Telegram Web Link
TIKVAH-SPORT
ሆሴሉ ሪያል ማድሪድን ሊለቅ ነው ! ስፔናዊው የፊት መስመር አጥቂ ሆሴሉ በሚቀጥለው የውድድር አመት ከሪያል ማድሪድ ጋር ላለመቀጠል ከውሳኔ መድረሱ ተገልጿል። ሪያል ማድሪድ በሆሴሉ የውሰት ውል ውስጥ የተካተተውን አማራጭ ተጠቅመው 1.5 ሚልዮን ዩሮ ወጪ በማድረግ በቋሚነት ለማስፈረም መወስናቸው ይታወሳል። ይሁን እንጂ ሆሴሉ ኪሊያን ምባፔ እና ኢንድሪክ ወደ ሪያል ማድሪድ መምጣታቸውን ተከትሎ ሎስ…
ሆሴሉ የኳታሩን ክለብ አል ሀራፋ በይፋ ተቀላቀለ

ያለፈውን የውድድር አመት በሪያል ማድሪድ ቤት ያሳለፈው ስፔናዊው የፊት መስመር አጥቂ ሆሴሉ የኳታሩን ክለብ አል ሀራፋ በይፋ ተቀላቅሏል።

የኳታሩ ክለብ አል ሀራፋ ተጫዋቹን በ1.5 ሚልዮን ዩሮ የኮንትራት ማፍረሻ ሒሳብ ለአንድ ተጨማሪ አመት የመቆየት አማራጭ ባካተተ የሁለት አመት ውል ማስፈረማቸው ይፋ ሆኗል።

ሎስ ብላንኮዎቹ ተጨዋቹ ከክለባቸው ጋር መለያየቱን ባወጡት ይፋዊ መግለጫ ያረጋገጡ ሲሆን ሆሴሉ በክለቡ ለሰጠው ትልቅ ግልጋሎት ምስጋና አቅርበዋል።

ሪያል ማድሪድ ሆሴሉን በክለቡ የማቆየት ፍላጎት ቢኖራቸውም ተጨዋቹ አዲስ ክለብ ለመቀላቀል መፈለጉ መገለፁ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ጄሴ ማርሽ አርጀንቲና እንድትቀጣ ጠይቀዋል ! የካናዳ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ጄሴ ማርሽ የትላንት ተጋጣሚያቸው አርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ቅጣት እንዲጣልበት አወዳዳሪውን አካል ጠይቀዋል። አሰልጣኙ ቅጣቱ እንዲጣል የጠየቁት የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ከእረፍት መልስ ከመልበሻ ቤት ለመውጣት የተወሰኑ ደቂቃዎች መዘግየታቸውን ተከትሎ ነው። አሰልጣኝ ጄሴ ማርሽ በንግግራቸውም " ከእኛ ጋር…
አሰልጣኝ ሊዮኔል ስካሎኒ ቅጣት ተጣለባቸው !

የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሊዮኔል ስካሎኒ የአንድ ጨዋታ እገዳ ቅጣት እንደተጣለባቸው ተገልጿል።

አሰልጣኝ ሊዮኔል ስካሎኒ ቅጣቱ የተጣለባቸው አርጀንቲና ከካናዳ ጋር በነበራት የኮፓ አሜሪካ የመጀመሪያ ጨዋታ በእረፍት ሰዓት ተጨዋቾች ማዘግየታቸውን ተከትሎ መሆኑ ተነግሯል።

ይህንንም ተከትሎ አርጀንቲና ነገ ሌሊት ከፔሩ ጋር በምታደርገው የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ ቡድኑን የማይመሩ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዩናይትድ ማትያስ ዴሊትን ማስፈረም ይፈልጋል !

ማንችስተር ዩናይትድ ኔዘርላንዳዊውን የባየር ሙኒክ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ማትያስ ዴሊት በዚህ ክረምት ለማስፈረም በማሰብ ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች ተጨዋቹን ለማስፈረም እንቅስቃሴ ቢጀምሩም እስካሁን ይፋዊ ጥያቄ እንዳላቀረቡ እና ከባየር ሙኒክ ጋርም ንግግር እንዳልጀመሩ ተዘግቧል።

በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የሚመራው ማንችስተር ዩናይትድ ማትያስ ዴሊትን አሁን ላይ የመጀመሪያ ምርጫ ማድረጋቸው ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አስቶን ቪላ ተጨዋች አስፈርመዋል !

አስቶን ቪላ ኔዘርላንዳዊውን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች አያን ማትሰን ከምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ማስፈረማቸውን በይፋ አስታውቀዋል።

ያለፈውን የውድድር አመት በውሰት በቦርስያ ዶርትመንድ ቤት ያሳለፈው አያን ማትሰን አስቶን ቪላን በስድስት አመት ኮንትራት መቀላቀሉ ተገልጿል።

የቀጣይ የውድድር አመት የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊው አስቶን ቪላ ለተጨዋቹ ዝውውር 44 ሚልዮን ዩሮ ማውጣታቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሊዮኔል ሜሲ በፔሩ ጨዋታ ላይሳተፍ ይችላል ! የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን አምበል ሊዮኔል ሜሲ ብሔራዊ ቡድኑ በቀጣይ ላለበት የኮፓ አሜሪካ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ ትላንት ባደረገው ልምምድ አለመሳተፉ ተገልጿል። ሊዮኔል ሜሲ ለሩብ ፍፃሜ ጨዋታ ዝግጁ እንዲሆን አርጀንቲና ቅዳሜ ሌሊት ከፔሩ ጋር በምታደርገው የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ እረፍት ሊያደርግ እንደሚችል ተነግሯል። ሩብ ፍፃሜውን መቀላቀሏን ያረጋገጠችው…
ሊዮኔል ሜሲ በፔሩ ጨዋታ ውጪ ሆነ !

የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን አምበል ሊዮኔል ሜሲ በጉዳት ምክንያት ከነገው የፔሩ የኮፓ አሜሪካ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ ውጪ እንደሚሆን ተገልጿል።

ከቀናት በፊት አርጀንቲና ቺሊን ባሸነፈችበት ጨዋታ መጠነኛ ጉዳት አጋጥሞት የነበረው ሊዮኔል ሜሲ ትላንት በነበረው የቡድኑ ልምምድ ላይም ሳይሳተፍ ቀርቶ ነበር።

የስምንት ጊዜ ባሎን ዶር አሸናፊው ሊዮኔል ሜሲ አርጀንቲና በሩብ ፍፃሜው ለምታደርገው ጨዋታ ወደ ሜዳ ይመለሳል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማኑኤል ኡጋርት ወደ ማንችስተር ዩናይትድ ?

ማንችስተር ዩናይትድ ዩራጓዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ማኑኤል ኡጋርት ለማስፈረም ከፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ ጋር ንግግር ማድረጋቸው ተገልጿል።

የ 23ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ማኑኤል ኡጋርት ማንችስተር ዩናይትድ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ባይሳተፍም እንኳን የመቀላቀል ፍላጎት እንዳለው ተነግሯል።

ባለፈው አመት ፒኤስጂን ከስፖርቲንግ ሊስበን በአምስት አመት ኮንትራት የተቀላቀለው ማኑኤል ኡጋርት በዚህ ክረምት ክለቡን ይለቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ተጨዋቹ በሌሎች ክለቦችም እንደሚፈለግ የተገለፀ ሲሆን ቀያዮቹ ሴጣኖች አስካሁን ይፋዊ የዝውውር ጥያቄ #እንዳላቀረቡ ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
Stock Clearance Discount 2

📞 0925927457 @eBRO4
📞 0953964175 @heymobile

•iP 7+, Black, 128GB, 99% 12K
•iP X, Black, 256 GB, 100%,12K ⚠️
•iP XS, White, 64 GB, 100% 19K
•iP XS Max, Gold, 64GB, 83%, 25K
•iP XS Max, Gold, 256GB, 88% 29K
•iP 11, Red, 64GB, 100% 28K ⚠️
•iP 11, Black, 128GB, 85%, 33K
•iP 11, Purple, 128GB, 88% 33K
•11 Pro, Black, 64GB, 100% 39K ⚠️
•11 Pro, White, 64GB, 87% 36K
•11 Pro Max, Black, 64GB, 86%, 46K

•11 Pro Max, Black, 256GB, -% 40⚠️
•iP 12, Red, 128GB, 88%, 42K
•iP 12, White, 128GB, 88% 42K
•iP 12, Green, 128GB, 86% 42K
•12 Pro, Blue, 128GB, 89% 49K
•12 Pro Max, Blue, 512GB, 84% 64K
•iP 13 Min, Pink, 256GB, 92% 34K
•iP 13, Blueback, 128GB, 90% 56K
•iP 13, Black, 128GB, 92% 49K ⚠️

•iP 13, Red, 128GB, 86%, 56K
•iP 13, Black, 128GB, 89%, 58K
•13 Pro, Golden, 256GB, 87% 69K
•13 Pro, Blue, 512GB/88% 69K ⚠️
•13 ProMax, Black, 128 GB, 87% 74K
•13 ProMax, 256GB, 86%, 64K⚠️
•13 ProMax, 256GB, 85%, 74K⚠️
•13 ProMax, Gold, 256GB, 86%, 79K
•13 Pro Max, Gold, 256 GB,88% 79K
•13 Pro Max, Blue, 256GB, 94% 79K
•13 Pro Max, 1TB, 88%, 69K ⚠️
•13 Pro Max, Blu, 256GB/ -% 70K ⚠️

Exchange Available!
Free Delivery 🚚

@heyonlinemarket
https://heymobile.store/catalogue
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
" ብራዚልን የሚገባት ቦታ ማስቀመጥ እንፈልጋለን " ቪንሰስ ጁኒየር

የብራዚል ብሔራዊ ቡድን ትላንት ሌሊት ከፓራጓይ ጋር ያደረገውን የኮፓ አሜሪካ ጨዋታ በቪንሰስ ጁኒየር 2x ፣ ሳቪዮ እና ፓኩዌታ ግቦች 4ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

በጨዋታው ኮኮብ ተብሎ የተመረጠው ቪንሰስ ጁኒየር ከጨዋታው በኋላ በሰጠው አስተያየት ቡድኑ ብራዚልን " የሚገባት ቦታ " ማስቀመጥ ይፈልጋል በማለት ተናግሯል።

" ብሔራዊ ቡድኑን ለመርዳት አሁንም ካለሁበት ደረጃ መሻሻል እችላለሁ " ያለው ቪንሰስ ጁኒየር ብራዚልን የሚገባት ቦታ ማስቀመጥ እንፈልጋለን እኔ በጭራጭ ለግሌ አልጫወትም ሁልጊዜም ለቡድኑ ነው።"ብሏል።

ቪንሰስ ጁኒየር አያይዞም የሜዳው አለመመቸት እና የጨዋታው ዳኛ በእነሱ ላይ ጥሩ አለመሆን ጨዋታውን አስቸጋሪ አድርጎባቸው እንደነበር ገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ዴንማርክ ጠንካራ ተፎካካሪ ይሆናሉ " ኔግልስማን

የጀርመን ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ጁሊያን ኔግልስማን የዛሬ ተጋጣሚያቸው ዴንማርክ ብሔራዊ ቡድን የተደራጀ ቡድን መሆኑን በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።

አሰልጣኝ ጁሊያን ኔግልስማን በንግግራቸውም " የዴንማርክ ብሔራዊ ቡድን የተደራጀ እና አጥቅቶ የሚጫወት ቡድን ነው እንዲሁም በጥሩ ሁኔታ ይከላከላሉ ፣ ጠንካራ ተፎካካሪ ይሆናሉ።"ሲሉ ተደምጠዋል።

" ጀርመን አዘጋጅ ሀገር ብትሆንም ባትሆንም ደጋፊዎች የሚጠብቁት ተመሳሳይ ነገር ነው ፣ ደጋፊዎች ለእኛ የተለየ ድጋፍ ያደርጋሉ ይህ ለእኛ ተጨማሪ ሀይል ይሆነናል።" ጁሊያን ኔግልስማን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ክርስቲያን ኤሪክሰን በጀርመን ጨዋታ ይሳተፋል ?

የዴንማርክ ብሔራዊ ቡድን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ክርስቲያን ኤሪክሰን ቡድኑ ዛሬ ከጀርመን ጋር ከሚያደርገው ጨዋታ በፊት ባደረገው የመጨረሻ ልምምድ አለመሳተፉ ተገልጿል።

የማንችስተር ዩናይትዱ ተጨዋች ክርስቲያን ኤሪክሰን በቡድኑ ልምምድ ያልተሳተፈው የሆድ ህመም አጋጥሞት መሆኑ ተነግሯል።

የዴንማርክ አሰልጣኝ ካስፐር ሁልማንድ ስለ ኤሪክሰን በሰጡት አስተያየት " አሁን በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል በዛሬው የዴንማርክ ጨዋታ ዝግጁ እንደሚሆን እጠብቃለሁ።"በማለት ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ራፋኤል ቫራን ወደ ኮሞ ?

በቅርቡ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር የተለያየው ፈረንሳዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ራፋኤል ቫራን ጣልያኑን ክለብ ኮሞ ለመቀላቀል በንግግር ላይ መሆኑ ተገልጿል።

ራፋኤል ቫራን አሁን ላይ ከክለቡ ቦርድ እና ከክለቡ አሰልጣኝ ሴስክ ቫብሬጋስ ጋር ለመነጋገር ወደ ጣልያን ኮሞ ማምራቱ ተነግሯል።

በዚህ አመት ወደ ጣልያን ሴርያ ማደጉን ያረጋገጠውን የአሰልጣኝ ሴስክ ቫብሬጋሱ ቡድን ኮሞ ራፋኤልን ቫራንን በነፃ ዝውውር ማስፈረም እንደሚፈልጉ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ኦማሪ ኬሊማን ዛሬ የህክምና ምርመራ ያደርጋል ! እንግሊዛዊውን ወጣት የፊት መስመር ተጨዋች ኦማሪ ኬሊማን ከአስቶን ቪላ ወደ ቼልሲ የሚያደርገውን ዝውውር ለማጠናቀቅ ዛሬ የህክምና ምርመራውን እንደሚያደርግ ተገልጿል። ሰማያዊዎቹ የ 18ዓመቱን የፊት መስመር ተጨዋች ኦማሪ ኬሊማንን ከአስቶን ቪላ በ 19 ሚልዮን ፓውንድ ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ይታወሳል። ተጨዋቹ በክንፍ አጥቂነት ወይም በአጥቂ…
ቼልሲ በይፋ ተጨዋች አስፈርመዋል !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ እንግሊዛዊውን ወጣት የፊት መስመር ተጨዋች ኦማሪ ኬሊማን ከአስቶን ቪላ ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ሰማያዊዎቹ የ 18ዓመቱን የፊት መስመር ተጨዋች ኦማሪ ኬሊማን ለማስፈረም 22 ሚልዮን ዩሮ ወጪ ማድረጋቸው ተገልጿል።

በክንፍ አጥቂነት እንዲሁም በአጥቂ አማካይ ቦታ ተሰልፎ ግልጋሎት መስጠት የሚችለው ኦማሪ ኬሊማን በቼልሲ ቤት የስድስት አመት ኮንትራት መፈረሙ ይፋ ሆኗል።

" ቼልሲ ትልቅ ታሪክ ያለው አስደናቂ ክለብ ነው ወደዚህ መምጣቴ አስደስቶኛል ህልሜ እውን ሆኖልኛል።"ሲል ተጨዋቹ ከፊርማው በኋላ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
🇪🇹 ዋናው 🤝 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ደጋፊዎች ጥምረት 🇪🇹

እግር ኳስን ለቱሪዝም የመጠቀም ዓላማን በማንገብ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ደጋፊዎች ጥምረት ከዋናው ስፖርት ጋር በመሆን ያዘጋጀው የጀልባ ቀዘፋ ውድድር ዛሬ በሃዋሳ ከተማ ይካሄዳል። ከውድድሩ በተጨማሪም ለኢትዮጵያ የልብ ህሙማን መርጃ ማዕከል እርዳታ የገቢ ማሰባሰቢያ በጎ ስራም ይከናወናል።

ዋናው ስፖርትም የዚህ መርሃግብር ዋና አጋር በመሆኑ የተሰማውን ኩራት ለመግለፅ ይወዳል።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
የኢትዮጵያ  ቡና ይፋዊ አጋር የሆነው ቤቲካ - የኢትዮጵያ ቡናን  24ኛ የጨዋታ ቀን የዲጂታል መፅሄት ይዞ ቀርቧል።
በመፅሄቱ ላይ የዕለቱ ጨዋታን የተመለከቱና ሌሎች የተለያዩ መረጃዎች የሚቀርቡ ይሆናል፡፡

መፅሄቱን ለማግኘት ተከታዩን ሊንክ ይጫኑ።

https://www.tg-me.com/betikaethiopia/5366

የጨዋታ መፅሄት ቁጥር 24
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኢትዮጵያ ቡና
ዛሬ 12:00

ቤቲካ - የኢትዮጵያ ቡና ይፋዊ አጋር
" ኩርቱዋ አለመጠራቱ አስደስቶኛል " ካማቪንጋ

የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኤድዋርዶ ካማቪንጋ ቲቧ ኩርቱዋ በቤልጅየም ብሔራዊ ቡድን ስብስብ ውስጥ አለመኖሩ እንዳስደሰተው ገልጿል።

የሰኞ ተጋጣሚያቸው ቤልጂየም ስብስብ ውስጥ የክለብ የቡድን አጋሩ ቲቧ ኩርቱዋ " አለመኖሩ አስደስቶኛል " ሲል የተደመጠው ካማቪንጋ ምክንያቱም እሱ ሁሉንም ኳሶች መያዝ ይችላል ያስቸግረን ነበር በማለት ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጣልያን የተጨዋቾቿን ግልጋሎት አታገኝም !

ጣልያን ዛሬ ምሽት 1:00 ሰዓት ከስዊዘርላንድ ጋር በምታደርገው የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ጥሎ ማለፍ ጨዋታ የተጨዋቾቿን ግልጋሎት የማታገኝ ይሆናል።

በጨዋታው ተከላካዩ ሪካርዶ ካላፊዮሪ በቅጣት ምክንያት እንዲሁም ፌዴሪኮ ዴማርኮ በጉዳት ምክንያት ለብሔራዊ ቡድኑ ግልጋሎት አይሰጡም።

የሮማው ተከላካይ ጂያንሉካ ማንቺኒ በምሽቱ ጨዋታ ሪካርዶ ካላፊዮሪን በመተካት በቋሚ አሰላለፍ እንደሚገባ አሰልጣኝ ሉቺያኖ ስፓሌቲ ገልጸዋል።

በተጨማሪም ከጉንፋን ህመም ያገገመው የኢንተር ሚላኑ ተከላካይ አሌሳንድሮ ባስቶኒ ለጨዋታው መድረሱ አጠራጣሪ መሆኑን አሰልጣኙ ጠቁመዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" አውሮፓ ዋንጫውን ለማሸነፍ ነው የመጣነው " ሳውዝጌት

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት ቡድናቸው ጀርመን የሚገኘው የአውሮፓ ዋንጫውን ለማሸነፍ መሆኑን በሰጡት አስተያየት ገልፀዋል።

" እኛ ወደ ውድድሩ የመጣነው ከምድባችን ለመሰናበት ሳይሆን የአውሮፓ ዋንጫውን አሸንፈን ለመመለስ ነው።" ሲሉ አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት ተናግረዋል።

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ነገ ምሽት 1:00 ሰዓት ከስሎቫኪያ አቻው ጋር የጥሎ ማለፍ ጨዋታውን ያደርጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ልምምድ ላይ ፍፁም ቅጣት ምት አልመልስባቸውም " ዶናሩማ

የጣልያን ብሔራዊ ቡድን ቁጥር አንድ ግብ ጠባቂ ጂያንሉጂ ዶናሩማ ከስዊዘርላንድ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ወደ መለያ ምታ ካመራ ዝግጅት ማድረጋቸውን ገልጿል።

" ጨዋታው ወደ መለያ ምት የሚያመራ ከሆነ ጥሩ ዝግጅት አድርገናል " ያለው የቡድኑ አምበል ዶናሩማ በልምምድ ላይ ተጨዋቾቹ ሲመቱ በራስ መተማመናቸው እንዲጨምር አልመልስባቸውም እንዲያስቆጥሩ እፈቅድላቸዋለሁ።"ሲል ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EthiopiaPL

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ ዘጠነኛ ሳምንት መርሐ ግብር ወላይታ ድቻ ከፋሲል ከነማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ወላይታ ድቻ ካለፉት አስራ ስድስት የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው በሁለቱ ነው።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

6️⃣ ፋሲል ከነማ :- 44 ነጥብ

1️⃣3️⃣ ወላይታ ድቻ :- 34 ነጥብ

ቀጣይ መርሐግብር ምን ይመስላል ?

እሮብ - ወላይታ ድቻ ከ ሀዋሳ ከተማ

ሐሙስ - ፋሲል ከነማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/12/28 03:27:18
Back to Top
HTML Embed Code: