Telegram Web Link
የጀርመን ቡንደስሊጋ ፍፃሜውን አገኘ !

የጀርመን ቡንደስሊጋ የ2023/24 የውድድር አመት ከደቂቃዎች በፊት ከተጠናቀቁ የመጨረሻ ሳምንት መርሐ ግብሮች በኋላ ፍፃሜውን አግኝቷል።

ባየር ሊቨርኩሰን በዘንድሮውን የጀርመን ቡንደስሊጋ ውድድር ምንም ጨዋታ ሳይሸነፍ ዋንጫውን በማሳካት አዲስ ታሪክ ፅፈዋል።

ባየር ሙኒክ በሆፌንሄም 4ለ2 መሸነፉን ተከትሎ የውድድር አመቱን በስቱትጋርት ተበልጦ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ለማጠናቀቅ ተገዷል።

ቦርስያ ዶርትመንድ ከዳርምስታድት ያደረገውን ጨዋታ 4ለ0 ሲያሸን የመጨረሻ ጨዋታውን ያደረገው ማርኮ ሪውስ ግብ አስቆጥሯል።

እንግሊዛዊው የፊት መስመር አጥቂ ሀሪ ኬን በሰላሳ ስድስት ግቦች የውድድሩ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በመሆን ማጠናቀቅ ችሏል።

የባየር ሊቨርኩሰኑ የፊት መስመር ተጨዋች አሌሀንድሮ ግሪማልዶ አስራ ሶስት ለግብ የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ በማቀበል የአመቱ ምርጥ ኳስ አቀጣጣይ በመሆን አጠናቋል።

ባየር ሊቨርኩሰን ፣ ስቱትጋርት ፣ ባየር ሙኒክ ፣ ሌፕዚግ እና ቦርስያ ዶርትመንድ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊ መሆናቸውን ያረጋገጡ ክለቦች ናቸው።

እንዲሁም ኢንትራንክት ፍራንክፈርት ለዩሮፓ ሊግ ሆፌንሄም ለኮንፈረንስ ሊግ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።

ዳርምስታድት እና ኮለን ከሊጉ መውረዳቸውን ሲያረጋግጡ ቦህም ከሊጉ ላለመውረድ የማጣሪያ ጨዋታ የሚያደርግ ይሆናል።

*የዛሬ ውጤቶች እና ሙሉ የደረጃ ሰንጠረዥ ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የእንግሊዝ ሴቶች ሱፐር ሊግ ዛሬ ይጠናቀቃል ! አሸናፊውን ክለብ እስከመጨረሻው ሳምንት መርሐ ግብር ያላሳወቀው የእንግሊዝ የሴቶች ሱፐር ሊግ ውድድር ዛሬ በተመሳሳይ ሰዓት በሚደረጉ ጨዋታዎች ፍፃሜውን ያገኛል። ሊጉን የቼልሲ ሴቶች ቡድን እና የማንችስተር ሲቲ ሴቶች ቡድን በተመሳሳይ ሀምሳ ሁለት ነጥብ በሁለት የግብ ክፍያ ተበላልጠው አንደኛ እና ሁለተኛ በመሆን እየመሩት ይገኛሉ። ሁለቱ ክለቦች አስካሁን…
ቼልሲ የሴቶች ሱፐር ሊግ ሻምፒዮን ሆነ !

የቼልሲ ሴቶች ቡድን ከማንችስተር ዩናይትድ ሴቶች ቡድን ጋር ያደረገውን የእንግሊዝ የሴቶች ሱፐር ሊግ የመጨረሻ ሳምንት መርሐግብር 6ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

ይህንንም ተከትሎ የቼልሲ ሴቶች ቡድን ሀምሳ አምስት ነጥቦችን ሰብስቦ በማጠናቀቅ የዘንድሮው የእንግሊዝ ሱፐር ሊግ ውድድር ሻምፒዮን መሆኑን አረጋግጧል።

የቼልሲ ሴቶች ቡድን የእንግሊዝ ሱፐር ካፕ ዋንጫን ለ #አምስተኛ ተከታታይ አመታት በማሸነፍ ወርቃማ ታሪክ መፃፍ ችለዋል።

የማንችስተር ሲቲ ሴቶች ቡድን በተመሳሳይ ሀምሳ አምስት ነጥቦችን ይዞ ቢያጠናቅቅም በቼልሲ በግብ ክፍያ ተብልጦ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።

ቼልሲ ፣ ማንችስተር ሲቲ እና አርሰናል በሚቀጥለው የውድድር አመት በሴቶች የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር የሚሳተፉ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መቻል ወሳኝ ድል አሳክቷል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የሀያ አምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር መቻል ከሀዋሳ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የመቻልን የማሸነፊያ ግቦች ከነዓን ማርክነህ 2x እና አብዱ ሞታላቡ ከመረብ ሲያሳርፉ ለሀዋሳ ከተማ ዓሊ ሱሌይማን 2x አስቆጥሯል።

ኤርትራዊው የሀዋሳ ከተማ የፊት መስመር ተጨዋች ዓሊ ሱሌይማን በውድድር አመቱ ያስቆጠራቸውን የሊግ ግቦች አስራ አምስት አድርሷል።

መቻል ተከታታይ ሶስተኛ ድሉን በማስመዝገብ ከሊጉ መሪ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሶስት ማጥበብ ችለዋል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

2️⃣ መቻል :- 50 ነጥብ

1️⃣0️⃣ ሀዋሳ ከተማ :- 33 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

አርብ - መቻል ከ ሻሸመኔ ከተማ

እሁድ - ሀድያ ሆሳዕና ከ ሀዋሳ ከተማ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#TkvahGoal

የጀርመን ቡንደስሊጋ ዋንጫን ምንም ሳይሸነፍ ያሳካው ባየር ሊቨርኩሰን የዋንጫ ድላቸውን በስታዲየማቸው ከደጋፊዎቻቸው ጋር አክብረዋል።

በቪዲዮ ለመመልከት የጎል ቻናላችንን መቀላቀል ይችላሉ።

የጎል ቻናላችን 👉 https://www.tg-me.com/+rbdEU4UaEdQxYWFk

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ሲቲን ለማሸነፍ የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን " ሞይስ

የዌስትሀም ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ዴቪድ ሞይስ በነገው የማንችስተር ሲቲ ጨዋታ ለራሳችን ስንል ጨዋታውን ለማሸነፍ የቻልነውን እናደርጋለን በማለት ተናግረዋል።

" ከዘጠነኛ በታች ሆነን ሊጉን ማጠናቀቅ አንችልም " ያሉት ዴቪድ ምይስ " ለራሳችን ስንል ጨዋታውን ለማሸነፍ የቻልነውን ሁሉ እናደርጋለን ፣ የምናደርገው ነገር ለዌስትሀም እንጂ ለሌላ ክለብ አይደለም " ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የባርሴሎና ሴቶች ቡድን ሻምፒዮን ሆኗል !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ሴቶች ቡድን ከሪያል ሶሴዳድ ጋር ያደረገውን የስፔን ኮፓ ዴላሬና ፍፃሜ ጨዋታ 8ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የዋንጫ አሸናፊ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

የባርሴሎና ሴቶች ቡድን #አስረኛ የስፔን ኮፓ ዴላሬና ዋንጫቸውን ማሳካት ችለዋል።

በዚህ አመት የሊጉን እና የስፔን ሱፐር ካፕ ዋንጫን ያሸነፈው የባርሴሎና ሴቶች ቡድን የሀገር ውስጥ የሶስትዮሽ ዋንጫ ስኬትን አስመዝግበዋል።

ባርሴሎና በተጨማሪም በአውሮፓ የሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ከፈረንሳዩ ክለብ ሊዮን ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኤሲ ሚላን ሽንፈት አስተናግዷል !

በጣልያን ሴርያ የሰላሳ ሰባተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኤሲ ሚላን ከቶሪኖ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ተሸንፈዋል።

የቶሪኖንን የማሸነፍ ግቦች ዛፓታ ፣ ኢች እና ሮድሪጉዌዝ ከመረብ ሲያሳርፉ እስማኤል ቤን ናስር የኤሲ ሚላንን ብቸኛ ግብ አስቆጥሯል።

ኤሲ ሚላን በውድድር አመቱ ሰባተኛ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

2️⃣ ኤሲ ሚላን :- 74 ነጥብ

9️⃣ ቶሪኖ :- 53 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

እሁድ - አታላንታ ከ ቶሪኖ

እሁድ - ኤሲ ሚላን ከ ሳለርኒታና

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
🔹iPhone 15 Pro Max
🔹iPhone 14 Pro Max

🔹 Samsung S24 Ultra
🔹 Samsung S23 Ultra

♦️ New & Slightly Used Available

Contact us :
0925927457
@Heyonlinemarket
https://heymobile.store/
የዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዎች !

9:00 አዳማ ከተማ ከ ሲዳማ ቡና

12:00 ሻሸመኔ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ቡና

12:00 አርሰናል ከ ኤቨርተን

12:00 ማንችስተር ሲቲ ከ ዌስትሀም

12:00 ብራይተን ከ ማንችስተር ዩናይትድ

12:00 ቼልሲ ከ በርንማውዝ

12:00 ሊቨርፑል ከ ዎልቭስ

12:00 ሼፍልድ ከ ቶተንሀም

1:00 ኢንተር ሚላን ከ ላዝዮ

2:00 ባርሴሎና ከ ራዮ ቫዬካኖ

2:00 ቪያሪያል ከ ሪያል ማድሪድ

4:00 ሜትዝ ከ ፒኤስጂ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የቀድሞ የመድፈኞቹ ተጨዋች ጫማውን ሰቅሏል !

ለላሊጋው ክለብ ሪያል ቤቲስ በመጫወት ላይ የሚገኘው የቀድሞ የአርሰናል ግሪካዊ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሶክራተስ ጫማውን መስቀሉን በይፋ አሳውቋል።

የ 35ዓመቱ ተጨዋች ስክራተስ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባሰፈረው መልዕክትም በቀጣይ ከሪያል ቤቲስ ጋር የመጨረሻ ሁለት የላሊጋ ጨዋታዎችን እንደሚያደርግ ገልጿል።

ሶክራተስ በእግርኳስ ህይወቱ የስኩዲቶ ፣ የጀርመን ፖካል ዋንጫ ፣ የኤፌ ካፕ እና ጀርመን ሱፐር ካፕ 2x እንዲሁም ሌሎች ዋንጫዎችን ማሳካት ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፔፕ ጋርዲዮላ በሲቲ እንደሚቀጥሉ ገለጹ !

ስፔናዊው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በሚቀጥለው የውድድር ዘመን በማንችስተር ሲቲ አሰልጣኝነታቸው እንደሚቀጥሉ በሰጡት አስተያየት ገልፀዋል።

በማንችስተር ሲቲ ቤት እስከ 2025 የሚያቆይ ኮንትራት ያላቸው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ " ውሌ እስከሚጠናቀቅ እዚህ አለሁ " ብለዋል።

እኔ እዚህ እስካለሁ ሌሎች ክለቦች ሊጉን ለማሸነፍ ይቸገራሉ የሚል እምነት የለኝም ያሉት ፔፕ ጋርዲዮላ " ልዩነቱ በጣም ትንሽ ነው አርሰናል ማሸነፍ ይችላል ሊቨርፑልም አድርጎታል " ብለዋል።

በሌላ በኩል የማንችስተር ሲቲ ሀላፊዎች አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ኮንትራታቸው ሲጠናቀቅ በክለቡ ላይቀጥሉ ይችላሉ የሚል ስጋት እንዳላቸው ለክለቡ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ዘግበዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#TheFinalDay 🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿

የዋንጫ አሸናፊው ተለይቶ ያልታወቀበት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የዘንድሮው የ2023/24 የውድድር አመት በዛሬው ዕለት በተመሳሳይ ሰዓት በሚደረጉ መርሐ-ግብሮች ፍፃሜውን ያገኛል።

- ሊጉን በሁለት ነጥብ ልዩነት እየመራ የሚገኘው ማንችስተር ሲቲ ለአራተኛ ተከታታይ አመታት ሊጉን በማሳካት አዲስ ታሪክ ሊፅፍ በሜዳው ዌስትሀም ዩናይትድን ያስተናግዳል።

- ጥሩ የሚባል የውድድር አመት በማሳለፍ ላይ የሚገኘው አርሰናል በበኩሉ ከሀያ አመታት በኋላ ዋንጫውን ወደ ኤምሬትስ ለመመለስ የሲቲን ነጥብ መጣል እየተጠባበቀ ከኤቨርተን ጋር ይጫወታል።

- የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ በታሪኩ ለ #አስረኛ ጊዜ የዋንጫ አሸናፊውን ክለብ በመጨረሻ ቀን ውሎው የሚለይ ይሆናል።

- ከዚህ በፊት የፕርሚየር ሊጉ አሸናፊ ክለብ በመጨረሻ ሳምንት መርሐ ግብር በታወቀባቸው ዘጠኝ አጋጣሚዎች ሊጉን እየመሩ የነበሩ ክለቦች ሻምፒዮን ሆነዋል።

- በዘንድሮው የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ከወትሮው በተለየ መልኩ የዋንጫ አሸናፊነት እድል ባላቸው ማንችስተር ሲቲ እና አርሰናል ስታዲየሞች ሁለት የሊግ ዋንጫዎች እንደሚቀመጡ ተገልጿል።

- ቼልሲ እና ኒውካስል ዩናይትድ የአውሮፓ መድረክ ቦታን ለማግኘት ሲፋለሙ ማንችስተር ዩናይትድም በሊጉ በሒሳባዊ ስሌት በአውሮፓ መድረክ የመሳተፍ እድሉ አለው።

- የፕርሚየር ሊጉ ዋን ስራ አስፈፃሚ ሪቻርድ ማስተርስ በዛሬው ጨዋታ የአርሰናል እና ኤቨርተንን ጨዋታ ለመታደም ወደ ኤምሬትስ ያቀናሉ።

ሊጉን ማን ሊያሸንፍ ይችላል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ይህንን እድል መልሰን አናገኘውም " ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ዋንጫን ለተከታታይ አራተኛ ጊዜ ለማሸነፍ የሚደረግ ጥረት " በህይወት ዘመን አንድ ጊዜ የሚከሰት ነዉ " ሲሉ ገልጸዋል።

" በድጋሜ የሊጉን ዋንጫ ለአራተኛ ጊዜ ለማሸነፍ መፎካካር የማይቻል ነገር ነው " ሲሉ የገለፁት ፔፕ ጋርዲዮላ " ሁላችንም ይህንን አድል መልሰን አናገኘውም በህይወት ዘመን አንድ ጊዜ የሚፈጠር ነው " ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ምባፔ በፒኤስጂ ስብስብ አልተካተተም !

ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ ፔኤስጂ ዛሬ ምሽት ከሜትዝ ጋር በሚያደርገው የሊጉ የመጨረሻ ጨዋታ በሚጠቀመው ስብስብ ውስጥ ሳይካተት ቀርቷል።

ይህንንም ተከትሎ ኪሊያን ምባፔ በፈረንሳይ ሊግ የውድድር አመቱ የመጨረሻ ጨዋታ ላይ የማይሳተፍ ይሆናል።

በቀጣይ ሪያል ማድሪድን ይቀላቀላል ተብሎ የሚጠበቀው ኪሊያን ምባፔ ከቀናት በፊት ፒኤስጂን እንደሚለቅ በይፋ ማሳወቁ ይታወሳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/27 09:27:52
Back to Top
HTML Embed Code: