Telegram Web Link
ይህን ቡድን ማሰልጠን መታደል ነው “

የማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርድዮላ ከምሽቱ የሻምፒየንስ ሊግ ድል በኃላ ለቡድናቸው ያላቸውን ፍቅር ገልፀዋል።

“ ይህን ቡድን እወደዋለሁ “ ሲሉ የገለፁት ፔፕ ጋርድዮላ “ የዚህ ቡድን አሰልጣኝ መሆን መታደል ነው “ በማለት ገልፀውታል።

አሰልጣኝ ፔፕ ጋርድዮላ በጨዋታው ኤርሊንግ ሀላንድን የቀየሩት እረፍት ለመስጠት አስበው እንደሆነም ከጨዋታው በኃላ ተናግረዋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
አርሰናል ማሸነፍ ይገባቸዋል “

ትላንት ምሽት በአርሰናል የተሸነፉት ፒኤስጂ አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ ለተመዘገበው ውጤት ሀላፊነት እንደሚወስዱ ተናግረዋል።

በተጋጣሚያቸው የተወሰደባቸውን ብልጫ “ አርሰናል ጫና አድረገው በመጫወት ከኛ የተሻሉ ነበሩ “ ሲሉ “ ለውጤቱ ተጠያቂው እኔ ነኝ “ ብለዋል።

“ በውጤቱ አዝኛለሁ ፣ አርሰናል ማሸነፍ ይገባቸው ነበር “ አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ

ፒኤስጂ ከ 5️⃣1️⃣ ተከታታይ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች በኃላ ግብ ሳያስቆጠሩ ወጥተዋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
2024/10/02 06:25:57
Back to Top
HTML Embed Code: