Telegram Web Link
ጣልያን ስብስቧን አሳውቃለች !

የጣልያን ብሔራዊ ቡድን ለቀጣዩ የ2024 የጀርመን አውሮፓ ዋንጫ ውድድር የመጀመሪያ ሰላሳ የቡድን ስብስቡን አሳውቋል።

ብሔራዊ ቡድኑ ከስብስቡ ውስጥ አራት ተጨዋቾችን ቀንሶ ወደ አውሮፓ ዋንጫው ያመራል ተብሎ ይጠበቃል።

በአሰልጣኝ ሉቺያኖ ስፓሌቲ የሚመራው ብሔራዊ ቡድኑ ከአውሮፓ ዋንጫው በፊት ከቱርክ እና ቦስኒያ ጋር የወዳጅነት ጨዋታዎች ያደርጋል።

ሙሉ የቡድን ስብስቡ ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ድሬዳዋ ከተማ ድል አድርጓል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ድሬዳዋ ከተማ ከወልቂጤ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የድሬዳዋ ከተማን የማሸነፊያ ግቦች ካርሎስ ዳምጠው 2x እና ሱራፌል ጌታቸው ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

የድሬዳዋ ከተማው የፊት መስመር ተጨዋች ካርሎስ ዳምጠው ሰባተኛ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ወልቂጤ ከተማ ያለፉትን ስድስት የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች ሽንፈት አስተናግደዋል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

8️⃣ ድሬዳዋ ከተማ :- 37 ነጥብ

1️⃣4️⃣ ወልቂጤ ከተማ :- 16 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

ሐሙስ - ወልቂጤ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና

አርብ - ድሬዳዋ ከተማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የዩናይትድ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ታውቋል !

ማንችስተር ዩናይትድ የ 2023/24 የውድድር አመት የአመቱን ምርጥ ተጨዋች ይፋ አድርገዋል።

በዚህም መሰረት ፖርቹጋላዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ብሩኖ ፈርናንዴዝ የማንችስተር ዩናይትድ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች በመሆን በአብላጫ ድምፅ መመረጥ ችሏል።

ብሩኖ ፈርናዴዝ አርባ በመቶ የሚሆነውን ድምፅ በማግኘት ማሸነፉ ሲገለፅ ዲያጎ ዳሎት ሁለተኛ ፣ ኮቢ ማይኖ ሶስተኛ እንዲሁም አሌሀንድሮ ጋርናቾ አራተኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቃቸው ታውቋል።

ብሩኖ ፈርናንዴዝ ለሶስተኛ ጊዜ የማንችስተር ዩናይትድ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ሽልማትን ሲያሸንፍ ከእሱ በላይ በዙ ግዜ ያሸነፉት ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና ዴቪድ ዴህያ አራት ጊዜ መሆኑ ተገልጿል።

በተጨማሪም ዲያጎ ዳሎት የተጨዋቾች የአመቱ ምርጥ ተጨዋች በመሆን በማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋቾች መመረጡ ይፋ ተደርጓል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
"ስለ ቤቲካ ማን መረጃ ይነግራችኋል?
ልብ በሉ እንግዲህ… የቤቲካን የማኅበራዊ ሚዲያ ገፆች ስትፈልጉ እነዚህን አድራሻዎች ተጠቀሙ FB/Messanger - https://m.me/BetikaET Telegram - https://www.tg-me.com/betikaeth Email - [email protected]
ቤቲካ በሁሉም ዋና ዋና የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ ይገኛል።
ወደ 8692 ነጻ የስልክ መስመር ይደውሉልን!
የአሸናፊዎች ቤት የሆነው ቤቲካ ሁሌም ጥያቄዎችዎን ለማስተናገድ ዝግጁ ነው"
TIKVAH-SPORT
የማድሪድ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል በአሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ የሚሰለጥነው የላሊጋው መሪ ሪያል ማድሪድ የወርሀ ሚያዚያ የወሩ ምርጥ ተጨዋች #አምስት እጩዎችን ይፋ አድርገዋል። በዚህም መሰረት ሮድሪጎ ፣ ቪንሰስ ጁኒየር ፣ ዳኒ ካርቫል ፣ ሩዲገር ፣ እና ቫልቬርዴ የወርሀ ሚያዝያ የሪያል ማድሪድ ወሩ ምርጥ ተጨዋች እጩ ሆነው መቅረብ ችለዋል። @tikvahethsport     @kidusyoftahe
የማድሪድ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ታውቋል !

በአሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ የሚመራው የስፔን ላሊጋ አሸናፊው ሪያል ማድሪድ የወርሀ ሚያዝያ የወሩ ምርጥ ተጨዋቻቸውን ይፋ አድርገዋል።

በዚህም መሰረት ጀርመናዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች አንቶኒዮ ሩዲገር የወርሀ ሚያዝያ የሪያል ማድሪድ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ተብሎ መመረጥ ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሉካስ ፓኩዌታ ክስ ተከፈተበት !

የዌስትሀም ዩናይትድ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሉካስ ፓኩዌታ ከህገ-ወጥ የስፖርት ውርርድ ጋር በተያያዘ ከእንግሊዝ እግርኳስ ማህበር ክስ እንደቀረበበት ተገልጿል።

ተጨዋቹ በሚቀጥሉት አስር ቀናት ውስጥ ንፁህ መሆኑን ለእንግሊዝ እግርኳስ ማህበር ማረጋገጥ ካልቻለ ቅጣት እንደሚጣልበት ተነግሯል።

በማንችስተር ሲቲ የሚፈለገው ሉካስ ፓኩዌታ ባለፈው ክረምት ሲቲን ለመቀላቀል ተቃርቦ የእንግሊዝ ኤፍኤ ከዚሁ ጋር የተያያዘ ምርመራ መክፈቱን ተከትሎ ዝውውሩ መቋረጡ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዩናይትድ የተጫዋቹን ግልጋሎት አያገኝም !

ማንችስተር ዩናይትድ በቅዳሜው የእንግሊዝ ኤፌ ካፕ ፍፃሜ የወሳኝ ተጫዋቹን ግልጋሎት እንደማያገኝ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ አረጋግጠዋል።

በጨዋታው እንግሊዛዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሀሪ ማጓየር በጉዳት ምክንያት እንደማይደርስ አሰልጣኙ ገልጸዋል።

ሜሰን ማውንት ፣ ቪክቶር ሊንድሎፍ እና አንቶኒ ማርሻል በበኩላቸው ለጨዋታው ዝግጁ መሆናቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ወደዚህ የመጣሁት ዋንጫ ለማሸነፍ ነው " ቴንሀግ

የማንችስተር ዩናይትድ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ቡድናቸው ቅዳሜ ከማንችስተር ሲቲ ጋር ከሚያደርገው የኤፌ ካፕ ፍፃሜ ጨዋታ በፊት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ምን አሉ ?

- " ወደዚህ የመጣሁት ዋንጫ ለማሸነፍ ነው ቅዳሜ ደግሞ የምናሸንፍበት እድል አለን እንደ ቡድን ለፍፃሜ መድረስ ይገባናል ዋንጫውን ማሸነፍ እንፈልጋለን።

- ስለወደፊት ቆይታዬ ማውራት አልፈልግም ትኩረት የማደርገው ስራዬ ላይ ነው የቅዳሜውን ፍፃሜ ማሸነፍ እና የጀመርነውን እቅድ መቀጠል።

- ሁሉም ነገር ዋንጫ ስለማሸነፍ ነው ቅዳሜ የማሸነፍ ትልቅ እድል አለን ማንችስተር ዩናይትድ ባለፉት አስር አመታት ብዙ ዋንጫ አላሸነፈም ነገርግን እኛ በሁለት አመት ሁለት ዋንጫ የማሸነፍ እድል አለን።

- ስለቀጣዩ ክረምት የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት በማሰብ ላይ ነኝ ነገርግን በዚህ ሰዓት ሙሉ ትኩረታችንን ማድረግ የምንፈልገው ፍፃሜው ላይ ነው።"ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኢትዮጵያ መድን በአሸናፊነቱ ቀጥሏል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ መድን ከአዳማ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 4ለ1 በሆነ ሰፊ ውጤት በማሸነፍ ደረጃቸውን ማሻሻል ችለዋል።

የኢትዮጵያ መድንንን የማሸነፊያ ግቦች አቡበከር ሳኒ ፣ ሀይደር ሸረፋ ፣ አለን ካይዋ እና አብዲሳ ጀማል ሲያስቆጥሩ ለአዳማ ከተማ ጀሚል ያዕቆብ ከመረብ አሳርፏል።

ያለፉትን ዘጠኝ ጨዋታዎች ያልተሸነፈው ኢትዮጵያ መድን ስድስተኛ ተከታታይ ድሉን ማስመዝገብ ችሏል።

ኢትዮጵያ መድን ባለፉት ስድስት ጨዋታዎች አስራ ሰባት ግቦችን በተጋጣሚ መረብ ላይ ሲያስቆጥር የተቆጠረበት ሁለት ግብ ብቻ ነው

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

5️⃣ አዳማ ከተማ :- 41 ነጥብ

1️⃣0️⃣ ኢትዮጵያ መድን :- 34 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

እሁድ - ሻሸመኔ ከተማ ከ ኢትዮጵያ መድን

ቅዳሜ - ሀዋሳ ከተማ ከ አዳማ ከተማ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማድሪድ በሜዳው የፍፃሜ ጨዋታውን ያስመለክታል !

ሪያል ማድሪድ ከዶርትመንድ ጋር የሚያደርገውን የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ ወደ ለንደን ተጉዘው መመልከት ላልቻሉ ደጋፊዎች በሳንቲያጎ በርናቦ ስታዲየም እንዲመለከቱ ማዘጋጀቱ ተገልጿል።

ክለቡ ሳንቲያጎ በርናቦ ስታዲየም ሜዳ ላይ ግዙፍ የጨዋታ መመልከቻ ስክሪኖችን በማዘጋጀት ለደጋፊዎቹ ክፍት እንደሚያደርግ አሳውቋል።

ጨዋታውን በስታዲየሙ ተገኝቶ ለመከታተል የቲኬቶች ዋጋ ለህዝብ በ15 ዩሮ ከዛሬ ጀምሮ ለሽያጭ እንደሚቀርቡ ተዘግቧል።

ጨዋታውን ለመመልከት እስከ 80,000 የሚደርሱ የሪያል ማድሪድ ደጋፊዎች በስታዲየሙ ሊገኙ እንደሚችሉ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አያክስ በይፋ አዲስ አሰልጣኝ ሾመ !

የኔዘርላንዱ ክለብ አያክስ ጣልያናዊውን አሰልጣኝ ፍራንሴስኮ ፋርዮሊን የክለቡ ዋና አሰልጣኝ አድርገው በሀላፊነት መሾማቸውን ይፋ አድርገዋል።

የ 35ዓመቱ አሰልጣኝ ፍራንሴስኮ ፋርዮሊ አያክስን በአሰልጣኝነት የመሩ በክለቡ ታሪክ የመጀመሪያው ጣልያናዊ አሰልጣኝ መሆናቸው ተገልጿል።

አሰልጣኝ ፍራንሴስኮ ፋርዮሊ አያክስን እስከ 2027 ለማሰልጠን ፊርማቸውን ማኖራቸው ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሲቲ የግብ ጠባቂውን ውል አራዘመ !

በአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የሚመራው ማንችስተር ሲቲ የግብ ጠባቂያቸው ስኮት ካርሰንን ኮንትራት ለተጨማሪ አመት ማራዘማቸውን ይፋ አድርገዋል።

የ 38ዓመቱ እንግሊዛዊ ግብ ጠባቂ ስኮት ካርሰን በማንችስተር ሲቲ ቤት እስከ 2025 የሚያቆየውን ውል መፈረሙ ተገልጿል።

" ከዚህ ድንቅ ክለብ ጋር ተጨማሪ አመት ለማሳለፍ ጓጉቻለሁ በየቀኑ ጠንክሬ በመስራት ከጋርዲዮላ አንድ ነገር መማር እፈልጋለሁ፣ ተጨማሪ ዋንጫ ለማሸነፍ ግብ ጠባቂዎችን እንደማግዝ ተስፋ አደርጋለሁ።"ሲል ስኮት ካርሰን ተናግሯል።

ግብ ጠባቂው ማንችስተር ሲቲን ከአምስት አመታት በፊት ከተቀላቀለ ወዲህ ተሰልፎ መጫወት የቻለው በሁለት ጨዋታዎች ብቻ መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አሰልጣኝ ኬራን ማክኬና ወዴት ሊያመሩ ይችላሉ ?

ከአሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲዘርቢ ጋር የተለያየው ብራይተን ኢፕስዊች ታውንን ወደ እንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ማሳደግ የቻሉትን አሰልጣኝ ኬራን ማክኬናን ለመሾም ጥያቄ ማቅረባቸው ተገልጿል።

በቼልሲ አሰልጣኝ ዝርዝር ውስጥ የሚገኙት አሰልጣኝ ኬራን ማክኬና አሁን ላይ የሰማያዊዎቹን የመጨረሻ ውሳኔ መጠበቅ እንደሚፈልጉ ተነግሯል።

አሰልጣኙ በተጨማሪም ከኢፕስዊች ታውን ውላቸውን እንዲያራዝሙ አዲስ ኮንትራት እንደቀረበላቸው ተዘግቧል።

የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ ምክትል አሰልጣኝ የነበሩት ኬራን ማክኬና ኢፕስዊች ታውን ከሊግ አንድ ወደ ሻምፒዮን ሺፑ ባደገበት አመት ወደ ፕርሚየር ሊግ ማሳደግ የቻሉ ናቸው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
Zamalek - Future FC
Besiktas - Trabzonspor
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
Forwarded from HEY Online Market
Affordable Gaming PC

•HP Pavilion
•HP Victus

•HP Omen 15
•HP Omen 16

Contact Us
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
ኦሊቬ ጅሩ ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ ሊያገል ነው !

የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን የምንግዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪው ኦሊቬ ጅሩ ከዘንድሮው የአውሮፓ ዋንጫ ውድድር በኋላ ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ እንደሚያገል አስታውቋል።

የ 37ዓመቱ የቀድሞ አርሰናል ፣ ቼልሲ እና ኤሲ ሚላን ተጨዋች ኦሊቬ ጅሩ ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ ለማግለል የወሰነው ለወጣት ተጨዋቾች እድል ለመስጠት እንደሆነ ገልጿል።

በሀምሳ ሰባት ግቦች የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን የምንግዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ የሆነው ኦሊቬ ጅሩ ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር የአለም ዋንጫን ማሳካት ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዋይን ሩኒ ወደ አሰልጣኝነት ሊመለስ ነው !

የእንግሊዝ ሻምፒየን ሺፑ ክለብ ፕለይ ማውዝ እንግሊዛዊውን የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋች ዋይን ሩኒ በአሰልጣኝነት ለመሾም በማሰብ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ዋይን ሩኒ ከወራት በፊት በርሚንግሃም ሲቲን ከተረከበ ሰማንያ ሶስት ቀናት በኋላ ከክለቡ ከተሰናበተ በኋላ ያለ ሀላፊነት ይገኛል ።

የሻምፒየን ሺፑ ክለብ ፕለይ ማውዝ በዚህ አመት ወደ ታችኛው ሊግ ለመውረድ ተቃርቦ በመጨረሻ ሰዓት በሻምፒዮን ሺፑ መቆየቱን አረጋግጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የሱዳን ክለቦች በሞሪታንያ ሊግ ሊወዳደሩ ነው !

የሱዳን ክለቦች አል ሂላል እና አል ሜሪክ ከሚቀጥለው የውድድር አመት ጀምሮ በምሪታኒያ ሊግ እንዲወዳደሩ የሞሪታኒያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከስምምነት መደረሱን አስታውቋል።

የሞሪታኒያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ሁለቱ ክለቦች በሀገሪቱ ሊግ እና በቀጣይ በአፍሪካ መድረክ ሲወዳደሩ የመኖሪያ እና የሀገር ውስጥ ትራንስፖርት እንዲሁም ሌሎች ወጪዎችን እንደሚሸፍንላቸው ይፋ አድርጓል።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ መሰረት የመጀመሪያው የሞሪታኒያ ክለብ ሞሪታኒያን በካፍ ውድድሮች ሲወክል የመጀመሪያው የሱዳን ክለብ ደግሞ ሱዳንን እንዲወክል እንደሚደረግ ተገልጿል።

የሀገሪቱ እግርኳስ ፌዴሬሽን ውሳኔውን ለአፍሪካ እግርኳስ የበላይ ካፍ ማሳወቁን እና ፍቃድ እስኪያገኝ በመጠባበቅ ላይ መሆኑን ገልጿል።

ክለቦቹ በሞሪታኒያ ሊግ ለመወዳደር የሚፈልጉት ሱዳን ውስጥ ባለው የሰላም እጦት ምክንያት የእግርኳስ ውድድሮች መታገዳቸውን ተከትሎ እንደሆነ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኬይለር ናቫስ ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ አገለለ !

ከፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ ጋር የተለያየው ግብ ጠባቂው ኬይለር ናቫሳ ከኮስታሪካ ብሔራዊ ቡድን ራሱን ማግለሉን በይፋ አሳውቋል።

የቀድሞ የሪያል ማድሪድ ግብ ጠባቂ ኬይለር ናቫስ ለኮስታሪካ ብሔራዊ ቡድን በአንድ መቶ አስራ አራት ጨዋታዎች ተሰልፎ መጫወት ችሏል።

አስራ ስድስት አመታትን ለብሔራዊ ቡድኑ ግልጋሎት የሰጠው ኬይለር ናቫስ በሶስት የአለም ዋንጫ ውድድሮች መሳተፍም ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የአሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊ የኤሲ ሚላን ቆይታ ? የጣልያን ሴርያው ክለብ ኤሲ ሚላን በውድድር አመቱ መጨረሻ አሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊን ከሀላፊነታቸው ለማሰናበት በወሰነው ውሳኔ መፅናቱ ተገልጿል። አሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊ በቅርቡ ስለወደፊት ቆይታቸው ተጠይቀው " በውድድር አመቱ መጨረሻ ከክለቡ ጋር እነጋገራለሁ አሁን አስተያየት መስጠት አልፈልግም።" ብለው ነበር። ኤሲ ሚላን አሁን ላይ አሰልጣኙን የማሰናበት…
ኤሲ ሚላን ከአሰልጣኙ ጋር ተለያየ !

የጣልያን ሴርያው ክለብ ኤሲ ሚላን በውድድር አመቱ መጨረሻ ከአሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊ ጋር ለመለያየት መወሰኑን በይፋ አስታውቋል።

አሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊ ኤሲ ሚላን ነገ በስታዲዮ ጁሴፔ ሜዛ ከሳለርኒታና ጋር በሚያደርገው የሊግ የመጨረሻ ሳምንት መርሐ ግብር ክለቡን ይሰናበታሉ።

ከ 2019 ጀምሮ ኤሲ ሚላንን በሀላፊነት የመሩት አሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊ ክለቡን የሴርያ ዋንጫ አሸናፊ በማድረግ ወደ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድርም መመለስ ችለዋል።

ኤሲ ሚላን በቀጣይ የአሰልጣኝ ስቴፋኖ ፒዮሊ ተተኪ በማድረግ ፖርቹጋላዊውን የሊል አሰልጣኝ ፓውሎ ፎንሴካን ይሾማል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/05 03:21:15
Back to Top
HTML Embed Code: