Telegram Web Link
አል ናስር ቀጣዩን ዙር ተቀላቅሏል !

በሰዑዲ ዓረቢያ ኪንግስ ካፕ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ አል ነስር ከ አል ሀዜም ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የአል ነስርን የማሸነፊያ ግቦች ሳዲዮ ማኔ እና አል ቡሻይል ማስቆጠር ችለዋል።

አል ነስር ማሸነፉን ተከትሎ የሰዑዲ ዓረቢያ ኪንግስ ካፕ አስራ ስድስት ውስጥ መቀላቀላቸውን አረጋግጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሀዋሳ ከተማ አመቱን በድል ጀምረዋል !

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የ 2017 የውድድር ዘመን ሀዋሳ ከተማ ከሲዳማ ቡና ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የሀዋሳ ከተማን የማሸነፊያ ግብ ተባረክ ሄፋሞ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ቀጣይ መርሐ ግብራቸው ምን ይመስላል ?

አርብ ⏩️  ሀዋሳ ከተማ ከ ስሑል ሽረ

ቅዳሜ ⏩️ መቻል ከ ሲዳማ ቡና

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
Forwarded from HEY Online Market
iPhone 16 Promax
iPhone 16 Pro
iPhone 16 Plus
iPhone 16
Available Now!

0925927457 @eBRO4
0953964175 @heymobile
@heyonlinemarket
ዋልያዎቹ ቀጣይ ጨዋታቸውን የት ያደርጋሉ ?

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለ 2025 የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የሚረዳውን የምድብ ሶስተኛ እና አራተኛ ጨዋታ ከጊኒ አቻቸው ጋር የሚያደርጉ ይሆናል።

የሁለቱ ሀገራት የደርሶ መልስ ጨዋታ በኮትዲቯር ሊደረግ እንደሚችል ለማወቅ ተችሏል።

ከጊኒ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እየወጡ ባሉ መረጃዎች ሁለቱንም ጨዋታ በ ኮትዲቯር ለማድረግ የሁለቱ ሀገራት ፌዴሬሽኖች በንግግር ላይ እንደሚገኙ ተዘግቧል።

የጊኒ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የካፍን መስፈርት የሚያሟላ ስታዲየም ስለሌለው ለማጣርያ ጨዋታዎች ኮትዲቯርን ምርጫው አድርጎ ቆይቷል።

የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ 20,000 ተመልካችን በሚይዘው በያሙሶኩሮ ቻርለስ ኮናን ባኒ ስታዲየም ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

የደርሶ መልስ መርሐ ግብሩ መስከረም 30 እና ጥቅምት 4/2017 ዓ.ም ለማድረግ መታሰቡም ታውቋል።

ዋልያዎቹ በአንድ ነጥብ ሶስተኛ እንዲሁም ጊኒ ያለ ምንም ነጥብ የመጨረሻውን ደረጃ ይዘው በምድባቸው ይገኛሉ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የፓርቲዛን ደጋፊዎች አሰልጣኛቸውን ደብድበዋል !

በሰርቢያ ሊግ የሚጠበቀው የቤልግሬድ ኢተርናል ደርቢ ጨዋታ ትላንት ምሽት ሲካሄድ ሬድ ስታር ቤልግሬድ ፓርቲዛንን በሜዳው 4ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

በገጠማቸው ከባድ ሽንፈት የተበሳጩት የፓርቲዛን ደጋፊዎች የክለባችን መልበሻ ቤት ሰብረው መግባታቸው ተገልጿል።

ደጋፊዎቹ የክለቡ አሰልጣኝ አሌክሳንደር ስታኖጄቪች  እና ተጨዋቾች ላይ ስብርባሪዎችን በመወርወር ጉዳት ማድረሳቸው ተነግሯል።

ፓርቲዛን መሸነፉን ተከትሎ ሊጉን ከሚመራው ታሪካዊ ተቀናቃኙ ሬድ ስታር ቤልግሬድ በአስር ነጥብ ርቆ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ ተገዷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቤን ቺልዌል ወደ ስብስብ ይመለሳል !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የመስመር ተጨዋች ቤን ቺልዌል ወደ ቡድኑ ስብስብ እንደሚመለስ አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ገልጸዋል።

እንግሊዛዊው የመስመር ተጨዋች ቤን ቺልዌል ዛሬ ሰማያዊዎቹ ከባሮው ጋር በሚያደርጉት የሊግ ካፕ ጨዋታ ሜዳ ላይ ልንመለከተው እንደምንችል ተገልጿል።

ተጨዋቹ በቅርቡ በአሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ እንደማይፈልግ ተነግሮት ቼልሲን ለመልቀቅ ተቃርቦ እንደነበር አይዘነጋም።

አሰልጣኙ ስለ ስብሰባቸው ሲናገሩም ቀላል ነው በእኔ የአጨዋወት እሳቤ ውጪ የተገዙ ተጨዋቾች አይጫወቱም በማለት ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሊቨርፑል የአሊሰንን ግልጋሎት አያገኝም !

ሊቨርፑል ነገ ከዌስትሀም ዩናይትድ ጋር በሚያደርገው የካራባኦ ካፕ ጨዋታ የግብ ጠባቂው አሊሰን ቤከርን ግልጋሎት እንደማያገኝ አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ገልጸዋል።

በተጨማሪም ሊቨርፑል ቅዳሜ ከዎልቭስ ጋር በሚያደርገው የሊግ መርሐግብር የአሊሰንን ግልጋሎት ላያገኝ እንደሚችል አሰልጣኙ ተናግረዋል።

ብራዚላዊው ግብ ጠባቂ አሊሰን ቤከር በኤሲ ሚላን የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ወቅት የጡንቻ ጉዳት እንዳጋጠመው መገለፁ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
💥የሳምንቱ ምርጥ ጨዋታዎች

ካራባው ካፕ ፣ አውሮፓ ሊጊን እና የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዋች ጨምሮ የተለያዩ ድንቅ የሊግ ፍልሚያዎች በቀጥታ በዲኤስቲቪ ይከታተሉ!

⚽️Arsenal vs Bolton ረብዕ ከምሽቱ 3፡45 በSS Variety 4 ቻናል 229 በቤተሰብ ፓኬጅ
⚽️Man United vs Twente ረቡዕ ከምሽቱ 3፡45 በSS Football ቻናል 225 በጎጆ ፓኬጅ
⚽️Arsenal vs Leicester City ቅዳሜ ከሰዓት 11፡00 ሰዓት በSS Premier League በቻናል 223 በ ሜዳ ፓኬጅ
⚽️Man United vs Tottenham እሁድ ከምሽቱ 12፡30 በSS Premier League በቻናል 223 በ ሜዳ ፓኬጅ

👉 ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት ለመከታተል ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!

ዲኤስቲቪ ያስገቡ ፣ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://bit.ly/3RFtEvh

#PremierLeagueAllonDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
ማርቲን ኦዴጋርድ መቼ ወደ ሜዳ ይመለሳል ?

ኖርዌያዊው የመድፈኞቹ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ማርቲን ኦዴጋርድ ያጋጠመው ጉዳት የሳምንታት ጉዳይ መሆኑን አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ገልጸዋል።

“ ለሳምንታት ከሜዳ ይርቃል ብዬ አስባለሁ ነገርግን የሚመለስበትን ጊዜ በትክክል መናገር አልችልም “ ሲሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ ሚኬል አርቴታ ማርቲን ኦዴጋርድ ከቀጣዩ የብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ እረፍት በፊት ወደ ሜዳ ይመለሳል ብለው እንደማይጠብቁ ገልጸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ከትልቅ አሰልጣኞች መማር አለብህ “ አርቴታ

የመድፈኞቹ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በአሰልጣኝነት ህይወታቸው ውስጥ የአሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ ተፅዕኖ መኖሩን ገልጸዋል።

“ ከትልቅ አሰልጣኞች ብዙ መማር እና እንዴት ስኬታማ መሆን እንደቻሉ ለመረዳት መሞከር አለብህ የጆዜ ሞሪንሆ ተፅዕኖ እኔ ውስጥ አለ “ ሲሉ ሚኬል አርቴታ ተናግረዋል።

ተጨዋቾቻቸው በድጋሜ ኳስ ለማዘግየት ሞክረው ቀይ እንዳይመለከቱ ምን እንዳሏቸው የተጠየቁት ሚኬል አርቴታ “ ኳስ እንዳይነኩ ነግሬያቸዋለሁ ኳስ ሳትነኩ እግርኳስ ተጫወቱ ብያቸዋለሁ “ ሲሉ መልሰዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ከሌላ ክለብ ብጫወት እመርጥ ነበር “ ቴንሀግ

የማንችስተር ዩናይትዱ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ነገ በዩሮፓ ሊግ አሰልጣኝነት የጀመሩበትን ክለብ ትዌንቴ መግጠም ከባድ እንደሚሆንባቸው ገልጸዋል።

“ ከሌላ ክለብ ብጫወት እመርጥ ነበር “ ያሉት አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የምትወደውን ነገር መጉዳት ጥሩ አይደለም በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

አሰልጣኙ አያይዘውም ሉክ ሾው ከብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ እረፍት በኋላ ወደ ሜዳ ሊመለስ እንደሚችል ጠቁመዋል።

በክሪስታል ፓላስ ጨዋታ ራሽፎርድን ተጠባባቂ በማድረጋቸው መተቸታቸው “ አግባብ አይደለም “ ያሉት ኤሪክ ቴንሀግ " ሰው የመተቸት መብት አለው ግን ማብራሪያ ከሰጠሁ እኔን ማመን አለብት “ ብለዋል።

ቡድናቸው በዚህ አመት የዩሮፓ ሊግ ዋንጫን ማሸነፍ አላማው መሆኑን አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ አክለው ገልፀዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የዚነዲን ዚዳን ልጅ ጫማውን ሰቅሏል !

የፈረንሳዊው አሰልጣኝ ዚነዲን ዚዳን ልጅ ኢንዞ ዚዳን በ 29ዓመቱ ከእግርኳስ ራሱን ማግለሉን በይፋ አስታውቋል።

በአማካይ ስፍራ የሚጫወተው ኢንዞ ባለፈው አመት ከስፔን ሶስተኛ ዲቪዚዮኑ ክለብ ፉንላብራዳ ጋር ከተለያየ ወዲህ ክለብ አለማግኘቱን ተከትሎ ጫማውን ለመስቀል መወሰኑ ተገልጿል።

ተጨዋቹ በእግርኳስ ህይወቱ 203 ጨዋታዎች በማድረግ አስራ ሶስት ግቦች አስቆጥሮ ሀያ አራት አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

ተጨዋቹ በቀጣይ ከእግርኳስ በመራቅ በግል ስራ ለመሰማራት መወሰኑን የስፔን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
🔊 ለስፖርት ትጥቅ ፍላጎትዎ #ዋናው ብለው ያግኙን!

📌 ለበለጠ መረጃና ትዕዛዝ 📲 09011382830910851535 እና 0913586742 ላይ ይደውሉ።

👉🏾 እንዲሁም በቴሌግራም @Wanawsales ላይ የሽያጭ ሰራተኞቻችንን በቀጥታ በማናገር ወይም በቴሌግራም ቦት @WanawSportBot ይዘዙን።

Instagram | Facebook | TikTok

🏅ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
TIKVAH-SPORT
የኒውካስል ካራባኦ ካፕ ጨዋታ ተራዘመ ! ኒውካስል ዩናይትድ ነገ ከዌምብለደን ጋር ሊያደርገው የነበረው የካራባኦ ካፕ ሶስተኛ ዙር ጨዋታ ለሌላ ጊዜ መራዘሙ ይፋ ተደርጓል። ጨዋታው የተራዘመው በዌምብለደን ቼሪ ሬድ ሪኮርድስ ስታዲየም በገጠመ የጎርፍ አደጋ ምክንያት ስታዲየሙ ጉዳት ስለደረሰበት መሆኑ ተገልጿል። አሰልጣኝ ኤዲ ሀው ጨዋታውን አስመልክቶ ዛሬ ጠዋት ሊሰጡ የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ መሰረዙ…
ኒውካስል ለተጋጣሚው የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል !

ኒውካስል ዩናይትድ ስታዲየሙ በጎርፍ አደጋ ለተጎዳበት የካራባኦ ካፕ ሶስተኛ ዙር ተጋጣሚው ዌምብለደን ክለብ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጋቸው ተገልጿል።

ሁለቱ ክለቦች ዛሬ ሊያደርጉት የነበረው የካራባኦ ካፕ ጨዋታ የዌምብለደን ቼሪ ሬድ ሪኮርድስ ስታዲየም በገጠመው የጎርፍ አደጋ ምክንያት መራዘሙ ይታወቃል።

ኒውካስል ዩናይትድ ዌምብለደን ስታዲየሙን ማስጠገኛ እንዲሆነው 15,000 ፓውንድ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጋቸው ተገልጿል።

ጨዋታው በቀጣይ በኒውካስል ዩናይትድ ስታዲየም ሴንት ጄምስ ፓርክ እንደሚደረግ ሲገለፅ ዌምብለደን ከስታዲየሙ ገቢ 45% እንደሚያገኙ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ባሎን ዶር ከቪንሰስ ሌላ የሚገባው የለም “ ኔይማር

ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኔይማር ቪንሰስ ጁኒየር የባሎን ዶር ሽልማት እንደሚገባው በሰጠው አስተያየት ገልጿል።

“ ቪንሰስ ጁኒየር ባሎን ዶር እንዲያሸንፍ አግዘዋለሁ “ የሚለው ኔይማር “ ከቪንሰስ ሌላ የሚገባው እጩ የለም “ በማለት ተናግሯል።

“ ቪንሰስ ጁኒየር ባሎን ዶር የሚገባው ተጨዋች ነው ምክንያቱም እሱ ተፋላሚ ነው ፤ አሁን ላይ የሁላችንም አርአያ መሆን ችሏል።“ ሲል ኔይማር አስተያየቱን ሰጥቷል።

“ ቪንሰስ ጁኒየር በህይወቱ ብዙ ችግሮች አጋጥመውታል ነገርግን የሚጠበቅበትን ሁሉ ተወጥቷል ትችቶቹን ሁሉ አሸንፏል።“ ኔይማር

የባሎን ዶር ሽልማት ስነ-ስርዓት ሰኞ ጥቅምት 18/2017 ዓ.ም ሲካሄድ ቪንሰስ ጁኒየር ፣ ሮድሪ ፣ ቤሊንግሀም እና ዳኒ ካርቫል የአሸናፊነት ግምት አግኝተዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ሮድሪ ባሎን ዶር ይገባዋል “ አሰልጣኝ ጆዜ ቦርዳላስ

የስፔኑ ክለብ ሄታፌ አሰልጣኝ ጆዜ ቦርዳላስ ሮድሪ የዘንድሮው የባሎን ዶር ሽልማት እንደሚገባው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

“ ሮድሪ አስደናቂ የውድድር ዘመን አሳልፏል “ ያሉት አሰልጣኝ ጆዜ ቦርዳላስ “ የባሎን ዶር ሽልማት ይገባዋል እንደሚሰጠው ተስፋ አደርጋለሁ “ በማለት ተናግረዋል።

ነገ ከባርሴሎና ጋር ስላለባቸው ጨዋታ ያነሱት አሰልጣኙ “ እኛ ባርሴሎናን አንፈራም ሌሎች ክለቦችንም እንዲሁ “ በማለት ገልጸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ በአለም አቀፍ ደረጃ ዩናይትድ ከሙኒክ ትልቅ ነው “

የማንችስተር ዩናይትድ የመስመር ተጨዋች ናስር ማዝራዊ ክለቡን በአነስተኛ የዝውውር ሒሳብ መቀላቀሉ ጫናዎች እንደቀነሱለት ገልጿል።

“ ለእኔ ጥሩ ስራ ሆኖልኛል ምክንያቱም ውድ ዋጋ አልወጣብኝም ጥሩ ጅማሮም አለኝ ፤ ለደጋፊዎቹ ጥሩ ፊርማ ነው ብለው ለማሰብ ቀላል ሆኖላቸዋል።“ሲል ናስር ማዝራዊ ተናግሯል።

ከዩናይትድ እና ባየር ሙኒክ ትልቁ ማን ነው የሚል ጥያቄ የቀረበለት ተጨዋቱ “ ለማወዳደር ከሞከርክ አንዱን ትልቅ አንዱን ትንሽ ማድረግ አትችልም ነገርግን በአለም አቀፍ ደረጃ ዩናይትድ ትልቅ ክለብ ነው “ ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማድሪድ ለኤንድሪክ ጎል እስከ መቼ ይከፍላል ?

ሪያል ማድሪድ ብራዚላዊውን ወጣት አጥቂ ኤንድሪክ ከፓልሜራስ ሲያስፈርሙ በኮንትራቱ ውስጥ ግብ ሲያስቆጥር ክፍያ የሚፈፅሙበት ውል መካተቱ ይታወቃል።

የፓልሜራስ አካዳሚ ዳይሬክተር ጇ ፓውሎ ስለ ውሉ ሲያብራሩ ኤንድሪክ ለሪያል ማድሪድ ጎል ሲያስቆጥር እና አመቻችቶ ሲያቀበል ገንዘብ እንቀበላለን ብለዋል።

ዳይሬክተሩ ሲናገሩም ኤንድሪክ አምስት ጎሎች ሲያስቆጥር 1.5 ሚልዮን ዩሮ ያስገኝልናል ብለዋል።

ይህ ክፍያ የሚቀጥለው ኤንድሪክ የሚያስቆጥራቸው ግቦች 60 ሚልዮን ዩሮ እስከሚደርሱ መሆኑን ዳይሬክተሩ አያይዘው ገልጸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/09/28 13:22:36
Back to Top
HTML Embed Code: