Telegram Web Link
ነገ አዲስ ቀን ነው “ ኤሪክ ቴን ሀግ

“ ራሴን በመስታወት መመልከት ይኖርብኛል “

አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ቡድናቸው ምሽቱን ባስመዘገበው ውጤት ብስጭታቸውን ገልፀዋል።

“ በምሽቱ ጨዋታ የሚያስተቹ ነገሮች አሉ ያሉት ቴን ሀግ “ ቡድኑ ብቻ ሳይሆን እኔም ራሴን በመስታወት መመልከት ይኖርብኛል “ ብለዋል።

“ በጨዋታው ስህተቶች ነበሩ “ ያሉት ቴን ሀግ “ ተጋጣሚያችን ስህተታችንን ተጠቅሞብናል ፣ የአቻ ውጤቱ ያበሳጫል “ ሲሉም ተናግረዋል።

በጨዋታ ወቅት 99% ብቻ በቂ አለመሆኑን የገለፁት ቴን ሀግ “ ጨዋታዎችን ገድለን መውጣት አለብን “ ብለዋል።

“ ይህ እግር ኳስ ነው ወደፊት መጓዛችንን እንቀጥላለን ፣ ነገ አዲስ ቀን ነው ፣ ነገሮችን እንደ አዲስ እንጀምራለን “ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ድሉ ይገባን ነበር “ ሀንስ ፍሊክ

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ተከታታይ ሰባተኛ ድላቸውን በሊጉ ሲያስመዘግቡ ውጤቱ ተገቢ መሆኑን አሰልጣኙ ተናግረዋል።

“ ድሉ ይገባናል “ ያሉት ሀንስ ፍሊን “ ብዙ ጎሎችን ማስቆጠር እንችል ነበር “ ሲሉም ከጨዋታው በኃላ ተናግረዋል።

የቡድናቸውን ግብ አስቆጣሪ ሮበርት ሊዋንዶውስኪ ያወደሱት ሀንስ ፍሊክ “ ባለፉት አስር አመታት በዘጠኝ ቁጥር ቦታ እሱ ምርጡ ተጫዋች ነው “ ብለዋል።

“ ሮበርት ሊዋንዶውስኪ ስራው ግብ ማግባት ነው ፣ ይህንንም እያደረገ ይገኛል “ አሰልጣኝ ሀንስ ፍሊክ

አሰልጣኝ ሀንስ ፍሊክ ቡድናቸው በሊጉ 2️⃣3️⃣ ጎሎችን ሲያስቆጥር ምንም ነጥብ ሳይጥል በ 4️⃣ ነጥብ ልዩነት ላሊጋውን እየመሩ ይገኛሉ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የ ዴቪድ ራያ የጉዳት መጠን ?

አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ከምሽቱ ጨዋታ በኃላ በሰጡት አስተያየት የቡድኑን ወጣት ተጫዋቾች አወድሰዋል።

“ ኢታን ንዋኔሪ ግብ በማስቆጠሩ ደስ ብሎኛል “ ያሉት አሰልጣኙ “ በአጠቃላይ በምሽቱ ጨዋታ ጥሩ ነበር “ ብለዋል።

“ በምሽቱ ከተመለከትናቸው ታዳጊ ተጫዋቾች ውስጥ አንዳንዶቹ ጠዋት ትምህርት አለባቸው “ ሚኬል አርቴታ

ሚኬል አርቴታ ስለ ግብ ጠባቂያቸው ራያ ሲጠየቁ “ የጡንቻ ህመም “ ነው ሲሉ ከጉዳት የሚመለስበትን ቀን እንደማይታወቅ ተናግረዋል።

ራሂም ስተርሊንግ በምሽቱ ጨዋታ ያሳየውን ብቃት በማድነቅ “ በአካል ብቃት ረገድ እኛ በምንፈልገው ደረጃ መገኘት አለበት “ ብለዋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ቀጣይ ጨዋታችን ፈታኝ ነው “ አርኔ ስሎት

“ ሽንፈት አይገባንም “ ሎፕቲጌ

የመርሲሳይዱ ክለብ ዋና አሰልጣኝ አርኔ ስሎት እንግሊዝ ውስጥ እያንዳንዱ ጨዋታ ፈታኝ መሆኑን ከምሽቱ ጨዋታ በኃላ ተናግረዋል።

በተጨማሪም ካነሷቸው ሀሳቦች መካከል :-

አሰልጣኝ አርኔ ስሎት አዲሱ ፈራሚ ፍሬድሪኮ ኬይሳ “ ክለቡን መላመድ አለበት “ ሲሉ ጊዜ እንደሚያስፈልገው ገልፀዋል።

ቀጣይ ጨዋታቸው ከባድ መሆኑን የገለፁት አርኔ ስሎት “ ከብራይተን ጋር ፈታኛ መርሐ ግብር ነው “ ብለዋል።

የምሽቱ ተጋጣሚያቸው ዌስትሀም አሰልጣኝ ሎፕቲጌ በበኩላቸው “ ሽንፈት አይገባንም “ ሲሉ ተደምጠዋል።

አሰልጣኙ ቀጥለውም “ ግልፅ የሆነ ከጨዋታ ውጪ የሆነ ጎል ተቆጥሮብናል “ ሲሉ ትችታቸውን ሰንዝረዋል።

አርኔ ስሎት ለዌስትሀም ያላቸውን አድናቆት ሲገልፁ “ ዌስትሀም ብዙ ኳሊቲ ያለው ቡድን ነው “ ብለዋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ውጤቱ የሽንፈት ያህል ነው “ ኤሪክሰን

የቀያይ ሴጣኖቹ ተጫዋች ኤሪክሰን ቡድኑ ትላንት ምሽት በሜዳው ባስመዘገበው ውጤት ማዘኑን ገልፆል።

“ ውጤቱ የሽንፈት ያህል ነው “ ሲል የገለፀው ኤሪክሰን “ በሜዳችን በትዌንቴ ይህ ውጤት መፈጠር አልነበረበትም “ ብሏል።

ክሪስቲያን ኤሪክሰን የምሽቱ ጨዋታ ጎል ክለቡን ከተቀላቀለ በኃላ በአውሮፓ መድረክ ያስቆጠረው የመጀመሪያ ጎሉ መሆኑ ተገልፆል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
“ አቡበከር ናስር አሁን ከእኛ ጋር አይደለም “ ማንቆባ ማንጊቲ ኢትዮጵያዊው የፊት መስመር ተጨዋች አቡበከር ናስር ከማሜሎዲ ሰንዳውንስ በውሰት ሌላኛውን የደቡብ አፍሪካ ክለብ ሱፐር ስፖርት ዩናይትድ እንደሚቀላቀል ተገልጿል። የማሜሎዲ ሰንዳውንስ አሰልጣኝ ማንቆባ ማንጊቲ ትላንት ምሽት በሰጡት አስተያየት “ አቡበከር ናስር በዚህ ሰዓት ከእኛ ጋር አይደለም “ ብለዋል። “ አቡበክር በአሁኑ ሰዓት…
“ አቡበከር ናስር ለሱፐር ስፖርት ፈርሟል “  ወኪሉ

የኢትዮጵያዊው የፊት መስመር አጥቂ አቡበከር ናስር ወኪል ስቲቭ ካፔሉሺኒክ አቡበከር ናስር ሱፐር ስፖርት ዩናይትድን በቋሚ ውል እንደተቀላቀለ አረጋግጧል።

የማሜሎዲ ሰንዳውንስ ዋና አሰልጣኝ ማንቆባ ማንጊቲ አቡበከር ናስር ወደ ስፐር ስፖርት ዩናይትድ ማቅናቱን መግለፃቸው አይዘነጋም።

የአቡበከር ናስር ወኪል በሰጠው አስተያየት “ አቡበከር ናስር ለሱፐር ስፖርት ዩናይትድ የአንድ አመት ውል ፈርሟል አሁን የእነሱ ተጨዋች ነው “ ሲል ተናግሯል።

የደቡብ አፍሪካው ክለብ ሱፐር ስፖርት ዩናይትድ እስካሁን የአቡበከር ናስርን ዝውውር በይፋ አላሳወቀም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
iPhone 16 Promax
iPhone 16 Pro
iPhone 16 Plus
iPhone 16
Available Now!

0925927457 @eBRO4
0953964175 @heymobile
@heyonlinemarket
መልካም የመስቀል ደመራ በዓል ይሁንላችሁ !

#TikvahEthiopiaFamily

@tikvahethiopia
የላሊጋ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ?

የስፔን ላሊጋ የ 2024/25 የውድድር ዘመን የወርሀ መስከረም የወሩ ምርጥ ተጨዋች እጩዎች ይፋ ተደርገዋል ።

በዚህም መሰረት :-

ኪሊያን ምባፔ

ላሚን ያማል

ኢናኪ ዊሊያምስ

ሎ ሴልሶ

ካርሎስ ቪሴንቴ በእጩነት መቅረብ የቻሉ ተጨዋቾች ናቸው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አንዲ ካሮል የአራተኛ ሊግ ክለብ ሊቀላቀል ነው ! የቀድሞ የሊቨርፑል እና ኒውካስል ዩናይትድ የፊት መስመር አጥቂ አንዲ ካሮል በፈረንሳይ አራተኛ ሊግ ለሚወዳደረው ቦርዶ ለመፈረም መቃረቡ ተገልጿል። የ 35ዓመቱ አንዲ ካሮል ከፈረንሳይ ሁለተኛ ሊግ ክለብ አምዬንስ ቦርዶን ለመቀላቀል ከስምምነት መድረሱን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል። የስድስት ጊዜ የፈረንሳይ ሊግ አሸናፊው ቦርዶ በገጠመው ከፍተኛ የገንዘብ…
“ ገንዘብ ሳይሆን እግርኳስ መጫወት ነው የሚያስደስተኝ “ አንዲ ካሮል

የቀድሞ የሊቨርፑል እና ኒውካስል ዩናይትድ እንግሊዛዊ የፊት መስመር አጥቂ አንዲ ካሮል ቦርዶን መቀላቀሉ ገንዘብ እንዳሳጣው ገልጿል።

አንዲ ካሮል በቅርቡ አምዬንስን በመልቀቅ በፈረንሳይ አራተኛ ሊግ እርከን ለሚወዳደረው ቦርዶ መፈረሙ ይታወቃል።

“ እውነት ለመናገር ለቦርዶ ለመጫወት በመወሰኔ ገንዘብ እያሳጣኝ ነው ነገርግን እግርኳስ እየተጫወትኩ ነው በዚህ በጣም ደስተኛ ነኝ “ ሲል አንዲ ካሮል ተናግሯል።

በገጠመው የፋይናስን እጥረት ወደ አራተኛ ሊግ ለመውረድ የተገደደው ቦርዶ “ የታሪኩ አካል መሆን እፈልጋለሁ በእግርኳስ ህይወቴ ገንዘብ ጥያቄ ሆኖብኝ አያውቅም “ ብሏል።

የ 35ዓመቱ ተጨዋች አንዲ ካሮል በቦርዶ በወር 3,500 ዩሮ ክፍያ እንደሚያገኝ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
በሊባኖስ እግርኳስ ጨዋታዎች ተራዘሙ !

የሊባኖስ እግርኳስ ፌዴሬሽን በሀገሪቱ ውስጥ የሚደረጉ ሁሉም የእግርኳስ ጨዋታዎች ለላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘሙ መወሰኑን ይፋ አድርጓል።

የሀገሪቱ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጨዋታዎቹ እንዲራዘሙ የወሰነው እስራኤል ከሂዝቦላ ጋር እያደረገች የምትገኘውን ግጭት ተከትሎ መሆኑ ተገልጿል።

የሊባኖስ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በእስራኤል በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ 558 ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ እና ከ 1,835 በላይ ሰዎች ደግሞ እንደቆሰሉ ገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
Forwarded from WANAW SPORT
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሰዎ!

ዋናው የስፖርት አልባሳት ብራንድ

Instagram | Facebook | TikTok

🏅ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
#EthPL

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የ 2017 የውድድር ዘመን ሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ፋሲል ከነማ ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የመቐለ 70 እንደርታን ግብ ያሬድ ብርሀኑ ከመረብ ሲያሳርፍ ቢኒያም ላንቃሞ ፋሲል ከነማን አቻ ማድረግ ችሏል።

ቀጣይ መርሐ ግብራቸው ምን ይመስላል ?

ሰኞ ⏩️  ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ መቐለ 70 እንደርታ

ማክሰኞ ፋሲል ከነማ ከ ስሁል ሽረ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ዩናይትድ ከፈለገኝ እመለሳለሁ “ ሶልሻየር

የቀድሞው የቀያይ ሴጣኖቹ ተጨዋች እና አሰልጣኝ ኦሌ ገነር ሶልሻየር ማንችስተር ዩናይትድ በድጋሜ አድል የሚሰጣቸው ከሆነ እንደሚቀበሉ ገልጸዋል።

“ ሌሎች አሰልጣኞች ስለያዙት ቦታ መናገር አልፈልግም “ ያሉት አሰልጣኝ ኦሌ ገነር ሶልሻየር “ ነገርግን ማንችስተር ዩናይትድ በድጋሜ እንዳሰለጥን ከጠየቀኝ እቀበላለሁ “ ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ የቡድኑ ችግር በቂ ግብ አለማስቆጠሩ ነው “ ቴንሀግ

የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ቡድናቸው እሁድ ከቶተንሀም ጋር ከሚያደርገው ጨዋታ በፊት ከጋዜጠኞች ጋር ቆይታ አድርገዋል።

ኤሪክ ቴንሀግ ካነሷቸው ሀሳቦች መካከል :-

- " አዲስ ከጉዳት የተመለሰ ተጨዋች የለንም በቶተንሀም ጨዋታ የሚኖረን የቡድን ስብስብ በመጨረሻ ጨዋታችን ካለን ጋር ተመሳሳይ ነው።

- የቡድኑ ችግር በቂ ግብ አለማስቆጠር ነው ማስቆጠር የሚችሉ ተጨዋቾች አሉን ነገርግን ከምንፈጥራቸው የግብ አድሎች አንፃር በበቂ ሁኔታ አላስቆጠርንም።

- ሁሉም ቡድን ጠንካራ እና ደካማ ጎን አለው ቶተንሀም አጥቅቶ የሚጫወት ቡድን ነው ጥሩ መሆን አለብን።

- ከቶተንሀም ጋር የምናደርገው ጨዋታ ጠንካራ እና አዝናኝ ይሆናል።

- እስካሁን ሁለት ዋንጫዎችን አሳክተናል በዚህ አመት ተጨማሪ ዋንጫዎችን ማሸነፍ እንፈልጋለን።" ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#EthPL

በ 2017 የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ቀጣይ መርሐ ግብራቸው ምን ይመስላል ?

ሰኞ ⏩️  ኢትዮጵያ መድን ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ

እሮብ ኢትዮጵያ ቡና ከ ሀዋሳ ከተማ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የዩናይትድ እና ቶተንሀምን ጨዋታ ማን ይመራል ?

የፊታችን እሁድ በማንችስተር ዩናይትድ እና ቶተንሀም መካከል የሚደረገውን የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ስድስተኛ ሳምንት መርሐግብር የሚመሩት ዳኛ ታውቀዋል።

እሁድ አመሻሽ 12:30 በኦልድትራፎርድ ስታዲየም የሚደረገውን ተጠባቂ ጨዋታ ክሪስ ካቫናህ በመሐል ዳኝነት እንደሚመሩት ይፋ ተደርጓል።

ጨዋታውን ማን ያሸንፋል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቶተንሀም ድል አድርጓል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም ከካራባህ ጋር ያደረገውን የዩሮፓ ሊግ የመጀመሪያ ጨዋታ 3ለ0 በሆነ ውጤ ማሸነፍ ችሏል።

የቶተንሀምን የማሸነፊያ ግቦች ብሬናን ጆንሰን ፣ ፓፔ ሳር እና ዶምኒክ ሶላንኬ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ቶተንሀም በጨዋታው ገና በስምንተኛው ደቂቃ ተከላካያቸው ራዱ ድራጉሲን በቀይ ካርድ መውጣቱን ተከትሎ በአስር ተጨዋቾች ጨዋታውን ለመጨረስ ተገደዋል።

በሌላ ጨዋታ ሮማ ከስፔኑ ክለብ አትሌቲክ ቢልባኦ ጋር ያደረገውን የዩሮፓ ሊግ የመጀመሪያ ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቋል።

የሌሎች የዩሮፓ ሊግ ጨዋታዎች ውጤት ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/27 04:23:23
Back to Top
HTML Embed Code: