Telegram Web Link
51 ' ቶተንሀም 0 - 1 ማንችስተር ሲቲ

ሀላንድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
88 ' ቶተንሀም 0 - 1 ማንችስተር ሲቲ

                          ሀላንድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
90 ' ቶተንሀም 0 - 2 ማንችስተር ሲቲ

                          ሀላንድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
90+10 ' ቶተንሀም 0 - 2 ማንችስተር ሲቲ

                          ሀላንድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማንችስተር ሲቲ የሊጉን መሪነት ተረከበ !

ማንችስተር ሲቲ ከቶተንሀም ጋር ያደረገውን የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ሰላሳ አራተኛ ሳምንት ተስተካካይ መርሐ ግብር 2ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የሊጉን መሪነት መረከብ ችለዋል።

የማንችስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ኤርሊንግ ሀላንድ 2x ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ኬቨን ዴብሮይን አንድ መቶ አስራ ሁለተኛ ለግብ የሆነ ኳሱን አመቻችቶ በማቀበል በሊጉ ታሪክ ብዙ አመቻችቶ ያቀበለ #ሁለተኛው ተጨዋች ሆኗል።

ኖርዊያዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኤርሊንግ ሀላንድ በውድድር ዘመኑ ሀያ ሰባተኛ የሊግ ግቡን ማስቆጠር ችሏል።

ማንችስተር ሲቲ በአዲሱ የቶተንሀም ስታዲየም የመጀመሪያ የፕርሚየር ሊግ ጎል ማስቆጠር ችሏል።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?

1️⃣ ማንችስተር ሲቲ :- 88 ነጥብ

5️⃣ ቶተንሀም :- 63 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

እሁድ - ማንችስተር ሲቲ ከ ዌስትሀም ዩናይትድ

እሁድ - ሼፍልድ ከ ቶተንሀም

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አስቶን ቪላ በሻምፒየንስ ሊግ መሳተፉን አረጋገጠ !

ቶተንሀም በማንችስተር ሲቲ መሸነፉን ተከትሎ አስቶን ቪላ በሚቀጥለው የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር ተሳታፊ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

በአሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ የሚመራው አስቶን ቪላ ከአርባ አንድ አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር የሚሳተፉ ይሆናል።

በቀጣይ እነማን በሻምፒየንስ ሊግ ይሳተፋሉ ?

- ማንችስተር ሲቲ

- አርሰናል

- ሊቨርፑል

- አስቶን ቪላ ተሳታፊ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ኦርቴጋ ታድጎን ወጥቷል " ሮድሪ

የማንችስተር ሲቲው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሮድሪ ግብ ጠባቂው ኦርቴጋ በምሽቱ ጨዋታ በድናቸውን ታድጎ መውጣቱን ከጨዋታው በኋላ በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

" ኦርቴጋ ታድጎን ወጥቷል " በማለት የገለፀው ሮድሪ ለመግለጽ ቃል የማይገኝለት ጥሩ እድሎችን አድኗል ፣ ዛሬ ጥሩ አልነበርንም ነገርግን ወደዚህ የመጣነው ለማሸነፍ ነው ያደረግነውም ይህንኑ ነው ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሻምፒዮኖቹ ድል አድርገዋል !

በስፔን ላሊጋ የሰላሳ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሪያል ማድሪድ ከዲፖርቲቮ አላቬስ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 5 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የሪያል ማድሪድን የማሸነፊያ ግቦች ቪንሰስ ጁኒየር 2x ፣ ጁድ ቤሊንግሀም ፣ አርዳ ጉለር እና ቫልቬርዴ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

እንግሊዛዊው የሪያል ማድሪድ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ጁድ ቤሊንግሀም በውድድር አመቱ አስራ ዘጠነኛ የሊግ ግቡን አስቆጥሯል።

ብራዚላዊው ተጨዋች ቪንሰስ ጁንየር በውድድር አመቱ ያስቆጠራቸውን የሊግ ግቦች ወደ አስራ አምስት ከፍ አድርጓል።

የሁለቱ ክለቦች ደረጃ ምን ይመስላል ?

1️⃣ ሪያል ማድሪድ :- 93 ነጥብ

1️⃣1️⃣ ዲፖርቲቮ አላቬስ :- 42 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ?

እሁድ - ቪያሪያል ከ ሪያል ማድሪድ 

ቅዳሜ - ዲፖርቲቮ አላቬስ ከ ሄታፌ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" በሜዳችን የነበረው ድጋፍ ያልተለመደ ነበር " ፖስቴኮግሉ

የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም ዋና አሰልጣኝ አንሄ ፖስቴኮግሉ በምሽቱ የማንችስተር ሲቲ ጨዋታ ቡድናቸው በሜዳው ቢጫወትም የነበረው ድጋፍ ያልተለመደ ሆኖ እንዳገኙት ገልፀዋል።

የተመዘገበው ውጤት እንዳበሳጫቸው የገለፁት አሰልጣኝ አንሄ ፖስቴኮግሉ " የነበረው የደጋፊዎች ድባብ በሜዳችን አይተነዋል የማናውቀው ነበር " ሲሉ ገልፀዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቀጣዩ ሚሊየነር ይሁኑ! በሳምንታዊ ጃክፖት የ1 ሚሊዮን ብር አሸናፊ ይሁኑ! የሳምንታዊ ጃክፖት ላይ ለመወራረድ - (betika.et/weeklyjackpot)
Forwarded from HEY Online Market
🔹iPhone 15 Pro Max
🔹iPhone 14 Pro Max

🔹 Samsung S24 Ultra
🔹 Samsung S23 Ultra

♦️ New & Slightly Used Available

Contact us :
0925927457
@Heyonlinemarket
https://heymobile.store/
ተጠባቂ የዛሬ መርሐ ግብሮች !

3:45 ብራይተን ከ ቼልሲ

4:00 ማንችስተር ዩናይትድ ከ ኒውካስትል ዩናይትድ

4:00 ኒስ ከ ፒኤስጂ

ኮፓ ኢታሊያ ፍፃሜ 🏆

4:00 አታላንታ ከ ጁቬንቱስ

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ማንችስተር ዩናይትድ ታዳጊ ቡድኑ ሻምፒዮን ሆኗል !

የማንችስተር ዩናይትድ የታዳጊ ቡድን ( ከ 18ዓመት ) በታች ቡድን በዓመቱ የሶስትዮሽ ዋንጫን በማሳካት ሻምፒዮን መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

ትላንት ምሽት የማንችስተር ዪናይትድ ከ 18ዓመት በታች ቡድን የሊጉን ዋንጫ ማሸነፍ ቸለዋል።

ታዳጊ ቡድኑ በውድድር ዓመቱ :-

- ከ 18ዓመት በታች ዋንጫ

- ከ 18ዓመት በታች “ National “ ዋንጫ ማሸነፍ ችለው ነበር።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የአርሰናል ደጋፊዎች የሲቲን ተጨዋቾች ለመረበሽ ሞክረዋል ! በበሊጉ ዋንጫ ፉክክር ውስጥ የሚገኙት አርሰናል ደጋፊዎች የተፎካካሪያቸው ማንችስተር ሲቲ ተጨዋቾች አርፈውበታል ተብሎ የታሰበ ሆቴል ለመረበሽ መሞከራቸው ተገልጿል። ማንችስተር ሲቲ ዛሬ ምሽት ከቶተንሀም ጋር ወሳኝ ጨዋታውን ሰሜን ለንደን በማምራት የሚያደርግ ይሆናል። የመድፈኞቹ ደጋፊዎች የሲቲ ተጨዋቾች አርፈውበታል ወደተባለ ሆቴል በመሄድ…
ለመረበሽ የተሞከረው በሌለንበት ነው “

እንግሊዛዊው የማንችስተር ሲቲ የኋላ መስመር ተጫዋች ካይል ዎከር ቀሪ ጨዋታቸውን ማሸነፍ እንዳለባቸው አሳስቧል።

ከምሽቱ ጨዋታ በኋላ በሰጠው አስተያየት “ የአርሰናል ደጋፊዎች ሆቴል ውስጥ #በሌለንበት ተቀጣጣይ ነገሮች የርችት ድምፆችን በሆቴላችን ፊት ለፊት ሲያሰሙ አምሽተው ነበር “ ብሏል።

ይህ ድርጊት እና ድባብ ፕርሚየር ሊጉን የበለጠ እንዲወደው እንደሚያደርገው ካይል ዎከር አያይዞ ገልጿል።

ስለ ዋንጫው የተጠየቀው ዎከር “ ገና አላለቀም “ ሲል “ አንድ ጨዋታ ይቀረናል ይህንንም መርሕ ግብር ማሸነፍ አለብን “ ሲል አሳስቧል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
" አርሰናል ሳንቾን ማስፈረም አለበት " ኢማኑኤል ፔቲት

የቀድሞ ፈረንሳዊ ተጨዋች ኢማኑኤል ፔቲት አርሰናል በማንችስተር ዩናይትድ የተገለሉ ተጨዋቾችን ቢያስፈርም ተጠቃሚ እንደሚሆን መክሯል።

አርሰናል ዩናይትድ ያገለላቸውን እንደ ሳንቾ አይነት ተጨዋቾችን ቢያስፈርም ይጠቀማል ያለው ተጨዋቹ " አደጋ ይኖረዋል ነገርግን አርቴታ ለተጨዋቾች አዲስ ህይወት መስጠት ያውቅበታል።"ብሏል።

ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ካይ ሀቨርትዝ ነው በማለት የገለፀው ኢማኑኤል ፔቲት ጄደን ሳንቾን በሻምፒየንስ ሊጉ የተለየ ነገር አይቼበለሁ አርሰናል ቢሄድ የፊት መስመሩን ያጠናክራል ሲል ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሁለት የፕርሚየር ሊግ ዋንጫዎች ይዘጋጃሉ !

የእንግሊዝ ፕርሚየር የዘንድሮው የውድድር አመት አሸናፊውን ክለብ ለመለየት የፊታችን እሁድ በተመሳሳይ ሰዓት የሚደረጉ የመጨረሻ ሳምንት መርሐ ግብሮች ይጠበቃሉ።

ሊጉን በመምራት ላይ የሚገኘው ማንችስተር ሲቲ እንዲሁም ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው አርሰናል ዋንጫውን የማሸነፍ እድልን ይዘዋል።

ሁለቱም ክለቦች ዋንጫውን የማሸነፍ እድል ያላቸው መሆኑን ተከትሎ በኢትሀድ እና ኤምሬትስ ስታዲየሞች #ሁለት ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ዋንጫዎች እንደሚዘጋጁ ተገልጿል።

በተጨማሪም በሁለቱም ስታዲየሞች አርባ ሜዳሊያዎች እንደሚዘጋጁ የተገለፀ ሲሆን በአመቱ ውስጥ ቢያንስ አምስት ጨዋታዎች ያደረገ ተጨዋች ሜዳልያ እንደሚሰጠው ተጠቁሟል።

እንዲሁም በሁለቱም ክለቦች ስታዲየሞች ለዋንጫ ድል ክብረ በዓል ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉ ነገሮች ተዘጋጅተው አሸናፊውን ይጠባበቃሉ ተብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
📢 እጅግ ልዩ የሽያጭ ብስራት #ከዋናው!

⚽️ ለእግር ኳስ ቡድንዎ ከዋናው ማሊያ በምጣ ለአጭር ጊዜ በሚቆየው ዋጋ በ #699 ብር ፦

👉🏾 ከ20 ብዛት ጀምሮ ሲገዙ ተጨማሪ 2 ባለኮሌታ ቲ-ሸርቶችን በነፃ ያገኛሉ።
👉🏾 ከ 50 ብዛት ጀምሮ ሲገዙ 5 ባለኮሌታ ቲ-ሸርቶችን እና 1 ባንዲራን በነፃ እንሰጥዎታለን።
👉🏾 ከ100 ብዛት ጀምሮ ሲገዙ ደግሞ 1 Molten 1ኛ ደረጃ ኳስ እና 1 ባንዲራን በነፃ የሚያገኙ ይሆናል።

🔥 #እንዳያመልጥዎ፣ አሁኑኑ ይዘዙን!

📍አድራሻችን:- ገርጂ መብራት ሃይል የካቲት ወረቀት ፊትለፊት፣ አለም ገብሬ ህንፃ፣ 2ተኛ ፎቅ።

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ወይም በቴሌግራም ቦት @WANAWSbot በኩል ይዘዙን።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
ፊፋ የሴቶች የአለም ክለቦች ዋንጫ ሊያዘጋጅ ነው !

የአለም እግርኳስ የበላይ ፊፋ በቀጣይ ለመጀመሪያ ጊዜ የሴቶች የአለም ክለቦች ዋንጫ ውድድር ሊያዘጋጅ መሆኑን አስታውቋል።

የመጀመሪያው የሴቶች የአለም ክለቦች ዋንጫ ውድድር እ.ኤ.አ 2026 ጥር እና የካቲት ወር ላይ እንደሚጀመር እና በየአራት አመቱ እንደሚካሄድ ፊፋ ይፋ አድርጓል።

በመጀመሪያው ውድድር በአለም ላይ የሚገኙ አስራ ስድስት ክለቦች ተሳታፊ እንደሚሆኑ የተገለፀ ሲሆን ክለቦቹ በምን መልኩ ተለይተው ወደ ውድድሩ እንደሚያመሩ አልተነገረም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የፕርሚየር ሊግ የዝውውር መስኮት መቼ ይከፈታል ?

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የ2024/25 የውድድር አመት የክረምት እና የጥር የዝውውር መስኮት የሚከፈትበት ቀን ይፋ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት የክረምቱ የዝውውር መስኮት ሐሙስ ሰኔ 6/2016 ዓ.ም ተከፍቶ አርብ ነሀሴ 24/2016 ዓ.ም እንደሚዘጋ ይፋ ሆኗል።

በተጨማሪም የጥር የዝውውር መስኮት ሐሙስ ጥር 22/2017 ዓ.ም ተከፍቶ ሰኞ የካቲት 26/2017 ዓ.ም እንደሚዘጋ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቼልሲ ከማድሪድ የጉርሻ ክፍያ እንደሚያገኝ ተገለፀ !

ሪያል ማድሪድ ለአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ መድረሱን ተከትሎ የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ አምስት ሚልዮን ፓውንድ የሚደርስ ገንዘብ እንደሚቀበል ተገልጿል።

ሰማያዊዎቹ ከአመታት በፊት ኤደን ሀዛርድን ለሪያል ማድሪድ ሲሸጡ ሎስ ብላንኮዎቹ ለአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ሲደርሱ እንዲከፍሏቸው የተስማሙት የጉርሻ ክፍያ አሁንም አለመጠናቀቁ ተዘግቧል።

ቤልጂየማዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኤደን ሀዛርድ ከሰባት ወራት በፊት ከሪያል ማድሪድ ጋር ያለውን ኮንትራት በስምምነት በማቋረጥ ጫማውን መስቀሉ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/29 08:27:31
Back to Top
HTML Embed Code: