Telegram Web Link
አያክስ በይፋ አዲስ አሰልጣኝ ሾመ !

የኔዘርላንዱ ክለብ አያክስ ጣልያናዊውን አሰልጣኝ ፍራንሴስኮ ፋርዮሊን የክለቡ ዋና አሰልጣኝ አድርገው በሀላፊነት መሾማቸውን ይፋ አድርገዋል።

የ 35ዓመቱ አሰልጣኝ ፍራንሴስኮ ፋርዮሊ አያክስን በአሰልጣኝነት የመሩ በክለቡ ታሪክ የመጀመሪያው ጣልያናዊ አሰልጣኝ መሆናቸው ተገልጿል።

አሰልጣኝ ፍራንሴስኮ ፋርዮሊ አያክስን እስከ 2027 ለማሰልጠን ፊርማቸውን ማኖራቸው ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሲቲ የግብ ጠባቂውን ውል አራዘመ !

በአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የሚመራው ማንችስተር ሲቲ የግብ ጠባቂያቸው ስኮት ካርሰንን ኮንትራት ለተጨማሪ አመት ማራዘማቸውን ይፋ አድርገዋል።

የ 38ዓመቱ እንግሊዛዊ ግብ ጠባቂ ስኮት ካርሰን በማንችስተር ሲቲ ቤት እስከ 2025 የሚያቆየውን ውል መፈረሙ ተገልጿል።

" ከዚህ ድንቅ ክለብ ጋር ተጨማሪ አመት ለማሳለፍ ጓጉቻለሁ በየቀኑ ጠንክሬ በመስራት ከጋርዲዮላ አንድ ነገር መማር እፈልጋለሁ፣ ተጨማሪ ዋንጫ ለማሸነፍ ግብ ጠባቂዎችን እንደማግዝ ተስፋ አደርጋለሁ።"ሲል ስኮት ካርሰን ተናግሯል።

ግብ ጠባቂው ማንችስተር ሲቲን ከአምስት አመታት በፊት ከተቀላቀለ ወዲህ ተሰልፎ መጫወት የቻለው በሁለት ጨዋታዎች ብቻ መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አሰልጣኝ ኬራን ማክኬና ወዴት ሊያመሩ ይችላሉ ?

ከአሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲዘርቢ ጋር የተለያየው ብራይተን ኢፕስዊች ታውንን ወደ እንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ማሳደግ የቻሉትን አሰልጣኝ ኬራን ማክኬናን ለመሾም ጥያቄ ማቅረባቸው ተገልጿል።

በቼልሲ አሰልጣኝ ዝርዝር ውስጥ የሚገኙት አሰልጣኝ ኬራን ማክኬና አሁን ላይ የሰማያዊዎቹን የመጨረሻ ውሳኔ መጠበቅ እንደሚፈልጉ ተነግሯል።

አሰልጣኙ በተጨማሪም ከኢፕስዊች ታውን ውላቸውን እንዲያራዝሙ አዲስ ኮንትራት እንደቀረበላቸው ተዘግቧል።

የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ ምክትል አሰልጣኝ የነበሩት ኬራን ማክኬና ኢፕስዊች ታውን ከሊግ አንድ ወደ ሻምፒዮን ሺፑ ባደገበት አመት ወደ ፕርሚየር ሊግ ማሳደግ የቻሉ ናቸው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
Zamalek - Future FC
Besiktas - Trabzonspor
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
Forwarded from HEY Online Market
Affordable Gaming PC

•HP Pavilion
•HP Victus

•HP Omen 15
•HP Omen 16

Contact Us
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
ኦሊቬ ጅሩ ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ ሊያገል ነው !

የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን የምንግዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪው ኦሊቬ ጅሩ ከዘንድሮው የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር በኋላ ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ እንደሚያገል አስታውቋል።

የ 37ዓመቱ የቀድሞ አርሰናል ፣ ቼልሲ እና ኤሲ ሚላን ተጨዋች ኦሊቬ ጅሩ ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ ለማግለል የወሰነው ለወጣት ተጨዋቾች እድል ለመስጠት እንደሆነ ገልጿል።

በሀምሳ ሰባት ግቦች የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን የምንግዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ የሆነው ኦሊቬ ጅሩ ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር የአለም ዋንጫን ማሳካት ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዋይን ሩኒ ወደ አሰልጣኝነት ሊመለስ ነው !

የእንግሊዝ ሻምፒየን ሺፑ ክለብ ፕለይ ማውዝ እንግሊዛዊውን የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋች ዋይን ሩኒ በአሰልጣኝነት ለመሾም በማሰብ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ዋይን ሩኒ ከወራት በፊት በርሚንግሃም ሲቲን ከተረከበ ሰማንያ ሶስት ቀናት በኋላ ከክለቡ ከተሰናበተ በኋላ ያለ ሀላፊነት ይገኛል ።

የሻምፒየን ሺፑ ክለብ ፕለይ ማውዝ በዚህ አመት ወደ ታችኛው ሊግ ለመውረድ ተቃርቦ በመጨረሻ ሰዓት በሻምፒዮን ሺፑ መቆየቱን አረጋግጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የሱዳን ክለቦች በሞሪታንያ ሊግ ሊወዳደሩ ነው !

የሱዳን ክለቦች አል ሂላል እና አል ሜሪክ ከሚቀጥለው የውድድር አመት ጀምሮ በምሪታኒያ ሊግ እንዲወዳደሩ የሞሪታኒያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከስምምነት መደረሱን አስታውቋል።

የሞሪታኒያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ሁለቱ ክለቦች በሀገሪቱ ሊግ እና በቀጣይ በአፍሪካ መድረክ ሲወዳደሩ የመኖሪያ እና የሀገር ውስጥ ትራንስፖርት እንዲሁም ሌሎች ወጪዎችን እንደሚሸፍንላቸው ይፋ አድርጓል።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ መሰረት የመጀመሪያው የሞሪታኒያ ክለብ ሞሪታኒያን በካፍ ውድድሮች ሲወክል የመጀመሪያው የሱዳን ክለብ ደግሞ ሱዳንን እንዲወክል እንደሚደረግ ተገልጿል።

የሀገሪቱ እግርኳስ ፌዴሬሽን ውሳኔውን ለአፍሪካ እግርኳስ የበላይ ካፍ ማሳወቁን እና ፍቃድ እስኪያገኝ በመጠባበቅ ላይ መሆኑን ገልጿል።

ክለቦቹ በሞሪታኒያ ሊግ ለመወዳደር የሚፈልጉት ሱዳን ውስጥ ባለው የሰላም እጦት ምክንያት የእግርኳስ ውድድሮች መታገዳቸውን ተከትሎ እንደሆነ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኬይለር ናቫስ ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ አገለለ !

ከፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ ጋር የተለያየው ግብ ጠባቂው ኬይለር ናቫሳ ከኮስታሪካ ብሔራዊ ቡድን ራሱን ማግለሉን በይፋ አሳውቋል።

የቀድሞ የሪያል ማድሪድ ግብ ጠባቂ ኬይለር ናቫስ ለኮስታሪካ ብሔራዊ ቡድን በአንድ መቶ አስራ አራት ጨዋታዎች ተሰልፎ መጫወት ችሏል።

አስራ ስድስት አመታትን ለብሔራዊ ቡድኑ ግልጋሎት የሰጠው ኬይለር ናቫስ በሶስት የአለም ዋንጫ ውድድሮች መሳተፍም ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የአሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊ የኤሲ ሚላን ቆይታ ? የጣልያን ሴርያው ክለብ ኤሲ ሚላን በውድድር አመቱ መጨረሻ አሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊን ከሀላፊነታቸው ለማሰናበት በወሰነው ውሳኔ መፅናቱ ተገልጿል። አሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊ በቅርቡ ስለወደፊት ቆይታቸው ተጠይቀው " በውድድር አመቱ መጨረሻ ከክለቡ ጋር እነጋገራለሁ አሁን አስተያየት መስጠት አልፈልግም።" ብለው ነበር። ኤሲ ሚላን አሁን ላይ አሰልጣኙን የማሰናበት…
ኤሲ ሚላን ከአሰልጣኙ ጋር ተለያየ !

የጣልያን ሴርያው ክለብ ኤሲ ሚላን በውድድር አመቱ መጨረሻ ከአሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊ ጋር ለመለያየት መወሰኑን በይፋ አስታውቋል።

አሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊ ኤሲ ሚላን ነገ በስታዲዮ ጁሴፔ ሜዛ ከሳለርኒታና ጋር በሚያደርገው የሊግ የመጨረሻ ሳምንት መርሐ ግብር ክለቡን ይሰናበታሉ።

ከ 2019 ጀምሮ ኤሲ ሚላንን በሀላፊነት የመሩት አሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊ ክለቡን የሴርያ ዋንጫ አሸናፊ በማድረግ ወደ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድርም መመለስ ችለዋል።

ኤሲ ሚላን በቀጣይ የአሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊ ተተኪ በማድረግ ፖርቹጋላዊውን የሊል አሰልጣኝ ፓውሎ ፎንሴካን ይሾማል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
በርካታ የጣልያን ክለቦች በአውሮፓ መድረክ ይሳተፋሉ !

በሚቀጥለው የውድድር አመት የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር በሚያዘጋጃቸው ውድድሮች ላይ ዘጠኝ የጣልያን ሴርያ ክለቦች ተሳታፊ እንደሚሆኑ ተገልጿል።

በሴርያው የሻምፒየንስ ሊግ ቦታን የያዘው አታላንታ የዩሮፓ ሊግ ዋንጫ ማሸነፉን ተከትሎ አንድ ተጨማሪ የሴርያ ክለብ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ እንደሚሳተፍ ተነግሯል።

ይህንንም ተከትሎ በሚቀጥለው የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር #ስድስት የጣልያን ሴርያ ክለቦች ተሳታፊ የሚሆኑ ይሆናል።

በወቅታዊ ደረጃ በአውሮፓ መድረክ እነማን ሊሳተፉ ይችላሉ ?

- ሻምፒየንስ ሊግ :- ኢንተር ሚላን ፣ ኤሲ ሚላን ፣ ቦሎኛ ፣ ጁቬንቱስ ፣ አታላንታ እና ሮማ

- ዩሮፓ ሊግ :- ላዝዮ እና ፊዮሬንቲና

- ኮንፈረንስ ሊግ :- ቶሪኖ ( ባለበት ደረጃ ካጠናቀቀ )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ፓርቴ በአርሰናል መቀጠል እንደሚፈልግ ገለጸ ! ጋናዊው የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የመሐል ሜዳ ተጨዋች ቶማስ ፓርቴ በአርሰናል ቤት መጫወት መቀጠል እንደሚፈልግ ተናግሯል። " ስለእኔ የወደፊት ቆይታ ብዙ እንደሚባል አውቃለሁ ነገርግን እኔ እዚህ በመሆኔ ደስተኛ ነኝ ፣ አርሰናልን እወደዋለሁ እዚህ መጫወት መቀጠል እፈልጋለሁ።"ሲል ቶማስ ፓርቴ ተናግሯል። @tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቶማስ ፓርቴ ከአርሰናል ጋር ሊለያይ ነው !

ጋናዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ቶማስ ፓርቴ ከሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ጋር ሊለያይ እንደሆነ ተገልጿል።

ተጨዋቹ በቅርቡ በሰጠው አስተያየት በአርሰናል ቤት ደስተኛ እንደሆነ እና በክለቡ መጫወት መቀጠል እንደሚፈልግ ተናግሮ ነበር።

መድፈኞቹ አዲስ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ለማስፈረም የተለያዩ አማራጮችን መመልከታቸው የተገለፀ ሲሆን በቀጣይ እንቅስቃሴ እንደሚጀምሩ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አሰልጣኝ ኬራን ማክኬና ወዴት ሊያመሩ ይችላሉ ? ከአሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲዘርቢ ጋር የተለያየው ብራይተን ኢፕስዊች ታውንን ወደ እንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ማሳደግ የቻሉትን አሰልጣኝ ኬራን ማክኬናን ለመሾም ጥያቄ ማቅረባቸው ተገልጿል። በቼልሲ አሰልጣኝ ዝርዝር ውስጥ የሚገኙት አሰልጣኝ ኬራን ማክኬና አሁን ላይ የሰማያዊዎቹን የመጨረሻ ውሳኔ መጠበቅ እንደሚፈልጉ ተነግሯል። አሰልጣኙ በተጨማሪም ከኢፕስዊች…
ዩናይትድ አሰልጣኝ ኬራን ማክኬናን አነጋገሩ !

ማንችስተር ዩናይትዶች የኢፕስዊች ታውኑን አሰልጣኝ ኬራን ማክኬናን ተወካዮች አግኝተው ማነጋገራቸው ተገልጿል።

ማንችስተር ዩናይትድ ከነገው የኤፌ ካፕ ፍፃሜ በኋላ ከአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ጋር የሚለያዩ ከሆነ አሰልጣኝ ኬራን ማክኬናን በተተኪነት ለመሾም ማነጋገራቸው ተገልጿል።

አሰልጣኝ ኬራን ማክኬና በተጨማሪም ከአሰልጣኞቻቸው ጋር በተለያዩት በብራይተን እና ቼልሲ እየተፈለጉ እንደሚገኙ ይታወቃል።

አሰልጣኙ ከዚህ በፊት በማንችስተር ዩናይትድ ቤት በምክትል አሰልጣኝነት ማገልገላቸው አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ብሩኖ ፈርናንዴዝ ለደጋፊው ጥሪ አቀረበ !

የማንችስተር ዩናይትዱ አምበል ብሩኖ ፈርናንዴዝ በመላው አለም የሚገኙ የክለቡ ደጋፊዎች በነገው የኤፌ ካፕ የፍፃሜ ጨዋታ ከቡድኑ ጎን እንዲቆሙ ጠይቋል።

በመላው አለም ለምትገኙ የማንችስተር ዩናይትድ ደጋፊዎች ከፍፃሜው በፊት ልናገራቸው የምፈልጋቸው ቃላቶች አሉኝ በማለት ንግግሩን የጀመረው ብሩኖ ፈርናንዴዝ " ለእናንተ ቀላል አመት እንዳልነበረ አውቃለሁ።

የሚገባችሁ ደረጃ ላይ አልደረስንም ፣ ያደረጋችሁልንን ድጋፍ እንደ አምበል ከማንም በላይ ይሰማኛል ፣ ነገርግን አሁን ወደ ዌምብሌይ እናመራለን ለአንድ የመጨረሻ ጊዜ ከጎናችን ቁሙ።"ሲል ጠይቋል።

" በኦልድትራፎርድ ስታዲየም መጫወት በአለም ላይ ካለ ከየትኛውም ቦታ ጋር አወዳድሬ አላውቅም ማንችስተር ዩናይትድን መልቀቅ አልፈልግም ሁልጊዜም ብቸኛ ህልሜ ነው።" ፈርናንዴዝ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የሴርያ የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ ታውቋል !

በኢንተር ሚላን አሸናፊነት የተጠናቀቀው የጣሊያን ሴርያ የ2023/24 የውድድር ዘመን የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ ይፋ ተደርጓል።

በዚህ መሰረት ከኢንተር ሚላን ጋር የሊጉን ዋንጫ ማሳካት የቻሉት አሰልጣኝ ሲሞን ኢንዛጊ የጣልያን ሴርያ የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ በመሆን መመረጥ ችለዋል።

አሰልጣኝ ሲሞን ኢንዛጊ ኢንተር ሚላንን እየመሩ እስካሁን ካደረጓቸው ሰላሳ ሰባት ጨዋታዎች ሀያ ዘጠኙን ሲያሸንፉ በስድስቱ አቻ ተለያይተው በሁለቱ ተሸንፈዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ማድሪድ ተጨዋቹ ለፍፃሜ ላይደርስ ይችላል ! ለዘንድሮው የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ ማለፋቸውን ያረጋገጡት ሎስ ብላንኮዎቹ ወሳኝ ተጨዋቻቸው ለፍፃሜ መድረሱ አጠራጣሪ መሆኑ ተገልጿል። ፈረንሳዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኦርሊየን ቹዋሜኒ በትላንት ምሽቱ የባየር ሙኒክ ጨዋታ ያጋጠመው ጉዳት ከሀያ ሶስት ቀናት በኋላ ለሚደረገው የፍፃሜ ጨዋታ መድረሱን አጠራጣሪ እንዳደረገው ተነግሯል። ሎስ ብላንኮዎቹ…
ማድሪድ ተጨዋቹ ከሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ውጪ ሆነ !

የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ተፋላሚው ሪያል ማድሪድ ወሳኝ የመሐል ሜዳ ተጨዋቹ በጉዳት ምክንያት ለፍፃሜው እንደማይደርስ ተረጋግጧል።

ፈረንሳዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኦርሊየን ቹዋሜኒ ቀጣይ ሳምንት ለሚደረገው የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ እንደማይደርስ አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ አረጋግጠዋል።

ሪያል ማድሪድ ከቦርስያ ዶርትመንድ ጋር የሚያደርጉት የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ ቀጣይ ሳምንት ቅዳሜ ግንቦት 24/2016 ዓ.ም በዌምብሌይ ስታዲየም ይደረጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Tecno #Camon30Pro5G

ቴክኖ ሞባይል በአይነቱ የተራቀቀውን አዲሱን Tecno Camon 30 pro 5G ምርጫዎ ያድርጉ ሲል ይጋብዛል!

#Camon30Et #Camon30pro5GEt #Camon30 #Camon30Pro5G #TecnoEt
Forwarded from WANAW SPORT
📢 #ለቸኮሉ መፍትሔ ከ #ዋናው!

👉🏾#ዋናው ስፖርትን ለስፖርት አልባሳት ፈጣን አቅርቦት ችግርዎ ሁነኛ መፍትሔን እናስታውስዎ፣ አስቀድመው የተዘጋጁ ማልያዎች!

👉🏾 እርስዎ ብቻ አስቀድመን ካዘጋጀናቸው ዲዛይኖች የፈለጉትን በመምረጥ ትጥቅዎን ይውሰዱ!

🚀 ዛሬውኑ #ይምጡ፣ ቀላል አማራጩን ይጠቀሙ!

📍አድራሻችን:- ገርጂ መብራት ሃይል የካቲት ወረቀት ፊትለፊት፣ አለም ገብሬ ህንፃ፣ 2ተኛ ፎቅ።

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 0901138283፣ 0910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ወይም በቴሌግራም ቦት @WANAWSbot በኩል ይዘዙን።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
TIKVAH-SPORT
የአሰልጣኝ ዣቪ የባርሴሎና ቆይታ ? ስፔናዊው የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ዋና አሰልጣኝ ዣቪ ከክለቡ ሊሰናበቱ እንደሚችሉ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን በመዘገብ ላይ ናቸው። አሰልጣኝ ዣቪ ከቀናት በፊት ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ የሰጡት አስተያየት ከባርሴሎናው ፕሬዝዳንት ሁዋን ላፖርታ ጋር አለመግባባት ውስጥ ሳይከታቸው እንዳልቀረ ተዘግቧል። ዣቪ ከቀናት በፊት ቡድናቸው ከሌሎች ክለቦች ጋር ለመፎካከር…
ባርሴሎና አሰልጣኝ ዣቪን አሰናበተ !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ስፔናዊውን አሰልጣኝ ዣቪ ሀርናንዴዝ በዛሬው ዕለት ከሀላፊነታቸው ማሰናበቱን ይፋ አድርጓል።

የባርሴሎናው ፕሬዝዳንት ሁዋን ላፖርታ በዛሬው እለት ከአሰልጣኝ ዣቪ ሀርናንዴዝ ጋር እንደተነጋገሩ እና ውሳኔውን እንዳሳወቁ ተዘግቧል።

አሰልጣኝ ዣቪ ከወራት በፊት በአመቱ መጨረሻ ባርሴሎናን እንደሚለቁ አሳውቀው የነበረ ቢሆንም በቅርቡ ክለቡ ሀሳባቸውን አስቀይሯቸው ለመቆየት ወስነው እንደነበር አይዘነጋም።

በቀጣይ ጀርመናዊው አሰልጣኝ ሀንሲ ፊሊክ ባርሴሎናን በሀላፊነት ይረከባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/11/15 10:45:21
Back to Top
HTML Embed Code: