Telegram Web Link
66 '

ቼክ 1 - 1 ቱርክ

ሱሴክ          ካልሀኖግሉ

ጆርጂያ 2 - 0 ፖርቹጋል

ቅቫራትስኬሊያ
ሚካውታድዝ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
88 '

ጆርጂያ 2 - 0 ፖርቹጋል

ቅቫራትስኬሊያ
ሚካውታድዝ

ቼክ 1 - 1 ቱርክ

ሱሴክ          ካልሀኖግሉ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
90+3 '

ቼክ 1 - 2 ቱርክ

ሱሴክ          ካልሀኖግሉ
ቶሱን

ጆርጂያ 2 - 0 ፖርቹጋል

ቅቫራትስኬሊያ
ሚካውታድዝ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፖርቹጋል ሽንፈት አስተናግዳለች !

በአውሮፓ ዋንጫ የምድብ ስድስት የመጨረሻ ጨዋታዎች ሲደረጉ የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ከጆርጂያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፈዋል።

ለጆርጂያ ብሔራዊ ቡድን የማሸነፊያ ግቦችን ቅቫራትስኬሊያ እና ሚካውታድዝ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

በምድቡ ሌላኛው ጨዋታ የቱርክ ብሔራዊ ቡድን ከቼክ ሪፐብሊክ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

የቱርክን የማሸነፊያ ግብ ካልሀኖግሉ እና ቶሱን ማስቆጠር ሲችሉ ቶማስ ሱሴክ የቼክ ሪፐብሊክን ግብ ከመረብ አሳርፏል።

የምድቡ ደረጃ ምን ይመስላል ?

1️⃣ ፖርቹጋል :- 6 ነጥብ

2️⃣ ቱርክ :- 6 ነጥብ

3️⃣ ጆርጂያ :- 4 ነጥብ

4️⃣ ቼክ ሪፐብሊክ :- 1 ነጥብ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጥሎ ማለፍ ተጋጣሚዎች ተለይተዋል !

የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር የምድብ ጨዋታዎች መጠናቀቃቸውን ተከትሎ ጥሎ ማለፉን የተቀላቀሉ አስራ ስድስት ብሔራዊ ቡድኖች ተጋጣሚዎቻቸውን አውቀዋል።

በዚህም መሰረት :-

- ስፔን ከ ጆርጅያ
- ጀርመን ከ ዴንማርክ
- ፖርቹጋል ከ ስሎቬኒያ
- ፈረንሳይ ከ ቤልጅየም

- ሮማንያ ከ ኔዘርላንድ
- ኦስትሪያ ከ ቱርክ
- እንግሊዝ ከ ስሎቫኪያ
- ጣልያን ከ ስዊዘርላንድ የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
Samsung Galaxy S22 Ultra
256 GB - 67,000 ETB
512 GB - 78,000 ETB

Samsung Galaxy S23 Ultra
256 GB - 92,000 ETB
512 GB - 109,000 ETB

Samsung Galaxy S24 Ultra
256 GB - 109,000 ETB
512 GB - 124,000 ETB

Exchange Available
🏍️ Free Delivery

Contact us :
0925927457 @eBRO4
@Heyonlinemarket
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
" በጆርጂያ እግርኳስ ውስጥ ትልቅ ታሪክ ፅፈናል " ቅቫራትስኬሊያ

የጆርጂያ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጨዋች ቅቫራትስኬሊያ ቡድናቸው ፖርቹጋልን በማሸነፍ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ አስራ ስድስቱን በመቀላቀል ታሪክ መፃፉን ከጨዋታው በኋላ ተናግሯል።

" ይህ ለጆርጂያ ምርጡ ቀን ነው " ያለው ቅቫራትስኬሊያ ማንም ፖርቹጋልን ያሸንፋሉ ብሎ አልገመተም ነበር ተስፋ የማይቆርጥ ጠንካራ ቡድን ነው ያለን ትልቅ ታሪክ መፃፍ ችለናል በማለት ተናግሯል።

" ከጨዋታው በፊት ከሮናልዶ ጋር ተነጋግሬ ነበር ያልጠበቅኩት ነበር መልካም ውጤት ተመኝቶልኛል ፣ እሱ ምርጥ ተጨዋች እና ምርጥ ሰው ነው ትልቅ ክብር አለኝ ማልያውን በማገኝቴ በጣም ተደስቻለሁ።" ቅቫራትስኬሊያ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" በእኛ ደረጃ የተጫወቱት ጀርመኖች ብቻ ናቸው " ፔድሮ ኔቶ

የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጨዋች ፔድሮ ኔቶ በምድብ ጨዋታዎች ፖርቹጋል ከሌሎች የተሻለ እንቅስቃሴ ማሳየቷን ገልጿል።

" ከጀርመን ብሔራዊ ቡድን ውጪ በፖርቹጋል ደረጃ የተጫወተ ቡድን አልተመለከትኩም " ያለው ፔድሮ ኔቶ እኛ በራሳችን እንተማመናለን ለቀጣይ ጨዋታዎች ዝግጁ ነን ሲል ተደምጧል።

የፖርቹጋል ዋና አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ በበኩላቸው " ያሸነፍነውም የተሸነፍነውም እንደ ቡድን ነው " ያሉ ሲሆን መሸነፍ አንፈልግም ነገርግን ሁሉም ተጨዋቾች ጥሩ ተንቀሳቅሰዋል ሌሎቹን ደግሞ አሳርፈናል ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የስዊዘርላንድ አሰልጣኞች ኮምፒውተሮች ተሰርቀዋል !

ከጣልያን ጋር ላለበት የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ዝግጅት ላይ የሚገኘው የስዊዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን የአሰልጣኝ ቡድን አባላት ሶስት ኮምፒውተሮች ከቡድኑ ሆቴል መሰረቃቸው ተገልጿል።

ይሁን እንጂ የተሰረቁት ኮምፒውተሮች ቡድኑ ከጣልያን ላለበት የጥሎ ማለፍ ጨዋታ በሚያደርገው ዝግጅት ተፅዕኖ የሚያሳድር መረጃ አለመያዛቸው ተነግሯል።

በተሰረቁት ሶስት የአሰልጣኞች ቡድን ኮምፒውተሮች ውስጥ የብሔራዊ ቡድኑ ዝግጅት መረጃ እና ታክቲካል መረጃዎች አለመኖራቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport    @kidusyoftahe
ማርሴይ ሜሰን ግሪንውድን ማስፈረም ይፈልጋል !

ጣልያናዊውን አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዘርቢን በአሰልጣኝነት የሾመው የፈረንሳዩ ክለብ ማርሴይ ሜሰን ግሪንውድን ከማንችስተር ዩናይትድ ለማስፈረም ንግግር መጀመሩ ተገልጿል።

ማርሴይ በተጨዋቹ ዝውውር ዙሪያ ማንችስተር ዩናይትድን ማነጋገር መጀመራቸው የተገለፀ ሲሆን እስካሁን በዝውውር ሒሳብ ዙሪያ መደራደር እንዳልጀመሩ ተጠቁሟል።

የ 22ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ሜሰን ግሪንውድ ከሌሎች ክለቦች ይልቅ ማርሴን ለመቀላቀል እንደሚመርጥ ተዘግቧል።

@tikvahethsport    @kidusyoftahe
ቼልሲ ተጨዋች ለማስፈረም ተቃርበዋል !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ አርጀንቲናዊውን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች አሮን አንሴልሚኖ ከቡካ ጁኒየር ለማስፈረም መቃረባቸው ተገልጿል።

ሰማያዊዎቹ የ 19ዓመቱን ተከላካይ አሮን አንሴልሚኖን 17 ሚልዮን ፓውንድ በሚደርስ የዝውውር ሒሳብ በስድስት አመት ኮንትራት እንደሚያስፈርሙ ተነግሯል።

ተጨዋቹ ቼልሲን ከተቀላቀለ በኋላ በውሰት ወደ ስትራስቡርግ ሊያመራ እንደሚችል ተዘግቧል።

በሌላ በኩል ሰማያዊዎቹ ከባርሴሎና ለማስፈረም ከስምምነት የደረሱት ማርክ ጉዩ የህክምና ምርመራውን በዛሬው ዕለት እንደሚያደርግ ተገልጿል።

@tikvahethsport    @kidusyoftahe
ዩናይትድ አሰልጣኝ ሬኔ ሀኬን መሾም ይፈልጋል !

ማንችስተር ዩናይትድ ኔዘርላንዳዊውን የጎ አሄድ ኤግልስ ዋና አሰልጣኝ ሬኔ ሀኬን በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የአሰልጣኞች ቡድን ውስጥ ለመካተት በመስራት ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች በተጨማሪም የቀድሞ ኮከባቸውን ሩድ ቫን ኔስትሮይን ወደ ቡድናቸው አሰልጣኝ ስብስብ ለማካተት መቃረባቸው መገለፁ አይዘነጋም።

የክለቡ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ በበኩላቸው በቅርቡ የተጨማሪ ሁለት አመታት ኮንትራት ይፈርማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethsport    @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ናቾ ወደ ሳውዲ አረቢያ ለማምራት ተስማማ ! ስፔናዊው የሪያል ማድሪድ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ናች ፈርናንዴዝ የሳውዲ አረቢያውን ክለብ አል ካድስያ ለመቀላቀል የህክምና ምርመራውን ማጠናቀቁ ተገልጿል። ናቾ ሪያል ማድሪድን ከሀያ ሶስት አመታት በኋላ በመልቀቅ ለሳውዲ አረቢያውን ክለብ አል ካድስያ የሁለት አመት ኮንትራት እንደሚፈርም ተነግሯል። ናቾ ከዚህ በፊት አል ኢትሀድን ለመቀላቀል ተቃርቦ የነበረ…
" ማድሪድን መልቀቅ የህይወቴ ከባድ ውሳኔ ነው " ናቾ

ስፔናዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ናቾ ፈርናንዴዝ ሪያል ማድሪድ የሳውዲ አረቢያውን ክለብ አል ቃዲሲያ መቀላቀሉ ይፋ ተደርጓል።

ከሀያ ሶስት አመታት በኋላ ከሪያል ማድሪድ ጋር የተለያየው ናቾ ፈርናንዴዝ በሳውዲ አረቢያ ሊግ አዲስ አዳጊው አል ቃዲሲያ የሁለት አመት ኮንትራት መፈረሙ ተገልጿል።

" ማድሪድን የመልቀቅ ውሳኔ የህይወቴ ከባዱ ውሳኔ ነው " ሲል የገለፀው ናቾ በክለቡ ባደረግኩት ነገር ደስተኛ ነኝ ሪያል ማድሪድ ውስጥ ምንም የማሳካው ነገር አልቀረኝም።"ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" እኛ ፈረንሳይን አንፈራም " ቫውት ፋስ

የቤልጅየም ብሔራዊ ቡድን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ቫውት ፋስ ቡድናቸው ቀጣይ የጥሎ ማለፍ ተጋጣሚው ፈረንሳይን እንደማይፈራ ገልጿል።

የሌስተር ሲቲው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ቫውት ፋስ በንግግሩም " እኛ ፈረንሳይ በፍፁም አታስፈራንም " ያለ ሲሆን " እኛ እነሱን ማሸነፍ እንችላለን " በማለት ተናግሯል።

ቫውት ፋስ ቀጥሎም በአሁን ሰዓት ብራዚላዊው ተጨዋች ዴቪድ ሉዊዝ 2014 በነበረው ደረጃ መጫወት እንደሚችል ገልጿል።

የቤልጅየም ብሔራዊ ቡድን ከፈረንሳይ ጋር የጥሎ ማለፍ ጨዋታቸውን ቀጣይ ሳምንት ሰኞ ምሽት 1:00 ሰዓት ያደርጋሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EthiopiaPL 🇪🇹

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ ዘጠነኛ ሳምንት መርሐ ግብር ባሕር ዳር ከተማ ከሀዋሳ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የባሕር ዳር ከተማን ግብ ፍቅረሚካኤል አለሙ ሲያስቆጥር ዓሊ ሱሌይማን ሀዋሳ ከተማን አቻ ማድረግ ችሏል።

ኤርትራዊው የሀዋሳ ከተማ አጥቂ ዓሊ ሱሌይማን በውድድር አመቱ ያስቆጠራቸውን የሊግ ግቦች አስራ ስምንት በማድረስ የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ደረጃውን እየመራ ይገኛል።

የሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ምን ይመስላል ? 

4️⃣ ባሕር ዳር ከተማ :- 50

1️⃣0️⃣ ሀዋሳ ከተማ :- 38 ነጥብ

ቀጣይ መርሐ ግብር ምን ይመስላል ?

እሮብ - ሀዋሳ ከተማ ከ ወላይታ ድቻ

ሐሙስ - ሲዳማ ቡና ከ ባሕር ዳር ከተማ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
📢 ለቸኮለ ዘዴ ከ #ዋናው!

🏃🏾‍♂ #ይምጡ#ትጥቅዎን ይውሰዱ!

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ይዘዙን።

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
ናኒ ወደ ኢትዮጵያ ሊመጣ መሆኑ ተገለጸ !

ፖርቹጋላዊው የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ የፊት መስመር ተጨዋች ተጨዋች ሉዊስ ናኒ በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ሊመጣ መሆኑን ገልጿል።

ናኒ ወደ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ የሚመጣው የሰማንያኛ አመት ክብረ በዓሉን በማክበር ላይ ለሚገኘው መቻል እግርኳስ ክለብ የክብር እንግዳ ሆኖ እንደሚሆን ተገልጿል።

ናኒ ባስተላለፈው አጭር የቪዲዮ መልዕክትም " ሰላም ኢትዮጵያውያን ሰማንያኛ አመቱን ከሚያከብረው መቻል ግብዣ ስለቀረበልኝ ኩራት እና ደስታ ተሰምቶኛል።

ለእኔ ልዩ ቦታ ያላትን ኢትዮጵያ ለመጎብኘት ጓጉቻለሁ በቅርቡ እንገናኝ።"ሲል ተደምጧል።

ምንጭ :- አራዳ ኤፍኤም

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/29 12:29:10
Back to Top
HTML Embed Code: