Telegram Web Link
ራፋኤል ቫራን ወደ ኮሞ ?

በቅርቡ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር የተለያየው ፈረንሳዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ራፋኤል ቫራን ጣልያኑን ክለብ ኮሞ ለመቀላቀል በንግግር ላይ መሆኑ ተገልጿል።

ራፋኤል ቫራን አሁን ላይ ከክለቡ ቦርድ እና ከክለቡ አሰልጣኝ ሴስክ ቫብሬጋስ ጋር ለመነጋገር ወደ ጣልያን ኮሞ ማምራቱ ተነግሯል።

በዚህ አመት ወደ ጣልያን ሴርያ ማደጉን ያረጋገጠውን የአሰልጣኝ ሴስክ ቫብሬጋሱ ቡድን ኮሞ ራፋኤልን ቫራንን በነፃ ዝውውር ማስፈረም እንደሚፈልጉ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ኦማሪ ኬሊማን ዛሬ የህክምና ምርመራ ያደርጋል ! እንግሊዛዊውን ወጣት የፊት መስመር ተጨዋች ኦማሪ ኬሊማን ከአስቶን ቪላ ወደ ቼልሲ የሚያደርገውን ዝውውር ለማጠናቀቅ ዛሬ የህክምና ምርመራውን እንደሚያደርግ ተገልጿል። ሰማያዊዎቹ የ 18ዓመቱን የፊት መስመር ተጨዋች ኦማሪ ኬሊማንን ከአስቶን ቪላ በ 19 ሚልዮን ፓውንድ ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ይታወሳል። ተጨዋቹ በክንፍ አጥቂነት ወይም በአጥቂ…
ቼልሲ በይፋ ተጨዋች አስፈርመዋል !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ እንግሊዛዊውን ወጣት የፊት መስመር ተጨዋች ኦማሪ ኬሊማን ከአስቶን ቪላ ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ሰማያዊዎቹ የ 18ዓመቱን የፊት መስመር ተጨዋች ኦማሪ ኬሊማን ለማስፈረም 22 ሚልዮን ዩሮ ወጪ ማድረጋቸው ተገልጿል።

በክንፍ አጥቂነት እንዲሁም በአጥቂ አማካይ ቦታ ተሰልፎ ግልጋሎት መስጠት የሚችለው ኦማሪ ኬሊማን በቼልሲ ቤት የስድስት አመት ኮንትራት መፈረሙ ይፋ ሆኗል።

" ቼልሲ ትልቅ ታሪክ ያለው አስደናቂ ክለብ ነው ወደዚህ መምጣቴ አስደስቶኛል ህልሜ እውን ሆኖልኛል።"ሲል ተጨዋቹ ከፊርማው በኋላ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
🇪🇹 ዋናው 🤝 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ደጋፊዎች ጥምረት 🇪🇹

እግር ኳስን ለቱሪዝም የመጠቀም ዓላማን በማንገብ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ደጋፊዎች ጥምረት ከዋናው ስፖርት ጋር በመሆን ያዘጋጀው የጀልባ ቀዘፋ ውድድር ዛሬ በሃዋሳ ከተማ ይካሄዳል። ከውድድሩ በተጨማሪም ለኢትዮጵያ የልብ ህሙማን መርጃ ማዕከል እርዳታ የገቢ ማሰባሰቢያ በጎ ስራም ይከናወናል።

ዋናው ስፖርትም የዚህ መርሃግብር ዋና አጋር በመሆኑ የተሰማውን ኩራት ለመግለፅ ይወዳል።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
የኢትዮጵያ  ቡና ይፋዊ አጋር የሆነው ቤቲካ - የኢትዮጵያ ቡናን  24ኛ የጨዋታ ቀን የዲጂታል መፅሄት ይዞ ቀርቧል።
በመፅሄቱ ላይ የዕለቱ ጨዋታን የተመለከቱና ሌሎች የተለያዩ መረጃዎች የሚቀርቡ ይሆናል፡፡

መፅሄቱን ለማግኘት ተከታዩን ሊንክ ይጫኑ።

https://www.tg-me.com/betikaethiopia/5366

የጨዋታ መፅሄት ቁጥር 24
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኢትዮጵያ ቡና
ዛሬ 12:00

ቤቲካ - የኢትዮጵያ ቡና ይፋዊ አጋር
" ኩርቱዋ አለመጠራቱ አስደስቶኛል " ካማቪንጋ

የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኤድዋርዶ ካማቪንጋ ቲቧ ኩርቱዋ በቤልጅየም ብሔራዊ ቡድን ስብስብ ውስጥ አለመኖሩ እንዳስደሰተው ገልጿል።

የሰኞ ተጋጣሚያቸው ቤልጂየም ስብስብ ውስጥ የክለብ የቡድን አጋሩ ቲቧ ኩርቱዋ " አለመኖሩ አስደስቶኛል " ሲል የተደመጠው ካማቪንጋ ምክንያቱም እሱ ሁሉንም ኳሶች መያዝ ይችላል ያስቸግረን ነበር በማለት ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጣልያን የተጨዋቾቿን ግልጋሎት አታገኝም !

ጣልያን ዛሬ ምሽት 1:00 ሰዓት ከስዊዘርላንድ ጋር በምታደርገው የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ጥሎ ማለፍ ጨዋታ የተጨዋቾቿን ግልጋሎት የማታገኝ ይሆናል።

በጨዋታው ተከላካዩ ሪካርዶ ካላፊዮሪ በቅጣት ምክንያት እንዲሁም ፌዴሪኮ ዴማርኮ በጉዳት ምክንያት ለብሔራዊ ቡድኑ ግልጋሎት አይሰጡም።

የሮማው ተከላካይ ጂያንሉካ ማንቺኒ በምሽቱ ጨዋታ ሪካርዶ ካላፊዮሪን በመተካት በቋሚ አሰላለፍ እንደሚገባ አሰልጣኝ ሉቺያኖ ስፓሌቲ ገልጸዋል።

በተጨማሪም ከጉንፋን ህመም ያገገመው የኢንተር ሚላኑ ተከላካይ አሌሳንድሮ ባስቶኒ ለጨዋታው መድረሱ አጠራጣሪ መሆኑን አሰልጣኙ ጠቁመዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" አውሮፓ ዋንጫውን ለማሸነፍ ነው የመጣነው " ሳውዝጌት

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት ቡድናቸው ጀርመን የሚገኘው የአውሮፓ ዋንጫውን ለማሸነፍ መሆኑን በሰጡት አስተያየት ገልፀዋል።

" እኛ ወደ ውድድሩ የመጣነው ከምድባችን ለመሰናበት ሳይሆን የአውሮፓ ዋንጫውን አሸንፈን ለመመለስ ነው።" ሲሉ አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት ተናግረዋል።

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ነገ ምሽት 1:00 ሰዓት ከስሎቫኪያ አቻው ጋር የጥሎ ማለፍ ጨዋታውን ያደርጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ልምምድ ላይ ፍፁም ቅጣት ምት አልመልስባቸውም " ዶናሩማ

የጣልያን ብሔራዊ ቡድን ቁጥር አንድ ግብ ጠባቂ ጂያንሉጂ ዶናሩማ ከስዊዘርላንድ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ወደ መለያ ምታ ካመራ ዝግጅት ማድረጋቸውን ገልጿል።

" ጨዋታው ወደ መለያ ምት የሚያመራ ከሆነ ጥሩ ዝግጅት አድርገናል " ያለው የቡድኑ አምበል ዶናሩማ በልምምድ ላይ ተጨዋቾቹ ሲመቱ በራስ መተማመናቸው እንዲጨምር አልመልስባቸውም እንዲያስቆጥሩ እፈቅድላቸዋለሁ።"ሲል ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EthiopiaPL

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ ዘጠነኛ ሳምንት መርሐ ግብር ወላይታ ድቻ ከፋሲል ከነማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ወላይታ ድቻ ካለፉት አስራ ስድስት የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው በሁለቱ ነው።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

6️⃣ ፋሲል ከነማ :- 44 ነጥብ

1️⃣3️⃣ ወላይታ ድቻ :- 34 ነጥብ

ቀጣይ መርሐግብር ምን ይመስላል ?

እሮብ - ወላይታ ድቻ ከ ሀዋሳ ከተማ

ሐሙስ - ፋሲል ከነማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

1:00 ጣልያን ከ ስዊዘርላንድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
38 '

ስዊዘርላንድ 1 - 0  ጣልያን

ፍሩለር

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#እረፍት

ስዊዘርላንድ 1 - 0  ጣልያን

ፍሩለር

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሸገር ደርቢ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ ዘጠነኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያደረጉትን የሸገር ደርቢ ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የቡናማዎቹን ግብ መሐመድ ኑር ናስር ከመረብ ማሳረፍ ሲችል ፍሪምፖንግ ክዋሜ ፈረሰኞቹን አቻ ማድረግ ችሏል።

ኢትዮጵያ ቡና ከአምስት ተከታታይ ድል በኋላ ነጥብ ጥለዋል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ካለፉት አስራ አንድ የሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻሉት አንዱን ሲሆን በአምስቱ አቻ ተለያይተዋል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

3️⃣ ኢትዮጵያ ቡና :- 51 ነጥብ

5️⃣ ቅዱስ ጊዮርጊስ :- 45 ነጥብ

ቀጣይ መርሐግብር ምን ይመስላል ?

እሮብ - ኢትዮጵያ ቡና ከ ሀድያ ሆሳዕና

ሐሙስ - ፋሲል ከነማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
45 '

ስዊዘርላንድ 2 - 0  ጣልያን

ፍሩለር
ቫርጋስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

4:00 ጀርመን ከ ዴንማርክ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጣልያን ከአውሮፓ ዋንጫ ውጪ ሆነች !

በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ጥሎ ማለፍ የስዊዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን ከጣልያን ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል።

የስዊዘርላንድን የማሸነፊያ ግቦች ራሞ ፍሩለር እና ሩበን ቫርጋስ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ውጤቱን ተከትሎ የወቅቱ የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ሻምፒዮን ጣልያን ብሔራዊ ቡድን ከውድድሩ ውጪ ሆነዋል።

ስዊዘርላንድ በሩብ ፍፃሜው የእንግሊዝ እና ስሎቫኪያን አሸናፊ ቀጣይ ሳምንት ቅዳሜ የሚገጥሙ ይሆናል።

ያለፉት ሶስት የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር አሸናፊ ሀገራት ስፔን ፣ ፖርቹጋል እና ጣልያን በቀጣዩ ውድድር በጥሎ ማለፉ ተሸንፈው ተሰናብተዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ደጋፊዎችን ይቅርታ እንጠይቃለን " ዶናሩማ

ከአውሮፓ ዋንጫ የተሰናበተው ጣልያን ብሔራዊ ቡድን አምበል ጂያንሉጂ ዶናሩማ ከጨዋታው በኋላ በሰጠው አስተያየት ደጋፊዎችን ይቅርታ ጠይቋል።

" በጨዋታው ጥሩ አልነበርንም የሆነው ነገር ተቀባይነት የሌለው ነው ፣ እውነታውን መቀበል ያስፈልጋል ደጋፊዎቻችንን ይቅርታ መጠየቅ እንፈልጋለን።" ሲል ዶናሩማ ከጨዋታው በኋላ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ተጨዋቾቹን ለማወቅ በቂ ጊዜ አልነበረኝም " ስፓሌቲ

የጣልያን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሉቺያኖ ስፓሌቲ ተጨዋቾቻቸውን ለማወቅ በቂ ጊዜ አለማግኘታቸውን ከአውሮፓ ዋንጫው ከተሰናበቱ በኋላ በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።

" ተጨዋቾቹን ለማወቅ በቂ ጊዜ አልነበረኝም " ያሉት አሰልጣኝ ሉቺያኖ ስፓሌቲ የበፊት አሰልጣኞችን ብንመለከት ከሀያ በላይ ጨዋታዎች ሞክረው ነበር ተጨማሪ ጨዋታዎች ያግዙኝ ነበር።"ብለዋል።

ጥሩ ቡድን ለመገንባት የተወሰነ ጊዜ እንደሚያስፈልጋቸው የጠቆሙት አሰልጣኝ ሉቺያኖ ስፓሌቲ የቡድኑን መሰናበት ሀላፊነቱን እኔ እወስዳለሁ በማለት ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/01 14:22:07
Back to Top
HTML Embed Code: