Telegram Web Link
ሞሪንሆ የዳኛን ውሳኔ በተለየ መልኩ ተቃውመዋል !

ፖርቹጋላዊው የፌነርባቼ ዋና አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ትላንት ምሽት ቡድናቸው ባደረገው የሊግ ጨዋታ ላይ የዳኛን ውሳኔ በተለየ መልኩ ሲቃወሙ ተስተውለዋል።

በጨዋታው በዳኛው ውሳኔ የተበሳጩት ጆዜ ሞሪንሆ ውሳኔው ስህተት መሆኑን ለማስረዳት ቪዲዮውን በላፕቶፓቸው ከፍተው ጨዋታውን በቀጥታ በሚያስተላልፈው ካሜራ ፊት አስቀመጠውታል።

አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ባደረጉት በዚህ ድርጊታቸው ዳኛው የማስጠንቀቂያ ካርድ አስመልክቷቸዋል።

ጨዋታውን ፌነርባቼ 2ለ0 ሲያሸንፍ በሊጉ ከመሪው ጋላታሳራይ በሶስት ነጥብ ርቆ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አሸናፊዎች ተለይተዋል።

ትክክለኛ ምላሽ ቀድመው የሰጡት ከስር የተገለፁት የቤተሰባችን አባላት ናቸው።

ትክክለኛ ምላሽ የሰጡትን በመፈለጉ ሂደት የተዘለለ እና ያልታየ ካለ ማሳወቅ ይቻላል። Edit የተደረገ መልስ ተቀባይነት አይኖረውም።

ስጦታ የሚበረከትላቸው ቀድመው የመለሱ ሶስት አሸናፊዎች ብቻ ናቸው።

የማንችስተር ዩናይትድ እና ቶተንሀም

1️⃣ኛ. @Nalosmigad
2️⃣ኛ. @Bella5078
3️⃣ኛ. 555555

የሪያል ማድሪድ እና አትሌቲኮ ማድሪድ

1️⃣ኛ. @Miku03_26
2️⃣ኛ. Abu Liyana
3️⃣ኛ. JXB

@tikvahethsport
ቲቧ ኩርቱዋ ጉዳት አጋጥሞታል !

ቤልጂየማዊው የሪያል ማድሪድ ግብ ጠባቂ ቲቧ ኩርቷ በምሽቱ የማድሪድ ደርቢ ጨዋታ የጡንቻ ጉዳት እንዳጋጠመው አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ ገልፀዋል።

ግብ ጠባቂው ስላጋጠመው ጉዳት መጠን ለማወቅ በዛሬው እለት የህክምና ምርመራዎች እንደሚደረጉለት አሰልጣኙ አያይዘው ተናግረዋል።

ሎስ ብላንኮዎቹ የፊታችን እሮብ ከሊል ጋር የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ሁለተኛ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፒኤስጂ የተጨዋቾቹን ግልጋሎት ላያገኝ ይችላል !

የፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ ነገ ከአርሰናል ጋር በሚያደርገው ተጠባቂ የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ የኦስማን ዴምቤሌን ግልጋሎት እንደማያገኝ አርኤምሲ አስነብቧል።

ተጨዋቹ ጉዳት እንዳላጋጠመው ሲገለፅ ይሁን እንጂ ውሳኔው የአሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ መሆኑ ተዘግቧል።

በተጨማሪም ፒኤስጂ በነገው ጨዋታ :-

- የዶናሩማ

- ማርኮ አሴንሲዮ

- ቪቲኒሀ

- ኑኖ ሜንዴዝን ግልጋሎት ላያገኙ እንደሚችሉ ተገልጿል።

ፒኤስጂ ነገ ምሽት 4:00 በኤምሬትስ ስታዲየም ከአርሰናል ጋር የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ሁለተኛ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አንቷን ግሪዝማን ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ አገለለ !

ፈረንሳዊው የአትሌቲኮ ማድሪድ የፊት መስመር ተጨዋች አንቷን ግሪዝማን በ 33ዓመቱ ከፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ራሱን ማግለሉን በይፋ አስታውቋል።

“ በበርካታ ትዝታዎች የተሞላውን አስደሳች የህይወት ክፍል በዚሁ እዘጋዋለሁ ሁሉንም ሰው በጣም አመሰግናለሁ “ ሲል አንቷን ግሪዝማን ተናግሯል።

ግሪዝማን ለፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን 137 ጨዋታዎች ሲያደርግ 44 ግቦችን አስቆጥሮ 38 ለግብ የሆኑ ኳሶች አመቻችቶ አቀብሏል።

አንቷን ግሪዝማን ከፈረንሳይ ጋር ምን አሳካ ?

1️⃣ የአለም ዋንጫ

1️⃣ ዩኤፋ ኔሽንስ ሊግ

1️⃣ የአውሮፓ ዋንጫ ወርቅ ጫማ አሸናፊ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ፒኤስጂ የተጨዋቾቹን ግልጋሎት ላያገኝ ይችላል ! የፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ ነገ ከአርሰናል ጋር በሚያደርገው ተጠባቂ የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ የኦስማን ዴምቤሌን ግልጋሎት እንደማያገኝ አርኤምሲ አስነብቧል። ተጨዋቹ ጉዳት እንዳላጋጠመው ሲገለፅ ይሁን እንጂ ውሳኔው የአሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ መሆኑ ተዘግቧል። በተጨማሪም ፒኤስጂ በነገው ጨዋታ :- - የዶናሩማ - ማርኮ አሴንሲዮ - ቪቲኒሀ …
ኦስማን ዴምቤሌ ለምን ከስብስብ ተቀነሰ ?

የፒኤስጂው ዋና አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ ፈረንሳዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ኦስማን ዴምቤሌ ኦስማን ዴምቤሌ ከነገው የአርሰናል ጨዋታ ውጪ አድርገዋል።

አሰልጣኙ ተጫዋቹን ከስብስባቸው የቀነሱት ከዲሲፕሊን ጋር በተያያዘ መሆኑን የፈረንሳይ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል።

ፒኤስጂ ከቀናት በፊት ሬንስን ባሸነፈበት ጨዋታ ኦስማን ዴምቤሌ ከአሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ ጋር አለመግባባት ውስጥ ገብተው እንደነበር ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቲቧ ኩርቱዋ ጉዳት አጋጥሞታል ! ቤልጂየማዊው የሪያል ማድሪድ ግብ ጠባቂ ቲቧ ኩርቷ በምሽቱ የማድሪድ ደርቢ ጨዋታ የጡንቻ ጉዳት እንዳጋጠመው አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ ገልፀዋል። ግብ ጠባቂው ስላጋጠመው ጉዳት መጠን ለማወቅ በዛሬው እለት የህክምና ምርመራዎች እንደሚደረጉለት አሰልጣኙ አያይዘው ተናግረዋል። ሎስ ብላንኮዎቹ የፊታችን እሮብ ከሊል ጋር የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ሁለተኛ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።…
ቲቧ ኩርቱዋ ለሳምንታት ከሜዳ ይርቃል !

ቤልጂየማዊው የሪያል ማድሪድ ግብ ጠባቂ ቲቧ ኩርቱዋ በተደረገለት ምርመራ የጡንቻ ጉዳት እንዳጋጠመው መረጋገጡን ክለቡ አሳውቋል።

ይህንንም ተከትሎ ቲቧ ኩርቱዋ ለሚቀጥሉት ሁለት ወይም ሶስት ሳምንታት ከሜዳ እንደሚርቅ ተገልጿል።

ሎስ ብላንኮዎቹ በቀጣይ ከሊል እና ቪያሪያል በሚያደርጓቸው ጨዋታዎች አንድሬ ሉኒን እንደሚጠቀሙ ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ፒኤስጂ በጣም ጠንካራ ነው “ አርቴታ

የመድፈኞቹ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የነገ ምሽት ተጋጣሚያቸው ፒኤስጂ ጠንካራ መሆኑን ገልፀዋል።

“ ፒኤሴጂ በጣም ጠንካራ ነው ጨዋታውን ተቆጣጥረው ይጫወታሉ ግልፅ የሆነ ፍላጎት ነው ያላቸው ኳስ ሲቀሙ በፍጥነት ለማግኘት ይሞክራሉ “ ሲሉ ሚኬል አርቴታ ተናግረዋል።

በነገው ጨዋታ የኋላ መስመር ተጨዋቾቹ ሪካርዶ ካላፊዮሪ እና ቤን ዋይት መሰለፋቸውን ተገምግመው እንደሚወስኑ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አያይዘው ገልጸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
ካፍ ከሱፐር ስፖርት ጋር ስምምነት ፈፅሟል !

የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን ( ካፍ ) ከሱፐር ስፖርት ጋር የቴሌቪዥን መብት ስርጭት ስምምነት መፈፀሙን ይፋ አድርጓል።

ስምምነቱ ካፍ የሚያዘጋጃቸውን የአፍሪካ ወንዶች እና ሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ ፣ የካፍ ኮንፌዴሬሽን ካፕ እና የአፍሪካ ሱፐር ካፕ ውድድሮችን የተመለከተ መሆኑ ተገልጿል።

በዘንድሮው የካፍ ሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር ሀገራችን ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሴቶች ቡድን የምትወከል ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/30 12:13:09
Back to Top
HTML Embed Code: