Telegram Web Link
#Paris2024

የ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር አምስተኛ ቀኑን ሲይዝ በዛሬው ውሎው አስራ ስምንት የወርቅ ሜዳልያዎች ለአሸናፊዎች ይበረከታሉ።

በውድድሩ ጃፓን የወርቅ ሜዳልያ ቁጥሯን ወደ ሰባት ከፍ በማድረግ የሜዳልያ ሰንጠረዡን መምራቷን ቀጥላለች።

በሜዳልያ ብዛት አሜሪካ አጠቃላይ ሃያ ስድስት ሜዳልያዎችን በመሰብሰብ ቀዳሚ ስትሆን አዘጋጇ ሀገር ፈረንሳይ አስራ ስምንት ሜዳልያዎች በማግኘት ትከተላለች።

በዛሬው ዕለት በጂምናስቲክ ፣ ብስክሌት ፣ ታንኳ ፣ በሴቶች ዳይቪንግ ፣ ፌንሲንግ ፣ ጁዶ ፣ ቀዘፋ ፣ ዋና ፣ ሹቲንግ እና ትርያትሎን ለሜዳልያ ከሚደረጉት ውድድሮች መካከል ዋነኞቹ  ናቸው።

ወቅታዊ የሜዳልያ ሰንጠረዡ ምን ይመስላል ?

1️⃣ ጃፓን :- 🥇🥇🥇🥇🥇🥇🥇🥈🥈🥉🥉🥉🥉

2️⃣ ቻይና :-🥇🥇🥇🥇🥇🥇🥈🥈🥈🥈🥈🥈🥉🥉

3️⃣ አውስትራሊያ :- 🥇🥇🥇🥇🥇🥇🥈🥈🥈🥈🥉

4️⃣ ፈረንሳይ :-🥇🥇🥇🥇🥇🥈🥈🥈🥈🥈🥈🥈🥈🥈🥉🥉🥉🥉

5️⃣ ደቡብ ኮርያ :-🥇🥇🥇🥇🥇🥈🥈🥈🥉🥉🥉

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሊቨርፑል በቀጣይ ተጨዋች ያስፈርማሉ ?

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል በዘንድሮው ክረምት የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት እስካሁን ምንም ተጨዋች አላስፈረሙም።

በአሰልጣኝ አርኔ ስሎት የሚመራው ሊቨርፑል በዚህ ክረምት ምንም ተጨዋች ያላስፈረመ ብቸኛው የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ክለብም ነው።

ሊቨርፑል በክረምቱ የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት መጨረሻ በተጨዋቾች ሽያጭ ላይ ተመርኩዘው ሁለት ወይም ሶስት ተጨዋቾች ለማስፈረም ማቀዳቸው ተዘግቧል።

አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ቡድናቸውን ለማጠናከር የመሐል ተከላካይ እና የመሐል ሜዳ ተጨዋች ማስፈርምን ቅድሚያ እንደሚሰጡ ተነግሯል።

በተጨማሪም ሊቨርፑል በቀጣይ ለማስፈረም የሚመርጣቸው ተጨዋቾች እድሜያቸው ከ 24ዓመት በታች የሆኑ እንደሚሆኑ ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የዋልያዎቹን ጨዋታ ማን ይመራዋል ?

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሚቀጥለው ወር ከታንዛኒያ አቻው ጋር የሚያደርገውን የ2025 ሞሮኮ አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታን የሚመሩት ዳኛ ታውቀዋል።

ዋልያዎቹ ከሜዳቸው ውጪ የሚያደርጉትን የማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታ ሴኔጋላዊው ዳኛ ኢሳ ሳይ በመሐል ዳኝነት እንደሚመሩት ተገልጿል።

የ 40ዓመቱ ዳኛ የኢትዮጵያ እና ታንዛኒያ ብሔራዊ ቡድኖችን ጨዋታ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚመሩ ይሆናል።

የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ ነሐሴ 29/2016 ዓ.ም የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" በቅርቡ ወደ ሀላፊነት የምመጣ አይመስለኝም " ክሎፕ

ጀርመናዊው የቀድሞ የሊቨርፑል አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ በሚቀጥለው የውድድር ዘመን ወደ አሰልጣኝነት የሚመጡበት እድል ጠባብ መሆኑን ተናግረዋል።

" ሊቨርፑልን ከለቀቅኩ ወዲህ ከየትኛውም ክለብ ወይም ብሔራዊ ቡድን ጥያቄ አልቀረበልኝም " ያሉት የርገን ክሎፕ በዚህ አመት ወደ ሀላፊነት መመለሴ የማይመስል ነው ፤ ጠባብ እድል ነው።"ሲሉ ተደምጠዋል።

አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ አያይዘውም ቀጣዩ የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ እንደማይሆኑ አረጋግጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ኤደርሰን መልቀቅ ከፈለገ እየከፋኝም ቢሆን እሸኘዋለሁ " ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ብራዚላዊው ግብ ጠባቂ ኤደርሰን በክለቡ እንዲቆይ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።

" ኤደርሰን እዚህ የምወደው እና እንዲቆይ የምፈልገው ተጨዋች ነው ፣ የመጨረሻ ውሳኔውን በቶሎ እንዲያሳውቅ እፈልጋለሁ እዚህ ለመቆየት እንደሚወስን ተስፋ አለኝ።"ሲሉ ፔፕ ጋርዲዮላ ተናግረዋል።

ኤደርሰን ማንችስተር ሲቲን ለመልቀቅ የሚወስን ከሆነ ግን እየከፋኝም ቢሆን ውሳኔውን ተቀብዬ እሸኘዋለሁ ሲሉ ፔፕ ጋርዲዮላ ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሲፋን ሀሰን በአራት ርቀቶች ልትወዳደር ነው ! ለኔዘርላንድ የምትሮጠው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሲፋን ሀሰን በቀጣዩ የፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር በአራት ርቀቶች ልትወዳደር መሆኑን የሀገሪቱ ፌዴሬሽን አረጋግጧል። አትሌቷ በፓሪስ ኦሎምፒክ በ10000 ፣ 5000 ፣ 1500 ሜትር እና ማራቶን ውድድሮች እንደምትሳተፍ ተገልጿል። የ 31ዓመቷ አትሌት ሲፋን ሀሰን በሁሉም ውድድሮች ፍፃሜ የምትደርስ ከሆነ…
ሲፋን ሀሰን በ1500 እንደማትሮጥ አሳወቀች !

ኔዘርላንዳዊቷ አትሌት ሲፋን ሀሰን በቀጣዩ የ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር በ1500 ሜትር ላለመሮጥ መወሰኗን በማህበራዊ ትስስር ገጿ አስታውቃለች።

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሲፋን ሀሰን በአራት ርቀቶች ልትወዳደር መሆኑን የሀገሪቱ ፌዴሬሽን አሳውቆ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ በ1500ሜ ላለመሮጥ መወሰኗን ገልፃለች።

አትሌቷ በፓሪስ ኦሎምፒክ የወቅቱ ሻምፒዮን በሆነችባቸው 10,000 እና 5,000 እንዲሁም ማራቶን ውድድሮች እንደምትሳተፍ አሳውቃለች።

አትሌት ሲፋን ሀሰን በቶኪዮ ኦሎምፒክ ውድድር በሶስት ርቀቶች መሳተፏ የሚታወስ ሲሆን ሁለት የወርቅ እና አንድ የነሀስ ሜዳልያ ማስመዝገቧ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኒኮ ዊሊያምስ በአትሌቲክ ቢልባኦ ሊቆይ ነው !

ስፔናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኒኮ ዊሊያምስ በሚቀጥለው የውድድር ዘመን በአትሌቲክ ቢልባኦ ቤት ሊቆይ መሆኑ ተገልጿል።

የካታላኑን ክለብ ባርሴሎና የፊት መስመር ተጫዋቹን ለማስፈረም ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ ይታወቃል።

የ 22ዓመቱ ተጨዋች ኒኮ ዊሊያምስ ካደገበት ክለብ አትሌቲክ ቢልባኦ ጋር በአውሮፓ መድረክ ለመጫወት ማሰቡ ተዘግቧል።

ባርሴሎና በበኩሉ የተጫዋቹን ይፋዊ ማረጋገጫ በመጠበቅ ላይ እንደሚገኙ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
🌍🤩 WANAW IS COOKING SOMETHING IN WEST AFRICA! 🌍🤩

📌 COMING REAL SOON...

🎙 STAY TUNED!

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
ፒኤስጂ ተጨዋች ለማስፈረም ተስማማ !

የፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ ወጣቱን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ጇ ኔቬዝ ከፖርቹጋሉ ክለብ ቤኔፊካ ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

ፒኤስጂ 19ዓመቱን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ጇ ኔቬዝ አጠቃላይ 70 ሚልዮን ዩሮ በማውጣት እንደሚያስፈርሙት ተዘግቧል።

በተጨዋቹ ዝውውር ውስጥ ሌላኛው ፖርቹጋላዊ ተጨዋች ሬናቶ ሳንቼዝ ተካቶ ወደ ቤኔፊካ በውሰት ለማምራት ከስምምነት መድረሱ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Paris2024

በ2024 የፓሪስ ኦሎምፒክ የነጠላ ሜዳ ቴኒስ ውድድር ሰርቢያዊው ኖቫክ ጆኮቪች እና ስፔናዊው ካርሎስ አልካራዝ ተጋጣሚዎቻቸውን በመርታት ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቀሉ።

ሰርቢያዊው ኖቫክ ጆኮቪች በሩብ ፍፃሜው ከግሪካዊው የሜዳ ቴኒስ ተጨዋች ስቴፋኖስ ሲቲፓስ ጋር የሚገናኝ ይሆናል።

ወጣቱ ስፔናዊ ተጨዋች ካርሎስ አልካራዝ በበኩሉ በሩብ ፍፃሜው አሜሪካዊውን ቶሚ ፓውል ይገጥማል።

ኖቫክ ጆኮቪች እና ካርሎስ አልካራዝ በዘንድሮው የፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር የመጀመሪያ የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳልያቸውን ለማሳካት እየተፋለሙ ይገኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማንችስተር ሲቲ ቅጣት ተጣለበት !

ማንችስተር ሲቲዎች ባለፉት ሁለት የውድድር አመታት በተለያዩ ጨዋታዎች መዘግየታቸውን ተከትሎ በፕርሚየር ሊጉ የቅጣት ውሳኔ እንደተላለፈባቸው ተገልጿል።

ክለቡ በሀያ ሁለት ጨዋታዎች ከእረፍት ሰዓት በኋላ ዘግይቶ መገኘቱ የተገለፀ ሲሆን በዚህም ምክንያት ከሁለት ሚልዮን ፓውንድ በላይ መቀጣታቸው ተነግሯል።

ማንችስተር ሲቲ ቅጣቱን መቀበሉን ያሳወቀ ሲሆን የክለቡ ተጨዋቾች እና አመራሮች ሰዓት እንዲያከብሩ እና ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ በሩዲገር እና ኤንድሪክ መካከል ፀብ አልተፈጠረም “ አንቾሎቲ

የሪያል ማድሪዱ ዋና አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ በአንቶኒዮ ሩዲገር እና ኤንድሪክ መካከል የተፈጠረ ችግር አለመኖሩን በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።

አንቶኒዮ ሩዲገር በትላንቱ የቡድኑ ልምምድ ላይ  ከአዲሱ አጥቂ ኤንድሪክ ጋር በተገናኘባቸው አጋጣሚዎች ከባድ የሚባሉ ጥፋቶችን ሲሰራ ተስተውሎ ነበር።

ምንም እንኳን ልምምድ ቢሆንም አንቶኒዮ ሩዲገር ከኤንድሪክ ጋር ሀይለ ቀላቅሎ ሲሰራ እንደነበር ሲገለፅ “ በአንድ ለአንድ ግንኙነቶች ጠንካራ ሁን " ሲልም ተደምጧል።

አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ሲሰጡ " በሁለቱ ተጨዋቾች መካከል የተፈጠረ ችግር የለም ሩዲገር እንኳን ደህና መጣህ እያለው ነው " ብለዋል።

አሰልጣኙ አክለውም " ጠንካራው ተከላካያችን ሩዲገር ጥሩ ሰው ነው ፣ ኪሊያን ምባፔም ወደ ቡድኑ ሲመጣ ተመሳሳይ ነገር ያደርጋል " ሲሉ ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ ማህበራዊ ገፁ ተጠልፎ ነበር !

አርጀንቲናዊው የማንችስተር ዩናይትድ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ የኢንስታግራም ማህበራዊ ትስስር ገፁ በጠላፊዎች እጅ ገብቶበት እንደነበር አሳውቋል።

ተጨዋቹ ገፁ በጠላፊዎች እጅ በገባበት ወቅት የተላለፉ መልዕክቶች የእሱ አለመሆናቸውን የገለፀ ሲሆን አሁን ላይ ከጠላፊዎቹ መመለስ መቻሉንም አሳውቋል።

ጠላፊዎቹ በማህበራዊ ገፁ ሊዮኔል ሜሲ ጭምብል ለብሶ የባሎን ዶር ሽልማትን ይዞ የሚያሳይ ምስል አጋርተው ተስተውለዋል።

ሊዮኔል ሜሲ በበኩሉ በኢንስታግራም ሊሳንድሮ ማርቲኔዝን " Unfollow " አድርጎት እንደነበር ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የቼልሲ ተጨዋቾች ኢንዞ ፈርናንዴዝን ተቃወሙ ! የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ያሰሙት ዝማሬ በምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የሚጫወቱ ፈረንሳዊ ተጨዋቾችን ማበሳጨቱ ተገልጿል። ፈረንሳዊ የቼልሲ ተጨዋቾችን ያበሳጨው በተለይም ዝማሬው በቡድን አጋራቸው ኢንዞ ፈርናንዴዝ ማህበራዊ ትስስር ገፅ መሰራጨቱ እንደሆነ ተነግሯል። ፈረንሳዊው ተጨዋች ዊስሌይ ፎፋና በ " X " ማህበራዊ ትስስር ገፁ " እግርኳስ…
" ኢንዞ ፈርናንዴዝ ዘረኛ አይደለም " ዌስሌይ ፎፋና

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ዌስሌይ ፎፋና የቡድን አጋሩ ኢንዞ ፈርናንዴዝ ወደ ቡድኑ በመመለሱ ደስተኛ መሆኑን ገልጿል።

" ኢንዞ ፈርናንዴዝ ወደ ቡድኑ በመመለሱ ደስተኛ ነኝ “ ያለው ዌስሌይ ፎፋና " እኔ እሱን አውቀዋለሁ ዘረኛ አይደለም " ሲል ተናግሯል።

" ለኢንዞ ቪዲዮን እንዳልወደድኩት ነግሬዋለሁ ፤ እሱም ይቅርታ ጠይቆኛል ፤ እኔ በይቅርታ አምናለሁ እሱ በጣም አስፈላጊው ነገር ነው" ሲል ዌስሌይ ፎፋና ተናግሯል።

ዌስሌይ ፎፋና የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ካሰሙት ዝማሬ በኃላ የቡድን አጋሩ ኢንዞ ፈርናንዴዝን በማህበራዊ ገፆቹ "Unfollow" ማድረጉ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ናዳል እና አልካራዝ ከውድድር ውጪ ሆኑ !

ስፔናዊዎቹ የሜዳ ቴኒስ ተጨዋቾች ራፋኤል ናዳል እና ካርሎስ አልካራዝ ከፓሪስ ኦሎምፒክ የሜዳ ቴኒስ ጥንድ ውድድር ውጪ ሆነዋል።

ለመጀመሪያ ጊዜ የተጣመሩት ራፋኤል ናዳል እና ካርሎስ አልካራዝ በአሜሪካኖቹ ኡስቲን ክራጂኬች እና ራጄቭ ራም 6-2 እና 6-4 ተሸንፈዋል።

የፈረንሳይ ኦፕን በርካታ ጊዜ በማሸነፍ ባለሪከርዱ ራፋኤል ናዳል በነጠላ የሜዳ ቴኒስ ጨዋታ በኖቫክ ጆኮቪች ተሸንፎ ከውድድሩ መውጣቱ አይዘነጋም።

ካርሎስ አልካራዝ በበኩሉ በነጠላ የሜዳ ቴኒስ ውድድር ሩብ ፍፃሜ መድረስ ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Paris2024

በ2024 የፓሪስ ኦሎምፒክ ቅርጫት ኳስ ውድድር የአሜሪካ ቅርጫት ኳስ ብሔራዊ ቡድን ከደቡብ ሱዳን አቻው ጋር ያደረገውን ጨዋታ ማሸነፍ ችሏል።

ከፍተኛ ፉክክር በታየበት ጨዋታ የአሜሪካ ቅርጫት ኳስ ብሔራዊ ቡድን የደቡብ ሱዳን ቅርጫት ኳስ ብሔራዊ ቡድንን 103-86 መርታት ችለዋል።

የአሜሪካ ቅርጫት ኳስ ብሔራዊ ቡድን የምድብ ሁለት ጨዋታዎችን በማሸነፍ ጥሎ ማለፉን መቀላቀል ችለዋል።

በቀጣይ አሜሪካ ከፑኤርቶ ሪኮ እንዲሁም ደቡብ ሱዳን ከሰርቢያ ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አርቴታ አማካይ ማስፈረም ይፈልጋሉ ! የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ዋና አሰልጣኝ ሜኬል አርቴታ በቀጣይ አንድ አማካይ እንዲገዛላቸው እንደሚፈልጉ ተገልጿል። መድፈኞቹ ለማስፈረም የመጀመሪያ ምርጫቸው የሪያል ሶሴዳዱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሚኬል ሜሪኖ መሆኑ ሲገለፅ ይሁን እንጂ እስካሁን ንግግር አለመጀመራቸው ተዘግቧል። ተጨዋቹ በሌሎች ክለቦች እየተፈለገ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን በተጨማሪም ሪያል…
አርሰናል ተጨዋች ለማስፈረም ተቃርቧል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ስፔናዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሚኬል ሜሪኖ ከሪያል ሶሴዳድ ለማስፈረም ለስምምነት መቅረባቸው ተገልጿል።

መድፈኞቹ ከተጨዋቹ ጋር በግል የሚያደርጉት ንግግር ለዝውውሩ ችግር እንደማይሆንባቸው እና ተጨዋቹ ወደ አርሰናል መዘዋወር እንደሚፈልግ ተነግሯል።

አርሰናል ተጫዋቹን 30 ሚልዮን ዩሮ በሚደርስ የዝውውር ሒሳብ ለማስፈረም ከሪያል ሶሴዳድ ጋር በንግግር ላይ መሆናቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Liverpool   #Arsenal

በአሜሪካ ለሊቱን በሊቨርፑል እና አርሰናል መካከል በነበረው ተጠባቂ የወዳጅነት ጨዋታ ሊቨርፑል 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

በጨዋታው የሊቨርፑልን ግቦች መሀመድ ሳላህ እና ካርቫሎ ሲያስቆጥሩ ብቸኛውን የአርሰናል ግብ ካይ ሀቨርትዝ ማስቆጠር ችሏል።

ከጨዋታው መጠናቀቅ በኃላ አስታየታቸውን የሰጡት የሊቨርፑሉ አሰልጣኝ አርኔ ስሎት "እኛ ሁሉንም ጨዋታ ማሸነፍ እንፈልጋለን ፣ በልምምድ ላይ እራሱ የምንሰራው ይህንኑ ነው " ብለዋል።

የአርሰናሉ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በበኩላቸው "ሊቨርፑል የራሱ የአጨዋወት ባህሪ አለው ፤ በጨዋታው ካይ ሃቨርትዝ ጥሩ ተጫውቷል " በማለት ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሪያል ማድሪድ ተሸንፏል !

የስፔኑ ክለብ ሪያል ማድሪድ የቅድመ ውድድር ዝግጅት የመጀመሪያ የወዳጅነት ጨዋታውን ከኤሲ ሚላን ጋር አድርጎ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

በጨዋታው ካርሎ አንቾሎቲ ወጣቶቹን ተጫዋቾች ልምድ ካላቸው ጋር በመቀላቀል የተጠቀሙ ሲሆን የኤሲ ሚላንን የማሸነፊያ ግብ ቼኩዌንዜ አስቆጥሯል።

ከጨዋታው በኃላ አስታያየታቸውን የሰጡት አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ " ይህ ለወጣቶች እድል የምንሰጥበት ጨዋታ ነበር ፤ አርዳ ጉለር እና ኤንድሪክ ወደፊት ለክለቡ በጣም አስፈላጊ ተጨዋቾች ይሆናሉ " ብለዋል።

ሪያል ማድሪድ በቀጣይ እሁድ ዕለት ከ ባርሴሎና ጋር ሁለተኛ የወዳጅነት ጨዋታውን የሚያደርግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዩናይትድ ተጫዋቾቹ ለበርካታ ጊዜ ከሜዳ ይርቃሉ !

የእንግሊዙ ክለብ ማንችስተር ዩናይትድ ከአርሰናል ጋር በነበረው የወዳጅነት ጨዋታ ጉዳት ያስተናገደው የተከላካይ መስመር ተጨዋች ሌኒ ዮሮ ለወራት ከሜዳ እንደሚርቅ በይፋ ተገልጿል።

የ18ዓመቱ አዲሱ ፈራሚ ሌኒ ዮሮ ጣቱ ላይ በደረሰበት ጉዳት ምክንያት #ለሶስት ወራት ከሜዳ እንደሚርቅ ተዘግቧል።

ሌላኛው በአርሰናሉ ጨዋታ ጉዳት ያስተናገደው የፊት መስመር አጥቂው ራስሙስ ሆይሉንድ በጡንቻ መሳሳብ ጉዳት #ለስድስት ሳምንታት ከሜዳ እንደሚርቅ ክለቡ አሳውቋል።

ከደቂቃዎች በፊት ሪያል ቤቲስን 3ለ2 ያሸነፉት ቀያይ ሴጣኖቹ ማርከስ ራሽፎርድ እና አንቶኒ ጉዳት ያስተናገዱ አዲስ ተጫዋቾች ሆነዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
2024/10/05 05:26:39
Back to Top
HTML Embed Code: