Telegram Web Link
⚽️ የፕሪሚየር ሊጉ የመጨረሻ ጨዋታዎች አጓጊነታቸው ጨምሯል፡፡

👉 ዛሬ ምሽት ቶተንሃም ከማን ሲቲ የሚያደርጉት ተጠባቂ ጨዋታ በኳስ ወዳጆች ዘንድ መነጋገሪያ ሆኗል፡፡ ቶተንሃም ቻምፒየንስ ሊጉን መሳተፍ ይችላል?

🤔 እርስዎስ ምን ይላሉ?

ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ። ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት ይከታተሉ!

የዲኤስቲቪ ዲኮደር በ1,999 ብር ከ1 ወር ነፃ የሜዳ ፓኬጅ ጋር ሁሉንም የኢንግሊዝ ፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎችን ይከታተሉ።

#PremierLeagueOnDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvSelfServiceET
" ለማድሪድ የምባፔ መምጣት ዋንጫ አያረጋግጥለትም "

የስፔን ላሊጋው ፕሬዝዳንት ዣቪየር ቴባስ ሪያል ማድሪድ ኪሊያን ምባፔን ማስፈረሙ የላሊጋውን ዋንጫ በበላይነት ለማሸነፍ ዋስትና እንደማይሆነው ተናግረዋል።

" የኪሊያን ምባፔ ሪያል ማድሪድ መምጣት ዋንጫ የማሸነፍ ዋስትና አይሆንም " ያሉት ፕሬዚዳንቱ ባርሴሎናም ከላሚን ያማል ፣ ፔድሪ እና ጃቪ ጋር ተፎካካሪ ይሆናል ብለዋል።

ስለ ዝውውሩ የተጠየቁት ፕሬዝዳንት ዣቪየር ቴባስ " ኪሊያን ምባፔ ማድሪድን ተቀላቅሏል ማለት ይቻላል ከቀጣይ አመት ጀምሮ ለአምስት አመታት ስፔን ውስጥ እንመለከተዋለን " ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
" ስለ አርሰናል አይመለከተንም ሲቲን ለማሸነፍ እንገባለን " ኩሉሴቭስኪ ስዊድናዊው የቶተንሀም የፊት መስመር ተጨዋች ኩሉሴቭስኪ ቡድናቸው በነገው ተጠባቂ የሊግ ጨዋታ ማንችስተር ሲቲን ለማሸነፍ ወደ ሜዳ እንደሚገባ ገልጿል። እግርኳስ ከተጫወትክ ለማሸነፍ መሆን አለበት በማለት ያስረዳው ተጨዋቹ ስለዚህ ነገ ወደ ሜዳ የምንገባው ማንችስተር ሲቲን ለማሸነፍ ነው ሲል ተደምጧል። " ማንችስተር ሲቲን ካሸነፍነው…
" የቶተንሀም ተጨዋቾች እንደ ደጋፊው አያስቡም "

የቀድሞ የአርሰናል ተጫዋች ዊሊያም ጋላስ በዛሬው የቶተንሀም እና ማንችስተር ሲቲ ጨዋታ የቶተንሀም ተጨዋቾች እንደ ደጋፊው አይነት አስተሳሰብ እንደማይኖራቸው ገልጿል።

ቶተንሀም ከአርሰናል ጋር ትልቅ ባላንጣ እንደሆኑ እናውቃለን ነገርግን ይህ የሚያሳስበው ደጋፊዎችን ብቻ
ነው የተጨዋቾቹን ሀሳብ አይቀይረውም በማለት ዊሊያም ጋላስ ተናግሯል።

" የቶተንሀም ደጋፊዎች አርሰናል ዋንጫ ከሚያሸንፍ ቡድናቸው በሲቲ ተሸንፎ በሻምፒየንስ ሊግ ባይሳተፍ እንደሚመርጡ እናውቃለን ነገርግን ተጨዋቾቹ የተወለዱት ሰሜን ለንደን አይደለም አስተሳሰባቸው ይለያያል።" ዊሊያም ጋላስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዩናይትድ ተጨዋቹ ወደ ሜዳ ይመለሳል !

በጉዳት ምክንያት በዚህ አመት ለቡድኑ ብዙም ግልጋሎት ያልሰጠው አርጀንቲናዊው የማንችስተር ዩናይትድ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ ለጨዋታ ዝግጁ መሆኑ ተገልጿል።

ተጨዋቹ ማንችስተር ዩናይትድ ነገ ከኒውካስል ዩናይትድ ጋር በሚያደርገው ተስተካካይ የሊግ መርሐግብር ወደ ሜዳ እንደሚመለስ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ አረጋግጠዋል።

ለመጨረሻ ጊዜ ከሁለት ወር በፊት ተሰልፎ የተጫወተው ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ በዚህ አመት ለቡድኑ ግልጋሎት የሰጠው በአስራ አንድ ጨዋታዎች ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ለማሸነፍ ሁሉንም መስጠት አለብን " ቴንሀግ

የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ከነገው የኒውካስል ዩናይትድ የሊግ መርሐ ግብር በፊት ከጋዜጠኞች ጋር ቆይታ አድርገዋል።

አሰልጣኙ በቆይታቸው ምን አሉ ?

- " ነገ ከኒውካስል ጋር የምናደርገው በጣም አስፈላጊ ጨዋታ ነው ድሉ ያስፈልገናል ለማሸነፍ ሁሉንም ነገር መስጠት አለብን።

- ብሩኖ ፈርናንዴዝ ብዙ የግብ እድል ይፈጥራል አመቻችቶ ያቀብላል ግብ ያስቆጥራል በጣም እሱ አስፈላጊ ተጨዋቻችን ነው።

- ራስሙስ ሆይሉንድን የገዛነው ለአሁን እና ለወደፊት ነው በዚህ አመት ሶስት ጉዳቶች አጋጥመውታል ነገርግን አስራ አራት ግብ አስቆጥሯል ለወጣት ተጨዋች ትልቅ ቁጥር ይመስለኛል።" ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቡድኖች እኩል ነጥብ ካመጡ በምን ይለያሉ ?

በዘንድሮው የ2023/24 የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ውድድር የዋንጫ ፉክክር ላይ የሚገኙት አርሰናል እና ማንችስተር ሲቲ ሊጉን በአኩል ነጥብ እና ጎል የማጠናቀቅ እድል አላቸው።

ሊጉን በእኩል ነጥብ የሚያጠናቅቁ ክለቦች ሲፈጠሩ አሸናፊው የሚለይባቸው ህጎች የትኞቹ ናቸው ?


- ከሁለት በላይ ክለቦች ሊጉን በእኩል ነጥብ ካጠናቀቁ በቀጣይ ለመለየት የጎል ልዩነት የሚታይ ይሆናል።

- ክለቦቹ ተመሳሳይ የጎል ልዩነት ካላቸው ብዙ ግብ ያስቆጠረው ክለብ የሚለይ ይሆናል።

- ክለቦቹ ያስቆጠሩት ግብ ተመሳሳይ ሆኖ ከተገኘ የክለቦቹ እርስ በእርስ ግንኙነት ውጤት የሚታይ ይሆናል።

- በመቀጠልም በእርስ በእርስ ግንኙነታቸው ከሜዳ ውጪ ብዙ ግብ ያስቆጠረው ክለብ የሚለይ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የአርሰናል ሴት ቡድን በኤምሬትስ ሊጫወት ነው !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ሴቶች ቡድን በሚቀጥለው የውድድር አመት አብዛኛውን የሜዳ ጨዋታዎች በኤምሬትስ ስታዲየም ሊያደርግ መሆኑ ተገልጿል።

የአርሰናል ሴቶች ቡድን ከዚህ በፊት የሜዳ ጨዋታዎቹን በሜዶው ፓርክ የሚያደርግ ቢሆንም በዚህ አመት የተመልካች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ ወደ ኤምሬትስ ስታዲየም ለማዛወር መወሰኑ ተነግሯል።

በዚህ አመት ሁለት ጨዋታዎች ትኬቶች ተሸጠው መጠናቀቃቸውን የገለፀው ክለቡ ቀጣይ አመት ኤምሬትስ ስታዲየምን ዋና ሜዳው ማድረጉ ተጨማሪ ደጋፊዎችን ለመሳብ እንደሚያግዘው ጠቁሟል።

ክለቡ በሚቀጥለው አመት በኤምሬትስ ስታዲየም ስምንት የሴቶች ሱፐር ሊግ እና ሶስት የሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች ለማድረግ ማቀዱን አስታውቋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ጥሩ ስራ እየሰራን ነው " ፖቼቲኖ

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ዋና አሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖ ቡድናቸው ከጨዋታ ጨዋታ እየተሻሻለ እና ጥሩ ስራ እየሰራ መሆኑን ከነገው የብራይተን ጨዋታ በፊት ገልጸዋል።

" በሚቀጥለው የውድድር አመት ስለቡድናችን ወጣትነት እና ስለጉዳት ማውራት አልፈልግም " ያሉት ፖቼቲኖ ጥሩ ባልሆነ ሁኔታ ውስጥ ሆነንም ጥሩ ስራ እየሰራን ነው ብዬ አስባለሁ ብለዋል።

" አስተሳሰባችንን ማጠንከር አለብን የአውሮፓ መድረክ ቦታ እንደምናገኝ ማመን አለብን ዋናው ማመን ነው ቡድኑ ጥሩ እየሰራ ነው ባለፉት ጨዋታ ድንቅ ነው።" ፖቼቲኖ

የነገው የቼልሲ ተጋጣሚ ብራይተን አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዘርቢ በበኩላቸው " ቼልሲ ጥሩ ይጫወታሉ ለአውሮፓ መድረክ መፋለም ይገባቸዋል " በማለት ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ሲቲን ለማሸነፍ ያለንን ሁሉ እንሰጣለን "

የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም የመሐል ሜዳ ተጨዋች ጄምስ ማዲሰን በምሽቱ ጨዋታ ቡድናቸው ማንችስተር ሲቲን ለማሸነፍ ያለውን ሁሉ ለመስጠት መዘጋጀቱን ተናግሯል።

" እኛ እግርኳሱን እናከብራለን ምሽት የምንጫወተው ሲቲን ለማሸነፍ ሁሉንም ነገር በመስጠት ነው " ያለው ማዲሰን ሻምፒየንስ ሊግ የምንገባበት ብቸኛው ተስፋ ቀሪ ሁለት ጨዋታዎችን ማሸነፍ ነው ብሏል።

ቡድናቸው ማንችስተር ሲቲን ካሸነፈ አርሰናል ስለመጠቀሙ ደጋፊዎች ይነጋገሩበት እኛ ተጨዋቾችን አይመለከትም ሲል ማዲሰን አክሎ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የሴካፋ ካጋሜ ካፕ ውድድር ሊካሄድ ነው !

በሴካፋ አባል ሀገራት የውድድር አሸናፊ ክለቦች መካከል የሚደረገው የሴካፋ ካጋሜ ካፕ ውድድር በቀጣይ ሐምሌ ወር በታንዛኒያ አዘጋጅነት ሊካሄድ መሆኑ ይፋ ተደርጓል።

በውድድሩ ሀገራችን ኢትዮጵያን ጨምሮ የአስራ ሁለት የሴካፋ አባል ሀገራት አሸናፊ ክለቦች እንዲሁም አራት ተጋባዥ ክለቦች እንደሚሳተፉ ተገልጿል።

ይህም ማለት የዘንድሮው የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አሸናፊ ክለብ ኢትዮጵያን ወክሎ በውድድሩ ተሳታፊ የሚሆን ይሆናል።

ላለፉት አመታት ተቋርጦ የነበረው ውድድሩ በታንዛንያ አዘጋጅነት ከሐምሌ 13 /2016 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 28/2016 ዓ.ም እንደሚካሄድ ይፋ ሆኗል።

የሴካፋ የክለቦች ካጋሜ ካፕ ውድድር ለመጨረሻ ጊዜ የተደረገው ከሶስት አመት በፊት 2021 ታንዛኒያ ዳሬ ሰላም ከተማ እንደነበር ይታወሳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ብራይተን የተጨዋቾቹን ውል አራዘመ !

በአሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዘርቢ የሚመራው ብራይተን የተጨዋቾቹ ጄምስ ሚልነር እና ዳኒ ዌልቤክን ኮንትራት ለተጨማሪ አመታት ማራዘማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ጄምስ ሚልነር ለተጨማሪ አንድ አመት ውሉን ሲያራዝም ዳኒ ዌልቤክ የሁለት አመት ኮንትራት መፈረሙ ይፋ ሆኗል።

አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዘርቢ ስለተጫዋቾቹ ሲናገሩ " የእነሱ የእግርኳስ ተጨዋችነት ጥራት በግልጽ የሚታይ ነው እንደግለሰብም ጥሩ ናቸው ውላቸውን ማራዘማቸው ለእኛ ጥሩ ዜና ነው " ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from Post Bot
ሄኒከን የተለያዩ አጓጊ የሆኑ ሽልማቶችን አዘጋጅቶ በየሳምንቱ እጅ ከስጦታ ይሎታል።
እርስዎሰ ባለ እድል ለመሆን ምን ይጠብቃሉ?
ይምጡ ሊንኩን በመከተል ይቀላቀሉ የቀረቡ ጥያቄዎችን በመመለስ ሰጦታዎችን የግልዎ ያድርጉ።

@HNKQuizBot

መልካም እድል!
Forwarded from WANAW SPORT
🎁 በድጋሚ #ይገምቱ#ይሸለሙ! 🎁

🇬🇧 የዛሬውን ምሽት ወሳኝ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ማን ያሸንፍ ይሆን?

🇬🇧ቶተንሃም ወይስ ማንቺስተር ሲቲ 🇬🇧

💬 ግምትዎን በቴሌግራም ገፃችን (https://www.tg-me.com/wanawsportwear) ኮሜንት ላይ ብቻ ያስቀምጡልን!

⚠️ የውድድሩ ህጎች፦
👉🏾 የጨዋታውን አሸናፊ ክለብ እስከ የግብ መጠኑ #በትክክል ቀድመው የሚገምቱ #3 ተከታታዮቻችን የዋናውን የጂም ማልያዎች ይሸለማሉ።
👉🏾 የዋናውን ማህበራዊ ገፆች መከተል፣ መወዳጀትና ማጋራት አይዘንጉ።
👉🏾 የተስተካከሉ መልሶች ተቀባይነት የላቸውም።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ብሩኖ ፈርናንዴዝ በዩናይትድ ቤት ይቆያል !

ፖርቹጋላዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ብሩኖ ፈርናንዴዝ ባለፈው ሳምንት በማንችስተር ዩናይትድ የወደፊት ቆይታው ዙሪያ ከክለቡ ጋር ለንግግር ተቀምጦ እንደነበር ተገልጿል።

ማንችስተር ዩናይትድ ብሩኖ ፈርናንዴዝን በቀጣይ በክለቡ የማቆየት ፍላጎት እንዳላቸውና እንዲለቅ እንደማይፈልጉ መግለፃቸው ተነግሯል።

ብሩኖ ፈርናንዴዝ በበኩሉ በማንችስተር ዩናይትድ ቤት የመቀጠል ፍላጎት እንዳለው ለክለቡ ማረጋገጡ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#PremiereLeague 🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿

ቶተንሀም ከማንችስተር ሲቲ ጋር በሜዳው ያደረጋቸውን ያለፉት አራት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች ምንም ግብ ሳይቆጠርበት ሁሉንም በአሸናፊነት መወጣት ችለዋል።

ማንችስተር ሲቲ በአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ስር ከየትኛውም ክለብ በላይ በቶተንሀም ስድስት የፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ተሸንፏል።

ቶተንሀም ባለፉት ሶስት አመታት ካደረጋቸው የሊጉ የመጨረሻ የሜዳ ጨዋታዎች በሁለቱ ሲሸነፍ በአንዱ አቻ ተለያይቷል።

ማንችስተር ሲቲ በቶተንሀም ስታዲየም ካደረጋቸው ሀያ ስድስት ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው በስድስቱ ብቻ ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

4:00 ቶተንሀም ከ ማንችስተር ሲቲ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ይህ ስታዲየም ሁልጊዜ አስቸጋሪ ነው " ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ከደቂቃዎች በኋላ ጨዋታቸውን የሚያደርጉበት የቶተንሀም ስታዲየም ሁልጊዜ አስቸጋሪ መሆኑን ተናግረዋል።

ቶተንሀምን በዚህ ስታዲየም መግጠም ሁልጊዜም አስቸጋሪ እንደሆነብን ነው እነሱ ጥራት አላቸው በማለት የተናገሩት ፔፕ ጋርዲዮላ ሁሉም ተመልክቶታል የተደበቀ አይደለም ብለዋል።

አሰልጣኝ አንሄ ፖስቴኮግሉ በበኩላቸው " በቻልነው መጠን ጨዋታውን ለማንችስተር ሲቲ ከባድ ለማድረግ እንሞክራለን ጫና ለማሳደር ጥረት እናደርጋለን ቡድኑ ማሸነፍ ይፈልጋል " ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ተጀመረ

ቶተንሀም 0 - 0 ማንችስተር ሲቲ

- ቶተንሀም በ 4-3-3 የጨዋታ አሰላለፍ ወደ ሜዳ ሲገቡ ማንችስተር ሲቲዎች 4-2-3-1 በሆነ የጨዋታ አሰላለፍ ጨዋታውን ጀምረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የእረፍት ሰዓት !

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ተስተካካይ መርሐ ግብር ቶተንሀም ከማንችስተር ሲቲ ጋር እያደረጉ የሚገኙትን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት ወደ መልበሻ ቤት አምርተዋል።

- በመጀመሪያው አጋማሽ በቶተንሀም በኩል ቤንታንኩር የማስጠንቀቂያ ካርድ ተመልክቷል።

የጨዋታው የኳስ ቁጥጥር ምን ይመስላል ?

- በመጀመሪያው አጋማሽ ቶተንሀም 55% - 45% የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ነበራቸው።

- ሁለቱ ክለቦች በመጀመሪያው አጋማሽ አንድ ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ ማድረግ ችለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/29 06:28:03
Back to Top
HTML Embed Code: