Telegram Web Link
31 ' ፖላንድ 1 - 1 ኦስትሪያ

ፒያቴክ                  ትራውነር

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እረፍት | ፖላንድ 1 - 1 ኦስትሪያ

ፒያቴክ                  ትራውነር

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሀድያ ሆሳዕና ድል አድርገዋል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ ስምንተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሀድያ ሆሳዕና ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

የሀድያ ሆሳዕናንን የማሸነፊያ ግቦች ግርማ በቀለ ፣ ቃለአብ ውብሸት እና ሰመረ ሀፍተይ ከመረብ ሲያሳርፉ ለድሬዳዋ ከተማ አድናን መኪ አስቆጥሯል።

የሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ምን ይመስላል ? 

8️⃣ ድሬዳዋ ከተማ :- 40 ነጥብ

9️⃣ ሀድያ ሆሳዕና :- 38 ነጥብ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
67 ' ፖላንድ 1 - 2 ኦስትሪያ

ፒያቴክ              ትራውነር
ቡምጋርትነር

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
78 ' ፖላንድ 1 - 3 ኦስትሪያ

ፒያቴክ              ትራውነር
                              ቡምጋርትነር
አርናውቶቪች

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

4:00 ኔዘርላንድ ከ ፈረንሳይ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኦስትሪያ የመጀመሪያ ድሏን አሳክታለች !

በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ የኦስትሪያ ብሔራዊ ቡድን ከፖላንድ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

ለኦስትሪያ ብሔራዊ ቡድን የማሸነፊያ ግቦችን ትራውነር ፣ ቡምጋርትነር እና አርናውቶቪች ከመረብ ሲያሳርፉ ለፖላንድ ፒያቴክ አስቆጥሯል።

የኦስትሪያ ብሔራዊ ቡድን በአንድ የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር ጨዋታ ከሶስት በላይ ግቦች ሲያስቆጥር በታሪኩ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ተገልጿል።

በጨዋታው ኦስትሪያ የመጀመሪያ ሶስት ነጥቧን ስታሳካ ፖላንድ ምንም ነጥብ ማስመዝገብ ሳትችል ቀርታ የመጨረሻውን ደረጃ ይዛለች።

በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ሐሙስ ፖላንድ ከፈረንሳይ እንዲሁም ኔዘርላንድ ከኦስትሪያ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቼልሲ ኦሊሴን ለማስፈረም ንግግር ጀመሩ ! የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በፈረንሳዊው ተጨዋች ሚሼል ኦሊሴ ዝውውር ዙሪያ ክለቡ ክሪስታል ፓላስን ማነጋገራቸው ተገልጿል። ሰማያዊዎቹ ፈረንሳዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ሚሼል ኦሊሴን በግል ጥቅማጥቅም ዙሪያ ለማነጋገር ከክሪስታል ፓላስ ፍቃድ መጠየቃቸው ተነግሯል። ባየር ሙኒክ እና ኒውካስል ዩናይትድ በበኩላቸው ተጫዋቹን ለማስፈረም ክሪስታል ፓላስን ማነጋገራቸው…
ቼልሲ የኦሊሴን ዝውውር ማቋረጣቸው ተገለጸ !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ፈረንሳዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ሚሼል ኦሊሴን ለማስፈረም የሚያደርጉትን ጥረት ማቋረጣቸው ተገልጿል።

ሰማያዊዎቹ በዚህ ሳምንት ፈረንሳዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ሚሼል ኦሊሴን እንዲሁም ክለቡ ክሪስታል ፓላሴን አነጋግረው እንደነበር ተነግሯል።

ይሁን እንጂ ቼልሲ ለተጨዋቹ የሚያወጡት የውል ማፍረሻ ካሳ ክፍያ ፣ ደሞዝ ፣ የፊርማ ጉርሻ እንዲሁም ሌሎች አጠቃላይ ክፍያዎች ከፍተኛ ናቸው በማለት ዝውውሩን ማቋረጣቸው ተገልጿል።

ባየር ሙኒክ ፣ ኒውካስል ዩናይትድ እና ማንችስተር ዩናይትድ በበኩላቸው ተጫዋቹን ለማስፈረም አሁንም ፍላጎት እንዳላቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#እረፍት

ኔዘርላንድ 0-0 ፈረንሳይ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቼልሲ የኦሊሴን ዝውውር ማቋረጣቸው ተገለጸ ! የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ፈረንሳዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ሚሼል ኦሊሴን ለማስፈረም የሚያደርጉትን ጥረት ማቋረጣቸው ተገልጿል። ሰማያዊዎቹ በዚህ ሳምንት ፈረንሳዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ሚሼል ኦሊሴን እንዲሁም ክለቡ ክሪስታል ፓላሴን አነጋግረው እንደነበር ተነግሯል። ይሁን እንጂ ቼልሲ ለተጨዋቹ የሚያወጡት የውል ማፍረሻ ካሳ ክፍያ ፣ ደሞዝ ፣…
ባየር ሙኒክ ኦሊሴን ለማስፈረም ተስማማ !

የጀርመን ቡንደስሊጋው ክለብ ባየር ሙኒክ የክሪስታል ፓላሱን የፊት መስመር ተጨዋች ሚሼል ኦሊሴ ለማስፈረም ከተጨዋቹ ጋር በግል ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ሚሼል ኦሊሴ ከክሪስታል ፓላስ የቀረበለትን አዲስ ውል ውድቅ በማድረግ ባየር ሙኒክን ለመቀላቀል ከስምምነት መድረሱ ተነግሯል።

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ኦሊሴን ለማስፈረም ሲያደርጉ የነበረውን ሙከራ ማቋረጣቸው መዘገቡ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
70 '

ኔዘርላንድ 0 - 0 ፈረንሳይ

*ኔዘርላንድ በዣቪ ሲሞንስ አማካኝነት ያስቆጠረችው ግብ ከጨዋታ ውጪ በሚል በቫር ተሽሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

በአውሮፓ ዋንጫ ውድድር የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ከኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ፈረንሳዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ንጎሎ ካንቴ በመጀመሪያዎቹ ሁለት የአውሮፓ ዋንጫ የምድብ ጨዋታዎች የጨዋታው ኮከብ ተብሎ መመረጥ ችሏል።

ውጤቱን ተከትሎ የመጀመሪያ ሁለት ጨዋታዎችን የተሸነፈው የፖላንድ ብሔራዊ ቡድን ከውድድሩ የተሰናበተ የመጀመሪያው ቡድን መሆኑ ተረጋግጧል።

የምድብ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

1️⃣ ኔዘርላንድ :- 4 ነጥብ

2️⃣ ፈረንሳይ :- 4 ነጥብ

3️⃣ ኦስትሪያ :- 3 ነጥብ

4️⃣ ፖላንድ :- ምንም ነጥብ

በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ሐሙስ ፈረንሳይ ከፖላንድ እንዲሁም ኔዘርላንድ ከኦስትሪያ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
Samsung Galaxy S22 Ultra
256 GB - 67,000 ETB
512 GB - 78,000 ETB

Samsung Galaxy S23 Ultra
256 GB - 92,000 ETB
512 GB - 109,000 ETB

Samsung Galaxy S24 Ultra
256 GB - 109,000 ETB
512 GB - 124,000 ETB

Exchange Available
🏍️ Free Delivery

Contact us :
0925927457 @eBRO4
@Heyonlinemarket
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
ቀጣዩ የአፍሪካ ዋንጫ መቼ ይደረጋል ?

በሞሮኮ አዘጋጅነት የሚካሄደው የ2025 አፍሪካ ዋንጫ ውድድር የሚደረግበትን ወቅት የካፍ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በትላንትናው ዕለት ባደረገው ስብሰባ ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት የ2025 የሞሮኮ አፍሪካ ዋንጫ ውድድር ከታኅሣሥ 12/2018 ዓ.ም እስከ ጥር 10/2018 ዓ.ም ለማድረግ መታቀዱን ካፍ አስታውቋል።

ውድድሩ ከሚቀጥለው አመት ክረምት ወር ወደ ጥር ወር የተዘዋወረው ቀጣይ ክረምት ከሚደረገው አዲሱ የፊፋ የአለም ክለቦች ዋንጫ ውድድር ጋር እንዳይደራረብ መሆኑ ተገልጿል።

በተጨማሪም ካፍ በተመሳሳይ በሞሮኮ የሚካሄደው የ2024 የሴቶች አፍሪካ ዋንጫ ውድድር በሚቀጥለው ክረምት ሐምሌ ወር እንደሚደረግ ይፋ አድርጓል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" አቡበከር ናስር የማሜሎዲ ሰንዳውንስ ተጨዋች አይደለም " ሩላኒ ሞክዌና

በደቡብ አፍሪካ ሊግ ለማሜሎዲ ሰንዳውንስ የሚጫወተው ኢትዮጵያዊው የፊት መስመር ተጨዋች አቡበከር ናስር አሁን ላይ የክለቡ ተጨዋች አለመሆኑን አሰልጣኝ ሩላኒ ሞክዌና ተናግረዋል።

የማሜሎዲ ሰንዳውንስ ዋና አሰልጣኝ ሩላኒ ሞክዌና ትላንት ምሽት ከሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን ጋር ባደረጉት ቆይታ ስለ አቡበከር ናስር የክለቡ ሁኔታ ተጠይቀው ነበር።

ለወራት በጉዳት ላይ የነበረው አቡበከር ናስር በዘንድሮው የውድድር አመት በሁለተኛው ዙር ከማሜሎዲ ሰንዳውንስ የቡድን ዝርዝር ውጪ ተደርጎ እንደነበር ይታወሳል።

አሰልጣኝ ሩላኒ ሞክዌና በሰጡት አስተያየትም በቡድን ዝርዝራቸው ውስጥ ስላልተመዘገበ ተጨዋች መናገር እንደማይፈልጉ በመግለፅ " አቡበከር ናስር አሁን ላይ የእኛ ተጨዋች አይደለም "ሲሉ ተደምጠዋል።

አሰልጣኝ ሩላኒ ሞክዌና ይህንን ይበሉ እንጂ ክለቡ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ እስካሁን ስለ አቡበከር ናስር ሁኔታ በይፋ ያለው ነገር የለም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጄሴ ማርሽ አርጀንቲና እንድትቀጣ ጠይቀዋል !

የካናዳ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ጄሴ ማርሽ የትላንት ተጋጣሚያቸው አርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ቅጣት እንዲጣልበት አወዳዳሪውን አካል ጠይቀዋል።

አሰልጣኙ ቅጣቱ እንዲጣል የጠየቁት የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ከእረፍት መልስ ከመልበሻ ቤት ለመውጣት የተወሰኑ ደቂቃዎች መዘግየታቸውን ተከትሎ ነው።

አሰልጣኝ ጄሴ ማርሽ በንግግራቸውም " ከእኛ ጋር እንዴት እንደሚጫወቱ ቪዲዮች እየተመለከቱ ሲተነትኑ እንደነበር አውቃለሁ ዳኞች የሆነ ነገር ማድረግ ነበረባቸው እኛ ብንዘገይ እንቀጣ ነበር አርጀንቲና መቀጣት አለባት።"ብለዋል።

ጨዋታውን የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ከእረፍት በኋላ ባስቆጠራቸው ግቦች 2ለ0 ማሸነፉ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" የምድቡ መሪ ሆነን ማለፍ እንፈልጋለን " ከሪም አክቱርኮግሉ

የቱርክ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጨዋች ከሪም አክቱርኮግሉ የምሽቱን የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ጨዋታ ለማሸነፍ አልመው ወደ ሜዳ እንደሚገቡ ገልጿል።

" ለየትኛውም ጨዋታ የምንዘነጋጀው ለማሸነፍ ብቻ ነው " የሚለው ከሪም አክቱርኮግሉ ፖርቹጋልን ለማሸነፍ በጥሩ ሁኔታ ተዘጋጅተናል አሸንፈን የምድቡ የበላይ ሆነን ማለፍ እንፈልጋለን ብሏል።

የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ከቱርክ ብሔራዊ ቡድን ጋር የአውሮፓ ዋንጫ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታቸውን ዛሬ ምሽት 1:00 ያደርጋሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የኢትዮጵያ  ቡና ይፋዊ አጋር የሆነው ቤቲካ - የኢትዮጵያ ቡናን  23ኛ የጨዋታ ቀን የዲጂታል መፅሄት ይዞ ቀርቧል።
በመፅሄቱ ላይ የዕለቱ ጨዋታን የተመለከቱና ሌሎች የተለያዩ መረጃዎች የሚቀርቡ ይሆናል፡፡

መፅሄቱን ለማግኘት ቀጣዩን ሊንክ ይጫኑ

https://www.tg-me.com/betikaethiopia/5347

የጨዋታ መፅሄት ቁጥር 23
ኢትዮጵያ መድን ከ ኢትዮጵያ ቡና
ዛሬ 9:00

ቤቲካ - የኢትዮጵያ ቡና ይፋዊ አጋር
2024/09/29 12:26:35
Back to Top
HTML Embed Code: