Telegram Web Link
ሰማያዊዎቹ ወሳኝ ድል አሳክተዋል !

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ሰላሳ አራተኛ ሳምንት ተስተካካይ መርሐ ግብር ቼልሲ ከብራይተን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የሰማያዊዎቹን የማሸነፊያ ግቦች ኮል ፓልመር እና ክርስቶፈር ንኩንኩ ከመረብ ሲያሳርፉ ለብራይተን ዳኒ ዌልቤክ አስቆጥሯል።

እንግሊዛዊው ተጨዋች ኮል ፓልመር በውድድር አመቱ ሀያ ሁለት የሊግ ግቦች አስቆጥሮ አስር አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

በጨዋታው እንግሊዛዊው የቼልሲ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሬስ ጄምስ ቀይ ካርድ የተመለከተ ሲሆን በዚህም ምክንያት የቀጣይ አመት የመጀመሪያ ሁለት የሊግ ጨዋታዎች ያመልጡታል።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?

6️⃣ ቼልሲ :- 60 ነጥብ

1️⃣0️⃣ ብራይተን :- 48 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

እሁድ - ብራይተን ከ ማንችስተር ዩናይትድ

እሁድ - ቼልሲ ከ በርንማውዝ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማንችስተር ዩናይትድ ድል አድርጓል !

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የሰላሳ አራተኛ ሳምንት ተስተካካይ መርሐግብር ማንችስተር ዩናይትድ ከኒውካስል ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የማንችስተር ዩናይትድን የማሸነፊያ ግቦች ኮቢ ማይኖ ፣ አማድ ዲያሎ እና ራስሙስ ሆይሉንድ ሲያስቆጥሩ ለኒውካስል ዩናይትድ አንቶኒ ጎርደን እና ሀል አስቆጥረዋል።

ማንችስተር ዩናይትድ በአንድ የውድድር አመት ሰማንያ አራት ግቦች ሲቆጠሩባቸው ከስልሳ አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ተገልጿል።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?

7️⃣ ኒውካስል ዩናይትድ :- 57 ነጥብ

8️⃣ ማንችስተር ዩናይትድ :- 57 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

እሁድ - ብራይተን ከ ማንችስተር ዩናይትድ

እሁድ - ብሬንትፎርድ ከ ኒውካስል ዩናይትድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጁቬንቱስ ሻምፒዮን ሆነዋል !

ጁቬንቱስ ከአትላንታ ጋር ያደረገውን የኮፓ ኢታልያ ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሻምፒዮን መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

ጁቬንቱስን ለዋንጫ ድል ያበቃች ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ዱሳን ቪላሆቪች ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ጁቬንቱስ በታሪኩ የኮፓ ኢታልያ ዋንጫን ለአስራ አምስተኛ ጊዜ ማሸነፍ ችለዋል።

አሰልጣኝ ማሴሚላኖ አሌግሪ ከየትኛውም አሰልጣኝ በበለጠ አምስተኛ የኮፓ ኢታልያ ዋንጫቸውን ማሳካት ችለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ዋንጫውን ለማምጣት ሁሉንም እንሰጣለን " ቴንሀግ

በኦልድትራፎርድ ስታዲየም የውድድር አመቱ የመጨረሻ ጨዋታውን ያደረገው ማንችስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ከምሽቱ ጨዋታ በኋላ በስታዲየሙ ለደጋፊው መልዕክት አስተላልፈዋል።

" አመቱ ለእኛ ከባድ ነበር ነገርግን ላመሰግናችሁ እፈልጋለሁ እናንተ የአለም ምርጥ ደጋፊዎች ናችሁ " በማለት ንግግራቸውን የጀመሩት ኤሪክ ቴንሀግ አመቱ አሁንም አላለቀም ወሳኝ ጨዋታዎች አሉን ብለዋል።

የኤፌ ካፕ ፍፃሜ ጨዋታን ለማሸነፍ መዘጋጀታቸውን የጠቆሙት አሰልጣኙ ለደጋፊው " ተጨዋቾቹ ጨዋታውን አሸንፈው ዋንጫውን ወደ ኦልድትራፎርድ ለማምጣት ያላቸውን ሁሉ እንደሚሰጡ ቃል እገባላችኋለሁ " ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሽመልስ በቀለ 1⃣8⃣ ገስት ሀውስ

በውቢቷ ሀዋሳ ቆይታዎ የት ለማረፍ አስበዋል ? ንፁህ እና በደንበኞቻችን ተወዳጅ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን መጥተው የእረፍት ጊዜውን ያሳልፉ።

እንግዶቻችንን ተቀበልን ለእይታ ሳቢ በሆነው የእንግዳ ማረፊያችን ማስተናገድ ከጀመርን አመታትን አስቆጥረናል።

አድራሻችን :- ሀዋሳ አርቴፍሻል ስታዲየም መንገድ ላይ ያገኙናል።

ለተጨማሪ መረጃ እና ለትዕዛዝዎ ይደውሉልን :- 0928684848

#ShemelesBekele18
Forwarded from HEY Online Market
🔹iPhone 15 Pro Max
🔹iPhone 14 Pro Max

🔹 Samsung S24 Ultra
🔹 Samsung S23 Ultra

♦️ New & Slightly Used Available

Contact us :
0925927457
@Heyonlinemarket
https://heymobile.store/
ሴልቲክ ሻምፒዮን ሆነዋል !

የስኮትላንዱ ክለብ ሴልቲክ ትላንት ምሽት ከኪልማርኖክ ጋር ያደረጉትን የሊግ ጨዋታ 5ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የስኮትላንድ ሊግ ሻምፒዮን መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

በአሰልጣኝ ብሬንዳን ሮጀርስ የሚመራው ሴልቲክ ለተከታታይ ሶስት የውድድር አመታት የሊጉ ሻምፒዮን መሆን ችለዋል።

ሴልቲክ በታሪኩ ሀምሳ አራተኛ የስኮትላንድ ሊግ ዋንጫውን ማሳካት ችለዋል።

ካለፉት አስራ ሶስት አመታት ውስጥ ሴልቲክ አስራ ሁለቱን የሊግ ዋንጫዎች አሳክተዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" የቫር ቴክኖሎጂ ሊቀር ይገባል " ጎርደን

የኒውካስል ዩናይትድ የፊት መስመር ተጨዋች አንቶኒ ጎርደን በትላንት ምሽቱ ጨዋታ ሶፍያን አምራባት የሰራበት ጥፋት ግልጽ ፍፁም ቅጣት ምት እንደነበር ገልጿል።

" ጥፋቱን ደጋግሜ ተመልክቼዋለሁ ግልጽ ፍፁም ቅጣት ምት ነበር " ያለው አንቶኒ ጎርደን የቫር ጥቅም አልገባኝም ከሊጉ ይጥፋ ወይም በተሻለ ቴክኖሎጂ ይተካ በማለት ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ትክክለኛውን አምራባት አልተመለከታችሁም "

ሞሮኳዊው የማንችስተር ዩናይትድ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሶፍያን አምራባት ትላንት ምሽት ያደረገው ጥሩ እንቅስቃሴ የእሱን ሙሉ አቅም የሚያሳይ አለመሆኑን ገልጿል።

" ትክክለኛውን አምራባት አልተመለከታችሁም " በማለት አስተያየቱን የሰጠው ተጨዋቹ በአምስት ወራት ውስጥ ዘጠና ደቂቃ ስጫወት ለሁለተኛ ጊዜ ነው እስካሁን ያለኝን ትልቅ ችሎታ ሙሉ ለሙሉ አላሳየሁም ብሏል።

ሶፍያን አምራባት ማንችስተር ዩናይትድን በውሰት ውል መቀላቀሉ የሚታወስ ሲሆን ቀያዮቹ ሴጣኖች በ25 ሚልዮን ዩሮ በቋሚነት የማስፈረም አማራጭ አላቸው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የሜጀር ሊግ ሶከር ከፍተኛ ተከፋይ ተጨዋቾች !

የአሜሪካ ሜጀር ሊግ ሶከር ውድድር በአሁን ሰዓት ከፍተኛ አመታዊ ክፍያ የሚያገኙ ተጨዋቾች ይፋ ተደርገዋል።

አርጀንቲናዊው የስምንት ጊዜ ባሎን ዶር አሸናፊው ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ 20,446,667 ዶላር በማግኘት ቀዳሚውን ስፍራ መያዙ ተገልጿል።

ክፍያው ሊዮኔል ሜሲ ከአፕል ጋር ካለው ድርሻ ፣ ከማስታወቂያ እና ሌሎች አጋሮቹ ከሚያገኘው ገንዘብ ውጪ መሆኑ ተነግሯል።

ብዙ የሚከፈላቸው ተጨዋቾች የትኞቹ ናቸው ?

- ሊዮኔል ሜሲ :- 20.4 ሚልዮን ዶላር

- ሎሬንዞ ኢንሲኜ :- 15.4 ሚልዮን ዶላር

- ሰርጅዮ ቡስኬት :- 8.8 ሚልዮን ዶላር

- ሻኪሪ :- 8.2 ሚልዮን ዶላር

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኢንድሪክ ጉዳት አጋጥሞታል !

ብራዚላዊው ቀጣዩ የሪያል ማድሪድ የፊት መስመር ተጨዋች ኢንድሪክ ትላንት ክለቡ ፓልሜራስ ባደረገው ጨዋታ ጉዳት አጋጥሞት ተቀይሮ ለመውጣት መገደዱ ተገልጿል።

ተጨዋቹ ካጋጠመው ጉዳት በኋላ በእርዳታ ሰጪ አምቡላንስ ታግዞ ከሜዳ ሲወጣ የተስተዋለ ሲሆን ስለጉዳት መጠኑ በይፋ የታወቀ ነገር የለም።

የ 17ዓመቱ ተስፈኛ አጥቂ ኢንድሪክ ብራዚል ለቀጣዩ ኮፓ አሜሪካ ውድድር ጥሪ ካቀረበችላው የፊት መስመር ተጨዋቾች አንዱ መሆኑ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ተጠባቂ ጨዋታዎችን የሚመሩ ዳኞች ታውቀዋል !

በሳምንቱ መጨረሻ እሁድ የሊጉን አሸናፊ ክለብ ለመለየት የሚደረጉ ተጠባቂ የፕርሚየር ሊግ የመጨረሻ ሳምንት ጨዋታዎችን የሚመሩ ዳኞች ታውቀዋል።

የሊጉ መሪ ማንችስተር ሲቲ ከዌስትሀም ዩናይትድ ጋር የሚያደርጉትን ተጠባቂ ጨዋታ ጆን ብሩክስ በመሐል ዳኝነት እንደሚመሩት ይፋ ተደርጓል።

ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በበኩሉ ከኤቨርተን ጋር የሚያደርገውን ተጠባቂ ጨዋታ ማይክል ኦሊቨር በመሐል ዳኝነት ይመሩታል።

ጨዋታዎቹን እነማን ያሸንፋሉ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
📢 አሁንም እጅግ ልዩ የሽያጭ ብስራት ከ #ዋናው!

ለአትሌቲክስ፣ ለቴኳንዶ እና ሌሎች ስፖርቶች ከዋናው፦
👉🏾 ከ50 ብዛት ጀምሮ ቲ-ሸርቶችን ሲያዙ 1 ባለኮሌታ ቲ-ሸርትና 1 ባንዲራ በነፃ ያገኛሉ።
👉🏾 ከ 100 ብዛት ጀምሮ ሲያዙ ደግሞ 2 ባለኮሌታ ቲ-ሸርትን እና 2 ባንዲራን፣ በፈለጉት ዲዛይን ሰርተን በነፃ እንሰጥዎታለን።

🔥 #እንዳያመልጥዎ፣ አሁኑኑ ይዘዙን!

📍አድራሻችን:- ገርጂ መብራት ሃይል የካቲት ወረቀት ፊትለፊት፣ አለም ገብሬ ህንፃ፣ 2ተኛ ፎቅ።

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ወይም በቴሌግራም ቦት @WANAWSbot በኩል ይዘዙን።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
በአሜሪካ ቅርጫት ኳስ ውድድር በዌስተርን ኮንፈረንስ ደረጃ ሰንጠረዥ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙት " Nuggets " እና " Timberwolves " ተጠባቂ የኮንፈረንስ ግማሽ ፍፃሜ ስድስተኛ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ሁለቱ ተጋጣሚዎች ካለፉት አስር ጨዋታዎች በተመሳሳይ ስድስቱን በመርታት የሚገናኙ ይሆናል።

ጨዋታው ሐሙስ ሌሊት 9:30 ሰዓት ይደረጋል።
በጨዋታው ለመወራረድ - betika.et
ቤቲካ! የአሸናፊዎች ቤት!
አርሰናል እና ሲቲ አዲሱን ማልያ ለብሰው አይገቡም !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል እና ማንችስተር ሲቲ በዛሬው ዕለት በሚቀጥለው የውድድር አመት የሚጠቀሙትን አዲስ የሜዳ ማልያቸውን አስተዋውቀዋል።

ይሁን እንጂ ክለቦቹ እሁድ በሚያደርጉት የመጨረሻ ሳምንት መርሐ ግብር ለማስተዋወቅ አዲሱን ማልያ ለብሰው እንደማይገቡ ተገልጿል።

ሁለቱም ክለቦቹ ዋንጫውን የማሸነፍ እድል ያላቸው መሆኑን ተከትሎ ሊጉ በአመቱ የተጫወቱበትን ማልያ ለብሰው እንዲገቡ እንደሚያስገድድ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ለቶማስ ፓርቴ የምሰጠው ነገር አለኝ " ኩዱስ

የዌስትሀም ዩናይትድ የፊት መስመር ተጨዋች መሐመድ ኩዱስ የሀገሩ ልጅ ቶማስ ፓርቴ የሊጉን ዋንጫ እንዲያሸንፍ ለማገዝ ለእሁዱ የሲቲ ጨዋታ መዘጋጀቱን ገልጿል።

የአመቱ መጨረሻ ጨዋታ ለእነሱ ትልቅ ትርጉም እንዳለው የገለፀው መሐመድ ኩዱስ " እሁድ ለወንድሜ ቶማስ ፓርቴ የምሰጠው ነገር አለኝ ሊጉን ከአርሰናል ጋር ያሸንፍ ይሆናል"።ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጀርመን ስብስቧን አሳውቃለች !

የጀርመን ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ ሀገሪቱ በምታዘጋጀው የ2024 አውሮፓ ዋንጫ ውድድር የሚጠቀመውን ስብስብ ይፋ አድርጓል።

በአሰልጣኝ ጁሊያን ኔግልስማን የሚመራው ብሔራዊ ቡድኑ የአውሮፓ ዋንጫ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከወር በኋላ ከስኮትላንድ ጋር ያደርጋል።

ሙሉ ስብስቡ ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የደጋፊዎች የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ?

የእንግሊዝ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጨዋቾች ማህበር ( ፒኤፍኤ ) የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የደጋፊዎች የአመቱ ምርጥ ተጨዋች #ስምንት እጩዎችን ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት ፊል ፎደን ፣ ኤርሊንግ ሀላንድ ፣ ማርቲን ኦዴጋርድ ፣ ኮል ፓልመር ፣ ዴክላን ራይስ ፣ ሮድሪ ፣ ዊሊያም ሳሊባ እና ኦሊ ዋትኪንስ በእጩነት መቅረብ ችለዋል።

የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጄሱስ ናቫስ ከሲቪያ ጋር ሊለያይ ነው !

ስፔናዊው የመስመር ተጨዋች ጄሱስ ናቫስ በውድድር አመቱ መጨረሻ ከሲቪያ ጋር እንደሚለያይ አስታውቋል።

ጄሱስ ናቫስ በሲቪያ ቤት በቆየባቸው አመታት ስድስት መቶ ሰማንያ ስምንት ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ መጫወት ችሏል።

የ 38ዓመቱ ተጨዋች ጄሱስ ናቫስ ከሲቪያ ጋር ዘጠኝ የተለያዩ ዋንጫዎችንም ማሸነፍ ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/29 12:22:00
Back to Top
HTML Embed Code: