Telegram Web Link
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
ካፍ ከሱፐር ስፖርት ጋር ስምምነት ፈፅሟል !

የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን ( ካፍ ) ከሱፐር ስፖርት ጋር የቴሌቪዥን መብት ስርጭት ስምምነት መፈፀሙን ይፋ አድርጓል።

ስምምነቱ ካፍ የሚያዘጋጃቸውን የአፍሪካ ወንዶች እና ሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ ፣ የካፍ ኮንፌዴሬሽን ካፕ እና የአፍሪካ ሱፐር ካፕ ውድድሮችን የተመለከተ መሆኑ ተገልጿል።

በዘንድሮው የካፍ ሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር ሀገራችን ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሴቶች ቡድን የምትወከል ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዩናይትድ ቴንሀግን ቢያሰናብት ስንት ያወጣል ?

በቅርቡ ውላቸውን ያራዘሙት አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ጥሩ ያልሆነ የውድድር ዘመን ጅማሮ ማድረጋቸውን ተከትሎ በድጋሜ ጫና ውስጥ መግባታቸው እየተነገረ ይገኛል።

ማንችስተር ዩናይትድ በአሁን ሰዓት አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግን ቢያሰናብቷቸው 17.5 ሚልዮን ፓውንድ እንደሚያወጡ ተነግሯል።

ክለቡ አሰልጣኙን ውላቸውን ሳያራዝሙ በፊት ባለፈው ክረምት ቢያሰናብት 10 ሚልዮን ፓውንድ ካሳ መክፈል ይጠበቅበት እንደነበር ተዘግቧል።

ማንችስተር ዩናይትድ በአሁን ሰዓት አሰልጣኙን ለማሰናበት አለማሰቡ ሲገለፅ በቀጣይ የሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች የኤሪክ ቴንሀግን እጣፈንታ እንደሚወስኑ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፊሊፔ ሉዊስ በሀላፊነት ተሾመ !

ብራዚላዊው የቀድሞ የአትሌቲኮ ማድሪድ የመስመር ተጨዋች ፊሊፔ ሉዊስ የብራዚሉ ክለብ ፍላሚንጎ ጊዜያዊ አሰልጣኝ በመሆን መሾሙ ተገልጿል።

ፍላሚንጎ በዛሬው ዕለት አሰልጣኛቸው የነበረውን የቀድሞ የብራዚል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ቲቴ በይፋ አሰናብተዋል።

የ 39ዓመቱ ፊሊፔ ሉዊስ አሰልጣኙን ተከቶ በጊዜያዊነት ቡድኑን እንደሚመራ ተገልጿል።

ፊሊፔ ሉዊስ ከዚህ በፊት የፍላሚንጎን ከ 20ዓመት በታች ቡድን በማሰልጠን ላይ ይገኝ ነበር።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ለንደን የምንሄደው ለማሸነፍ ነው “ ጇ ኔቬስ

ፖርቹጋላዊው የፒኤስጂ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ጇ ኔቬስ ቡድናቸው በነገው የአርሰናል ጨዋታ ማሸነፍ እንደሚፈልግ ገልጿል።

“ አቻ ለመውጣት ወደ ለንደን አንጓዝም “ ያለው ጇ ኔቬስ “  ወደዛ የምንሄደው አርሰናልን ለማሸነፍ ነው ይህ የእኛ ስነልቦና ነው እኛ ፒኤስጂዎች ነን “ በማለት ተናግሯል።

የአርሰናል እና ፒኤስጂ ጨዋታ ነገ ምሽት 4:00 በኤምሬትስ ስታዲየም የሚካሄድ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አርሰናል ተጨዋቾቹ ልምምድ ሰርተዋል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል አዲስ ፈራሚ ሚኬል ሜሪኖ ካጋጠመው የትከሻ ጉዳት በማገገም ልምምድ መስራቱ ተገልጿል።

በተጨማሪም ሪካርድ ካላፊዮሪ እና ቶሚያሱ መድፈኞቹ ከፒኤስጂ ጨዋታ በፊት ባደረጉት የመጨረሻ ልምምድ መሳተፍ ችለዋል።

ቤን ዋይት በበኩሉ በዛሬ የክለቡ መደበኛ የቡድን ልምምድ ላይ ሳይሳተፍ መቅረቱ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መቐለ 70 እንደርታ የመጀመሪያ ድሉን አሳክቷል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር መቐለ 70 እንደርታ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

የመቐለ 70 እንደርታን የማሸነፊያ ግብ ያሬድ ብርሀኑ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ፈረሰኞቹ በውድድር ዘመኑ ሁለተኛ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።

ቀጣይ መርሐ ግብራቸው ምን ይመስላል ?

እሁድ ⏩️  መቐለ 70 እንደርታ ከ መቻል

እሁድ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሳሙኤል ኤቶ በፊፋ ቅጣት ተጣለበት !

የካሜሮን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት እና የቀድሞ ታሪካዊ ተጨዋች ሳሙኤል ኤቶ በፊፋ የጨዋታ እግድ ቅጣት እንደተጣለበት ተገልጿል።

ሳሙኤል ኤቶ የተጣለበት እግድ በቅርቡ በተካሄደው የ 20ዓመት በታች ሴቶች አለም ዋንጫ ውድድር ላይ ያልተገባ ባህሪ አሳይቷል በሚል መሆኑ ተገልጿል።

ይህንንም ተከትሎ ሳሙኤል ኤቶ ለስድስት ወራት የካሜሮን ብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎችን እንዳይታደም መታገዱ ተገልጿል።

በተጨማሪም የሀገሪቱ ክለቦች በሚያደርጓቸው ኢንተርናሽናል ጨዋታዎች ላይ እንዳይታደም መታገዱ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ኦስማን ዴምቤሌ ለምን ከስብስብ ተቀነሰ ? የፒኤስጂው ዋና አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ ፈረንሳዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ኦስማን ዴምቤሌ ኦስማን ዴምቤሌ ከነገው የአርሰናል ጨዋታ ውጪ አድርገዋል። አሰልጣኙ ተጫዋቹን ከስብስባቸው የቀነሱት ከዲሲፕሊን ጋር በተያያዘ መሆኑን የፈረንሳይ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል። ፒኤስጂ ከቀናት በፊት ሬንስን ባሸነፈበት ጨዋታ ኦስማን ዴምቤሌ ከአሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ ጋር…
“ ለቡድኔ የሚበጀውን ስለምፈልግ ነው ያስቀረሁት “ ኤንሪኬ

የፒኤስጂው ዋና አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ ኦስማን ዴምቤሌን ከቡድኑ ስብስብ የቀነሱት ለቡድኑ ጥሩውን በመፈለግ መሆኑን ተናግረዋል።

ከተጨዋቹ ጋር አለመግባባት አለመኖሩን ያስረዱት አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ “ ችግሩ በቡድኑ ያለውን ግዴታ ያለመወጣት ነው “ ብለዋል።

“ በእኔና በደምበሌ መካከል ምንም ፀብ አልበረም ለቡድኔ የሚበጀውን ስለምፈልግ ነው ያስቀረሁት “ ሉዊስ ኤንሪኬ

አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ አያይዘውም ውሳኔያቸውን የክለቡ ሀላፊዎች መደገፋቸውን ገልጸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ፒኤስጂን መግጠም የሚፈልግ ቡድን የለም “ ሀኪሚ

የፒኤስጂው የመስመር ተጨዋች አሽራፍ ሀኪሚ “ እኛን መግጠም የሚፈልግ ቡድን የለም “ ሲል በቡድኑ ጠንካሬ እምነት እንዳለው ገልጿል።

“ በጣም እርግጠኛ ነኝ እኛን መጋፈጥ የሚፈልግ የአውሮፓ ክለብ የለም “ የሚለው አሽራፍ ሀኪሚ በተጨዋቾች መካከል ጠንካራ ግንኙነት አለ ጥሩው ጎናችን ይህ ነው ብሏል።

“ አርሰናል ለመጫወት አስቸጋሪ የሆነ ቡድን ነው ፤ በአዲሱ አቀራረብ ለእኛ በጣም አስፈላጊው ጨዋታ ነው።" አሽራፍ ሀኪሚ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ለጨዋታው ዝግጁ መሆን አለብን “ ዴክላን ራይስ

የመድፈኞቹ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ዴክላን ራይስ ቡድናቸው ለነገው የፒኤስጂ ጨዋታ ዝግጁ መሆን እንዳለበት አሳስቧል።

“ ፔኤስጂ ጥሩ ቡድን ነው “ ሲል የገለፀው ዴክላን ራይስ ለጨዋታው ዝግጁ መሆን ይጠበቅብናል በማለት ተናግሯል።

“ ከዚህ በፊት ከፔኤስጂ ጋር ተጫውተን አናውቅም ስለዚህ ለጨዋታው ጎጉተናል ዝግጅታችን ጥሩ ነው" ሲል ዴክላን ራይስ ጨምሮ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዴብሮይን መቼ ወደ ሜዳ ይመለሳል ?

የማንችስተር ሲቲ ወሳኝ ተጫዋች የሆነው ኬቨን ዴብሮይን በቅርቡ ወደ ሜዳ እንደማይመለስ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ገልጸዋል።

ተጨዋቹ ከጉዳቱ አገግሞ ወደ ሜዳ የሚመለሰው ከብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ እረፍት በኋላ መሆኑን ፔፕ ጋርዲዮላ አረጋግጠዋል።

ይህንንም ተከትሎ ኬቨን ዴብሮይን ማንችስተር ሲቲ ነገ በሻምፒየንስ ሊጉ ከስሎቫን ብራቲስላቫ እንዲሁም በሊጉ ከፉልሀም የሚያደርጉት ጨዋታ የሚያመልጠው ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EthPL 🇪🇹

በ 2017 የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ መድን ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ቀጣይ መርሐግብር ምን ይመስላል ?

ቅዳሜ ሲዳማ ቡና ከ ኢትዮጵያ መድን

ማክሰኞ ⏩️ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ ባሕር ዳር ከተማ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አል ነስር ድል አድርጓል !

በእስያ ሻምፒየንስ ሊግ ሁለተኛ ጨዋታ የሰዑዲ ዓረቢያው ክለብ አል ነስር ከኳታሩ ክለብ አል ራያን ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የአል ነስርን የማሸነፊያ ግቦች ሳዲዮ ማኔ እና ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ፖርቹጋላዊው ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ በእግርኳስ ህይወቱ 904ኛ ግቡን ማስቆጠር ችሏል።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ በዘንድሮው የውድድር ዘመን ለሀገሩ እና ክለቡ ስምንት ግቦች አስቆጥሮ ሁለት አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
Forwarded from HEY Online Market
iPhone 16 Promax
iPhone 16 Pro
iPhone 16 Plus
iPhone 16
Available Now!

0925927457 @eBRO4
0953964175 @heymobile
@heyonlinemarket
የዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዎች !

10:00 ፋሲል ከነማ ከ ስሑል ሽረ

1:00 ባሕር ዳር ከተማ ከ ሀድያ ሆሳዕና

3:45 ኒውካስል ከ ዌምበልደን ( ሊግ ካፕ )

4:00 አርሰናል ከ ፒኤስጂ

4:00 ስሎቫን ብራቲስላቫ ከ ማንችስተር ሲቲ

4:00 ባርሴሎና ከ ያንግ ቦይስ

4:00 ባየር ሌቨርኩሰን ከ ኤሲ ሚላን

4:00 ዶርትመንድ ከ ሴልቲክ

4:00 ኢንተር ሚላን ከ ሬድ ስታር ቤልግሬድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ አርሰናል ከአውሮፓ ምርጥ ቡድኖች አንዱ ነው “ ኤንሪኬ

የፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ ዋና አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ የዛሬ ምሽት ተጋጣሚያቸው አርሰናል ከአውሮፓ ምርጥ ቡድኖች አንዱ መሆኑን ገልጸዋል።

“ አርሰናል በአሁኑ ሰዓት ከአውሮፓ ምርጥ ቡድኖች አንዱ ነው ኳስ ሲቆጣጠሩም ከኳስ ውጪም በትልቅ ደረጃ መሆናቸውን መመልከት ይቻላል “ ሲሉ አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ ተናግረዋል።

አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪክ አክለውም አርሰናል በትልቅ ደረጃ የሚጠቀስ ጠንካራ የተከላካይ ክፍል እንዳለው ገልፀዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የዋልያዎቹ ተጋጣሚ ስብስቧን አሳውቃለች !

የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ሶስተኛ እና አራተኛ ጨዋታዋን ከኢትዮጵያ ጋር የምታደርገው ጊኒ ስብስቧን ይፋ አድርጋለች።

በቅርቡ ብሔራዊ ቡድኑን የተረከቡት አሰልጣኝ ሚሼል ዱሱዬር የሴልታ ቪጎውን አማካይ ኢላክስ ሞሪባ ለቡድኑ ጥሪ ሳያቀርቡለት ቀርተዋል።

የኢትዮጵያ እና ጊኒ ጨዋታዎች :-

ጥቅምት 2/2017 ዓ.ም እና

ጥቅምት 5/2017 ዓ.ም በአይቮሪኮስት አቢጃን ስታድ ደ ኢቢምፔ ስታዲየም ይደረጋል።

ሙሉ የቡድን ስብስቡ ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አንድሬስ ኢኔስታ ጫማውን ሊሰቅል ነው !

ስፔናዊው የቀድሞ የባርሴሎና ታሪካዊ የመሐል ሜዳ ተጨዋች አንድሬስ ኢኔስታ በ 40ዓመቱ ጫማውን መስቀሉን በይፋ ሊያሳውቅ መሆኑ ተገልጿል።

አንድሬስ ኢኔስታ በእግርኳስ ህይወቱ 1016 ጨዋታዎችን ሲያደርግ 107 ጎሎች አስቆጥሮ 191 ለግብ የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

አንድሬስ ኢኔስታ በእግርኳስ ህይወቱ ምን አሳካ ?

9️⃣ የላሊጋ ዋንጫ

7️⃣ ሱፐር ኮፓ

6️⃣ ኮፓ ዴላሬ

4️⃣ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ

3️⃣ የአለም ክለቦች ዋንጫ ፣ ዩኤፋ ሱፐር ካፕ

2️⃣ አውሮፓ ዋንጫ

1️⃣ የአለም ዋንጫ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/02 02:33:27
Back to Top
HTML Embed Code: