Telegram Web Link
TIKVAH-SPORT
የአሰልጣኝ ዣቪ የባርሴሎና ቆይታ ? ስፔናዊው የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ዋና አሰልጣኝ ዣቪ ከክለቡ ሊሰናበቱ እንደሚችሉ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን በመዘገብ ላይ ናቸው። አሰልጣኝ ዣቪ ከቀናት በፊት ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ የሰጡት አስተያየት ከባርሴሎናው ፕሬዝዳንት ሁዋን ላፖርታ ጋር አለመግባባት ውስጥ ሳይከታቸው እንዳልቀረ ተዘግቧል። ዣቪ ከቀናት በፊት ቡድናቸው ከሌሎች ክለቦች ጋር ለመፎካከር…
ባርሴሎና አሰልጣኝ ዣቪን አሰናበተ !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ስፔናዊውን አሰልጣኝ ዣቪ ሀርናንዴዝ በዛሬው ዕለት ከሀላፊነታቸው ማሰናበቱን ይፋ አድርጓል።

የባርሴሎናው ፕሬዝዳንት ሁዋን ላፖርታ በዛሬው እለት ከአሰልጣኝ ዣቪ ሀርናንዴዝ ጋር እንደተነጋገሩ እና ውሳኔውን እንዳሳወቁ ተዘግቧል።

አሰልጣኝ ዣቪ ከወራት በፊት በአመቱ መጨረሻ ባርሴሎናን እንደሚለቁ አሳውቀው የነበረ ቢሆንም በቅርቡ ክለቡ ሀሳባቸውን አስቀይሯቸው ለመቆየት ወስነው እንደነበር አይዘነጋም።

በቀጣይ ጀርመናዊው አሰልጣኝ ሀንሲ ፊሊክ ባርሴሎናን በሀላፊነት ይረከባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ባርሴሎና አሰልጣኝ ዣቪን አሰናበተ ! የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ስፔናዊውን አሰልጣኝ ዣቪ ሀርናንዴዝ በዛሬው ዕለት ከሀላፊነታቸው ማሰናበቱን ይፋ አድርጓል። የባርሴሎናው ፕሬዝዳንት ሁዋን ላፖርታ በዛሬው እለት ከአሰልጣኝ ዣቪ ሀርናንዴዝ ጋር እንደተነጋገሩ እና ውሳኔውን እንዳሳወቁ ተዘግቧል። አሰልጣኝ ዣቪ ከወራት በፊት በአመቱ መጨረሻ ባርሴሎናን እንደሚለቁ አሳውቀው የነበረ ቢሆንም በቅርቡ ክለቡ…
ዣቪ እሁድ የመጨረሻ ጨዋታቸውን ይመራሉ !

ስፔናዊው የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና አሰልጣኝ ዣቪ በሚቀጥለው የውድድር አመት ከክለቡ ጋር እንደማይቀጥሉ በዛሬው ዕለት ይፋ ተደርጓል።

አሰልጣኝ ዣቪ ሀርናንዴዝ የባርሴሎና የመጨረሻ ጨዋታቸውን እሁድ ከሲቪያ ጋር በሚደረግ መርሐ ግብር እንደሚመሩ ተገልጿል።

ዣቪ ሀርናንዴዝ ባርሴሎናን በአሰልጣኝነት እየመሩ ባለፈው አመት የላሊጋውን ዋንጫ ማሳካት ችለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የዩናይትድ እና ሲቲን ጨዋታ ማን ይመራዋል ?

ማንችስተር ዩናይትድ ከ ማንችስተር ሲቲ ጋር በነገው ዕለት የሚያደርጉትን የእንግሊዝ ኤፌ ካፕ ፍፃሜ ጨዋታ የሚመሩት ዳኛ ታውቀዋል።

ዌምብሌይ ስታዲየም የሚደረገውን ተጠባቂ የማንቹንያን ደርቢ የኤፌ ካፕ ፍፃሜ ጨዋታ አንዲ ማድሌይ በመሐል ዳኝነት እንደሚመሩት ይፋ ተደርጓል።

ጨዋታውን ማይክል ኦሊቨር በቫር ዳኝነት እንደሚመሩት ተገልጿል።

ጨዋታውን ማን ያሸንፋል ?

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
" ወደዚህ የመጣሁት ዋንጫ ለማሸነፍ ነው " ቴንሀግ የማንችስተር ዩናይትድ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ቡድናቸው ቅዳሜ ከማንችስተር ሲቲ ጋር ከሚያደርገው የኤፌ ካፕ ፍፃሜ ጨዋታ በፊት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ምን አሉ ? - " ወደዚህ የመጣሁት ዋንጫ ለማሸነፍ ነው ቅዳሜ ደግሞ የምናሸንፍበት እድል አለን እንደ ቡድን ለፍፃሜ መድረስ ይገባናል ዋንጫውን ማሸነፍ እንፈልጋለን።…
" የነገው ጨዋታ ከሊጉ የተለየ ነው " ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ቡድናቸው ነገ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ከሚያደርገው የኤፌ ካፕ ፍፃሜ ጨዋታ በፊት ከጋዜጠኞች ጋር ቆይታ አድርገዋል።

አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ምን አሉ ?

" በፕርሚየር ሊጉ ከማንችስተር ዩናይትድ የተሻልን ነበርን ቀጣይነት ያለው አቋምም አሳይተናል የነገው ጨዋታ ግን የተለየ ነው የሚሆነው አንድ ጨዋታ ነው ዩናይትድ ያው ዩናይትድ ነው።

- ማንችስተር ዩናይትድ አሁን ላይ ያላቸው የቡድን ስብስብ ጥሩ እና የተለየ ነው።

- ባለፉት አስር አመታት ማንችስተር ሲቲ የተሻለ ክለብ ነበር ነገርግን በታሪክ ደረጃ ማንችስተር ዩናይትድ የእንግሊዝ ምርጡ ክለብ ነው ለእነሱ ትልቅ ክብር አለን።

- ኤሪክ ቴንሀግ ማንችስተር ዩናይትድ ውስጥ ለሰራው ነገር ክብር አለኝ ፣ ብዙ ጉዳቶች ነበሩበት ጥሩ ተጨዋቾች ቢኖሩትም ከተጎዱ መጠቀም አይችልም።

- አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በቆይታቸው ወቅት ማንችስተር ሲቲ በጨዋታው ከኤደርሰን ውጪ ሁሉም ተጨዋቾቹ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ዣቪ እሁድ የመጨረሻ ጨዋታቸውን ይመራሉ ! ስፔናዊው የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና አሰልጣኝ ዣቪ በሚቀጥለው የውድድር አመት ከክለቡ ጋር እንደማይቀጥሉ በዛሬው ዕለት ይፋ ተደርጓል። አሰልጣኝ ዣቪ ሀርናንዴዝ የባርሴሎና የመጨረሻ ጨዋታቸውን እሁድ ከሲቪያ ጋር በሚደረግ መርሐ ግብር እንደሚመሩ ተገልጿል። ዣቪ ሀርናንዴዝ ባርሴሎናን በአሰልጣኝነት እየመሩ ባለፈው አመት የላሊጋውን ዋንጫ ማሳካት ችለዋል። …
ባርሴሎና አዲስ አሰልጣኝ ሊሾም ነው !

ከአሰልጣኝ ዣቪ ሀርናንዴዝ ጋር እንደሚለያይ ያሳወቀው የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና በምትካቸውም አዲስ አሰልጣኝ ለመሾም ከስምምነት መድረሱ ተገልጿል።

ባርሴሎና የቀድሞውን የጀርመን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ በሀላፊነት ለመሾም መቃረባቸው ተገልጿል።

አሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ ባርሴሎናን ለሁለት የውድድር አመታት ለማሰልጠን ፊርማቸውን እንደሚያኖሩ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ዩናይትድ አሰልጣኝ ኬራን ማክኬናን አነጋገሩ ! ማንችስተር ዩናይትዶች የኢፕስዊች ታውኑን አሰልጣኝ ኬራን ማክኬናን ተወካዮች አግኝተው ማነጋገራቸው ተገልጿል። ማንችስተር ዩናይትድ ከነገው የኤፌ ካፕ ፍፃሜ በኋላ ከአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ጋር የሚለያዩ ከሆነ አሰልጣኝ ኬራን ማክኬናን በተተኪነት ለመሾም ማነጋገራቸው ተገልጿል። አሰልጣኝ ኬራን ማክኬና በተጨማሪም ከአሰልጣኞቻቸው ጋር በተለያዩት በብራይተን…
ኤሪክ ቴንሀግ ከዩናይትድ ጋር ሊለያዩ ይችላሉ !

ማንችስተር ዩናይትድ ከነገው የእንግሊዝ ኤፌ ካፕ ፍፃሜ ጨዋታ በኋላ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግን ከሀላፊነት ለማሰናበት ከውሳኔ መድረሳቸው እየተገለፀ ይገኛል።

ማንችስተር ዩናይትድ የነገውን የፍፃሜ ጨዋታ ማሸነፍ ቢችሉም አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግን ከመሰናበት እንደማያድናቸው በመዘገብ ላይ ነው።

ቀያዮቹ ሴጣኖች ለመሾም በዝርዝራቸው ውስጥ የያዟቸው አሰልጣኞች ኬራን ማክኬና ፣ ቱሄል ፣ ፖቼቲኖ ፣ ቶማስ ፍራንክ እና ግራም ፖተር እንደሚገኙበት ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መቻል ከሻሸመኔ ከተማ ነጥብ ተጋራ !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር መቻል ከሻሸመኔ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የመቻልን ግቦች በረከት ደስታ እና ምንይሉ ወንድሙ ከመረብ ሲያሳርፉ ለሻሸመኔ ከተማ አብዱልቃድር ናስር እና ሙሉጌታ ወልደ ጊዮርጊስ አስቆጥረዋል።

መቻል ነጥብ መጣሉን ተከትሎ ከሊጉ መሪ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለውን የነጥብ ልዩነት ማጥበብ የሚችልበትን እድል ሳይጠቀም ቀርቷል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

2️⃣ መቻል :- 51 ነጥብ

1️⃣5️⃣ ሻሸመኔ ከተማ :- 14 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

አርብ - ፋሲል ከነማ ከ መቻል

እሁድ - ሻሸመኔ ከተማ ከ ኢትዮጵያ መድን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
🏆የዋንጫውን አሸናፊ ይገምቱ🏆

🔥 ማንቼስተሮቹ ለዚህ ዓመት ለመጨረሻ ጊዜ ለኤፍ ኤ ካፕ ዋንጫ ፍፃሜ ይገናኛሉ!

ቅዳሜ ፣ ግንቦት 17 ከሰዓት 11 ሰዓት ማን ሲቲ ከ ማን ዩናይትድ ጋር በዌንብሊ ለዋንጫው ይፋለማሉ!

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫንያሸነፈው ማን ሲቲ ሁለተኛ ዋንጫውን ያሸንፋል?

👉 ይህንን ደማቅ ፍልሚያ በSS Football 225 በጎጆ ፓኬጅ እና በSS Football 222 በሜዳ ለመከታተል ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ           

የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/eth2

#PremierLeagueOnDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvSelfServiceET
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
ኢኳቶሪያል ጊኒ በፊፋ ቅጣት ተጣለባት !

የኢኳቶሪያል ጊኒ ብሔራዊ ቡድን በመጀመሪያ ሁለት የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ብሔራዊ ቡድኑን ለመወከል ብቁ ያልሆነውን ኤምሊዮ ኑስ በማሰለፉ ምክንያት በፊፋ ቅጣት እንደተጣለበት ተገልጿል።

ፊፋ ኢኳቶሪያል ጊኒ በመጀመሪያ እና ሁለተኛ የምድብ የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ያስመዘገበቻቸውን ድሎች ለተቃራኒ ቡድን በፎርፌ እንዲሰጡ መወሰኑን አሳውቋል።

የ 2023 አፍሪካ ዋንጫ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ኤምሊዮ ኑስ በበኩሉ ለስድስት ወራት ከኢንተርናሽናል እግርኳስ መታገዱ ተገልጿል።

ስፔን ውስጥ የተወለደው ኤምሊዮ ኑስ ለኢኳቶሪያል ጊኒ ብሔራዊ ቡድን አርባ ሶስት ጨዋታዎች አድርጎ ሀያ ሶስት ግቦችን በማስቆጠር የምንግዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የሴርያ የአመቱ ምርጦች እነማን ይሆናሉ ? በኢንተር ሚላን አሸናፊነት የተጠናቀቀው የጣልያን ሴርያ የዘንድሮው የ2023/24 የውድድር አመት በየዘርፉ የአመቱ ምርጥ እጩዎች ይፋ ተደርገዋል። በዚህም መሰረት :- - የአመቱ ምርጥ አጥቂ እጩዎች :- ፓብሎ ዲባላ ፣ ራፋኤል ሊያኦ እና ቭላሆቪች - የአመቱ ምርጥ አማካይ :- ካልሀኖግሉ ፣ ኮፕሜነርስ እና ክርስቲያን ፑልሲች - የአመቱ ምርጥ ተከላካይ…
የጣልያን ሴርያ የአመቱ ምርጦች ታውቀዋል !

በኢንተር ሚላን አሸናፊነት የተጠናቀቀው የጣልያን ሴርያ የዘንድሮው የ2023/24 የውድድር አመት በየዘርፉ የአመቱ ምርጥ ተጨዋቾች ይፋ ተደርገዋል።

በዚህም መሰረት የአመቱ ምርጥ የፊት መስመር አጥቂ በመሆን የጁቬንቱሱ ተጨዋች ዱሳን ቭላሆቪች በአብላጫ ድምፅ መመረጥ ችሏል።

እንዲሁም የአመቱ ምርጥ አማካይ በመሆን የኢንተር ሚላኑ ሀካን ካልሀኖግሉ ተመርጧል።

በተጨማሪም የአመቱ ምርጥ ተከላካይ በመሆን የኢንተር ሚላኑ አሌሳንድሮ ባስቶኒ ምርጥ ግብ ጠባቂ የሞንዛው ሚሼል ዲ ግሪጎርዮ ተመርጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኢናኪ ዊሊያምስ የጠርሙስ ስብርባሪው ወጣለት !

ጋናዊው የአትሌቲክ ቢልባኦው የፊት መስመር ተጨዋች ኢናኪ ዊሊያምስ ከአመታት በፊት በእግሩ ውስጥ የገባ የተሰበረ የጠርሙስ ቁርጥራጭ እንደወጣለት ተገልጿል።

ተጨዋቹ ላለፉት ሁለት አመታት የጠርሙስ ቁርጥራጩ በውስጥ እግሩ ውስጥ እንዳለ ሲጫወት እንደነበር እና በዛሬው ዕለት በቀዶ ጥገና ህክምና እንደወጣለት ተነግሯል።

ይህንንም ተከትሎ ኢናኪ ዊሊያምስ የላሊጋው የመጨረሻ ሳምንት መርሐግብር እንደሚያመልጠው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EthiopianPL 🇪🇹

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ባሕር ዳር ከተማ ከወላይታ ድቻ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ባሕር ዳር ከተማ ያለፉትን አስራ ሁለት ጨዋታዎች አልተሸነፉም ሰባቱን ሲያሸንፉ በአምስቱ አቻ ተለያይተዋል።

ወላይታ ድቻ ከሶስት ተከታታይ ሽንፈት በኋላ ነጥብ ይዘው መውጣት ችለዋል።

በሊጉ ደረጃ ስንተኛ ናቸው ?

3️⃣ ባሕር ዳር ከተማ :- 45 ነጥብ

1️⃣3️⃣ ወላይታ ድቻ :- 29 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ?

ሐሙስ - ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ባሕር ዳር ከተማ

እሁድ - ወላይታ ድቻ ከ ሀድያ ሆሳዕና

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ካሴሚሮ ተጠባባቂ ሆኖ ሊጀምር ይችላል !

አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ማንችስተር ዩናይትድ ነገ ከማንችስተር ሲቲ ጋር በሚያደርገው የኤፌ ካፕ ፍፃሜ ጨዋታ ካሴሚሮን ተጠባባቂ ለማድረግ ማሰባቸው ተገልጿል።

ማንችስተር ዩናይትድ በሳምንቱ ውስጥ ለጨዋታው  ዝግጅት በሚያደርግበት ወቅት ካሴሚሮ ከቋሚ አሰላለፍ ውጪ ሆኖ ሲዘጋጅ እንደነበር ተነግሯል።

አሰልጣኙ በጨዋታው ከካሴሚሮ ይልቅ ሶፍያን አምራባትን የመጀመሪያ ተመራጭ አማካይ ለማድረግ በማሰብ ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

ሶፍያን አምራባት ከወራት በኋላ ወደ ቡድኑ ተመልሶ በተሰለፈባቸው ያለፉት ሶስት የሊግ ጨዋታዎች ክለቡ ስድስት ነጥቦች ሲሰበስብ ሶስት ጎሎች ተቆጥረውበታል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
Forwarded from HEY Online Market
Affordable Gaming PC

•HP Pavilion
•HP Victus

•HP Omen 15
•HP Omen 16

Contact Us
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
የዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዎች !

9:00 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ፋሲል ከነማ

11:00 ማንችስተር ሲቲ ከ ማንችስተር ዩናይትድ ( ኤፌ ካፕ ፍፃሜ )

12:00 ሲዳማ ቡና ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ

1:00 ጁቬንቱስ ከ ሞንዛ

3:00 ካይሰርስላውተርን ከ ባየር ሊቨርኩሰን ( የጀርመን ፖካል ፍፃሜ )

3:45 ኤሲ ሚላን ከ ሳለርኒታና

4:00 ሊዮን ከ ፒኤስጂ ( ፍፃሜ )

4:00 ሪያል ማድሪድ ከ ሪያል ቤቲስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ስለ ሲቲ አናስብም ጨዋታችንን ማሸነፍ አለብን "

አርጀንቲናዊው የማንችስተር ዩናይትድ የፊት መስመር ተጨዋች አሌሀንድሮ ጋርናቾ በዛሬው የፍፃሜ ጨዋታ ቡድናቸው ስለ ማንችስተር ሲቲ ጥሩነት እንደማይጨነቅ ተናግሯል።

" ማንችስተር ሲቲ አያስጨንቀንም ሄደን ጨዋታችንን ማሸነፍ ነው ያለብን ፣ ጨዋታው ለእኛ በጣም አስፈላጊ ነው ዋንጫውን ማሸነፍ እንፈልጋለን።" ሲል አሌሀንድሮ ጋርናቾ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቼልሲ ምን አይነት አሰልጣኝ መሾም ይፈልጋል ?

አሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖን ያሰናበተው የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በቀጣይ ተተኪ አሰልጣኝ ለመሾም በማፈላለግ ላይ ይገኛሉ።

ሰማያዊዎቹ በቀጣይ ለመሾም በዝርዝራቸው ውስጥ ከያዟቸው አሰልጣኞች መካከል አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ፣ ኬራን ማክኬና እና ቶማስ ፍራንክ ተጠቃሽ ናቸው።

ቼልሲ በቀጣይ የሚሾመው አዲስ አሰልጣኝ ማሟላት ያለበትን መስፈርቶች ማስቀመጣቸው ሲነገር

- ክለቡን በፍጥነት መላመድ የሚችል

- የአጨዋወት ባህሪው ኳስ ተቆጣጥሮ መጫወት ላይ የተመሰረተ

- ከአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ እና ፔፕ ጋርዲዮላ ጋር ለመፎካከር ዝግጁ የሆነ መሆን እንደሚጠበቅበት ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/27 21:31:52
Back to Top
HTML Embed Code: