Telegram Web Link
ዋንጫ የምንበላበት አመት ነው “ ቡካዮ ሳካ

የመድፈኞቹ ኮከብ ተጫዋች ቡካዮ ሳካ የዘንድሮው የውድድር ዓመት ስኬታማ የሚሆኑበት እመት ሊሆን እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል።

“ ራሳችን ላይ ጫና መፍጠር አልፈልግም ግን ዋንጫ የምንመላበት አመት ዘንድሮ ነው ብዬ አስባለሁ “ ቡካዮ ሳካ

ስለ ክለቡ የአጫወወት ዘይቤ ሲጠይቀም “ ለእኛ ዋናው ነገር ውጤት ነው ፣ የምንፈልገው ማሸነፍ ነው “ ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

ቡካዮ ሳካ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ በኤምሬትስ ስታዲየም ባደረጋቸው ስድስት ጨዋታዎች :-

- አምስት ጎል እና
- ሶስት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ይህን ቡድን ማሰልጠን መታደል ነው “

የማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርድዮላ ከምሽቱ የሻምፒየንስ ሊግ ድል በኃላ ለቡድናቸው ያላቸውን ፍቅር ገልፀዋል።

“ ይህን ቡድን እወደዋለሁ “ ሲሉ የገለፁት ፔፕ ጋርድዮላ “ የዚህ ቡድን አሰልጣኝ መሆን መታደል ነው “ በማለት ገልፀውታል።

አሰልጣኝ ፔፕ ጋርድዮላ በጨዋታው ኤርሊንግ ሀላንድን የቀየሩት እረፍት ለመስጠት አስበው እንደሆነም ከጨዋታው በኃላ ተናግረዋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
አርሰናል ማሸነፍ ይገባቸዋል “

ትላንት ምሽት በአርሰናል የተሸነፉት ፒኤስጂ አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ ለተመዘገበው ውጤት ሀላፊነት እንደሚወስዱ ተናግረዋል።

በተጋጣሚያቸው የተወሰደባቸውን ብልጫ “ አርሰናል ጫና አድረገው በመጫወት ከኛ የተሻሉ ነበሩ “ ሲሉ “ ለውጤቱ ተጠያቂው እኔ ነኝ “ ብለዋል።

“ በውጤቱ አዝኛለሁ ፣ አርሰናል ማሸነፍ ይገባቸው ነበር “ አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ

ፒኤስጂ ከ 5️⃣1️⃣ ተከታታይ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች በኃላ ግብ ሳያስቆጠሩ ወጥተዋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
Forwarded from HEY Online Market
Apple M3 Pro 16 inch

🔹14 inches
512GB / 18GB
275,00 ETB

🔸16 inches
512GB / 18GB
349,000 ETB

🔹16 Inches
512GB / 32GB
379,000 ETB

Contact Us
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
የዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዎች !

10:00 ኢትዮጵያ ቡና ከ ሀዋሳ ከተማ

1:00 መቻል ከ ወላይታ ድቻ

4:00 አስቶን ቪላ ከ ባየር ሙኒክ

4:00 ቤኔፊካ ከ አትሌቲኮ ማድሪድ

4:00 ሊል ከ ሪያል ማድሪድ

4:00 ሊቨርፑል ከ ቦሎኛ

4:00 ሌፕዚግ ከ ጁቬንቱስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ በራስ መተማመናችንን ጨምሮታል “ አርቴታ

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የምሽቱ ድል ለቡድናቸው በራስ መተማመን እንደጨመረለት ገልጸዋል።

“ ድሉ የትኛውንም ቡድን ማሸነፍ እንደምንችል እንድናምን እና በራስ መተማመናችን እንዲጨምር አድርጓል ትልቅ እድገት አሳይተናል “ ሲሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ተናግረዋል።

“ በምሽቱ ጨዋታ ተጨዋቾቼ ከአውሮፓ ምርጥ ቡድኖች ጋር ሲጫወቱ የበላይ መሆን እንደሚችሉ ማረጋገጥ ፈልገው ነበር።“ አርቴታ

አሰልጣኙ አያይዘውም ጁሪየን ቲምበርን ከእረፍት በኋላ ቀይረው ያስወጡት መጠነኛ የጉዳት ስሜት ስለነበረው መሆኑን አስረድተዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ በዚህ አመት ስኬታማ እንሆናለን “ ቴንሀግ

የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ቡድናቸው በዚህ የውድድር አመት ስኬታማ እንደሚሆን እርግጠኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።

“ በዚህ አመት ማንችስተር ዩናይትድ ውስጥ ዋንጫ ማሸነፍ እችላለሁ ፤ ስኬታማ የውድድር አመት እንደምናሳልፍ እርግጠኛ ነኝ “ ሲሉ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ተናግረዋል።

“ እሰናበታለሁ የሚል ስጋት የለብኝም “ ሲሉ በድጋሜ ያረጋገጡት ኤሪክ ቴንሀግ ማንችስተር ዩናይትድ ውስጥ ማሸነፍ እንደምንችል ባለፉት አመታት አሳይተናል ብለዋል።

“ በአሰልጣኝነት ህይወቴ ሁልጊዜም ዋንጫ እንደማሸንፍ አረጋግጫለሁ ባለፉት ስድስት አመታት ስምንት ዋንጫዎችን አሸንፌያለሁ።“ ኤሪክ ቴንሀግ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ አዲስ ታሪክ መፃፍ እንፈልጋለን “ ኡናይ ኤምሬ

የአስቶን ቪላው ዋና አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ ቡድናቸው በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር አዲስ ታሪክ መፃፍ እንደሚፈልግ ገልጿል።

አስቶን ቪላ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ያለውን ትልቅ ታሪክ ማስታወስ እንደሚገባ ያነሱት አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ “ ለዚህ ክብር ሲባል “አዲስ ታሪክ መፃፍ እንፈልጋለን “ ብለዋል።

“ ባየር ሙኒክ ለዋንጫ የሚገመት አንዱ ቡድን ነው ምርጡን ቡድን ይዘን እንገባለን የምንፈልገው ፈተና ነው እንደዚህ አይነት ጨዋታዎች እፈልጋለሁ “ ኡናይ ኤምሬ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዩናይትድ ተጨዋቾቹ ልምምድ ሰርተዋል !

ማንችስተር ዩናይትድ ከቀናት በፊት በቶተንሀም ጋር ባደረገው ጨዋታ ጉዳት ያጋጠመው ኮቢ ማይኖ በዛሬው ዕለት ልምምድ ሰርቷል።

በተጨማሪም እንግሊዛዊው ተከላካይ ሀሪ ማጓየር ከጉዳቱ በማገገም ወደ ልምምድ መመለሱ ተገልጿል።

የጭንቅላት ጉዳት ያጋጠመው ሜሰን ማውንት በበኩሉ ልምምድ አለመስራቱ የተገለፀ ሲሆን በነገው የፖርቶ የዩሮፓ ሊግ ጨዋታ መድረሱ አጠራጣሪ መሆኑ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አሊዮ ሲሴ በሀላፊነት እንደማይቀጥሉ ተገለጸ !

የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ አሊዮ ሲሴ በብሔራዊ ቡድኑ ሀላፊነት እንደማይቀጥሉ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

በብሔራዊ ቡድኑ ያላቸው ውል የተጠናቀቀው
አሰልጣኝ አሊዮ ሲሴ የሀገሪቱ እግርኳስ ፌዴሬሽን ኮንታራታቸውን ማራዘም እንደማይፈልግ ተነግሯል።

የሀገሪቱ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከአሰልጣኙ ጋር ላለመቀጠል የወሰነው ባለበት ከፍተኛ ግፊት እና ከደጋፊዎች ጋር ያለው ግኑኝነት በመበላሸቱ መሆኑ ተዘግቧል።

አሰልጣኝ አሊዮ ሲሴ ውሳኔው በውስጥ እንደተነገራቸው ሲገለፅ ፌዴሬሽኑ በቀጣይ ሴኔጋላዊ አሰልጣኝ መሾም ይፈልጋል ተብሏል።

ባለፉት ዘጠኝ አመታት የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድንን የመሩት አሰልጣኝ አሊዮ ሲሴ የ 2022 አፍሪካ ዋንጫን ማሳካታቸው አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ አርሰናልን ከተቀላቀልኩ ወዲህ የተሻለ ተጨዋች ሆኛለሁ “ ሚኬል ሜሪኖ

የመድፈኞቹ አዲስ ፈራሚ ሚኬል ሜሪኖ በአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ መሰልጠን በጀመረ አራት ሳምንታት በራሱ ላይ ትልቅ ለውጥ መኖሩን ገልጿል።

“ አሁን ከአራት ሳምንት በፊት የነበርኩት ተጨዋች አይደለሁም “ የሚለው ሚኬል ሜሪኖ አሁን የበለጠ ጥሩ ተጨዋች ሆኛለሁ በተለየ ደረጃ ላይ ነኝ ብሏል።

" ሜዳ ላይ ብቻ ሳይሆን ልምምድ ቦታ ላይ ጭምር አርሰናል ውስጥ ያለው አስተሳሰብ አስደናቂ ነው " ሚኬል ሜሪኖ

ስፔናዊው አማካይ ሚኬል ሜሪኖ አርሰናልን ከተቀላቀለ ወዲህ ትላንት ምሽት ተቀይሮ በመግባት የመጀመሪያ ጨዋታውን አድርጓል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
🇪🇹 WANAW 🤝 LISCR FC 🇱🇷

⚽️ LIBERIA'S LISCR FC 2024/25 SEASON OFFICIAL KITS FROM WANAW ⚽️

Instagram | Facebook | TikTok

🏅ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
TIKVAH-SPORT
ሼዝኒ ባርሴሎናን ለመቀላቀል ተስማማ ! ፖላንዳዊው የቀድሞ የአርሰናል እና ጁቬንቱስ ግብ ጠባቂ ሼዝኒ በቅርቡ ጓንቱን መስቀሉን ይፋ ቢያደርግም ተመልሶ ለባርሴሎና ለመጫወት ከስምምነት መድረሱ ተገልጿል። የቴር ስቴገንን መጎዳት ተከትሎ ባርሴሎና በምትኩ ሼዝኒን ለአንድ አመት ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ተነግሯል። “ አሁን ላይ ወደ እግርኳስ ተመልሼ ባርሴሎናን ለመቀላቀል በንግግር ላይ ነኝ “…
ባርሴሎና በይፋ ግብ ጠባቂ አስፈረመ !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና የቁጥር አንድ ግብ ጠባቂያቸው ቴር ስቴገንን መጎዳት ተከትሎ አዲስ ግብ ጠባቂ ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ባርሴሎና ፖላንዳዊውን የቀድሞ የአርሰናል እና ጁቬንቱስ ግብ ጠባቂ ሼዝኒ ለአንድ የውድድር አመት ማስፈረማቸውን በይፋ አሳውቀዋል።

ሼዝኒ በቅርቡ ጓንቱን መስቀሉን ይፋ ቢያደርግም በድጋሜ ወደ እግርኳስ ተመልሶ ለባርሴሎና ለመጫወት ፊርማውን አኑሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፒኤስጂ ለያማል ትልቅ ሒሳብ ሊያቀርቡ ነበር !

የፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ ስፔናዊውን ባለተሰጥኦ ተጨዋች ላሚን ያማል ከባርሴሎና ለማስፈረም ከፍተኛ ገንዘብ አዘጋጅተው እንደነበር ተገልጿል።

ፒኤስጂ ላሚን ያማልን ለማስፈረም ያሰበው ኪሊያን ምባፔ ሪያል ማድሪድን ለመቀላቀል ከውሳኔ በደረሰበት ወቅት እንደነበር ተገልጿል።

ፔኤስጂ ላሚን ያማልን ለማስፈረም የአለም ሪከርድ የሆነ 200 ሚልዮን ዩሮ ለማቅረብ አዘጋጅተው እንደነበር የዝውውር ጉዳዮችን የሚከታተለው ጋዜጠኛ ፋብሪዝዮ ሮማኖ ገልጿል።

ይሁን እንጂ ባርሴሎና በላሚን ያማል ያማል ጉዳይ ለመነጋገር እንኳን ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ፒኤስጂ ሒሳቡን በይፋ ሳያቀርብ መቅረቱ ተነግሯል።

ባርሴሎና ላሚን ያማል ቀሪ የሁለት አመት ውል ቢኖረውም 2025 ከመግባቱ በፊት ለረጅም ጊዜ ለማራዘም እንደሚሰሩ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቡናማዎቹ የመጀመሪያ ድላቸውን አሳክተዋል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ከሀዋሳ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የቡናማዎቹን የማሸነፊያ ግቦች ራምኬል ጄምስ ፣ ኮንኮኒ ሀፍዝ እና ዳዊት ሽፈራው ከመረብ ሲያሳርፉ ለሀዋሳ ከተማ ዓሊ ሱሌይማን አስቆጥሯል።

አንድ ቀሪ ጨዋታ ያለው ኢትዮጵያ ቡና የመጀመሪያ ድሉን ሲያሳካ ሀዋሳ ከተማ በበኩሉ የመጀመሪያ ሽንፈቱን አስተናግዷል።

የሊግ ደረጃቸው ?

5️⃣ኛ ኢትዮጵያ ቡና :- 4 ነጥብ

7️⃣ኛ ሀዋሳ ከተማ :- 4 ነጥብ

ቀጣይ መርሐግብር ምን ይመስላል ?

ቅዳሜ ሀድያ ሆሳዕና ከ ሀዋሳ ከተማ

ማክሰኞ ⏩️ ወላይታ ድቻ ኢትዮጵያ ቡና

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዋልያዎቹ ተጋጣሚያቸውን መቼ ያውቃሉ ?

የ 2024 የአፍሪካ ሀገራት የቻን ማጣሪያ ጨዋታዎች ድልድል የሚካሄድበት ቀን ታውቋል።

በዚህም መሰረት የማጣሪያ ተጋጣሚዎች ቀጣይ ሳምንት ማክሰኞ በግብፅ ካይሮ በሚደረግ የእጣ ማውጣት ስነስርዓት የሚለዩ ይሆናል።

የማጣሪያ ውድድሩ በሁለት ዙሮች በደርሶ መልስ መርሐ ግብር እንደሚካሄድ ተገልጿል።

ኢትዮጵያ በውድድሩ ለመሳተፍ በሁለተኛው ዙር ስትሳተፍ በደርሶ መልስ ካሸነፈች ማለፏን የምታረጋግጥ ይሆናል።

የዘንድሮው የቻን ውድድር በኬንያ ፣ ዩጋንዳ እና ታንዛኒያ በጋራ ያዘጋጅቷል።

አዘጋጆቹ በቀጥታ ማለፋቸውን ተከትሎ ከሴካፋ ሀገራት አንድ ኮታ የሚጨመር ሲሆን የውድድሩ ተሳታፊ ሀገራት ከ 18 ወደ 19 ከፍ እንደሚደረጉ ታውቋል።

የማጣሪያ ውድድሩ መቼ ይካሄዳል ?

የመጀመሪያ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታ ከጥቅምት 15-17 ባሉት ቀናት እንዲሁም የመልስ ጨዋታዎች ከጥቅምት 22-24/2017 ባሉት ቀናት ይደረጋል።

የሁለተኛ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታ ከ ታህሳስ 11 - 13 እንዲሁም የመልስ ጨዋታዎች ከታህሳስ 18-20/2017 ባሉት ቀናት ይካሄዳል።

ውድድሩ መቼ ይካሄዳል ?

የ 2024 የቻን አፍሪካ ዋንጫ ውድድር ከጥር 24 እስከ የካቲት 21/2017 ዓ.ም ይካሄዳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/05 11:15:27
Back to Top
HTML Embed Code: