Telegram Web Link
ሌኒ ዮሮ ማድሪድን ሊመርጥ ይችላል !

ባሳለፍነው የውድድር አመት ጥሩ ጊዜን ማሳለፍ የቻለው የሊሉ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሌኒ ዮሮ በቀጣይ ሪያል ማድሪድን ለመቀላቀል ሊመርጥ እንደሚችል ተገልጿል።

ፈረንሳዊው ተጨዋች ሌኒ ዮሮ ከሪያል ማድሪድ በተጨማሪ በፕርሚየር ሊጎቹ ሊቨርፑል እና ማንችስተር ዩናይትድ በጥብቅ እየተፈለገ ይገኛል።

የተጨዋቹ ፈላጊዎች የፕርሚየር ሊጎቹ ማንችስተር ዩናይትድ እና ሊቨርፑል ተጨዋቹ ከእነሱ ይልቅ ሪያል ማድሪድን ለመቀላቀል እንደሚመርጥ እንደሚያውቁ ተገልጿል።

የ 19ዓመቱ የመሐል ተከላካይ ሌኒ ዮሮ የዝውውር ሒሳብ 50 ሚልዮን ዩሮ ሊደርስ እንደሚችል ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ካንሴሎ በባርሴሎና መቆየት ይፈልጋል !

ፖርቹጋላዊው የማንችስተር ሲቲ ተጨዋች ጇ ካንሴሎ በቀጣይ በካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ቤት መቀጠል እንደሚፈልግ በሰጠው አስተያየት አረጋግጧል።

ያለፈውን የውድድር አመት በውሰት በባርሴሎና ያሳለፈው ጇ ካንሴሎ " ባርሴሎና ውስጥ መሆን እፈልጋለሁ ምችት ተሰምቶኛል ቤተሰቦቼም ደስተኞች ናቸዉ እዚህ እንደምቀጥል ተስፋ አለኝ።"ሲል ተደምጧል።

ባርሴሎና በበኩሉ በሚቀጥለው የውድድር አመት ጇ ካንሴሎን በድጋሜ በውሰት ለማስፈረም እየሰሩ መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
📯 አስቀድመው ተዘጋጅተው የሚወስዷቸው ትጥቆች ከ #ዋናው!

🏃🏾‍♂ #ይምጡ#ይዘዙን!

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ይዘዙን።

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
የፈረንሳይ እና ኔዘርላንድን ጨዋታ ማን ይመራዋል ?

የፊታችን አርብ የፈረንሳይ እና ኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድኖች የሚያደርጉትን የአውሮፓ ዋንጫ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ የሚመሩት ዳኛ ታውቀዋል።

ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች አርብ ምሽት 4:00 ሰዓት በሌፕዚግ ስታዲየም የሚያደርጉትን ተጠባቂ ጨዋታ እንግሊዛዊው ዳኛ አንቶኒ ቴለር በመሐል ዳኝነት እንደሚመሩት ተገልጿል።

አንቶኒ ቴለር ከዚህ በፊት አንድ ጊዜ ሁለቱን ብሔራዊ ቡድኖች ያገናኘ ጨዋታ የመሩ ሲሆን ጨዋታውን ብርቱካናማዎቹ በአሸናፊነት ማጠናቀቅ ችለዋል።

ጨዋታውን ማን ያሸንፋል ?

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የፈረንሳይ ሊግ የቴሌቪዥን መብቱን ለመሸጥ ተቸግሯል ! የፈረንሳይ ሊግ ለሚቀጥለው የውድድር ዘመን የቴሌቪዥን መብቱን የሚገዛው የጨዋታ አስተላላፊ ተቋም ለማግኘት መቸገሩ ተገልጿል። ሊጉ ከቴሌቪዥን መብት ሽያጭ #አንድ ቢልዮን ዩሮ ለማግኘት እቅድ ይዞ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ በግማሽ ወርዶ እስከ 500 ሚልዮን ዩሮ ለማግኘት ማለሙ እየተገለፀ ይገኛል። የሊጉ ክለቦች ከቴሌቪዥን መብት የሚያገኙትን…
የፈረንሳይ ሊግ የቀረበለትን ሒሳብ ውድቅ አደረገ !

የሚቀጥለው የውድድር አመት የሊጉን የቴሌቪዥን መብት ለመሸጥ የተቸገረው የፈረንሳይ ሊግ አሁን ላይ ከ " DAZN " የቀረበለትን 400 ሚልዮን ዩሮ ክፍያ ውድቅ ማድረጉ ተገልጿል።

የፈረንሳይ ሊግ ከቴሌቪዥን መብት አንድ ቢልዮን ዩሮ ለማግኘት ቢያቅድም ፍላጎት ያሳየ የእግርኳስ አስተላላፊ ተቋም ማግኘት እንዳልቻለ እና ገንዘቡን በግማሽ ሊቀንስ ማሰቡ ተዘግቦ ነበር።

የእንግሊዙ የእግርኳስ አስተላላፊ ተቋም " DAZN " ከዚህ በፊት ለሊጉ የቴሌቪዥን መብት 500 ሚልዮን ዩሮ አቅርቦ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቶ ነበር።

ተቋሙ አሁን ላይ ሌሎች ተቋማት የፈረንሳይ ሊግን የቴሌቪዥን መብት ለመግዛት ፍላጎት አለማሳየታቸውን ተከትሎ በድጋሜ ገንዘቡን ቀንሶ 400 ሚልዮን ዩሮ አቅርቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

10:00 ክሮሽያ ከ አልባንያ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

የአልባንያ ብሔራዊ ቡድን ከደቂቃዎች በኋላ ከክሮሽያ ብሔራዊ ቡድን ጋር በሚያደርገው ጨዋታ በጣልያን ከተሸነፈበት የመጀመሪያ ጨዋታ የሁለት ተጨዋቾች ለውጥ አድርጓል።

ብሔራዊ ቡድኑ አርማንዶ ብሮሀን በሬይ ማናህ እንዲሁም ቃዚም ላቺን በታውላንት ሴፌሪን ተክቶ ወደ ሜዳ ይገባል።

የክሮሽያ ብሔራዊ ቡድን በበኩሉ ሽንፈት ካስተናገደበት የስፔን ጨዋታ ውስጥ ሶስት ተጨዋቾችን ተጠባባቂ አድርጎ ጨዋታውን የሚጀምር ይሆናል።

ክሮሽያ ሁለቱን ተከላካዮች ጆሲፕ ስታንሲች እና ማሪን ፖንግራቺች በጁራኖቪች እና ኢቫን ፔርሲች ስትተካ አጥቂው አንቴ ቡዲሚር በበኩሉ ብሩኖ ፔትኮቪችን ተክቷል።

ኢቫን ፔሪሲች በቋሚ አሰላለፍ መካተቱን ተከትሎ የማንችስተር ሲቲው የመስመር ተጨዋች ጆስኮ ግቫርዲዮል የግራ መሐል ተከላካይ ሆኖ እንደሚጫወት ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ተጀመረ

ክሮሽያ 0 - 0 አልባንያ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
11 '

ክሮሽያ 0 - 1 አልባንያ

ላቺ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ሮናልዶ አሞበላችን በመሆኑ በጣም ደስተኞች ነን " በርናርዶ ሲልቫ

የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን የመሐል ሜዳ ተጨዋች በርናርዶ ሲልቫ ቡድናቸው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአውሮፓ ዋንጫው ግብ እንዲያስቆጥር የቻለውን እንደሚያግዝ ተናግሯል።

" ሮናልዶ የብሔራዊ ቡድናችን አምበል በመሆኑ በጣም ደስተኞች ነን " የሚለው በርናርዶ ሲልቫ እሱ ግብ እንዲያስቆጥር እና ቡድኑን እንዲያግዝ ሁሉንም ነገር እናደርጋለን ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
33 '

ክሮሽያ 0 - 1 አልባንያ

              ላቺ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#እረፍት

ክሮሽያ 0 - 1 አልባንያ

              ላቺ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
60 '

ክሮሽያ 0 - 1 አልባንያ

              ላቺ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ፍፃሜ ከደረሰን ፈረንሳይን መግጠም እንፈልጋለን "

የቱርክ ብሔራዊ ቡድን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች አብዱልከሪም ባርዳክቺ ፍፃሜ የሚደርሱ ከሆነ ፈረንሳይ እንድትገጥማቸው እንደሚፈልግ በሰጠው አስተያየት ገልጿል።

ቱርክ በአውሮፓ ዋንጫ ውድድሩ ለፍፃሜ የምትደርስ ከሆነ " የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን የፍፃሜ ተፋላሚያችን እንዲሆን እፈልጋለሁ " ሲል አብዱልከሪም ባርዳክቺ ተናግሯል።

ስለ ቀጣይ ተጋጣሚያቸው ፖርቹጋል አስተያየት የሰጠው ተጨዋቹ " ከሮናልዶ ጋር መጫወት ለእኔ የተለየ ስሜት ይፈጥርብኛል ፣ በዚህ በጣም ተደስቻለሁ ፣ ሮናልዶ ለእኔ የአለም ምርጡ ተጨዋች ነው።"ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
74 '

ክሮሽያ 1 - 1 አልባንያ

ክራማሪች              ላቺ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
76 '

ክሮሽያ 2 - 1 አልባንያ

ክራማሪች              ላቺ
ግሀሱላ ( በራስ ላይ )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
90+5 '

ክሮሽያ 2 - 2 አልባንያ

ክራማሪች              ላቺ
ጋሱላ ( በራስ ላይ ) ጋሱላ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EURO2024

የክሮሽያ ብሔራዊ ቡድን ከአልባንያ አቻቸው ጋር ያደረጉትን የአውሮፓ ዋንጫ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ለክሮሽያ ብሔራዊ ቡድን ግቦችን አንድሬ ክራማሪቾ እና ጋሱላ በራሱ ግብ ላይ ከመረብ ሲያሳርፉ ለአልባንያ ቃዚም ላቺ እና ጋሱላ አስቆጥረዋል።

ክሮሽያ በአንድ ነጥብ በግብ ክፍያ ተበልጣ የምድቡን የመጨረሻ ደረጃ ስትይዝ አልባንያ በተመሳሳይ አንድ ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ቀጣይ ሳምንት ሰኞ ክሮሽያ ከጣልያን እንዲሁም አልባንያ ከስፔን ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/29 22:28:01
Back to Top
HTML Embed Code: