Telegram Web Link
የጨዋታ አሰላለፍ !

4:00 አልባንያ ከ ስፔን

4:00 ክሮሽያ ከ ጣልያን

@tikvahethsport           @kidusyoftahe
#EURO2024

በምሽቱ የጣልያን እና ክሮሽያ ብሔራዊ ቡድን ጨዋታ 38,000 ተመልካች በሚይዘው የሌፕዚግ ስታዲየም 25,000 ገደማ የክሮሽያ ደጋፊዎች እንደሚገኙ ይጠበቃል።

የፊት መስመር ተጨዋቹ ኢቫን ፔርሲችን ተጠባባቂ ያደረገችው ክሮሽያ የአጥቂ አማካዩ ክራማሪችን በፊት መስመር ቦታ ላይ አሰልፋለች።

የክሮሽያ ብሔራዊ ቡድን በጨዋታው ያለ ተፈጥሯዊ አጥቂ ሲገቡ 4-6-0 የሆነ የጨዋታ አሰላለፍ ሊጠቀሙ ይችላሉ።

የጣልያን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሉቺያኖ ስፓሌቲ በምሽቱ የክሮሽያ ጨዋታ የሶስት ተጨዋቾች ለውጥ አድርገው ወደ ሜዳ ይገባሉ።

የጣልያን ብሔራዊ ቡድን በጨዋታው የ3-5-2 የጨዋታ አሰላለፍ ይዘው እንደሚገቡ ይጠበቃል።

@tikvahethsport           @kidusyoftahe
13 '

አልባንያ 0-1 ስፔን

ቶሬስ

ክሮሽያ 0-0 ጣልያን

@tikvahethsport           @kidusyoftahe
31 '

አልባንያ 0 - 1 ስፔን

         ቶሬስ

ክሮሽያ 0 - 0 ጣልያን

@tikvahethsport           @kidusyoftahe
#እረፍት

አልባንያ 0 - 1 ስፔን

         ቶሬስ

ክሮሽያ 0 - 0 ጣልያን

@tikvahethsport           @kidusyoftahe
54 '

ክሮሽያ 1 - 0 ጣልያን

ሞድሪች

አልባንያ 0 - 1 ስፔን

         ቶሬስ

@tikvahethsport           @kidusyoftahe
77 '

ክሮሽያ 1 - 0 ጣልያን

ሞድሪች

አልባንያ 0 - 1 ስፔን

         ቶሬስ

*ወቅታዊ የምድቡ ደረጃ ሰንጠረዥ

1️⃣ ስፔን :- 9 ነጥብ

2️⃣ ክሮሽያ :- 4 ነጥብ

3️⃣ ጣልያን :- 3 ነጥብ

4️⃣ አልባንያ :- 1 ነጥብ

@tikvahethsport           @kidusyoftahe
90+8'

ክሮሽያ 1 - 1 ጣልያን

ሞድሪች ዛካኚ

@tikvahethsport           @kidusyoftahe
ጣልያን ጥሎ ማለፉን ተቀላቀለች !

በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር የምድብ ሁለት የመጨረሻ ጨዋታ ስፔን አልባንያን 1ለ0 በሆነ ውጤት ስታሸንፍ ክሮሽያ ከጣልያን ጋር 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።

ለስፔን ብሔራዊ ቡድን የማሸነፊያ ግቧን ፌራን ቶሬስ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ለክሮሽያ ብሔራዊ ቡድን ሉካ ሞድሪች ማስቆጠር ሲችል ለጣልያን ዛካኚ በጨዋታው መጠናቀቂያ ደቂቃ የአቻነት ግብ አስቆጥሮ ቡድኑን መታደግ ችሏል።

ጣልያን አቻ መውጣቷን ተከትሎ ስፔንን በመከተል አስራ ስድስቱን መቀላቀሏን አረጋግጣለች።

ሉካ ሞድሪች በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ታሪክ ለክሮሽያ ብሔራዊ ቡድን አራት ግቦችን በማስቆጠር የኢቫን ፔሪሲችን ታሪክ መጋራት ችሏል።

የ 38ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሉካ ሞድሪች በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ግብ ማስቆጠር የቻለ በታሪክ በእድሜ ትልቁ ተጨዋች መሆን ችሏል።

የአልባንያ ብሔራዊ ቡድን በበኩሉ የምድቡን የመጨረሻ ደረጃ ይዞ ማጠናቀቁን ተከትሎ ከአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ውጪ መሆኑ ተረጋግጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
Samsung Galaxy S22 Ultra
256 GB - 67,000 ETB
512 GB - 78,000 ETB

Samsung Galaxy S23 Ultra
256 GB - 92,000 ETB
512 GB - 109,000 ETB

Samsung Galaxy S24 Ultra
256 GB - 109,000 ETB
512 GB - 124,000 ETB

Exchange Available
🏍️ Free Delivery

Contact us :
0925927457 @eBRO4
@Heyonlinemarket
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
" እግርኳስ ሁልጊዜም ጨካኝ ነች " ሞድሪች

የክሮሽያ ብሔራዊ ቡድን ትላንት ምሽት በመጨረሻ ደቂቃ ግብ አስተናግዶ አቻ ከተለያየበት ጨዋታ በኋላ ሉካ ሞድሪች " እግርኳስ ጨካኝ ነች " ሲል ገልጿል።

" የተቆጠረብን ግብ አይገባንም ነበር " ያለው ሉካ ሞድሪች እግርኳስ ሁልጊዜም ጨካኝ እና ምህረት የለሽ ነች ፣ ምን ማለት እንዳለብኝ አላውቅም አሸንፈን ባለማለፋችን በጣም አዝኛለሁ።"ሲል ተደምጧል።

የጨዋታው ኮከብ ተብሎ የተመረጠው ሉካ ሞድሪች በቀጣይ ከብሔራዊ ቡድኑ ራሱን ያገል እንደሆን ሲጠየቅ " አሁን ትክክለኛው ጊዜ አይደለም " ሲል መልሷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባርሴሎና ህንድ ያለውን አካዳሚ መዝጋቱ ተገለጸ !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና በህንድ ዴልሂ እና ሙምባይን ጨምሮ በአራት ከተሞች ያላቸውን የታዳጊዎች አካዳሚ ለመዝጋት መወሰናቸው ተገልጿል።

ባርሴሎና አካዳሚውን ለመዝጋት የወሰኑት ከተከፈተበት እ.ኤ.አ 2010 ወዲህ ባለፉት አስራ አራት አመታት አንድም ጥሩ ተሰጥኦ ያለው ተጨዋች ሊገኝ ባለመቻሉ መሆኑ ተነግሯል።

ባርሴሎና በአራት ከተሞች አካዳሚውን የከፈተባት የደቡብ እስያዋ ሀገር ህንድ የ 1.4 ቢልዮን ህዝብ ብዛት ባለቤት ነች።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" የምድቡ መሪ መሆን እንፈልጋለን " ኮማን

የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሮናልድ ኮማን ቡድናቸው የምሽቱን የኦስትሪያ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ አሸንፎ የምድቡ መሪ መሆን እንደሚፈልግ ተናግረዋል።

" ጨዋታውን ማሸነፍ እና የምድቡ መሪ መሆን እንፈልጋለን " ያሉት ሮናልድ ኮማን " ነገርግን ተጋጣሚ ማክበር እና ኳስ ተቆጣጥረን መጫወት አለብን ካልሆነ ኦስትሪያ ያስቸግራሉ አውሮፓ ዋንጫው በፉክክር የተሞላ ነው።"ብለዋል።

አሰልጣኝ ሮናልድ ኮማን ቀጥለውም እስካሁን በውድድሩ ላይ ለዋንጫ የማጫቸው ብዙ ቡድኖች አላየሁም በማለት ገልጸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሉዊስ ዲያዝ ሊቨርፑልን ሊለቅ ይችላል ?

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል የፊት መስመር ተጨዋች ሉዊስ ዲያዝ በሚቀጥለው የውድድር ዘመን በአዲሱ አሰልጣኝ አሬኔ ስሎት እቅድ ውስጥ እንደሚገኝ ተገልጿል።

በተጨማሪም አየርላንዳዊው ግብ ጠባቂ ኮሚን ኬለር በቀጣይ የውድድር አመት በአሰልጣኝ አሬኔ ስሎት እቅድ ውስጥ መሆኑ ተዘግቧል።

ይሁን እንጂ ሊቨርፑል ለሉዊስ ዲያዝ 50 ሚልዮን ፓውንድ እንዲሁም ለግብ ጠባቂ ኮሚን ኬለር 25 ሚልዮን ፓውንድ ከቀረበለት ለመሸጥ ሊያስብበት እንደሚችል ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/29 22:30:09
Back to Top
HTML Embed Code: