Telegram Web Link
" መጥፎ እድል አብሮን ነበር " ዴብሮይን

የቤልጅየም ብሔራዊ ቡድን ተጨዋች ኬቨን ዴብሮይን በምሽቱ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ቡድናቸው እድለኛ እንዳልነበረ ከጨዋታው በኋላ በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

" ጥሩ መጫወት ብንችልም ያገኘነውን አጋጣሚ መጠቀም አልቻልንም " ያለው ዴብሮይን ያልሆነ ኳስ ተቆጥሮብናል በዛሬው ጨዋታ መጥፎ እድል ነበረን እጅግ ያበሳጫል ሲል ተደምጧል።

" በግል በውድድሩ ጥሩ ጊዜ ነበረኝ ቡድኑን ለማገዝ ሁሉንም ነገር ሰጥታቻለሁ ፣ ያገኘኋቸውን የግብ እድሎች አልተጠቀምኩም ይህ አለመታደል ነው ነገርግን ሁሉንም ሰጥቻለሁ።" ዴብሮይን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" በራስ ላይ የሚቆጠር ግብ የፈረንሳይ ምርጥ አጥቂ ሆኗል " ቼሊኒ

የቀድሞ ጣልያናዊ ተከላካይ ጆርጂዮ ቼሊኒ በአውሮፓ ዋንጫው በራስ ላይ የሚቆጠር ግብ " የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ምርጥ አጥቂ ሆኗል " በማለት ከምሽቱ ጨዋታ በኋላ ተናግሯል።

የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን በአውሮፓ ዋንጫው ባደረጋቸው አራት ጨዋታዎች በጨዋታ ምንም ግብ ሳያስቆጥር ሩብ ፍፃሜ መድረስ የቻለ በውድድሩ ታሪክ የመጀመሪያው ብሔራዊ ቡድን ሆኗል።

ፈረንሳይ ባደረገቻቸው ጨዋታዎች ካስቆጠረቻቸው ሶስት ጎሎች ሁለት ግቦቿ በተቃራኒ ተጨዋቾች በራስ ላይ ሲቆጠሩ አንድ ግብ በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አርሰናል ዴቪድ ራያን በቋሚነት አስፈርሟል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በውሰት ከብሬንትፎርድ ያስፈረሙትን ስፔናዊ ግብ ጠባቂ ዴቪድ ራያ ኮንትራት የመግዛት አማራጫቸውን ተጠቅመው ቋሚ ማድረጋቸው ተገልጿል።

መድፈኞቹ ለግብ ጠባቂው የዝውውር ሒሳብ በውሉ ውስጥ ተካቶ የነበረውን የመግዛት አማራጭ ሒሳብ 27 ሚልዮን ፓውንድ መክፈላቸው ተነግሯል።

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የወርቅ ጓንት አሸናፊው ዴቪድ ራያ አሁን ላይ በይፋ የአርሰናል ተጨዋች መሆኑ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#እረፍት

ፖርቹጋል 0 - 0 ስሎቬኒያ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
55 '

ፖርቹጋል 0 - 0 ስሎቬኒያ

- ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአውሮፓ ዋንጫው አስራ ስድስት የግብ ሙከራዎች አድርጎ ግብ ያላስቆጠረ የመጀመሪያው ተጨዋች ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#ተጠናቀቀ

ፖርቹጋል 0 - 0 ስሎቬኒያ

- ጨዋታው በአቻ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ ተጨማሪ ሰላሳ ደቂቃ አምርተዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
105 '

ፖርቹጋል 0 - 0 ስሎቬኒያ

- ክርስቲያኖ ሮናልዶ ያገኘውን የፍፁም ቅጣት ምት መጠቀም ሳይችል ቀርቷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
112 '

ፖርቹጋል 0 - 0 ስሎቬኒያ

- የስሎቬኒያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ማጃዝ ኬክ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብተዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#ተጠናቀቀ

ፖርቹጋል 0 - 0 ስሎቬኒያ

- ጨዋታው በአቻ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች ወደ መለያ ምት አምርተዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የመለያ ምት ተጀምሯል !

🇵🇹 ፖርቹጋል

🇸🇮 ስሎቬንያ

ውጤት በዚሁ ፖስት ላይ " Update " ይደረጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፖርቹጋል ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቀሉ !

በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ጥሎ ማለፍ የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ከስሎቬኒያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ በመለያ ምት 3ለ0 በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል።

ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች መደበኛውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ጨዋታቸውን 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ፖርቹጋላዊው ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ በጨዋታው ያገኘውን የፍፁም ቅጣት ምት መጠቀም ሳይችል ቀርቷል።

የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ ዲያጎ ኮስታ የተመቱበትን ሶስት የመለያ ምቶች በሙሉ መመለስ ችሏል።

የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን በሩብ ፍፃሜው ከፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ጋር አርብ ምሽት 4:00 ሰዓት የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
Forwarded from HEY Online Market
Stock Clearance Discount 2

📞 0925927457 @eBRO4
📞 0953964175 @heymobile

•iP 7+, Black, 128GB, 99% 12K
•iP X, Black, 256 GB, 100%,12K ⚠️
•iP XS, White, 64 GB, 100% 19K
•iP XS Max, Gold, 64GB, 83%, 25K
•iP XS Max, Gold, 256GB, 88% 29K
•iP 11, Red, 64GB, 100% 28K ⚠️
•iP 11, Black, 128GB, 85%, 33K
•iP 11, Purple, 128GB, 88% 33K
•11 Pro, Black, 64GB, 100% 39K ⚠️
•11 Pro, White, 64GB, 87% 36K
•11 Pro Max, Black, 64GB, 86%, 46K

•11 Pro Max, Black, 256GB, -% 40⚠️
•iP 12, Red, 128GB, 88%, 42K
•iP 12, White, 128GB, 88% 42K
•iP 12, Green, 128GB, 86% 42K
•12 Pro, Blue, 128GB, 89% 49K
•12 Pro Max, Blue, 512GB, 84% 64K
•iP 13 Min, Pink, 256GB, 92% 34K
•iP 13, Blueback, 128GB, 90% 56K
•iP 13, Black, 128GB, 92% 49K ⚠️

•iP 13, Red, 128GB, 86%, 56K
•iP 13, Black, 128GB, 89%, 58K
•13 Pro, Golden, 256GB, 87% 69K
•13 Pro, Blue, 512GB/88% 69K ⚠️
•13 ProMax, Black, 128 GB, 87% 74K
•13 ProMax, 256GB, 86%, 64K⚠️
•13 ProMax, 256GB, 85%, 74K⚠️
•13 ProMax, Gold, 256GB, 86%, 79K
•13 Pro Max, Gold, 256 GB,88% 79K
•13 Pro Max, Blue, 256GB, 94% 79K
•13 Pro Max, 1TB, 88%, 69K ⚠️
•13 Pro Max, Blu, 256GB/ -% 70K ⚠️

Exchange Available!
Free Delivery 🚚

@heyonlinemarket
https://heymobile.store/catalogue
" የመጨረሻ አውሮፓ ዋንጫዬ ነው " ሮናልዶ

ፖርቹጋላዊው የአምስት ጊዜ ባሎን ዶር አሸናፊ ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ የዘንድሮው የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር የመጨረሻው መሆኑን በሰጠው አስተያየት አሳውቋል።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ የአውሮፓ ዋንጫን ከፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ጋር ከስምንት አመት በፊት ማሳካት ችሏል።

የ 39ዓመቱ ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ታሪክ በአስራ አራት ግቦች የምንግዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ተጨዋች ነው።

በምሽቱ ጨዋታ ፍፁም ቅጣት ምት በመሳቴ የፖርቹጋልን ህዝብ ይቅርታ እጠይቃለሁ በማለት የተናገረው ሮናልዶ " ግብ ጠባቂያችን አድኖናል " ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#CopaAmerica2024

በኮፓ አሜሪካ ውድድር የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ የውድድሩ አዘጋጅ ሀገር አሜሪካ በዩራጓይ 1ለ0 መሸነፏን ተከትሎ ከውድድሩ ውጪ ሆናለች።

በምድቡ ሌላኛው ጨዋታ ፓናማ ቦሊቪያን 3ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን መቀላቀል ችለዋል።

ምድቡን ዩራጓይ አንደኛ እንዲሁም ፓናማ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል።

በሩብ ፍፃሜው ዩራጓይ ከመጨረሻው ምድብ ሁለተኛ እንዲሁም ፓናማ አንደኛ ደረጃን ይዞ ከሚያጠናቅቅው ቡድን ጋር ይገናኛሉ።

የኮፓ አሜሪካ የመጨረሻው ምድብ የመጨረሻ ጨዋታዎች ዛሬ ቀጥለው ሲደረጉ :-

ሌሊት 10:00 - ብራዚል ከ ኮሎምቢያ

ሌሊት 10:00 - ኮስታሪካ ከ ፓራጓይ ጋር ይጫወታሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሊዮኔል ሜሲ ወደ ልምምድ ተመልሷል !

አርጀንቲናዊው የስምንት ጊዜ ባሎን ዶር አሸናፊ ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ ካጋጠመው መጠነኛ ጉዳት በማገገም ወደ ብሔራዊ ቡድኑ ልምምድ መመለሱ ተገልጿል።

ይሁን እንጂ ሊዮኔል ሜሲ አርጀንቲና ሐሙስ ሌሊት 10:00 ከኢኳዶር ጋር በምታደርገው የኮፓ አሜሪካ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ መድረሱ አሁንም አጠራጣሪ መሆኑ ተነግሯል።

ሊዮኔል ሜሲ ከቀናት በፊት አርጀንቲና ከፔሩ ጋር ያደረገችው የኮፓ አሜሪካ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ እንዳመለጠው የሚታወስ ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሁዋን ጋርሽያ ወደ አርሰናል ?

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በዚህ ክረምት የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ከአሮን ራምስዴል ጋር የሚለያዩ ከሆነ አዲስ ግብ ጠባቂ እንደሚመለከቱ ተገልጿል።

መድፈኞቹ አሮን ራምስዴል ከለቀቀ ለመተካት የሚመለከቱት ግብ ጠባቂ ስፔናዊው የእስፓኞል ግብ ጠባቂ ሁዋን ጋርሽያ እንደሚሆን ለክለቡ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ገልጸዋል።

በአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የሚመሩት አርሰናሎች በውሰት የነበረውን ዴቪድ ራያ በቋሚነት ማስፈረማቸው ይታወቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቶተንሀም ተጨዋች ለማስፈረም አነጋግረዋል ! የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም እንግሊዛዊውን ወጣት የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች አርቼ ግሬይ ከሊድስ ዩናይትድ ለማስፈረም ንግግር ላይ መሆናቸው ተገልጿል። የ 18ዓመቱ ተጨዋች አርቼ ግሬይ ቶተንሀምን መቀላቀል እንደሚፈልግ የተገለፀ ሲሆን በቀጣይ ክለቦቹ ከስምምነት ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል። ሊድስ ዩናይትድ ተጨዋቹን ለማስፈረም ከብሬንትፎርድ የቀረበላቸውን…
ቶተንሀም ተጨዋች በይፋ አስፈርመዋል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም እንግሊዛዊውን ወጣት የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች አርቼ ግሬይ ከሊድስ ዩናይትድ ማስፈረማቸውን በይፋ አስታውቀዋል።

የ 18ዓመቱ ተስፈኛ ተከላካይ አርቼ ግሬይ በቶተንሀም ቤት እስከ 2030 የሚያቆየውን የስድስት አመት ኮንትራት መፈረሙ ተገልጿል።

ቶተንሀም ለዝውውሩ 40 ሚልዮን ፓውንድ ማውጣታቸው ሲገለፅ ተጨዋቹ በቶተንሀም የአስራ አራት ቁጥር ማልያ እንደሚለብስ ተጠቁሟል።

ቶተንሀም አርቼ ግሬይን ከሌሎች የሜዳ ክፍሎች በበለጠ የመሐል ሜዳ ተጨዋች አድርጎ ለማጫወት ማሰቡ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#BiniyamGirmay🇪🇷

ኤርትራዊው ብስክሌተኛ ቢንያም ግርማይ በዓለም ላይ ከፍተኛ የሆነ ስፍራ የሚሰጠውን ቱር ደ ፍራንስ የተሰኘውን የፈረንሳዩን የብስክሌት ውድድር ‘ስቴጅ 3’ በማሸነፍ የመጀመሪያው ጥቁር አፍሪካዊ በመሆን ለኤርትራ እና ለአፍሪካ ታሪክ ሰርቷል።

ከውድድሩ መጠናቀቅ በኋላ የውድድሩ ተሳታፊዎች ወደ ቢኒያም በመሄድ " እንኳን ደስ አለህ ! አንተ በጣም ምርጡ ነበርክ ፤ በጣምም ጠንካራ ነህ፤ ለአፍሪካ እና ለዓለም ታሪክ ሰርተሃል ፤ እንኮራብሃለን " ሲሉ አወድሰውታል።

ቢኒያም ፤ " ሁሉንም ጥንካሬ እና ድጋፍ ስለሰጠኝ ስለ ሁሉም ነገር ፈጣሪ ይመስገን " ሲል ተናግሯል።

ኤርትራዊው ቢኒያም በተለያዩ ጊዜያት ባስመዘገበው ስኬት " የአፍሪካ የብስክሌት ንጉሥ " የሚል ስም ተሰጥቶታል።

ኤርትራውያን በተለይ በብስክሌት ግልቢያ በዓለም መድረክ በእጅጉ ይታወቃሉ።

#Eritrea
#NBC_Sport
#BBC
@tikvahethiopia
2024/11/20 06:21:50
Back to Top
HTML Embed Code: