Telegram Web Link
" ሻምፒየንስ ሊግ ከባሎን ዶር ይበልጣል " ሲልቫ

የማንችስተር ሲቲው ፖርቹጋላዊ የፊት መስመር ተጨዋች በርናርዶ ሲልቫ ለእሱ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ከባሎን ዶር ሽልማት የበለጠ ዋጋ እንዳለው ገልጿል።

" የቡድን አጋሮቼን ለማገዝ እና ለቡድናችን ጥሩ ነገር ለማድረግ ሁልጊዜም ያለኝን ሁሉ እሰጣለሁ " የሚለው በርናርዶ ሲልቫ " የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግን ማሸነፍ ባሎን ዶርን ከማሸነፍ ይበልጣል በፍጹም አልለውጥም።"ሲል ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አሌሀንድሮ ጋርናቾ በኦሎምፒክ ውድድር ይሳተፋል ?

የአርጀንቲና ኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዣቪየር ማሼራኖ የማንችስተር ዩናይትዱን የፊት መስመር ተጨዋች አሌሀንድሮ ጋርናቾ በኦሎምፒክ ስብስቡ ውስጥ ማካተት እንደሚፈልግ ተገልጿል።

ማንችስተር ዩናይትዶች በበኩላቸው እስካሁን አሌሀንድሮ ጋርናቾ በኦሎምፒክ ውድድር እንዲሳተፍ መፍቀድ አለመፍቀዳቸውን አለማሳወቃቸው ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
📢 #ለቸኮሉ መፍትሔ ከ #ዋናው!

👉🏾 #ዋናው ስፖርት ጊዜዎን ቆጣቢ የሆነ ሁነኛ መፍትሔን ይዞሎት መጥቷል፣ አስቀድመው ተዘጋጅተው የሚወስዷቸው ማልያዎች!

🚀 #ይምጡ፣ ይህን ቀላል አማራጭ ይጠቀሙ!

📍አድራሻችን:- ገርጂ መብራት ሃይል የካቲት ወረቀት ፊትለፊት፣ አለም ገብሬ ህንፃ፣ 2ተኛ ፎቅ።

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ወይም በቴሌግራም ቦት @WANAWSbot በኩል ይዘዙን።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
የሳውዲ ክለቦች ቤከርን ማስፈረም ይፈልጋሉ !

የሳውዲ አረቢያ ክለቦች ብራዚላዊውን የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ቁጥር አንድ ግብ ጠባቂ አሊሰን ቤከር የማስፈረም ፍላጎት እንዳላቸው ተገልጿል።

ሳውዲ አረቢያዎች ባለፉት ወራት ሊቨርፑል አሊሰን ቤከርን ለሽያጭ ያቀርብ እንደሆነ ጥያቄ አቅርበው እንደነበር ተነግሯል።

ይሁን እንጂ ሊቨርፑልም ሆነ አሊሰን ቤከር የመለያየት ፍላጎት እንደሌላቸው ለክለቦቹ ማሳወቃቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኤቨርተን የተጫዋቹን ውል ሊያራዝም ነው !

የመርሲሳይዱ ክለብ ኤቨርተን የፊት መስመር ተጨዋቻቸው ዶምኒክ ካልቨርት ሌዊንን ኮንትራት ለማራዘም ንግግር መጀመራቸው ተገልጿል።

የ 27ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ዶምኒክ ካልቨርት ሌዊን በኤቨርተን ቤት ያለው ኮንትራት ሊጠናቀቅ አንድ አመት ይቀረዋል።

ተጨዋቹ በሌላኛው የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ክለብ ኒውካስል ዩናይትድ ለረጅም ጊዜ ሲፈለግ እንደነበር ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ስለ ማድሪድ ታሪኩ ይናገራል " ሳንቾ

የቦርስያ ዶርትመንድ የፊት መስመር ተጨዋች ጄደን ሳንቾ የቅዳሜው የሪያል ማድሪድ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ትልቅ ፍልሚያ እንደሚሆን ተናግሯል።

" የሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ በጣም የምወደው ጨዋታ ነው " ያለው ጄደን ሳንቾ " ትልቅ ጨዋታ ይሆናል የሪያል ማድሪድ ታሪክ በራሱ ይናገራል።"ሲል ተደምጧል።

" ሪያል ማድሪድ ውስጥ ቪንሰስ እና ቤሊንግሀምን የመሳሰሉ ጓደኞች አሉኝ ፣ ከሙኒክ ጨዋታ በኋላ አውርተናል በፍፃሜው እንገናኝ ብያቸዋለሁ ፣ ለጨዋታው ጓጉቻለሁ።" ሳንቾ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ካሜሮን አዲስ አሰልጣኟን ማሰናበቷ ተገለጸ ! በቀድሞ ተጨዋች ሳሙኤል ኤቶ የሚመራው የካሜሮን እግርኳስ ፌዴሬሽን ከወር በፊት የሾሙትን አዲስ የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ማርክ ብራይስ ምንም ጨዋታ ሳያደርጉ ማሰናበታቸው ተገልጿል። አሰልጣኝ ሪጎበርት ሶንግን ከአፍሪካ ዋንጫው ውድድር በኋላ ያሰናበተው የካሜሩን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ማርክ ብራይስን የሾመው በሀገሪቱ ስፖርት ሚንስቴር በኩል ነበር። በአዲሱ…
ሳሙኤል ኤቶ አሰልጣኙን ይቅርታ ጠየቀ !

የካሜሮን እግርኳስ ፌዴሬሽንን እየመራ የሚገኘው የቀድሞ ተጨዋች ሳሙኤል ኤቶ ቤልጂየማዊውን አሰልጣኝ ማርክ ብራይስ ይቅርታ መጠየቁ ተገልጿል።

ሳሙኤል ኤቶ ከቀናት በፊት ከእሱ ፍቃድ ውጪ በሀገሪቱ ስፖርት ሚንስቴር ከተሾሙት የብሔራዊ ቡድኑ አዲስ አሰልጣኝ ማርክ ብራይስ ጋር ፀብ ውስጥ መግባቱ እና ከሀላፊነት ማሰናበቱ ይታወሳል።

አሁን ላይ ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ኤቶ ይቅርታ መጠየቁ እና አሰልጣኝ ማርክ ብራይስ በሀላፊነታቸው እንዲቀጥሉ ከስምምነት መድረሱ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ኬረን ማኬን ኮንትራታቸውን ሊያራዝሙ ነው ! በሊጉ ታላላቅ ክለቦች እየተፈለጉ የሚገኙት አሰልጣኝ ኬረን ማኬን አዲስ የረጅም ጊዜ ኮንትራት ሊፈራረሙ መሆኑ ተዘግቧል። ኢፕስዊች ታውንን በማሰልጠን ላይ የሚገኙት ኬረን ማኬን ክለቡን ወደ ሊጉ ካሳደጉ በኋላ ኮንትራታቸውን ለማራዘም ከጫፍ መድረሳቸው ታውቋል። ቼልሲ ፣ ማንችስተር ዩናይትድ እና ብራይተን የ 38ዓመቱን አሰልጣኝ ኬረን ማኬንን ለማስፈረም…
አሰልጣኝ ኬረን ማኬና ኮንትራታቸውን አራዘሙ !

ከሊጉ ታላላቅ ክለቦች ጋር ስማቸው በስፋት ሲያያዝ የቆዩት አሰልጣኝ ኬረን ማኬና አዲስ የረጅም ጊዜ ኮንትራት መፈራረማቸው ይፋ ሆኗል።

ኢፕስዊች ታውንን በማሰልጠን ላይ የሚገኙት አሰልጣኝ ኬረን ማኬና ክለቡን ወደ ሊጉ ካሳደጉ በኋላ ኮንትራታቸውን እስከ 2028 ማራዘማቸው ታውቋል።

" ባለፉት አመታት በጋራ ባመጣናቸው አስደናቂ ስኬቶች ተደስተናል ኢትስዊችን ከሀያ ሁለት አመታት በኋላ በሊጉ የሚያደርገውን ጉዞ እንድመራ በተሰጠኝ ሀላፊነት እና እድል ተደስቻለሁ።" ሲሉ ኬረን ማኬና ከፊርማው በኋላ ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጀርመን ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ከፖሊስ ጋር ልምምድ ሰርተዋል !

ሀገራቸው ለምታዘጋጀው የ2024 አውሮፓ ዋንጫ ውድድር በዝግጅት ላይ የሚገኙት የጀርመን ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ዛሬ ከፖሊስ ጋር የተለየ የልምምድ ጊዜ ማሳለፋቸው ተገልጿል።

ተጨዋቾቹ ከፖሊስ ጋር በነበራቸው ስልጠና ወቅት የተለያዩ መስናክሎችን ሲወጡ እና አጫጭር የውጊያ ስልጠናዎችን ሲወስዱ እንዲሁም ልዩ ተግባራትን ሲፈከውኑ መስተዋላቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም ተጨዋቾቹ የፖሊስ ደህንነት መከላከያ በማድረግ እርስበርስ መደባደባቸው ሲገለፅ ሀያ ሜትር ከፍታ ያለው ግምብ ላይ በመውጣት የጀርመንን ባንዲራ እንዲሰቅሉ መታዘዛቸው ተነግሯል።

ልዩ ስልጠናውን ያዘጋጁት የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ጁሊያን ኔግልስማን መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን አላማውም አብሮነትን ፣ መግባባትን እና ለቡድኑ ዋጋ የመክፈል አስተሳሰብን ለማሳደግ መሆኑ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኤዲሰን ካቫኒ ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ አገለለ !

ዩራጓዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኤዲሰን ካቫን በሰላሳ ሰባት አመቱ ራሱን ከዩራጓይ ብሔራዊ ቡድን ማግለሉን ይፋ አድርጓል።

ለአርጀንቲናው ክለብ ቦካ ጁኒየር በመጫወት ላይ የሚገኘው ኤዲሰን ካቫኒ ለብሔራዊ ቡድኑ ባደረጋቸው አንድ መቶ ሰላሳ ስድስት ጨዋታዎች ሀምሳ ስምንት ግቦችን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

በተጨማሪም ኤዲሰን ካቫኒ ከዩራጓይ ብሔራዊ ቡድን ጋር እ.ኤ.አ 2011 የኮፓ አሜሪካ ዋንጫን ማሳካት ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የሮድሪጎ የሪያል ማድሪድ ቆይታ ? ብራዚላዊው የሪያል ማድሪድ የፊት መስመር ተጨዋች ሮድሪጎ በቀጣይ ሎስ ብላንኮዎቹን ስለመልቀቅ ሊያስብ የሚችልበት አጋጣሚ ሊፈጠር እንደሚችል ተገልጿል። ተጨዋቹ አሁን ላይ በሪያል ማድሪድ ቤት ደስተኛ እንደሆነ እና ለመልቀቅ እያሰበ እንደማይገኝ ተነግሯል። ይሁን እንጂ ሮድሪጎ በክለቡ ያለውን የመጫወቻ ጊዜ በሌላ ተጨዋች የሚቀማ ከሆነ ሌሎች ተጨዋቾች እንደሚያደርጉት…
" ሲቲ የአለም ምርጡ ክለብ ነው " ሮድሪጎ

ብራዚላዊው የሪያል ማድሪድ የፊት መስመር ተጨዋች ሮድሪጎ ማንችስተር ሲቲ አሁን ላይ የአለማችን ምርጡ ክለብ መሆኑን በሰጠው አስተያየት ገልጿል።

" እውነት ለመናገር በሩብ ፍፃሜው ማንችስተር ሲቲ ከእኛ የበላይ እንደነበር ሁላችንም እናውቃለን " ያለው ሮድሪጎ እነሱ የአለም ምርጥ ክለብ ናቸው የሚጫወቱት ምርጥ እግርኳስ ነው ነገርግን እኛ ልገልጸው የማልችለው የተለየ ነገር አለን።"ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
በርንሌይ ፍራንክ ላምፓርድን መሾም ይፈልጋል !

ከአሰልጣኝ ቪንሴንት ኮምፓኒ ጋር የተለያየው በርንሌይ አሰልጣኝ ፍራንክ ላምፓርድን በሀላፊነት ለመሾም ፍላጎት እንዳላቸው ተገልጿል።

ወደ እንግሊዝ ሻምፒዮን ሺፕ የወረደው በርንሌይ አሰልጣኝ ቪንሴንት ኮምፓኒን በባየር ሙኒክ ከተቀማ ወዲህ አዲስ አሰልጣኝ እያፈላለገ ሲሆን ፍራንክ ላምፓርድ የመጀመሪያ ተመራጭ መሆኑ ተነግሯል።

የ 45ዓመቱ አሰልጣኝ ፍራንክ ላምፓርድ ባለፈው የውድድር አመት መጨረሻ ቼልሲን በጊዜያዊ አሰልጣኝነት ከመራ ወዲህ ያለ ሀላፊነት ይገኛል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
🥁ተጀመረ ተጀመረ ተተተጀመረ!🔥
በነጻ ውርርዶች ደንበኞችን ሊያንበሸብሽ የአቪዬተር ሻሞ ተጀመረ!
በየቀኑ እስከ 4000 ብር ዋጋ ያላቸው ሻሞዎች እርሶን ይጠብቃሉ!
በውርርዶች እያሸነፉ ከሻሞው የድርሻዎን ይቅለቡ!
አሁን ነው መብረር!

ቤቲካ - የአሸናፊዎች ቤት!"
Forwarded from HEY Online Market
Apple Vision Pro

🔹VisionPro provides a comprehensive set of vision tools for applications like inspection, gauging, and guidance.
🔸It's commonly used in industries such as automotive, electronics, pharmaceuticals, and more to improve manufacturing processes, ensure product quality, and increase productivity.

Contact Us
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
ጆቤ ቤሊንግሀም ወዴት ሊያመራ ይችላል ?

ለሰንደርላንድ የሚጫወተው እንግሊዛዊው የጁድ ቤሊንግሀም ወንድም ወጣቱ ጆቤ ቤሊንግሀም በፕርሚየር ሊግ ክለቦች እየተፈለገ ይገኛል።

የ 18ዓመቱ ተጨዋች ጆቤ ቤሊንግሀምን ለማስፈረም በአሰልጣኝ ቶማስ ፍራንክ የሚመራው ብሬንትፎርድ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም ክሪስታል ፓላስ ተጨዋቹን ለማስፈረም ወደ ዝውውሩ መግባታቸው እና ንግግር መጀመራቸው ተዘግቧል።

ተጨዋቹ በመሐል ሜዳ እና በፊት መስመር ተጨዋችነት ግልጋሎት የመስጠት ክህሎት እንዳለው ሲገለፅ ባለፈው አመት ለሰንደርላንድ ባደረጋቸው አርባ አምስት ጨዋታዎች ሰባት ግቦች አስቆጥሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቼልሲ አዲስ አጥቂ ማስፈረም ይፈልጋል !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በክረምቱ የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት አዲስ የፊት መስመር አጥቂ ማስፈረም እንደሚፈልጉ ተገልጿል።

በሚቀጥለው አመት ተፎካካሪ ሆነው መቅረብ የሚፈልጉት ሰማያዊዎቹ አሁን ላይ ለማስፈረም ከሚፈልጓቸው አጥቂዎች መካከል ናይጄሪያዊው ተጨዋች ቪክቶር ኦሲሜን #አለመኖሩ ተነግሯል።

ሰማያዊዎቹ በቀጣይ ቤልጂየማዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ሮሜሎ ሉካኩ እና አርማንዶ ብሮሀን በቋሚነት ለመሸጥ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጄራርድ ፒኬ ምርመራ እንደተከፈተበት ተገለጸ !

የቀድሞ የስፔን ብሔራዊ ቡድን እና ባርሴሎና የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ጄራርድ ፒኬ በሙስና ወንጀል ተጠርጥሮ ምርመራ እየተደረገበት እንደሆነ ተገልጿል።

ጄራርድ ፒኬ ምርመራው የተከፈተበት ሉዊስ ሩብያሌስ የስፔን እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት በነበሩበት ወቅት የስፔን ሱፐር ካፕ ውድድር ወደ ሳውዲ አረቢያ ማምራት ጋር በተያያዘ መሆኑ ተነግሯል።

የስፔን ሱፐር ካፕ ውድድር ሳውዲ አረቢያ ላይ እንዲደረግ የአምስት አመት ውል ሲፈፀም የጄራርድ ፒኬ ተቋም የኮሚሽን ክፍያ ማግኘቱ ተገልጿል።

እስከ 2025 በሚዘልቀው ስምምነቱ የጄራርድ ፒኬ ተቋም እንደ ኮሚሽን በአመት #አራት ሚልዮን ዩሮ እንደሚቀበል ሲገለፅ የስፔን እግርኳስ ፌዴሬሽን #አርባ ሚልዮን ዩሮ እንደሚያገኝ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጆዜ ሞሪንሆ ወደ ቱርክ ሊያመሩ ነው !

ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ የቱርክ ሱፐር ሊጉን ክለብ ፌነርባቼ በሀላፊነት ለመረከብ በንግግር ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

ስማቸው ከሳውዲ አረቢያ ክለቦች ጋር ሲያያዝ የቆዩት አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ፌነርባቼን ለሁለት የውድድር አመታት ለማሰልጠን በቃል ደረጃ መስማማታቸው ተገልጿል።

አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ከወራት በፊት ከሴርያው ክለብ ሮማ ከተሰናበቱ ወዲህ ያለ ሀላፊነት እንደሚገኙ ይታወቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሞናኮ ተጨዋቹ የጨዋታ እገዳ ተጣለበት !

ማሊያዊው የሞናኮው የመሐል ሜዳ ተጨዋች መሐመድ ካማራ ከፈረንሳይ እግርኳስ ሊግ የአራት ጨዋታዎች እገዳ ቅጣት እንደተጣለበት ተገልጿል።

ተጨዋቹ እገዳው የተጣለበት በሊጉ የመጨረሻ ሳምንት መርሐ ግብር በማልያው ላይ የነበረውን ግብረ ሰዶማዊያንን የሚደግፍ አርማ እንዳይታይ መሸፈኑን ተከትሎ መሆኑ ተነግሯል።

ተጨዋቹ በተጨማሪም ጨዋታው ከመጀመሩ አስቀድሞ ተጨዋቾቹ ከግብረ ሰዶማዊያን አርማ ጋር በነበራቸው የፎቶ ጊዜ ላይ ለመገኘት ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቶ እንደነበር ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/04 07:36:41
Back to Top
HTML Embed Code: