Telegram Web Link
" የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲፈርደኝ እፈልጋለሁ " ፍሬወይኒ ሀይሉ

ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ፍሬወይኒ ሀይሉ ያለአግባብ በፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር ተሳታፊ አትሌቶች ዝርዝር ውስጥ ሳልካተት ቀርቻለሁ ስትል ቅሬታዋን ህዝብ ይወቅልኝ በማለት ገልፃለች።

በ1500 እና 5000 ሜትር ተወዳዳሪ መሆኗን ያስታወሰችው አትሌት ፍሬወይኒ ሀይሉ በአመቱ ውስጥ በሁለቱም ርቀቶች ከሌሎች አትሌቶች የተሻለ ውጤት አስመዝግቤ ነበር ትላለች።

አትሌቷ በ2024 የቤት ውስጥ ሻምፒዮና በ1500ሜ ወርቅ እና የተሻለ ሰዓት እንዲሁም በ5000ሜ የ2024 የአለም ምርጥ 3ኛ ሰዓት ባስመዘግብም ከሁለቱም ርቀቶች ከኦሎምፒክ ውጪ ሆኛለሁ ብላለች።

አትሌት ፍሬወይኒ ሀይሉ ቀጥላም " እኔ በዚህ አመት የተሻለ ሰዓት ባስመዘግብም ከአመት በፊት ጥሩ ውጤት ያላቸው አትሌቶች ተመርጠው እኔ ቀርቻለሁ የኢትዮጵያ ህዝብ ይወቅልኝ።

በ2024 ምንም ውድድር ሳይወዳደሩ የ2023 አላቸው ተብሎ መምረጥ አግባብ አይደለም ለምን በሀቀኝነት አይመረጥም ምንም ሳይሮጡ እየተመረጡ ነው እኛ ግን ደክመንም እየቀረን ነው።

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ እና አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለምንድን ነው የእኛን ማየት የማይችለው በዚህ ላይ ማብራሪያም እፈልጋለሁ።"ስትል ተናግራለች።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በትላንትናው ዕለት ኢትዮጵያን በኦሎምፒክ የሚወክሉ አትሌቶችን ይፋ ሲያደርግ አትሌት ፍሬወይኒ ሀይሉ የ5000ሜ ተጠባባቂ ሆና ተመርጣለች።

ምንጭ - ሀገሬ ቴሌቪዥን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዌስትሀም ዩናይትድ ተጨዋች አስፈረሙ !

ዌስትሀም ዩናይትድ እንግሊዛዊውን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ማክስ ኪልማን ከዎልቭስ ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ዌስትሀም ለተጨዋቹ ዝውውር 40 ሚልዮን ፓውንድ ወጪ ማድረጋቸው ሲነገር ተጨዋቹ በክለቡ የሰባት አመት ኮንትራት መፈረሙ ተገልጿል።

" ዌስትሀም እንደሚፈልገኝ ሳውቅ ለመቀላቀል ፈልጊያለሁ ፣ ዌስትሀም ትልቅ ክለብ ነው የእግርኳስ ህይወቴ አንድ እርምጃ እንዳደገ ይሰማኛል።"ሲል ማክስ ኪልማን ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አዲዳስ የጫማ ምርቱን ስያሜ በክሩስ ስም ሰየመ !

እውቁ የትጥቅ አምራች ተቋም አዲዳስ ቶኒ ክሩስ በብቸኝነት እስካሁን እየተጠቀመው የሚገኘውን " adidas 11pro " ጫም ስያሜ በክሩስ ስም መቀየሩን ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት የእግርኳስ መጫወቻ ጫማ ምርቱ ስያሜ ከዚህ በኋላ " Toni Kroos Pro boots " ተብሎ እንደሚጠራ ተገልጿል።

ጀርመናዊው ታሪካዊ ተጨዋች ቶኒ ክሩስ ባለፉት አስራ ሶስት አመታት ተመሳሳይ የአዲዳስ " adidas 11pro " ምርት የሆነ ጫማን ሲጠቀም እንደነበር ይታወቃል።

ቶኒ ክሩስ በቀድሞው የአዲዳስ " adidas 11pro " ምርት የሆነ ጫማ እየተጫወተ የሚያሻማቸው ኳሶች ትክክለኛነታቸው ከ90% በላይ እንደነበር ተገልጿል።

ስኬታማ የእግርኳስ ህይወት ማሳለፍ የቻለው ቶኒ ክሩስ ከእግርኳስ አለም ራሱን ማግለሉ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" አላማችን ሊጉን ማሸነፍ መሆን አለበት " አርኔ ስሎቶ

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ዋና አሰልጣኝ አርኔ ስሎት በሚቀጥለው የውድድር አመት አላማቸው የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ዋንጫን ማሳካት እንደሆነ ገልጸዋል።

" በቀጣይ አላማችን እና ሙሉ ትኩረታችን የፕርሚየር ሊጉን ዋንጫ ማሳካት ላይ መሆን አለበት " የሚሉት አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ይህ ማድረግ የምንፈልገው ነገር ነው የሊጉ የበላይ መሆን እንፈልጋለን ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቶኒ ክሩስ ፔድሪን ይቅርታ ጠይቋል !

ጀርመናዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ቶኒ ክሩስ ትላንት በስፔን በተሸነፉበት ጨዋታ ፔድሪ ላይ ለሰራው ጥፋት በማህበራዊ ትስስር ገፁ ተጫዋቹን ይቅርታ ጠይቋል።

" ፔድሪ ጉዳት እንዲያጋጥመው ሆንብዬ አስቤ አልነበረም ጥፋቱን የሰራሁት " ያለው ቶኒ ክሩስ ይቅርታ ማለት እና ቶሎ እንድትመለስ መመኘት እፈልጋለሁ አንተ ምርጥ ተጨዋች ነህ።"ሲል ተናግሯል።

በጨዋታው ፔድሪ ባጋጠመው ከባድ ጉዳት ምክንያት ተቀይሮ ለመውጣት መገደዱ የሚታወስ ሲሆን በቀጣይ በአውሮፓ ዋንጫ ጨዋታዎች ይሳተፋል ተብሎ አይጠበቅም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የቱርክ ደጋፊዎች የኔዘርላንድን ተጨዋቾች ለመረበሽ ሞክረዋል !

የአውሮፓ ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታቸውን ከኔዘርላንድ ጋር የሚያደርጉት ቱርክ ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች የተጋጣሚያቸውን ደጋፊዎች ለመረበሽ መሞከራቸው ተገልጿል።

የቱርክ ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች ትላንት ሌሊት የኔዘርላንድ ተጨዋቾች ባረፉበት ሆቴል በማምራት ርችት እና ተቀጣጣይ ነገሮችን በማጮህ ለመረበሽ መሞከራቸው ተነግሯል።

የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ ዛሬ ምሽት 4:00 ሰዓት በርሊን በሚገኘው ግዙፉ ኦሎምፒያስታድዮን ስታዲየም ይደረጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
📢 #ዋናው የቴሌግራም ቦት እንዴት የስፖርት አልባሳትን ያዛሉ?

🤖 @WanawSportBot 🤖

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
TIKVAH-SPORT
ቶኒ ክሩስ ፔድሪን ይቅርታ ጠይቋል ! ጀርመናዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ቶኒ ክሩስ ትላንት በስፔን በተሸነፉበት ጨዋታ ፔድሪ ላይ ለሰራው ጥፋት በማህበራዊ ትስስር ገፁ ተጫዋቹን ይቅርታ ጠይቋል። " ፔድሪ ጉዳት እንዲያጋጥመው ሆንብዬ አስቤ አልነበረም ጥፋቱን የሰራሁት " ያለው ቶኒ ክሩስ ይቅርታ ማለት እና ቶሎ እንድትመለስ መመኘት እፈልጋለሁ አንተ ምርጥ ተጨዋች ነህ።"ሲል ተናግሯል። በጨዋታው ፔድሪ…
ፔድሪ በብሔራዊ ቡድኑ ስብስብ ይቆያል !

የስፔን ብሔራዊ ቡድን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ፔድሪ ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት በቀጣይ በአውሮፓ ዋንጫው በሚኖሩ ጨዋታዎች መሳተፍ እንደማይችል ይፋ ሆኗል።

ይሁን እንጂ የባርሴሎናው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ፔድሪ እስከ ውድድሩ መጨረሻ በስፔን ብሔራዊ ቡድን ስብስብ እንደሚቆይ ተገልጿል።

ፔድሪ ያጋጠመው የጉልበት ጉዳት እስከ አንድ ወር ከሜዳ ሊያርቀው እንደሚችል ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

1:00 እንግሊዝ ከ ስዊዘርላንድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሻምፒዮን ሆነ !

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከኢትዮጵያ መድን ጋር ያደረገውን የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የመጨረሻ ሳምንት መርሐ ግብር 2ለ0 በማሸነፍ ሻምፒዮን መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

ንግድ ባንክ በውድድር ዘመኑ የሰበሰባቸውን ነጥቦች ስልሳ አራት በማድረስ ከመቻል በአንድ ነጥብ በልጠው የሊጉ አሸናፊ ሆነዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወደ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ በመጣበት አመት በታሪኩ የመጀመሪያው የሆነውን የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ዋንጫ ማሳካት ችሏል።

ኤርትራዊው የሀዋሳ ከተማ የፊት መስመር ተጨዋች ዓሊ ሱሌይማን በውድድር ዘመኑ ሀያ የሊግ ግቦችን በማስቆጠር ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በመሆን አጠናቋል።

ሀምበሪቾ ዱራሜ እና ሻሸመኔ ከተማ ከኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ወደ ከፍተኛ ሊግ የወረዱ ክለቦች ናቸው።

ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና አርባምንጭ ከተማ በበኩላቸው በሚቀጥለው አመት ወደ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አድገዋል።

በተጨማሪም ከውድድር ውጪ የነበሩት የትግራይ ክልል ክለቦች መቐለ ሰባ እንደርታ ፣ ስሑል ሽረ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርስቲ ቀጣይ አመት ወደ ሊጉ ይመለሳሉ።

በሚቀጥለው የ2017 የውድድር አመት የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ በአስራ ዘጠኝ ክለቦች መካከል የሚደረግ ሲሆን አምስት ክለቦች ወደ ከፍተኛ ሊግ ይወርዳሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" የባንካችንን ስም የሚመጥን ቡድን በመሆኑ ተደስተናል " አቶ አቤ ሳኖ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ ኤቤ ሳኖ ከሶስት አመታት በፊት በድጋሜ እንዲቋቋም ያደረጉት የባንኩ የእግርኳስ ቡድን ሻምፒዮን በመሆኑ መደሰታቸውን ገልጸዋል።

" ከፍተኛ ደስታ ነው የተሰማኝ ለንግድ ባንክ አዲስ ታሪክ ነው " ሲሉ የገለፁት ፕሬዝዳንቱ ክለቡ ረጅም ታሪክ ቢኖረውም በሶስት አመት ተሰርቶ ሻምፒዮን ሆኗል ፣ ባንካችንን ስሙን የሚመጥን ቡድን በመሆኑ ደስተኞች ነን ብለዋል።

ክለቡ ዋንጫውን ባያሳካም በድጋሜ በማቋቋማቸው እንደማይፀፀቱ የገለፁት ፕሬዝዳንት ኤቤ ሳኖ የሀገሪቱ ትልቅ ተቋም ስፖርቱ ላይ መስራት አለበት በቀጣይም እቅዶች አሉን ብለዋል።

ባንኩ ያለውን ስታዲየም ጥራት ያለው አድርጎ የመስራት እቅድ መያዙን እና ራሱ በሚያሳድጋቸው ተጨዋቾች ቡድን ሰርቶ ለሀገር የሚጠቅሙ ስፖርተኞች ማፍራት እንደሚፈልግ ፕሬዝዳንቱ ጨምረው ገልጸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እረፍት | እንግሊዝ 0 - 0 ስዊዘርላንድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
75 ' እንግሊዝ 0 - 1 ስዊዘርላንድ

ኢምቦሎ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
80 ' እንግሊዝ 1 - 1 ስዊዘርላንድ

ሳካ                   ኢምቦሎ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/03 04:25:22
Back to Top
HTML Embed Code: