Telegram Web Link
#SaudiLeague 🇸🇦

በሰዑዲ ዓረቢያ ሊግ የአምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር አል ኢትሐድ አል ካሊጅን 4ለ1 ሲያሸንፍ አል አህሊ በአል ቃዲሲያ 1ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

የአል ኢትሀድን የማሸነፊያ ግቦች ካሪም ቤንዜማ ፣ ጋምዲ ፣ ስቴቨን ቤርግዊን እና ሁሴም ኡራ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

የአል ቃዲሲያን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ፔር ኤምሪክ ኦባምያንግ ማስቆጠር ችሏል።

ፈረንሳዊው የፊት መስመር አጥቂ ካሪም ቤንዜማ በውድድር ዘመኑ ስድስተኛ የሊግ ግቡን ማስቆጠር ችሏል።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?

1️⃣ኛ አል ኢትሀድ :- 12 ነጥብ
4️⃣ኛ አል ቃዲሲያ :- 10 ነጥብ
7️⃣ኛ አል አህሊ :- 7 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ?

ሐሙስ ⏩️ አል አክዱድ ከ አል ኢትሀድ

ቅዳሜ ⏩️ አል አህሊ ከ አል ሂላል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኤሲ ሚላን ድል አድርጓል !

በጣልያን ሴርያ የስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኤሲ ሚላን ከሊቼ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የኤሲ ሚላንን የማሸነፊያ ግቦች አልቫሮ ሞራታ ፣ ቲኦ ሄርናንዴዝ እና ክርስቲያን ፑልሲች ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

የሊግ ደረጃቸው ?

2️⃣ኛ ኤሲ ሚላን :- 11 ነጥብ
1️⃣7️⃣ኛ ሊቼ :- 5 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታቸው ምን ይመስላል ?

እሁድ ፊዮሬንቲና ከ ኤሲ ሚላን

ቅዳሜ ዩዲኔዜ ከ ሊቼ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
Forwarded from HEY Online Market
iPhone 16 Promax
iPhone 16 Pro
iPhone 16 Plus
iPhone 16
Available Now!

0925927457 @eBRO4
0953964175 @heymobile
@heyonlinemarket
የዛሬ ተጠባቂ ጨዋታዎች !

8:30 ኒውካስል ከ ማንችስተር ሲቲ

10:00 መቻል ከ ሲዳማ ቡና

10:00 ዩድኒዜ ከ ኢንተር ሚላን

11:00 አርሰናል ከ ሌስተር ሲቲ

11:00 ቼልሲ ከ ብራይተን

1:00 ድሬዳዋ ከተማ ከ ወላይታ ድቻ

1:00 ጂኖኣ ከ ጁቬንቱስ

1:30 ባየር ሙኒክ ከ ባየር ሌቨርኩሰን

1:30 ዎልቭስ ከ ሊቨርፑል

4:00 ኦሳሱና ከ ባርሴሎና

🔴 የ የዛሬው የይግምቱ ሽልማታችን የማንችስተር ሲቲ ፣ አርሰናል ፣ ቼልሲ ፣ ሊቨርፑል እና ባርሴሎና ጨዋታዎች ናቸው።

🔴 የዛሬ አምስት ሽልማቶቻችን 7:00 ፣ 9:30 ፣ 9:40 ፣ 12:00 ፣ 3:00 ሰዓት ላይ ወደ ቤተሰቦቻችን የሚደርሱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቼልሲ ተጨዋቾቹ ባይጫወቱም ስታዲየም እንዲገኙ ጠይቋል !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ዋና አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ የክለቡ ተጨዋቾች ቡድኑ በሜዳው የሚያደርጋቸውን ጨዋታዎች እንዲታደም ማሳሰባቸው ተገልጿል።

አሰልጣኙ ተጨዋቾቹ በጨዋታው የቡድን ስብስብ ውስጥ ባይካተቱም እንኳን በሜዳው ሲጫወት ግዴታ ስታዲየም በመገኘት እንዲያበረታቱ መንገራቸው ተዘግቧል።

ሰማያዊዎቹ በሳምንቱ አጋማሽ ባሮውን በሊግ ካፕ ሲያሸንፉ ኮል ፓልመርን ጨምሮ ለጨዋታው ያልተመረጡ ተጨዋቾች ስታምፎርድ ብሪጅ መገኘታቸው ይታወሳል።

አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ውሳኔያቸው የቡድኑን መንፈስ ለማሳደግ አስፈላጊ ነው የሚል እምነት እንዳላቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
“ ስለ ሲቲ ሁሉም መረጃ አለኝ “ ሚኬል አርቴታ የአርሰናሉ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የማንችስተር ሲቲ ተጨዋቾች ስለ ቡድናቸው የአጨዋወት ዘይቤ የሰጡት አስተያየት አግባብ አይደለም ስለ እነሱም አውቃለሁ ብለዋል። “ እኔ ማንችስተር ሲቲ ውስጥ አራት አመታት አሳልፌያለሁ ከእነሱ በፊት እዛ ነበርኩ ስለዚህ እመኑኝ ስለ እነሱ ሁሉም መረጃ አለኝ “ ሲሉ ሚኬል አርቴታ ገልፀዋል። “ ኢትሀድ ላይ ባደረግነው…
“ አርቴታ ለተናገረው ነገር ማብራሪያ መስጠት አለበት “ ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ  አሰልጣኝ ሜኬል አርቴታ ከቀናት በፊት የተናገሩትን “ ግልጽ ማድረግ አለባቸው “ ሲሉ አሳስብዋል።

ሚኬል አርቴታ ከቀናት በፊት በሲቲ ጨዋታ በተከተሉት አጨዋወት ምክንያት ለቀረበባቸው ትችት ምላሽ ሲሰጡ “ ሲቲ በነበርኩበት አራት አመት ስለ እነሱ ሁሉንም መረጃ አውቃለሁ “ ብለው ነበር።

“ በቀጣይ አርቴታ ነገሩን የበለጠ ግልጽ ማድረግ አለበት “ ያሉት ፔፕ ጋርዲዮላ “ እዚህ በነበረበት ሰዓት ሁሉንም ነገር አውቃለሁ ሲል ምን ለማለት እንደፈለገ በግልጽ ያብራራ ብለዋል።

“ ምክንያቱም ንግግሩ በሂደት ላይ ካለው 115 ክስ ጋር ሊገናኝ ይችላል ፤ ምናልባት ስለዛ የሚያውቀው ሊኖር ይችላል አላውቅም “ ሲሉ ፔፕ ጋርዲዮላ ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ከሲቲ ያለንን ርቀት ለማጥበብ እንሞክራለን “ አርኔ ስሎት

የሊቨርፑሉ ዋና አሰልጣኝ አርኔ ስሎት በቀጣይ ቡድናቸው የሚሰጠው ግምት ከፍም ይበል ይነስ ክለቡ ባለፈው አመት ካሳካው ነጥብ ለማሻሻል እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

“ ሊቨርፑል ዋንጫ የማንሳት እድሉ ከፍ ወይም ዝቅ ተደርጎ ይነገር አይመለከተኝም ባለፉት ሁለት አመታት ሲቲ ከእኛ በላይ 31 ነጥቦች ሰብስቧል ያንን ክፍተት ለማጥበብ እንሞክራለን “ ሲሉ አርኔ ስሎት ተናግረዋል።

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ውስጥ ቀላል ጨዋታ እንደሌለ ብዙ አሰልጣኞች ሲናገሩ ሰምቼ ነበር እውነት መሆኑን አረጋግጫለሁ ሲሉ አርኔ ስሎት ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ አርሰናል ቤቴ ነው “ ካይ ሀቨርትዝ

ጀርመናዊው የመድፈኞቹ የፊት መስመር ተጨዋች ካይ ሀቨርትዝ በአርሰናል ቤት ደስተኛ መሆኑን ገልጿል።

“ እዚህ ምቾት ተሰምቶኛል አርሰናል ቤቴ ነው በየቀኑ እዚህ መሆኔን እወደዋለሁ “ ሲል ካይ ሀቨርትዝ በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

ከተቀናቃኝ ቡድን በመሄዱ እና ትልቅ ክፍያ በማግኘቱ በእሱ ላይ ጥርጣሬ ቢቀርብ እንደማይገርመው የገለፀው ካይ ሀቨርትዝ " ነገርግን እኔ አቅሜን አውቀዋለሁ በራሱ አምናለሁ “ ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
“ በሜዳችን በደንብ እንጠብቃቸዋለን “ ጋብሬል የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የኋላ መስመር ተጨዋች ጋብሬል ማግሀሌስ ቡድናቸው ማንችስተር ሲቲን በሜዳው ሲገጥም ለማሸነፍ እንደሚጠብቅ ገልጿል። በመጨረሻ ደቂቃ በተቆጠረ ግብ ነጥብ ከጣሉበት ከምሽት ጨዋታ በኋላ አስተያየቱን የሰጠው ጋብሬል ማግሀሌስ “ አሁን እነሱን በሜዳችን በጥሩ ሁኔታ እንጠብቃቸዋለን “ ሲል ተናግሯል። ጋብሬል ማግሀሌስ አርሰናል…
" ጋብሬል ጦርነት ከፈለገ እንዋጋለን “ ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የመድፈኞቹ ተከላካይ ጋብሬል ማግሀሌስ ጦርነት ከፈለገ እንዋጋለን በማለት ተናግረዋል።

ጋብሬል ከሳምንቱ ጨዋታ በኋላ ስለሰጠው አስተያየት ምላሽ የሰጡት ፔፕ ጋርዲዮላ " ጋብሬል በደንብ ተናግሯል ጦርነት ነው ብሏል እዚህ ነን ጦርነት ከፈለገ እንዋጋለን “ ብለዋል።

ጋብሬል ከጨዋታው በኋላ “ ይህ የጦርነት ፍልሚያ ነው ተቃዋሚን ማናደድ እና መገፋፋት የተለመደ ነው አሁን እዚህ አልቋል በሜዳችን በደንብ እንጠብቃቸዋለን “ ብሎ ነበር።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
⚡️ በዕለታዊ የዳታ ጥቅሎች ቀኑን ሙሉ ፈታ እንበል! 🥳

በM-PESA ላይ ስንገዛ ሁሉም ቅናሽ አላቸው!

በልዩ ልዩ አማራጮች የቀረበልንን የሳፋሪኮም የኢንተርኔት ጥቅል የM-PESA Appን በመጠቀም አሁኑኑ እንግዛ! በፈጣን ዳታ እንንበሽበሽ!

🔗የM-PESA ሳፋሪኮም መተግበሪያ በዚህ ሊንክ እናዉርድ:
https://play.google.com/store/apps/details?id=et.safaricom.mpesa.lifestyle

የቴሌግራም ቦታችንን
https://www.tg-me.com/official_safaricomet_bot በመጠቀም የአየር ሰዓት ወይንም ልዩ ልዩ ጥቅሎችን እንግዛ!

ስለ አገልግሎታችን ማንኛውንም ጥያቄ ወይም መረጃ በቴሌግራም ቻናላችን
https://www.tg-me.com/Safaricom_Ethiopia_PLC 24/7 ማግኘት ይቻላል!

#MPESASafaricom
#SafaricomEthiopia
#1wedefit
#Furtheraheadtogether
ይገምቱ ይሸለሙ

የማንችስተር ሲቲ እና ኒውካስል ዩናይትድን ጨዋታ ውጤት ገምተው በትክክል ላወቁ ሶስት ቤተሰቦቻችን የአንድ መቶ ብር ካርድ የምንሸልምዎ ይሆናል።

የውድድሩ ህጎች ምን ይመስላሉ ?

√ ተሳታፊዎች ግምቶቻቸውን ከዚህ ፖስት ስር ባለው የሀሳብ መስጫ ሳጥን #ብቻ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።

√ ኤዲት የተደረጉ ምላሾች በፍፁም ተቀባይነት አይኖራቸውም።

√ ግምትዎን መላክ የሚቻለው እስከ 8:30 ሰዓት ብቻ ነው።

መልካም ዕድል !

@tikvahethsport    
የጨዋታ አሰላለፍ !

8:30 ኒውካስል ከ ማንችስተር ሲቲ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኤሚሊያኖ ማርቲኔዝ ቅጣት ተጣለበት !

የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ቁጥር አንድ ግብ ጠባቂ ኤሚሊያኖ ማርቲኔዝ በፊፋ የሁለት ጨዋታዎች ቅጣት እንደተጣለበት ተገልጿል።

ግብ ጠባቂው የስፖርታዊ ጨዋነትን ደንብ ያልተከተለ ባህሪ አሳይቷል በሚል ቅጣቱ እንደተጣለበት ይፋ ተደርጓል።

ይህንንም ተከትሎ አርጀንቲና በቀጣይ ከቬንዙዌላ እና ቦሊቪያ ጋር በምታደርጋቸው የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች የኤሚሊያኖ ማርቲኔዝን ግልጋሎት የማታገኝ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ቪንሰስ ባሎን ዶር ያሸንፋል “ ካርሎ አንቾሎቲ

የሎስ ብላንኮዎቹ ዋና አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ ከነገው ተጠባቂ የማድሪድ ደርቢ ጨዋታ በፊት ከጋዜጠኞች ጋር ቆይታ አድርገዋል።

ካርሎ አንቾሎቲ ምን አሉ ?

- " ቪንሰስ ጁኒየር ባሎን ዶር ማሸነፍ ይገባዋል እሱ የሚያሸንፍ ይመስለኛል።

- አትሌቲኮ ማድሪድ በዚህ አመት ከአምናው የተሻሉ ናቸው ጥሩ ተጨዋቾች አስፈርመዋል ከእኛ እና ባርሴሎና ጋር ለዋንጫው ይፎካከራሉ።

- ኤድዋርዶ ካማቪንጋ ከጉዳቱ አገግሟል ለጨዋታ ዝግጁ ነው መጫወት ይችላል።

- ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር ከሜዳ ውጪ መጫወት ሁልጊዜም አስቸጋሪ ነው የበለጠ ተሻሽለን መቅረብ አለብን።" ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ተጀመረ

ኒውካስል ዩናይትድ 0 - 0 ማንችስተር ሲቲ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
10 ' ኒውካስል ዩናይትድ 0 - 0 ማንችስተር ሲቲ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
25 ' ኒውካስል ዩናይትድ 0 - 0 ማንችስተር ሲቲ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/29 13:30:05
Back to Top
HTML Embed Code: