መድፈኞቹ ሽንፈት አስተናግደዋል !
የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ከኒውካስል ጋር ያደረገውን የካራባኦ ካፕ ግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።
የኒውካስል ዩናይትድን የማሸነፊያ ግቦች አሌክሳንደር አይሳክ እና አንቶኒ ጎርደን ከመረብ አሳርፈዋል።
ሁለቱ ቡድኖች የካራባኦ ካፕ ግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታቸውን ከአንድ ወር በኋላ በኒውካስሉ ሴንት ጄምስ ፓርክ የሚያደርጉ ይሆናል።
አርሰናል ከአስራ ሶስት ጨዋታዎች ያለመሸነፍ ጉዞ በኋላ ሽንፈት አስተናግደዋል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe

ታላቅ የገና ስጦታ እስከ ጥር 4 የሚቆይ ቅናሽ
Exchange Available (ባሎት PlayStation ላይ ጨምረው መቀየር ይችላሉ)
Ps4 Slim NEW
Republish south korea
2 Orginal jestic
5 Game installed
<Fc25
<Batman
<rocket league
<Formula one
<EA football 25 installed
Storage 500gb
Version 12:00
Full accessories
1 years guarantee
ዋጋ=43,000
አድራሻ፦
ቁጥር 1 መገናኛ ሱቅ የአድራሻ ለውጥ በቅርቡ ስለምናደርግ ከመምጣቶ በፊት አስቀድመው ይደውሉ
ቁጥር 2 ቦሌ Celavi burger አጠገብ ዘንባባ ህንፃ ምድር ላይ
ስልክ፦ 0910529770 ወይም 0977349492
0914646972 ይደውሉ
Telegram channel ፦
https://www.tg-me.com/CanPlaystation
👍Update Your Life

“ ኳሷ ⚽ ከሊጉ የተለየች ነበረች “ አርቴታ
⏩ “ እንደምናልፍ ሙሉ እምነት አለኝ “
የመድፈኞቹ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቡድናቸው ትላንት ቢሸነፍም ኒውካስል ዩናይትድን በሜዳው አሸንፎ ለፍፃሜ መድረስ እንደሚችል ገልጸዋል።
አሰልጣኙ አክለውም ቡድኑ በካራባኦ ካፕ ጥቅም ላይ እየዋለች የምትገኘውን ኳስ በደንብ መላመድ እንዳለበት አሳስበዋል።
ሚኬል አርቴታ በንግግራቸውም “ ኒውካስልን በሜዳው ሄደን በማሸነፍ ለፍፃሜ መድረስ እንደምንችል ሙሉ እምነት አለኝ “ ሲሉ ተናግረዋል።
በምሽቱ ጨዋታ ጥቅም ላይ የዋለውን ኳስ አንዱ የሽንፈቱ ምክንያት አድርገው ያነሱት አርቴታ “ በካራባኦ ካፕ ያለው ኳስ ከሊጉ ኳስ ፍፁም የተለየ ነው “ ብለዋል።
አሰልጣኙ አክለውም “ የካራባኦ ካፑ ኳስ በተለየ መልኩ ነው የሚንቀሳቀሰው “ ያሉ ሲሆን " በመልሱ ጨዋታ በደንብ መላመድ አለብን " ሲሉ አሳስበዋል።
በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ አገልግሎት ላይ የሚውለው የመጫወቻ ኳስ ከናይኪ እንዲሁም የካራባኦ ካፕ ኳስ የፑማ ስሪት መሆናቸው ተገልጿል።

" የመጣነው ለማሸነፍ ነበር " አይሳክ
የኒውካስል ዩናይትዱ የፊት መስመር ተጨዋች አሌክሳንደር አይሳክ ቡድናቸው ትላንት ወደ ኤምሬትስ ያቀናው ጥሩ ውጤት ለመውሰድ እንደነበር ገልጿል።
“ ወደዚህ የመጣነው ጥሩ ውጤት ይዘን ለመመለስ በማሰብ ነው ያንን አድርገነዋል በሜዳችን ተመሳሳይ ነገር ማድረግ እንፈልጋለን “ ሲል አይሳክ ተናግሯል።
አንቶኒ ጎርደን በበኩሉ “ አይሳክ የአውሮፓ ምርጡ አጥቂ መሆኑን ሁሉም የሚስማማ ይመስለኛል “ ሲል ስለ ቡድን አጋሩ ተናግሯል።

ዲዲዬ ዴሻምፕ ውላቸውን አያራዝሙም !
የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ዲዲዬ ዴሻምፕ በብሔራዊ ቡድኑ ያላቸውን ውል ላለማራዘም ማሰባቸው ተገልጿል።
ይህንንም ተከትሎ አሰልጣኝ ዲዲዬ ዴሻምፕ ከ 2026 አለም ዋንጫ ውድድር በኋላ ከፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ጋር እንደሚለያዩ ተነግሯል።
ብሔራዊ ቡድኑን ላለፉት አስራ ሶስት አመታት በሀላፊነት የመሩት አሰልጣኝ ዲዲዬ ዴሻምፕ አንድ የአለም ዋንጫ አሳክተዋል።

ዩናይትድ የአካዳሚ ተጨዋቾቹን ሊሸጥ ይችላል !
ማንችስተር ዩናይትድ የገጠመውን የፋይናንሻል ፌር ፕሌይ ችግር ለማስተካከል የአካዳሚ ተጨዋቾቹን ሊሸጥ እንደሚችል ተገልጿል።
ክለቡ ችግሩን ለማስተካከል አሌሀንድሮ ጋርናቾ እና ኮቢ ማይኖን ለመሸጥ ሊያስብ እንደሚችል ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።
ቀያዮቹ ሴጣኖች አሁን ላይ ተጨዋቾቹን ለመሸጥ እንቅስቃሴ ለማድረግ ባያስቡም ጥሩ የዝውውር ሒሳብ ከቀረበ ለመሸጥ ማሰባቸው ተነግሯል።
ክለቡ ጥሩ ሒሳብ ከቀረበ የአካዳሚ ተጨዋቾቹን ለመሸጥ ያስቀመጠው እቅድ ማርከስ ራሽፎርድንም እንደሚመለከት ተዘግቧል።

ናይጄሪያ አዲስ አሰልጣኝ ሾመች !
የናይጄሪያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለብሔራዊ ቡድኑ አዲስ አሰልጣኝ በሀላፊነት መሾሙን በይፋ አስታውቋል።
የናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞውን የማሊ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ኤሪክ ቼሌ በሀላፊነት መሾማቸው በይፋ ተገልጿል።
የ 47ዓመቱ አሰልጣኝ ኤሪክ ቼሌ የናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድንን ለ 2026 አለም ዋንጫ ውድድር የማሳለፍ ስራ እንደተቀበለ ተነግሯል።
ዘ ሱፐር ኤግል በሚል ቅፅል ስም የሚታወቀው የናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን በአለም ዋንጫ ማጣሪያው ያደረጋቸውን አራት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም።
ብሔራዊ ቡድኑ በሶስት ነጥቦች በምድቡ አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ማርከስ ራሽፎርድ ወደ ኤሲ ሚላን ?
የማንችስተር ዩናይትዱ የፊት መስመር ተጨዋች ማርከስ ራሽፎርድ ከሴርያው ክለብ ኤሲ ሚላን ጋር ንግግር ማድረጉ ተገልጿል።
የማርከስ ራሽፎርድ ወኪል እና ወንድም ወደ ጣልያን ሚላን ማምራታቸው ሲገለፅ በውሰት ዝውውር ዙሪያ ከኤሲ ሚላን ጋር መነጋገራቸው ተነግሯል።
በቀጣይ ቀናት ደግሞ ወደ ጀርመን በማምራት ከቦርስያ ዶርትመንድ ጋር ለንግግር እንደሚቀመጡ ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።
ማርከስ ራሽፎርድ በተከፈተው የዝውውር መስኮት ክለቡን እንደሚለቅ ሲጠበቅ ኤሲ ሚላን ፣ ጁቬንቱስ እና ዶርትመንድ ተጫዋቹን ፈላጊ ክለቦች ናቸዉ።

ቪኒሰስ ጁኒየር የሁለት ጨዋታ ቅጣት ተጣለበት !
ብራዚላዊው የሪያል ማድሪድ የፊት መስመር ተጨዋች ቪኒሰስ ጁኒየር ከቀናት በፊት ቡድኑ ከቫሌንሽያ ባደረገው ጨዋታ ቀይ ካርድ መመልከቱ ይታወሳል።
ቪኒሰስ ጁኒየር አሁን ላይ በተመለከተው ቀይ ካርድ ምክንያት የሁለት ጨዋታዎች ቅጣት እንደተጣለበት ተገልጿል።
ተጨዋቹ በቀጣይ ሪያል ማድሪድ ከላስ ፓልማስ እና ቫላዶሊድ ጋር የሚያደርጋቸው የላሊጋ ጨዋታዎች የሚያመልጡት ይሆናል።
በተጨማሪም ሪያል ማድሪድ 700 ዩሮ እንዲሁም ቪኒሰስ ጁኒየር የ 600 ዩሮ የገንዘብ ቅጣት እንደተጣለባቸው ተገልጿል።
ሎስ ብላንኮዎቹ በቀጣይ ቪኒሰስ ጁኒየር ላይ የተጣለው ቅጣት ተገቢ አይደለም በሚል ይግባኝ እንደሚጠይቁ ተነግሯል።

TIKVAH-SPORT
ዲዲዬ ዴሻምፕ ውላቸውን አያራዝሙም ! የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ዲዲዬ ዴሻምፕ በብሔራዊ ቡድኑ ያላቸውን ውል ላለማራዘም ማሰባቸው ተገልጿል። ይህንንም ተከትሎ አሰልጣኝ ዲዲዬ ዴሻምፕ ከ 2026 አለም ዋንጫ ውድድር በኋላ ከፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ጋር እንደሚለያዩ ተነግሯል። ብሔራዊ ቡድኑን ላለፉት አስራ ሶስት አመታት በሀላፊነት የመሩት አሰልጣኝ ዲዲዬ ዴሻምፕ አንድ የአለም ዋንጫ አሳክተዋል።…
ዲዲዬ ዴሻምፕ ከፈረንሳይ ጋር ይለያያሉ !
የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ዲዲዬ ዴሻምፕ ከ 2026 አለም ዋንጫ ውድድር በኋላ በሀላፊነት እንደማይቀጥሉ በይፋ አስታውቀዋል።
የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድንን ለ 1️⃣3️⃣ አመታት በሀላፊነት የመሩት አሰልጣኝ ዲዲዬ ዴሻምፕ ውላቸው ሲጠናቀቅ እንደማይቀጥሉ አረጋግጠዋል።
አሰልጣኝ ዲዲዬ ዴሻምፕ በፈረንሳይ ምን አሳኩ ?
🏆 የአለም ዋንጫ
🏆ኔሽንስ ሊግ
🥈የአለም ዋንጫ ፣ አውሮፓ ዋንጫ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።
በቀጣይ አሰልጣኝ ዚነዲን ዚዳን የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድንን በሀላፊነት ሊረከብ እንደሚችል በመዘገብ ላይ ይገኛል።

ዌስትሀም የአሰልጣኙን መግለጫ ሰረዘ !
የዌስትሀም ዩናይትድ አሰልጣኝ ጁሊያን ሎፕቲጌ የአስቶን ቪላን ጨዋታ አስመልክቶ ዛሬ ጠዋት ሊሰጡት የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ መሰረዙ ተገልጿል።
ስፔናዊው አሰልጣኝ ጁሊያን ሎፕቲጌ በዌስትሀም ዩናይትድ ያላቸው የወደፊት ቆይታ እንዳልተረጋገጠ ተነግሯል።
በሌላ በኩል ዌስትሀም ዩናይትድ በአሁን ሰዓት የአሰልጣኝ ለውጥ ለማድረግ በማሰብ ላይ መሆናቸው እየተዘገበ ይገኛል።
በቀጣይ ዌስትሀም ዩናይትድን ለመረከብ ንግግር ላይ የሚገኙት የቀድሞ የብራይተን እና ቼልሲ አሰልጣኝ ግራም ፖተር መሆናቸው ተዘግቧል።

Forwarded from WANAW SPORT (Wanaw Sportswear)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Betika Ethiopia Official Channel
የቤቲካ የገና ስጦታ ተመልሷል!
ጨምሯል፣አድጓል፣ያንበሸብሻል!!
በየሳምንቱ ጓደኞቻችሁን በዕለተ ሰኞ በምንለቀው የፌስቡክ ፖስታችን ስር ታግ ያድርጉ፣ ይሸለማሉ!
በየሳምንቱ 5 አሸናፊዎች!
በየሳምንቱ ስማርት ስልክክክክክ እንዲሁም በመጨረሻም ለ2 ደንበኞች የ50,000 ብርርርር ሽልማት!! ሌሎችም ብዙ ስጦታዎች ከቤቲካ!
ለዚህ ሳምንት ፣ በየፌስቡክ ፖስታችን ስር ብቻ ያሉ ታግ የተደረጉ ቁጥሮች የሚመዘገቡ ይሆናል!
አሁኑኑ https://web.facebook.com/BetikaET ላይታግ ያድርጉ!
ቤቲካ የአሸናፊዎች ቤት!

“ እንደ ሳላህ አይነት ተጨዋች አላየሁም “ ሮድሪ
ስፔናዊው የማንችስተር ሲቲ ተጨዋች ሮድሪ መሐመድ ሳላህ የተለየ ተጨዋች መሆኑን በሰጠው አስተያየት ገልጿል።
" እንደ መሐመድ ሳላህ አይነት ተጨዋች አላየሁም " የሚለው ሮድሪ እሱ እንደ መፋለሚያ መሳሪያ ነው በማለት ተናግሯል።
ሮድሪ አክሎም " መሐመድ ሳላህ እንደ ኔይማር እና ቪኒሰስ በተሰጥኦ የተካነ አይደለም ነገርግን ግቦችን አስቆጥሮ የግብ እድልም ይፈጥራል “ ሲል ተደምጧል።
በእግርኳስ ህይወቱ የተፈተነበት የማንችስተር ሲቲ የመጀመሪያ አመቱ እንደነበር የገለፀው ሮድሪ “ ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ ድንቅ የነበረው የሊቨርፑል ቡድን ነው " ብሏል።

የኮፓ ዴላሬ ተጋጣሚዎች ተለይተዋል !
የስፔን ኮፓ ዴላሬ አስራ ስድስቱን የተቀላቀሉ ክለቦች የጥሎ ማለፍ ተጋጣሚዎቻቸውን አውቀዋል።
በዚህም መሰረት :-
⏩ ሪያል ማድሪድ ከ ሴልታ ቪጎ
⏩ ባርሴሎና ከ ሪያል ቤቲስ
⏩ ኤልቼ ከ አትሌቲኮ ማድሪድ ጋር ተደልድለዋል።
ሙሉ መርሐግብር ከላይ በምስሉ ተያይዟል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
የስፔን ኮፓ ዴላሬ አስራ ስድስቱን የተቀላቀሉ ክለቦች የጥሎ ማለፍ ተጋጣሚዎቻቸውን አውቀዋል።
በዚህም መሰረት :-
⏩ ሪያል ማድሪድ ከ ሴልታ ቪጎ
⏩ ባርሴሎና ከ ሪያል ቤቲስ
⏩ ኤልቼ ከ አትሌቲኮ ማድሪድ ጋር ተደልድለዋል።
ሙሉ መርሐግብር ከላይ በምስሉ ተያይዟል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe
ባሕርዳር ከተማ የሊጉን መሪነት ተረከበ !
በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አስራ ሶስተኛ ሳምንት መርሐግብር ባሕርዳር ከተማ ከሀዋሳ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።
የባሕር ዳር ከተማን የማሸነፊያ ግብ ጄሮም ፊሊፕ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።
የጣና ሞገዶቹ ማሸነፋቸውን ተከትሎ በግብ ክፍያ በልጠው የሊጉን መሪነት መረከብ ችለዋል።
ሀዋሳ ከተማ ያለፉትን ስምንት የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻሉም።
ባሕርዳር ከተማ ያለፉትን ስምንት ጨዋታዎች አልተሸነፉም።
የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?
1️⃣ ባሕርዳር ከተማ :- 22 ነጥብ
1️⃣7️⃣ ሀዋሳ ከተማ :- 10 ነጥብ

#SpainSuperCup 🇪🇸
ባለፉት ሶስት አመታት በሳውዲ አረቢያ ሪያድ ሲካሄድ የቆየው የስፔን ሱፐር ካፕ ውድድር ዘንድሮ የቦታ ለውጥ በማድረግ በጄዳህ ከተማ ይካሄዳል።
የስፔን ሱፐር ካፕ ውድድር የዚህን አመት ጨምሮ በሳውዲ አረቢያ ሲካሄድ ይህ ለአራተኛ ጊዜ መሆኑ ተዘግቧል።
ውድድሩ በሳውዲ አረቢያ ጄዳህ ከተማ በሚገኘው ንጉሥ አብደላህ ስታዲየም ከዛሬ ጀምሮ በሚቀጥሉት ቀናት ይካሄዳል።
የጨዋታ መርሐ ግብሩ ምን ይመስላል ?
⏩ ዛሬ ምሽት 4:00 - ባርሴሎና ከ አትሌቲክ ቢልባኦ
⏩ ነገ ምሽት 4:00- ሪያል ማድሪድ ከ ማዮርካ
⏩ የፍፃሜ ጨዋታ እሁድ ምሽት 4:00
በስፔን ሱፐር ካፕ ምን አዲስ ነገር ይኖራል ?
በስፔን ሱፐር ካፕ ውድድር ላይ ለተጨዋቾች የመጫወቻ ሰዓትን ለመቀነስ በማሰብ ተጨማሪ ሰዓት መሰረዙ ይፋ ተደርጓል።
ይህንንም ተከትሎ ጨዋታዎቹ በአቻ ውጤት የሚጠናቀቁ ከሆነ በቀጥታ ወደ መለያ ምት እንደሚያመሩ ይፋ ሆኗል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe

ዌስትሀም የአሰልጣኙን መግለጫ ሰረዘ ! የዌስትሀም ዩናይትድ አሰልጣኝ ጁሊያን ሎፕቲጌ የአስቶን ቪላን ጨዋታ አስመልክቶ ዛሬ ጠዋት ሊሰጡት የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ መሰረዙ ተገልጿል። ስፔናዊው አሰልጣኝ ጁሊያን ሎፕቲጌ በዌስትሀም ዩናይትድ ያላቸው የወደፊት ቆይታ እንዳልተረጋገጠ ተነግሯል። በሌላ በኩል ዌስትሀም ዩናይትድ በአሁን ሰዓት የአሰልጣኝ ለውጥ ለማድረግ በማሰብ ላይ መሆናቸው እየተዘገበ ይገኛል።…
ዌስትሀም ዩናይትድ አሰልጣኙን አሰናበተ !
ዌስትሀም ዩናይትድ ስፔናዊውን አሰልጣኝ ጁሊያን ሎፕቲጌ ከአሰልጣኝነት ማሰናበታቸውን በይፋ አስታውቀዋል።
ጥሩ ያልሆነ የውድድር አመት በማሳለፍ ላይ የሚገኘው ዌስትሀም ዩናይትድ አሰልጣኙን በተመዘገበው ደካማ ውጤት ምክንያት ማሰናበቱ ተገልጿል።
ዌስትሀም ዩናይትድ በቀጣይ አሰልጣኝ የቀድሞ የብራይተን እና ቼልሲ አሰልጣኝ ግራም ፖተርን በሀላፊነት ለመሾም መቃረቡ ተነግሯል።
አሰልጣኝ ጁሊያን ሎፕቲጌ ከአሰልጣኝ ሩሴል ማርቲን ፣ ስቲቭ ኩፐር ፣ ኤሪክ ቴንሀግ እና ጋሪ ኦኔል በመቀጠል አምስተኛው ተሰናባች የፕርሚየር ሊግ አሰልጣኝ ሆነዋል።