩ 30 ሚልዮን ዩሮ የሚደርስ የዝውውር ሒሳብ ሲያቀርቡ ማንችስተር ሲቲ በበኩሉ ውድቅ ማድረጉ ተነግሯል።

ማንችስተር ሲቲ ኤደርሰንን ከለቀቀው ከ 50 ሚልዮን ዩሮ በላይ እንደሚፈልግ የተገለፀ ሲሆን ተጨዋቹ ከአል ናስር ጋር በግል ከስምምነት ደርሰዋል ተብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/01 17:35:22
Back to Top
HTML Embed Code: