Telegram Web Link
TIKVAH-SPORT
የዋልያዎቹ ተጋጣሚ ስብስቧን አሳውቃለች ! የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ሶስተኛ እና አራተኛ ጨዋታዋን ከኢትዮጵያ ጋር የምታደርገው ጊኒ ስብስቧን ይፋ አድርጋለች። በቅርቡ ብሔራዊ ቡድኑን የተረከቡት አሰልጣኝ ሚሼል ዱሱዬር የሴልታ ቪጎውን አማካይ ኢላክስ ሞሪባ ለቡድኑ ጥሪ ሳያቀርቡለት ቀርተዋል። የኢትዮጵያ እና ጊኒ ጨዋታዎች :- ጥቅምት 2/2017 ዓ.ም እና ጥቅምት 5/2017 ዓ.ም በአይቮሪኮስት…
ዋልያዎቹ ስብስባቸውን አሳውቀዋል !

ለሞሮኮው የአፍሪካ ዋንጫ ከጊኒ አቻው ጋር የደርሶ መልስ ጨዋታ ያለበት የ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ስብስቡን ይፋ አድርጓል።

በአሰልጣኝ ገብረ መድህን ሀይሌ የሚመራው ብሔራዊ ቡድኑ ለሀያ ሶስት ተጫዋቾች ጥሪ አቀርበዋል።

ሀያ ተጫዋቾች ከሀገር ውስጥ ሲመረጡ ሶስት ተጫዋቾች:-

- ሱራፌል ዳኛቸው
- አቤል ያለው እና
- ከንአን ማርክነህ ከሀገር ውጪ እየተጫወቱ ጥሪ የቀረበላቸው ተጫዋቾች ሆነዋል።

ዋልያዎቹ በማጣርያው በአንድ ነጥብ ሶስተኛ ላይ ሲገኙ ጊኒ ያለምንም ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች የደርሶ መልስ ጨዋታ በኮትዲቯር አቢጃን ከተማ የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የፕርሚየር ሊግ የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ማን ይሆናል ?

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የ 2024/25 የውድድር ዘመን የወርሀ መስከረም የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ አምስት እጩዎች ይፋ ተደርገዋል።

በዚህም መሰረት :-

አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ

አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ

አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ

አሰልጣኝ ማርኮ ሲልቫ

አሰልጣኝ አርኔ ስሎት በእጩነት መቅረብ ችለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሶላንኬ ለብሔራዊ ቡድኑ ጥሪ ይቀርብለታል !

የቶተንሀሙ የፊት መስመር ተጨዋች ዶምኒክ ሶላንኬ ከሰባት አመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ጥሪ ሊቀርብለት መሆኑ ተገልጿል።

ዶምኒክ ሶላንኬ ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች ለቶተንሀም ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ጥሩ ጊዜን በማሳለፍ ላይ ይገኛል።

በብሔራዊ ቡድኑ ስብስብ ውስጥ የማንችስተር ዩናይትዱ ተከላካይ ሀሪ ማጓዌር ሳይካተት መቅረቱ ተገልጿል።

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ ከግሪክ እና ፊንላንድ ጋር የኔሽንስ ሊግ ጨዋታዎቹን የሚያደርግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
💥ማን ዩናይትድ ከ ቶተንሃም 0-3 ሸንፈት በኋካ ዛሬ ምሽት ወደ ፖርቹጋል ተጉዞ ከፖርቶ ጋር ይጫወታል!

ዩናይትድ ወደ አሸናፊነት መንገድ ይመለሳል?

👉 ዛሬውኑ ፓኬጅዎን ያሳድጉ ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሜዳ ፕላስ ፓኬጅ ይከታተሉ!

ደንብና ሁኔታዎች ተፈፀሚነት አላቸው! ለበለጠ መረጃ
👇
www.dstv.com/en-et

ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

#ChampionsLeagueAllonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvSelfServiceET
Forwarded from WANAW SPORT
📞 ዋናው ብለው ይደውሉ፣ በቀላሉ ይዘዙን! 📞

8⃣2⃣8⃣9⃣#ዋናው!

Instagram | Facebook | TikTok

🏅ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
ፈረንሳይ ስብስቧን አሳውቃለች !

የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ ላለበት የኔሽንስ ሊግ ጨዋታ አሰልጣኝ ዲዲዬ ዴሻምፕ ለተጨዋቾች ጥሪ አቅርበዋል።

በስብስቡ ውስጥ ከጉዳት የተመለሰው የብሔራዊ ቡድኑ አምበል ኪሊያን ምባፔ ሳይካተት ቀርቷል።

ንጎሎ ካንቴ ፣ ፌርላንድ ሜንዲ እና አድሪያን ራቢዮ በስብስቡ ውስጥ ያልተካተቱ ሌሎች ተጨዋቾች ናቸው።

ፈረንሳይ በቀጣይ ከእስራኤል እና ቤልጅየም ጋር የኔሽንስ ሊግ ጨዋታዋን የምታደርግ ይሆናል።

የቡድን ስብስቡ ከላይ በምስሉ ተያይዟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አልቫሮ ሞራታ መኖሪያውን ለመቀየር ተገዷል !

ስፔናዊው የኤሲ ሚላን ተጨዋች አልቫሮ ሞራታ ጣልያን ውስጥ ከሚኖርበት ስፍራ በከተማዋ ከንቲባ ንግግር ምክንያት ለመቀየር መገደዱን ገልጿል።

ሞራታ ጣልያን ውስጥ ፀጥታ የሰፈነበት ስፍራ በመፈለግ ከሚላን ወጣ ባለች አነስተኛ ከተማ ለመኖር ወስኖ እንደነበር ተነግሯል።

ይሁን እንጂ የከተማዋ ከንቲባ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው “ ሻምፒዮኑ አልቫሮ ሞራታ በእኛ ከተማ ለመኖር መርጧል “ ብለው ይፋ አድርገዋል።

አልቫሮ ሞራታ በበኩሉ “ ውድ ከንቲባ የነፃነት መብቴን በማጣቴ ከአሁን በኋላ አዲስ መኖሪያ ቤት ለመፈለግ ተገድጃለሁ “ ሲል ገልጿል።

ከንቲባው በምላሹም የኢንተር ሚላንን አርማ ተጠቅመው “ ቻው “ የሚል መልዕክት አስፍረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የሴርያ የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ታውቋል !

የጣሊያን ሴርያ የ 2024/25 የውድድር ዘመን የወርሀ መስከረም የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ይፋ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት የናፖሊው ዋና አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ የጣልያን ሴርያ የወርሀ መስከረም የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ተብለው መመረጥ ችለዋል።

አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ ናፖሊን እየመሩ የጣልያን ሴርያን በ 13 ነጥቦች በመምራት ላይ ይገኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጃክ ስቴፈንስ ዳኛ መሳደቡን አምኗል !

የሳውዝሀምፕተኑ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ጃክ ስቴፈንስ ዳኞችን በመሳደቡ የተጨማሪ ሁለት ጨዋታዎች ቅጣት እንደተጣለበት ተገልጿል።

ጃክ ስቴፈንስ ቡድኑ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ባደረጉት ጨዋታ ቀይ ካርድ ከተመለከተ በኋላ የጨዋታውን ዳኛ እና አራተኛ ዳኛ ተሳድቧል በሚል ክስ ቀርቦበት ነበር።

ተጨዋቹ ዳኞቹን በአፀያፊ ቃላት መሳደቡን በማመኑ የተጨማሪ ሁለት ጨዋታ እና 50,000 ፓውንድ ገንዘብ ቅጣት እንደተጣለበት ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሶላንኬ ለብሔራዊ ቡድኑ ጥሪ ይቀርብለታል ! የቶተንሀሙ የፊት መስመር ተጨዋች ዶምኒክ ሶላንኬ ከሰባት አመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ጥሪ ሊቀርብለት መሆኑ ተገልጿል። ዶምኒክ ሶላንኬ ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች ለቶተንሀም ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ጥሩ ጊዜን በማሳለፍ ላይ ይገኛል። በብሔራዊ ቡድኑ ስብስብ ውስጥ የማንችስተር ዩናይትዱ ተከላካይ ሀሪ ማጓዌር ሳይካተት መቅረቱ ተገልጿል።…
እንግሊዝ ስብስቧን አሳውቃለች !

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ ላለበት የኔሽንስ ሊግ ጨዋታ የሚጠቀመውን ስብስብ ይፋ አድርጓል።

ዶምኒክ ሶላንኬ ከሰባት አመታት በኋላ ለብሔራዊ ቡድኑ ጥሪ ቀርቦለታል።

ሀሪ ማጓየር ፣ ጄምስ ማዲሰን ፣ ኢዜ እና ጃሮድ ቦውን በስብስቡ ሳይካተቱ ቀርተዋል።

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ ከግሪክ እና ፊንላንድ ጋር የኔሽንስ ሊግ ጨዋታዎቹን የሚያደርግ ይሆናል።

የቡድን ስብስቡ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የዩናይትድ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የሚመሩት ማንችስተር ዩናይትዶች የወርሀ መስከረም የወሩ ምርጥ ተጨዋች #ሶስት እጩዎችን ይፋ አድርገዋል። በዚህም መሰረት :- ክርስቲያን ኤሪክሰን አሌሀንድሮ ጋርናቾ አንድሬ ኦናና የመስከረም ወር የማንችስተር ዩናይትድ ምርጥ ተጨዋች እጩ ሆነው መቅረብ ችለዋል። የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል @ti…
የዩናይትድ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ታውቋል !

በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የሚመሩት ማንችስተር ዩናይትዶች የወርሀ መስከረም የወሩ ምርጥ ተጨዋቻቸውን ይፋ አድርገዋል።

በዚህም መሰረት ካሜሮናዊው ግብ ጠባቂ አንድሬ ኦናና የመስከረም ወር የማንችስተር ዩናይትድ ምርጥ ተጨዋች ተብሎ መመረጥ ችሏል።

አንድሬ ኦናና ከተሰጠው ድምፅ አርባ ሰባት በመቶ የሚሆነውን በማግኘት ማሸነፉ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ንግድ ባንክ አመቱን በድል ጀምሯል !

የአምናው የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አሸናፊ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመጀመሪያ የሊግ ጨዋታውን ከአርባምንጭ ከተማ ጋር አድርጎ 3ለ1 ማሸነፍ ችሏል።

የንግድ ባንክን የማሸነፊያ ግቦች ኪቲካ ጅማ 2x እና ፉአድ ፈረጃ ከመረብ ሲያሳርፉ ለአርባምንጭ ከተማ አህብዋ ብራይን አስቆጥሯል።

የሊግ ደረጃቸው ምን ይመስላል ?

8️⃣ኛ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ :- 3 ነጥብ

1️⃣7️⃣ኛ አርባምንጭ ከተማ :- 1 ነጥብ

ቀጣይ መርሐ ግብር ?

እሁድ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የሊቨርፑል የወሩ ምርጥ ተጨዋች ታውቋል !

በአሰልጣኝ አርኔ ስሎት የሚመራው የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል የወርሀ መስከረም የወሩ ምርጥ ተጨዋቻቸውን ይፋ አድርገዋል።

በዚህም መሰረት ኔዘርላንዳዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሪያን ግራቨንበርች የሊቨርፑል የወርሀ መስከረም የወሩ ምርጥ ተጨዋች በመሆን በአብላጫ ድምፅ መመረጥ ችሏል።

“ የወሩ ምርጥ ሽልማት በማሸነፌ ተደስቻለሁ የመጀመሪያዬ ነው ኮርቻለሁ ድምፅ ለሰጡኝ ደጋፊዎች አመሰግናለሁ “ ሲል ሪያን ግራቨንበርች ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፊፋ አዲስ የዝውውር መስኮት ሊያዘጋጅ ነው !

የአለም እግርኳስ የበላይ ፊፋ በሚቀጥለው ክረምት አዲስ የዝውውር መስኮት ለማስጀመር ማቀዱ ተገልጿል።

አዲሱ የዝውውር መስኮት የሚጀመረው በአዲሱ የአለም ክለቦች ዋንጫ ውድድር የሚሳተፉ ክለቦች ዝውውሮችን እንዲያካሂዱ እንዲያስችላቸው መሆን ተነግሯል።

ይህንንም ተከትሎ የዝውውር መስኮቱ ውድድሩ ከመጀመሩ አምስት ቀናት በፊት ከግንቦት 24 እስከ ሰኔ 3/2017 ዓ.ም እንደሚሆን ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ዩናይትድ የእንግሊዝ ትልቁ ክለብ ነው “ ዲያጎ ኮስታ

የፖርቶው ግብ ጠባቂ ዲያጎ ኮስታ የምሽት ተጋጣሚያቸው ማንችስተር ዩናይትድ የልጅነት ደጋፊ መሆኑን ተናግሯል።

" ዩናይትድ ጥሩ እንደማይጫወት እናውቃለን “ ያለው ዲያጎ ኮስታ “ ነገርግን ማንችስተር ዩናይትድ ማን እንደሆነም እናውቃለን “ ሲሉ ቡድኑ ሊዘናጋ እንደማይገባ አሳስቧል።

“ ለእኔ ማንችስተር ዩናይትድ የእንግሊዝ ትልቁ ክለብ ነው ፣ የተለየ ክለብ ነው ከልጅነቴ ስደግፈው ነበር ጨዋታ ልክ እንደ ሻምፒየንስ ሊግ ነው። “ ዲያጎ ኮስታ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ቅዳሜ ሳንቲያጎ በርናቦ እገኛለሁ “ ቶኒ ክሩስ

በቅርቡ ጫማውን የሰቀለው ጀርመናዊው ተጨዋች ቶኒ ክሩስ ቅዳሜ ሳንቲያጎ በርናቦ ስታዲየም ተገኝቶ የሪያል ማድሪድ እና ቪያሪያልን ጨዋታ እንደሚታደም ገልጿል።

የሪያል ማድሪድ ተጨዋቾች ለማሸነፍ መንገድ መፈለግ አለባቸው ያለው ቶኒ ክሩስ " ክለቡ ጥሩ ተጨዋቾች አሉ ይህንን ማድረግ ይችላሉ “ ብሏል።

የእሱ መልቀቅ ስለፈጠረው ክፍተት ያነሳው ቶኒ ክሩስ “ ሮናልዶ እና ራሞስ ሲለቁ ሪያል ማድሪድ በፍጥነት ተላምዶ ማሸነፉን ቀጥሏል " በማለት ተናግሯል።

“ ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና ራሞስ በጣም አስፈላጊ እና ወሳኝ ተጨዋቾች ነበሩ ነገርግን ያለ እነሱ ሁለት ሻምፒየንስ ሊግ አሸንፈናል አሁንም ተመሳሳይ ነገር ነው የእኔ።“ ቶኒ ክሩስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፎች !

4:00 ፖርቶ ከ ማንችስተር ዩናይትድ ( ዩሮፓ ሊግ )

4:00 ቼልሲ ከ ጄንት ( ኮንፈረንስ ሊግ )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሲዳማ ቡና ድል አድርጓል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሲዳማ ቡና ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የሲዳማ ቡናን የማሸነፊያ ግብ ያሬድ ባየህ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ሶስተኛ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።

የሊግ ደረጃቸው ?

3️⃣ኛ ሲዳማ ቡና :- 6 ነጥብ
1️⃣8️⃣ኛ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ :- ምንም ነጥብ

ቀጣይ መርሐግብር ምን ይመስላል ?

ቅዳሜ ሲዳማ ቡና ከ ኢትዮጵያ መድን

ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርስቲ በቀጣይ መርሐግብር አራፊ ክለብ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/05 05:27:27
Back to Top
HTML Embed Code: